Fana Media Corporation S.C (FMC) – Telegram
Fana Media Corporation S.C (FMC)
208K subscribers
76.6K photos
1.91K videos
23 files
62.6K links
This is FMC's official Telegram channel.

For more updates please visit
https://fanamc.com
Download Telegram
ተደራራቢ ግብርን ለማስቀረትና በታክስ ላይ የሚፈጸመውን ማጭበርበር ለመካለከል የቀረበው አዋጅ ጸደቀ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 22፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ተደራራቢ ግብርን ለማስቀረት እና በታክስ ላይ የሚፈጸመውን ማጭበርበር ለመከላከል የቀረበውን አዋጅ አጸደቀ፡፡

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 23ኛ መደበኛ ስብሰባውን በማካሄድ ላይ ይገኛል።

ምክር ቤቱ በኢትዮጵያ፣ስዊዘርላንድ እና በግራንድ ዱቺ ኦፍ ሉዘምበርግ መንግስት መካከል በገቢ ላይ የሚከፈለውን ግብር በሚመለከት በቀረበ ረቂቅ አዋጅ ዙሪያ መክሯል፡፡

በሀገራቱ መካከል ተደራራቢ ግብርን ለማስቀረት እና በታክስ ላይ የሚፈጸምን ማጭበርበር ለመከላከል የቀረበውን ረቂቅ አዋጅ አስመልክቶ የፕላን፣ በጀትና ፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ያቀረበውን ሪፖርትና የውሳኔ ሃሳብ መርምሮ አዋጁን አጽድቋል፡፡

ቋሚ ኮሚቴው ከገንዘብ ሚኒስቴር የሕግ አማካሪ በተለያዩ መድረኮች በረቂቅ አዋጁ አስፈላጊነት ላይ እንደተወያየም የምክር ቤቱ መረጃ ያመላክታል፡፡

የምክር ቤቱ አባላትም÷ረቂቅ አዋጁ በታክስ ማጭበርበር የሚታዩ ግድፈቶችን ለማረም የሚያስችል እና የሀገራቱን ግንኙነት የሚያጠናክር አዋጅ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
👍36😁42👏1🤬1
በሱዳን የተኩስ አቁም ሥምምነቱ ለተጨማሪ 5 ቀናት ተራዘመ

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 22 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የሱዳን ተፋላሚ ኃይሎች የተኩስ አቁም ሥምምነቱን ለተጨማሪ 5 ቀናት አራዘሙት፡፡

የሱዳን ጦር እና የሱዳን ፈጥኖ ደራሽ ሃይል አዲስ ስምምነት ላይ የደረሱት በፈረንጆቹ ግንቦት 20 ቀን 2023 በሳዑዲ አረቢያ መዲና ጅዳ ከመከሩ በኋላ መሆኑን ሺንዋ አል-አረቢያን ዋቢ አድርጎ ዘግቧል፡፡

ሁለቱ ኃይሎች ሠላማዊ ዜጎች ከጦርነት ቀጣናው ለመውጣት የሚያደርጉትን ጥረት መንገድ በመክፈት ለማሳለጥ ሥምምነት ላይ መድረሳቸውም ነው የተመላከተው፡፡... https://www.fanabc.com/archives/195398
👍194😱1
በሞስኮ ከተማ የድሮን ጥቃት መሰንዘሩ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 22፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በሩሲያ ርዕሰ መዲና ሞስኮ ከተማ የድሮን ጥቃት መሰንዘሩን የከተማዋ ከንቲባ ሰርጌ ሶቢያኒን ተናገሩ፡፡

ዛሬ ማለዳ ድሮኖች በሩሲያ ዋና ከተማ ጥቃት በመፈፀም በሕንፃዎች ላይ ጉዳት ማድረሳቸውን ነው ከንቲባው የተናገሩት።

ሶቢያኒን ነዋሪዎች ኢላማ ከተደረጉ ሁለት አፓርታማዎች እንዲወጡ ማዘዛቸው ተገልጿል።

ከንቲባው ከከተማው የህክምና አገልግሎት የተገኘን መረጃ በመጥቀስ በድሮን በተመታ ህንጻ ውስጥ ምንም አይነት ነዋሪ ላይ ከባድ ጉዳት እንዳልደረሰ ገልፀዋል።... https://www.fanabc.com/archives/195402
👍4510😁5😱3
የብልፅግና ፓርቲ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ መደበኛ ስብሰባውን ማካሄድ ጀመረ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 22፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የብልፅግና ፓርቲ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ መደበኛ ስብሰባውን ማካሄድ ጀምሯል።

ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴው ውይይቱን የጀመረው በቅርቡ በአሳዛኝ ሁኔታ ህይወታቸውን ላጡት ለፓርቲው ስራ አስፈፃሚ አባል ለአቶ ግርማ የሺጥላ የሕሊና ፀሎት በማድረግ ነው።

ኮሚቴው በሚኖረው ቆይታ በሀገራዊ እንዲሁም በፓርቲያዊ ጉዳዮች ላይ ጥልቅ ውይይት በማካሄድ ውሳኔዎችንና ቀጣይ አቅጣጫዎችን ያስቀምጣል ተብሎ ይጠበቃል።

ለውይይት በተዘጋጁ ሰነዶች ላይ የጋራ ግምገማ በማድረግም መላውን ህዝብ በማሳተፍ የሚሳኩ የብልፅግና ጉዞ ትልሞች ላይ እንደሚመክር ከፓርቲው ፅህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።... https://www.fanabc.com/archives/195405
👍44😁1412💩5🥰3🤔2🤬2🤩2
በሐዋሳ ከወ/ሪት ፅጌ መጠለፍ ጋር በተያያዘ 6 ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 22፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ሰሞኑን በሐዋሳ ከተማ ወ/ሪት ፅጌ በላቸው የተባለች ወጣት በአንድ ግለሰብ የመጠለፏ ጉዳይ የማህበራዊ ሚዲያዎች አጀንዳ ሆኖ ቆይቷል።

የከተማዋ ፖሊስ በጉዳዩ ላይ ዛሬ መግለጫ ያወጣ ሲሆን ፥ ከጠለፋ ወንጀሉ ጋር የተጠረጠሩ 6 ሰዎች በቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ እየተደረገ መሆኑን ነው ያስታወቀው።

የወንጀሉ ድሪጊት የተፈፀመው በሐዋሳ ከተማ በመናኸሪያ ክ/ከተማ መሆኑን የከተማው ፖሊስ ገልጿል፡፡

በዚህም ወ/ሪት ፅጌ በላቸው የተባለች ግለሰብ በቀን 15/9/2015 ዓ.ም ቤተሰቦቿ ተጠልፋ የት እንደደረሰች አናውቅም በማለት ለመነኸሪያ ክ/ከተማ ፖሊስ ባቀረቡት ማመልከቻ መሰረት ምርመራ መጀመሩ ተገልጿል።... https://www.fanabc.com/archives/195413
👍60😁10🤔3😱31
ማይክ ሐመር በኢትዮጵያ ይፋዊ የሥራ ጉብኝት ሊያደርጉ ነው

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 22 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በአፍሪካ ቀንድ የአሜሪካ ልዩ መልዕክተኛ ማይክ ሐመር በኢትዮጵያ እና ጅቡቲ ይፋዊ የሥራ ጉብኝት ሊያደርጉ ነው።
የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት እንዳስታወቀው ልዩ መልዕክተኛው እስከ መጭው ማክሰኞ በኢትዮጵያ እና ጅቡቲ ጉብኝት ያደርጋሉ።

በኢትዮጵያ በሚኖራቸው ቆይታም ከመንግስት ከፍተኛ የሥራ ሃላፊዎች ጋር በተደረሰው የሰላም ስምምነት አተገባበር ላይ ይመክራሉ ተብሎ ይጠበቃል።

የሽግግር ፍትህና ተጠያቂነትን የማስፈን ሂደትን እንዲሁም የትጥቅ ማስፈታት እና የመልሶ ማቋቋም ሂደቶችን ጨምሮ በሰላም ስምምነቱ በታዩ መሻሻሎች እና ቅድሚያ በሚሰጣቸው ጉዳዮች ላይ እንደሚወያዩም ሚኒስቴሩ አስታውቋል።

ውይይቱ ከመንግስት የሥራ ሃላፊዎች እና ከትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ጋር የሚካሄድ መሆኑም ነው የተገለጸው።

በጅቡቲ ቆይታቸውም በአፍሪካ የአሜሪካ ወታደራዊ ዕዝ እና የምስራቅ አፍሪካ የተቀናጀ የጋራ ግብረ ኃይል በጋራ በሚያስተናግዱት የምስራቅ አፍሪካ የደህንነት ፎረም ላይ ይካፈላሉ ተብሏል።

በተጨማሪም ከጅቡቲ ከፍተኛ የሥራ ሃላፊዎች ጋር በሁለትዮሽ ትብብር እና ቀጣናዊ ጉዳዮች ላይ እንደሚመክሩም ነው የተገለጸው።

ከዚህ ባለፈም ከምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት (ኢጋድ) ዋና ፀሃፊ ወርቅነህ ገበየሁ (ዶ/ር) ጋር ኢጋድ በሚያከናውናቸው ተግባራት ዙሪያም ይወያያሉ ነው የተባለው።
👍425🤔4🤬4💩4😁2🎉1
አየር መንገዱ የኢ-ኮሜርስ ሎጀስቲክስ አገልግሎት ሊጀምር ነው

