Addis Standard Amharic – Telegram
Addis Standard Amharic
18K subscribers
4.75K photos
123 videos
3 files
3.78K links
አዲስ ስታንዳርድ በጃኬን አሳታሚ ኃ.የተ.የግ.ማ. ባለቤትነት ስር የሚታተም በኢትዮጵያ የሚገኝ ነፃ እና ገለልተኛ ሚዲያ ነው። አዲስ ስታንዳርድ አማርኛ የአዲስ ስታንዳርድ እንግሊዝኛ ሕትመት አካል ነው።
ፌስቡክ: https://rb.gy/xwxb3
ትዊተር (X)፡ https://rb.gy/34uh4
Download Telegram
ዜና፡ ዋሻ የተናደባቸው #የኦፓል ማዕድን አውጭዎችን ለማትረፍ የሚደረገው ጥረት አራተኛ ቀኑን ቢያስቆጥርም ውጤት አልተገኘም ተባለ

በደቡብ #ወሎ ዞን ደላንታ ወረዳ "018 አለኋት" ቀበሌ በተለምዶ ቆቅ ውኃ እየተባለ በሚጠራ አካባቢ ጥር 30 ቀን 2016 ዓ.ም ሌሊት የኦፓል ማዕድን በቁፋሮ ለማውጣት ሲሞክሩ የነበሩ ከሃያ በላይ ወጣቶች የቆፈሩት አለት በመናዱ ያሉበትን ሁኔታ ለማወቅ አስቸጋሪ ሁኔታ መፈጠሩ ይታወቃል።

የተዳፈኑትን ወጣቶች ለማውጣት የቦታው አቀማመጥ ለማሽን የተመቸ ባለመሆኑ በሰው ኃይል በቁፋሮ ህይወታቸውን ለማትረፍ ርብርብ እየተደረገ እንደሚገኝ የደቡብ ወሎ ዞን ኮሙዩኒኬሽን ያጋራው መረጃ ያሳያል።

ሰዎቹን ለማውጣት የአካባቢው ማኅበረሰብ ጥረት እያደረገ ቢሆንም እስካሁን ውጤት አልተገኘም ሲሉ የአካባቢው ባለሥልጣን እና የከበረ ማዕድን አውጪዎች ማኅበር ሊቀመንበር እንደነገሩት ቢቢሲ በዘገባው ጠቁሟል።

የወረዳው አስተዳዳሪ አቶ አያሌው በሪሁን ባለፉት ቀናት ከአምስት መቶ በላይ ሰዎች በነፍስ አድን ሥራው ላይ እገዛ ለማድረግ ወደ ሥፍራው ቢያቀኑም፣ ወደ ዋሻው ለማምራት የሚያስችለው መንገድ ጠባብ እና በአንድ ጊዜ ከአስር ሰዎች በላይ ማስገባት ባለመቻሉ ጥረታቸው አዝጋሚ እንዳደረገባቸው ዘገባው አመላክቷል።
https://wp.me/pfjhHd-W9
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
የአዲስ ስታንዳርድ አማርኛ ዕለታዊ አርዕስተ ዜናዎች - የካቲት 4/ 2016 ዓ.ም

ዕለታዊ አርዕስተ ዜናዎች፣ ዘገባዎችና ቃለ መጠይቆቸን በቲክቶክ ለመከታተል ሊንኩን ይጠቀሙ: https://www.tiktok.com/@addisstandardamh?_t=8jFUq1nJS58&_r=1
ዜና፡ #በትግራይ 105 ትምህርት ቤቶች ተፈናቃዮች ተጠልለውባቸዋል፣ 522 የሚሆኑት ደግሞ በተለያዩ ሀይሎች ስር ናቸው ተባለ

በዶ/ር ዲማ ነጎ የተመራ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የውጭ ግንኙነትና ሰላም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አባላት በትግራይ ክልል የመስክ ምልከታ በማድረግ ላይ እንደሚገኝ ተጠቆመ።

