Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/ – Telegram
Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/
25.9K subscribers
40K photos
302 videos
7 files
5.75K links
Ethiopian Press Agency, established in 1940 , is a public printing media enterprise operating in Ethiopia.
Download Telegram
ከ345 በላይ ዓለም-አቀፍ ወደቦችን መዳረሻ በማድረግ የገቢ ጭነቶች ወደ ሀገር ውስጥ እንደሚጓጓዙ ተገለጸ
*****
(ኢ ፕ ድ)

የኢትዮጵያ ባህር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክ አገልግሎት ከ345 በላይ ዓለም-አቀፍ ወደቦችን መዳረሻ በማድረግ የኢትዮጵያን ገቢ ጭነቶች እያጓጓዘ እንደሚገኝ የድርጅቱ ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ ሮባ መገርሳ ተናግረዋል።

የኢትዮጵያ ባህር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክ አገልግሎት ከኢትዮ-ጅቡቲ ባቡር ትራንስፖርት አ.ማ የስራ ኃላፊዎች ጋር ዘርፉን ማሳደግ በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ መክረዋል።

ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ ሮባ መገርሳ እንደገለፁት ድርጅቱ ከ345 በላይ ዓለም-አቀፍ ወደቦችን መዳረሻ አድርጎ የኢትዮጵያን ገቢ ጭነቶች እያጓጓዘ ይገኛል።

ዘርፉ የሚጠይቀውን የሰለጠነ የሰው ኃይል በማሟላትና ዘመናዊ ቴክኖሎጂን ተግባራዊ በማድረግ ከዓለም-አቀፍ ኩባንያዎች ጋር ተወዳዳሪ ሆኖ እየሰራና ትርፋማነቱን አስጠብቆ እየሄደ ነው ብለዋል፡፡

የድርጅቱ ካፒታል 20 ቢሊዮን ብር መሆኑን የገለጹት አቶ ሮባ ካፒታሉን ለማሳደግ እየተሰራ መሆኑንም ጠቁመዋል፡፡

የባቡር ትራንስፖርት አገልግሎት የገቢና ወጪ ጭነቶችን በፍጥነት በብዛትና ደህንነታቸው ተጠብቆ እንዲጓጓዙ በማድረግ ረገድ ከፍተኛ ጠቀሜታ አለው ያሉት አቶ ሮባ አገልግሎቱን የበለጠ እናሳድገዋለን ብለዋል፡፡

የኢትዮ-ጅቡቲ ባቡር ትራንስፖርት አ.ማ ዋና ዳይሬክተር አብዲ ዘነበ (ዶ/ር)፣ ውይይት ሁለቱ ድርጅቶች ይበልጥ ተቀራርበው ለመስራትና አገልግሎቱን ከዚህ የበለጠ ለማስፋት ትልቅ ፋይዳ አለው። የተጀመሩ መልካም ስራዎቸ እየጎለበቱ መሄድ እንዳለባቸው ገልጸዋል።

ኢትዮጵያን እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ሀገርን በዘላቂነት እናልማ
የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ
ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ
”ያልተረጋጋ የፖለቲካ ሁኔታን ንግግር እንጂ ጦርነት አይፈታውም"
– አቶ ሞገስ ባልቻ የዴሞክራሲ ሥርዓት ማስተባበሪያ ዘርፍ ኃላፊ ሚኒስትር
********************
(ኢ ፕ ድ)
በየትኛውም የዓለም ክፍል ያለውን ያልተረጋጋ የፖለቲካ ሁኔታ ንግግር እንጂ ጦርነት አይፈታውም ሲሉ የዴሞክራሲ ሥርዓት ማስተባበሪያ ዘርፍ ኃላፊ ሚኒስትር አቶ ሞገስ ባልቻ ገለጹ፡፡ አገራዊ ምክክሩ አገራዊ ተስፋ የሚሰጥ እንደሆነም ጠቅሰዋል፡፡

በጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት የዴሞክራሲ ሥርዓት ማስተባበሪያ ዘርፍ ኃላፊ ሚኒስትር አቶ ሞገስ ባልቻ ከኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ጋር በነበራቸው ቆይታ እንደጠቀሱት፤ በየትኛውም የዓለም አካባቢ ያለውን ያልተረጋጋ የፖለቲካ ሁኔታ የሚፈታው በጦርነት ሳይሆን በውይይት መድረክ ነው፡፡

ከጦርነት ይልቅ ንግግር ለመግባባት አዎንታዊ ሚና እንዳለው የገለጹት ሚኒስትሩ፤ ሁሉም የኢትዮጵያ ሕዝብ በተለያየ ማህበራዊ ትስስር ውስጥ ያለ በመሆኑ መለያየት እንደማይችል፤ መፍትሄው ደግሞ ተነጋግሮ አንድ መሆንና በተግባቦት ችግሮችን መፍታት የሚቻልበትን ሁኔታ መፍጠር ነው ብለዋል፡፡ ለዚህ ደግሞ አገራዊ ምክክሩ ጠቃሚ እንደሆነ ጠቅሰዋል፡፡ የማያግባቡና ልዩነት ላይ ያሉ ጉዳዮችን...

ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ
https://www.press.et/?p=70741

ኢትዮጵያን እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ክልሉ የሕዝብ ጥያቄዎችን ለመመለስ የሦስት ወራት ዕቅድ አዘጋጅቶ መተግበር መጀመሩን ገለጸ
******************
(ኢ ፕ ድ)

አንገብጋቢ የሕዝብ ጥያቄዎችን ለመመለስ የሦስት ወራት ዕቅድ በማዘጋጀት ወደ ትግበራ መግባቱን የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል አስታወቀ፡፡

የክልሉ ብልጽግና ፓርቲ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ይስሀቅ አብድልቃድር ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለጹት፤ ክልሉ በብልጽግና ፓርቲ ጉባኤ በተቀመጡ አቅጣጫዎች ዙሪያ ከሕዝቡ ጋር ውይይት በማድረግ የሕዝቡን አንገብጋቢ ጥያቄዎች ምላሽ ለመስጠት የሦስት ወራት ዕቅድ በማዘጋጀት ተግባራዊ እንቅስቃሴ ጀምሯል፡፡

ፓርቲው በአስቀመጣቸው አቅጣጫዎች ዙሪያ ከሕዝብ ውይይት መደረጉን አመልክተው፤ ፓርቲው ያስቀመጣቸውና ሕዝብ ያነሳቸው ጥያቄዎችን ለመመለስ ሕዝቡ፣ መንግሥትና ባለድርሻ አካላት እጅና ጓንት ሆነው ዕቅዱን ለመፈጸም ወደ ተግባር መገባቱን ገልጸዋል፡፡

ክልሉ የሕዳሴ ግድብ ግንባታ የሚካሄድበት ከመሆኑም አንጻር የተለያዩ ጸረ ሰላም ኃይሎች ፍላጎታቸውን የሚያንጸባርቁበት መሆኑን አመልክተው፤ ሸኔና በርታ ነፃ አውጪ የተሰኘው ቡድንና ሌሎች ጸንፈኞች ኃይሎች...

ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ
https://www.press.et/?p=70742

ኢትዮጵያን እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
በዘንድሮው ክረምት በደን ለመሸፈን ከታቀደው ከ448 ሺ በላይ ሄክታር መሬት መለየቱ ተጠቆመ
*******************
(ኢ ፕ ድ)

በመጪው ክረምት በደን ለመሸፈን ከታቀደው 800ሺ ሄክታር መሬት ውስጥ 448 ሺ 468 ሄክታር መሬት ለችግኝ ተከላ መለየቱን የኢትዮጵያ ደን ልማት አስታወቀ፡፡

