አቶ #አደም_ፋራህ በፌደራል መንግስት እና በ #ህወሃት መካከል ሳይደረግ የዘገየውን የፖለቲካ ውይይት ለማስጀመር ወደ #መቀለ አመሩ
በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ የዴሞክራሲ ስርአት ግንባታ ማስተባበሪያ ማዕከል ሃላፊ ተደርገው የተሾሙት አቶ አደም ፋራህ፤ በፌደራል መንግስት እና በህወሃት መካከል የተዘገየውን የፖለቲካ ውይይት ለማስጀመር ወደ መቀለ አምርተዋል።
ህወኃት ባሰራጨው መረጃ መሰረት፤ አቶ አደም ፋራህ በ #ፕሪቶሪያው የሰላም ስምምነት መሰረት ለሁለት አመታት የተካሄደውን ደም አፋሳሽ ጦርነት መሰረታዊ ምክንያት ላይ የፖለቲካ ውይይት ለማስጀመር መቐለ ሲገቡ በህወሓት ሊቀመንበር ዶ/ር ደብረጺዮን ገ/ሚካዔል አቀባበል የተደረገላቸው ሲሆን ከሌሎች የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች ጋርም ተገናኝተዋል።
የገዥው ብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ አደም ፋራህ፣ ከመከላከያ ሚኒስትር ዶ/ር አብርሃም በላይ እና የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስትር ዶ/ር አለሙ ስሜን ጨምሮ ከሌሎች የፌዴራል መንግስት ከፍተኛ ባለስልጣናት ጋር በመሆን ነው ወደ መቀሌ ያመሩት።
በትግራይ በኩል በትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት አቶ ጌታቸው ረዳን ጨምሮ የህወሓት ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላት በስብሰባው ላይ ተሳትፈዋል።
እንደ ህወሓት መረጃ መሰረት፤ በውይይቱ ወቅት ሁለቱም ወገኖች በሁለቱ ፓርቲዎች መካከል የፖለቲካ ውይይት ቀደም ብሎ መጀመር እንዳለበት ገልጸዋል። ይሁን እንጂ ሁለቱም ወገኖች ከዚህ በኋላ መደበኛ ውይይቶችን ለመጀመር ተስማምተዋል።

ዜና: አንድ #ተከራይ ቤት ተከራይቶ ውል ከፈፀመ በኋላ ለሁለት ዓመት የቤት ኪራይ መጨመር እና ቤት ማስለቀቅ የሚከለክል አዋጅ ጸደቀ
የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ መጋቢት 24 ቀን 2016 ዓ.ም ባካሄደው 19ኛ መደበኛ ስብሰባው የመኖሪያ ቤት ኪራይ ቁጥጥር እና አስተዳደር አዋጅን መርምሮ አፅድቋል፡፡
በአዋጁ መሠረት አንድ ተከራይ ቤት ተከራይቶ ውል ከፈፀመ በኋላ ለሁለት ዓመት የቤት ኪራይ መጨመር እና ቤት ማስለቀቅ አይቻልም ተብሏል፤ ተከራይ ቤቱን ከጎዳ እና ሌሎች አዋኪ ተግባራትን ከፈፀመ ግን በአዋጁ አንቀፅ 16 መሠረት ቤቱን ለመልቀቅ እንደሚገደድም ተደንግጓል።
ወደፊት ለሚደረግ ጭማሪ አሁን ላይ ያለው የኪራይ ዋጋ መሠረት ተደረጎ በመንግሥት የሚሰላ እንደሚሆንም በአዋጁ ተገልጿል።
ለቤት ኪራይ የሚሆን አዲስ ቤት የገነቡ አካላት እንደማበረታቻ ለ4 ዓመት ያህል በድርድር ዋጋ ማስቀመጥ የሚችሉ ሲሆን፤ ከዛ በኋላ ግን አዋጁ ተፈፃሚ እንደሚሆንባቸው ተገልጿል።
ለዚህ አዋጅ ተፈፃሚነት ምዝገባው በቀጣይ ባሉት 3 ወራት ይጠናቀቃል ተብሎ የሚጠበቅ ሲሆን በክልሎች እና ከተማ አስተዳደሮች የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራዎች መስራታቸውም ተገልጿል።