ለቋሚ ኮሚቴው ሪፖርት ካቀረቡት መካከል የክልሉ አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ሲሆን በትግራይ ክልል ከሚገኙ ትምህርት ቤቶች ውስጥ 105 የሚሆኑት ትምህርት ቤቶች ተፈናቃዮች እንደተጠለሉባቸውና 522 የሚሆኑት ደግሞ በተለያዩ ሀይሎች ሥር እንደሚገኙ አስታውቋል። ይህም ልጆች ትምህርት እንዳይማሩ ተፅዕኖ እንዳሳደረባቸው ጠቁሟል።
https://wp.me/pfjhHd-Wd
ዜና፡ ግብረ ሰዶማዊነትንና ተያያዥነት ያላቸውን ተግባራት "አስርጎ በማስገባት ስምምነቶች እንዲፈጸሙ ለማድረግ" ያለው ሃደት በአፋጣኝ እንዲፈተሽ ቋሚ ሲኖዶስ ጠየቀ

#ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ቋሚ ሲኖዶ፤ የምዕራቡ ዓለም ሀገራት የፖለቲካና የኢኮኖሚ ጫና በማሳደር የአፍሪካና የምሥራቁ ዓለም ሀገራት ግብረ ሰዶማዊነትንና ተያያዥነት ያላቸውን ተግባራት እንዲቀበሉ ለማድረግ እየተከናወኑ ያሉትን “ድብቅና ግልጽ እንቅስቃሴዎችን” በጽኑ እንደሚቃወም አስታወቋል፡፡

ይህ ተግባር በዘመናችን ተቀባይነት እንዲኖረው፣ የሚደረጉ ሁለገብ ማግባባቶች፣ ተጽዕኖዎችና ተያያዥነት ያላቸው ስምምነቶች በሀገራችን መንግሥት ተቀባይነት አግኝተው እንዳይፈጸሙ ቋሚ ሲኖዶስ በጥብቅ አሳስቧል።

የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤም ኢትዮጵያ ፈርማለች የተባለውን የሳሞአ የንግድና የኢኮኖሚ የአጋርነት ስምምነትን ተቃውሟል። ለማንበብ ሊንኩን ይጠቀሙ፡ https://wp.me/pfjhHd-Wh
ዜና፡ በ #አማራ ክልል በጥር ወር ብቻ ቢያንስ ከ66 በላይ ሲቪል ሰዎች "በመንግስት ጸጥታ ኃይሎች ከሕግ ውጭ" መገደላቸውን ኢሰመኮ አስታወቀ

አሳሳቢነቱ በቀጠለው በአማራ ክልል የትጥቅ ግጭት ምክንያት ባሳለፍነው ጥር ወር ብቻ ከ 66 በላይ ሲቪል ሰዎች "በመንግስት ጸጥታ ኃይሎች ከሕግ ውጭ" መገደላቸውን የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ገለጸ።

ኮሚሽኑ በሰሜን ጎጃም ዞን በመራዊ ከተማ ጥር 20 ቀን 2016 ዓ.ም. “ለ #ፋኖ ድጋፍ አድርጋችኋል” በሚል ምክንያት ማንነታቸውን ማረጋገጥ የተቻለ ቢያንስ 45 ሲቪል ሰዎች በመንግሥት ጸጥታ ኃይሎች ከሕግ ውጭ ተገድለዋል ብሏል።

ተጨማሪ ያንብቡ፡ https://wp.me/pfjhHd-Wp
ዜና፡ የፌደራል መንግስቱ ተቋማት በምዕራብ #ትግራይ የህዝብ አሰፋፈር ለመቀየር ተሳትፎ እያደረጉ ባለበት ሁኔታ ሪፈረንደም አይታሰብም - ጌታቸው ረዳ