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 22፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ አየር መንገድ የዕቃ ጭነት እና ሎጀስቲክስ አገልግሎት ዓለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ የኢ-ኮሜርስ ሎጀስቲክስ አገልግሎት ሊጀምር መሆኑን አስታወቀ፡፡

አየር መንገዱ የአፍሪካን የኢ-ኮሜርስ ንግድ ወደ ላቀ ደረጃ ለማድረስ የመጨረሻ ምዕራፍ ላይ መድረሱንም በመረጃው አስታውቋል፡፡ https://www.fanabc.com/archives/195462
👍326😁2
"የፒያኖዋ እመቤት" ን የሚዘክር መርሐግብር ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 22፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) "የፒያኖዋ እመቤት" እማሆይ ፅጌማርያም ገብሩ ለኢትዮጵያ ዘመናዊ ሙዚቃ ያበረከቱትን አስተዋጽኦ የሚዘክር መርሐግብር ተካሂዷል፡፡

መርሐግብሩ በእንጦጦ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የተካሄደ ሲሆን ፥ ለዘርፉ ያደረጉትን አበርክቶ በማስመልከት የኮሌጁ የሙዚቃ ትምህርት ክፍል በስማቸው ተሠይሟል።

በመርሐግብሩ የጥንታዊት ኢትዮጵያ ጀግኖች አርበኞች ማኅበር ፕሬዚዳንት ልጅ ዳንኤል ጆቴ መስፍን፣ የቀድሞ ተፈሪ መኮንን ትምህርት ቤት ተማሪዎች ሰብሳቢ አርቲስት ደበበ እሸቱ እንዲሁም አንጋፋና ወጣት የኪነጥበብ ባለሙያዎች ተገኝተዋል።... https://www.fanabc.com/archives/195490
👍3410😁2👏1
በሽብር ወንጀል በተጠረጠሩ 38 ግለሰቦች ላይ ተጨማሪ ምርመራ እንዲደረግ ለፖሊስ የ14 ቀን ጊዜ ተፈቀደ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 22፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ፍርድ ቤቱ በሽብር ወንጀል በተጠረጠሩ በ 38 ግለሰቦች ላይ ተጨማሪ የማጣሪያ ምርመራ እንዲደረግ ለፖሊስ የ14 ቀን ጊዜ ፈቀደ፡፡

የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 1ኛ ጊዜ ቀጠሮ ችሎት በ3 መዝገብ የቀረቡ የ38 ተጠርጣሪዎችን ጉዳይ ተመልክቷል።

ተጠርጣሪዎቹን ፍርድ ቤት ያቀረበው የፌደራል ፖሊስ መርማሪ በቀዳሚነት በነመላክ ምሳሌ መንግስቱ መዝገብ የተካተቱ 16 ግለሰቦችን እና በነደበበ በሻህ ውረድ መዝገብ የተካተቱ በ12 ተጠርጣሪዎች አጠቃላይ 26 ግለሰቦች ላይ የሽብር ወንጀል የጥርጣሬ መነሻውን በፅሁፍም በቃልም አቅርቧል። ... https://www.fanabc.com/archives/195505
👍59😁1312🤬4😢4🤔3
ማስታወቂያ!
አቶ ደመቀ መኮንን በቻይና ያደረጉት ጉብኝት የሁለቱን አገራት ትብብር ወደ ላቀ ደረጃ ያሸጋገረ ነው - የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 23፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን በቻይና ያደረጉት ጉብኝት የሁለቱን አገራት ትብብርና ወዳጅነት ወደ ላቀ ደረጃ ያሸጋገረ መሆኑን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ገለፀ።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር መለስ ዓለም ዛሬ በሰጡት ሳምንታዊ መግለጫ÷የአቶ ደመቀ መኮንን የአምስት ቀናት የቻይና ጉብኝት ውጤታማ መሆኑን ገልፀዋል።

አምባሳደር መለስ ዓለም÷ በጉብኝቱ ቻይና የኢትዮጵያ ሁነኛ አጋር አገር እንደሆነች እና በቀጣይም በፖለቲካና ዲፕሎማሲ መስኮች የተሻለ ወዳጅነት ለመመስረት የሚያስችል መግባባት ላይ መደረሱን ገልፀዋል።

ከአገሪቱ ምክትል ፕሬዚዳንት፣ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር፣ ከጉዋንዱንግ ግዛት አስተዳደሮች ከጉዋንዡ ከተማ ከንቲባ ጋር ጥሩ ውይይት መካሄዱንም አንስተዋል።https://www.fanabc.com/archives/195524
👍43😁5👏43💩3🥰2
ዓለም አቀፉ የአቶሚክ ኃይል ኤጀንሲ የዛፓሮዢያ የኒውክሌር ኃይል ማመንጫ ደኅንነት ያሳስበኛል አለ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 23፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ዓለም አቀፉ የአቶሚክ ኃይል ኤጀንሲ የዛፓሮዢያ የኒውክሌር ኃይል ማመንጫ ደኅንነት እንደሚያሳስበው አስታወቀ፡፡