ውል አለማስመዝገብ አስተዳደራዊ ቅጣት የሚያስከትል መሆኑ ተገልፆ፤ እስከ 3 ወር የሚደርስ የቤት ኪራዩን ዋጋ ያስቀጣልም ተብሏል።
አዋጁ በርካታ አዳዲስ አሰራሮችን ያካተተ ሲሆን ያከራይንም ሆነ የተከራይን ፍትሐዊ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጥ በመሆኑ ህብረተሰቡ መብቱን እና ግዴታውን በማወቅ ለተፈፃሚነቱ እንዲተባበር ጥሪ መቅረቡን ከኢቲቪ ያገኘነው መረጃ ያሳያል።
======
የአዲስ ስታንዳርድ አማርኛ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን ይቀላቀሉ፡
ቴሌግራም: https://rb.gy/rekjr
ፌስቡክ: https://rb.gy/xwxb3
ትዊተር (X)፡ https://rb.gy/34uh4

ዜና: #የህዳሴ ግድብ ቀሪ ስራዎችን ለማጠናቀቅ 50 ቢሊየን ብር ያስፈልጋል ተባለ
የህዳሴ ግድብ ፕሮጀክት አጠቃላይ የፋይናንስ ወጪ 191 ነጥብ 3 ቢሊዮን ብር መድረሱን እና ቀሪ የግድቡን የግንባታ ሥራዎች ለማጠናቀቅም 50 ቢሊዮን ብር እንደሚያስፈልግ የፕሮጀክቱ ሥራ አስኪያጅ ኢንጅነር ክፍሌ ሆሮ አስታወቁ።
የኮንትራት ማሻሻያ መደረጉ፣ የተጣበበ የፕሮጀክት ጊዜ ሰሌዳና በግንባታ ወቅት በግድቡ መሠረት ላይ ያጋጠመ ልል ድንጋይ መኖሩ እንዲሁም የልምድ ማነስ እና የጥራትና ልኬት በሚፈለገው ደረጃ አለመሆን በፕሮጀክቱ ግንባታ ላይ ያጋጠሙ ተግዳሮቶች እንደነበሩ ጠቅሰዋል።
ከ10 ነጥብ 7 ሚሊዮን ሜትር ኪዩብ የኮንክሪት ሙሌት ውስጥ የ10 ነጥብ 65 ሚሊዮን ሜትር ኪዩብ ሙሌት ተጠናቋል ሲሉ የተናገሩት ስራ አስኪያጁ በአሁኑ ወቅት የግድቡ የሲቪል ሥራዎች 99 ነጥብ 2 በመቶ እንዲሁም የኤሌክትሮ ሜካኒካል ሥራዎች አፈፃፀም 79 በመቶ መድረሱንም ጠቁመዋል።
https://wp.me/pfjhHd-14X

Addis standard
የህዳሴ ግድብ ቀሪ ስራዎችን ለማጠናቀቅ 50 ቢሊየን ብር ያስፈልጋል ተባለ - Addis standard
አዲስ አበባ፣ መጋቢት 25/2016 ዓ.ም፡- የህዳሴ ግድብ ፕሮጀክት አጠቃላይ የፋይናንስ ወጪ 191 ነጥብ 3 ቢሊዮን ብር መድረሱን እና ቀሪ የግድቡን የግንባታ ሥራዎች ለማጠናቀቅም 50 ቢሊዮን ብር እንደሚያስፈልግ የፕሮጀክቱ ሥራ አስኪያጅ ኢንጅነር ክፍሌ ሆሮ አስታወቁ። ስራ አስኪያጁ ይህንን ያስታወቁት “በህብረት ችለናል” በሚል መሪ ቃል የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የመሰረት ድንጋይ የተጣለበትን 13ኛ…
ዜና: አይ ኤም ኤፍ እና #ኢትዮጵያ ሳይስማሙ ቀሩ
ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር ሲደራደር የቆየው የአለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት (#አይኤምኤፍ) የልዑካን ቡድን ከስምምነት ላይ ሳይደርስ ጉብኝቱን ማጠናቀቁን ሮይተርስ አስታወቀ።
#የፓሪስ ክለብ በመባል የሚታወቀው የአበዳሪ አገራት ቡድን እስከ መጋቢት 22 ቀን 2016 ዓ.ም ድረስ ከአለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት ጋር ስምምነት ላይ የማትደርስ ከሆነ ብድር ለመክፈል የጠየቀችው የእፎይታ ግዜ ተቀባይነት እንደማያገኝ መግለጹ ይታወሳል።
በዚህም ሳቢያ ከአለም አቀፍ አበዳሪ ሀገራት ለኢትዮጵያ እንሰጠዋለን ያሉትን እስከ ሚቀጥለው የፈረንጆቹ አመት 2025 የሚቆይ የብድር መክፈያ የእፎይታ ግዜ ይሰርዙት ወይንም ተግባራዊ ያድርጉት የታወቀ ነገር አለመኖሩን የዜና አውታሩ በዘገባው አመላክቷል።
የአይኤምኤፍ ልዑክ ቡድን የሀገሪቱ ባለስለጣናት ያቀረቡትን የኢኮኖሚ ፕሮግራም ማገዝ በሚቻልበት ሁኔታ ዙሪያ ባካሄደው ውይይት ጥሩ መሻሻሎች ተስተውለዋል ሲል ተቋሙ መግለጹን ሮይተር በዘገባው አስታውቋል።
በአይኤምኤፍ እና በኢትዮጵያ መካከል የሚካሄደው ውይይት በሚያዚያ ወር መጨረሻ አከባቢ በዋሽንግተን እንደሚቀጥል የዜና አውታሩ በዘገባው ጠቁሟል።
================
የአዲስ ስታንዳርድ አማርኛ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን ይቀላቀሉ፡
ቴሌግራም: https://rb.gy/rekjr
ፌስቡክ: https://rb.gy/xwxb3
ትዊተር (X)፡ https://rb.gy/34uh4
ዩቲዩብ፡ https://rb.gy/bjcbg
ድረገጽ: https://rb.gy/5td6n
ቲክቶክ፡https://rb.gy/3bghek

ዜና: ከመርከብ የሚነሳ እሳት መከላከል የሚያስችል ስልጠና የወሰዱ #የኢትዮጵያ ባህር ሃይል አባላት በባቦጋያ ማሪታይም አካዳሚ ሰልጥነው ተመረቁ
#ከመርከብ የሚነሳ እሳት እንዴት መከላከል እና የእሳት አደጋ ከተነሳም በፍጥነት መቆጣጠር የሚያስችል ስልጠና የኢትዮጵያ ባህር ትራንስፖርትና ሎጀስቲክስ ማሪታይም ባቦጋያ አካዳሚ ለኢትዮጵያ ባህር ሃይል አባላት መስጠቱ ተገለጸ።
በስልጠናው ማጠቃለያ ላይ ተገኝተው ለተመራቂዎች የሥራ መመሪያ የሰጡት የኢትዮጵያ ባህር ሃይል ዋና አዛዥ ተወካይ ሬር አዲሚራል ናስር አባድጋ የባህር ሃይል ሠልጣኝ ተመራቂዎች የኢትዮጵያ ባህር ሃይል የጀርባ አጥንት በመሆናችሁ የሚጠበቅባችሁን ሁሉ መወጣት አለባችሁ ብለዋል።
አዛዡ አክለውም የባህር ሃይል አባል መሆንና መርከብ ላይ ግዳጅን መወጣት ጥሩ ሥነ-ምግባር፤ ወታደራዊ ዲሲፒሊን፤ ጠንካራ ግዳጅ አፈፃፀምና የህይወት መስዋዕትነትን ጭምር የሚጠይቅ ሙያ በመሆኑ እናንተ ተመራቂ የመርከብ ሙያተኞች በስልጠና ያገኛችሁትን አቅም ወደ ተግባር በመለወጥ ሙያዊ ሃላፊነታችሁን ልትወጡ ይገባል ሲሉ አሳስበዋል፡፡
የኢትዮጵያ ባህር ትራንስፖርትና ሎጀስቲክስ ባቦጋያ አካዳሚ ዲን ቺፍ ቴድሮስ ሚሊዮን ተመራቂ የኢትዮጵያ ባህር ሃይል አባላት በንድፈ ሀሳብ እና በተግባር የተደገፈ ሥልጠና በአግባቡ መከታተላቸውን ገልፀዋል።
ከተመራቂ አባላቱ መካከል አንዳንዶቹ በሰጡት አስተያየት መርከብ ላይ ስንወጣ በርካታ ውጣ ውረዶች የበዛበት በመሆኑ በመርከብ ላይ የሚነሳ የእሳት አደጋን በቀላሉ ለማጥፋት የሚያስችል ሙያዊ ስልጠና ወስደናል ብለዋል።
=========

ዜና: #የጃፓን መንግስት ከ1875 ጀምሮ ለውጭ ሃገር ዜጎች የሚሰጠውን አንጋፋና ክብር ያለዉ ሽልማት #ለደራርቱ ቱሉ አበረከተ
#የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት ረዳት ኮሚሽነር ደራርቱ ቱሉ ከጃፓን መንግስት የተበረከተላቸውን የወርቅ ጨረር ያለውን ኒሻን ሽልማታቸውን ተረከቡ።
ይህ እውቅናና ሽልማት እኤአ ከ1875 ጀምሮ ለውጭ ሃገር ዜጎች በጃፓን መንግስት የሚሰጥ አንጋፋና ክብር ያለዉ መሆኑን ከፌደሬሽኑ ያገኘነው መረጃ ያሳያል።
ከኢትዮጵያ የወርቅ ጨረር ያለው ኒሻን ሽልማት ከጃፓን መንግስት ሲሰጥ ረዳት ኮሚሽነር ደራርቱ ቱሉ የመጀመሪያዋ መሆኑም ተጠቁሟል።
በጃፓን እና በኢትዮጵያ መካከል በስፖርት ዲፕሎማሲ እና ልውውጥ ዘርፍ ላበረከቱት የላቀ አስተዋፅዖ፣ በሌሎች ሀገራት እና አካባቢዎች መካከል ያለውን ወዳጅነት ለማሳደግ፣ ለአትሌቲክስ እድገት፣ ለአገር ሰላም ላበረከቱት አስተዋፅኦ እውቅና በመስጠት በዓለም አቀፍ መስኮች የላቀ ስኬት ምክንያት ሽልማቱን አግኝተዋል በተብሏል።
ረዳት ኮሚሽነር ደራርቱ ሽልማታቸውን በኢትዮጵያ ከጃፓን አምባሳደር ሚስተር ሺባታ ሂሮኖሪ እጅ መረከባቸዉን የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ያጋራው መረጃ ያሳያል።

ዜና: #የሚኒስትሮች ምክር ቤት በማክሮ ኢኮኖሚና ፊሲካል ማዕቀፉ እንዲሁም በተጨማሪ እሴት ታክስ ረቂቅ አዋጅ ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳለፈ
የሚኒስትሮች ምክር ቤት በዛሬው ዕለት መጋቢት 25 ቀን 2016 ዓ.ም ባካሄደው 28ኛ መደበኛ ስብሰባ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳለፈ።
በቅድሚያ ምክር ቤቱ የተወያየው የመካከለኛ ዘመን 2017-2021 የማክሮ ኢኮኖሚ እና ፊሲካል ማዕቀፍ ላይ ነው፡፡
የማክሮ ኢኮኖሚና ፊሲካል ማዕቀፉ የመንግስት በጀት ከማክሮ ኢኮኖሚ ሁኔታው እና የፊሲካል አቅም ጋር ተጣጥሞ እንዲዘጋጅ ለማድረግ፤ ከመንግስት ገቢ አሰባሰብ እና ሀብት አመዳደብ አኳያ የፖሊሲ አቅጣጫዎችን በማመላከት ለቀጣይ በጀት አመት የበጀት ዝግጅት ለማድረግ፤ የመካከለኛ ዘመን የመንግስት ገቢና ወጪ እንዲሁም የፊሲካል ሚዛን የፖሊሲ አቅጣጫዎችን ለመለየት እና ለማመላከት የሚያገለግል ማዕቀፍ በመሆኑ ምክር ቤቱ በሰፊው ከተወያየበት በኋላ በስራ ላይ እንዲውል በሙሉ ድምጽ ወስኗል፡፡
በመቀጠል ምክር ቤቱ የተወያየው የተጨማሪ እሴት ታክስ ረቂቅ አዋጅ ላይ ነው።
የተጨማሪ እሴት ታክስ ስራ ላይ ከዋለበት ጊዜ ጀምሮ በሀገሪቱ የእኮኖሚ እንቅስቃሴ ውስጥ የተደረጉ ለውጦችን በህግ ማእቀፉ ውስጥ ማስገባት በማስፈለጉ፣ ዝቅተኛ ገቢ ያላቸው የህብረተሰብ ክፍሎች የተጨማሪ እሴት ታክስ ጫና እንዳያርፍባቸው ለማድረግ የሚያስችል ረቂቅ አዋጁ ተዘጋጅቶ ለሚኒስትሮች ምክር ቤት ቀርቧል።
ምክር ቤቱም በረቂቅ አዋጁ ላይ በሰፊው ከተወያየበት በኋላ ግብዓቶችን በማከል ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንዲተላለፍ በሙሉ ድምጽ መወሰኑን ከጠ/ሚኒስትር ጽ/ቤት ያገኘነው መረጃ ያሳያል።

ዜና: በመዲናዋ በመፍረስ ላይ ያሉ ቤቶች "በቅርስነት ለመመዝገብ የሚያስችል መስፈርት ያላሟሉ" ናቸው - #የኢትዮጵያ ቅርስ ባለስልጣን