የትግራይ ክልል ፕሬዝዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ ትላንት የካቲት 5 ቀን 2016 ቀን ለክልሉ መገናኛ ብዙሃን በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ በምዕራብ ትግራይ የፌደራል መንግስቱ ተቋማት የአከባቢውን የህዝብ አሰፋፈር እንዲቀየር እየሰሩ ባለበት እንዲሁም በአከባቢው ነዋሪ የሆኑ የትግራይ ተወላጆች አሁንም በተጨማሪ እየተፈናቀሉ ባለበት ሁኔታ ሪፈረንደም ማካሄድ የማይታሰብ ነው ሲሉ ጠቁመዋል።

ሪፈረንደም የሚካሄድ ከሆነም #በፕሪቶርያው ስምምነት መሰረት ህገመንግስቱን ተከትሎ ነው ብለዋል።

የሰላም ስምምነቱን እንደግዜ መግዣ በመጠቀም ሌላ አጀንዳችሁን ለማስፈጸሚያነት እያዋለችሁት ነው፤ የጊዜያዊ አስተዳደሩ #ከኤርትራ እና ከሌሎች የሀገሪቱ ክልል ታጣቂዎች ጋር በጋራ በመሆን የፌደራል መንግስቱ ላይ እያሴራችሁ ነው የሚል ወቀሳ ከመንግስት በኩል እንደቀረበባቸው ጠቁመዋል።
ተጨማሪ ያንብቡ፡ https://wp.me/pfjhHd-Wr
ዓለም አቀፍ የቀይ መስቀል ኮሚቴ በግጭት የተጎዱ ሰዎችን ለማከም የሚውል የሕክምና ቁሳቁስ ድጋፍ አደረገ

ዓለም አቀፍ የቀይ መስቀል ኮሚቴ በግጭት በተጎዱ አካባቢዎች የቆሰሉና የታመሙ ሰዎችን ለማከም የሚውል የሕክምና ቁሳቁስ እና የመድኃኒት አቅርቦት ድጋፍ ማድረጉን አስታወቀ።

ኮሚቴው በግጭት በተጎዱ አካባቢዎች የሚገኙ የጤና ተቋማት የቆሰሉና የታመሙ ሰዎችን ለማከም የሕክምና ቁሳቁስ እና የመድኃኒት አቅርቦት ያስፈልጋቸዋል ብሏል።

በዚህም መሰረት ዓለም አቀፍ የቀይ መስቀል ኮሚቴ ለ #ወልዲያ#ላሊበላ#አላማጣ እና #ቆቦ ሆስፒታሎች እንዲሁም #ለሙጃ#ሮቢት እና #ጀመዶ የጤና ማዕከሎች የሕክምና ቁሳቁስ እና የመድኃኒት ድጋፍ ማደረጉን ገልጿል።

================
የአዲስ ስታንዳርድ አማርኛ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን ይቀላቀሉ፡
ቴሌግራም: https://rb.gy/rekjr
ፌስቡክ: https://rb.gy/xwxb3
ትዊተር (X)፡ https://rb.gy/34uh4
ዩቲዩብ፡ https://rb.gy/bjcbg
ድረገጽ: https://rb.gy/5td6n
ቲክቶክ፡https://rb.gy/3bghek
ዜና፡ በመላ #ሀገሪቱ ከ930 በላይ የቅዳሜና እሁድ ገበያ ማዕከላት ይገኛሉ ተባለ

የዋጋ ንረትን ለማረጋጋት በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍል ከ930 በላይ የቅዳሜና እሁድ ገበያዎች መዘርጋታቸውን የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር አስታወቀ።

በእነዚህ የግብይት ማዕከላት የግብርና እና የኢንዱትሪ ምርቶች በአጠረ የግብይት ሰንሰለት ከመደበኛው ገበያ ከ10-50 ብር በሚደርስ ቅናሽ እየቀረቡ መሆኑን የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር አቶ ገብረመስቀል ጫላ መናገራቸውን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያሳያል።

ሚኒስትሩ በተጨማሪም የግብይት ቦታዎችን ቁጥር ከማስፋት ጎን ለጎን በቂ ምርት እንዲቀርብባቸው ማድረግ፣ ግብይቱን ማዘመን እና ለህገ-ወጦች እና ደላላዎች እንዳይጋለጡ ጥብቅ ድጋፍና ክትትል ማድረግ በየደረጃው ከሚገኝ አመራር የሚጠበቅ ቁልፍ ተግባር ነው ማለታቸውን መረጃው አካቷል።

