ኢትዮጵያ የዓረብ ሊግ በሕዳሴ ግድብ ላይ ያሳለፈውን የውሳኔ ሃሳብ እንደማትቀበል ገለጸች
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 14፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ÷የዓረብ ሊግ በሕዳሴ ግድብ ላይ ያሳለፈውን የውሳኔ ሃሳብ እንደማትቀበለው አስታውቃለች፡፡
የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ጉዳዩን አስመልክቶ ባወጣው መግለጫ÷በቅርቡ የተካሄደው የዓረብ ሊግ የመሪዎች ጉባኤ ያሳለፈው የውሳኔ ሀሳብ የኢትዮጵያን መንግስት እንዳሳዘነ ገልጿል፡፡
ውሳኔው በተለይም በግድቡ ዙሪያ ያለውን አለመግባባት በሰላማዊ ድርድር አንዲፈታ እየሰሩ ያሉትን የአፍሪካ ህብረትና አባል ሀገራትን ሚና የሚያኮስስ ነው ሲል አብራርቷል፡፡
የውሳኔ ሃሳቡ ታሪክን ከሚጋራው የአፍሪካ እና የዓረብ ሀገራት ግንኙነት በተቃራኒ የተላለፈ መሆኑንም አስገንዝቧል፡፡
በሊጉ የተላለፈው የውሳኔ ሃሳብ የግብጽን የናይል ወንዝ ፍትሃዊ ያልሆነ አጠቃቀም የሚደግፍ መሆኑንም አጽንኦት ሰጥቷል፡፡
ግብጽ በቅኝ ግዛት ወቅት የተፈረመን ስምምነት በመጥቀስ የምታቀርበውን አላስፈላጊ ቅሬታም ሚኒስቴሩ ውድቅ አድርጓል፡፡
ኢትዮጵያ ከሱዳን ጋር የሕዳሴ ግድብን ጨምሮ በሌሎች የሁለትዮሽ ግንኙነቶች ላይ በቅርበት እየሰራች መሆኑም መግለጫው አመላክቷል፡፡

👍44❤16😱3
አዲስ አበባ እና ዴንቨር በጋራ ለመስራት የመግባቢያ ሰነድ ተፈራረሙ
አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 14፣ 2015 (ኤፍ ቢሲ) የአዲስ አበባ እና ዴንቨር ከተሞች በጋራ መስራት የሚያስችላቸውን የመግባቢያ ሰነድ ተፈራርመዋል፡፡
ከንቲባ አዳነች አቤቤ÷ስምምነቱ የሁለቱን ከተሞች ግንኙነት ይበልጥ በማጠናከር በንግድ፣ በኢንቨስትመንት እና በቴክኖሎጂ ዘርፎች በጋራ ለመስራት የሚስችል ነው ብለዋል፡፡
ከተማ አስተዳደሩ በዓለም የንግድ ቀን ፕሮግራም ላይም ኢትዮጵያን የሚያስተዋውቁ ምርቶችን ማስተዋወቁን ከንቲባዋ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው አስፍረዋል፡፡
ከንቲባ አዳነች እና ልዑካቸው በዴንቨር ከተማ ለተደረገላቸው አቀባበል እና መስተንግዶ ለከተማዋ ከንቲባ ምስጋና አቅርበዋል፡፡

👍56😁20🤔8👏3❤2😢2
ለዘንድሮው የአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ ግብር 6 ነጥብ 5 ቢሊየን ችግኝ እየተዘጋጀ ነው - ጠ/ሚ ዐቢይ
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 15፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ለአምስተኛው ዓመት የአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ ግብር 6 ነጥብ 5 በሊየን ችግኝ እየተዘጋጀ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ገለጹ፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሑፍ ÷"በ5ኛው ዓመት የአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ ግብር በጋራ ለምንተክለው 6 ነጥብ 5 ቢሊየን ችግኝ ዝግጅት እየተካሄደ ነው" ብለዋል።
በዘንድሮው መርሐ ግብር የፍራፍሬ ዛፎችን በብዛት እንተክላለን ሲሉም አስገንዝበዋል፡፡

👍45😁23❤14🤔7🥰2😢1💩1
በሀገር በቀል ኢኮኖሚ ማሻሻያ አጀንዳ ላይ ውይይት እየተካሄደ ነው
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 15፣ 2015(ኤፍ ቢ ሲ) በሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ አጀንዳ የመጀመሪያ ምዕራፍ አፈጻጸም ላይና የሁለተኛው ምዕራፍ ዝግጅት ላይ ውይይት እየተካሄደ ይገኛል፡፡
ትናንት የመንግስት የ2015 በጀት ዓመት ዘጠኝ ወራት አፈጻጸም መገምገሙ ይታወቃል።
እየተካሄደ ባለው ውይይት ሚኒስትር ዴኤታዎች፣ የተቋማት ኃላፊዎችና የሕዝብ ተወካዮችና ፌዴሬሽን ምክር ቤት አባላት ተገኝተዋል።
በዛሬው የግምገማ መድረክ ከ2012 እስከ 2015 ዓ.ም የተተገበረው የሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ አጀንዳ አፈጻጸምን በመዳሰስ በተዘጋጀው ሁለተኛው የሀገር በቀል ኢኮኖሚ ሪፎርም ላይ ምክክር ይደረጋል። ... https://www.fanabc.com/archives/194654