የኢትዮጵያ ቅርስ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ረዳት ፕሮፌሰር አበባው አያሌው #ከአዲስ አበባ ኮሪደር ልማት ጋር ተያይዞ የሚነሱ ጉዳዮችን አስመልክቶ በሰጡት መግለጫ በመዲናዋ በኮሪደር ልማት ስራ ምክንያት የሚፈርሱ ቤቶች "በቅርስነት ለመመዝገብ የሚያስችል መስፈርት የሚያሟሉ ባለመሆናቸው" ነው ብለዋል።
ከዚህ ቀደም በመዲናዋ የቅርስ መስፈርቶችን ያላሟሉ ሁሉ የተመዘገቡ መኖራቸውን አስታውሰው፤ በተዘጋጀው መስፈርት መሰረት በአዲስ መልክ የቅርስ ምዝገባ እየተካሄደ መሆኑን ተናግረዋል።
በዚሁ መሰረት ከዚህ በፊት የተመዘገቡ በቅርስነት የሚቀጥሉ ሲኖሩ በመመሪያው መሰረት መስፈርቱን የማያሟሉ ደግሞ የማይቀጥሉ መሆናቸውን ገልፀዋል።
ከቀናት በፊት ባለስልጣኑ በአዲስ አበባ የመልሶ ግንባታና ኮሪደር ልማት የቅርስ መስፈርት የማያሟሉ ቤቶችንና አካባቢዎችን በመልሶ ማልማት የቀደመ ስያሜና አገልግሎታቸው እንዲቀጥል እንደሚደረግ ማስታወቁን ፕሬስ ድርጅት መዘገቡ ይታወሳል።
ቤቶቹን በቅርስነት ለመመዝገብ ያላቸው ታሪክ፣ አሁን ያሉበት ውጫዊ እና ውስጣዊ ገፅታ፣ እድሜያቸው፣ አርክቴክቸርን ጨምሮ በርካታ መስፈርቶች መቀመጣቸውን ገልጸዋል።
በተቀመጡት መመዘኛዎች መሰረት ከ50 በመቶ በላይ ውጤት ያመጣ በቅርስነት እንደሚመዘገብ እና በአንጻሩ ከ50 በታች የሆነ ቤት ቅርስ ተብሎ ሊመዘገብ እንደማይችል ጠቁመዋል።
ለየሀገር ከፍተኛ ትርጉም ያላቸውን ቅርሶችን መጠበቅ እና መንከባከብ ላይ በትኩረት ይሰራል ብለዋል።
የኢትዮጵያ ቅርስ ባለስልጣን የባለሙያዎች ቡድን በማዋቀር በኮሪደር ልማቱ የሚፈርሱ ቤቶች ላይ የክትትልና የቁጥጥር ስራ እየሰራ ይገኛል ማለታቸውን ከኢቲቪ ያገኘነው መረጃ ያሳያል።

ዜና: #ኢትዮጵያ እና #ፑንትላንድ ዘርፈ ብዙ ያሉትን ግንኙነታቸውን ለማሳደግ ተስማምተናል አሉ
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ምስጋናው አረጋ በፑንትላንድ ፋይናንስ ሚኒስትር ሞሃመድ ፋራህ ሞሃመድ የተመራ የሀገሪቱ ከፍተኛ የሚኒስትሮች ልዑክን በጽ/ቤታቸው ተቀብለው ማነጋገራቸው ተገለጸ።
በውይይታቸውም የሁለቱን ሀገራት ግንኙነት ለማስፋት እና ለማሳደግ በሚያስችሉ የንግድ፣ ኢንቨስትመንት፣ የሀይል አቅርቦት ትብብር እና የጋራ መሰረተ ልማት ላይ አተኩሮ መስራት እንደሚገባ መስማማታቸው ተጠቁሟል።
የፑንትላንድ ልዑክ ሀገራቸው ከኢትዮጵያ ጋር የቆየ የወንድማማችነት ግንኙነት እንዳላት አንስተው ኢትዮጵያ በጸጥታና በትምህርት ዘርፍ ድጋፍ እያደረገችልን ነው ሲሉ መግለጻቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባጋራው መረጃ ተካቷል።
በፑንትላንድ አዲስ የተመረጠው መንግስት ከኢትዮጵያ ጋር ያለውን ግንኙነት የማሳደግ ፍላጎት እንዳለው ልዑኩ ገልጿል ያለው የውጭ ጉዳይ ሚስቴር መረጃ በተለይም በንግድ፣ መሰረተ ልማት፣ በኢኮኖሚ ትብብር ዙሪያ ትኩረት ማድረግ እንፈልጋለን ማለቱንም አመላክቷል።
አምባሳደር ምስጋናው አረጋ በበኩላቸው ኢትዮጵያ ከፑንትላንድ ጋር ያላትን ዘርፍ ብዙ ትብብሮች ለማጠናከር ቁርጠኛ መሆኗን ገልፀዋል ብሏል፡፡