በንግድ ሴክተሩ በተከናወኑ የገበያና ዋጋ ማረጋጋት ስራዎች ባለፈው በጀት ዓመት 34.2 በመቶ የነበረው አጠቃላይ የዋጋ ግሽበት ባለፉት 6 ወራተ አንፃራዊ መረጋጋገት በማሳየት በህዳር ወር ወደ 28.3 በመቶ ዝቅ ብሏል ሲሉ ሚኒስትሩ መናገራቸውንም መረጃው አመላክቷል።

================
የአዲስ ስታንዳርድ አማርኛ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን ይቀላቀሉ፡
ቴሌግራም: https://rb.gy/rekjr
ፌስቡክ: https://rb.gy/xwxb3
ትዊተር (X)፡ https://rb.gy/34uh4
ዩቲዩብ፡ https://rb.gy/bjcbg
ድረገጽ: https://rb.gy/5td6n
ቲክቶክ፡https://rb.gy/3bghek
#አውሮፓ_ህብረት በመራዊ ከተማ ተፈጸመው የሲቪል ሰዎች ግድያና የአማራ ክልል የአቸኳይ ጊዜ አዋጅ መራዘም "በእጅጉ እንዳሳሰበው" ገለፀ

የአውሮፓ ህብረት ዛሬ ባወጣው መግለጫ "በአማራ ክልል መራዊ ከተማ በሲቪል ሰዎች ላይ የተፈፀመው ግድያ በእጅጉ እንዳሳሰበው" ገለፀ። ህብረቱ “ገለልተኛ ምርመራ” እንዲካሄድም ጥሪ አቅርቧል።

በተጨማሪም በአማራ ክልል የታወጀው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መራዘሙ “የአካባቢውን ሰዎች ሰብዓዊ መብቶችን በከፍተኛ ሁኔታ የሚገድብ በመሆኑ አሳሳቢ ክስተት ነው" ሲል ገልጿል።

በማከልም ህብረቱ "አሁን ያለውን ግጭት በፖለቲካዊ መንገድ ለመፍታት ወደ ውይይት፣ እርቅ እና ሰላም የሚያመራ ማንኛውንም ሂደት ለመደገፍ ዝግጁ መሆኑን በድጋሚ ያረጋግጣል" ሲል ገልጾ ሁሉም ኢትዮጵያውያን የውይይት መንገድ እንዲከተሉ አሳስቧል።

የአውሮፓ ህብረት በመግለጫው "በአገሪቱ ውስጥ ለሚፈጠሩ ግጭቶች ዘላቂ መፍትሄ የሚያመጣው ሰላማዊ መፍትሄ ብቻ ነው" ብሏል።

================
የአዲስ ስታንዳርድ አማርኛ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን ይቀላቀሉ፡
ቴሌግራም: https://rb.gy/rekjr
ፌስቡክ: https://rb.gy/xwxb3
ትዊተር (X)፡ https://rb.gy/34uh4
ዩቲዩብ፡ https://rb.gy/bjcbg
ድረገጽ: https://rb.gy/5td6n
ቲክቶክ፡https://rb.gy/3bghek
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
የአዲስ ስታንዳርድ አማርኛ ዕለታዊ አርዕስተ ዜናዎች - የካቲት 5 / 2016 ዓ.ም

ዕለታዊ አርዕስተ ዜናዎች፣ ዘገባዎችና ቃለ መጠይቆቸን በቲክቶክ ለመከታተል ሊንኩን ይጠቀሙ: https://www.tiktok.com/@addisstandardamh?_t=8jFUq1nJS58&_r=1
በመዲናዋ ለሶስት ቀናት ሞተር ብስክሌት ማሽከርከር ተከለከለ

