Addis Standard Amharic – Telegram
Addis Standard Amharic
18K subscribers
4.67K photos
121 videos
3 files
3.72K links
አዲስ ስታንዳርድ በጃኬን አሳታሚ ኃ.የተ.የግ.ማ. ባለቤትነት ስር የሚታተም በኢትዮጵያ የሚገኝ ነፃ እና ገለልተኛ ሚዲያ ነው። አዲስ ስታንዳርድ አማርኛ የአዲስ ስታንዳርድ እንግሊዝኛ ሕትመት አካል ነው።
ፌስቡክ: https://rb.gy/xwxb3
ትዊተር (X)፡ https://rb.gy/34uh4
Download Telegram
#ትግራይ ክልል ሓውዜን ወረዳ በተቀበረ ተተኳሽ የአራት ታዳጊ ልጆች ህይወት አለፈ

በትግራይ ክልል ለሁለት አመታት በተካሄደው አውዳሚ ጦርነት ወቅት በተቀበረ ተተኳሸ በደረሰ አደጋ የአራት ታዳጊ ልጆች ህይወት አለፈ።

በትግራይ ክልል በምሰራቃዊ ዞን ሓውዜን ወረዳ ማይጎቦ ቀበሌ ሰኔ 1/2016 ዓ.ም በፈነዳው ተተኳሽ ህይወታቸው ያለፈው አራቱ ታዳጊዎች ዕድሜያቸው ​​ከ9 እስከ 14 አመት ሲሆን ሦስቱ የአንድ ቤተሰብ አባላት መሆናቸውን የክልሉ ሚዲያ ዘግቧል።

በአካባቢው ለቁጥር የሚያዳግቱ ፈንጂዎች መኖራቸውን የገለጹት የማይጎቦ ቀበሌ አስተዳዳሪ አቶ ፀጋይ ገ/የሱስ፤ እስካሁን 10 ሰዎች መሞታቸውንና 8 ሰዎች መቁሰላቸው ገልጸዋል። መንግሥት ባለሙያዎችን በመላክ አካባቢውን ማጽዳት ይገባል ሲሉ አሳስበዋል።

በትግራይ በጦርነቱ ወቅት መሬት ላይ ተጥለው ወይ ተቀብረው ሳይፈነዱ የቀሩ የጦር መሳሪያዎች ባደረሱት አደጋ፤ ከ100 በላይ ሰዎች ህይወታቸው ማለፉንና በርካቶች መቁሰላቸውን የቆላ ተምቤን ወረዳ አስተዳዳሪ አቶ ተክላይ ተስፋዬ መግለጻቸው ይታወሳል።

የወረዳው አስተዳዳሪ በወቅቱ፤ "ፈንጂ ያልተዘራበት አካባቢ የለም ማለት ይቻላል” ብለዋል።

================
የአዲስ ስታንዳርድ አማርኛ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን ይቀላቀሉ፡
ቴሌግራም: https://rb.gy/rekjr
ፌስቡክ: https://rb.gy/xwxb3
ትዊተር (X)፡ https://rb.gy/34uh4
ዩቲዩብ፡ https://rb.gy/bjcbg
ድረገጽ: https://rb.gy/5td6n
ቲክቶክ፡ https://rb.gy/3bghek
ዜና: ቋሚ ኮሚቴው #ቃሊቲ ማረሚያ ማዕከል ድረስ በመሄድ አቶ ክርስቲያን ታደለን ጎብኝቻለሁ አለ

የፌደራል ማረሚያ ቤት በጸጥታ ችግር ምክንያት ታራሚዎችን ወደ ሸዋ ሮቢት መውሰድ ባለመቻሉ በቂሊንጦ መጨናነቅ ተፈጥሯል ብሏል

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የህግ እና ፍትህ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ በፌደራል ማረሚያ ቤት በህግ ጥላ ስር የሚገኙ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የምክር ቤት አባል የነበሩ እና ያለመከሰስ መብታቸው ተነስቶ በማቆያ ስፍራ የሚገኙ ግለሰቦችን አያያዝ መመልከቱን አስታወቀ።

ቋሚ ኮሚቴው የተመለከታቸው በፌደራል ማረሚያ ቤት ኮሚሽን በቃሊቲ ማረሚያ ማዕከል አቶ ክርስቲያን ታደለን እና በቂሊንጦ የሚገኘው የቀጠሮ ማረፊያ አቶ ጫላ ዋቶ (ዶ/ር )ናቸው።

ስለማረሚያ ቤቱ አጠቃላይ አያያዝ ሁኔታ በቋሚ ኮሚቴው ሰብሳቢ ወ/ሮ እጸገነት እና ሌሎችም አባላት የተጠየቁት አቶ ክርስቲያን ታደለ አዋሽ አርባ ከነበረው አያያዝ የተሻለ መሆኑን ገልጸው የአዋሽ አርባ ማቆያ ሊታይ ይገባል ብለዋል።