እስካሁን ባለው መረጃ ሁለት ነጥብ 738 ቢሊዮን የደን ችግኝ ተፈልቶ መዘጋጀቱ ተጠቁሟል፡፡

በኢትዮጵያ ደን ልማት የደን ልማት ዳይሬክተር ጀነራል አቶ ቢተው ሽባባው ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለጹት፤ በሚቀጥለው ክረምት በደን ይሸፈናል ተብሎ ከታቀደው ስምንት መቶ ሺ ሄክታር መሬት መካከል እስካሁን በሁሉም የአገሪቱ አካባቢዎች 448 ሺ 468 ሄክታር መሬት ለችግኝ ተከላ ተለይቷል።፡

በዚህ ዓመት እንደ አገር የደንና የአገሮ ፎረስተሪው ችግኝ ተዳምሮ ስድስት ቢሊዮን ችግኝ ተፈልቶ ይተከላል ተብሎ ይጠበቃል፡፡ በደን ችግኝ በኩል ይለማል ተብሎ በዕቅድ የተያዘው አራት ቢሊዮን ችግኝ ሲሆን እስካሁን ባለው መረጃ ሁለት ነጥብ 738 ቢሊዮን ችግኝ ተፈልቶ ለተከላ...

ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ
https://www.press.et/?p=70772

ኢትዮጵያን እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
በክልሉ ለሚገኙ 71 ሺህ ተፈናቃዮች ድጋፍ መደረጉን ኮሚሽኑ አስታወቀ
*****
(ኢ ፕ ድ)

በአማራ ክልል ለሚገኙ 71 ሺህ ተፈናቃዮች በመንግሥት፣ በአካባቢው ማኅበረሰብ እና በአጋር አካላት ቅንጅት የገንዘብና የዓይነት ድጋፍ መደረጉን የአደጋ ሥራጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን አስታወቀ፡፡

ከኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ጋር ቆይታ ያደረጉት የአደጋ ሥጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ደበበ ዘውዴ እንደገለጹት፤ በአማራ ክልል ለሚገኙ 71 ሺህ ተፈናቃዮች ከ41 ሚሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ ለአንድ ወር ቀለብ የሚያገለግል 10 ሺህ 603 ኩንታል ምግብ ለተፈናቃዮች እንዲከፋፈል ተደርጓል።

በተጨማሪም 28 ሺህ 625 ልዩ ልዩ ምግብ ነክ ያልሆኑ ቁሳቁሶች ከኮሚሽኑ ክምችት ላይ ተቀናሽ ተደርጎ ለመጠለያ ካምፖቹ ተሠራጭቷል፡፡ ኮሚሽኑ 3 ነጥብ 5 ሚሊዮን ብር ለእነዚሁ ካምፖች ለወጪ እንዲውል ወደ ክልሉ እንዲላክ ማድረጉንም አቶ ደበበ ተናግረዋል፡፡

እንደ ኃላፊው ገለጻ፤ በአማራ ክልል ሰሜን ወሎ ዞን ከአላማጣ ከተማ፤ ከአላማጣ ዙሪያ ከኮረም፣ ከኦፍላ፣ ራያ ባላ፣ ዛታ እንዲሁም ከራያ ቆቦ ገጠር ቀበሌዎች ተፈናቅለው በራያ ቆቦ ከተማ በተለያዩ...

ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ
https://www.press.et/?p=70775

ኢትዮጵያን እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ሀገርን በዘላቂነት እናልማ
የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ
ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ
ልዩነቶችን ለሁለንተናዊ እድገት ለማዋል የጀመረውን ጥረት አጠናክሮ እንደሚቀጥል ሚኒስቴሩ ገለጸ
****
(ኢ ፕ ድ)

በኢትዮጵያ የሚታዩ የቋንቋ፣ የባህልና ሌሎች የልዩነት እሴቶችን ለሁለንተናዊ እድገት ለማዋል የጀመረውን ጥረት አጠናክሮ እንደሚቀጥል የባህልና ስፖርት ሚኒስቴር ገለጸ፡፡

ሚኒስትሩ አቶ ቀጄላ መርዳሳ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለጹት፤ በልዩነት ውስጥ የአንድነትና የወንድማማችነት እሴቶችን ማጉላት ለአገሪቱ ሁለንተናዊ እድገት ወሳኝ ነው፡፡