👍27❤8
ጀርመን ለኢትዮጵያ የምታደርገውን ድጋፍ አጠናክራ እንደምትቀጥል ገለጸች
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 15፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የገንዘብ ሚኒስትር አሕመድ ሽዴ የጀርመን የአፍሪካ ኢኮኖሚ ትብብር እና ልማት ዋና ዳይሬክተር ቢርጊት ፒከል ጋር ተወያይተዋል፡፡
ውይይቱ ከአፍሪካ ልማት ባንክ ቦርድ ስብሰባ ጎን ለጎን የተካሄደ መሆኑን የገንዘብ ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል፡፡
አቶ አህመድ ሽዴ ጀርመን በኢትዮጵያ ለሚከናወኑ የልማት ስራዎች ለምታደርገው የገንዘብ እና የቴክኒክ ድጋፍ ምስጋና አቅርበዋል፡፡
በግጭት የተጎዱ አካባቢዎችን መልሶ ለመገንባት እና ለማቋቋም በሚደረገው ጥረት የጀርመን ድጋፍ አስፈላጊ መሆኑንም አጽንኦት ሰጥተዋል፡፡
ቢርጊት ፒከል በበኩላቸው÷ ጀርመን ለኢትዮጵያ የምታደርገውን ሁለንተናዊ ድጋፍ አጠናክራ እንደምትቀጥል አረጋግጠዋል፡፡ https://www.fanabc.com/archives/194673

👍31🤬3
ከ20 በላይ ኩባንያዎች ወደ ግል በሚዞሩ ስኳር ፋብሪካዎች ጨረታ ላይ ለመሳተፍ ፍላጎት አሳዩ
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 15፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ከ20 በላይ ኩባንያዎች ወደ ግል እንዲዛወሩ ጨረታ የወጣባቸውን የስኳር ፋብሪካዎች ለመግዛት ፍላጎት ማሳየታቸው ተገለፀ፡፡
በመንግስት ባለቤትነት የተያዙ 8 የስኳር ፋብሪካዎችን ወደ ግሉ ለማዞር መንግስት እ.ኤ.አ. ነሐሴ 2022 ዓለም አቀፍ ጨረታ ማውጣቱ ይታወሳል፡፡
በዚህም በመንግስት ወደ ግሉ ዘርፍ ለማዛወር የታሰቡት የስኳር ፋብሪካዎች አርጆ ዴዴሳ፣ ከሰም፣ ኦሞ ኩራዝ 1፣ ኦሞ ኩራዝ 2፣ ኦሞ ኩራዝ 3፣ ኦሞ ኩራዝ 5፣ ጣና በለስ እና ተንዳሆ ናቸው።
ይህን ተከትሎም https://www.fanabc.com/archives/194704

👍40❤9
ተቋማት ለገበታ ለትውልድ የሚያደርጉት ድጋፍ ተጠናክሮ ቀጥሏል
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 15፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የተለያዩ ተቋማት ለገበታ ለትውልድ ፕሮጀክት የሚያደርጉት የገንዘብ ድጋፍ ተጠናክሮ እንደቀጠለ ነው፡፡
የጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት በ15ኛው ዙር የገበታ ለትውልድ ፕሮጀክት ድጋፍ ያደረጉ ተቋማትና ድርጅቶችን ይፋ አድርጓል፡፡
በዚህ መሰረትም አቢሲኒያ ባንክ 161 ሚሊየን 700 ሺህ ብር እና ብሔራዊ የአልኮልና አረቄ ፋብሪካ 6 ሚሊየን ብር ድጋፍ አድርገዋል፡፡
በተጨማሪም የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት 5 ሚሊየን እና በኢትዮጵያ የሁዋዌ ቴክኖሎጂ ኩባንያ 5 ሚሊየን ብር ድጋፍ ማድረጋቸውን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽኅፈት ቤት መረጃ ያመላክታል፡፡

👍30👏15😁7❤6
አቶ ደመቀ መኮንን ከነገ ጀምሮ በቻይና ይፋዊ የስራ ጉብኝት ያደርጋሉ
አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 15 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ከነገ ጀምሮ በቻይና ይፋዊ የስራ ጉብኝት ያደርጋሉ።
አቶ ደመቀ በቻይና ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቺን ጋንግ በቀረበላቸው ግብዣ መሰረት ጉብኝቱን እንደሚያደርጉ የቻይና ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል።
በቆይታቸውም ከሀገሪቱ ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች ጋር እንደሚወያዩ ይጠበቃል።

