Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/ – Telegram
Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/
25.9K subscribers
40K photos
303 videos
7 files
5.75K links
Ethiopian Press Agency, established in 1940 , is a public printing media enterprise operating in Ethiopia.
Download Telegram
የመንግሥት ሠራተኞች የጤና መድን ተጠቃሚ ሊሆኑ ነው
++++++++++++++++++++++++

#ጋዜጣ_ፕላስ | የመንግሥት ሠራተኞች በቀጣዩ 2019 ዓ.ም የጤና መድን አገልግሎት ተጠቃሚ ይሆናሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ የኢትዮጵያ ጤና መድን አገልግሎት አስታወቀ።

የኢትዮጵያ ጤና መድን አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር አቶ ተስፋዬ ወርቁ እንደገለጹት፤ መደበኛ በሆኑ የሥራ መስኮች የተሰማሩ ዜጎች የጤና መድን አገልግሎት እንዲያገኙ ታስቦ የተዘጋጀው የማኅበራዊ ጤና መድን አገልግሎት በአዋጅና ደንብ ከጸደቀ 14 ዓመታትን አስቆጥሯል።

አዋጁ ሠራተኛው ከደመወዙ ሦስት በመቶው እንዲቆረጥና የፌዴራልና የክልል መንግሥታትም ለቀጠሩት ሠራተኛ ሦስት በመቶውን እንዲሸፍኑ ይደነግጋል።

ሆኖም ግን ባለፉት ዓመታት በመንግሥት በኩል በቂ ገንዘብ ባለመኖሩና በኑሮ ዉድነት አማካኝነት ሳይተገበር ቢቆይም በዘንድሮዉ ዓመት ግን የተሻለ ተስፋ ታይቷል ብለዋል።

በዘንድሮው ዓመት በጤናው ዘርፍ የተሰማሩ ከ500 ሺህ በላይ ሠራተኞች ለአገልግሎቱ መመዝገባቸውን የጠቀሱት ዳይሬክተሩ፤ ከገንዘብ ሚኒስቴርም 4 ነጥብ 5 ቢሊዮን ብር መጽደቁን ተናግረዋል።

በሚቀጥለው ዓመትም ሁሉም የመንግሥት ሠራተኛ ተጠቃሚ እንዲሆን የፌዴራልም ሆነ የክልል መንግሥታት በጀት ይይዛሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ አመላክተዋል።

መስከረም ሰይፉ
#ጋዜጣ_ፕላስ #gazetteplus #ጤና_መድን #ጤና #ኢትዮጵያ
11👍3
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
በመደመር መንግሥት ዕይታ፣ የዘርፎች እመርታ!
+++++++++++
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
ለብልፅግና ከፍተኛ አመራሮች የሰጡት ስልጠና
ክፍል አንድ ዛሬ ምሽት 2:30 ይጠብቁን
1
የሚኒስትሮች ምክር ቤት ስብስባ ውሳኔዎች

የሚኒስትሮች ምክር ቤት በዛሬው ዕለት ባካሄደው 50ኛ መደበኛ ስብሰባ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳለፈ፡፡

1. ምክር ቤቱ በቅድሚያ የተወያየው በዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 ስትራቴጂ ላይ ነው፡፡ ስትራቴጂው ለዜጎች አዳዲስ ዕድሎችን ለመፍጠር፣ የቴክኖሎጂ አቅምን ለማሳደግና መሰረተ ልማቶቹን ለማስፋፋት፣ መልካም አስተዳደር ለማስፈንና የኢኮኖሚ ዕድገትን ለማፋጠን እየተደረጉ ያሉ ጥረቶችን በተሻለ መንገድ ማሳካትን ታሳቢ ያደረገ ነው፡፡ ምክር ቤቱም በስትራቴጂው ላይ በሰፊው ከተወያየበት በኋላ በምክር ቤቱ ከጸደቀበት ቀን ጀምሮ ተግባራዊ እንዲደረግ በሙሉ ድምጽ ወስኗል፡፡