በአዲስ አበባ ከተማ ከመጭው አርብ ከየካቲት 8 ቀን ጠዋት 12 ሰዓት ጀምሮ እስከ ሰኞ የካቲት 11 ቀን 2016 ዓ.ም ጠዋት 2 ሰዓት ድረስ ሞተር ብስክሌት ማሽከርከር መከልከሉን የከተማዋ ትራንስፖርት ቢሮ አስታውቋል፡፡

ቢሮው ክልከላው የጸጥታ እና የትራፊክ ቁጥጥር የሚሰሩ አካላትን እንደማያካትት ገልጿል፡፡

የሞተር ብስክሌት ባለንብረቶች እና አሽከርካሪዎች እስከ ተጠቀሰው ቀን ድረስ በትዕግስት እንዲጠብቁ የተጠየቀ ሲሆን ክልከላ በሚተላለፉ አካላት ላይ ጥብቅ እርምጃ የሚወሰድ መሆኑንም ትራንስፖርት ቢሮ አስታውቋል፡፡

================
የአዲስ ስታንዳርድ አማርኛ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን ይቀላቀሉ፡
ቴሌግራም: https://rb.gy/rekjr
ፌስቡክ: https://rb.gy/xwxb3
ትዊተር (X)፡ https://rb.gy/34uh4
ዩቲዩብ፡ https://rb.gy/bjcbg
ድረገጽ: https://rb.gy/5td6n
ቲክቶክ፡https://rb.gy/3bghek
በመራዊ በመንግስት ጸጥታ ኃይሎች ከተገደሉት ውስጥ 18ቱ ለቀን ሥራ ከቤታቸው ወጥተው ድንገት ተኩስ ሲከፈት በአንድ ቦታ ተጠልለው የነበሩ ሲቪል ሰዎች መሆናቸውን መንግስታዊው ተቋም ኢሰመኮ ገልጿል።

በተጨማሪም በዚያው መራዊ ከተማ አንድ የጠፋ አባልን ሲያፈላልጉ የነበሩ የመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች “በፍለጋው አልተባበሩም” ያሏቸውን 8 ሲቪል ሰዎችን መግደላቸውን እንዲሁም 12 ባጃጆችን ማቃጠላቸውን ትላንት ባወጣው ሪፖርት አስታውቋል።

ሴቶችን ጨምሮ 15 ሰዎች በምሥራቅ ጎጃም ዞን ሸበል በረንታ ወረዳ የዕድውኃ ከተማ በመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች ከሕግ ውጭ መገደላቸውና በሌሎች ሁለት ሰዎች ላይ የአካል ጉዳት መድረሱን ኢሰመኮ አመላክቷል።

ተጨማሪ ያንብቡ፡ https://wp.me/pfjhHd-Wp
#ኢትዮጵያ #አልሸባብ በሞቃዲሾ የፈጸመውን ጥቃት አወገዘች

ኢትዮጵያ አልሸባብ ቅዳሜ ዕለት በ #ሶማሊያ መዲና #ሞቃዲሾ ጀነራል ጎርደን ወታደራዊ ካምፕ ውስጥ የተጸመውን ጥቃት አወገዘች።

ወታደራዊ መኮንኖችን ዒላማ ባደረገው የአልሸባብ ጥቃት አራት ወታደሮች መሞታቸው የተገለጽ ሲሆን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ታዬ አፅቀስላሴ በጥቃቱ በደረሰው የሰው ህይወት መጥፋት እና አካል ጉዳት ጥልቅ ሃዘን እንደተሰማቸው ገልፀዋል።

በኢትዮጵያ መንግስት እና ህዝብ እንዲሁም በራሳቸው ስም የተሰማቸውን ጥልቅ ሃዘን ለሶማሊያ መንግስት እና ህዝብ የገለጹት ሚኒስትሩ ፤ “በልምምድ ወቅት ወታደራዊ መኮንኖችን ኢላማ በማድረግ የተፈፀመውን ጥቃት የወንጀል ተግባር ነው” ብለዋል።