👍82❤18👏6😁5🤔5🥰2
በዘመናዊው የአውሮፓ እግር ኳስ የዘረኝነት ጥቃት አሁንም እልባት አላገኘም
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 16፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በዘመናዊው የአውሮፓ እግር ኳስ በጥቁር ተጫዋቾች ላይ የሚደርሰው የዘረኝነት ጥቃት እስካሁን አልባት አለማግኘቱ ይነገራል፡፡
ለዚህም ማሳያ በአውሮፓ እግርኳስ በተለያዩ ጊዜያት በጥቁር ተጫዋቾች ላይ የሚሰነዘረው ጥቃት በእግርኳስ ህግጋቶችን አልፎ ዛሬም ድረስ ይስተዋላል፡፡
ከሰሞኑ በሪያል ማድሪዱ አጥቂ ቪኒሺየስ ጁኒየር ከቫሌንሲያ ደጋፊዎች የደረሰበት የዘረኝነት ጥቃት እና በዕለቱ የነበሩት ዋና ዳኛ እና የቫር ዳኞች ውሳኔ ዓለምን እያነጋገረ ይገኛል፡፡... https://www.fanabc.com/archives/194772

👍42😢11❤6😁3🥰2👏1🤔1
ኬኔዲ የተዘረፈውን ዶላር ለማስመለስ ሲጣጣር ለሞት የሚያበቃ ሁኔታ ውስጥ እራሱን ያገኘዋል፡፡ በሌላ በኩል ይትባረክ ከልጁ ጋር ሆኖ ልጁ መገኘት የሌለባት አስጨናቂና አስፈሪ ነገር ውስጥ ይገባል-
ሙሉ ቪዲዮውን ለመመልከት ሊንኩን ይጫኑ:-
👉 https://www.youtube.com/watch?v=0vE5iv2T5fg

YouTube
ሰኔ እና ሰኞ Sene ena Segno ምዕራፍ 1 ክፍል-3 Season 1 EP-3
#ሰኔ_እና_ሰኞ, #Sene_ena_Segno #ፋና #አዲስ_አበባ #Ethiopia #ኢትዮጵያ #fana_tv
ኬኔዲ የተዘረፈውን ዶላር ለማስመለስ ሲጣጣር ለሞት የሚያበቃ ሁኔታ ውስጥ እራሱን ያገኘዋል፡፡ በሌላ በኩል ይትባረክ ከልጁ ጋር ሆኖ ልጁ መገኘት የሌለባት አስጨናቂና አስፈሪ ነገር ውስጥ ይገባል

👍30😁6❤4
በአቶ ደመቀ መኮንን የተመራ ልዑክ ለይፋዊ የሥራ ጉብኝት ቤጂንግ ገባ
አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 16 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን የተመራ ልዑክ ለይፋዊ የሥራ ጉብኝት ቻይና ቤጂንግ ገባ።
ልዑኩ ቤጂንግ ሲደርስ በቻይና የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የስራ ሃላፊዎች፣ በቻይና የኢትዮጵያ ኤምባሲ ሰራተኞች እና በቻይና የዳይስፖራ ማህበረሰብ ተወካዮች አቀባበል ተደርጎለታል።
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን የቻይና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቺን ጋንግ በቻይና ጉብኝት እንዲያደርጉ ባቀረቡላቸው ግብዣ መሰረት ነው ዛሬ ቤጂንግ የገቡት።
አቶ ደመቀ በቆይታቸው ከቻይና የመንግስት የሥራ ሃላፊዎች ጋር ይወያያሉ ተብሎ ይጠበቃል።

👍66❤9😁4🤔4👏2
ዘጠኝ ኢትዮጵያውያን ተማሪዎች በ7ኛው የሁዋዌ ዓለም አቀፍ የአይ ሲ ቲ ፍጻሜ ውድድር ይሳተፋሉ
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 16፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ዘጠኝ የተለያዩ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ኢትዮጵያን ወክለው በ7ኛው የሁዋዌ ዓለም አቀፍ የኢንፎርሜሽን ኮሙኒኬሽን ቴክኖሎጅ (አይ ሲ ቲ) ፍጻሜ ውድድር ለመሳተፍ ቻይና ገብተዋል፡፡
ሁዋዌ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት በላከው መግለጫ ፥ ውድድሩ ከዛሬ ጀምሮ እስከ ግንቦት 20 ቀን 2015 ዓ.ም በቻይና ሼንዘን ከተማ ይካሄዳል፡፡
በዚህ ውድድር ላይ የሚሳተፉት ተማሪዎች የተለያዩ ሀገር አቀፍ እና አህጉር አቀፍ ውድድሮች ላይ ተሳትፈው በየደረጃው በአሸናፊነት ያጠናቀቁ መሆናቸው ታውቋል።
.... https://www.fanabc.com/archives/194821