አሁን ባሉበት ማቆያ የቤተሰብ ጥየቃ ሰአት ከ6 ሰዓት እስከ 8 ሰዓት መሆኑንና እንደ አስፈላጊነቱ መሻሻል ቢችል ሲሉ መጠየቃቸውም ታውቋል።
https://wp.me/pfjhHd-1c1
በርካታ #ኢትዮጵያውን ስደተኞችን የያዘች ጀልባ ተገልብጣ ቢያንስ 38 ሰዎች ሞቱ

አብዛኞቹ ኢትዮጵያውያን የሆኑ ስደተኞችን አሳፍራ ስትጓዝ የነበረች ጀልባ ከ #የመን የባሕር ዳርቻ አቅራቢያ ተገልብጣ ቢያንስ 38 ሰዎች መሞታቸውን ባለሥልጣናት አስታወቁ።

ከአደጋው የተረፉ ሰዎች ለነፍስ አድን ሠራተኞች እንደተናገሩት ጀልባዋ 250 የሚጠጉ ሰዎችን አሳፍራ የነበረ ሲሆን፣ ለመገልበጥ የበቃችውም በካበድ ነፋስ ምክንያት ነው ተብሏል።

መሞታቸው ከታወቀው 38 ሰዎች ውጪ ሌሎች 100 ሰዎች የደረሱበት ያልታወቀ ሲሆን፣ እነሱን ለማግኘት ፍለጋ እየተደረገ ነው።

በስፍራው የነበሩ ሰዎች 250 የሚሆኑ ስደተኞችን አሳፍራ አደጋው የደረሰባት ጀልባ ላይ የነበሩ በርካታ ሰዎችን ሕይወት ማትረፋቸው ተነግሯል።

“ዓሳ አስጋሪዎች እና ነዋሪዎች አብረዋቸው በጀልባዋ ላይ የነበሩ 100 የሚሆኑት ሰዎች የደረሱበት አለመታወቁን የተናገሩ 78 ሰዎችን በሕይወት አድነዋል” ሲሉ ከየመን ዋና ከተማ አደን በስተምሥራቅ የምትገኘው የሩደም አካባቢ ባለሥልጣኑ ተናግረዋል ሲል የዘገበው ቢቢሲ አማርኛ።

================
የአዲስ ስታንዳርድ አማርኛ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን ይቀላቀሉ፡
ቴሌግራም: https://rb.gy/rekjr
ፌስቡክ: https://rb.gy/xwxb3
ትዊተር (X)፡ https://rb.gy/34uh4
ዩቲዩብ፡ https://rb.gy/bjcbg
ድረገጽ: https://rb.gy/5td6n
ቲክቶክ፡ https://rb.gy/3bghek
ዜና: በ11 ወራት ከ252 ሺ ቶን በላይ #ቡና ለውጭ ገበያ በማቅረብ ከአንድ ነጥብ ሁለት ቢሊየን ዶላር በላይ ተገኝቷል ተባለ

በ2016 በጀት ዓመት 11 ወራት ወደ ውጪ ከተላከ የቡና ምርት ከፍተኛ ውጤት መመዝገቡን #የኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለስልጣን አስታወቀ።

ባለስልጣኑ በበጀት ዓመቱ 11 ወራት ውስጥም በአጠቃላይ 252,466.98 ቶን የቡና ምርት በመላክ 1 ቢሊየን 208 ሚሊየን 73ሺህ የአሜሪካን ዶላር በማግኘት “ሪከርድ የመስበሩን ግስጋሴ ተያይዘነዋል” ብሏል።

ኢትዮጵያ በግንቦት ወር ብቻ 43,481.02 ቶን በመላክ በወሩ ብቻ 209.54 ከእቅዷ ሚሊየን የአሜሪካን ዶላር ገቢ ማሳካት ችያለሁ ሲል ገልጿል።

ይህ ውጤት ከባለፉት 2013/2014/2015 በጀት ዓመቶች ተመሳሳይ ወራት ከተላከው ምርት እጅግ ከፍተኛ ውጤት የታየበት መሆኑን ከባለስልጣኑ ያገኘነው መረጃ ያሳያል።

ባለስልጣኑ ከዘንድሮው በጀት አመት ጋር ተቀራራቢ ገቢ ያገኘው በ2014 ዓ.ም የበጀት አመት መሆኑን በመጠቆም ለዘንድሮ አመት ስኬቱን በማስመልከት ለባለድርሻ አካላት እንኳን ደስ ያለን የሚል መልዕክት በዋናው ዳይሬክተሩ ዶ/ር አዱኛ ደበላ አስተላልፏል።

================
የአዲስ ስታንዳርድ አማርኛ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን ይቀላቀሉ፡
ቴሌግራም: https://rb.gy/rekjr
ፌስቡክ: https://rb.gy/xwxb3
ትዊተር (X)፡ https://rb.gy/34uh4
ዩቲዩብ፡ https://rb.gy/bjcbg
ድረገጽ: https://rb.gy/5td6n
ቲክቶክ፡https://rb.gy/3bghek
ዜና: ምክር ቤቱ፤ የሕዝብ #በዓላት እና የበዓላትን አከባበር ለመወሰን የወጣውን ረቂቅ አዋጅ አጸደቀ