የወንጀል ተግባሩን ኢትዮጵያ "በፅኑ እንደምታወግዘውም" አስታውቀዋል።

እንደ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ሚኒስትሩ ጥቃቱ አልሸባብ የሽብር ቡድን በሶማሊያ እና በክፍለ አህጉሩ ደህንነት አደጋ መደቀኑን በግልፅ ያረጋገጠ መሆኑን በመግለፅ የአካባቢው ሀገራት በፀረ ሽብር የሚያደርጉትን ትብብር ሊያጠናክሩ እንደሚገባም አመልክተዋል።
የሶማሊያን ሰላም እና ደህንነት በጋራ ለማረጋገጥ ኢትዮጵያ ትብብሯን አጠናክራ በቁርጠኛነት እንደምትቀጥልም አስታውቀዋል።

================
የአዲስ ስታንዳርድ አማርኛ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን ይቀላቀሉ፡
ቴሌግራም: https://rb.gy/rekjr
ፌስቡክ: https://rb.gy/xwxb3
ትዊተር (X)፡ https://rb.gy/34uh4
ዩቲዩብ፡ https://rb.gy/bjcbg
ድረገጽ: https://rb.gy/5td6n
ቲክቶክ፡https://rb.gy/3bghek
አማርኛ ቋንቋ በአፍሪካ ሕብረት የስራ ቋንቋ ሆኖ እንዲካተት ተጠየቀ

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ታየ አጽቀ ሥላሴ አማርኛ ቋንቋ በአፍሪካ ሕብረት የስራ ቋንቋ ሆኖ እንዲካተት ጠየቁ።

ሚኒስትሩ ጥያቄውን ያቀረቡት ዛሬ በአዲስ አበባ መካሄድ በጀመረው በ44ኛው የአፍሪካ ሕብረት የስራ አስፈጻሚዎች ምክር ቤት መደበኛ ስብስባ ላይ የመክፈቻ ንግግር ባደረጉበት ወቅት ነው።

አምባሳደር ታየ የመጀመሪያው የአፍሪካ አንድነት ድርጅት ቻርተር አማርኛን ጨምሮ በአራት ቋንቋዎች የተፈረመ እንደነበር አስታውሰው አማርኛ ቋንቋ የሕብረቱ የስራ ቋንቋ እንዲሆን ሀሳብ ማቅረባቸውን የመንግስት ሚዲያዎች ዘግበዋል።

እ.አ.አ አቆጣጠር በ1963 በአዲስ አበባ የተፈረመው ቻርተሩ በአማርኛ፣ እንግሊዝኛ፣ ፈረንሳይኛ እና አረብኛ ቋንቋዎች ነበር።
አሁን የአፍሪካ ሕብረት ከ6 በላይ የስራ ቋንቋዎች ያሉት ሲሆን አማርኛ ቋንቋም እንዲካተት ተጠይቋል።

================
የአዲስ ስታንዳርድ አማርኛ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን ይቀላቀሉ፡
ቴሌግራም: https://rb.gy/rekjr
ፌስቡክ: https://rb.gy/xwxb3
ትዊተር (X)፡ https://rb.gy/34uh4
ዩቲዩብ፡ https://rb.gy/bjcbg
ድረገጽ: https://rb.gy/5td6n
ቲክቶክ፡https://rb.gy/3bghek
#ኢትዮጵያ እና የ #ጣሊያ በወታደራዊ ትብብር ዙሪያ አብረው ለመስራት የሚያስችላቸውን ውይይት አደረጉ

የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ ከጣሊያን ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም አድሚራል ጁሴፔ ቻቮ ጋር ሁለቱ ሀገራት በወታደራዊ ትብብር ዙሪያ አብረው ለመስራት የሚያስችላቸውን ውይይት አደረጉ።

በመከላከያ ጠቅላይ መምሪያ በተደረገው ውይይት ሁለቱ ሀገራት ያላቸውን መልካም ግንኙነት ማጠናከር በሚያስችላቸው እንዲሁም በጋራ መስራት በሚያስችላቸው ጉዳይ ዙሪያም መወያየታቸው ተገልጿል።

