ዜና፡ ቅዱስ ሲኖዶሱ በሀገራዊ ምክክር ኮሚሽኑ ላይ ቅሬታ ማሰማቱን ተከትሎ ኮሚሽኑ ከሲኖዱሱ ጋር ለመወያየት ዝግጁ መሆኑን ገለጸ
የ #ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ በሀገራዊ ምክክር ቤተክርስቲያኗ እንድትሳተፍ ጥሪ ባለመቅረቡ ቅሬታ ማሰማቱን ተከትሎ ኮሚሽኑ የሲኖዱሱ ጽ/ቤት ድረስ በመሄድ ለመወያየት ዝግጁ መሆኑን አስታወቀ።
ቅዱስ ሲኖዶሱ ትላንት ባወጣው መግለጫ ቤተክርስቲያኒቱ በኮሚሽኑ በኩል በይፋ የቀረበ የተሳትፎ ጥሪ እንዳልተደረገላት በመግለጽ በሂደቱ ቅር መሰኘቷን አስታውቋል።
ይህን ተከትሎ የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በሰጠው መግለጫ፤ ኮሚሽኑ ገና ሥራውን እንደጀመረ የመግባቢያ ሠነድ የተፈራረመው ከአምስቱ ተባባሪ አካላት አንዱ ከሆነው ከኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባዔ ጋር ነው ብሏል።
ሙሉ ዘገባውን ይመልከቱ፦ https://wp.me/pfjhHd-1bA

Addis standard
ቅዱስ ሲኖዶሱ በሀገራዊ ምክክር ኮሚሽኑ ላይ ቅሬታ ማሰማቱን ተከትሎ ኮሚሽኑ ከሲኖዱሱ ጋር ለመወያየት ዝግጁ መሆኑን ገለጸ - Addis standard
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 30/ 2016 ዓ/ም፦ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ በሀገራዊ ምክክር ቤተክርስቲያኗ እንድትሳተፍ ጥሪ ባለመቅረቡ ቅሬታ ማሰማቱን ተከትሎ ኮሚሽኑ የሲኖዱሱ ጽ/ቤት ድረስ በመሄድ ለመወያየት ዝግጁ መሆኑን አስታወቀ። ቅዱስ ሲኖዶሱ ከግንቦት 21 እስከ ግንቦት 28 ቀን 2016 ዓ/ም ድረስ ሲያካሄድ የቆየውን የርክበ ካህናት መደበኛ ስብሰባውን ማጥናቀቁን ተከትሎ…
እነ #ዮሐንስ_ቧያለው ቅሬታ እና የክስ መቃወሚያ ለፍርድ ቤት አቀረቡ
በእነ አቶ ዮሐንስ ቧያለው መዝገብ የተከሰሱ 52 ተከሳሾች ትላንት ሐሙስ ግንቦት 29/2016 ዓ.ም. የክስ መቃወሚያቸውን ለፍርድ ቤት በጽሁፍ አቅርበዋል።
ተከሳሾች ጉዳያቸውን እየተመለከተ ከሚገኘው ፍርድ ቤት የዳኝነት ሥልጣን ጋር የተያያዘ መቃወሚያም አቅርበዋል። ከዚህ ጋር በተያያዘ ቀዳሚው የተከሳሾች መቃወሚያ፤ “ፍርድ ቤቱ አማራዊ ማንነትን ለመዳኘት ሥልጣን [የለውም]” የሚል ነው።
በተጨማሪም ፍርድ ቤቱ በተወሰኑ ተከሳሾች ላይ “የአስተዳደር አካባቢ የዳኝነት ሥልጣን የለውም” የሚል መቃወሚያ ቀርቧል።
ወንጀሉ ተፈጸመ የተባለው በ #አማራ ክልል መሆኑን ያስታወሱት ተከሳሾች፤ “ይህን ጉዳይ ለማየት ሥልጣን ያለው የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ነው በማለት ጉዳዩን ወደ አማራ ክልል እንዲልከው በማክበር እንጠይቀለን” ብለዋል።
በመቃወሚያ አቶ ዮሐንስ የፌዴሬሽን ምክር ቤት አባል በመሆናቸው ያላቸው ያለመከከስ መብት አለመነሳቱ በመቃወሚያው ላይ ተጠቅሷል። በዚህም መሰረት “በ1ኛ ተከሳሽ ላይ የቀረበው የወንጀል ክስ ተቋርጦ ከእስር እንዲፈቱ” የሚል ጥያቄ አቅርቧል።
https://www.bbc.com/amharic/articles/c100qz32e0mo