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ባካሄደው 31ኛ መደበኛ ስብሰባው የሕዝብ በዓላትን እና የበዓላትን አከባበር ለመወሰን የወጣውን ረቂቅ አዋጅ መርምሮ አጽድቋል።

ምክር ቤቱ የአዋጁን መጽደቅ አስመልክቶ ባጋራው መረጃ በሀገር አቀፍ ደረጃ የሚከበሩ በዓላትን አልዘረዘረም።

አዋጁ በሀገር አቀፍ ደረጃ የሕዝብ በዓላት እና የበዓላትን አከባበር የሚመለከት መሆኑን ጠቁሞ ክልሎች በራሳቸው ነባራዊ ሁኔታ ህግ አውጥተው በክልል ደረጃ የሚከበሩ አዋጆችን አከባበር መወሰን እንደሚችሉ ገልጿል።

ነባሩ የሕዝብ በዓላት እና የዕረፍት ቀን መወሰኛ አዋጅ የሕዝብ በዓላት ሲከበሩ ጥቅም ሊያስገኙ በሚችሉ መልኩ በድምቀት የሚከበሩበትን ዝርዝር የአከባበር ሥነ-ሥርዓት አለማስቀመጡም ተመላክቷል፡፡

የህዝብ በዓላት አከባበር ላይ ከመንግስት የሚጠበቀውን ሰላምና ደህንነት የማስጠበቅ እንዲሁም በቂ የሚዲያ ሽፋን የሚሰጥ እንደሆነም በቀረበው የውሳኔ ሀሳብ መብራራቱ ተጠቁሟል።

የምክር ቤቱ አባላት በረቂቅ አዋጁ ላይ ሀሳብና ጥያቄ ያቀረቡ ሲሆን ከነዚህም መካከል አንዳንድ የሀይማኖት ተቋማት በረቂቅ አዋጁ ላይ ውይይት እንዳላደረጉና ቅሬታ እንዳላቸው መጠቆማቸው ይገኝበታል።

በምክር ቤቱ የጤና፣ ማህበራዊ ልማትና ስፖርት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ወ/ሮ ወርቀስሙ ማሞ በሰጡት ምላሽ ከሁሉም የሀይማኖት ተቋማት የተወከሉ የሀይማኖት አባቶች በረቂቅ አዋጁ ላይ ተወያይተዋል ብለዋል።

ምክር ቤቱ በዛሬ ሰኔ 4 ቀን 2016 ዓ.ም ውሎው የግዥ እና ንብረት አስተዳደር ረቂቅ አዋጅን ያጸደቀ ሲሆን በመንግስት ልማት ድርጅቶች ላይም ተፈፃሚ ይሆናል ተብሏል።
ዜና፡ በ #አላማጣ በተካሄደው የተቃውሞ ሰልፍ የአንድ ሰው ህይወት አለፈ፤ ነዋሪዎቹ የ #ህወሓት ታጣቂዎች ከአካባቢው እንዲወጡ ጠየቁ

ባሳለፍነው ሳምንት መገባደጃ የአላማጣ ከተማ ነዋሪዎች የመብራት ኃይል ሰራተኛ “በህወሃት ታጣቂዎች” ተገድሏል በማሉን ተከትሎ ነዋሪዎቹ ባደረጉት ሰልፍ የአንድ ሰው ህይወት ሲያልፍ፤ በርካቶች ቆስለዋል።

የአካባቢው ነዋሪ ሰልፉ የተጠራው የህወሓት ኃይሎች ከአላማጣ እና ከአካባቢው እንዲወጡ ለመጠየቅ መሆኑን ገልጿል። ነዋሪው “እየተፈጸሙ ያሉ አፈና፣ ግድያ እና ጥቃቶች ያስከተሉት ፍርሃትና ስጋት ለጥያቄው ምክንያት መሆኑን” ለአዲስ ስታንዳርድ ተናግሯል።

የአላማጣ ከተማ አስተዳደር ኃላፊ ሀይሉ አበራ በአላማጣ እና በአቅራቢያው በምትገኘው ኮረም ከተማ ውስጥ የእገታና ግድያ ወንጀል ድርጊቶች መበራከታቸውን፣ ነዋሪዎቹ “ጥቃት እየደረሰባቸው መሆኑንና ከእገታ ለመለቀቀ ክፍያ እንዲከፍሉ” እየተገደዱ መሆኑን ለአዲስ ስታንዳርድ አስረድተዋል።