ብዝሃነት ለአንድ አገር የውበት ምንጭና የተለያየ ተፈጥሯዊ ማንነት መገለጫ ሆኖ ሳለ ባለፉት ዓመታት ከአንድነትና ከወንድማማችነት እሴቶች ይልቅ በልዩነት ላይ ሰፊ ሥራ በመሠራቱ በአሁኑ ጊዜ ብዝሃነታችን የጭቅጭቅ ምንጭ ሲሆን ይታያል ብለዋል፡፡

በቴክኖሎጂና በኢኮኖሚ እድገት ቀዳሚ ተርታ ላይ የሚሰለፉ እንደ አሜሪካና ካናዳ ያሉ አገሮች ለአንድነትና ወንድማማችነት ቅድሚያ በመስጠታቸው የባህልና የቋንቋ ልዩነት.....

ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ
https://www.press.et/?p=70772

ኢትዮጵያን እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ሀገርን በዘላቂነት እናልማ
የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ
ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ
የሕዝብ ጥያቄዎችን ለመመለስና ፓርቲው ያሳለፋቸውን ውሳኔዎች ተግባራዊ ለማድረግ ወደ ስራ መግባቱን የሀረሪ ክልል ብልፅግና ፓርቲ አስታወቀ
****
(ኢ ፕ ድ)

ብልፅግና ፓርቲ የሕዝብ ጥያቄዎችን ለመመለስ በጉባኤው ያስቀመጣቸውን አቅጣጫዎችና ያሳለፋቸውን ውሳኔዎች ተግባራዊ ለማድረግ ወደ ስራ መግባቱን የሀረሪ ክልል ብልፅግና ፓርቲ አስታወቀ።

በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የክልሉ ብልፅግና ፓርቲ ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ አብዱጀባር መሀመድ በሰጡት መግለጫ እንደገለጹት፤ ብልፅግና ፓርቲ በጉባኤው ባስቀመጠው አቅጣጫና ውሳኔ መሰረት ከህዝብ ጋር በተደረጉ ውይይቶች ሲነሱ የነበሩ ጥያቄዎች ለመመለስ የአጭርና ረጅም ጊዜ ዕቅድ በማውጣት ወደ ተግባር መግባቱን ገልጸዋል።

የክልሉ ብልፅግና ፓርቲ በክልል ደረጃ በእቅዱ መሰረት ስራዎችን እየተከናወኑ እንደሚገኙ በየአራት ቀናት ከአመራሩ ጋር እየገመገመ እንደሚገኝ ተናግረዋል።

የክልሉን ሕዝብ ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ማሕበራዊ ችግሮችን ለመፍታት የሚያስችለውን የ90 ቀን ዕቅድ በማዘጋጀት ወደ ትግበራ ምዕራፍ መሸጋገሩን ገልጸዋል።

በክልሉ በተለያዩ አካባቢዎች ሕዝባዊ የውይይት መድረኮች ከተደረጉ በኋላ ከመጋቢት 29 ቀን ጀምሮ እስከ ሰኔ 30,2014 ዓ.ም ድረስ አንገብጋቢ የሕዝብ ጥያቄዎች ምላሽ የሚሰጥበት መሆኑን አመልክተዋል።

በትግበራው ምዕራፍ በፓርቲው የተቀመጡ ግቦችን መሠረት በማድረግ እያንዳንዱ መስሪያ ቤት በሚመለከተው ልክ የራሱን መሪ ዕቅድ በማዘጋጀት ወደ ትግበራ እንዲገቡ አቅጣጫ ተቀምጦ የሕዝብ ጥያቄዎችን ለመመለስ ተግባራዊ እንቅስቃሴ መጀመሩንም አስታውቀዋል።

