Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/ – Telegram
Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/
25.8K subscribers
40K photos
304 videos
7 files
5.76K links
Ethiopian Press Agency, established in 1940 , is a public printing media enterprise operating in Ethiopia.
Download Telegram
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) በቡድን 20 ጉባኤ ጎን ለጎን...... 

✍️ ከጣልያን ጠቅላይ ሚኒስትር ጂኦርጂያ ሜሎኒ ጋር በአለምአቀፍና ቀጠናዊ ጉዳዮች ላይ ብሎም በቁልፍ የሁለትዮሽ ጉዳዮች ላይ ትኩረት አድርገው መክረዋል።

✍️ ከኔዘርላንድ ጠቅላይ ሚኒስትር ዲክ ሾፍ ጋር በነበራቸው ውይይት በኢትዮጵያና ኔዘርላንድ መካከል ያለውን ጠንካራ ትስስር ለማጠናከር ተወያይተዋል። ከኢትዮጵያ የውጪ ንግድ ቁልፍ መዳረሻዎች አንዷ የሆነችው ኔዘርላንድ ኢንቨስትመንትና የኢኮኖሚ ትብብር ለማድረግ ጉልህ አቅም አላት። የአየር ንብረት ለውጥ ጥበቃ ሥራ ትብብርን አስመልክቶም የሁለትዮሽ ግንኙነትን፣ በጉብኝትና የልውውጥ መርሐግብሮች ይከወናሉ።

✍️ ከብራዚል ፕሬዝደንት ሉዊዝ ኢናችዮ ሉላ ደ ሲልቫ ጋር የነበራቸው ውይይት በኢኮኖሚና ዘላቂ የመሠረተ ልማት ጉዳዮች ላይ በማተኮር የሁለትዮሽ ግንኙነቶች የሚጠናከሩበት እድሎች አስመልክቶ የተካሄደ ነበር። ብራዚል በቅርቡ የተካሄደው የCOP30 አስተናጋጅ ሀገር እንደመሆኗ COP32ን በኢትዮጵያ ስናዘጋጅ ከብራዚል የምንወስደው ብዙ ጠቃሚ ልምዶች አሉ። የአለም የአየር ንብረት ጥበቃ ሥራን የሚያራምድ በሚገባ የተሰናዳ መስተንግዶ እንዲኖረን ከልምዶች የተገኙ ሃሳቦችን መለዋወጡን አጠናክረን ለመቀጠል መታቀዱም ተገልጿል።

✍️ ከካፍ ፕሬዝደንት ከዶክተር ፓትሪስ ሞትሲፒ በአፍሪካ እግር ኳስና ኢትዮጵያ በእድገቱ ስለሚኖራት ሚና፤ ለወጣቶች እድገት፣ የስፖርት መሠረተ ልማት ብሎም የአፍሪካን እግርኳስ በአለም መድረክ ለማላቅ ከካፍ ጋር ስለሚኖር ትብብር ተወያይተዋል።

#COP32 #CAF #southafrica #G20summit
👍42💊1
የሲንጋፖር ጠቅላይ ሚኒስትር ሎውረንስ ዎንግ በኢትዮጵያ ለሚያደርጉት ይፋዊ ጉብኝት አዲስ አበባ ሲገቡ በቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ተቀብያቸዋለው።

ይህ ጉብኝት የሁለቱ ሀገራት አጋርነትን ለማጠናከር ወሳኝ እርምጃ ሲሆን፣ ተጨማሪ አዳዲስ የትብብር እድሎችን ለመዳሰስም ትልቅ ፋይዳ ይኖረዋል።

- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር)
8👍5👎1
የሲንጋፖርን ስኬት እና ትምህርት የሚሰጡ  የልማት ጉዞ ልምዶችን ከሲንጋፖር ጠቅላይ ሚኒስትር ሎውረንስ ዎንግ ጋር “የሀገር ግንባታ፣ አለማትን ማገናኘት” በሚል ርዕስ በተሰናዳው ወግ ተካፍለናል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዎንግ በሀገር ግንባታ፣ በአመራር ዘዴ፣ በኢኮኖሚ ለውጥና በጂኦፖለቲካ ላይ ላካፈሏቸው ሀሳቦች ምስጋናዬን አቀርባለሁ።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር)
8
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
"የኢትዮጵያ እና ሲንጋፖር ትብብርን ማስፋት"

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር)
4
"ዛሬ ጠዋት የዩናይትድ ስቴትስ የአፍሪካ እዝ አዘዥ ጄነራል ዳግቪን አር ኤም አንደርሰንን አግኝቼ በቀጠናዊ የጸጥታ እና የበለጠ ትብብር ለማድረግ በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ ውይይት አድርገናል"

-ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር)
7
"በዚህ ዓመት ከቡና የወጪ ንግድ 3 ቢሊዮን ዶላር ለማግኘት በትኩረት ይሰራል"

-የኢፌዴሪ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ተመስገን ጥሩነህ
++++++++++++

#ጋዜጣ_ፕላስ | በ2018 ዓ.ም ከቡና የወጪ ንግድ 3 ቢሊዮን ዶላር ለማግኘት እየተሰራ መሆኑን የኢፌዴሪ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ተመስገን ጥሩነህ ገለጹ።

"ፈጠራና ፍጥነት ለቡናችን ስኬት" በሚል መሪ ቃል ሃገር አቀፍ የቡና ኤግዚቢሽንና እውቅና መርሃ ግብር በሳይንስ ሙዚየም ተካሂዷል።

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ተመስገን ጥሩነህ በመርሐግብሩ ላይ ባደረጉት ንግግር የአረንጓዴ ልማት ስራውን ካሻሻለው አንዱ የቡና ዘርፍ ነው።

በዚህም አርሶ አደሩ ቡናን በክላስተር እንዲያመርት፣ በተሻለ ዋጋ እንዲሸጥ እና ወደ ውጪ የሚላከው ምርት እንዲጨምር አድርጓል ብለዋል።

በ2018 በጀት ዓመት 600 ሺህ ቶን ቡና ወደ ውጪ በመላክ 3 ቢሊዮን ዶላር ለማግኘት በትኩረት እንደሚሰራም ገልፀዋል።

ቡና ኢኮኖሚያዊ ብቻ ሳይሆን ማህበራዊ ጠቀሜታው ከፍተኛ በመሆኑ የአገር ውስጥ ፍጆታውም በዛው ልክ ከፍ ማለቱን አመላክተዋል ።

ቡናን በዘመናዊ መንገድ የማልማት ስራው ላይ በማተኮርና በዓለም ተወዳዳሪ እንዲሆን ማድረግ ያስፈልጋል ያሉት አቶ ተመስገን እሴት ጨምሮ ወደ ውጭ መላክ ቀጣይ የቤት ስራ ስለሚሆንም የዘርፉ ላኪዎች እራሳቸውን የማብቃት ስራዎችን እንዲሰሩ አሳስበዋል።

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በ2017 ዓ.ም በቡና፣ ሻይ እና ቅመማ ቅመም የላቀ ውጤት ላስመዘገቡ ላኪዎች እውቅና ሰጥተዋል።

በዳግማዊት አበበ
+++++++++++
#gazette_plus #ጋዜጣ_ፕላስ
4
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ እና ጠቅላይ ሚኒስትር ላውረንስ ዎንግ በእድገትና አመራር ልምዶቻቸውን ለመለዋወጥ ለእሳት ዳር ወግ ተቀምጠዋል። #PMOEthiopia
5👍3
በማርበርግ ቫይረስ እስካሁን የ6 ሰዎች ሕይዎት አልፏል
++++++++++++++++++

#ጋዜጣ_ፕላስ | በማርበርግ ቫይረስ የ6 ሰዎች ሕይዎት ማለፉን የጤና ሚኒስቴር አስታወቀ።

የጤና ሚኒስቴር የማርበርግ ቫይረስ ወቅታዊውን ሁኔታን በሚመለከት ለመገናኛ ብዙኃን መግለጫ ሰጥቷል።

የጤና ሚኒስትር መቅደስ ዳባ (ዶ/ር) እንደገለጹት፤ ጤና ሚኒስቴር የማርበርግ በሽታ ካሳወቀበት ህዳር 5 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ ቫይረሱን ለመግታት በርካታ ስራዎችን እየሰሩ ይገኛል።

ቫይረሱ ከተከሰተበት ጊዜ ጀምሮ እሰከ ዛሬ ጠዋት ድረስ 73 ላብራቶሪ ተሰርቶ በ11 ግለሰቦች ላይ ቫይረሱ መኖሩ ተረጋግጧል ብለዋል።

ቫይረሱ ከተገኘባቸው 11 ሰዎች የ6 ሰዎች ሕይዎት ማለፉን እና 5 ሰዎች በህክምና ላይ እንደሚገኙ አስታውቀዋል።

በሕክምና ላይ ካሉት ሰዎች መካከል ደግሞ አንዱ ጽኑ ህሙም እንደሆነ አመላክተዋል።

በበሽታው ከተያዙ ሰዎች ጋር ንክኪ አላቸው ተብለው የተጠረጠሩ 349 ሰዎች ተለይተው ክትትል ሲደረግ መቆየቱን ገልጸው፤ 119 የክትትል ጊዜ ገድብ ጨርሰው ወጥተዋል ብለዋል።

ምልክት ከታየባቸው ሰዎች ጋር ንክኪ ሲኖር እራስን መለየት፣ እጅን በሳሙና መታጠብ እና ሌሎች የጥንቃቄ ስራዎችን መስራት ከሁሉም እንደሚጠበቅ ገልጸዋል።

በሄለን ወንድምነው

#ጋዜጣ_ፕላስ #ጤና #ኢትዮጵያ #ማርበርግ #ቫይረስ
14