Addis Standard Amharic – Telegram
Addis Standard Amharic
18K subscribers
4.75K photos
123 videos
3 files
3.78K links
አዲስ ስታንዳርድ በጃኬን አሳታሚ ኃ.የተ.የግ.ማ. ባለቤትነት ስር የሚታተም በኢትዮጵያ የሚገኝ ነፃ እና ገለልተኛ ሚዲያ ነው። አዲስ ስታንዳርድ አማርኛ የአዲስ ስታንዳርድ እንግሊዝኛ ሕትመት አካል ነው።
ፌስቡክ: https://rb.gy/xwxb3
ትዊተር (X)፡ https://rb.gy/34uh4
Download Telegram
ዜና፡ በደቡብ ምዕራብ ሸዋ ዞን የሰደን ሶዶ ወረዳ አስተዳዳሪ በታጣቂዎች ተገደሉ

#ኦሮሚያ ክልል የደቡብ ምዕራብ ሸዋ ዞን ሰደን ሶዶ ወረዳ አስተዳዳሪ አቶ በቀለ ቀጫ ማክሰኞ ሰኔ 13 2015 ዓ.ም በታጣቂዎች መገደላቸውን የወረዳው ኮሚኒኬሽን አስታወቀ፡፡

የደቡብ ምዕራብ ሸዋ ኮሚኒኬሽን የሰዴን ሶዶ ገለፃ አቶ አስታዳሪው የተደገሉት በአዳማ ከተማ ስብሰባ ተሳትፈው ከተመለሱ በኋላ እሁድ ማታ 3፡00 አካባቢ ማንነታቸው ባልታወቀ ሰዎች ኢሉ ወረዳ አስጎሪ ከተማ ከሚገኘው ቤታቸው ተወስደው ማክሰኞ እለት ተገለዋል ሲል ገልጧል፡፡

ለማንበብ፡ https://rb.gy/67h8f
ዜና፡ በ ሰሜን ሸዋ መጤ ተምች በሰብል ላይ ጉዳት እያደረሰ ነው ተባለ

#አማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን የአፍሪካ እና አሜሪካ መጤ ተምች ጉዳት እያደረሰ መሆኑን የዞኑ ግብርና መምሪያ አስታወቀ፡፡

በዞኑ አራት ወረዳዎች 27 ቀበሌዎች ላይ የተከሰተው የአፍሪካ ተምች ከ 5 ሺህ ሄክታር ሰብል በላይ ጉዳት ማድረሱን የመምሪያው የሰብል ልማት ቡድን መሪ አበበ ጌታቸው ጠቁመዋል፡፡ ተምቹ በማሽላ፣ በቆሎና ጤፍ ላይ ጉዳት እንደሚያደርስም ነው አቶ አበበ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት የገለጹት፡፡

እስካሁን ኬሚካልና ባህላዊ መንገድን በመጠቀም በ3 ሺህ 300 ሄክታር ላይ እየለማ ያለን ሰብል ማዳን ስለመቻሉም አስረድተዋል፡፡ እንዲሁም በስድስት ወረዳዎች ላይ የተከሰተው የአሜሪካ መጤ ተምች በ 5 ሺህ 300 ሄክታር በለማ ሰብል ላይ ጉዳት ማድረሱን አረጋግጠዋል፡፡

እስካሁንም በ2 ሺህ 800 ሄክታር ላይ የለማውን ሰብል መከላከል ተችሏል ነው ያሉት፡፡
በዞኑ የተከሰተውን የአፍሪካ ተምች ለመከላከል ኬሚካል እየቀረበ መሆኑን ገልጸው÷ የአሜሪካ ተምቹ ከፍተኛ ጉዳት እያደረሰ መሆኑን እና መከላከያ ኬሚካል እየቀረበ አለመሆኑን አንስተዋል፡፡

አርሶ አደሩ በባህላዊ መንገድ እንዲከላከልም ጥሪ አቅርበዋል፡፡ የአማራ ክልል ግብርና ቢሮ በምስራቅ አማራ በሚገኙ ዞኖች ተምች መከሰቱን አረጋግጦ÷ በክልሉ ለተከሰተው ተምች መከላከያ በቂ ኬሚካል በኮምቦልቻ ከተማ መቅረቡንና ግብርና መምሪያዎች መጠቀም ይችላሉ ብሏል፡፡

ኤፍ ቢ ሲ
ዜና፡ #የአሜሪካ ኤምባሲ #ዲፕሎማቶች በደቡብ ትግራይ ያካሄዱትን ጉብኝት አቶ #ጌታቸው ረዳ አወገዙ

የትግራይ ክልል ግዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ የአሜሪካን ኤምባሲ ዲፕሎማቶች በደቡብ #ራያ #አላማጣ ከተማ ያካሄዱትን ጉብኝት አወገዙ።
የአሜሪካን ኤምባሲ የዲፕሎማቶቹን ጉብኝት አስመልክቶ የሰጠው ይፋዊ ማብራሪያ የለም። በርካታ የትግራይ ተወላጆች የዲፕሎማቶቹን ጉብኝት በመቃወም በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው አስተያየታቸውን አስፍረዋል።

ጉዳዩን በተመለከተ የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ በማህበራዊ ሚዲያ የትዊተር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሁፍ “የአማራ ኃይሎች በሕገወጥ መንገድ በኃይል የያዙትን አካባቢ ዲፕሎማቶቹ መጎብኘታቸው የትግራይ ግዛቶች በጽንፈኛ ኃይሎች የኃይል ቁጥጥር ስር መኾኑን እንደመቀበል ይቆጠራል ብለዋል። ዲፕሎማቶቹ የአካባቢዎቹ ሕገወጥ አስተዳደር ባላሥልጣናት ባቀነባበሩት ድራማ ለምን እንደተሳተፉ ግልጽ አይደለም ሲሉ ገልጸው ድርጊቱ አሜሪካ ለፕሪቶሪያው ግጭት ማቆም ስምምነት ያላትን ቁርጠኝነት የሚጻረርና ተቀባይነት የሌለው ነው” ብለዋል።

በክልሉ የሚንቀሳቀሰው #ሳልሳይ ወያነ ፓርቲ የውጭ ግንኙነት ክፍል ሃላፊ #ሀይሉ ከበደ በበኩላቸው የዘር ማጽዳት ተግባር በፈጸሙና አከባቢውን በጉልበት በተቆጣጠሩ ሃይሎች ግብዣ በአከባቢው የሚደረግ ማንኛውም ይፋዊ ጉብኝት ተቀባይነት የለውም፣ አደገኛ ተግባርም ነው ሲሉ ገልጸዋል።
https://rb.gy/q8k9b
ዜና፡ #በኢትዮጵያ #በኮሌራ ወረርሽኝ ሳቢያ የሞቱ ሰዎች ቁጥር 156 መድረሱ ተገለጸ

በኢትዮጵያ ከባለፈው አመት ነሃሴ ወር ጀምሮ የተከሰተው የኮሌራ ወረርሺኝ 156 ሰዎችን መግደሉን #የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ያወጣው ሪፖርት አመላከተ።

ከሚያዚያ 29 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ 85 በመቶ የሚሆን ተጨማሪ በወረርሽኙ መያዛቸው የተረጋገጠ በሽተኞች መገኘታቸውን ሪፖርቱ አካቷል። በኮሌራ የተያዙ ከ11 ሺ በላይ ሰዎች መኖራቸውን አስታውቋል።

በአሁኑ ወቅት በኢትዮጵያ የተከሰተው የኮሌራ ወረርሽኝ እስካሁን #በምስራቅ አፍሪካ ከተከሰቱ ወረርሽኞች ብዙ ግዜን ያስቆጠረ ነው ሲል ተመድ በሪፖርቱ ገልጿል።
ቀጣይ ወራቶች ዝና የሚስተናገድባቸው በመሆናቸው ጎርፍ ሊከሰት እንደሚችል እና ይህም የኮሌራ ወረርሽኝ እንዲስፋፋ የማድረግ እድሉ ሰፊ መሆኑን ጠቁሟል።

በአፍ የሚወሰድ የኮሌራ ክትባት ውስን አቅርቦት መኖር፣ በቂ የውሃ አቅርቦት አለመኖር የአካባቢ ጽዳትና የግል ንፅህና አጠባበቅ እንዳይኖር ማድረጉ ሰባት ነጥብ ሰባት ሚሊየን የሚሆኑ ወረርሽኙ በተከሰተባቸው አከባቢ የሚኖሩ ሰዎችን ለአደጋ እንዲጋለጡ ማድረጉን ተመድ በሪፖርቱ አስታውቋል።

https://rb.gy/dmmuw
ቃለ ምልልስ፡ “በ #ኢዜማ ጉዳይ ላይ #ብልፅግና ገብቶ ከፋፍሏል ብዬ አላምንም ምክንያቱም ኢዜማን እንደገደለው ያውቃል”- አቶ ሀብታሙ ኪታባ የቀድሞ የኢዜማ ስራ አስፈፃሚ አባል

አቶ ሀብታሙ ኪታባ የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትህ (ኢዜማ) ፓርቲ ከመስራች ኮሚቴ አንዱ ሲሆኑ በስራ አስፈፃሚነትም አገልግለዋል፡፡ በአዲስ አበባ በምርጫ ክልላቸውም ስራ አስፈፃሚ ሆነው ሰርተዋል፡፡ በተጨማሪም ለኢዜማ መሪነት በተደረገ ምርጫ ውድድር ላይ #አንዷለም አራጌ ለመሪነት ሲወዳደሩ አቶ ሀብታሙ ለምክትል መሪነት ተወዳድረዋል፡፡

አቶ ሀብታሙ ኪታባ በቅርቡ ከኢዜማ ፓርቲ ከለቀቁ ሰባት ስራ አስፈፃሚ አባላት መካከል አንዱ ናቸው፡፡ ከኢዜማ በጋራ ከመልቀቃቸው ጋር ተያይዞ ከአዲስ ስታንዳርዱ ጋዜጠኛ #ብሩክ_አለሙ ጋር ያደረጉት ሙሉ ቃለ መልልስ እንደሚከተለው ቀርቧል፡፡

በኢዜማ ጉዳይ ላይ ብልፅግና ገብቶ ከፋፍሏል ብዬ አላምንም ምክንያቱም ኢዜማን እንደገደለው ያውቃል፡፡ ገዢው ፓርቲ መሪዎችን አቅርቦ ስርዓቱን በመምታት ማዳከም ላይ ሚና አለው እንጂ በኢዜማ ጉዳይ ላይ እጁን አስገብቷል የሚል ንባብ ግን የለኝም፡፡

ኢዜማ ገዢውን ፓርቲ በተለየ ሁኔታ ማጠናከር የሚችልበት አቅም የለውም፤ በተለየ ሁኔታም ታግሎ መቀየር የሚችልበት አቅም የለውም፤ አቅሙን ጨርሷል ብዬ ነው የማምነው፡፡

ሙሉ ቃለ ምልልሱን ለማንበብ፡ https://amharic.addisstandard.com/%e1%89%83%e1%88%88-%e1%88%9d%e1%88%8d%e1%88%8d%e1%88%b5%e1%8d%a1-%e1%89%a0%e1%8a%a2%e1%8b%9c%e1%88%9b-%e1%8c%89%e1%8b%b3%e1%8b%ad-%e1%88%8b%e1%8b%ad-%e1%89%a5%e1%88%8d%e1%8d%85%e1%8c%8d/
ዜና፡ ዶ/ር #አብይ እና #አልሲሲ #በፓሪስ ተገናኝተው ደማቅ ፈገግታ የተሞላበት ሰላምታ መለዋወጣቸው በግብጻውያን ዘንድ መነጋገሪያ ሁኗል

የኢትዮጵያ ጠ/ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ እና #የግብጹ ፕሬዝዳንት አብዱል ፈታህ አልሲሲ በፓሪሱ #የፋይናንስ ስብሰባ ተገናኝተው በመጨባበጥ ሰላምታ መለዋወጣቸው እና ፈገግታን መለዋወጣቸው የግብጽ መገናኛ ብዙሃን ሰፊ ሽፋን ሰጥተውታል።
ለሚዲያዎቹ ትኩረት ዋነኛ ምክንያቱ ኢትዮጵያ እና ግብጽ በህዳሴ ግድብ ሳቢያ ፍጥጫ ላይ ሁነው እያለ የሁለቱ መሪዎች በፈገግታ የተሞላ ሰላምታ መለዋወጣቸው ነው ሲል ሚድልኢስት ሞኒተር በድረገጹ ባስነበበው ዘገባ አስታውቋል።

አልአረቢ የአረብኛ ድረገጽ በጉዳዩ ዙሪያ ባስነበበው ሰፋ ያለ የአረብኛ ዘገባ እንዳመለከተው በግብጽ የሚገኙ ታላላቅ መገናኛ ብዙሃን የሁለቱን መሪዎች በፈገግታ የተሞላበት ሰላምታ በማህበራዊ ሚዲያዎቻቸው ሽፋን ከሰጡ በኋላ እንዲነሳ መደረጉን አስታውቋል።

#አልአረቢ በድረገጹ ባስነበበው ዘገባ #ካይሮ ኒውስ ቻናል፣ #ኤክስትራ ኒውስ እና #ካይሮ24 የተሰኙ ታላላቅ መገናኛ ብዙሃን የሁለቱን መሪዎች ምስል በልዩ ዘገባነት በማህበራዊ ሚዲያዎቻቸው አሰራጭተው የነበረ ቢሆንም ወዲያውኑ እንዲነሳ መደረጉን የውስጥ ምንጮቹን ዋቢ በማድረግ አስታውቋል።

በግብጽ የማህበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎች ዘንድ ጉዳዩ መነጋገሪያ መሆኑን ያስታወቀው የለንደኑ አልአረቢ ድረገጽ በሁለት ጎራ እሰጣገባ ማስተናገዱን አመላክቷል።

https://rb.gy/vabjm
ዜና፡ #ሩሲያ #ኢትዮጵያን ጨምሮ ለአራት የአፈሪካ ሀገራት የ10 ሚሊየን ዶላር እርዳታ ለገሰች

ሩሲያ ኢትዮጵያን ጨምሮ ለአራት የአፈሪካ ሀገራት የ10 ሚሊየን ዶላር እርዳታ በአለም #የምግብ ፕሮግራም በኩል እንደምትልክ አስታወቀች።

#ቡርኪናፋሶ#ማዕከላዊ አፍሪካ ሪፐብሊክ፣ ዲሞክራቲክ #ኮንጎ እና ኢትዮጰያ እያንዳንዳቸው ሁለት ነጥብ አምስት ሚሊየን ዶላር እንደሚደርሳቸው በአዲስ አበባ የሚገኘው የሩሲያ ኤምባሲ በማህበራዊ ትስስር የፌስቡክ ገጹ ባወጣው ጋዜጣዊ መግለጫ አስታውቋል።

የሩሲያ መንግስት በለገሰው ገንዘብ ሀገራቱ በሩሲያ ከሚገኙ ኩባንያዎች እርዳታውን እንዲገዙ እንደሚደረገ መግለጫው አመላክቷል።

ለአራቱ የአፍሪካ ሀገራት የተደረገው የሩሲያ ልገሳ በአህጉሩ ያላትን ቦታ ያሳያል ሲል መግለጫው ጠቁሟል።
https://rb.gy/9qy6s
ዜና፡ በሕገወጥ የወርቅ ምርትና ግብይት ተሳትፎ ነበራቸው የተባሉ 32 የመንግሥት ኃላፊዎችና የጸጥታ አመራሮች በቁጥጥር ስር ዋሉ

በሕገወጥ የወርቅ ምርት፣ ግብይትና ዝውውር ተሳትፎ ነበራቸው የተባሉ 32 የመንግሥት ኃላፊዎች፣ የጸጥታ መዋቅር አመራሮችና አምራቾች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት አስታወቀ፡፡

በቁጥጥር ስር ከዋሉት 32 ግለሰቦች መካከል ስምንቱ የመንግሥትና የጸጥታ መዋቅር አመራሮች ሲሆኑ፤ ሰባቱ ደግሞ ሕጋዊ ፈቃድን ሽፋን አድርገው በሕገወጥ መንገድ ሲሠሩ የነበሩ አምራቾች እንዲሁም 17 አዘዋዋሪዎችና በሕገወጥ ድርጊቱ የተለያየ ተሳትፎ ያላቸው መሆናቸው ተገልጿል፡፡

በዚህ መሰረትም ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የኩምሩክ ወረዳ ገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ፅ/ቤት ኃላፊ ከማል መሀመድ፣ የግብርና ፅ/ቤት ኃላፊ አብዱልከሪም ዬሚዳ፣ የወረዳው ፖሊስ አመራር ም/ኮ አብዱልሙንየም ሱሌማን እንዲሁም ምክትል አስተዳዳሪ የነበረው አሳይድ አልዕግብ በቁጥጥር ውለዋል፡፡

https://amharic.addisstandard.com/ዜና፡-በሕገወጥ-የወርቅ-ምርትና-ግብይት-ተ/
ዜና፡የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ብርቱካን ሚደቅሳ ከሥራ መልቀቃቸውን አስታወቁ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ዋና ሰብሳቢ ብርቱካን ሚደቅሳ ሥራቸውን በፈቃዳቸው መልቀቃቸውን በይፋ አስታውቁ፡፡

የምርጫ ቦርድ ዋና ሰብሳቢ ብርቱካን ሚደቅሳ ጤናዬን በሚገባ ለመጠበቅ የረጅም ጊዜ እረፍት የሚያስፈልገኝ ሆኖ በመገኘቱ ከ ነሀሴ 1 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ቦርድ ሰብሳቢነቴ በገዛ ፍቃዴ መልቀቄን ለተወካዮች ምክር ቤት አፈጉባኤ ጽህፈት ቤት ሰኔ 5 ቀን 2015 ዓ.ም አሳውቄያለሁ ሲሉ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው አስታውቀዋል።

ሰብሳቢዋ በሚቀራቸው ጊዜም ያልተጠናቀቁ ሥራዎችን የማጠናቀቅ እና አስተዳደራዊ ሽግግር ሥራዎችን ለመሥራት ኃላፊነታቸውን እንደሚወጡም አስታውቀዋል፡፡


https://amharic.addisstandard.com/ዜና፡የኢትዮጵያ-ብሔራዊ-ምርጫ-ቦርድ-ሰብ/
ዜና፡ ጋዜጠኛ #ተመስገን_ደሳለኝ በፌዴራል ፖሊስ አባላት ዛሬ ጠዋት ከመኖሪያ ቤቱ ተወሰደ
“ፍትሕ” መጽሔት መስራች እና ማኔጂንግ ዳይሬክተር ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ በፌዴራል ፖሊስ አባላት ዛሬ ጠዋት ከመኖሪያ ቤቱ መወሰዱን ወንድሙ ታሪኩ ደሳለኝ ለአዲስ ስታንዳርድ ገለፀ፡፡
የፌዴራል ደምብ ልብስ የለበሱ እና ሲቪል የለበሱ በሁለት ፓትሮል የታጀቡ የፀጥታ አካላት ጠዋት 12፡ 30 ላይ ወደ መኖሪያ ቤቱ በማምራት ተመስገን ደሳለኝን በቁጥጥር ስር ማዋላቸውን የገለፀው ወንድሙ ወዴት እንደተወሰደም የሚያውቁት ነገር አለመኖሩን ተናግሯል፡፡
https://rb.gy/tye7p
ዜና፡ #በኢትዮጵያ ድንበር አቅራቢያ #በሱዳን ጦር ሰራዊት እና አማጽያን መካከል ውጊያ መካሄዱ ተገለጸ

በኢትዮጵያ ድንበር አቅራቢያ በምትገኘው #የብሉናይል ግዛት #ኩርሙክ ከተማ በሱዳን ጦር ሰራዊት እና በአከባቢው በሚንቀሳቀሰው የሱዳን ህዝቦች ነጻ አውጪ ንቅናቄ ሰሜን በተሰኘ አማጺ ቡድን መካከል ትላንት ንጋት ላይ ውጊያ መካሄዱን ምንጮቹን ዋቡ በማድረግ ሮይተርስ የዜና ወኪል አስታወቀ።

በብሉ ናይል ግዛት የተነሳውን ውጊያ የሸሹ በመቶዎች የሚቆጠሩ የአከባቢው ነዋሪዎች ድንበር አቋርጠው ወደ ኢትዮጵያ መግባታቸውን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ማስታወቁን ዘገባው አካቷል።

በጉዳዩ ዙሪያ ሱዳን ፖስት ይዞት በወጣው ዘገባ ግጭቱ የተጀመረው በሱዳን ከሚንቀሳቀሱ አማጺ ቡድኖች ውስጥ ትልቁ እንደሆነ የሚነገረው የሱዳን ህዝቦች ነጻ አውጪ ንቅናቄ ሰሜን በሱዳን ጦር ሰራዊት ካምፕ ላይ ጥቃት በመፈጸሙ መሆኑን አመላክቷል።

https://rb.gy/s456m
ዜና፡ "ጥቂት አንቂዎች ማህበራዊ ሚዲያውን በመጠቀም የ #አማራ ህዝብና #መንግስት እረፍት እንዳይኖራቸው በሃሰት መረጃ የጥፋት መንገድን በመከተል ላይ ይገኛሉ" - የአማራ ክልል ሰላምና ጸጥታ ቢሮ

ጥቂት የሚባሉ አንቂዎች ማህበራዊ ሚዲያውን በመጠቀም የአማራ ህዝብና መንግስት ማኀበራዊ እረፍት እንዳይኖራቸው በሃሰት መረጃ የጥፋት መንገድን በመከተል ላይ ይገኛሉ ሲል የአማራ ክልል ሰላምና ጸጥታ ቢሮ አስታወቀ፡፡

ቢሮው ይህን ያለው በአማራ ክልል ከትላንት ሰኔ 19 ጀምሮ ለሶስት ቀን ህዝባዊ ሰልፍ ይካሄዳል የሚል መረጃ ሰሞኑን በማህበራዊ ሚዲያ መሰራጨቱን ተከትሎ ነው፡፡

የክልሉ ሰላምና ጸጥታ ቢሮ አንቂዎች ያላቸው አካላት የህዝብንና የመንግስትን ግንኙነት ጥርጣሬ ውስጥ የሚጥሉ አፍራሽ እንቅስቃሴዎች ላይ በመጠመድ የአማራ ህዝብን ማኀበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ጉዞ ወደ ኋላ የሚጎትት አሉታዊ ተግባር በመስራት ላይ መሆናቸውን ገልጧል፡፡
https://rb.gy/4jhua
#ኢትዮጵያ: ኦዲት በተደረጉ 131 መስሪያ ቤቶች ከ15 ቢሊዮን ብር በላይ ውዝፍ ተሰብሳቢ ሂሳብ መገኘቱን የፌደራል ዋና ኦዲተር መስሪያ ቤት የ2014 በጀት ዓመት ሪፖርት አመላከተ።

እንደ ፓርላማው ዘገባ በወቅቱ ያልተወራረደ ውዝፍ ተሰብሳቢ ሂሳብን በተመለከተ ኦዲት በተደረጉ 131 መስሪያ ቤቶች በጠቅላላው ከ15 ቢሊዮን 125 ሚሊዮን ብር በላይ ብር በወቅቱ ያልተወራረደና ያልተሰበሰበ ሂሳብ መኖሩ በኦዲት መረጋገጡን ዋና ኦዲር መሰረት ዳምጤ ገልጸዋል፡፡

"ጤና ሚኒስቴር፣ የውሃ፣ መስኖ፣ ቆላማ አካባቢና አካባቢ ልማት ሚኒስቴር፣ የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን፣ ባህልና ስፖርት ሚኒስቴር፣ የአደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን እና ትምህርት ሚኒስቴር በወቅቱ ያልተወራረደ ውዝፍ ተሰብሳቢ ሂሳብ ከተገኘባቸው ተቋማት ተጠቃሽ መሆናቸውንም ዋና ኦዲተሯ በሪፖርታቸው አንስተዋል፡" በማለት ፓርላማው በተጨማሪ ዘግቧል።

ወይዘሮ መሰረት እንዳሉት ተሰብሳቢ ሒሳቦቹ ከዓመት ወደ ዓመት በሂሳብ መግለጫዎቹ ላይ የሚታዩ ከሆነ ታአማኒነትን ከማሳጣታቸውም በላይ የመንግስትና የሕዝብ ኃብት ለብክነት ስለሚጋለጥ ተቋማቱ በደንብና መመሪያ መሰረት እንዲያወራርዱ እና መሰብሰብ የማይችሉትን ደግሞ አጣርተው እርምጃ እንዲወስዱ አስተያየት ተሰጥቷል ብለዋል፡፡
#ግብርና፡ በ #አማራ_ክልል በተከሰተው የአፈር ማዳበሪያ ግብዓት እጥረት ምክንያት የመኸር እርሻቸውን በአግባቡ ማከናወን እንዳልቻሉ የክልሉ አርሶ አደሮች ገለጹ

በአማራ ክልል፣ ምስራቅ ጎጃም ዞን አነደድ ወረዳ ነዋሪ አርሶ አደር አቶ ባይነሳኝ እንዳወቀ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለጹት፤ በክልሉ በተከሰተው የአፈር ማዳበሪያ እጥረት ምክንያት በቆሎ መዝራት አለመቻላቸውን ተናግረዋል።

የበቆሎ ማሳችንን ሙሉ በሙሉ በሰብል መሸፈን አልቻልንም ያሉት አርሶ አደሩ፤ ይህም የመኸር እርሻቸውን በአግባቡ ማከናወን እንዳንችል ተፅዕኖ ፈጥሮብናል ሲሉ ተናግረዋል።

በሌላ በኩልም ስንዴና ጤፍ መዝራት የሚያስችል የአፈር ማዳበሪያ ግብዓት በስፋት በገበሬ ቀበሌ ማኅበራት በኩል እየቀረበ አይደለም ብለዋል። የሀገሪቱ የኢኮኖሚ የጀርባ አጥንት ግብርና በመሆኑ ችግሩ ባስቸኳይ ሊፈታልን ይገባል ሲሉም ጠይቀዋል።

የክልሉ ግብርና ቢሮ በበኩሉ ያለውን ችግር ለመፍታት የሰብል ለውጥ አድርገው እንዲዘሩ እየሠራን ነው ብሏል።
https://press.et/?p=103495
ዜና፡ #በኢትዮጵያ የአትክልት እና ፍራፍሬ አመጋገብ ባህል እጅግ ዝቅተኛ መሆኑ ተገለጸ

በኢትዮጵያ #የአትክልት እና #ፍራፍሬ አመጋገብ ባህል እጅግ ዝቅተኛ መሆኑ አንድ ጥናት አመላከተ፤ ጎረቤት ሀገራት ከኢትዮጵያ በተሻለ ደረጃ ተጠቃሚዎች መሆናቸውም ተገልጿል። ይህም በቀላሉ ልንከላከላቸው የምንችለው በሽታዎች ተጋላጭ እንዳደረገን ጥናቱ አስታውቋል።

አትክልክት እና ፍራፍሬ እንዳንመገብ እንቅፋት የሆነብን የዋጋው መወደድ እና ያለን ገቢ አነስተኛ መሆኑ እንደሆነም በጥናቱ ተጠቁሟል። ይሁን እንጂ ይላል ጥናቱ፣ ደህና ገቢ ያላቸው ኢትዮጵያውያንም ጭምር የአትክልት እና ፍራፍሬ አጠቃቀም ባህላቸው አናሳ ነው፤ #የአለም የጤና ድርጅት በምክረ ሀሳብነት ካቀረበው መመገብ ያለብን የአትክልት እና ፍራፍሬ መጠን ጋር ሲነጻጸር ባለሃብት ኢትዮጵያውያን የሚመገቡት አነስተኛ ነው ተብሏል።

የኢትዮጵያውያንን የአትክልት እና ፍራፍሬ አመጋገብ ባህል ለማሳደግ እና በከተሞች አቅርቦቱ በበቂ ሁኔታ እንዲኖር ለማስቻል ትልቁን ሚና ሊጫወቱ የሚችሉት ጥቃቅን እና አነስተኛ ተቋማት ማለትም ነጋዴዎች እና ቸርቻሪዎች መሆናቸውን ጥናቱን ያካሄደው ተቋም CGIAR በምክረ ሀሳብነት አስቀምጧል።

https://rb.gy/ptilk
#ትግራይ ክልል ከ700 በላይ ሰዎች #በረኀብ እንደሞቱ ባለሥልጣናት ተናገሩ

በትግራይ የምግብ ርዳታ ሥርጭት ማቋረጣቸውን ተከትሎ፣ ከክልሉ ካሉ ሰባት ዞኖች ውስጥ በሶስቱ 728 ሰዎች በረሃብ መሞታቸውን ትግራይ ክልል የአደጋ ዝግጁነት ኮሚሽን መሪ ገብረህይወት ገብረ እግዚአብሔር አሶሺዬትድ ፕሬስ ገልፀዋል፡፡

“በክልሉ ያለው ሁኔታ እጅግ አሳዛኝ ነው፤ በርካታ ሰዎች በምግብ እጥረት የተነሳ በመሞት ላይ ናቸው” ሲሉ ገብረህይወት ተናግረዋል፡፡

በረኀብ ከሞቱት ከ728ቱ ውስጥ 350ዎቹ፣ በክልሉ ለሁለት ዓመታት በተካሔደው ጦርነት ምክንያት፣ ከቀዬአቸው የተፈናቀሉ በሺሕዎች የሚቆጠሩ ተፈናቃዮች ከተጠለሉበት ሰሜን ምዕራባዊ ዞን እንደኾኑ፣ ዘገባው አመልክቷል፡፡ እ.አ.አ መጋቢት አጋማሽ ላይ፣ የዩናይትድ ስቴትስ የተራድኦ ድርጅት ባለሥልጣናት፣ የዞኑ ትልቋ ከተማ በኾነችው ሽሬ በሚገኝ ገበያ፣ ለ134 ሺሕ ሰዎች የሚበቃ የምግብ ርዳታ ሲሸጥ ማግኘታቸውን ዘገባው ገልጧል፡፡

https://amharic.voanews.com/a/hunger-kills-hundreds-Ethiopia-s-Tigray/7158843.html?fbclid=IwAR1VigT3HdNtFyOxd_dfNMI_2zHa07CKVxDrCMxFO0C7Ut55zzblWXY_1Mg
ዜና፡ በ #ደብረ-ብርሃን መጠለያ ካምፖች ውስጥ ከ116 በላይ ተፈናቃዮች በኩፍኝ በሽታ መያዛቸው ተገለፀ

በአማራ ክልል በደብረ ብርሃን ከተማ ከ27 ሺሕ በላይ ተፈናቃዮች በሚገኙባቸው ወይንሸትና ቻይና መጠለያ የመጠለያ ካምፖች የኩፍኝ በሽታ መከሰቱን፣ የሰሜን ሸዋ ዞን ሃላፊዎችን ዋቢ አድርጎ ሪፖርተር ዘግቧል፡፡

በመጠለያ ጣቢያዎቹ ከፍተኛ የምግብ እጥረት በማጋጠሙና ተፈናቃዮች በሽታውን ለመቋቋም አቅም ስላነሳቸው በሽታው ሊከሰት መቻሉን የሰሜን ሸዋ ዞን አደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና ጽሕፈት ቤት መምርያ ኃላፊ አቶ አበባው ተናግረዋል፡፡