ከፍተኛ የካርበን ልቀት ያላቸው መኪኖች በመዲናዋ እንዳይነዱ የሚያግድ መመሪያ ስራ ላይ ሊውል ነው ተባለ
በተሽከርካሪዎች የበካይ ጋዝ ወይም ካርበን ልቀት የሚፈጠርን የአየር ብክለት ለመቆጣጠር ከፍተኛ የካርበን ልቀት ያላቸው መኪኖች ከአዱስ አበባ እንዳይነዱ የሚያስችል አስገዳጅ መመሪያ ተግባራዊ ሊደረግ መሆኑ ተገለፀ።
በአዲስ አበባ አካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን የተዘጋጀው አስገዳጅ መመሪያው በከተማዋ ያለው የአየር ብክለት መጠን ከአለም አቀፍ ብሎም እንደ ሀገር ከወጣው ስታንዳርድ ወይም መለኪያ በማለፉና አስጊ ደረጃ በመድረሱ መሆኑም ተነግሯል፡፡
በከተማዋ ከሚከሰተው የአየር ብክለት ውስጥ 27 በመቶው ከተሽከርካሪዎች የጭስ እና የጋዝ ብናኝ ምክንያት እየተከሰተ መሆኑንም ተገልጿል፡፡
በተሽከርካሪዎች ላይ በሚደረግ ፍተሻ ከጭስ እና ከጋዝ ልቀት አልፈው ከተገኙ ለጊዜወ አገልግሎት እንዳይሰጡ ይደረጋሉ ተብሏል፡፡
ሆኖም ግን ተሽከርካሪዎች የተሻለ ቴክኖሎጂዎች እንዲገጠምላቸው እና የብክለት መጠኑ እንዲቀንስ አስፈላጊውን የጥገና ስራ እንዲደረግላቸው ይደረጋልም ተብሏል፡፡
================
የአዲስ ስታንዳርድ አማርኛ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን ይቀላቀሉ፡
ቴሌግራም: https://rb.gy/rekjr
ፌስቡክ: https://rb.gy/xwxb3
ትዊተር (X)፡ https://rb.gy/34uh4
ዩቲዩብ፡ https://rb.gy/bjcbg
ድረገጽ: https://rb.gy/5td6n
ቲክቶክ፡https://rb.gy/3bghek

በአዲስ አበባ የአከራይና ተከራይ ህጋዊ ውል ምዝገባ ዛሬ ይጀመራል
በአዲስ አበባ የአከራይና ተከራይ ህጋዊ ውል ምዝገባ ዛሬ ሰኔ 1 ቀን 2016 ዓ.ም እንደሚጀመር የቤቶች ልማትና አስተዳደር ቢሮ አስታውቋል።
የመኖሪያ ቤት ኪራይ ቁጥጥርና አስተዳደር አዋጅ በሀገሪቱ ያለውን የቤት ኪራይ ችግር ለመፍታት እንዲሁም ፍትሃዊ ያልሆነ የዋጋ ጭማሪ በማህበረሰቡ ኑሮና በአጠቃላይ ሀገራዊ ምጣኔ ሀብት ላይ የሚፈጥረውን ጫና ከግምት በማስገባት ተዘጋጅቶ መጽደቁ ይታወሳል፡፡
ከሰኔ 1 እስከ 30 ቀን 2016 ዓ.ም በከተማዋ ውስጥ የሚገኙ የግል ቤት አከራዮች ከተከራዮቻቸው ጋር ህጋዊ ሰነዶቻቸውን ይዘው በመቅረብ ምዝገባ ማድረግ እንደሚችሉ አስገንዝቧል።
በስራ ሰዓት መመዘግብ የማይችሉ አከራይና ተከራዮች ቅዳሜና እሁድ እንዲሁም በስራ ቀን ማታ ከ12 ሰዓት በኋላ ህጋዊ የውል ምዝገባውን መፈጸም እንደሚችሉም ተገልጿል።
በምዝገባውና አዋጁን ተግባራዊ በማድረግ ሂደት ቅሬታዎችን በመቀበል ማስተናገድ የሚያስችል አሰራር መዘርጋቱም ተነግሯል።
(ፋና)