2. ከዚያም ምክር ቤቱ የተወያየው ከዓለም አቀፍ የልማት ማህበር ጋር በተፈረሙ ሁለት የፋይናንስ ድጋፍ ስምምነቶች ላይ ነው፡፡ የመጀመሪያው ዘላቂ እና ንፁህ የኢነርጂ ተደራሽነት ለውጥን ለማፋጠን ፕሮግራም ማስፈፀሚያ የሚውል 294,900,000 ኤስ. ዲ. አር የብድር ስምምነት ሲሆን የ6 አመት የችሮታ ጊዜን ጨምሮ በ38 አመታት ተከፍሎ የሚጠናቀቅ ነው፡፡ ሁለተኛው የምስራቅ አፍሪካ የክህሎት ትራንስፎርሜሽን እና ቀጠናዊ ውህደት ፕሮጀክት ማስፈፀሚያ የሚውል ተጨማሪ 20,000,000 ኤስ. ዲ. አር የብድር ስምምነት ሲሆን የ6 አመት የችሮታ ጊዜን ጨምሮ በ31 አመታት ተከፍሎ የሚጠናቀቅ ነው፡፡ ሁለቱም ብድሮች ከወለድ ነጻ እና 0.75% የአገልግሎት ክፍያ የሚከፈልባቸው ናቸው፡፡ ምክር ቤቱም የብድር ስምምነቶቹ ከአገራችን የብድር አስተዳደር ስትራቴጂ ጋር የሚጣጣሙ መሆናቸውን በማረጋገጥ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንዲተላለፉ ወስኗል።

3. በመቀጠል ምክር ቤቱ የተወያየው የአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን እና የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቴአትር ለሚሰጧቸው ልዩ ልዩ አገልግሎቶች የሚከፈሉ የአገልግሎት ክፍዎችን ለመወሰን በቀረቡ ሁለት ረቂቅ ደንቦች ላይ ነው፡፡ ተቋማቱ አገልግሎት ለመስጠት የሚያወጡትን ወጪ ሸፍነው ገቢያቸውን በማሳደግ ጥራት ያለው አገልግሎት በመስጠት የተገልጋይ እርካታን ማሳደግ በማስፈለጉ የተገልጋዩን አቅም ባገናዘበ መልኩ የአገልግሎት ክፍያ ተመን ተዘጋጅቶ ቀርቧል፡፡ ምክር ቤቱም በረቂቅ ደንቦቹ ላይ በሰፊው ከተወያየ በኋላ በፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ታትመው ከወጡበት ቀን ጀምሮ ተግባራዊ እንዲደረጉ በሙሉ ድምጽ ወስኗል፡፡

4. ቀጥሎም ምክር ቤቱ የተወያየው በአራት የሁለትዮሽ ስምምነቶች ላይ ነው፡፡ የመጀመሪያው ከህዝባዊት ቻይና ሪፐብሊክ መንግስት ጋር በወንጀል ጉዳዮች የጋራ የህግ ትብብር ለማድረግ የተደረገ ስምምነት ነው፡፡ ሌሎቹ ሁለት ስምምነቶች ከህዝባዊት ቻይና ሪፐብሊክ መንግስት እና ከብራዚል ፌዴራላዊ ሪፐብሊክ መንግስት ጋር ፍርደኞችን ለማስተላለፍ የተደረጉ ናቸው፡፡ ሌላው ከደቡብ አፍሪካ ሪፐብሊክ መንግስት ጋር የተደረገው የአሳልፎ መስጠት ስምምነት ነው፡፡ ምክር ቤቱም ስምምነቶች ቢጸድቁ ኢትዮጵያ ከሀገራቱ ጋር ዉጤታማ የወንጀል መከላከል የሁለትዮሽ ትብብር የሕግ ማዕቀፍ ለመፍጠር የሚያስችላት መሆኑን በመገንዘብ ረቂቅ አዋጆቹ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንዲተላለፉ በሙሉ ድምጽ ወስኗል፡፡