የፑንትላንድ መንግስት በቅርቡ ያካሄደውን ሰላማዊ ምርጫ አድንቀው እንኳን ደስ ያላችሁም ማለታቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያሳያል።
================
የአዲስ ስታንዳርድ አማርኛ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን ይቀላቀሉ፡
ቴሌግራም: https://rb.gy/rekjr
ፌስቡክ: https://rb.gy/xwxb3
ትዊተር (X)፡ https://rb.gy/34uh4
ድረገጽ: https://rb.gy/5td6n
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ምስጋናው አረጋ በፑንትላንድ ፋይናንስ ሚኒስትር ሞሃመድ ፋራህ ሞሃመድ የተመራ የሀገሪቱ ከፍተኛ የሚኒስትሮች ልዑክን በጽ/ቤታቸው ተቀብለው ማነጋገራቸው ተገለጸ።
በውይይታቸውም የሁለቱን ሀገራት ግንኙነት ለማስፋት እና ለማሳደግ በሚያስችሉ የንግድ፣ ኢንቨስትመንት፣ የሀይል አቅርቦት ትብብር እና የጋራ መሰረተ ልማት ላይ አተኩሮ መስራት እንደሚገባ መስማማታቸው ተጠቁሟል።
የፑንትላንድ ልዑክ ሀገራቸው ከኢትዮጵያ ጋር የቆየ የወንድማማችነት ግንኙነት እንዳላት አንስተው ኢትዮጵያ በጸጥታና በትምህርት ዘርፍ ድጋፍ እያደረገችልን ነው ሲሉ መግለጻቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባጋራው መረጃ ተካቷል።
በፑንትላንድ አዲስ የተመረጠው መንግስት ከኢትዮጵያ ጋር ያለውን ግንኙነት የማሳደግ ፍላጎት እንዳለው ልዑኩ ገልጿል ያለው የውጭ ጉዳይ ሚስቴር መረጃ በተለይም በንግድ፣ መሰረተ ልማት፣ በኢኮኖሚ ትብብር ዙሪያ ትኩረት ማድረግ እንፈልጋለን ማለቱንም አመላክቷል።
አምባሳደር ምስጋናው አረጋ በበኩላቸው ኢትዮጵያ ከፑንትላንድ ጋር ያላትን ዘርፍ ብዙ ትብብሮች ለማጠናከር ቁርጠኛ መሆኗን ገልፀዋል ብሏል፡፡
የፑንትላንድ መንግስት በቅርቡ ያካሄደውን ሰላማዊ ምርጫ አድንቀው እንኳን ደስ ያላችሁም ማለታቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያሳያል።
================
የአዲስ ስታንዳርድ አማርኛ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን ይቀላቀሉ፡
ቴሌግራም: https://rb.gy/rekjr
ፌስቡክ: https://rb.gy/xwxb3
ትዊተር (X)፡ https://rb.gy/34uh4
ድረገጽ: https://rb.gy/5td6n
ዜና: #የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ ባካሄደው መደበኛ ስብሰባ በሶስት ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳልፏል
የከተማ አስተዳደሩ ካቢኔ በ3ኛ ዓመት 11ኛ መደበኛ ስብሰባ ለከተማዋ ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ አቅም ጉልህ ሚና አላቸው ባላቸው ጉዳዮች ዙሪያ ትላንት መጋቢት 25 ቀን 2016 ዓ.ም ተወያይቶ ማጽደቁን ከከንቲባ ጽ/ቤት ያገኘነው መረጃ ያሳያል።
ካቢኔው ካጸደቃቸው ጉዳዮች መካከል አንደኛው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የከተማዋን የተሽከርካሪ አስተዳደር ህግ እና ሥርዓት ለማስከበር የከተማ አስተዳደሩ ባወጣው የተሽከርካሪ ማቆሚያ አገልግሎት አሰጣጥ ረቂቅ ደንብን ለአሰራር በሚያመች መልኩ ሀሳብ ተሰጥቶበት ደንቡ ፀድቋል።
ሌላኛው ካቢኔው የተወያየው የከተማዋን ስታንዳርድ እና መዋቅራዊ ፕላን ለማስጠበቅ እንዲሁም መልሶ ማፍረስ እንዳይገጥም፤ ግንባታዎች ከመንገድ ያላቸው ርቀት ከዚህ በኋላ ወጥነት ያለው የከተማ አሰራር አንዲኖር በማሰብ ከመንገድ መራቅ ያለባቸውን 3 ደረጃዎች ለማውጣት በቀረበው መተዳደሪያ ደንብ ላይ ነው።
ከአሁን በኋላ የሚገነቡ ማንኛውም ግንባታዎች ከዋና ከመንገድ በ10 ሜትር ርቀት መሆን እንደሚገባው ፤ ከንዑስ ዋና መንገድ 5 ሜትር ርቀት፤ ሰብሳቢ መንገድ ደግሞ 3 ሜትር ርቀት በተጨማሪም የውስጥ ለውስጥ መንገድ 2 ሜትር ርቀት መጠበቅ እንዳለባቸው ካቢኔው ተወያይቶ ውሳኔ አሳልፏል።
ሶስተኛው የውይይት ነጥብ ደግሞ የነገዋ የሴቶች ተሀድሶ እና ክህሎት ማበልፀጊያ ማዕከል ማቋቋሚያ ደንብ የተመለከተ ነበር። ማዕከሉን በተለይም ለጎዳና ህይወት፣ ለፆታዊ ጥቃት ሰለባ እና ለወሲብ ንግድ ተጋላጭ ለሆኑ ሴቶች መጠለያ፣ ማገገሚያ ማዕከል እንዲሆን ለማስቻል በሚያግዘው ማቋቋሚያ ደንብ ላይ ካቢኔው ተወያይቶ አጽድቋል።

ዜና: #በአማራ ክልል “የመንግስት የጸጥታ ሀይሎች ግድያ እየፈጸሙ በመሆኑ ከሰላም ማስከበር ተግባር ሊታገዱ ይገባዋል” - ሂዩማን ራይት ዎች
አለም አቀፉ የሰብአዊ መብት ተቆርቋሪው ተቋም ሂዩማን ራይት ዎች ዛሬ መጋቢት 26 ቀን 2016 ዓ.ም ባወጣው መግለጫ በአማራ ክልል “የሀገሪቱ መከላከያ ሰራዊት በደርዘኖች የሚቆጠሩ ሰዎችን ገድሏል” ሲል ከሷል፤ በመርአዊ የተፈጸመውን ግድያ በማሳያነት አቅርቧል።
#የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን በአማራ ክልል የተፈጸመውን የንጹሃን ግድያ በተመለከተ ገለልተኛ ምርመራ እንዲያካሂድ ጠይቋል።
የመንግስታቱ ድርጅትም ሆነ #የአፍሪካ ህብረት “የፌደራል መንግስቱ የጸጥታ ሀይሎችን በሰላም ማስከበር ተግባር ላይ እንዲሳተፉ ከማድረግ ለግዜው መቆጠብን አማራጭ እንዲያደርጉ” ሲል አሳስቧል።
https://wp.me/pfjhHd-150

በአማራ ክልል “የመከላከያ ሰራዊት አባላት ግድያ እየፈጸሙ በመሆኑ ከሰላም ማስከበር ተግባር ሊታገዱ ይገባዋል” - ሂዩማን ራይት ዎች - Addis standard
አዲስ አበባ፣ መጋቢት 26/2016 ዓ.ም፡- አለም አቀፉ የሰብአዊ መብት ተቆርቋሪው ተቋም ሂዩማን ራይት ዎች ዛሬ መጋቢት 26 ቀን 2016 ዓ.ም ባወጣው መግለጫ በአማራ ክልል “የሀገሪቱ መከላከያ ሰራዊት በደርዘኖች የሚቆጠሩ ሰዎችን ገድሏል” ሲል ከሷል። በመርአዊ የተፈጸመውን ግድያ በማሳያነት አቅርቧል። የመከላከያ ሰራዊቱ አባላት ከፋኖ ሀይሎች ጋር በሚያካሂዱት ውጊያ ንጹሃን ተገድለዋል ሲል ገልጿል።…
ዜና: በቀጣይ 4 አመታት የሚተገበር አዲስ ሀገራዊ #የኤችአይቪ/ኤድስ መከላከል እና መቆጣጠር ስትራቴጂክ እቅድ ይፋ ተደረገ
በቀጣይ 4 አመታት #በኢትዮጵያ የሚተገበር አዲስ ሀገራዊ የኤችአይቪ/ኤድስ መከላከል እና መቆጣጠር ስትራቴጂክ እቅድ (HIV/AIDS National Strategic Plan 2023/24-2026/7) ይፋ መደረጉ ተገለጸ።
ከጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ እንደሚያሳየው የስትራቴጂክ እቅዱ ዋና ግብ ለቀጣይ አራት አመታት የኤችአይቪ ስርጭትን ለመቆጣጠር እና ለመቀነስ ያለመ ነው።
በተጨማሪም አዳዲስ በኤችአይቪ የመያዝ እና የሞት ምጣኔ በመቀነስ በአገር አቀፍ ደረጃ በ10,000 ሕዝብ ከ1 በታች ለማድረስ መሆኑን አመላክቷል።
በስትራቴጂክ እቅድ ዝግጅት ሂደቱ ላይ ሁሉም ባለድርሻ አካላት እንዲሁም ዓለም አቀፍ እና የሀገር ውስጥ አማካሪዎች እንደተሳተፉበት ጠቁሟል።
https://wp.me/pfjhHd-156

በቀጣይ 4 አመታት የሚተገበር አዲስ ሀገራዊ የኤችአይቪ/ኤድስ መከላከል እና መቆጣጠር ስትራቴጂክ እቅድ ይፋ ተደረገ - Addis standard
ዜና: በቀጣይ 4 አመታት የሚተገበር አዲስ ሀገራዊ የኤችአይቪ/ኤድስ መከላከል እና መቆጣጠር ስትራቴጂክ እቅድ ይፋ ተደረገ አዲስ አበባ፣ መጋቢት 26/2016 ዓ.ም፡- በቀጣይ 4 አመታት የሚተገበር አዲስ ሀገራዊ የኤችአይቪ/ኤድስ መከላከል እና መቆጣጠር ስትራቴጂክ እቅድ (HIV/AIDS National Strategic Plan 2023/24-2026/7) ይፋ መደረጉ ተገለጸ። ከጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ…
ዜና: #ሶማሊያ የኢትዮጵያ አምባሳደርን አባረረች፣ #በፑንትላንድ እና #ሶማሊላንድ የሚገኙ የኢትዮጵያ ቆንስላ ጽ/ቤቶችን እንዲዘጉ አድርጋለች
የሶማሊያ መንግስት በሀገሩ #የኢትዮጵያ አምባሳደርን ሙክታር ሞሃመድ ዋሬ ማባረሩን ምንጮቹን ዋቢ በማድረግ ሮይተርስ የዜና ወኪል አስታወቀ።
ከሀገራቸው መንግስት ጋር እንዲመክሩ በሚል ሞቃዲሾን ለቀው እንዲወጡ ተደርገዋል ያለው ዘገባው በተጨማሪም የሶማሊያ መንግስት በሶማሊላንድ ዋና ከተማ #ሀርጌሳ እና በፑንትላንድ የሚገኙትን ቆንስላ ጽ/ቤቶችን እንዲዘጉ ማድረጓንም ጠቁሟል።
ሶማሊያ የኢትዮጵያ አምባሳደር የሆኑትን ሙክታር ሞሃመድ ዋሬ ከሞቃዲሾ ያባረረችው ዛሬ መጋቢት 26 ቀን 2016 ዓ.ም መሆኑን ሁለት የሶማሊያ መንግስት ባለስልጣናት እንደነገሩት አስታውቋል።
የሶማሊያ መንግስት በሶማሊላንድ ዋና ከተማ ሀርጌሳ እና በፑንትላንድ የሚገኙትን ቆንስላ ጽ/ቤቶችን እንዲዘጉ የማድረግ ስልጣን እንዳለው የታወቀ ነገር የለም።
ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ምንጮች ለአዲስ ስታንዳርድ እንደገለጹት አምባሳደር ሙክታር እስካሁን በይፋ ከሶማሊያ መንግስት የተገለጸላቸው ነገር የለም፤ በጉዳዩ ዙሪያም የሶማሊያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ያወጣው መግለጫ የለም።
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ምስጋናው አረጋ በፑንትላንድ ፋይናንስ ሚኒስትር ሞሃመድ ፋራህ ሞሃመድ የተመራ የሀገሪቱ ከፍተኛ የሚኒስትሮች ልዑክን በጽ/ቤታቸው ተቀብለው ማነጋገራቸውን ትላንት መጋቢት 25 ቀን 2016 ዓ.ም መዘገባችን ይታወሳል።