በ #ኦሮሚያ ክልል አሙሩ ወረዳ በታጣቂዎች በደረሰ ጥቃት ሶስት ሰዎች ተገደሉ
በኦሮሚያ ክልል ሆሮ ጉደሩ ወለጋ ዞን አሙሩ ወረዳ ረቡ ዕለት ታጣቂዎች ባደረሱት ጥቃት የሶስት ሰዎች ህይወት ማለፉን የአካባቢው ነዋሪዎች አስታወቁ፡፡ በጥቃቱ የተገደሉ ሰዎች በሞተር ሳይክል ወደ አጋምሳ ከተማ ሲጓዙ እንደነበር ነዋሪዎቹ ተናግረዋል፡፡
ከሞቱት መካከል አንድ መምህር እንደሚገኝበትም የገለጹት ነዋሪዎቹ፤ አሙሩ እና ምስራቅ ወለጋ ኪረሙ ወረዳ ሀሮ በሚባል አዋሳኝ አካባቢዎች የሚንቀሳቀሱ ታጣቂዎች ተደጋጋሚ ጥቃቶችን ሲያደርሱ እንደነበር ጠቁመዋል፡፡
የአሙሩ ወረዳ ምክትል አስተዳዳሪ አቶ ቂጠሳ በአሙሩ ወረዳና ኪረሙ ወረዳ መካከል በሚገኘው ጎንካ በሚባል ቦታ በደረሰው ጥቃት የሶስት ሰዎች ህይወት ማለፉን ማረጋገጣውን ዶቼ ቬለ ዘግቧል፡፡
"ታጣቂዎቹ በአዋሳኝ አካባቢዎች እየገቡ ነው ጥቃት አድርሰው የሚመለሱት" ያሉት አቶ ቂጠሳ በጸጥታ ጉዳይ ኦፕሬሽን የሚፈልጉ ቦታዎች አሉ፤ እንደ አሙሩ በዚህ ጉዳ ላይ እየተሰራ ነው” ብለዋል።
በአሙሩ ወረዳ ለ3 ዓመታት በነበረው አለመረጋጋት ምክንያት ከ40ሺ በላይ ሰዎች ተፈናቅለው መቆየታቸውን እና በአሁኑ ወቅት ወደ ቤታቸው መመለሳቸውን ይታወቃል።
================
የአዲስ ስታንዳርድ አማርኛ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን ይቀላቀሉ፡
ቴሌግራም: https://rb.gy/rekjr
ፌስቡክ: https://rb.gy/xwxb3
ትዊተር (X)፡ https://rb.gy/34uh4
ዩቲዩብ፡ https://rb.gy/bjcbg
ድረገጽ: https://rb.gy/5td6n
ቲክቶክ፡ https://rb.gy/3bghek

