የህብረት ስራ ማህበራት ለህብረተሰቡ የሚሰጡትን አገልግሎት ወደ ላቀ ደረጃ ለማሳደግ በየደረጃው የሚገኙ አመራሮች ድጋፍ እንዲያደርጉ ተጠየቀ
*********************
(ኢ ፕ ድ)
በከተማዋ የሚገኙ የህብረት ስራ ማህበራት ለህብረተሰቡ የሚሰጡትን አገልግሎት ወደ ላቀ ደረጃ ለማሳደግ በየደረጃው የሚገኙ አመራሮች ሁለንተናዊ ድጋፍ እንዲያደርጉ ተጠየቀ
የህብርት ስራ ማህበራት የሚስተዋሉባቸው ችግሮች ስር ነቀል በሆነ አግባብ ለመፍታት አላማ ያደረገ ከተማ አቀፍ የህብረት ስራ ማህበራት የንቅናቄ መድረክ በመካሄድ ላይ ነው፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ህብረት ስራ ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር አቶ ግዛቸው አሊ በመርሀ ግብሩ ላይ እንደገለጽት በከተማዋ በተለያዩ ዘርፎች ከ8 ሺህ በላይ የህብረት ስራ ማህበራት ተደራጅተው ይገኛሉ። የህብረት ስራ ማህበራቱ ከአንድ ነጥብ 5 ሚሊዮን አባላት አላቸው።
እንደ ዋና ዳይሬክተሩ ገለፃ በገንዘብ ቁጠባና ብድር አገልግሎት 1ሺህ 186 ህብረት ስራ ማህበራት በመደራጀት ከ6 ቢሊዮን ብር በላይ በመቆጠብ የከተማውን ነዋሪ የቁጠባ ባህል እንዲዳብር በማድረግ ከተቆጠበው ለማህበሩ አባላትና ለሌሎች ዜጎች የስራ እድል በመፍጠር የራሳቸውን ድርሻ እየተወጡ ይገኛሉ ብለዋል፡፡
በከተማዋ 148 መሰረታዊ የሸማቾች ህብርት ስራ ማህበራትና 10 የሸማች ህብርት ስራ ዩኒየኖች በመጠቀም ከገጠር ከተማ የገበያ ትስስር በመፍጠር ለአባሉ ብሎም ለመላው የከተማችን ነዋሪ የግብርናና የግብርና ውጤቶችን ተደራሽ እያደረጉ ነው። የኢንዱስትሪ ምርቶች ለተጠቃሚው በማቅረብም የበኩላቸውን ሚና እየተጫወቱ እንደሚገኙም አቶ ግዛቸው ገልጸዋል፡፡
የኅብረት ስራ ማኅበራቱ የሚጠበቅባቸውን ሚና ከመወጣት አኳያ ለአባላቶቻቸውም ሆነ ለህዝቡ ከሚሰጡት አገልግሎት አንጻር ሲታይ ፤ የብልሹ አሰራርና የመልካም አስተዳደር ችግሮች በስፋት ይነሳሉ። እነዚህን የዘመናዊነት አሰራርና የአገልጋይነት ችግሮች ለመፍታት ህብረት ስራ ማህበራቱን በአሰራር፤ በአደረጃጀት ፤በግብአት ስር ነቀል ሪፎረም በማድረግ ህብረት ስራ ማህበራቱን ማስተካከል አላማ ያደረገ የንቅናቄ መድረክ መሆኑንም ተናግረዋል።
የመንግስት አመራር አካላት ከፍተኛ ድጋፍ ከታከለበት በማህበራቱ በኩል የሚታዩ ጉድለቶች ለማረምና ማህበራቱን ለተሸለ አገልግሎት ለማብቃት ጉልህ ሚና ስለሚኖረው በተለይ በየደረጃው የሚገኝ አመራር አስፈላጊውን ድጋፍና ክትትል በማድረግ የበኩላቸውን ሚና እንዲወጡ ዋና ዳይሬክተሩ ጥሪ ማቅረባቸውን ከከንቲባ ጽ/ቤት መረጃ ያመለክታል።
ኢትዮጵያን እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ‼️
ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼️
የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ‼️
ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼️

በጀርመን የሚዘጋጁ የአፍሪካ ኹነቶችን በአዲስ አበባ ለማዘጋጀት የሚያስችል ምክክር ተካሄደ
**************
(ኢ ፕ ድ)
በጀርመን አዘጋጅነት የሚካሄዱ የአፍሪካ ኹነቶችን በአዲስ አበባ ከተማ ለማዘጋጀት የሚያስችል ምክክር ተካሄደ።
በምክክር መድረኩ ላይ የአፍሪካ ህብረት፣ በኢትዮጵያ የጀርመን ኤምባሲ እና የኢፌዲሪ ቱሪዝም ሚኒስቴር ተሳትፈዋል።
በመድረኩ የተገኙት ቱሪዝም ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ስለሺ ግርማ እንደገለፁት መሰል ሁነቶች ወደ ኢትዮጵያ መምጣታቸው ለሀገሪቱ ኢኮኖሚያዊ፣ ማህበራዊና ፖለቲካዊ ጠቀሜታቸው የጎላ ነው።
ኹነቶቹ ወደ ኢትዮጵያ መጥተው ሲከናወኑ ለዝግጅቱ የሚያሰፈልገው ወጪ ሙሉ በሙሉ በአዘጋጆቹ እንደሚሸፈን ተገልጸዋል።
በኢትዮጵያ የጀርመን አምባሳደር ስቴፈን አወር በበኩላቸው ጀርመን ኹነቱን ኢትዮጵያ ላይ መከናወኑ በሁለቱ ሀገራት መካከል ያውን በሁሉም ዘርፍ ያለውን ትብብር እንደሚያጠናክረው ገልፀዋል።
በዳግማዊት ግርማ

ገንዘብ እናባዛለን ብለው ከአንድ ነጥብ 5 ሚሊዮን ብር በላይ ለማጭበርበር የሞከሩ ግለሰቦችን በቁጥጥር ስር ማዋሉን ፖሊስ አስታወቀ
*****************
(ኢ ፕ ድ)
በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 13 ልዩ ቦታው ቦሌ ሆምስ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ገንዘብ እናባዛለን ብለው ከአንድ ግለሰብ ላይ ከአንድ ነጥብ 5 ሚሊዮን በላይ ብር ለማጭበርበር የሞከሩ ግለሰቦችን ይዞ ምርመራ እያጣራ መሆኑን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታወቀ።
በበዓላት መዳረሻ ወቅቶች ሃሰተኛ ገንዘቦች በገበያው ውስጥ ሊሰራጩ ስለሚችሉ ህብረተሰቡ አስፈላጊውን ጥንቃቄ ማድረግ እንደሚገባም ተገልጿል፡፡
አንድ ግለሰብ በአጋጣሚ ለተዋወቁት ሰው ገንዘብ እንደቸገራቸው ከነገሩትና ይህ ሰውም "ገንዘብ የሚያባዛ ሰው አውቃለሁ ችግር የለም ያባዛሎታል" ካላቸው በኋላ ነበር የወንጀል ድርጊቱ የተፈፀመው፡፡
ገንዘብ ቸግሮኛል ያሉት ግለሰብ እንዲባዛልኝ ብለው ለተጠርጣሪዎቹ 2 ሚሊዮን ብር ስለመስጠታቸው በምርመራ ወቅት መግለፃቸውን የጠቀሰው የአዲስ አበባ ፖሊስ ገንዘብ እንዲባዛ አደርጋለሁ ያለው ተጠርጣሪ የናይጄሪያ ዜግነት ካለው ግብራበሩ ጋር በመሆን የወንጀል ድርጊቱን ለመፈፀም በዝግጅት ላይ እያሉ ፖሊስ የደረሰውን መረጃ መሰረት በማድረግ ገንዘብ ይባዛበታል በተባለው ቤት ውስጥ በህግ አግባብ ብርበራ ማከናወኑን ገልጿል፡፡
በተደረገው ብርበራም እንዲባዛላቸው ግለሰቡ ሰጥቻለሁ ካሉት 2 ሚሊዮን ብር ውስጥ 1 ሚሊዮን 555 ሺህ 8 መቶ ብር በቁጥጥር ስር ውሏል፡፡ በተጨማሪም በብር መጠን የተቆራረጠ በርካታ ወረቀት፣ ኬሚካል እና ማተሚያ ማሽን ተይዟል፡፡
ከጉዳዩ ጋር በተያያዘ ሁለት ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ውለው ምርመራው የቀጠለ ሲሆን ፖሊስ ገንዘብ ይባዛበታል ወደ ተባለው ቤት ለብርበራ በሄደበት ወቅት ተጠርጣሪዎቹ ማስረጃ ለማጥፋት በማሰብ በብር መጠን ተቆራርጦ የተቀመጠውን ወረቀት በእሳት ለማቃጠል እና የጣራ ቆርቆሮ ገንጥለው ለማምለጥ መሞከራቸውን አስታውቋል፡፡
ህገ-ወጥ ተግባራት በህብረተሰቡ እና በፀጥታ አካላት ትብብር እየከሸፉ እንደሚገኙ የጠቀሰው የአዲስ አበባ ፖሊስ በተለይም ከበዓላት መቃረብ ጋር ተያይዞ ሃሰተኛ ገንዘቦችን ወደ ገበያ ውስጥ ለማሰራጨት የሚደረጉ እንቅስቃሴዎችን በተቀናጀ መንገድ በቁጥጥር ስር ማዋል እንደሚገባ እና ህብረተሰቡም አስፈላጊውን ጥንቃቄ ማድረግ እንደሚጠበቅበት መልዕክቱን አስተላልፏል፡፡

ለሁለተኛ ጊዜ የህክምና ቁሳቁሶችንና አስቸኳይ የምግብ ድጋፎችን የያዘ ቡድን መቀሌ ደርሷል
********************
(ኢ ፕ ድ)
በዚህ ወር ለሁለተኛ ጊዜ የህክምና ቁሳቁሶችን፣ አስቸኳይ የምግብ ድጋፎችን አስፈላጊ የቤት ውስጥ ቁሳቁሶችን የያዘ ቡድን መቀሌ መግባታቸውን የዓለም አቀፍ ቀይ መስቀል ኮሚቴ አሰታወቀ።
ለሁለተኛ ጊዜ የህክምና ቁሳቁሶችን፣ አስቸኳይ የምግብ ድጋፎችን፣ የውሃ ማጣሪያ ግብዓቶችንና አስፈላጊ የቤት ውስጥ ቁሳቁሶችን የያዘ ቡድን ዛሬ ሚያዝያ 6፣ 2014 ዓ.ም መቀሌ ገብተዋል።
በተጨማሪም ድጋፉ ለአካል ተሃድሶ ማዕከል አስፈላጊ የሆኑ የህክምና ቁሳቁሶችንም ያካተተ መሆኑንም የዓለም አቀፍ ቀይ መስቀል ኮሚቴ በማህበራዊ ትስስር ገጹ አሰታውቋል።
ኢትዮጵያን እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ‼
ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼
የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ‼
ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