ዜና: ምክር ቤቱ የግል #ዳታ ጥበቃ ረቂቅ አዋጅን አጸደቀ
የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ባካሄደው 20ኛ መደበኛ ስብሰባው የግል ዳታ ጥበቃ ረቂቅ አዋጅን አስመልክቶ የቀረበለትን ሪፖርትና የውሳኔ ሀሳብ መርምሮ አጽድቋል።
ሪፖርትና የውሳኔ ሀሳቡን የሰው ሀብት ልማት፣ ስራ ስምሪት እና ቴክኖሎጂ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ የተከበሩ ነገሪ ሌንጮ (ዶ/ር) ለምክር ቤቱ አቅርበዋል፡፡
በሪፖርታቸውም ረቂቅ አዋጁ ለዝርዝር እይታ ለቋሚ ኮሚቴው ከተመራ ከህዳር ወር 2016 ዓ.ም. ጀምሮ በርካታ ሂደቶችን ማለፉንና ጠቃሚ ግብአቶች የተገኙበት መሆኑን አስታውሰው፤ ግብአቶቹን ማካተትና ማሻሻያዎችን ማድረግ እንዲሁም አሻሚ ትርጉም ያላቸውን ቃላቶች ግልጽ ማድረግ በማስፈለጉ አዋጁን ማሻሻል አስፈልጓል ብለዋል፡፡
የግል ዳታ ጥበቃ ተቆጣጣሪ ተቋምን በመሠየም ጠንካራ የግል ዳታ ጥበቃ ሥርዓት እንዲፈጠር ማድረግ ወሳኝ መሆኑን፤ እንዲሁም ዳታ በሚሰበሰብበትና በሚቀናበርበት ወቅት የግል ዳታ ጥሰት እንዳይፈጠር መቆጣጠር የሚያስችል የግል ዳታ ጥበቃ አዋጅ ማውጣት አስፈሊጊ ሆኖ መገኘቱንም አስገንዝበዋል፡፡
ከግል ዳታ ጋር የተያያዙ የመብት ጥሰቶች ሲከሰቱ ውጤታማ መፍትሄዎችን መስጠት፣ ከዳታ ማቀናበር ሥራዎች ጋር የተያያዙ አደጋዎችን መቀነስ እና ኃላፊነት የሚሰማው የዳታ ማቀናበር ባህልን ማሳደግ ወሳኝነት ያለው መሆኑን እና በኢትዮጵያ የግል ዳታ ጥበቃ ሥርዓት ዓለማቀፋዊ ደረጃዎችን በጠበቀ መልኩ ለመገንባት አዋጁን ማውጣት አስፈላጊ ሆኖ መገኘቱ የሚሉት ነጥቦች በጭብጥነት መለየታቸውንም አንስተዋል፡፡
በመጨረሻም ምክር ቤቱ በግል ዳታ ጥበቃ ረቂቅ አዋጅ ላይ በጥልቀት ከተወያየ በኋላ ረቂቅ አዋጁን በአንድ ተቃውሞና በአብላጫ ድምጽ አዋጅ ቁጥር 1321/2016 አድርጎ አጽድቆታል፡፡

ዜና: በፍኖተሰላም ከተማ የመማሪያ ክፍል ዉስጥ ፈተና በሚፈተኑ ተማሪዎች ላይ በተጣለ #ቦምብ በተማሪዎች ላይ ጉዳት መድረሱ ተገለጸ
#በፍኖተሰላም ከተማ በዳሞት መሰናዶ ቁጥር 1 ትምህርት ቤት ላይ ፈተና በመውሰድ ላይ በነበሩ ተማሪዎች ክፍል ውስጥ በተጣለ ቦንም በርካታ ተማሪዎች መጎዳታቸው ተገለጸ።
በደረሰው ጥቃት 25 ተማሪዎች ጉዳት የደረሰባቸው መሆኑን እና ከነዚህም ውስጥ አራቱ ከፍተኛ ጉዳት እንደደረሰባቸው #ከአማራ ክልል ኮሙዩኒኬሽን ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያሳያል። የፍኖተ ሰላም ከተማ ፖሊስ ጽ/ቤት በበኩሉ በተፈፀመ የቦምብ ጥቃት ጉዳት የደረሰባቸው ተማሪዎች ቁጥር 31 መድረሱን ጠቁሟል።
ከፍተኛ ጉዳት ከደረሰባቸው ተማሪዎች ውስጥ ሁለቱ ተማሪዎች ለከፍተኛ ህክምና ሪፈር መባላቸውን የጠቆመው የክልሉ ኮሙዩኒኬሽን መረጃ ፖሊስ ፍንዳታውን ያደረሰውን ተጠርጣሪ በቁጥጥር ስር ማዋሉን አስታውቋል።
ፍንዳታውን ያደረሰው ተጠርጣሪ ዮሃንስ ተስፋየ ሹመት የሚባል መሆኑን ፖሊስ አረጋግጧል ያለው የክልል መረጃ ተጠርጣሪው እጁ እና እግሩ ላይ ቆስሎ ተይዟል ብሏል።
================
የአዲስ ስታንዳርድ አማርኛ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን ይቀላቀሉ፡
ቴሌግራም: https://rb.gy/rekjr
ፌስቡክ: https://rb.gy/xwxb3
ትዊተር (X)፡ https://rb.gy/34uh4
ዩቲዩብ፡ https://rb.gy/bjcbg