እንደ ጽ/ቤት ሀላፊ ገለጻ ፤ በሚቀጥሉት ሶስት ወራትም በክልሉ መልካም አስተዳደር በማስፈን ፣ ኑሮ ውድነትን በማረጋጋት ፣ አገልግሎት አሰጣጥን ማሻሻል ፣ የሕግ የበላይነት ማረጋገጥና ሌብነትን የሚጠየፍ ማሕበረሰብ በመፍጠር ጉዳዮች ላይ ትኩረት ይደረጋል ብለዋል።

በመጪዎቹ ሶስት ወራትም በአገልግሎት አሰጣጥ ማሻሻል በከተማና በገጠር የሥራ ዕድል መፍጠር የሚጠበቁ ውጤቶች ናቸው ብለዋል።

ክልሉ የሕዝብ ጥያቄዎች ለመመለስ የጀመረውን ተግባራዊ እንቅስቃሴ ስኬታማ እንዲሆንም የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት የበኩላቸውን አስተዋጽኦ እንዲያበረክቱ ጥሪ አቅርበዋል።

ኢትዮጵያን እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ሀገርን በዘላቂነት እናልማ
የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ
ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ
የኢትዮጵያ ለመጉዳት የተዘጋጁት 'ኤች አር 6600' እና 'ኤስ 3199' ረቂቅ ሕጎች እንዳይጸድቁ የዳያስፖራው ሁለገብ ጥረት ያስፈልጋል
****************
(ኢ ፕ ድ)
ኢትዮጵያንና ሕዝቦቿን ለመጉዳት እንዲሁም ከዓለም የፋይናንስ ስርዓት ለማስወጣት የተዘጋጁት 'ኤች አር 6600' እና 'ኤስ 3199' ረቂቅ ሕጎች እንዳይጸድቁ ዳያስፖራው ሁለገብ ጥረት እንዲያደርግ ተጠየቀ።
በቨርጂኒያ ግዛት የሚገኘው የ'ፑሽ ስታርት' ሚዲያ ጋዜጠኛና የመብት ተሟጋች ቤቲ ተከስተ፤ ከኢዜአ ጋር በነበራት ቆይታ እንዳለችው ረቂቅ ሕጎቹ ኢትዮጵያ ከአሜሪካ የምታገኛቸውን የልማትና የደህንነት ድጋፎች የሚያስቆሙ ናቸው።
በተለይም የልማት ድጋፎች መቆም በተለያዩ ፕሮጀክቶች ተጠቃሚ በሆነው ሕዝብ ላይ የሚያደርሰው ጉዳት ከፍተኛ መሆኑን ትናገራለች።
አሜሪካ ዓለም አቀፍ የፋይናንስ ተቋማትን በማስተባበር ለኢትዮጵያ እርዳታና ድጋፍ እንዳያደርጉ ተጽእኖ የሚያሳድር መሆኑንም ገልፃለች።
በረቂቅ ህጉ ላይ ኢትዮጵያ ከአሜሪካ መሳሪያና የመሳሪያ መለዋወጫዎችን እንዳትገዛ ጭምር የሚከለክሉና ከዓለም የፋይናንስ ስርዓት ውጪ የማድረግ አላማ ያላቸው መሆናቸውንም ጋዜጠኛዋ ተናግራለች።
ከሌሎች አገራት መሳሪያ ከገዛች ደግሞ አሜሪካ በሻጭ ሀገራት ላይ ማዕቀብ እንድትጥል ድንጋጌ የሚያስቀምጥ ስለመሆኑ ጠቁማ በኢትዮጵያ ሉዓላዊነት ላይ ጭምር ጫና የሚያሳድር ነው ብላለች።
የረቂቅ ሕጎቹን ይዘት መንግስትን ከመደገፍና ከመቃወም ጋር የሚያያዝ ሳይሆን አጠቃላይ በአገር ሉዓላዊነት ላይ ችግር የሚጋርጥና ሕዝብን የሚጎዳ መሆኑን ሁሉም ሊገነዘበው ይገባል ነው ያለችው።
በመሆኑም ረቂቅ ሕጎቹ ከጸደቁ ኢትዮጵያን ከዓለም የፋይናንስ ስርዓት የሚያስወጡ እና በሉዓላዊነቷ ላይ ጫና የሚያሳድር በመሆኑ ሁሉም በጋራ ተቃውሞውን ሊያሰማ ይገባል ብላለች።