ሙሉ ዘገባውን ለማንበብ፦ https://wp.me/pfjhHd-1c4
ዜና: የኢሠማኮ ፕሬዝዳንት አቶ ካሳሁን ፎሎ ለቀጣዮቹ 3 ዓመታት የዓለም ሥራ ድርጅት (ILO) አስተዳደር ዘርፍን እንዲመሩ ተመረጡ

በጀኔቫ ስዊዘርላንድ እየተካሄደ ባለው የዓለም ሥራ ድርጅት (ILO) 12ኛ ጉባኤ #የኢትዮጵያ ሠራተኞች ማኅበራት ኮንፈደሬሽን (ኢሠማኮ) ፕሬዝዳንት የሆኑትን አቶ ካሳሁን ፎሎ ለቀጣዮቹ 3 ዓመታት የድርጅቱን የአስተዳደር ዘርፍ (Governing Body) እንዲመሩ መምረጡ ተገለጸ።

የዓለም ሥራ ድርጅት (ILO) እያካሄደ ባለው ጉባኤው ድርጅቱን ለቀጣይ 3 ዓመታት በበላይነት የሚቆጣጠሩና የሚያስተዳድሩ አካላትን ከሠራተኞች፣ ከመንግሥታትና ከአሠሪዎች መካከል መምረጡ ተጠቁሟል።

ድርጅቱ ባካሄደው ምርጫም ካሳሁን ፎሎ ባገኙት ከፍተኛ ድምፅ የድርጅቱን የአስተዳደር አካል Governing Body እንዲመሩ መርጧል ሲል ኢሠማኮ በማህበራዊ ትስስር ፌስቡክ ገጹ ባጋራው መረጃ አመላክቷል።

የዓለም ሥራ ድርጅት (ILO) እያካሄደ ባለው ጉባኤው ድርጅቱን በበላይነት የሚያስተዳድሩ አባል ሀገራት መምረጡን እና ከተመረጡት ሀገራት መካከል ኢትዮጵያ አንዷ መሆናን የኢሠማኮ መረጃ ያሳያል።

ኢትዮጵያ ከአፍሪካ ከተወዳደሩት ሰባት ሀገራት መካከል ከደቡብ አፍሪካ ቀጥላ ሁለተኛ ደረጃን በመያዝ መመረጧን ጠቁሟል።

ጉባዔው ግንቦት 26 ቀን 2016 ዓ.ም መጀመሩን የጠቆመው የኢሰማኮ መረጃ ግንቦት 7 ቀን 2016 ዓ.ም ይጠናቀቃል ተብሎ እንደሚጠበቅ አስታውቋል።

==============
የአዲስ ስታንዳርድ አማርኛ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን ይቀላቀሉ፡
ቴሌግራም: https://rb.gy/rekjr
ፌስቡክ: https://rb.gy/xwxb3
ትዊተር (X)፡ https://rb.gy/34uh4
ዩቲዩብ፡ https://rb.gy/bjcbg
ድረገጽ: https://rb.gy/5td6n
ቲክቶክ፡https://rb.gy/3bghek
ዜና: የ2017 በጀት ዓመት የፌዴራል መንግስት #በጀት 971 ነጥብ 2 ቢሊዮን ብር ሆኖ ቀረበ

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ባካሄደው በ31ኛ መደበኛ ስብሰባው፤ ገንዘብ ሚኒስቴር ያቀረበውን የ2017 የፌዴራል መንግስት የካፒታል እና የመደበኛ ረቂቅ በጀት መግለጫ አድምጧል።

የገንዘብ ሚኒስትሩ አቶ አህመድ ሽዴ የ2017 ረቂቅ በጀት መግለጫ (Budget speech) በዝርዝር ለምክር ቤቱ አቅርበዋል።

በዚህም የ2017 በጀት አመት የፌዴራል መንግስት በጀት 9 መቶ 71 ነጥብ 2 ቢሊዮን ብር መሆኑን ገልጸው፤ ከባለፈው ዓመት ጋር ሲነፃጸር የ21 ነጥብ1 በመቶ እድገት ማሳየቱን አስረድተዋል።

ሚኒስትሩ አያይዘውም ለመደበኛ በጀት የዓመቱ የወጪ በጀት 451.3 ቢሊዮን ብር ሲሆን ለካፒታል ደግሞ 283.2 ቢሊዮን ብር በጀት መያዙን ለምክር ቤቱ አስረድተዋል።
https://wp.me/pfjhHd-1cc
ዜና: የዘንድሮ አመት የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ከ700 ሺህ በላይ ለሚሆኑ #ተማሪዎች በወረቀትና በኦላይን ይሰጣል ተባለ

የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ሀገር አቀፍ ፈተና ከ700 ሺህ በላይ ለሚሆኑ ተማሪዎች በወረቀትና በኦላይን ለመስጠት ዝግጅት እየተደረገ መሆኑ ትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ።

ዘንድሮ የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ሀገር አቀፍ ፈተና በድብልቅ (በወረቀትና በኦንላይን) ለመስጠት አስፈላጊው ዝግጅት እየተደረግ መሆኑን የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ም/ ዳይሬክተር አቶ ተፈራ ፈይሳ ገልጸዋል።