ድረገጽ: https://rb.gy/5td6n
ቲክቶክ፡https://rb.gy/3bghek

በ #ትግራይ ክልል ውዝፍ የጡረታ አበል ክፍያ መጀመሩ ተገለጸ
በትግራይ ክልል ውዝፍ የጡረታ አበል ክፍያ መጀመሩን የመንግስት ሰራተኞች ማህበራዊ ዋስትና አስተዳደር አስታወቀ።
በክልሉ 65 ሺህ 873 ከሚሆኑት ውዝፍ የጡረታ አበል ተከፋዮች 90 በመቶ የሚሆኑት መረጃዎች ተጣርተው ከትላንት መጋቢት 26/ 2016 ጀምሮ የ17 ወር ክፍያ እንዲፈጸም 1 ነጥብ 3 ቢሊየን ብር ተለቋል ተብሏል።
የመንግስት ሰራተኞች ማህበራዊ ዋስትና አስተዳደር ዋና ስራ አስፈጻሚ ዳባ ኦሪያ መረጃዎች ተጣርተው በአጭር ጊዜ ይከፈላል ሲሉ ገልጸዋል።
በዚህ መሰረት ከተጠቀሱት የዋና ባለመብቶች ትንሹ ውዝፍ ክፍያ 24 ሺህ 266 ሲሆን፤ ትልቁ ክፍያ 349 ሺህ 596 ብር መሆኑ ተመላክቷል፡፡
በክልሉ ካሉት አጠቃላይ የጡረታ አበል ተከፋይ 5 ሺህ የሚሆኑት ከፕሪቶሪያው ስምምነት በኋላ ወደ ጡረታ ስርአት የገቡ በመሆኑ ክፍያቸው ያልተቋረጠና አሁን እየተከፈላቸው ነው ተብሏል፡፡
ተተኪ የሚባሉ ወይም ወራሾች በ17 ወር ውስጥ እድሜያቸው ህጉ በሚጠይቀው መሰረት የስንት ወር ይደርሳቸዋል የሚለው እየተጣራ መሆኑንም ተናግረዋል፡፡
በፍርድ ቤት ሂደት ላይ የሚገኙና ውሳኔ ያገኙ በሚቀርቡ ማስረጃዎች መሰረት ክፍያው የሚፈጸም እንደሚሆንም ተመላክቷል፡፡
ይህ በእንዲህ እንዳለ ማንኛውም ጥያቄዎች በትግራይ ክልል #አዲግራት፣ #አክሱም፣ #እንደስላሴ ፣ #ማይጨውና #መቀሌ ቅርንጫፍን ጨምሮ በሀገሪቱ በሚገኙ ከ70 በላይ ቅርጫፎች ከቀረቡ ታይተው ምላሽ የሚያገኙበት ሁኔታም ተመቻችቷል መባሉን ፋና ዘግቧል፡፡

የ #ሶማሊላንድ እና #ፑንትላንድ ባለሥልጣናት #ሶማሊያ መንግስት የ #ኢትዮጵያ ቆንስላ ለመዝጋት የሰጠውን ማስጠንቀቂያ ውድቅ አደረጉ
የሶማሊላንድ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ሮዳ ኤልሚ፤ የሶማሊላንድ የመረጃ፣ የባህልና ብሔራዊ መመሪያ ሚኒስትር አሊ ሀሰን ሞሃመድ እና የፑንትላንድ የመረጃ ሚኒስትር ማህሙድ አይዲድ ዲሪር የሶማሊያ መንግስት በሶማሊላንድ መዲና #ሃርጌሳ እና በፑንትላንድ #ጋሮዌ የሚገኙትን የኢትዮጵያ ቆንስላ ጽ/ቤቶች እንዲዘጉ የሰጠውን ማስጠንቀቂያ ውድቅ አድርገዋል።
በትላንትናው ዕለት የሶማሊያ መንግስት በ #ሞቃዲሾ የሚገኙት የኢትዮጵያ አምባሳደር ሙክታር ሞሃመድ ዋሬ በ72 ሰዓት ውስጥ ሶማሊያን ለቀው እንዲወጡ ያዘዘ ሲሆን ሲሆን በተጨማሪም በኢትዮጵያ የሚገኙትን አምባሳደሩን ለምክክር በሚል መጥራቱን አስታውቋል።
ከዚህ በተጨማሪም፤ የሶማሊያ መንግስት በሶማሊላንድ ዋና ከተማ #ሀርጌሳ እና በፑንትላንድ ጋሮዌ ከተማ የሚገኙትን ቆንስላ ጽ/ቤቶች በሰባት ቀናት ውስጥ ይዘጋሉ ብሏል።
ይሁን እንጂ አምባሳደር ሮዳ ከቪኦኤ ሶማሊ ጋር ባደረጉት አጭር ቃለ መጠይቅ፤ (የሶማሊያ) ውሳኔው፤ "በህልም" ላይ የተመሰረተ እና "ጥቅም የሌለው" ነው ብለዋል።
የሶማሊላንድ የመረጃ፣ የባህልና ብሔራዊ መመሪያ ሚኒስትር አሊ ሀሰን ሞሃመድ በበኩላቸው በሰጡት መግለጫ፤ በሶማሊላንድ “የኢትዮጵያ ኢምባሲ በሶማሊ ላንድ ከመነሻው በሶማሊያ ፍቃድ አይደለም የተከፈተው፤ ስለዚህ ሞቃዲሾ ባለመፈቀዷ አይዘጋም” ሲሉ ለሶማሊያ ምላሽ ሰጥተዋል።
በተመሳሳይ መልኩ፤ የፑንትላንዱ ማህሙድ አይዲድ የሶማሊያ መንግስት በጋሮዌ የሚገኘውን የኢትዮጵያ ቆንስላ ለመዝጋት "የሚያስችል ስልጣን የለውም" ብለዋል።

#ኢትዮጵያ እና #የዓለም_ባንክ የ1 ነጥብ 72 ቢሊየን ዶላር የድጋፍ እና የብድር ስምምነት ተፈራረሙ
ኢትዮጵያ እና የዓለም ባንክ የ1 ነጥብ 72 ቢሊየን ዶላር የድጋፍ እና የብድር ስምምነት መፈራረማቸውን ገንዘብ ሚኒስቴር አስታወቀ።
በገንዘብ ሚኒስትሩ አሕመድ ሺዴ እና በዓለም ባንክ የኢትዮጵያ ዳይሬክተር ኦስማን ዲዮን በኩል የተፈረመው የብድር እና የድጋፍ ስምምነቱ በኢትዮጵያ ዘላቂ ልማትን ለማረጋገጥ የሚውሉ ስድስት ፕሮጀክቶችን ለመተገበር እንደሚውል ተገልጿል፡፡
ከተደረገው ድጋፍ ውስጥ 300 ሚሊየን ዶላር የሚሆነው በገጠር አካባቢዎች የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ የሚደረገው ጥረት ማሳለጥ ለሚያስችል የመንገድ መሰረት ልማት ግንባታ እንደሚውል ተገልጿል፡፡
200 ሚሊየን ዶላሩ ደግሞ በኢትዮጵያ እየተተገበረ የሚገኘውን የሴፍቲ ኔት ፕሮግራም ለማጠናከር እና ለማስፋፋት የሚውል ነወ ተብሏል።
በተመሳሳይ ከተሰጠው ብድር ውስጥ 340 ሚሊየን የሚሆነው በኢትዮጵያ ቆላማ አካባቢዎች የሚኖሩ አርብቶ አደር እና ከፊል አርብቶ አደር የማህበረሰብ ክፍሎችን የኑሮ ሁኔታ ለማሻሻል እንደሚውል ተጠቅሷል፡፡
522 ነጥብ 6 ሚሊየን ዶላር በላይ የሚሆነው ደግሞ በኢትዮጵያ የኤሌክትሪክ ሃይል ተደራሽነትን ለማስፋት እና ታዳሽ ሃይል ማመንጨት የሚቻልበትን ሁኔታ ለመደገፍ እንደሚውል የተገለጸ ሲሆን 275 ሚሊየን ዶላር የሚሆነው ደግሞ በኢትዮጵያ ከተሞች የንጹህ መጠጥ ውሃ አቅርቦትን እና ተደረሽነትን ለማስፋት ስራ ይውላል ትብሏል።

ዜና፡ በ #ትግራይና #አማራ አዋሳኝ አካባቢዎች መከላከያ ሰራዊት ሰላም እና ደህንነት የማስጠበቅ ኃላፊነቱን ይወስዳል – የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት
የፌዴራል መንግስት፤ በትግራይ እና አማራ አዋሳኝ አካባቢዎች “የወሰን እና የማንነት” ጥያቄዎች በህዝበ ውሳኔ እልባት እስኪያገኙ ድረስ የ #ኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ከአካባቢው መህበረሰብ ጋር በመሆን ሰላም እና ደህንነት እንደሚቆጣጠር ገለጸ።
“ከሰሞኑ በትግራይ ክልል በኩል በአማራ ክልል አዋሳኝ አካባቢዎች የሚታየው አዝማሚያ ተገቢነት የሌለው ብቻ ሳይኾን የፕሪቶሪያውን ስምምነት የሚጥስ ነው” ሲሉ የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትሩ ለገሰ ቱሉ (ዶ.ር) በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ በሰጡት መግለጫ ተናግረዋል።
ሚኒስትሩ አክለውም፤ የሚነሱ ጥያቄዎችን እና የሚያጋጥሙ ችግሮችን በውይይት እና በድርድር ከመፍታት ይልቅ “ወሰንን በኃይል እናስከብራለን የሚል አካሄድ ካለፈው ስሕተት አለመማርን ያመለክታል” ብለዋል፡፡
ተጨማሪ ይመልከቱ፡ https://wp.me/pfjhHd-15e

Addis standard
በትግራይ እና አማራ አዋሳኝ አካባቢዎች መከላከያ ሰራዊት ሰላም እና ደህንነት የማስጠበቅ ኃላፊነቱን ይወስዳል - የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት - Addis standard
አዲስ አበባ፣ መጋቢት 27/ 2016 ዓ/ም፦ የፌዴራል መንግስት ትላንት በሰጠው መግለጫ ፤ በትግራይ እና አማራ አዋሳኝ አካባቢዎች “የወሰን እና የማንነት” ጥያቄዎች በህዝበ ውሳኔ እልባት እስኪያገኙ ድረስ የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ከአካባቢው መህበረሰብ ጋር በመሆን ሰላም እና ደህንነት እንደሚቆጣጠር ገለጸ። የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትሩ ለገሰ ቱሉ (ዶ.ር) በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ በሰጡት…
ከ #አማራ ክልል ወደ #ኦሮሚያ ክልል የተመለሱት ተፈናቃዮች አሁንም ድረስ ችግር ላይ መሆናቸውን ገለፁ
የመንግስትን ጥሪ ተቀብለው ከአማራ ክልል ወደ ምስራቅ ወለጋ ዞን ኦሮሚያ ክልል የተመለሱት ተፈናቃዮች አሁንም በፀጥታ ችግር ሳቢያ ወደ ቤታቸው መመለስ አለመቻላቸውን ለዶቼ ቬለ ገልፀዋል።
ተመላሽ ተፈናቃዮቹ እንደገለፁት አብዛኛው ተመላሽ የሚገኘው በከተማ ውስጥ በተዘጋጀ ጊዜያዊ መጠለያ ጣቢያ ነው።
እነዚህ ተፈናቃዮች የፌደራል እና የክልል መንግስታትን ጥሪ ተቀብለው ከአንድ ወር በፊት ነበር ለበርካታ ጊዜ ተጠልለው ከነበሩበት ደብረ ብርሃን ከተማ ወደ ምስራቅ ወለጋ ዞን የተመለሱት።
ከኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ወለጋ ዞን ተፈናቅለው በአማራ ክልል ሀርቡ እና ጃራ መጠለያ ጣቢያ ከነበሩት ተፈናቃዮች መካከል ወደ 315 የሚደርሱ ተፈናቃዮች ከሁለት ወር ገደማ በፊት ወደ ጊምቢ ወረዳ መመለሳቸው ይታወሳል።
ዶቼ ቬለ
================
የአዲስ ስታንዳርድ አማርኛ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን ይቀላቀሉ፡
ቴሌግራም: https://rb.gy/rekjr
ፌስቡክ: https://rb.gy/xwxb3
ትዊተር (X)፡ https://rb.gy/34uh4
ዩቲዩብ፡ https://rb.gy/bjcbg
ድረገጽ: https://rb.gy/5td6n
ቲክቶክ፡https://rb.gy/3bghek
የመንግስትን ጥሪ ተቀብለው ከአማራ ክልል ወደ ምስራቅ ወለጋ ዞን ኦሮሚያ ክልል የተመለሱት ተፈናቃዮች አሁንም በፀጥታ ችግር ሳቢያ ወደ ቤታቸው መመለስ አለመቻላቸውን ለዶቼ ቬለ ገልፀዋል።
ተመላሽ ተፈናቃዮቹ እንደገለፁት አብዛኛው ተመላሽ የሚገኘው በከተማ ውስጥ በተዘጋጀ ጊዜያዊ መጠለያ ጣቢያ ነው።
እነዚህ ተፈናቃዮች የፌደራል እና የክልል መንግስታትን ጥሪ ተቀብለው ከአንድ ወር በፊት ነበር ለበርካታ ጊዜ ተጠልለው ከነበሩበት ደብረ ብርሃን ከተማ ወደ ምስራቅ ወለጋ ዞን የተመለሱት።
ከኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ወለጋ ዞን ተፈናቅለው በአማራ ክልል ሀርቡ እና ጃራ መጠለያ ጣቢያ ከነበሩት ተፈናቃዮች መካከል ወደ 315 የሚደርሱ ተፈናቃዮች ከሁለት ወር ገደማ በፊት ወደ ጊምቢ ወረዳ መመለሳቸው ይታወሳል።
ዶቼ ቬለ
================
የአዲስ ስታንዳርድ አማርኛ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን ይቀላቀሉ፡
ቴሌግራም: https://rb.gy/rekjr
ፌስቡክ: https://rb.gy/xwxb3
ትዊተር (X)፡ https://rb.gy/34uh4
ዩቲዩብ፡ https://rb.gy/bjcbg
ድረገጽ: https://rb.gy/5td6n
ቲክቶክ፡https://rb.gy/3bghek
ርዕስ አንቀጽ: #በአዲስ አበባ ግዜውን ያልጠበቀና ያለበቂ ዕቅድ እየተተገበረ የሚገኘው ከተማዋን የማነጽ ስራ አቅመ ዳካሞች ላይ ጫና ፈጥሯል፣ ቢያንስ ሂደቱ ሰብአዊነትን ሊላበስ ይገባዋል!!
የገዢው ፓርቲ ብልጽግና ባለስለጣናት አዲስ አበባ በከንቲባዋ አዳነች አቤቤ አማካኝነት በታሪኳ አይታው በማታውቀው ሁኔታ እየተለወጠች ትገኛለች በሚል በኩራት ሲናገሩ ይደመጣል።
ባለስልጣናቱ ከሚያነሷቸው ነጥቦች መካከል በቅርቡ በከተማዋ በተለዩ አምስት የመንገድ ኮሪደሮች ከ40 ኪሎሜትር በላይ በመገንባት ላይ ያለውን ከተማዋን የማሰዋብ ስራ ይጠቅሳሉ፤ መዲናዋን ዘመናዊ በማድረግ እንደ ስሟ አዲስ አበባ እንድትሆን እና ለነዋሪዎቿ ምቹ የማድረግ ስራ ነው ሲሉ ይደመጣል።
ከተማዋን የተመቸች ለማድረግ የሚደረገው ጥረት ግን በማፍረስ ላይ የተመሰረተ ሁኗል፤ የከተማዋን ነዋሪዎች በሚያሳምም ሁኔታ በብርሃን ፍጥነት እየተተገበረ ነው፣ መኖሪያ ቤቶች፣ የንግድ ተቋማት እና የአምልኮ ስፍራዎች በማፈራረስ።
የመንገድ ኮሪደር ልማቱ ቁጥር ስፍር የሌላቸውን በአራት ኪሎ፣ #መገናኛ፣ #ሲኤምሲ እና መሰል ቦታዎች የሚገኙ አነስተኛ ንግድ ስራዎችን ማስተጓጎሉ አይቀሬ ነው። የዚህ ኢኮኖሚያዊ አንድምታ ከንግድ ባለቤቶች በላይ የሚዘልቅ ሲሆን ከከተማው ርቀው የሚገኙትን ቤተሰቦቻቸውንም በር ማንኳኳቱ የማይቀር ነው።
ይህ ሁሉ ደግሞ በአንድ ሳምንት ሲተገበር የሚያመጣው ጣጣ ብዙ ነው፤ በየጊዜው የሚስተጓጎሉ አቅርቦቶችን ጨምሮ በአስደንጋጭ የዋጋ ግሽበት በመታመስ ላይ ላለችው አዲስ አበባ ተጽእኖው ለቀጣይ አመታት የሚንከባለል ይሆናል።
60 በመቶ የሚሆነው ህዝቡ በከፋ ድህነት ውስጥ ለሚኖርበት መንግስት፣ ከተማ ማስዋብ ቀዳሚ ተግባሩ መሆን አልነበረበትም። በአሁኑ ወቅት ኢትዮጵያ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተባባሰ ለመጣው የሰብዓዊ ቀውስ ምላሽ ለመስጠት ወደ አንድ ቢሊዮን ዶላር የሚጠጋ የገንዘብ እጥረት ገጥሟታል።
ለቤት ፈረሳ፣ ለካሳ ክፍያ እና ለመንገድ ኮሪደሮች ግንባታ የተመደበው በጀት በሌሎች የሀገሪቱ ክፍሎች በሞት አፋፍ ላይ የሚገኙትን በሺዎች የሚቆጠሩ የድርቅ ተጎጂዎችን ለመርዳት ጥቅም ላይ ሊውል በቻለ ነበር።
ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጠቀሙ https://wp.me/pfjhHd-15j

በአዲስ አበባ ግዜውን ያልጠበቀና ያለበቂ ዕቅድ እየተተገበረ የሚገኘው ከተማዋን የማነጽ ስራ አቅመ ዳካሞች ላይ ጫና ፈጥሯል፣ ቢያንስ ሂደቱ ሰብአዊነትን ሊላበስ ይገባዋል - Addis standard
የገዢው ፓርቲ ብልጽግና ባለስለጣናት አዲስ አበባ በከንቲባዋ አዳነች አቤቤ አማካኝነት በታሪኳ አይታው በማታውቀው ሁኔታ እየተለወጠች ትገኛለች በሚል በኩራት ሲናገሩ ይደመጣል። ባለስልጣናቱ ከሚያነሷቸው ነጥቦች መካከል በቅርቡ በከተማዋ በተለዩ አምስት የመንገድ ኮሪደሮች ከ40 ኪሎሜትር በላይ በመገንባት ላይ ያለውን ከተማዋን የማሰዋብ ስራ ይጠቅሳሉ፤ መዲናዋን ዘመናዊ በማድረግ እንደ ስሟ አዲስ አበባ እንድትሆን…
ተቋርጦ የነበረው የደብረብርሃን_ደሴ የፌደራል መንገድ ከዛሬ ጀምሮ ለተጓዦች ክፍት መደረጉን የማዕከላዊ ሸዋ ኮማንድ ፖስት ገለፀ
"ከፀጥታ ችግር" ጋር በተገናኘ ተቋርጦ የነበረው የደብረብርሃን_ደሴ የፌደራል መንገድ ትራንስፖርት ከዛሬ መጋቢት 28 ቀን 2016 ጀምሮ ለተጓዦች ክፍት መደረጉን የማዕከላዊ ሸዋ ኮማንድ ፖስት አስታውቋል።
መንገዱ ክፍት የተደረገው፤ "የቀጠናው የሰላም ሁኔታ ካሳየው መሻሻልና ከህብረተሰቡ ጥያቄ በመነሳት" መሆኑን ገልጿል።
ኮማንድ ፖስቱ፤ ህብረተሰቡ ለፀጥታ አካላት የሚያደርገውን ድጋፍና "የጥፋት ሀይሎችን" ወደ ተጠያቂነት እንዲቀርቡ የሚሰራውን ስራ አሁን በጀመረው መንገድ አጠናክሮ እንዲቀጥልም አሳስቧል።
"የሰላም መደፍረስና ቀውስን ምቹ የመኖሪያ እድል የሚያደርገው ሰላም ጠል ሀይል" ዳግም የማተራመስ እድል ሊኖረው በማይችልበት ሁኔታ የሰላም ማስከበር ስራውንም ከህዝቡ ጋር በመተባበር የሚሰራ ይሆናል ብሏል።
በአማራ ከልል ከደሴ- ሸዋሮቢት- ደ/ብረሀን እንዲሁም ከደ/ብረሀን -ሸዋሮቢት - ደሴ የትኛውም አይነት የትራንስፖርት እንቅስቃሴ የካቲት 16 ቀን ጀምሮ ላልተወሰነ ጊዜ እንዲቆም መደረጉ ይታወሳል።

ዜና: የፍቼ #ጫምባላላ የሲዳማ ዘመን መለዋጫ በዓል ከኩሽ ህዝቦች ስልጣኔ ጀምሮ በትውልድ ቅብብሎሽ እዚህ የደረሰ በዓል ነው - ቀጄላ መርዳሳ
የፍቼ ጫምባላላ #የሲዳማ ዘመን መለዋጫ በዓል ከኩሽ ህዝቦች ስልጣኔ ጀምሮ በትውልድ ቅብብሎሽ እዚህ የደረሰ በዓል ነው ሲሉ የኢፌዲሪ ባህል እና ስፖርት ሚንስቴር ሚኒስትር አቶ ቀጄላ መርዳሳ ገለጹ።
ሚንስቴሩ በፍቼ ጫምባላላ አከባበር በሚካሄድበት ጉዱማሌ አደባባይ በመገኘት መልዕክት አስተላልፈዋል።
የፍቼ ጫምባላላ የሲዳማ ዘመን መለዋጫ ነው በምንልበት ጊዜ በርካታ ነገሮችን በውስጡ ይዟል በማለት ከጥንት የኩሽ ህዝቦች ስልጣኔ ጀምሮ በትውልድ ቅብብሎሽ እዚህ የደረሰ በዓል መሆኑን አመላክተዋል።
ይሄንን ድንቅ በዓል ተንከባክበው እና ተቀብለው ለዛሬ ላደረሱ የስነ-ኳክብት ጠበብቶች (ለሲዳማ አያንቶዎች) ምስጋና አቅርበዋል።
የተፈጥሮ ስጦታዎች እንዲጠበቅ የሚያደርግ ድንቅ ባህል ነውም በማለት ይሄ ታላቅ በዓል እሴቶቹ ተጠብቀው ለትውልድ እንዲሸጋገር ባህሉን ሰንዶ በማስቀመጥ ረገድ የዘርፉ ምሁራኖች የድርሻቸው ሚና መጫወት አለባቸው ማለታቸውን ከደቡብ ሬድዮና ቴሌቪዥን ያገኘነው መረጃ ያሳያል።
================
የአዲስ ስታንዳርድ አማርኛ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን ይቀላቀሉ፡
ቴሌግራም: https://rb.gy/rekjr
ፌስቡክ: https://rb.gy/xwxb3
ትዊተር (X)፡ https://rb.gy/34uh4
ዩቲዩብ፡ https://rb.gy/bjcbg
ድረገጽ: https://rb.gy/5td6n
ቲክቶክ፡https://rb.gy/3bghek
የፍቼ ጫምባላላ #የሲዳማ ዘመን መለዋጫ በዓል ከኩሽ ህዝቦች ስልጣኔ ጀምሮ በትውልድ ቅብብሎሽ እዚህ የደረሰ በዓል ነው ሲሉ የኢፌዲሪ ባህል እና ስፖርት ሚንስቴር ሚኒስትር አቶ ቀጄላ መርዳሳ ገለጹ።
ሚንስቴሩ በፍቼ ጫምባላላ አከባበር በሚካሄድበት ጉዱማሌ አደባባይ በመገኘት መልዕክት አስተላልፈዋል።
የፍቼ ጫምባላላ የሲዳማ ዘመን መለዋጫ ነው በምንልበት ጊዜ በርካታ ነገሮችን በውስጡ ይዟል በማለት ከጥንት የኩሽ ህዝቦች ስልጣኔ ጀምሮ በትውልድ ቅብብሎሽ እዚህ የደረሰ በዓል መሆኑን አመላክተዋል።
ይሄንን ድንቅ በዓል ተንከባክበው እና ተቀብለው ለዛሬ ላደረሱ የስነ-ኳክብት ጠበብቶች (ለሲዳማ አያንቶዎች) ምስጋና አቅርበዋል።
የተፈጥሮ ስጦታዎች እንዲጠበቅ የሚያደርግ ድንቅ ባህል ነውም በማለት ይሄ ታላቅ በዓል እሴቶቹ ተጠብቀው ለትውልድ እንዲሸጋገር ባህሉን ሰንዶ በማስቀመጥ ረገድ የዘርፉ ምሁራኖች የድርሻቸው ሚና መጫወት አለባቸው ማለታቸውን ከደቡብ ሬድዮና ቴሌቪዥን ያገኘነው መረጃ ያሳያል።
================
የአዲስ ስታንዳርድ አማርኛ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን ይቀላቀሉ፡
ቴሌግራም: https://rb.gy/rekjr
ፌስቡክ: https://rb.gy/xwxb3
ትዊተር (X)፡ https://rb.gy/34uh4
ዩቲዩብ፡ https://rb.gy/bjcbg
ድረገጽ: https://rb.gy/5td6n
ቲክቶክ፡https://rb.gy/3bghek
በ #ጋምቤላ ክልል በታጣቂዎች በተፈጸመ ጥቃት 10 ሰዎች ሲሞቱ 19 ቆስለዋል
በጋምቤላ ክልል ትላንት አርብ #ፓንዪዱክ በሚባል የተፈናቃይ ካምፕ ላይ ማንነታቸው ባልታወቀ ታጣቂዎች በተፈጸመ ጥቃት 10 ሰዎች መሞታቸው እና 19 ሰዎች መቁሰላቸውን የካምፑ ኃላፊ ገለጹ።
ጥቃቱ ትላንት ሰስት ሰዓት ገደማ መፈጸሙን ለደቡብ ሱዳኑ “ሲቲ ሪቪው” የዜና ወኪል የገለጹት የካምፑ ኃላፊ ፒተር ሜከር፤ ጉዳት የደረሰባቸው ሰዎች አስቸኳይ የህክምና እርዳታ ለማግኘት ወደ ፓኒዲኩ ካምፕ ዋና ሆስፒታል ተወስደዋል ብለዋል።
ፒተር ሜከር፤ ወንጀለኞቹ ከ “ሙርሌ" ማህበረሰብ የመጡ የታጠቁ ወጣቶች ሊሆኑ ይችላሉ የሚል ጥርጣሬ እንዳላቸው ገልጸዋል። ታጣቂዎቹ ከጥቃቱ በኋላ ወደ #ፒቦር አስተዳደር ወደሆነው #ቦንጋክ መሸሻቸውን ገልጸዋል።
በካምፑ ውስጥ የፖሊስ አለመኖር ነዋሪዎቹ ለእንደዚህ ዓይነቱ ጥቃት ተጋላጭ እንዲሆኑ በማድረጉ ከፍተኛ ስጋት እንዳደረባቸው ለዜና ወኪሉ ገልፀዋል።
የተፈጸመው ጥቃት፤ የተባበሩት መንግሥታት የስደተኞች ጉዳይ ከፍተኛ ኮሚሽን፤ በ 2006 ዓ/ም በሰባት ዞኖች ያሰፈራቸውን ማህበረሰብ ስጋት ላይ ጥሏል።

ሰሞኑን ያጋጠመው የነዳጅ እጥረት ሙሉ በሙሉ ተቀርፏል_ የ #ኢትዮጵያ ነዳጅ አቅራቢ ድርጅት
በቅርቡ አጋጥሞ የነበረው የነዳጅ እጥረት በአሁኑ ጊዜ ሙሉ በሙሉ መቅረፍ ተችሏል ሲል የኢትዮጵያ ነዳጅ አቅራቢ ድርጅት አስታወቀ፡፡ በቀን ሦስት ሚሊዮን ሊትር የሚጠጋ ነዳጅ ወደ ሀገር እየገባ መሆኑም ገልጿል፡፡
በኢትዮጵያ ነዳጅ አቅራቢ ድርጅት ከፍተኛ የሕዝብ ግንኙነት ባለሙያ አቶ ዓለማየሁ ፀጋዬ፤ የነዳጅ እጥረቱ አጋጥሞ የነበረው በጅቡቲ ጥሎ በነበረው ከባድ ዝናብ ምክንያት መንገዶች በመዘጋጋታቸው መሆኑን ገልጸዋል። በዚህ ሳቢያም ነዳጅ የሚጭኑ ከባድ ቦቴዎች ወደ ሀገር መግባትም ሆነ መውጣት አልቻሉም ሲሉ ለኢፕድ ተናግረዋል።
ድርጅቱ ያጋጠመውን የነዳጅ እጥረት ለመቅረፍ ነዳጅ የጫኑ ተሽከርካሪዎች በ #ድሬዳዋ በኩል እንዲገቡ መደረጉን ጠቅሰው፤ በዚህም አጋጥሞ የነበረውን ችግር ሙሉ በሙሉ መቅረፍ መቻሉን ገልጸዋል፡፡
በቀጣይ እንዲህ አይነት ችግሮች ሲያጋጥሙ ቶሎ ምላሽ ለመስጠት ድርጅቱ በቂ መጠባበቂያ ነዳጅ በመያዝ ለኅብረተሰቡ ተደራሽ ለማድረግ ይሠራል ብለዋል።
አቶ ዓለማየሁ፤ ወደፊት ከፍ ያለ በጀት በመመደብ ነዳጅ በባቡር የማጓጓዝ ሥራ ቢጀመር ለዚህ አይነት ችግር አይነተኛ መፍትሔ መሆኑን ጠቁመዋል።
================
የአዲስ ስታንዳርድ አማርኛ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን ይቀላቀሉ፡
ቴሌግራም: https://rb.gy/rekjr
ፌስቡክ: https://rb.gy/xwxb3
ትዊተር (X)፡ https://rb.gy/34uh4
ዩቲዩብ፡ https://rb.gy/bjcbg
ድረገጽ: https://rb.gy/5td6n
ቲክቶክ፡https://rb.gy/3bghek
በቅርቡ አጋጥሞ የነበረው የነዳጅ እጥረት በአሁኑ ጊዜ ሙሉ በሙሉ መቅረፍ ተችሏል ሲል የኢትዮጵያ ነዳጅ አቅራቢ ድርጅት አስታወቀ፡፡ በቀን ሦስት ሚሊዮን ሊትር የሚጠጋ ነዳጅ ወደ ሀገር እየገባ መሆኑም ገልጿል፡፡
በኢትዮጵያ ነዳጅ አቅራቢ ድርጅት ከፍተኛ የሕዝብ ግንኙነት ባለሙያ አቶ ዓለማየሁ ፀጋዬ፤ የነዳጅ እጥረቱ አጋጥሞ የነበረው በጅቡቲ ጥሎ በነበረው ከባድ ዝናብ ምክንያት መንገዶች በመዘጋጋታቸው መሆኑን ገልጸዋል። በዚህ ሳቢያም ነዳጅ የሚጭኑ ከባድ ቦቴዎች ወደ ሀገር መግባትም ሆነ መውጣት አልቻሉም ሲሉ ለኢፕድ ተናግረዋል።
ድርጅቱ ያጋጠመውን የነዳጅ እጥረት ለመቅረፍ ነዳጅ የጫኑ ተሽከርካሪዎች በ #ድሬዳዋ በኩል እንዲገቡ መደረጉን ጠቅሰው፤ በዚህም አጋጥሞ የነበረውን ችግር ሙሉ በሙሉ መቅረፍ መቻሉን ገልጸዋል፡፡
በቀጣይ እንዲህ አይነት ችግሮች ሲያጋጥሙ ቶሎ ምላሽ ለመስጠት ድርጅቱ በቂ መጠባበቂያ ነዳጅ በመያዝ ለኅብረተሰቡ ተደራሽ ለማድረግ ይሠራል ብለዋል።
አቶ ዓለማየሁ፤ ወደፊት ከፍ ያለ በጀት በመመደብ ነዳጅ በባቡር የማጓጓዝ ሥራ ቢጀመር ለዚህ አይነት ችግር አይነተኛ መፍትሔ መሆኑን ጠቁመዋል።
================
የአዲስ ስታንዳርድ አማርኛ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን ይቀላቀሉ፡
ቴሌግራም: https://rb.gy/rekjr
ፌስቡክ: https://rb.gy/xwxb3
ትዊተር (X)፡ https://rb.gy/34uh4
ዩቲዩብ፡ https://rb.gy/bjcbg
ድረገጽ: https://rb.gy/5td6n
ቲክቶክ፡https://rb.gy/3bghek
በ #መቀለ ከተማ ሰልፍ የወጡ ተማሪዎች በፖሊስ ድብደባ እና እስር እንደተፈጸመባቸው ተናገሩ
ከመመረቂያ ጊዜ ጋር የተያያዘ ጥያቄ ይዘው ለሰላማዊ ሰልፍ አደባባይ የወጡ የመቀለ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች በፖሊስ ድብደባ እንደተፈጸመባቸው እና እንደታሰሩ ተማሪዎች ተናገሩ።
በ #ትግራይ በተካሄደው ደም አፋሳሽ ጦርነት ምክንያት ከሁለት ዓመት በላይ ተቋርጦ የነበረውን የከፍተኛ ትምህርት ለማካካስ ተጨማሪ ሴሚስተር እንዲሰጣቸው የጠየቁ ተማሪዎች ናቸው ትናንት መጋቢት 27/2016 ዓ.ም. አደባባይ የወጡት።
በዚህም ፖሊስ የተማሪዎቹ ሰልፍ ያልተፈቀደ እና ሕገወጥ እንደሆነ በመግለጽ እንዲበተኑ በወሰደው አርምጃ ተማሪዎች ላይ ድብደባ መፈጸሙን እና አስከ 20 የሚደርሱ ታስረው እንደነበር ቢቢሲ ያናገራቸው ተማሪዎች ገልጸዋል።
ተማሪዎቹ በጦርነቱ ጊዜ የባከነባቸውን የትምህርት ጊዜ ለማካካስ በዚህ ዓመት የሦስት ሴሚስተር ትምህርት ተሰጥቷቸው እንደሚመረቁ ተነግሯቸው እንደነበር እና አሁን ይህ ቃል በመታጠፉ ቅሬታቸውን ለመግለጽ ሰልፍ መውጣታቸውን ቢቢሲ ያናገራቸው ሁለት ተማሪዎች ገልጸዋል።
https://www.bbc.com/amharic/articles/cqe3ery5qmgo