👍24👏21❤8🥰4😱1
የአማርኛ ቋንቋ ትምህርት በሞስኮ ትምህርት ቤቶች ከመስከረም ጀምሮ ሊሰጥ ነው
አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 16 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በሞስኮ ትምህርት ቤቶች ከመስከረም ጀምሮ አማርኛ ቋንቋ ማስተማር ሊጀመር መሆኑ ተገለጸ፡፡
ጉዳዩን አስመልክቶ የስፑትኒክ አለም አቀፍ የዜና አገልግሎት ድርጅት እና ሬዲዮ÷ በሩሲያ - አፍሪካ የኢኮኖሚ ትብብር ተስፋዎች ዙሪያ ውይይት አካሂዷል።
ውይይቱ በአሌክሳንደር ጎርቻኮቭ ፐብሊክ ዲፕሎማሲ ፈንድ እና በሰብአዊ እርዳታ ማእከል ድጋፍ የተዘጋጀ ሲሆን÷ በሩሲያ እና በመካከለኛው ምስራቅና በአፍሪካ ሀገራት መካከል አዲስ የትብብር አድማስ” ለመፍጠር ያለመ የባለሙያዎች እና ትምህርታዊ ዝግጅት አካል መሆኑ ተጠቁሟል።
በውይይቱ ላይ ከሩሲያ እና አፍሪካ የተለያዩ ዩኒቨርስቲዎች የተውጣጡ የታሪክ ተመራማሪ ምሁራንና የሥራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል፡፡
የእስያ እና አፍሪካ ጥናት ኢንስቲትዩት ዳይሬክተር አሌክሲ ማስሎቭ ከፈረንጆቹ መስከረም 2023 ጀምሮ ቢያንስ አራት የሞስኮ ትምህርት ቤቶች ለህጻናት የአማርኛ እና የስዋሂሊ ቋንቋ ማስተማር እንደሚጀምሩ ይፋ አድርገዋል።
ማስሎቭ አክለውም በአዲሱ ልዩ መርሐ-ግብር በሞስኮ ትምህርት ቤቶች ዮሩባ ቋንቋን የሚያስተምሩበትን ዕድልም እየተመቻቸ መሆኑን ነው የገለፁት።
ወደ አፍሪካ በፍጥነት ፊትን ለማዞር ከኢኮኖሚው ጋር በቀጥታ ሊሰሩ የሚችሉ ፍጹም የተለዩ ባለሙያዎችን ማፍራት ያስፈልጋል ሲሉም ዳይሬክተሩ ተናግረዋል፡፡
አፍሪካ አንድ ትልቅ አህጉር ብቻ ሳትሆን የተለያዩ ቋንቋ፣ ባህል፣ ሃይማኖት እና ህብረ ብሔራዊ ማንነቶች ያሉባት አህጉር መሆኗን መገንዘብ ይገባል ብለዋል፡፡
https://www.fanabc.com/archives/194845

👍91❤32👏7😁4🥰3
ታዋቂዋ የፖፕ ሙዚቃ አቀንቃኟ ቲና ተርነር በ83 አመቷ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየች
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 16፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ታዋቂዋ የፖፕ ሙዚቃ አቀንቃኟ ቲና ተርነር ከዚህ ዓለም በሞት ተለየች።
በፈረንጆቹ በ1980ዎቹ የፖፕ አቀንቃኝ ለመሆን የበቃችው እውቋ የሮክ እና የሮል ኮከብ ቲና ተርነር ከረዥም ህመም በኋላ በ83 አመቷ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየች።
በቅርብ አመታት የጤና እክል አጋጥሟት የነበረችው ድምፃዊቷ በፈረንጆቹ 2016 የአንጀት ካንሰር እንዳለባት የታወቀ ሲሆን÷ በ2017 ደግሞ የኩላሊት ንቅለ ተከላ ማድረጓም ተገልጿል፡፡
ቲና ተርነር በሮክ እና ሮል የሙዚቃ ስልት የጥቁር ሴቶች ፈርጥ መሆኗን አስመስክራለች።
ከፍተኛ ኃይል እና ጉልበት የተሞላበት የቀጥታ ትርኢቶቿ በሙዚቃው ዓለም ትልቅ መነሳሳትን እንደፈጠሩ ይገለጻል ሲል ዘ ጋርዲያን ዘግቧል።
"ሪቨር ዲፕ፣ ማውንቴን ሃይ እና ፕራውድ ሜሪ" ታዋቂ ከሆኑት ዘፈኖቿ ተጠቃሾቹ ናቸው።

👍44😢10😁3❤1