በትምህርት ሚኒስቴር የትምህርት ዲጅታላይዜሽንና አይሲቲ መሪ ሥራ አስፈፃሚ ዶ/ር ዘላለም አሰፋ በበኩላቸው ዘንድሮ ሀገሪቱ ካላት አቅም አንጻር በድብልቅ ፈተናውን ለመስጠት አስፈላጊው ቅድመ ዝግጅት መደርጉን አንስተው በተለይም የኦንላይን ፈተናው በተመረጡ ከተሞች ብቻ እንደሚሰጥና ቅድመ ስልጠና እስከ ትምህርት ቤት ድርስ ሲሰጥ ቆይቷል ብለዋል።

በኦንላይን ፈተናቸውን የሚወስዱ ተማሪዎችን ቴክኖሎጂውን እንዲያውቁት የተግባር ልምምድ ፈተናዎች በሶፍትዌሩ ተጭኖላቸው እንዲለማመዱና የስነልቦና ዝግጅት እንዲያደርጉ መደርጉን መሪ ሥራ አስፈጻሚው ገልጸዋል።

በተለይም የኔትዎርክ እና የመብራት መጠባበቂያ ጀኔሬተር የሌላቸው ተቋማት በፈተና ጣቢያነት እንደማይመረጡ የገለጹ ሲሆን ለዩኒቨርሲቲዎችና ከዩኒቨርሲቲ ውጪ ላሉ ተቋማት በክላስተር በማድረግ በፈተና ወቅት አስፈላጊውን የቴክኒክ ድጋፍ የሚያደርጉ ባለሙያዎች መመደባቸውንም አብራርተዋል።

ሀገር አቀፍ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት የ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ፈተና ከሃምሌ 03/2016 ጀምሮ እንደሚሰጥ መግለጹ ይታወቃል።
ዜና: #በትግራይ ከሚገኙ ወጣቶች 81 በመቶ የሚሆኑት ስራአጥ መሆናቸውን እና 40 ከመቶዎቹ መሰደድ እንደሚፈልጉ አንድ ጥናት ጠቆመ

በትግራይ ከሚገኙ ወጣቶች መካከል 81 ከመቶዎቹ ስራአጥ መሆናቸውና 40 ከመቶዎቹ መሰደድ እንደሚፈልጉ የትግራይ ወጣቶች ማሕበር ያደረገው ጥናት ጠቆመ።

ጥናቱ እንደሚያሳየው በክልሉ ለሁለት ዓመት ከተደረገዉ ጦርነት በኋላ ያለዉ ሁኔታ ለወጣቶች ተስፋ አስቆራጭ ነዉ።

ከጦርነቱ በፊት በትግራይ የስራ አጥ ወጣቶች መጠን 30 ከመቶ እንደነበረ የጠቆመው ጥናቱ የደረሰው ውድመት፣ መፈናቀል እና ሌሎች ምክንያቶች ተደምረው አሁን ላይ በትግራይ ከሚገኙ ወጣቶች መካከል 81 ከመቶዎቹ ስራ አጥ መሆናቸውን አስታውቋል።

ስራ አጥ ከሆነው በተጨማሪ 89 ከመቶ የሚሆን በትግራይ የሚገኝ ወጣት ምንም ዓይነት ገቢ እንደሌለው የትግራይ ወጣቶች ማሕበር ስራአስኪያጅ ሰናይ ከሓሰ መግለጻቸውን ከጀርመን ድምጽ የአማራኛ ድረገጽ ያገኘነው መረጃ ያሳያል።

ከፖለቲካ ተሳትፎ ጋር በተያያዘ ጥናቱ ባደረገው ዳሰሳ 66 ከመቶ የሚሆኑ የትግራይ ወጣቶች በፖለቲካ ጉዳዮች መሳተፍ እንደማይፈልጉ ገልጸዋል ያሉት ስራ አስኪያጁ ይህም ባለው ፖለቲካዊ ሁኔታ ተስፋ ከማጣት የመነጨ ሊሆን ይችላል ሲሉ መላምታቸውን ማስቀመጣቸውን ዘገባው አመላክቷል።

በተለያየ መንገድ በፖለቲካዊ ጉዳዮች መሳተፍ እንደሚፈልጉ የገለፁ 34 ከመቶ የሚሆኑ ወጣቶች ሲሆኑ፥ 10 ከመቶዎቹ በተቃውሞ የፖለቲካ ረድፍ መሰልፍ እንደሚፈልጉ የጥናቱ ውጤት ያመለክታል ማለታቸውንም አካቷል።