5. ሌላው ምክር ቤቱ የተወያየበት አጀንዳ የኤሌክትሮኒክ ፊርማ ረቂቅ ደንብ ነው፡፡ የኤሌክትሮኒክ ፊርማ አዋጅ ቁጥር 1072/2010ን ሙሉ ለሙሉ ስራ ላይ ለማዋል የሚያስፈልጉ ስርዓቶችን በአዋጁና በተሻሻለው የኤሌክትሮኒክ ፊርማ አዋጅ ቁጥር 1358/2017 መሰረት ግልፅና ተጠያቂነት በሰፈነበት መልኩ ለመተግበር እንዲያስችል ሆኖ ደንቡ ተዘጋጅቶ ቀርቧል። ምክር ቤቱም በደንቡ ላይ በሰፊው ከተወያየበት በኋላ በፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ተግባራዊ እንዲደረግ በሙሉ ድምጽ ወስኗል፡፡

6. በመጨረሻም ምክር ቤቱ የተወያየው የኢሚግሬሽን የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር 114/1997 ለማሻሻል በቀረበ ደንብ ላይ ነው፡፡ ተቋሙ በአዋጅ የተሰጠውን ተግባርና ሀላፊነት ለመወጣት እንዲያስችለው ደንቡ ተዘጋጅቶ ቀርቧል፡፡ ምክር ቤቱም በደንቡ ላይ በሰፊው ከተወያየ በኋላ በፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ተግባራዊ እንዲደረግ በሙሉ ድምጽ ወስኗል፡፡

#PMOEthiopia

ህዳር 20 ቀን 2018 ዓ.ም
አዲስ አበባ
11
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
በመደመር መንግሥት እይታ፣ የዘርፎች እምርታ -ክፍል አንድ
'' የመደመር መንግስት መፍጠርን፣ መፍጠንን፣ የማብዛትና የማጥራት እሳቤን የያዘ ነው '' - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
+++++++++++
#ጋዜጣ_ፕላስ | የመደመር መንግስት መፍጠርን፣ መፍጠንን፣ ማብዛትና የማጥራት እሳቤን የያዘ ነው ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በመደመር መንግሥት እይታ፣ የዘርፎች እመርታ” በሚል ለብልፅግና ከፍተኛ አመራሮች ሲሰጥ በነበረው ስልጠና ላይ እንደገለጹት፤ ብዙ ያልፈጠረ ጥራትን ማረጋገጥ አይችልም፤ ከብዙ ፈጠራ ውስጥ ጥራት ያላቸው ጉዳዮች ይወጣሉ።

የመደመር መንግስት ፍጥነት የታከለበት ብዙ ፈጠራ በመስራት ጥራትን የማረጋገጥ ስራ እየሰራ ነው ሲሉ ተናግረዋል።

ብዙ በመፍጠርና ብዙ በመሮጥ ጥራትን መዞ የማውጣት ስራ እየተሰራ ነው ሲሉ ገልጸዋል።

ብዙ ፈጠራ ውስጥ አዳዲስ ነገር ለመፍጠር የምንማርበት ብቻ ሳይሆን የመጨረሻ ውጤት ለማቆየት የሚጠቅም ነው ሲሉ አብራርተዋል።

የመደመር መንግስት የመፍጠር፣ የመፍጠን፣ ማብዛትና የማጥራት እሳቤዎች ላይ የሚያጠነጥን ይሆናል ሲሉ ጠቁመዋል።

በታደሠ ብናልፈው
1
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
"ስንጀምርና ዛሬ አንድ አይደለም"

-ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
1
በአፋር ክልል የተከሰተውን የእሳተ ገሞራ ፍንዳታ አስመልክቶ በማዕድን ሚኒስቴር ከኢትዮጵያ ጂኦሎጂካል ኢንስቲትዩት የተሰጠ መግለጫ‼️

የኢትዮጵያ ጂኦሎጂካል ኢንስቲትዩት የተለያዩ የስነ ምድር የምርምር ስራዎችን እየሰራ የሚገኝ የምርምር ተቋም ሲሆን የስነ-ምድር አደጋዎችንም የማጥናት ተልኮ እንዳለው ይታወቃል፡፡ ይሀንን ምርምር ለመከወንም ሃገር ውስጥና ከሃገር ውጭ ካሉ የተለያዩ የመንግስት መስሪያ ቤቶች እና ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ጋር በጋራ በመሆን እየሰራ ይገኛል፡፡

በአሁን ወቅት በአፋር ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በኤርታሌ አካባቢ ልዩ ቦታው ሃይሊ ጉብ በተባለ ስፍራ ሀዳር 14/2018 ዓ.ም ጠዋት አራት ሰዓት አካባቢ የእሳተ ገሞራ ፍንዳታ(Volcanic Eruption) እንደተከሰተ ይታወቃል። ይህ የእሳተ ገሞራ ፈንዳታ ከመከሰቱ በፊት ከሃምሌ 2017 ዓ.ም ጀምሮ የተለያዩ ለእሳተ ገሞራ ፍንዳታ መከሰት አመላካች ምልክቶችን በቅርበት የመከታተል፣ መረጃዎችን የማሰባሰብና መረጃዎችን የመስጠት ስራ ሲሰራ ቆይቷል፡፡

አሁን ላይ የእሳተ ገሞራ ፍንዳታው ያለበትን ሁኔታ የሚመለከትና የሚያጠና የጥናት ቡድን ተቋቁሞ ወደ ቦታው በመላክ ጥናት እያደረገ የሚገኝ ሲሆን አሁን በቦታው ላይ ያለው ሁኔታ በአንጻራዊነት የተረጋጋ ስለሆነ ማሀበረሰቡ ተረጋግቶ ስራውን እንዲያከናውን እያሳሰብን በሃገር ውስጥና ከሃገር ዉጭ ካሉ ተቋማትና ተመራማሪዎች ጋር በጋራ እየተሰራ ያለው የምርምር ስራ ሲጠናቀቅ ተጨማሪ መግለጫ የምንሰጥ ይሆናል፡፡
1
"የሐረሪ የኮሪደር ልማት ለሌሎች ክልሎች ማሳያ ነው"
   -ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
+++++++++
#ጋዜጣ_ፕላስ| በሐረሪ ክልል  በኮራደር ልማት የተገኘው ውጤት ለሌሎች ክልሎች ማሳያ የሚሆን ነው ሲሉ የኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ተናገሩ።

ሐረሪ ክልል የራሱን የፈጠራ አቅም በመጠቀም የተሰራው ስራ ማራኪ በመሆኑ ለሌሎችም አስተማሪ የሚሆን ነው ብለዋል።

አዲስ አበባ ይብዛም ይነስም ብዙ አመራር፣ አጋዥና ብዙ አይን ያለው መሆኑንም ጠቅሰው፣ ክልሉ ባለው ውስን ሃብት ህዝብን አስተባብሮ ታሪካዊ ውጤት አምጥቷል።

ባነሰ ሀብት እንዲህ ያለ ታሪካዊ ስራ መስራት መቻላቸው ሁሉም ክልሎች ይችሉ እንደነበር ማሳያ ነው ሲሉ ገልጸዋል።

በየትኛውም መመዘኛ ሐረሪ ክልል ከሌሎች ክልሎች ያነሰ ስፋትና ሃብት እንጂ የበለጠ እንደሌለው አብራርተዋል።

በልጅዓለም ፍቅሬ
#ጋዜጣ ፕላስ # ኮሪደርልማት
1👍1