#ኢትዮጵያ በ #ሩሲያ በመካሄድ ላይ ባለው 3ኛው የብሪክስ አባል ሀገራት ተወካዮች ስብሰባ ላይ እየተሳተፈች ነው
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገዥ እና በብሪክስ የኢትዮጵያ ዋና ተወካይ አቶ ማሞ እስመልዓለም ምህረቱ የሚመራ የልዑካን ቡድን ዛሬ በሩሲያ በተጀመረው 3ኛው የብሪክስ የአባል ሀገራት ተወካዮች ስብሰባ ላይ እየተሳተፈ ይገኛል።
አቶ ማሞ በብሪክስ አባል አገራት መካከል በንግድ፣ ኢንቨስትመንት ፣ ቱሪስት ፍሰትና ሌሎች መስኮች ያለውን የኢኮኖሚ ግንኙነት ማሳደግ እንደሚገባና የልማት ፋይናንስን በመጨመር የአካታች እና ዘላቂ ልማትን መደገፍ አስፈላጊ መሆኑን በስብሰባው ላይ ባደረጉት ንግግር ገልጸዋል።
በተለዋዋጭና ሊተነበይ በማይቻል የአለም ኢኮኖሚና ፖለቲካ ምኅዳር ዉስጥ ብሪክስ ሀገራትን እና ሃብቶችን በማሰባሰብ ዓለም አቀፍ ተግዳሮቶችን በአጋርነት መንፈስ ለመቅረፍ አረጋጊ ኃይል ሆኖ ሊያገለግል እንደሚችል ጠቅሰዋል።
አክለውም፣ ኢትዮጵያ የብሪክስ ብሔራዊ ተሳትፎ ስትራቴጂን በብሔራዊ የሚኒስትሮች አስተባባሪ ኮሚቴ ማፅደቋን መግለጻቸውን የመንግስት ሚዲያዎች ዘግበዋል።

ዜና፡ የቀድሞ የ #ኢዜማ ሊቀመንበር አቶ የሺዋስ አሰፋ ከእስር ተፈቱ፤ አዋሽ አርባ የነበሩ ሰባት ፖለቲከኞች ወደ አዲስ አበባ ተዘዋወሩ
“ጦርነት ይቁም! ሰላም ይስፈን!” በሚል መሪ ቃል ህዳር 30 ተጠርቶ የነበረው ሰልፍ አስተባባሪ የሆኑት የቀድሞ የኢዜማ ሊቀመንበር አቶ የሺዋስ አሰፋ ከአንድ ሳምንት እስር በኋላ ትላንት ሰኔ 1/ 2016 ከእስር መፈታታቸውን ባለቤታቸው ወ/ሮ ሙሉ ብርሃን ገለጹ።
"አቶ የሺዋስ ታመው ስለነበር እንደተፈቱ ካሳንችስ አካባቢ ወደሚገኘው መቅረዝ ሆስፒታል በማምራት ህክምና ተደርጎላቸው ማታ ወደ ቢቤታቸው ገብለዋል ሲሉ" ወ/ሮ ሙሉ ለአዲስ ስታንዳርድ ገልጸዋል።
ይህ በእንዲህ እያለ ከሰልፍ ጋር ተያይዞ ከሁለት ወራት በላይ #አፋር በሚገኘው አዋሽ አርባ ወታደራዊ ካምፕ ታስረው የነበሩ ሰባት ፖለቲከኞች እርብ ዕለት ወደ አዲስ አበባ 3ኛ ፖሊስ ጣቢያ መዘዋወራቸውን የ #ኢሕአፓ ተቀዳሚ ምክትል ሊቀ መንበር መጋቢ ብሉይ አብርሃም ሃይማኖት ለአዲስ ስታንዳርድ ተናግረዋል።
ሙሉ ዘገባውን ይመልከቱ፦ https://wp.me/pfjhHd-1bI