በትግራይ ካሉ ወጣቶች መካከል 40 ከመቶዎቹ ትግራይን ለቀው መሰደድ እንደሚሹ የትግራይ ወጣቶች ማሕበር ጥናት ያሳያል ያለው ዘገባው ሁኔታው በትግራይ ወጣቶች ዘንድ እየታየ ያለ እና አሳሳቢ ደረጃ ላይ እንደደረሰ ጠቁሟል።
ዜና፡ ያለ ፍርድ ቤት ትዕዛዝ መገናኛዎችን መጥለፍ የሚፈቅድ ረቂቅ አዋጅ ለፓርላማ ቀረበ

በወንጀል የተገኘ ንብረትን ሕጋዊ ከማስመሰል ወይም ሽብርተኝነትን በገንዘብ ከመርዳት ወንጀል ጋር በተያያዘ ያለ ፍርድ ቤት ትዕዛዝ መገናኛዎችን እና ደብዳቤዎች ለመጥለፍ ለመርማሪዎች ፈቃድ የሚሰጥ ረቂቅ አዋጅ ለተወካዮች ምክር ቤት ቀረበ።

ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የቀረበው ረቂቅ አዋጅ መርማሪ አካል “አስቸኳይ ሁኔታ ካጋጠመው” የሚመለከተውን የዐቃቤ ሕግ ተቋም የበላይ ኃላፊ በማስፈቀድ ያለፍርድ ቤት ትዕዛዝ የመገናኛ እና የደብዳቤ ልውውጦችን መጥለፍ ይችላል።

በወንጀል የተገኘ ንብረትን ሕጋዊ በማስመሰል ወንጀል ጥፋተኛ የተባለ ግለሰብ ላይ ይጣል የነበረው ከ5 እስከ 10 ሺህ ብር የገንዘብ መቀጮ ተሻሽሎ ከ100 እስከ 500 ሺህ ብር የሚያስቀጣ ሆኗል።

ተጨማሪ ለመመልከት፦ https://wp.me/pfjhHd-1cf
ዜና: #ከዳያስፖራው በሕጋዊ መንገድ ከሚላክ ገንዘብ በየዓመቱ በአማካይ ከ4 እስከ 5 ቢሊዮን ዶላር እያገኘሁ ነው ሲል መንግስት ገለጸ

በ2016 በጀት ዓመት 10 ወራት ዳያስፖራው በሕጋዊ መንገድ ወደ ሀገር ቤት ከላከው ገንዘብ (ሬሚታንስ) 4 ነጥብ 2 ቢሊዮን ዶላር መገኘቱን የፕላንና ልማት ሚኒስትር ፍጹም አሰፋ (ዶ/ር) የሚኒስትሮች ምክር ቤት እያካሄደው በሚገኘው የበጀት አመቱ የመጨረሻዎቹ የ100 ቀናት ግምገማ ላይ ባቀረቡት ሪፖርት መግለጻቸው ተጠቆመ።

ዳያስፖራው በሕጋዊ መንገድ ከሚልከው ገንዘብ (ሬሚታንስ) ባለፉት 5 ዓመታት በየዓመቱ በአማካይ ከ4 እስከ 5 ቢሊዮን ዶላር መገኘቱን የኢትዮጵያ ዳያስፖራ አገልግሎት ምክትል ዋና ዳይሬክተር በላይነህ አቅናው መናገራቸውን ከኢዜአ ያገኘነው መረጃ ያሳያል።

ከዳያስፖራው በሕጋዊ መንገድ ወደ ሀገር ቤት የሚላከው የውጭ ምንዛሬ የተሻለና እድገት እያሳየነው ሲሉ ምክትል ዋና ዳይሬክተር በላይነህ አቅናው መናገራቸውን መረጃው አካቷል።

ዳያስፖራው በሕጋዊ መንገድ የሚልኩትን የገንዘብ መጠን ለማሳደግ ገንዘብ የሚልኩባቸውን አማራጮች ቀልጣፋ ማድረግን ጨምሮ የተለያዩ የአሰራር ስርዓቶችን በመዘርጋት ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር በትብብር እየተሰራ መሆኑንም አብራርተዋል።

በሌላ በኩል በ2016 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ስምንት ወራት 1 ሺህ 745 የዳያስፖራ አባላት በሀገር ውስጥ ባንኮች የውጭ ምንዛሬ የሂሳብ ቁጥሮችን በመክፈት ከ2 ነጥብ 2 ሚሊዮን ዶላር በላይ ተቀማጭ ማድረጋቸውን ጠቁመዋል።

================
የአዲስ ስታንዳርድ አማርኛ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን ይቀላቀሉ፡
ቴሌግራም: https://rb.gy/rekjr
ፌስቡክ: https://rb.gy/xwxb3
ትዊተር (X)፡ https://rb.gy/34uh4
ድረገጽ: https://rb.gy/5td6n
ዜና: አዲስ አበባ #ዩኒቨርሲቲ ለ12 ምሁራን የሙሉ ፕሮፌሰርነት ማዕረግ ሰጠ

አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ለ12 ምሁራን የሙሉ ፕሮፌሰርነት ማዕረግ መስጠቱን አስታወቀ።