የዓለም አቀፉ የአቶሚክ ኃይል ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር ራፋዔል ማሪያኖ ግሮሲ ለተመዱ የደኅንነት ምክር ቤት እንደገለጹት ÷ የኒውክሌር ኃይል ማመንጫው ሩሲያና ዩክሬን በሚፋለሙበት ግንባር አቅራቢያ መገኘቱ የደኅንነቱን ሁኔታ ይበልጥ አሳሳቢ ያደርገዋል፡፡

አሁን ባለው ሁኔታ በአካባቢው ወታደራዊ እንቅስቃሴዎች እየጨመሩ እንጂ እየቀነሱ አለመሆኑንም አስገንዝበዋል።

ማሪያኖ ግሮሲ ÷ “እስካሁን የኒውክሌር አደጋ ባለመከሰቱ ዕድለኞች ነን ፤ በአካባቢው ያለው ሁኔታ በዚሁ ከቀጠለ ግን አንድ ቀን ዕድላችን ያበቃል” ሲሉም ነው የሁኔታውን አሳሳቢነት የገለጹት።https://www.fanabc.com/archives/195518
👍226🥰1
የኦሮሚያ ክልል ሰላምን ለማረጋገጥ ከሃይማኖት ተቋማት ጋር በቅንጅት እየሰራ መሆኑን ገለጸ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 23፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኦሮሚያ ክልል መንግስት ሰላምን ለማረጋገጥ ከሃይማኖት ተቋማት ጋር በቅንጅት እየሰራ መሆኑን አስታውቋል፡፡

የክልሉ መንግስት ኮሙዩኒኬሽን ቢሮ ሃላፊ ሃይሉ አዱኛ በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ በሰጡት መግለጫ÷ኢትዮጵያ የተለያዩ እምነት ተከታይ ዜጎች ተከባብረው የሚኖሩባት ሀገር መሆኗን አንስተዋል፡፡

የክልሉ መንግስትም በሃይማኖት እኩልነት የሚያምን እና እውቅና የሚሰጥ መሆኑን ነው ሃላፊው የገለጹት፡፡

የሕገ-ወጥ ቤቶች ፈረሳ ሒደት መስጅድ ላይ ያተኮረ አለመሆኑን ጠቁመው ÷በክልሉ 600 በሚሆኑ ከተሞች የህገ ወጥ ቤቶች ፈረሳ ሒደት እንደሚከናወን ተናግረዋል፡፡

ሕግ የማስከበር ስራውም በዋናነት ህገ ወጥነትን በዘላቂነት ለመከላከል ያለመ ነው ሲሉ አጽንኦት ሰጥተዋል፡፡

በቀጣይም የክልሉ መንግስት በሃይማኖት ጉዳዮች ላይ ከሃይማኖትተቋማት ጋር በቅንጅት እንደሚሰራ ማረጋገጣቸውን የክልሉ ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡

የሃይማኖት ተቋማት እና የእምነቱ ተከታዮችም እምነትን ተገን አድርገው ሁከት እና ብጥብጥ ለመፍጠር የሚሞክሩ አካላትን በጋር እንዲከላከሉ ጥሪ አቅርበዋል፡፡
😁53👍31💩247🤬6👏2😱2🤔1🤩1
የፍጻሜ ውድድሩ የፊታችን ቅዳሜ ከቀኑ 6፡00 ጀምሮ የሚካሄድ ሲሆን አሸናፊዎች በድምሩ የ1,000,000 ብር ተሸላሚ ይሆናሉ፡፡
ይህን አጓጊ ውድድር በቀጥታ ለመከታተል የፋናን የዩቱዩብ ቻናል
👉https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ! https://www.youtube.com/watch?v=WoVDbXfGPo4
👍16🥰1
በሰሞኑ ዝናብ ቦረና ላይ በስፋት የእንስሳት መኖ እና ሰሊጥ ተመርቷል -ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 23፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በሰሞኑ ዝናብ ቦረና ላይ በስፋት የእንስሳት መኖ እና ሰሊጥ ተመርቷል ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ገለጹ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ባሰፈሩት ጽሑፍ÷ ዓመት ባልሞላ ጊዜ ከድርቅ ወደ አምራችነት መቀየሩ ተስፋ ሰጪ ነው ብለዋል።

ውኃን በማቆርና በመቆጠብ ብልሐት ከተጠቀምን የችግርን ጊዜ ሳንቸገርበት እናልፈዋለን ሲሉም አስገንዝበዋል።
👍82💩2219😁19🤬7👏3😱3🤩3