በተለይም የዳያስፖራው ማሕበረሰብ የኢትዮጵያን ትክክለኛ እውነታ ለዓለም በማስረዳትና ረቂቅ ሕጎቹን በፅኑ መቃወሙን አጠናክሮ መቀጠል አለበት በማለት መልዕክቷን አስተላልፋለች።
ረቂቅ ሕጎቹ በአሜሪካ ምክር ቤቶች ውስጥ ከፍተኛ ስልጣን ባላቸው የ'ዴሞክራት'ና የ'ሪፐብሊካ'ን ፓርቲ አባላት ድጋፍ ማግኘታቸውን አንስታለች።
ከዚህም አልፎ ሕጎቹ በአግባቢ ድርጅቶች ግፊት ወደ ሕግ አውጪው ምክር ቤት እንዲደርሱ መድረጉን ጋዜጠኛ ቤቲ አስታውሳለች።
በተለይም ‘ኤች.አር 6600’ ረቂቅ ሕግ በኮንግረሱ የውጭ ግንኙነት ኮሚቴ ድጋፍ በማግኘቱ በኮንግረሱ የአፍሪካ ጉዳዮች ንዑስ ኮሚቴ መታየት ቢኖርበትም እሱን አልፎ በቀጥታ ለኮንግረሱ መድረሱን አክላለች።
በአሁኑ ሰአት ሁለቱን ረቂቅ ሕጎች ኮንግረሱና ሴኔቱ እንዲያያቸው በኮሚቴዎች መመራታቸውንም ጠቅሳለች።
ይህም ቢሆን በዚህ ጊዜ ሕጎቹ በቀጥታ ድምጽ ሊሰጥባቸው እንደማይችልና ቀሪ የሕግ ሂደቶች እንዳሉ ሁሉም ሊገነዘብ ይገባል ብላለች።
በአሜሪካ የሚኖሩ ዳያስፖራዎችና የዳያስፖራ አደረጃጀቶች ረቂቅ ሕጎቹ ድምፅ እንዳይሰጥባቸው ተሰሚነት ያላቸውን የኮንግረስ አባላትና ሴናተሮች የማሳመን ስራ እየሰሩ መሆኑንም ጠቁማለች።
በተለይ የአሜሪካ ኮንግረስ አፈ-ጉባኤ ናንሲ ፔሎሲን በስልክ በማነጋገርና ደብዳቤ በመጻፍ በእጇ ላይ የሚገኘው የኤች.አር 6600 ለኮንግረስ በአጀንዳነት እንዳታቀርበው ጥረት እየተደረገ ነው ብላለች።
የአሜሪካ የሕግ አስፈጻሚው አካል ከኢትዮጵያ ጋር ያለንን ግንኙነት ማሻሻል እንደሚፈልግ እየገለጸ ባለበት ወቅት ረቂቅ ሕጎቹ መውጣታቸው ግራ የሚያገባ መሆኑንም ጋዜጠኛ ቤቲ ተናግራለች።
በመሆኑም ዳያስፖራው ግራ ሳይጋባ በአንድነት ሕጎቹ ሊጸድቁ የሚችሉበትን እድሎች ለመዝጋት ሁለገብ ትግል እንዲያደርግ ጠይቃለች።
ኤች.አር 6600 ረቂቅ ሕግ የአሜሪካ ኮንግረስ የውጭ ግንኙነት ኮሚቴ ተወያይቶበት ለኮንግረሱ መምራቱ የሚታወስ ነው።
የ'ኤች.አር 6600' አጋዥ የሆነው 'ኤስ 3199' ረቂቅ ሕግ የአሜሪካ ሴኔት እ.አ.አ በ2022 ዓ.ም ሊመለከታቸው በጊዜ ሰሌዳው ከያዛቸው ረቂቅ ሕጎች አንዱ ሆኖ እንዲካተት መወሰኑ ይታወሳል።
ኢትዮጵያን እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ‼️
ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼️
የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ‼️
ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼️
የመሬት ይዞታ ምዝገባና መረጃ ኤጀንሲ ከ25 ሺህ በላይ ይዞታዎችን ለመመዝገብ መዘጋጀቱን ገለጸ
*****************
(ኢ ፕ ድ)
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመሬት ይዞታ ምዝገባና መረጃ ኤጀንሲ ከ25 ሺህ በላይ የመሬት ሀብት ይዞታዎችን በመስክና በሰነድ አረጋግጦ ለመመዝገብ ዝግጅት ማጠናቀቁን አሰታወቀ።
የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር አቶ ክፍሌ ገብሬ በሰጡት መግለጫ እንዳስታወቁት ከ25 ሺህ በላይ የመሬት ሀብት ይዞታዎችን በመስክና በሰነድ አረጋግጦ ለመመዝገብ ዝግጅት ተጠናቋል። ምዝገባውና አዋጁ ከ15 ቀናት በኋላ ተግባራዊ ይሆናል።
ምዝገባው በአዲስ አበባ ከተማ ስር በሚገኙ ክፍለ ከተሞች እንደሚካሄድ የገለፁት አቶ ክፍሌ፣ ምዝገባው የለሚ ኩራን ክፍለ ከተማን ሳይጨምር እንደሚካሄድ ገልጸዋል።
በሥራው ሒደትም በአካባቢዎቹ የስም ዝውውርን ጨምሮ ሌሎች አገልግሎቶች አይኖሩም ብለዋል።
በምዝገባው ሂደት ወቅት ግልጽነት እንዲኖርም በ25 ቀጠናዎች የምዝገባ ሥራ ላይ ከከተማዋ የተወጣጡ የማህበረሠቡ ክፍሎች ይሳተፋል።
በሙሳ ሙሐመድ
ኢትዮጵያን እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ‼️
ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼️
የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ‼️
ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼️
ለግሉ ዘርፍ እድገት የሚሆን የ25 ሚሊየን ዩሮ ፕሮጀክት ይፋ ሆነ
****************
(ኢ ፕ ድ)
በኢትዮጵያ ለግሉ ዘርፍ እድገት የ25 ሚሊየን ዩሮ ፕሮጀክት የማስጀመሪያ ወርክሾፕ በአዲስ አበባ እየተካሄደ ነው።
ፕሮጀክቱ በኢንዱስትሪ ሚኒስቴር እና በጀርመን ዓለም አቀፍ የልማት ትብብር ድርጅት (ጂአይዜድ) የተዘጋጀ ሲሆን ለ4 ዓመታት የሚቆይና ከሚያዝያ ወር ጀምሮ ተግባራዊ የሚሆን ነው።
የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የኢንዱስትሪ ሚኒስትር ዴኤታ ሺሰማ ገብረሥላሴ የግሉ ዘርፍ በድህነት ቅነሳ ፈጣን እድገት ለማስመዝገብ እየተደረገ ባለው ሀገራዊ እንቅስቃሴ ከፍተኛ ሚና እንዳለው ተናግረዋል።
በተለይም ምርታማነትን በማሻሻልና የሥራ አጥን ቁጥር በመቀነስ የራሱ ድርሻ እንዳለው ጠቅሰዋል።
የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ለግሉ ዘርፍ እድገት የተለያዩ ተግባራትን እያከናወነ መሆኑን ጠቅሰው በተለይም የማምረቻ የኢንደስትሪ ዘርፉን እድገትና ተወዳዳሪነት ለማሻሻል እየሠራ ነው ብለዋል።
የግሉ ዘርፍ መር የሆነ ኢኮኖሚ ለመፍጠርም እየተሠራ ነው ብለዋል። የጀርመን መንግሥት በጂአይዜድ በኩል ለግሉ ዘርፍ እድገት ላለፉት ስድስት ዓመታት ድጋፍ በማድረግ ላይ መሆኑን ጠቅሰዋል።
በተለይም የጨርቃጨርቅ ኢንዱስትሪዎች አካባቢያዊ እና ማህበራዊ ጥበቃን መሠረት ያደረገ ደረጃ እንዲኖራቸው በሥራ እድል ፈጠራና በኢንቨስትመንት ትልቅ ሚና እየተጫወተ ነው ብለዋል።
የጀርመን መንግሥት በኢትዮጵያ በሥራ እድል ፈጠራ በገቢ እና በእሴት ጨማሪ ምርቶች ሚናቸውን እየተወጡ ለሚገኙ ጀማሪ፣ አነስተኛና መካከለኛ ኢንዱስትሪዎችን ለመደገፍ የጀመረው ፕሮጀክትም የሚበረታታ ነው ብለዋል።