ምሁራኑ የሙሉ ፕሮፌሰርነት ማዕረግ የተሰጣቸው በማስተማር ውጤታማነት፣ ባሳተሟቸው ጥናታዊ ጹሁፎች፣ ለማህበረሰብ ላበረከቱት አካዳሚያዊ አገልግሎትና በዩኒቨርሲቲው በነበራቸው የተቋም አስተዳደር ድምር ውጤት መሆኑን ገልጿል።

ወደ ሙሉ ፕሮፌሰርነት ማዕረግ ካደጉት መካከል ሁለት ሴት ምሁራን እንደሚገኙበት ያስታወቀው እነዚህም ዩኒቨርስቲው ፕሮፌሰር እንጉዳይ አደመ በካሪኩለም ጥናት፣ ፕሮፌሰር ይምጡበዝናሽ ወ/አማኑኤል ደግሞ በሜዲካል ማይክሮ ባዮሎጂ መሆኑን ጠቁሟል።

የዩኒቨርሲቲው ሴኔት የቀረቡለትን የማዕረግ እድገት ያጸደቀው የዩኒቨርሲቲው የስራ አመራር ቦርድ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ''ስለ ራስገዝ ዩኒቨርሰቲ ለመደንገግ በወጣ'' አዋጅ ቁጥር 1294/2015 በተሰጠው ስልጣን መሠረት መሆኑን አመላክቷል።

የሙሉ ፕሮፌሰርነት ማዕረግ የተሰጣቸው 12 ምሁራንም፡-

ፕሮፌሰር ይምጡበዝናሽ ወ/አማኑኤል በ ሜዲካል ማይክሮ ባዮሎጂ
ፕሮፌሰር እንጉዳይ አደመ በካሪኩለም ጥናት
ፕሮፌሰር አንተነህ በለጠ በፍርማሴዩቲክስ
ፕሮፌሰር ካሳሁን ተስፋዬ በፕላንት ጄኔቲክስ
ፕሮፌሰር አህመደ ሁሴን በ አናሊቲካል ኬሚስትሪ
ፕሮፌሰር ታደሰ እጓለ በማይክሮባዮሎጂ
ፕሮፌሰር ተክለሀይማኖት ኃ/ሥላሴ በፕላንት ባዮቴክኖሎጂ
ፕሮፌሰር ተሸመ ሰንበታ በኮንደንስድ ማተር ፊዝክስ
ፕሮፈፌሰር ሀብቴ ተኪኤ በሜዲካል ኢንቶሞሎጂ
ፕሮፌሰር ቃላብ ባዬ በ ሂዩማን ኒውትሪሽን
ፕሮፌሰር ሰለሞን ሙሉጌታ በአርባን ፕላኒንግ
ፕሮፌሰር ሙሉጌታ ፍሰሀ በፖሊዮኢንቨሮመንታል ጥናት ናቸው።
በተለያዩ አካባቢዎች 2 ሺህ የጤና ማዕከላትን መገንባት የሚያስችል የ250 ሚሊየን ዶላር ሥምምነት ተፈረመ

በሀገሪቱ በተለያዩ አካባቢዎች 2 ሺህ የጤና ማዕከላትን ለመገንባት የጤና ሚኒስቴር፣ ከሴቶችና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር፣ ቦንጋ ዩኒቨርሲቲና #ሩስያ ፓን-አፍሪካ ፐብሊክ ፕራይቬት አጋርነት ለልማት የተሰኘ ግብረ-ሰናይ ድርጅት ጋር የመግባቢያ ሥምምነት ተፈራረሙ።

ማዕከላቱን ለመገንባት ከ250 ሚሊየን ዶላር በላይ እንደሚፈጁና ወጪውም በሩስያ ፓን-አፍሪካ ፐብሊክ ፕራይቬት አጋርነት ለልማት የሚሸፈን መሆኑ ተጠቁሟል።

የጤና ሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር ደረጄ ዱጉማ በዚህ ጊዜ፤ በሥምምነቱ መሠረት ፕሮጀክቱ ለአምስት ዓመታት እንደሚቆይና 2 ሺህ የጤና ማዕከላትን ለመገንባት እንደሚሰራ ተናግረዋል።

ማዕከላቱ በዋናነት በእናቶችና ሕጻናት ጤና፣ በአረጋውያን፣ በወጣቶች እንዲሁም በወሊድ፣ በክትባት፣ በቤተሰበ እቅድና በሥነ-ተዋልዶ ጤና ላይ ትኩረት አድርገው እንደሚሰሩ ኢዜአ ዘግቧል።

የሩስያ የፓን-አፍሪካ ፐብሊክ ፕራይቬት አጋርነት ለልማት ግብረ-ሰናይ ተቋም ዋና ሥራ አስፈጻሚ ኦክሳና ማዮሮቫ በበኩላቸው፤ ፕሮጀክቱ የዜጎችን ጤናማ ሕይወት ለማስጠበቅ አቅም የሚፈጥር ነው ብለዋል።

==============
የአዲስ ስታንዳርድ አማርኛ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን ይቀላቀሉ፡
ቴሌግራም: https://rb.gy/rekjr
ፌስቡክ: https://rb.gy/xwxb3
ትዊተር (X)፡ https://rb.gy/34uh4
ዩቲዩብ፡ https://rb.gy/bjcbg
ድረገጽ: https://rb.gy/5td6n
ቲክቶክ፡https://rb.gy/3bghek
የሽግግር ፍትህ ፖሊሲ ማስተግበሪያ ፍኖተ ካርታ የሥነ ስርዓትና ፍሬ ነገር ህጎች እየተዘጋጁ መሆኑን የፍትህ ሚኒስቴር ገለጸ

የሽግግር ፍትህ ፖሊሲን ለመተግበር በአዋጁ የተጠቀሱ ተቋማትን ማቋቋም የሚያስችሉ የሥነ ስርዓትና ፍሬ ነገር ህጎች እየተዘጋጁ መሆኑን የፍትህ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቲዮስ (ዶ/ር) ገለጹ፡፡

ሚኒስትሩ ይህን የገለጹት ጠ/ሚ አብይ አህመድ( ዶ/ር) በተገኙበት የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የበጀት ዓመቱ የመጨረሻዎቹ 100 ቀናት የህግና ፍትህ ሥርዓቱ ያለበት አፈፃፀም ግምገማ ባቀረቡበት ወቅት ነው፡፡

ቀደም ሲል የሽግግር ፍትሕ ፖሊሲውን መተግበር የሚያስችል ፍኖተ ካርታ ተጠናቅቆ ለውይይት ዝግጁ መሆኑን ሚኒስቴሩ አስታውቋል። ፍኖተ-ካርታው የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች በአባልነት የሚሳተፉበት ጊዜያዊ እና ዘላቂ ተቋማዊ የቅንጅት አመራር ሥርዓት ስለሚቋቋምበት ሁኔታ፤ ስለ ሽግግር ፍትሕ ስልቶች አተገባበር ቅደም-ተከተል መካተቱም ተመላክቷል።

የፍትህ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቲዮስ(ዶ/ር) የሽግግር ፍትህ ፖሊሲውን መተግበር የሚያስችል ፍኖተ ካርታ መውጣቱን ገልጸው በፖሊሲው የተመላከቱ ተቋማትን ማቋቋም የሚያስችሉ የሥነ ስርዓትና ፍሬ ነገር ህጎች እየተዘጋጁ መሆኑንም ጠቁመዋል።

የፍትህ ዘርፉን ለማሻሻል በፌደራልና በክልል ደረጃ ገቢራዊ የሚደረጉ ሀገር አቀፍ ህጎችና አሰራሮች መውጣታቸውን ጠቅሰው፣ የአስተዳደር ሥነ ስርዓት አዋጅን ማስተግበር፣ የወንጀል ሥነ ስርዓት አጽድቆ ገቢራዊ ማድረግም በትኩረት እየተከናወነ ነው ብለዋል።
#አማራ ክልል ከአንድ ሚሊዮን በላይ ሰዎች በወባ በሽታ መያዛቸው ተገለፀ

በአማራ ክልል ባለፉት 11 ወራት ብቻ ከ1 ሚሊዮን በላይ ሰዎች በወባ በሽታ መጠቃታቸውን የክልሉ ህብረተሰብ ጤና እንስቲትዩት አስታወቀ።

የክልሉ ጤና ቢሮና የከተማ አስተዳደሩ ጤና መምሪያ ኃላፊዎችም በበኩላቸው በክልሉ የወባ በሽታ በከፋ ሁኔታ ጉዳት እያደረሰ መሆኑን ገልፀዋል።

የክልሉ የጤና ተቋማት ኃላፊዎች እንደገለፁት በክልሉ ያለው ግጭት ሳቢያ በተደጋጋሚ የመንገዶች መዘጋጋት የወባ ሥራ ቁጥጥርን አዳክሞታል። የመድኃኒት ስርጭትን ደግሞ አስተጓጉሎታል። ይህም ችግሩ እንዲባባስ አድርጓል። ህብረተሰቡ ወባን ለመከላከል ያለው ዝቅተናኛ ግንዛቤና ቸልተኝነት ደግሞ ሌላው ምክንያት ነው ሲሉ ሀላፊዎቹ ገልፀዋል።

የባህርዳር ነዋሪዎችም በበኩላቸው በከተማው የወባ ስርጭት መበራከቱን ይገልጻሉ። የባህር ዳር ከተማ አስተዳደር ጤና መምሪያ ኃላፊ ወ/ሮ ዓለም አሰፋ ባለፈው ሳምንት 7ሺህ ሰዎች የወባ ምርመራ አድርገው በ2ሺህ 460 ሰዎች ላይ በሽታው ተገኝቷል ብለዋል፡፡

(ዶቼ ቬሌ)