በጣሊያን ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም አድሚራል ጁሴፔ ቻቮ የተመራ ልዑክ መከላከያ ጠቅላይ መምሪያ ሲደርስ በጦር ሃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ እና በጀነራል መኮንኖች አቀባበል እንደተደረገላቸው ኢዜአ ዘግቧል።
ዜና፡ የኦፓል ማዕድን ዋሻ የተናደባቸውን ማዕድን አውጭዎችን ለማትረፍ ዘመናዊ ማሽኖች ድጋፍ እንዲደረግ ተጠየቀ

የደላንታ ወረዳ አስተዳዳሪ አቶ አያለው በሪሁን፤ ማዕድን አውጪዎቹን ለማትረፍ ለስድስት ቀናት እየተከናወነ ያለው ቁፋሮ ከ70 ሜትር ማለፉን ለአዲስ ስታንዳርድ ተናግረዋል። ቦታው ቆላማ እና መልክአ ምድሩ አስቸጋሪ በመሆኑ ችግሩን ባጭር ጊዜ እንዳይፈታ አድርጓል ብለዋል።

“በዚህም ምክንያት ሰዎቹን የማትረፍ ስራው ከአቅማችን በላይ ሆኗል” ሲሉ አስተዳዳሪው ለአዲስ ስታንዳርድ ገልጸዋል። በመሆኑም ሰዎቹን ከተደረመሰው የማዕድን ዋሻ ውስጥ ለማውጣት የሚረዳ ዘመናዊ ማሽኖች ድጋፍ እንዲደረግ ጥሪ አቅርበዋል።

https://wp.me/pfjhHd-Wz
ዕለታዊ ዜና፡ በሰላማዊ ዜጎች ላይ የሚቃጣ ጥቃት በአስቸኳይ እንዲቆም ኢዜማ ጠየቀ

በሰላማዊ ዜጎች ላይ የሚቃጣ ጥቃት በአስቸኳይ እንዲቆም እና መንግስት ግድያ የፈጸሙ የጸጥታ አካላት ላይ የፍትህ እርምጃ እንዲወስድ የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ (ኢዜማ) ጠየቀ።

እየተካሄደ ባለው ግጭት “እየተሳተፉችሁ ያላችሁ አካላት ለሰላማዊ ንግግር በራችሁን ክፍት በማድረግ ችግሮችን በውይይት በመፍታት ማኅበረሰቡ እየደረሰበት ካለው ቀውስ እንድትታደጉት” ሲል ጥሪ አቅርቧል።

ለማንበብ፡ https://wp.me/pfjhHd-WE
የአውሮፓ ህብረት በ #መራዊ ከተማ በተፈጸመው የሲቪል ሰዎች ግድያ ላይ “ገለልተኛ ምርመራ” እንዲካሄድም ጥሪ አቅርቧል።

ህብረቱ ትላንት ባወጣው መግለጫ የ #አማራ ክልል የአቸኳይ ጊዜ አዋጅ መራዘም "በእጅጉ እንዳሳሰበው" አስታውቋል።

አዋጅ መራዘሙ “የአካባቢውን ሰዎች ሰብዓዊ መብቶችን በከፍተኛ ሁኔታ የሚገድብ" በመሆኑ አሳሳቢ መሆኑን ገልጿል።

https://www.facebook.com/AddisstandardAmh/posts/pfbid0Eqfy7z8SS3bmtZ8jcdGjtdfR3KR5WKLQkbmT6rnEUfwu7PW9pNxhLjpXYU4sKijal
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
የአዲስ ስታንዳርድ አማርኛ ዕለታዊ አርዕስተ ዜናዎች - የካቲት 6/ 2016 ዓ.ም 

ዕለታዊ አርዕስተ ዜናዎች፣ ዘገባዎችና ቃለ መጠይቆቸን በቲክቶክ ለመከታተል ሊንኩን ይጠቀሙ: https://www.tiktok.com/@addisstandardamh?_t=8jFUq1nJS58&_r=1