የቀድሞ የኢዜማ ሊቀመንበር አቶ የሺዋስ አሰፋ ከአንድ ሳምንት እስር በኋላ ከእስር ተፈቱ - Addis standard
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 2/ 2016 ዓ/ም፡– “ጦርነት ይቁም! ሰላም ይስፈን!” በሚል መሪ ቃል ህዳር 30 ተጠርቶ የነበረው ሰልፍ አስተባባሪ የሆኑት የቀድሞ የኢዜማ ሊቀመንበር አቶ የሺዋስ አሰፋ ከአንድ ሳምንት እስር በኋላ ትላንት ሰኔ 1/ 2016 ከእስር መፈታታቸውን ባለቤታቸው ወ/ሮ ሙሉ ብርሃን ገለጹ። አቶ የሺዋስ ታመው ስለነበር እንደተፈቱ ካሳንችስ አካባቢ ወደሚገኘው መቅረዝ ሆስፒታል በማምራት ህክምና…
የ #ኢትዮጵያ አየር መንገድ ከአራት አመታት በኋላ ወደ አክሱም ከተማ ዳግም በረራ ጀምሯል።
በ #ትግራይ ጦርነት ጉዳት የደረሰበት አጼ ዮሐንስ 4ኛ አውሮፕላን ማረፊያ የተደረገለት ጥገና ተጠናቆ ዛሬ ሰኔ 2 ቀን 2016 መደበኛ ስራ ጀምራል።
ዛሬ በተደረገ የመጀመሪያ በረራም የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ስራ አስፈፃሚ የሆኑትን አቶ መስፍን ጣሰውን፣ የፌደራል እና የክልል የስራ ሃላፊዎችን ጨምሮ 140 ተጓዦች የያዘው አውሮፕላን አክሱም ሃፀይ ዮሐንስ አራተኛ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርስ አቀባበል ተደርጓል።
በአቀባበል ስነ ስርዓቱ የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዜዳንት አቶ ጌታቸው ረዳን ጨምሮ ሌሎች የክልሉ ባለስልጣናት ተገኝተዋል።
በረራውም በየቀኑ 1 ጊዜ የሚደረግ ሲሆን በቀጣይ የደንበኞችን ፍላጎት መሰረት በማድረግ በቀን ወደ 3 ጊዜ ለማሳደግ እንደሚሰራም ተጠቁሟል፡፡

ዜና፡ #ምዕራብ_ጎጃምና #ሰሜን_ጎጃም ዞኖች የ6ኛ እና 8ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተናን እንደማያስፈትኑ ተገለጸ
በ #አማራ ክልል ባለው የጸጥታ ሁኔታ ምክንያት ምዕራብ ጎጃምና ሰሜን ጎጃም ዞኖች የ6ኛ እና 8ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተናን እንደማያስፈትኑ የክልሉ ትምህርት ቢሮ አስታውቋል።
የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር ሙሉነሽ ደሴ በጽህፈት ቤታቸው በሰጡት መግለጫ በጸጥታ ችግር አመቱን ሙሉ በምዕራብ ጎጃምና ሰሜን ጎጃም ትምህርት ያልተማሩ ተማሪዎች መኖራቸውን ገልጸዋል።
የምስራቅ ጎጃም ዞን ትምህርት መምሪያ ባወጣው መግለጫ አጠቃላይ ካሉ 996 አንደኛና ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤቶች፤ የመማር ማስተማር ስራቸውን እያከናወኑ የሚገኙት 32 ትምህርት ቤቶች ብቻ መሆናቸውን አስታወቋል።
በክልሉ ባለው ግጭት ከ407 በላይ ት/ቤቶች መውደማቸውንና ከ290.3 ሚሊዮን በላይ የት/ቤቶች ሀብትና ንብረት መውደሙን አክሎ የዞኑ ትምህርት መምሪያ አስታውቋል።
ተጨማሪ ለመመልከት፦ https://wp.me/pfjhHd-1bP

ምዕራብ ጎጃምና ሰሜን ጎጃም ዞኖች የ6ኛ እና 8ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተናን እንደማያስፈትኑ ተገለጸ - Addis standard
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 3/ 2016 ዓ/ም፦ በአማራ ክልል የዘንድሮው የ8ኛ ክፍል ፈተና ከነገ ሰኔ 4 እስከ 5 ቀን 2016 ዓ.ም የሚሰጥ ሲሆን የ6ኛ ክፍል ፈተና ከሰኔ 13 እስከ 14 ቀን 2016 ዓ.ም ይሰጣል። በክልሉ ባለው የጸጥታ ሁኔታ ምክንያት ይህን ክልላዊ ፈተና በምዕራብና ሰሜን ጎጃም ዞኖች እንደማይሰጥ የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ አስታውቋል። የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ …