በ #ኦሮሚያ ክልል አሙሩ ወረዳ በታጣቂዎች በደረሰ ጥቃት ሶስት ሰዎች ተገደሉ
በኦሮሚያ ክልል ሆሮ ጉደሩ ወለጋ ዞን አሙሩ ወረዳ ረቡ ዕለት ታጣቂዎች ባደረሱት ጥቃት የሶስት ሰዎች ህይወት ማለፉን የአካባቢው ነዋሪዎች አስታወቁ፡፡ በጥቃቱ የተገደሉ ሰዎች በሞተር ሳይክል ወደ አጋምሳ ከተማ ሲጓዙ እንደነበር ነዋሪዎቹ ተናግረዋል፡፡
ከሞቱት መካከል አንድ መምህር እንደሚገኝበትም የገለጹት ነዋሪዎቹ፤ አሙሩ እና ምስራቅ ወለጋ ኪረሙ ወረዳ ሀሮ በሚባል አዋሳኝ አካባቢዎች የሚንቀሳቀሱ ታጣቂዎች ተደጋጋሚ ጥቃቶችን ሲያደርሱ እንደነበር ጠቁመዋል፡፡
የአሙሩ ወረዳ ምክትል አስተዳዳሪ አቶ ቂጠሳ በአሙሩ ወረዳና ኪረሙ ወረዳ መካከል በሚገኘው ጎንካ በሚባል ቦታ በደረሰው ጥቃት የሶስት ሰዎች ህይወት ማለፉን ማረጋገጣውን ዶቼ ቬለ ዘግቧል፡፡
"ታጣቂዎቹ በአዋሳኝ አካባቢዎች እየገቡ ነው ጥቃት አድርሰው የሚመለሱት" ያሉት አቶ ቂጠሳ በጸጥታ ጉዳይ ኦፕሬሽን የሚፈልጉ ቦታዎች አሉ፤ እንደ አሙሩ በዚህ ጉዳ ላይ እየተሰራ ነው” ብለዋል።
በአሙሩ ወረዳ ለ3 ዓመታት በነበረው አለመረጋጋት ምክንያት ከ40ሺ በላይ ሰዎች ተፈናቅለው መቆየታቸውን እና በአሁኑ ወቅት ወደ ቤታቸው መመለሳቸውን ይታወቃል።
================
የአዲስ ስታንዳርድ አማርኛ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን ይቀላቀሉ፡
ቴሌግራም: https://rb.gy/rekjr
ፌስቡክ: https://rb.gy/xwxb3
ትዊተር (X)፡ https://rb.gy/34uh4
ዩቲዩብ፡ https://rb.gy/bjcbg
ድረገጽ: https://rb.gy/5td6n
ቲክቶክ፡ https://rb.gy/3bghek

#ኢትዮጵያ በ #ሩሲያ በመካሄድ ላይ ባለው 3ኛው የብሪክስ አባል ሀገራት ተወካዮች ስብሰባ ላይ እየተሳተፈች ነው
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገዥ እና በብሪክስ የኢትዮጵያ ዋና ተወካይ አቶ ማሞ እስመልዓለም ምህረቱ የሚመራ የልዑካን ቡድን ዛሬ በሩሲያ በተጀመረው 3ኛው የብሪክስ የአባል ሀገራት ተወካዮች ስብሰባ ላይ እየተሳተፈ ይገኛል።
አቶ ማሞ በብሪክስ አባል አገራት መካከል በንግድ፣ ኢንቨስትመንት ፣ ቱሪስት ፍሰትና ሌሎች መስኮች ያለውን የኢኮኖሚ ግንኙነት ማሳደግ እንደሚገባና የልማት ፋይናንስን በመጨመር የአካታች እና ዘላቂ ልማትን መደገፍ አስፈላጊ መሆኑን በስብሰባው ላይ ባደረጉት ንግግር ገልጸዋል።
በተለዋዋጭና ሊተነበይ በማይቻል የአለም ኢኮኖሚና ፖለቲካ ምኅዳር ዉስጥ ብሪክስ ሀገራትን እና ሃብቶችን በማሰባሰብ ዓለም አቀፍ ተግዳሮቶችን በአጋርነት መንፈስ ለመቅረፍ አረጋጊ ኃይል ሆኖ ሊያገለግል እንደሚችል ጠቅሰዋል።
አክለውም፣ ኢትዮጵያ የብሪክስ ብሔራዊ ተሳትፎ ስትራቴጂን በብሔራዊ የሚኒስትሮች አስተባባሪ ኮሚቴ ማፅደቋን መግለጻቸውን የመንግስት ሚዲያዎች ዘግበዋል።

ዜና፡ የቀድሞ የ #ኢዜማ ሊቀመንበር አቶ የሺዋስ አሰፋ ከእስር ተፈቱ፤ አዋሽ አርባ የነበሩ ሰባት ፖለቲከኞች ወደ አዲስ አበባ ተዘዋወሩ
“ጦርነት ይቁም! ሰላም ይስፈን!” በሚል መሪ ቃል ህዳር 30 ተጠርቶ የነበረው ሰልፍ አስተባባሪ የሆኑት የቀድሞ የኢዜማ ሊቀመንበር አቶ የሺዋስ አሰፋ ከአንድ ሳምንት እስር በኋላ ትላንት ሰኔ 1/ 2016 ከእስር መፈታታቸውን ባለቤታቸው ወ/ሮ ሙሉ ብርሃን ገለጹ።
"አቶ የሺዋስ ታመው ስለነበር እንደተፈቱ ካሳንችስ አካባቢ ወደሚገኘው መቅረዝ ሆስፒታል በማምራት ህክምና ተደርጎላቸው ማታ ወደ ቢቤታቸው ገብለዋል ሲሉ" ወ/ሮ ሙሉ ለአዲስ ስታንዳርድ ገልጸዋል።
ይህ በእንዲህ እያለ ከሰልፍ ጋር ተያይዞ ከሁለት ወራት በላይ #አፋር በሚገኘው አዋሽ አርባ ወታደራዊ ካምፕ ታስረው የነበሩ ሰባት ፖለቲከኞች እርብ ዕለት ወደ አዲስ አበባ 3ኛ ፖሊስ ጣቢያ መዘዋወራቸውን የ #ኢሕአፓ ተቀዳሚ ምክትል ሊቀ መንበር መጋቢ ብሉይ አብርሃም ሃይማኖት ለአዲስ ስታንዳርድ ተናግረዋል።
ሙሉ ዘገባውን ይመልከቱ፦ https://wp.me/pfjhHd-1bI

Addis standard
የቀድሞ የኢዜማ ሊቀመንበር አቶ የሺዋስ አሰፋ ከአንድ ሳምንት እስር በኋላ ከእስር ተፈቱ - Addis standard
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 2/ 2016 ዓ/ም፡– “ጦርነት ይቁም! ሰላም ይስፈን!” በሚል መሪ ቃል ህዳር 30 ተጠርቶ የነበረው ሰልፍ አስተባባሪ የሆኑት የቀድሞ የኢዜማ ሊቀመንበር አቶ የሺዋስ አሰፋ ከአንድ ሳምንት እስር በኋላ ትላንት ሰኔ 1/ 2016 ከእስር መፈታታቸውን ባለቤታቸው ወ/ሮ ሙሉ ብርሃን ገለጹ። አቶ የሺዋስ ታመው ስለነበር እንደተፈቱ ካሳንችስ አካባቢ ወደሚገኘው መቅረዝ ሆስፒታል በማምራት ህክምና…
የ #ኢትዮጵያ አየር መንገድ ከአራት አመታት በኋላ ወደ አክሱም ከተማ ዳግም በረራ ጀምሯል።
በ #ትግራይ ጦርነት ጉዳት የደረሰበት አጼ ዮሐንስ 4ኛ አውሮፕላን ማረፊያ የተደረገለት ጥገና ተጠናቆ ዛሬ ሰኔ 2 ቀን 2016 መደበኛ ስራ ጀምራል።
ዛሬ በተደረገ የመጀመሪያ በረራም የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ስራ አስፈፃሚ የሆኑትን አቶ መስፍን ጣሰውን፣ የፌደራል እና የክልል የስራ ሃላፊዎችን ጨምሮ 140 ተጓዦች የያዘው አውሮፕላን አክሱም ሃፀይ ዮሐንስ አራተኛ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርስ አቀባበል ተደርጓል።
በአቀባበል ስነ ስርዓቱ የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዜዳንት አቶ ጌታቸው ረዳን ጨምሮ ሌሎች የክልሉ ባለስልጣናት ተገኝተዋል።
በረራውም በየቀኑ 1 ጊዜ የሚደረግ ሲሆን በቀጣይ የደንበኞችን ፍላጎት መሰረት በማድረግ በቀን ወደ 3 ጊዜ ለማሳደግ እንደሚሰራም ተጠቁሟል፡፡

ዜና፡ #ምዕራብ_ጎጃምና #ሰሜን_ጎጃም ዞኖች የ6ኛ እና 8ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተናን እንደማያስፈትኑ ተገለጸ
በ #አማራ ክልል ባለው የጸጥታ ሁኔታ ምክንያት ምዕራብ ጎጃምና ሰሜን ጎጃም ዞኖች የ6ኛ እና 8ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተናን እንደማያስፈትኑ የክልሉ ትምህርት ቢሮ አስታውቋል።
የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር ሙሉነሽ ደሴ በጽህፈት ቤታቸው በሰጡት መግለጫ በጸጥታ ችግር አመቱን ሙሉ በምዕራብ ጎጃምና ሰሜን ጎጃም ትምህርት ያልተማሩ ተማሪዎች መኖራቸውን ገልጸዋል።
የምስራቅ ጎጃም ዞን ትምህርት መምሪያ ባወጣው መግለጫ አጠቃላይ ካሉ 996 አንደኛና ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤቶች፤ የመማር ማስተማር ስራቸውን እያከናወኑ የሚገኙት 32 ትምህርት ቤቶች ብቻ መሆናቸውን አስታወቋል።
በክልሉ ባለው ግጭት ከ407 በላይ ት/ቤቶች መውደማቸውንና ከ290.3 ሚሊዮን በላይ የት/ቤቶች ሀብትና ንብረት መውደሙን አክሎ የዞኑ ትምህርት መምሪያ አስታውቋል።
ተጨማሪ ለመመልከት፦ https://wp.me/pfjhHd-1bP

ምዕራብ ጎጃምና ሰሜን ጎጃም ዞኖች የ6ኛ እና 8ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተናን እንደማያስፈትኑ ተገለጸ - Addis standard
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 3/ 2016 ዓ/ም፦ በአማራ ክልል የዘንድሮው የ8ኛ ክፍል ፈተና ከነገ ሰኔ 4 እስከ 5 ቀን 2016 ዓ.ም የሚሰጥ ሲሆን የ6ኛ ክፍል ፈተና ከሰኔ 13 እስከ 14 ቀን 2016 ዓ.ም ይሰጣል። በክልሉ ባለው የጸጥታ ሁኔታ ምክንያት ይህን ክልላዊ ፈተና በምዕራብና ሰሜን ጎጃም ዞኖች እንደማይሰጥ የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ አስታውቋል። የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ …
ባለፉት 10 ወራት 76 አዳዲስ የገጠር ከተሞች የኤሌክትሪክ ኃይል ተጠቃሚ ሆነዋል ተባለ
ባለፉት 10 ወራት በኢትዮጵያ 76 አዳዲስ የገጠር ከተሞችን የኤሌክትሪክ አገልግሎት ተጠቃሚ ማድረግ መቻሉን የ #ኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት አስታወቀ።
የሀገሪቷ የኤሌክትሪክ ታሪፍ ካለው የዋጋ ግሽበት አንጻር ወጪን የማይሸፍን መሆኑ ጥራት ያለው አገልግሎት ለመስጠትና ገጠራማ የሀገሪቷ ክፍሎች ላይ በስፋት የኤሌክትሪክ ኃይል ተደራሽ ለማድረግ እክል መፍጠሩ ተግልጿል።
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የኮርፖሬት ኮሙኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ መላኩ ታዬ ለኢፕድ እንደገለጹት፤ ባለፉት አስር ወራት ከ328 ሺህ በላይ አዲስ ደንበኞች ኃይል እንዲያገኙ ተደርጓል።
የተቋሙ የአገልግሎት ታሪፍ ወጪን መሠረት ያደረገ አለመሆኑ፣ ሂሳባቸው የማይከፍሉ መንግሥታዊ ተቋማት መኖራቸው፣ የፀጥታ ችግርና የኤሌክትሪክ ማከፋፈያ ጣቢያዎች አቅም ውስንነት የተቋሙ አፈጻጸም እንዳያድግ ምክንያት መሆናቸውን አንስተዋል።
በቀጣይ የታሪፍ ማሻሻያ ተግባራዊ ለማድረግ ጥናት ተጠናቆ ወደሚመለከው አካል መቅረቡን ገልጸዋል።
================
የአዲስ ስታንዳርድ አማርኛ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን ይቀላቀሉ፡
ቴሌግራም: https://rb.gy/rekjr
ፌስቡክ: https://rb.gy/xwxb3
ትዊተር (X)፡ https://rb.gy/34uh4
ዩቲዩብ፡ https://rb.gy/bjcbg
ድረገጽ: https://rb.gy/5td6n
ቲክቶክ፡ https://rb.gy/3bghek
ባለፉት 10 ወራት በኢትዮጵያ 76 አዳዲስ የገጠር ከተሞችን የኤሌክትሪክ አገልግሎት ተጠቃሚ ማድረግ መቻሉን የ #ኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት አስታወቀ።
የሀገሪቷ የኤሌክትሪክ ታሪፍ ካለው የዋጋ ግሽበት አንጻር ወጪን የማይሸፍን መሆኑ ጥራት ያለው አገልግሎት ለመስጠትና ገጠራማ የሀገሪቷ ክፍሎች ላይ በስፋት የኤሌክትሪክ ኃይል ተደራሽ ለማድረግ እክል መፍጠሩ ተግልጿል።
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የኮርፖሬት ኮሙኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ መላኩ ታዬ ለኢፕድ እንደገለጹት፤ ባለፉት አስር ወራት ከ328 ሺህ በላይ አዲስ ደንበኞች ኃይል እንዲያገኙ ተደርጓል።
የተቋሙ የአገልግሎት ታሪፍ ወጪን መሠረት ያደረገ አለመሆኑ፣ ሂሳባቸው የማይከፍሉ መንግሥታዊ ተቋማት መኖራቸው፣ የፀጥታ ችግርና የኤሌክትሪክ ማከፋፈያ ጣቢያዎች አቅም ውስንነት የተቋሙ አፈጻጸም እንዳያድግ ምክንያት መሆናቸውን አንስተዋል።
በቀጣይ የታሪፍ ማሻሻያ ተግባራዊ ለማድረግ ጥናት ተጠናቆ ወደሚመለከው አካል መቅረቡን ገልጸዋል።
================
የአዲስ ስታንዳርድ አማርኛ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን ይቀላቀሉ፡
ቴሌግራም: https://rb.gy/rekjr
ፌስቡክ: https://rb.gy/xwxb3
ትዊተር (X)፡ https://rb.gy/34uh4
ዩቲዩብ፡ https://rb.gy/bjcbg
ድረገጽ: https://rb.gy/5td6n
ቲክቶክ፡ https://rb.gy/3bghek
የሽግግር ፍትሕ ማስተግበሪያ ፍኖተ ካርታ ዝግጅት መጠናቀቁን የፍትሕ ሚኒስቴር አስታወቀ
የሽግግር ፍትሕ ፖሊሲውን መተግበር የሚያስችል ፍኖተ ካርታ ተጠናቅቆ ለውይይት ዝግጁ መሆኑን የፍትሕ ሚኒስቴር አስታውቋል።
ለውይይት ዝግጁ የሆነው ፍኖተ-ካርታ የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች በአባልነት የሚሳተፉበት ጊዜያዊ እና ዘላቂ ተቋማዊ የቅንጅት አመራር ሥርዓት ስለሚቋቋምበት ሁኔታ፤ ስለ ሽግግር ፍትሕ ስልቶች አተገባበር ቅደም-ተከተል መካተቱን የፍትሕ ሚኒስቴር ዛሬ ባወጣው መግለጫ ገልጿል።
ከትግበራ ምዕራፍ ረቂቅ ፍኖተ ካርታው በተጨማሪ የሽግግር ፍትሕ ጊዜያዊ የተቋማት የቅንጅት አመራር ሥርዓት ማቋቋሚያ ረቂቅ መመሪያ፣ የሽግግር ፍትሕ ስልቶች አተገባበር ቅደም-ተከተል ማብራሪያ ሰነድ መዘጋጀታቸውን ገልጿል።
በዚህም መሰረት የፍኖተ ካርታውን ረቂቅ ሰነድ ጨምሮ በተዘጋጁት የማስተግበሪያ ሰነዶች ላይ የሚደረጉ ውይይቶች ሲጠናቀቁ የፖሊሲው ትግበራ ምዕራፍ ዋና ዋና ተግባራት መከናወን እንደሚጀምሩ ሚኒስቴሩ አታውቋል።
ሚያዝያ 9 ቀን 2016 ዓ.ም በሚኒስትሮች ምክር ቤት የጸደቀው የሽግግር ፍትሕ ፖሊሲ፤ በሀገሪቱ በተለያዩ ጊዜያት የተከሰቱ መጠነ-ሰፊ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች እና ውስብስብ ችግሮችን በዘላቂነት ለመፍታት በወንጀል ተጠያቂነት፣ እውነትን ማፈላለግ፣ ይፋ ማውጣት እና ዕርቅ ማውረድ፣ በቅድመ-ሁኔታ ላይ የተመሰረተ ምሕረት፣ በተቋማዊ ማሻሻያ እንዲሁም በማካካሻ ስልቶች ላይ የተዋቀረ መሆኑን መግለጫ አስታውሷል።

በ #ሶማሊያ በጎሳ ግጭት ከ40 በላይ ሰዎች ሲገደሉ፣ አልሻባብ በመንግሥት ኃይሎች ላይ ጥቃት ፈጸመ
ባለፈው ሳምንት ማብቂያ ላይ በማዕከላዊ ሶማሊያ ማሬሃን እና ዲር በተባሉ ጎሳዎች መካከል በተከሰተ ግጭት ቢያንስ 40 ሰዎች መገደላቸው ሲገለጽ፣ የአልሻባብ ኃይሎች ጥቃት ሰንዝረው በርካቶች መሞታቸው ተገለጸ።
ቅዳሜ ሰኔ 1/2016 ዓ.ም. በጋልሙዱግ ግዛት በጎሳ አባላቱ መካከል የተከሰተው ግጭት እንዲረግብ የፌደራል መንግሥቱ እና የግዛቲቱ አስተዳደር ጠይቀዋል።
አንዳንድ የሶማሊያ መገናኛ ብዙኃን በዚህ የጎሳ ግጭት የሞቱ ሰዎች ቁጥርን 60፤ የቆሰሉትን ደግሞ 80 በማድረስ ዘግበዋል።
ቅዳሜ ሰኔ 1/2016 ዓ.ም. በጋልጉዱዱ ግዛት ኤል-ዴር ከተማ በሚገኝ ወታደራዊ ካምፕ ላይ አል-ሸባብ ድንገተኛ ጥቃት ፈጽሟል።
ይህን ድንገተኛ ጥቃት ተከትሎ የሶማሊያ መንግሥት ከአጎራባች አካባቢዎች ተጨማሪ ኃይል በማሰማራት ከ47 በላይ የቡድኑ አባላትን መግደሉን እና የተሰነዘረውን ጥቃት ማክሸፉን አስታውቋል።
አል-ሸባብ ጥቃቱን ከፈጸመ በኋላ ባወጣው መግለጫ በመንግሥት ኃይሎች ላይ ድልን ተጎናጽፊያለሁ ብሏል።
https://www.bbc.com/amharic/articles/cydd5jjmjlno

በ #ትግራይ ክልል ሓውዜን ወረዳ በተቀበረ ተተኳሽ የአራት ታዳጊ ልጆች ህይወት አለፈ
በትግራይ ክልል ለሁለት አመታት በተካሄደው አውዳሚ ጦርነት ወቅት በተቀበረ ተተኳሸ በደረሰ አደጋ የአራት ታዳጊ ልጆች ህይወት አለፈ።
በትግራይ ክልል በምሰራቃዊ ዞን ሓውዜን ወረዳ ማይጎቦ ቀበሌ ሰኔ 1/2016 ዓ.ም በፈነዳው ተተኳሽ ህይወታቸው ያለፈው አራቱ ታዳጊዎች ዕድሜያቸው ከ9 እስከ 14 አመት ሲሆን ሦስቱ የአንድ ቤተሰብ አባላት መሆናቸውን የክልሉ ሚዲያ ዘግቧል።
በአካባቢው ለቁጥር የሚያዳግቱ ፈንጂዎች መኖራቸውን የገለጹት የማይጎቦ ቀበሌ አስተዳዳሪ አቶ ፀጋይ ገ/የሱስ፤ እስካሁን 10 ሰዎች መሞታቸውንና 8 ሰዎች መቁሰላቸው ገልጸዋል። መንግሥት ባለሙያዎችን በመላክ አካባቢውን ማጽዳት ይገባል ሲሉ አሳስበዋል።
በትግራይ በጦርነቱ ወቅት መሬት ላይ ተጥለው ወይ ተቀብረው ሳይፈነዱ የቀሩ የጦር መሳሪያዎች ባደረሱት አደጋ፤ ከ100 በላይ ሰዎች ህይወታቸው ማለፉንና በርካቶች መቁሰላቸውን የቆላ ተምቤን ወረዳ አስተዳዳሪ አቶ ተክላይ ተስፋዬ መግለጻቸው ይታወሳል።
የወረዳው አስተዳዳሪ በወቅቱ፤ "ፈንጂ ያልተዘራበት አካባቢ የለም ማለት ይቻላል” ብለዋል።