“አብዛኞቹ ተፈናቃዮች በማኅበረሰቡ ውስጥ ነው ተጠልለው የሚገኙት፤” ያሉት አቶ ደረጀ፣ በዞኑ በሚገኙ 17 የመጠለያ ካምፖች ብቻ ከ90 ሺሕ በላይ ተፈናቃዮች እንዳሉና ሁሉም ተፈናቃዮች የምግብ እጥረት እንዳጋጠማቸው አክለው ገልጸዋል፡፡

https://rb.gy/1oq38
ዜና፡ #ይርጋጨፌ ቡና #በቻይና ከሻይ ጋር በመቀላቀል ልዩ ጣዕም ፈጥሯል ተባለ

ይርጋጨፌ ቡና በቻይና #ከሻይ ጋር በመቀላቀል የፈጠረው ጣዕም በቻይናውያን ዘንድ ተወዳጅነት ማግኘቱን ዢንዋ ባስነበበው ዘገባ አስታውቋል።

የቻይና ህዝብ ሻይ በመጠጣት ባህሉ የሚታወቅ ቢሆንም ቡናም በማጣጣም ላይ እንደሚገኝ ያስታወቀው ዘገባው አዲሱ የቻይና ትውልድ የቡና ፍላጎቱ በከፍተኛ ሁኔታ እያደገ እንደሚገኝ ጠቁሟል።

ባሳለፍነው የፈረንጆቹ አመት 2022 በቻይና ገበያ በኦንላይን የተሸጠ የቡና መጠን #27 ነጥብ 6ቢሊየን ዶላር ማውጣቱን ያስታወቀው የዜና አውታሩ ከሶስት አመታት በኋላ #ከ50 ቢሊየን ዶላር በላይ እንደሚደርስ መተንበዩን አመላክቷል። ይህም በከፍተኛ ደረጃ እያደገ የመጣውን የቻይናውያን የቡና ፍላጎት ያሳያል ተብሏል።

በቻይና በጥቂት ሰዎች ብቻ ይዘወተር የነበረው ቡና በአሁኑ ወቅት ሰዎች በቡድን ተሰባስበው የሚጠጡት ሁኗል ሲል ካሽ ኮፊ የተሰኘ የቡና ምርት በማቅረብ ላይ የሚገኝ የቻይና ኩባንያ መስራች ያኦ ሲዪ ገልጸውልኛል ሲል ያስነበበው ዢንዋ አዲሱ የቻይና ትውልድ የቡና ማሽኖችን በመግዛት እቤታቸው እንዴት ማፍላት እንደሚችሉ ትምህርት በመከታተል ላይ እንደሚገኙም ነግረውኛል ብሏል።
https://rb.gy/v54e6
ዜና፡ #በትግራይ የምግብ እርዳታ በመቋረጡ ምክንያት የሚሞቱ ሰዎች መጨመሩ #አሜሪካ ድጋጤ ፈጥሮብኛል ስትል ገለጸች

በኢትዮጵያ የረድኤት ድርጅቶች የምግብ እርዳታ አቅርቦታቸውን በማቋረጣቸው ሳቢያ የሚሞቱ ሰዎች ቁጥር እየጨመረ መምጣቱ ተዘግቧል። አሶሼትድ ፕሬስ በትግራይ የሚገኙ ባለስልጣናት በክልሉ በሚገኙ ሰባት ዞኖች የምግብ እርዳታ ከተቋረጠ ወዲህ #728 ሰዎች መሞታቸውን ገልጸውልኛል ሲል ዘግቧል።

ይህንንም ተከትሎ የአሜሪካ የተራድኦ ድርጅት ለዜና አውታሩ በላከው የኢሜይል መልዕክት በእርዳታው መቋረጥ ሳቢያ የሚሞቱ ሰዎች መጨመሩ ድንጋጤ እንደፈጠረበት አስታውቋል።
እርዳታ ስርጭቱን የማቆም ውሳኔ እጅግ መራራ መሆኑን

የገለጸው ተራድኦ ድርጅቱ በየትኛውም ሀገር ተፈጽሟል ተብሎ የማይገመት መጠን ያለው የምግብ እርዳታ በኢትዮጵያ መሰረቁን አመላክቷል።
በምግብ እጦት ከሚሰቃይ ህዝብ ጉሮሮ ስርቆት መፈጸም ተቀባይነት የሌለው ከመሆኑ ባሻገር ነገሩ ከአይምሮ በላይ ነው ሲል በአጽንኦት ኮንኗል።
https://rb.gy/q8djx