ጀርመን በኢትዮጵያ ለግሉ ዘርፍ እድገት አስተዋፅኦ ማድረጓ ተጠቅሷል።
በጂአይዜድ የኢትዮጵያ የግሉ ዘርፍ እድገት ዘርፍ ኃላፊ ወይዘሮ አረጋሽ አስፋው እንደተናገሩት ፕሮጀክቱ የግሉን ዘርፍ ለመደገፍ የሚውል ነው።
ጂአይዜድ ባካሄደው ጥናት ለአነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች የሚሰጠው የፋይናንስ ድጋፍ አነስተኛ መሆኑን አረጋግጧል ብለዋል።
በመሆኑም ኢንተርፕራይዞችን ለማጠናከር ከመንግሥት ጋር በትብብር ለመሥራት ለአራት ዓመታት የሚቆይ ፕሮጀክት ይፋ መሆኑን የኢዜአ ዘገባ ያመለክታል።
ፕሮጀክቱ የ25 ሚሊየን ዩሮ ሲሆን አዲስአበባን ጨምሮ በተለያዩ ክልሎች ተግባር ላይ እንደሚውል ጠቅሰዋል።
በመድረኩ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴኤታ ባይሳ በዳዳን ጨምሮ የመንግሥት ከፍተኛ ኃላፊዎች፣ የጀርመን ኤምባሲና የጂአይዜድ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።
ኢትዮጵያን እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ‼️
ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼️
የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ‼️
ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼️
ወልድያ ዩኒቨርሰቲ ለዋግኽምራ ተፈናቃዮች ከአንድ ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት ድጋፍ አደረገ
*************
(ኢ ፕ ድ)
የወልድያ ዩኒቨርሰቲ ለዋግኽምራ ተፈናቃዮች ከ1.3 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት የዓይነት ድጋፍ አደረገ፡፡
ከቤት ንብረታቸው ተፈናቅለው በሰቆጣ መጠለያ ጣቢያ ለሚገኙ ተፈናቃዮች ግምቱ ከ አንድ ነጥብ 3 ሚሊዮን ብር በላይ የሆነ 300 ኩንታል የስንዴ ዱቄት ድጋፍ ማድረጋቸውን የዩኒቨርስቲው ምርምርና የማህበረሰብ አገልግሎት ምክትል ፕሬዝደንት ዶ/ር ሰለሞን አበጋዝ ገልፀዋል፡፡
ድጋፉን የተረከቡት አቶ ሄኖክ ነጋሽ የወልድያ ዩኒቨርስቲ በርካታ ችግሮች እያለበት ችግራችን አሳስቦት ላደረገው ድጋፍ አመስግነው፣ ዩኒቨርስቲው የጀመረውን ድጋፎች አጠናክሮ እንዲቀጥልና ሌሎች ተቋማት ድጋፍ እንዲያደርጉ ጥሪ ማቅረባቸውን ከዞኑ ኮሙዩኒኬሽን የተገኘው መረጃ ያመለክታል።
ኢትዮጵያን እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ‼️
ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼️
የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ‼️
ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼️