ዜና: አዲስ አበባ #ዩኒቨርሲቲ ለ12 ምሁራን የሙሉ ፕሮፌሰርነት ማዕረግ ሰጠ
አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ለ12 ምሁራን የሙሉ ፕሮፌሰርነት ማዕረግ መስጠቱን አስታወቀ።
ምሁራኑ የሙሉ ፕሮፌሰርነት ማዕረግ የተሰጣቸው በማስተማር ውጤታማነት፣ ባሳተሟቸው ጥናታዊ ጹሁፎች፣ ለማህበረሰብ ላበረከቱት አካዳሚያዊ አገልግሎትና በዩኒቨርሲቲው በነበራቸው የተቋም አስተዳደር ድምር ውጤት መሆኑን ገልጿል።
ወደ ሙሉ ፕሮፌሰርነት ማዕረግ ካደጉት መካከል ሁለት ሴት ምሁራን እንደሚገኙበት ያስታወቀው እነዚህም ዩኒቨርስቲው ፕሮፌሰር እንጉዳይ አደመ በካሪኩለም ጥናት፣ ፕሮፌሰር ይምጡበዝናሽ ወ/አማኑኤል ደግሞ በሜዲካል ማይክሮ ባዮሎጂ መሆኑን ጠቁሟል።
የዩኒቨርሲቲው ሴኔት የቀረቡለትን የማዕረግ እድገት ያጸደቀው የዩኒቨርሲቲው የስራ አመራር ቦርድ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ''ስለ ራስገዝ ዩኒቨርሰቲ ለመደንገግ በወጣ'' አዋጅ ቁጥር 1294/2015 በተሰጠው ስልጣን መሠረት መሆኑን አመላክቷል።
የሙሉ ፕሮፌሰርነት ማዕረግ የተሰጣቸው 12 ምሁራንም፡-
ፕሮፌሰር ይምጡበዝናሽ ወ/አማኑኤል በ ሜዲካል ማይክሮ ባዮሎጂ
ፕሮፌሰር እንጉዳይ አደመ በካሪኩለም ጥናት
ፕሮፌሰር አንተነህ በለጠ በፍርማሴዩቲክስ
ፕሮፌሰር ካሳሁን ተስፋዬ በፕላንት ጄኔቲክስ
ፕሮፌሰር አህመደ ሁሴን በ አናሊቲካል ኬሚስትሪ
ፕሮፌሰር ታደሰ እጓለ በማይክሮባዮሎጂ
ፕሮፌሰር ተክለሀይማኖት ኃ/ሥላሴ በፕላንት ባዮቴክኖሎጂ
ፕሮፌሰር ተሸመ ሰንበታ በኮንደንስድ ማተር ፊዝክስ
ፕሮፈፌሰር ሀብቴ ተኪኤ በሜዲካል ኢንቶሞሎጂ
ፕሮፌሰር ቃላብ ባዬ በ ሂዩማን ኒውትሪሽን
ፕሮፌሰር ሰለሞን ሙሉጌታ በአርባን ፕላኒንግ
ፕሮፌሰር ሙሉጌታ ፍሰሀ በፖሊዮኢንቨሮመንታል ጥናት ናቸው።

በተለያዩ አካባቢዎች 2 ሺህ የጤና ማዕከላትን መገንባት የሚያስችል የ250 ሚሊየን ዶላር ሥምምነት ተፈረመ
በሀገሪቱ በተለያዩ አካባቢዎች 2 ሺህ የጤና ማዕከላትን ለመገንባት የጤና ሚኒስቴር፣ ከሴቶችና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር፣ ቦንጋ ዩኒቨርሲቲና #ሩስያ ፓን-አፍሪካ ፐብሊክ ፕራይቬት አጋርነት ለልማት የተሰኘ ግብረ-ሰናይ ድርጅት ጋር የመግባቢያ ሥምምነት ተፈራረሙ።
ማዕከላቱን ለመገንባት ከ250 ሚሊየን ዶላር በላይ እንደሚፈጁና ወጪውም በሩስያ ፓን-አፍሪካ ፐብሊክ ፕራይቬት አጋርነት ለልማት የሚሸፈን መሆኑ ተጠቁሟል።
የጤና ሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር ደረጄ ዱጉማ በዚህ ጊዜ፤ በሥምምነቱ መሠረት ፕሮጀክቱ ለአምስት ዓመታት እንደሚቆይና 2 ሺህ የጤና ማዕከላትን ለመገንባት እንደሚሰራ ተናግረዋል።
ማዕከላቱ በዋናነት በእናቶችና ሕጻናት ጤና፣ በአረጋውያን፣ በወጣቶች እንዲሁም በወሊድ፣ በክትባት፣ በቤተሰበ እቅድና በሥነ-ተዋልዶ ጤና ላይ ትኩረት አድርገው እንደሚሰሩ ኢዜአ ዘግቧል።
የሩስያ የፓን-አፍሪካ ፐብሊክ ፕራይቬት አጋርነት ለልማት ግብረ-ሰናይ ተቋም ዋና ሥራ አስፈጻሚ ኦክሳና ማዮሮቫ በበኩላቸው፤ ፕሮጀክቱ የዜጎችን ጤናማ ሕይወት ለማስጠበቅ አቅም የሚፈጥር ነው ብለዋል።
==============
የአዲስ ስታንዳርድ አማርኛ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን ይቀላቀሉ፡
ቴሌግራም: https://rb.gy/rekjr
ፌስቡክ: https://rb.gy/xwxb3
ትዊተር (X)፡ https://rb.gy/34uh4
ዩቲዩብ፡ https://rb.gy/bjcbg
ድረገጽ: https://rb.gy/5td6n
ቲክቶክ፡https://rb.gy/3bghek

የሽግግር ፍትህ ፖሊሲ ማስተግበሪያ ፍኖተ ካርታ የሥነ ስርዓትና ፍሬ ነገር ህጎች እየተዘጋጁ መሆኑን የፍትህ ሚኒስቴር ገለጸ
የሽግግር ፍትህ ፖሊሲን ለመተግበር በአዋጁ የተጠቀሱ ተቋማትን ማቋቋም የሚያስችሉ የሥነ ስርዓትና ፍሬ ነገር ህጎች እየተዘጋጁ መሆኑን የፍትህ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቲዮስ (ዶ/ር) ገለጹ፡፡
ሚኒስትሩ ይህን የገለጹት ጠ/ሚ አብይ አህመድ( ዶ/ር) በተገኙበት የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የበጀት ዓመቱ የመጨረሻዎቹ 100 ቀናት የህግና ፍትህ ሥርዓቱ ያለበት አፈፃፀም ግምገማ ባቀረቡበት ወቅት ነው፡፡
ቀደም ሲል የሽግግር ፍትሕ ፖሊሲውን መተግበር የሚያስችል ፍኖተ ካርታ ተጠናቅቆ ለውይይት ዝግጁ መሆኑን ሚኒስቴሩ አስታውቋል። ፍኖተ-ካርታው የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች በአባልነት የሚሳተፉበት ጊዜያዊ እና ዘላቂ ተቋማዊ የቅንጅት አመራር ሥርዓት ስለሚቋቋምበት ሁኔታ፤ ስለ ሽግግር ፍትሕ ስልቶች አተገባበር ቅደም-ተከተል መካተቱም ተመላክቷል።
የፍትህ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቲዮስ(ዶ/ር) የሽግግር ፍትህ ፖሊሲውን መተግበር የሚያስችል ፍኖተ ካርታ መውጣቱን ገልጸው በፖሊሲው የተመላከቱ ተቋማትን ማቋቋም የሚያስችሉ የሥነ ስርዓትና ፍሬ ነገር ህጎች እየተዘጋጁ መሆኑንም ጠቁመዋል።
የፍትህ ዘርፉን ለማሻሻል በፌደራልና በክልል ደረጃ ገቢራዊ የሚደረጉ ሀገር አቀፍ ህጎችና አሰራሮች መውጣታቸውን ጠቅሰው፣ የአስተዳደር ሥነ ስርዓት አዋጅን ማስተግበር፣ የወንጀል ሥነ ስርዓት አጽድቆ ገቢራዊ ማድረግም በትኩረት እየተከናወነ ነው ብለዋል።

በ #አማራ ክልል ከአንድ ሚሊዮን በላይ ሰዎች በወባ በሽታ መያዛቸው ተገለፀ
በአማራ ክልል ባለፉት 11 ወራት ብቻ ከ1 ሚሊዮን በላይ ሰዎች በወባ በሽታ መጠቃታቸውን የክልሉ ህብረተሰብ ጤና እንስቲትዩት አስታወቀ።
የክልሉ ጤና ቢሮና የከተማ አስተዳደሩ ጤና መምሪያ ኃላፊዎችም በበኩላቸው በክልሉ የወባ በሽታ በከፋ ሁኔታ ጉዳት እያደረሰ መሆኑን ገልፀዋል።
የክልሉ የጤና ተቋማት ኃላፊዎች እንደገለፁት በክልሉ ያለው ግጭት ሳቢያ በተደጋጋሚ የመንገዶች መዘጋጋት የወባ ሥራ ቁጥጥርን አዳክሞታል። የመድኃኒት ስርጭትን ደግሞ አስተጓጉሎታል። ይህም ችግሩ እንዲባባስ አድርጓል። ህብረተሰቡ ወባን ለመከላከል ያለው ዝቅተናኛ ግንዛቤና ቸልተኝነት ደግሞ ሌላው ምክንያት ነው ሲሉ ሀላፊዎቹ ገልፀዋል።
የባህርዳር ነዋሪዎችም በበኩላቸው በከተማው የወባ ስርጭት መበራከቱን ይገልጻሉ። የባህር ዳር ከተማ አስተዳደር ጤና መምሪያ ኃላፊ ወ/ሮ ዓለም አሰፋ ባለፈው ሳምንት 7ሺህ ሰዎች የወባ ምርመራ አድርገው በ2ሺህ 460 ሰዎች ላይ በሽታው ተገኝቷል ብለዋል፡፡
(ዶቼ ቬሌ)

ዜና፡ #ለፓርላማ የቀረበው ያለ ፍርድ ቤት ትዕዛዝ መገናኛዎችን መጥለፍ የሚፈቅድ ረቂቅ አዋጅ ተቃዋሚዎችን ማሳደጃ እንዳይሆን የምክር ቤቱ አባላት አሳሰቡ
ከምክር ቤቱ አባላት ጥያቄዎች እና አስተያያቶች ካነሱት መካከል በቅርቡ ለእስር ተዳርገው የተፈቱት የፓርላማው አባል ዶ/ር ደሳለኝ ጫኔ ይገኙበታል።
ዶ/ር ደሳለኝ ስጋት እና አስተያየት በሚል ባቀረቡት ሀሳብ ለምክር ቤቱ የሚቀርቡ ወንጀል እና ሽብር ነክ አዋጆች አስፈላጊነታቸው እንደተጠበቀ ሁኖ ተቃዋሚዎችን እና መንግስትን የሚተቹ ተቋማት የነዚህ አይነት ህጎች ሰለባ ሁነው ብዙ ጉዳት እንደደረሰባቸው በማውሳት ጥንቃቄ እንዲደረግባቸው አሳስበዋል።
አዋጆቹን ገዢው ፓርቲ ተቃዋሚዎችን ለማሳደድ እንዳያውለው ምን ዝግጅት ተደርጓል ሲሉ ማብራሪያ እንዲሰጥበት በመጠየቅ አዋጆቹ የወንጀል ፍሬ የሆኑትን ብቻ ለይቶ ለመከታተል እና ተቃዋሚዎችን ማሳደጃ እንዳይሆን ተገቢ ድንጋጌዎች እንዲካተቱባቸው ሲሉ አሳስበዋል።
ሌላ የምክር ቤቱ አባል በበኩላቸው በአካል በአዋጁ አንቀጽ “በቂ ቁጥጥር ከማያደርጉ የፋይናንስ ተቋማት ጋር የንግድ ግንኙነት ከመሰረተ ወይንም የነበረውን የንግድ ግንኙነት ካስቀጠለ” የሚለው ሃሳብ አሻሚ መሆኑን ጠቁመዋል።
ሃሳቡ ውስብስብ ከመሆኑ ባለፈ ባንኮቹ ትክክለኛ ቁጥጥር ከሚደረግባቸው መሆናቸውንም ሆነ አለመሆናቸውን ማን ነው የሚያረጋግጠው ሲሉ ጠይቀዋል፤ ውጭ ሀገር ያለን ባንክ እንዴት ነው ማረጋገጥ የምንችለው፣ እነዴት በዝርዝር ማስቀመጥ ይችላል ብለዋል።
https://wp.me/pfjhHd-1cj

Addis standard
ለፓርላማ የቀረበው ያለ ፍርድ ቤት ትዕዛዝ መገናኛዎችን መጥለፍ የሚፈቅድ ረቂቅ አዋጅ ተቃዋሚዎችን ማሳደጃ እንዳይሆን የምክር ቤቱ አባላት አሳሰቡ - Addis standard
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 6/2016 ዓ.ም፡- ለፓርላማ የቀረበው “በወንጀል የተገኘ ንብረትን ሕጋዊ ከማስመሰል ወይም ሽብርተኝነትን በገንዘብ ከመርዳት ወንጀል ጋር በተያያዘ ያለ ፍርድ ቤት ትዕዛዝ መገናኛዎችን እና ደብዳቤዎች ለመጥለፍ ለመርማሪዎች ፈቃድ የሚሰጥ ረቂቅ አዋጅ” ተቃዋሚዎችን ማሳደጃ እንዳይሆን የህ/ተ/ም አባላት አሳሰቡ። ትላንት ለህዝብ ተወካዮች ም/ ቤት የቀረበው ረቂቅ አዋጅ መርማሪ አካል “አስቸኳይ…
ዜና: #የኳታሩ አሚር ከጠ/ሚ አብይ እና #ከሶማሊያው ፕሬዝዳንት ሸክ ሀሰን ጋር በተናጠል በስልክ መወያየታቸው ተገለጸ
የኳታሩ አሚር ሸክ ታሚም ቢን ሃመድ አል ታኒ ከጠ/ሚኒስትር ዶ/ር #አብይ አህመድ ጋር በስልክ ማውራታቸው ተገለጸ።
የኳታሩ አሚር ከጠ/ሚኒስትር አብይ ጋር በስልክ ማውራታቸው ከተገለጸ በሰአታት ልዩነት ከሶማሊያ ፕሬዝዳንት ሸክ ሀሰን ጋር ማውራታቸውን የኳታር መገናኛ ብዙሃን አስታውቀዋል።
የኳታሩ መሪ ሸክ ታሚም ቢን ሃመድ አል ታኒ ከጠ/ሚኒስትር ዶ/ር አብይ ጋር የሀገራቱን ግንኙነት መደገፍ እና ማሳደግ በሚቻልባቸው መንገዶች እንዲሁም አሳሳቢ በሆኑ ቀጠናዊ እና አለም አቀፍ ጉዳዮች ላይ መክረዋል ብለዋል።
የኳታሩ መሪ ከጠ/ሚኒስትር ዶ/ር አብይ ጋር በወቅታዊ የኢትዮጵያ እና ሶማሊያ ውጥረት ዙሪያ ስለመወያየታቸው ያሉት ነገር የለም።
የሀገሪቱ መገናኛ ብዙሃን ሸክ ታሚም ቢን ሃመድ አል ታኒ ከሶማሊያው ፕሬዝዳንት ሸክ ሀሰን ጋር በስልክ መወያየታቸውን ባሳወቁበት ዘገባቸው ሁለቱ መሪዎች የሀገራቱን ግንኙነት ማሳደግ በሚቻልባቸው ሁኔታዎች ዙሪያ ተወያዩ ከማለት በቀር ያቀረቡት መረጃ የለም።
መሪዎቹ በሶማሊያ ወቅታዊ ሁኔታ፣ በቀጠናዊ እና አለምአቀፍ ጉዳዮች ተወያይተዋል ሲሉ ገልጸዋል።
ከቀናት በፊት የገንዘብ ሚኒስትሩ አቶ አህመድ ሺዴ ወደ ኳታር በማቅናት ከሀገሪቱ የገንዘብ ሚኒስትር ጋር መወያየታቸውን የመንግስት መገናኛ ብዙሃን መዘገባቸው ይታወሳል።
አህመድ ሽዴ ከኳታር አቻቸው አሊ ቢን አህመድ አል ኩዋሪ ጋር ባደረጉት ውይይት በኢትዮጵያና በኳታር በፋይናንስ፣ በልማት ትብብር እና ኢንቨስትመንት ዙሪያ መምከራቸውንም አስታውቀዋል።

ዜና፡ ከ #አዋሽ_አርባ ወደ #አዲስ_አበባ የተዘዋወሩት ፖለቲከኞች ፍርድ ቤት ቀረቡ፤ ሶስት ጋዜጠኞች “አካልን ነጻ የማውጣት” አቤቱታ አቀረቡ
ህዳር 30 ተጠርቶ ከነበረው ሰልፍ ጋር ተያይዞ ከሁለት ወራት በላይ አዋሽ አርባ የወታደራዊ ካምፕ እስር ላይ ቆይተው ወደ አዲስ አበባ ከተዘዋወሩት ተጠርጣሪዎች መካከል ዘጠኙ ለሁለተኛ ጊዜ ፍርድ ቤት ሲቀርቡ፤ “ከአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ጋር በተያያዘ” በእስር ላይ የሚገኙ ሶስት ጋዜጠኞች “አካልን ነጻ የማውጣት” አቤቱታ አቀረቡ።
“ጦርነት ይብቃ፣ ሰላም ይስፈን” በሚል መሪ ቃል ህዳር 30 ሰላማዊ ሰልፍ የጠሩት ፖለቲካኞች የተጠረጠሩት “በሁከት እና በብጥብጥ በተለያዩ ነገሮች ላይ በመሳተፍ ህገ መንግስታዊ ስረዓቱን ለመናድ ሲሰሩ” መሆኑን ፖሊስ ገልጿል።
ይህ በእንዲ እያለ የተፈጻሚነት የጊዜ ወሰኑ ባለፈው ሳምንት ካበቃው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ጋር በተያያዘ በእስር ላይ የሚገኙ ሶስት ጋዜጠኞች፤ “አካልን ነጻ የማውጣት” አቤቱታ ለፍርድ ቤት አቅርበዋል። አቤቱታውን በጠበቆቻቸው በኩል ለፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ያቀረቡት ጋዜጠኞች #በቃሉ_አላምረው፣ #በላይ_ማናዬ እና #ቴዎድሮስ_ዘርፉ ናቸው።
ሙሉ ዘገባውን ለማግኘት፦ https://wp.me/pfjhHd-1cn

ዜና፡ ከአዋሽ አርባ ወደ አዲስ አበባ የተዘዋወሩት ፖለቲከኞች ፍርድ ቤት ቀረቡ፤ ሶስት ጋዜጠኞች “አካልን ነጻ የማውጣት” አቤቱታ አቀረቡ - Addis standard
አዲስ አበባ ሰኔ 6/ 2016 ዓ/ም፦ ህዳር 30 ተጠርቶ ከነበረው ሰልፍ ጋር ተያይዞ ከሁለት ወራት በላይ አዋሽ አርባ የወታደራዊ ካምፕ እስር ላይ ቆይተው ወደ አዲስ አበባ ከተዘዋወሩት ተጠርጣሪዎች መካከል ዘጠኙ ለሁለተኛ ጊዜ ፍርድ ቤት ሲቀርቡ፤ “ከአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ጋር በተያያዘ” በእስር ላይ የሚገኙ ሶስት ጋዜጠኞች “አካልን ነጻ የማውጣት” አቤቱታ አቀረቡ። “ጦርነት ይብቃ፣ ሰላም ይስፈን” በሚል…
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
በአገሪቱ እየተካሄዱ ያሉ ግጭቶች የማክሮኢኮኖሚ ጉዳት አስከትለዋል _ የአማራ በሔራዊ ንቅናቄ (አብን) ተወካዪ ደሳለኝ ጫኔ ( ዶ/ር)
የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ባካሄደው በ31ኛ መደበኛ ስብሰባው፤ ገንዘብ ሚኒስቴር ያቀረበውን የ2017 የፌዴራል መንግስት የካፒታል እና የመደበኛ ረቂቅ በጀት መግለጫ ከትላንት በስቲያ አድምጧል፡፡ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላቱ የማክሮ ኢኮኖሚ አለመረጋጋትና እየተካሄዱ ያሉ ግጭቶች በአገሪቱ ኢኮኖሚ ላይ ያለው ተፅዕኖን በተመለከተ ስጋታቸውን አንስተዋል።
የአማራ በሔራዊ ንቅናቄ (አብን) ተወካዪ ደሳለኝ ጫኔ ( ዶ/ር) በ #ኦሮሚያ ለስድስት ዓመታት የዘለቀው ግጥት እና በ #አማራ፣ በ #ትግራይ እንዲሁም በ #አፋር ከሶስት ዓመታት በላይ የተካሄዱ ግጭቶች የማክሮኢኮኖሚ ጉዳት አስከትሏል ብለዋል።
የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ለተነሱ ጥያቄዎች ምላሽ የሰጡት የገንዘብ ሚንስትሩ አህመድ ሽዴ በኦሮሚያ፣ ትግራይ፣ አማራና አፋር በግጭቶች የተጎዱ አካባቢዎች መኖራቸውን አምኗል። ይሁን እንጂ የኢኮኖሚ ማሻሻያው "ጠንካራ እድገት" በማምጣቱን ገልጸዋል።
ይመልከቱ!

ዜና: #ኢትዮጵያ ምንም አይነት “የአቪዬሽን ደህንነት ስጋት የሌለባት ሀገር” ናት ሲል የዓለም አቀፉ አቪዬሽን ድርጅት ኦዲተሮች ማረጋገጫ ሰጥቷል ተባለ
የዓለም አቀፉ አቪዬሽን ድርጅት ኦዲተሮች ባለፉት 10 ቀናት የአቪዬሽን ኢንዱስትሪውን ደህንነት መፈተሻቸውን የገለጹት በብሔራዊ መረጃ ደህንነት አገልግሎት የሲቪል አቪዬሽን ደህንነት መምሪያ ዳይሬክተር አስራት ቀጀላ ፍተሻው የተከናወነው ከግንቦት 26 እስከ ሰኔ 6 መሆኑን አስታውቀዋል።
በቦሌ ኤርፖርት እና በሌሎች አየር ማረፊያዎች በተደረገው ኦዲት ኢትዮጵያ ምንም አይነት የአቪዬሽን ደህንነት ስጋት የሌለባት መሆኑን የድርጅቱ ገምጋሚዎች መገልፃቸውን ዳይሬክተሩ የፍተሻውን መጠናቀቅ አስመልክተው በሰጡት መግለጫ አመላክተዋል።
እንዲስተካከሉ አስተያየት የተሰጠባቸውን የሕግ ማዕቀፍ ማሻሻያ እና ሌሎች ጉዳዮች በፍጥነት እንደሚስተካከሉም ጠቁመዋል።
ከሲቪል አቪዬሽን ደህንነት አንፃር በድርጅቱ መስፈርት መሰረት በቁጥር የተሟላ የኦዲቱ ሪፖርት በቅርቡ አዘጋጅተው እንደሚያስረክቡ ተጠቅሷል።
ይህ የኦዲት ውጤት በዘርፉ ለመሰማራት ለሚፈልጉ አካላት ወደ ስራ እንዲገቡ፣ ለሀገሪቱ የቱሪዝም እና የአቪዬሽን ዘርፍ እድገት አስተዋፅኦው የላቀ ነው ተብሏል።
ለዚህ ውጤት መገኘት በዘርፉ በቅንጅት የሚሰሩት የኢትዮጵያ አየር መንገድ፣ የብሔራዊ መረጃ ደኅንነት አገልግሎት፣ ፌደራል ፖሊስ ፣ ጉሙሩክን ጨምሮ ሌሎች ባለድርሻ አካላት ሚና ትልቅ እንደነበርም በመግለጫው ተጠቅሷል።

ዜና: በበጀት ዓመቱ የመዲናዋን ሰላምና #ጸጥታ አስተማማኝ ለማድረግ የከተማዋ ከ140 ሺህ በላይ የሰላም ሠራዊት የነቃ ተሳትፎ ነበረው ተባለ
በመዲናዋ ሰላምና ጸጥታን አስተማማኝ በማድረግ ረገድ የተከናወኑ የተቀናጁ አሠራሮች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ #የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ ሊዲያ ግርማ ገለጹ።
ሃላፊዋ የመዲናዋን ሰላምና ጸጥታ በአስተማማኝ መልኩ በማስጠበቅና ሕገ-ወጥነትን በመከላከል ቅንጅታዊ አሠራሮች ተግባራዊ መደረጋቸውን አስታውቀዋል።
በዚህ ረገድ ከ21 የተለያዩ ተቋማት ጋር በቅንጅት መሠራቱን አስታውሰው፤ ይኸው ውጤታማ ተግባር ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም አረጋግጠዋል።
ከኅብረተሰቡ ጋር በመተባበር በወንጀል መከላከል፣ የፀረ-ሰላምና ጽንፈኛ ኃይሎችን እኩይ ዓላማ በማክሸፍ ረገድ በርካታ ስኬታማ ሥራዎች ተከናውነዋል ተብሏል።
በወንጀል ተግባር ላይ የተሰማሩ አካላትን በቁጥጥር ሥር በማዋል በሕግ ተጠያቂ እንዲሆኑ በማድረግም እንዲሁ።
የአዲስ አበባ ከተማ የሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ምክትል ቢሮ ኃላፊ ጌታሁን አበራ፤ የወንጀል መከላከሉ ሥራ ሕብረተሰቡን ያሳተፈ በመሆኑ ለውጤታማነቱ የላቀ አስተዋጽዖ ማበርከቱን አንስተዋል።
ከ140 ሺህ በላይ የሰላም ሠራዊት በየአካባቢያቸው የሰላምና ጸጥታ ሥራ በመሥራት የነበራቸውን የነቃ ተሳትፎም ለአብነት መጠቀሱን ከኢዜአ ያገኘነው መረጃ ያሳያል።
================
የአዲስ ስታንዳርድ አማርኛ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን ይቀላቀሉ፡
ቴሌግራም: https://rb.gy/rekjr
ፌስቡክ: https://rb.gy/xwxb3
ትዊተር (X)፡ https://rb.gy/34uh4
ዩቲዩብ፡ https://rb.gy/bjcbg
ድረገጽ: https://rb.gy/5td6n
ቲክቶክ፡https://rb.gy/3bghek
በመዲናዋ ሰላምና ጸጥታን አስተማማኝ በማድረግ ረገድ የተከናወኑ የተቀናጁ አሠራሮች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ #የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ ሊዲያ ግርማ ገለጹ።
ሃላፊዋ የመዲናዋን ሰላምና ጸጥታ በአስተማማኝ መልኩ በማስጠበቅና ሕገ-ወጥነትን በመከላከል ቅንጅታዊ አሠራሮች ተግባራዊ መደረጋቸውን አስታውቀዋል።
በዚህ ረገድ ከ21 የተለያዩ ተቋማት ጋር በቅንጅት መሠራቱን አስታውሰው፤ ይኸው ውጤታማ ተግባር ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም አረጋግጠዋል።
ከኅብረተሰቡ ጋር በመተባበር በወንጀል መከላከል፣ የፀረ-ሰላምና ጽንፈኛ ኃይሎችን እኩይ ዓላማ በማክሸፍ ረገድ በርካታ ስኬታማ ሥራዎች ተከናውነዋል ተብሏል።
በወንጀል ተግባር ላይ የተሰማሩ አካላትን በቁጥጥር ሥር በማዋል በሕግ ተጠያቂ እንዲሆኑ በማድረግም እንዲሁ።
የአዲስ አበባ ከተማ የሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ምክትል ቢሮ ኃላፊ ጌታሁን አበራ፤ የወንጀል መከላከሉ ሥራ ሕብረተሰቡን ያሳተፈ በመሆኑ ለውጤታማነቱ የላቀ አስተዋጽዖ ማበርከቱን አንስተዋል።
ከ140 ሺህ በላይ የሰላም ሠራዊት በየአካባቢያቸው የሰላምና ጸጥታ ሥራ በመሥራት የነበራቸውን የነቃ ተሳትፎም ለአብነት መጠቀሱን ከኢዜአ ያገኘነው መረጃ ያሳያል።
================
የአዲስ ስታንዳርድ አማርኛ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን ይቀላቀሉ፡
ቴሌግራም: https://rb.gy/rekjr
ፌስቡክ: https://rb.gy/xwxb3
ትዊተር (X)፡ https://rb.gy/34uh4
ዩቲዩብ፡ https://rb.gy/bjcbg
ድረገጽ: https://rb.gy/5td6n
ቲክቶክ፡https://rb.gy/3bghek
ዜና: #በጂቡቲ የሚገኝ የሶስት መርከቦች የአፈር ማዳበሪያ ወደ ሀገር ውስጥ ለማጓጓዝ ጥረት እየተደረገ ነው ተባለ
ከአንድ ነጥብ ሶስት ሚሊየን ሜትሪክ ቶን በላይ የአፈር ማዳበሪያ ወደ ሀገር ውስጥ መጓጓዙን እና ይህም የመንግስት አፈጻጸም 69 በመቶ መሆኑን የሚያመላክት መሆኑ ተገለጸ።
በጂቡቲ የሚገኝ የሶስት መርከቦች የአፈር ማዳበሪያ ወደ ሀገር ውስጥ ለማጓጓዝ ጥረት እየተደረገ መሆኑም ተጠቁሟል።
የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስትር ዶ/ር አለሙ ስሜ በጂቡቲ ከሚገኘው የአፈር ማዳበሪያ ኦፕሬሽን ኮሚቴ ጋር በኤምባሲው ቅጥር ግቢ በመገኘት በአፈር ማዳበሪያ ዝውውር አፈጻጸም ዙሪያ ውይይት ማካሄዳቸው ተገልጿል።
የማዳበሪያ ኦፕሬሽን ኮሚቴው ባቀረበው ሪፖርት እስከአሁን 27 የአፈር ማዳበሪያ የጫኑ መርከቦች ጂቡቲ የደረሱ ሲሆን ከዚህ ውስጥ የ24 መርከቦች የአፈር ማዳበሪያ ጭነት ከጂቡቲ ወደብ ወደ #ኢትዮጵያ እየተጓጓዙ መሆኑን በመግለጽ፣ ቀሪ 3 መርከቦች በኦፕሬሽን ላይ እንደሚገኙ አስታውቋል።
በዘህ መሰረት እስከአሁን 1,334,487.1 ሜትሪክ ቶን የአፈር ማዳበሪያ በተሳካ ሁኔታ ወደ ሀገር ውስጥ ማጓጓዝ በመቻሉ ከዓመታዊ እቅድ 68.78% መሳካቱን ኮሚቴው መግለጹን ከኤምባሲው ያገኘነው መረጃ ያሳያል።
ሚኒስትሩም እስከአሁን በተሰሩ የማጓጓዝ ስራዎች ኮሚቴውን በማመስገን፣ አሁንም የአፈር ማዳበሪያ ጉዳይ የሞት ሽረት ጉዳይ መሆኑን በመረዳት ኮሚቴው በማጓጓዝ ሂደቱ ላይ ያጋጠሙ ችግሮች ተቀርፈው ቀሪ የማዳበሪያ ጭነቶች በተጠናከረ መልኩ ተቀናጅቶ በመስራት በሰዓቱ ለአገራችን ገበሬዎች ማድረስ እንዲቻል አቅጣጫ መስጠታቸው ተጠቁሟል።

በ #ኦጋዴን ከ21 ቢሊዮን ሜትር ኪዩብ በላይ የተፈጥሮ ጋዝ መኖሩ ተረጋገጠ_ የማዕድን ሚኒስቴር
በ #ሶማሌ ክልል ኦጋዴን 19 ጉድጓዶችን በመቆፈር በተደረገ ዳሰሳ "21 ቢሊዮን 336 ሚሊዮን ኩቢክ ሜትር የተፈጥሮ ጋዝ እንዳለ" መረጋገጡን የማዕድን ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡
የማዕድን ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ሚሊዮን ማትዮስ፤ በሌሎች ስድስት ቦታዎች ላይም ነዳጅና የተፈጥሮ ጋዝ ሀብት መኖሩን ኢፕድ ተናግረዋል፡፡
#ኦጋዴን፣ #መቀሌ፣ #መተማ፣ #ደቡብ_ኦሞ እንዲሁም #ጋምቤላ አካባቢዎች በዋናነት ተጠቃሽ መሆናቸውንም አስገንዝበዋል፡፡
እንደ አቶ ሚሊዮን ገለጻ፤ በክልሉ የተገኘው የተፈጥሮ ጋዝ በቅርብ ዓመታት ወደ ምርት ለማስገባት ሰፋፊ ሥራዎች እየተሠሩ ነው፡፡ ሌሎች በፍለጋ ምዕራፍ ላይ ያሉትም በአጭር ጊዜ ውጤታማ የሚሆኑበት አቅጣጫ ተቀምጧል ብለዋል፡፡
================
የአዲስ ስታንዳርድ አማርኛ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን ይቀላቀሉ፡
ቴሌግራም: https://rb.gy/rekjr
ፌስቡክ: https://rb.gy/xwxb3
ትዊተር (X)፡ https://rb.gy/34uh4
ዩቲዩብ፡ https://rb.gy/bjcbg
ድረገጽ: https://rb.gy/5td6n
ቲክቶክ፡ https://rb.gy/3bghek

ዜና: #የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል አጠቃላይ ሀብቱ 672 ቢሊየን ብር ቢደርስም 367 ቢሊየን ብሩ በዕዳ የተመዘገበ ነው ተባለ
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል እና የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት በቅርቡ በሚያካሂደው የኃይል ሽያጭ ታሪፍ ማሻሻያ ዙሪያ ከተቋማት እና ከተለያዩ ማህበረሰብ ክፍሎች ጋር እየመከረ መሆኑን አስታውቋል።
የታቀደው የታሪፍ ክለሳ የኢነርጂ ዘርፉን ለማሳደግ እና አገልግሎቱን ለማሻሻል ከፍተኛ ሚና ይኖረዋል ተብሏል።
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል አጠቃላይ ሀብቱ 672 ቢሊየን ብር ቢደርስም 367 ቢሊየን ብሩ በዕዳ የተመዘገበ ነው ሲሉ የተቋሙ የኮርፖሬት ፕላኒንግ ሥራ አስፈፃሚ አቶ አንዱዓለም ሲዓ ከሚዲያ ሃላፊዎች ጋር ባካሄዱት ምክክር ገልጸዋል።
በአሁኑ ወቅት ኢትዮጵያ ከውሃ 4 ሺህ 820 ሜጋ ዋት፣ ከንፋስ 404 ሜጋ ዋት እና ከእንፋሎት 32 ሜጋ ዋት ኃይል እያመነጨች ትገኛለች ብለዋል።
https://wp.me/pfjhHd-1cq

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል አጠቃላይ ሀብቱ 672 ቢሊየን ብር ቢደርስም 367 ቢሊየን ብሩ በዕዳ የተመዘገበ ነው ተባለ - Addis standard
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 7/2016 ዓ.ም፡-የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል እና የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት በቅርቡ በሚያካሂደው የኃይል ሽያጭ ታሪፍ ማሻሻያ ዙሪያ ከተቋማት እና ከተለያዩ ማህበረሰብ ክፍሎች ጋር እየመከረ መሆኑን አስታውቋል። ትላንት ሰኔ 6 ቀን 2016 ዓ.ም ከተለያዩ የሚዲያ ባለሙያዎችና ባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት ማካሄዱን እና በዛሬው ዕለትም የከፍተኛ ኃይል ተጠቃሚ ደንበኞቹ ጋር በመምከር…
ዜና: በአሁኑ ወቀት “80 ወይም 90 በመቶ የሚሆነው #የአማራ አካባቢ በፋኖ ኃይሎች ቁጥጥር ስር ይገኛል” - እስክንድር ነጋ
የፋኖ ታጣቂ ቡድን መሪ ከሆኑት አንዱ እንደሆኑ የሚነገርላቸው የቀድሞው ጋዜጠኛ እና ፖለቲከኛ እስክንድር ነጋ ከመንግሥት ጋር ድርድር ለማድረግ ገና ከውሳኔ አልተደረሰም ሲሉ አስታወቁ።
እስክንድር ነጋ ከቢቢሲ ፎከስ ኦን አፍሪካ ጋር ባደረጉት ቃለ መጠይቅ፤ በአማራ ክልል ያለውን ግጭት በንግግር ለመፍታት ከመንግሥት ጋር ሊደረግ ስለሚቻልበት ውይይትን በተመለከተ “ገና ከውሳኔ አልደረስንም” ብለዋል።
“ከመንግሥት ጋር እየተዋጉ ያሉ በርካታ የፋኖ ቡድኖች አሉ። እያንዳንዱ ቡድን እራሱን የቻለ ነው” ያሉት እስክንድር፤ በክልሉ እየተንቀሳቀሱ ያሉ የተለያዩ የፋኖ ቡድኖችን ለማዋሃድ ጥረት እየተደረገ ነው ብለዋል።
“በአሁኑ ወቅት አንድነት ለመፍጠር እየተነጋገርን ነው። ይህ ሂደት ከተጠናቀቀ በኋላ ከመንግሥት ጋር ሊደረግ ስለሚችል ድርድር ውሳኔ ላይ መድረስ ይቻላል።”
እስክንድር ነጋ “በመርህ ደረጃ ድርድር ተቀባይነት ያለው ነገር ነው” ካሉ በኋላ፣ በአፍሪካ ያለውን ተሞክሮ በማንሳት ከብዙ የሰው እልቂት እና የንብረት ውድመት በኋላ ተዋጊ ኃይሎች ወደ ድርድር ሲመለሱ ተመልክተናል ብለዋል።
በአሁኑ ወቀት “80 ወይም 90 በመቶ የሚሆነው የአማራ አካባቢ በፋኖ ኃይሎች ቁጥጥር ስር ይገኛል” ያሉት እስክንድር፤ የመንግሥት ኃይሎች ዋነኛ ጥረት ሆኖ የቆየው በክልሉ የሚገኙ ዋና ዋና ከተሞችን ተቆጣጥሮ ማስተዳደር ነው ይላሉ።
በአማራ ክልል ከፍተኛ የሰብዓዊ ቀውስ መኖሩን ያስታወሱት እስክንድር፤ የፋኖ ኃይሎች ተቆጣጥረው በሚገኙባቸው አካባቢዎች ዓለም አቀፍ የሰብዓዊ ድርጅቶች የሰብዓዊ እርዳታ ሥራ እንዲሰሩ ፍቃደኞች ነን ማለታቸውን ከቢቢሲ ያገኘነው መረጃ ያሳያል።

ዜና: በሀገሪቱ በ2023 ከተመዘገቡ የሰብአዊ መብት ጥሰቶች መካከል 70 በመቶ የሚሆኑት በመንግስት #የጸጥታ ሀይሎች የተፈጸሙ ናቸው - የመንግስታቱ ድርጅት
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰብአዊ ጉዳዮች ከፍተኛ ኮሚሽን #በኢትዮጵያ የሰብአዊ መብት ሁኔታን አስመልክቶ በቅርቡ ይፋ ባደረገው ሪፖርት በኢትዮጵያ በተለይም #በኦሮምያ እና #አማራ ክልሎች የሚፈጸሙ ሰብአዊ መብት ጥሰቶች አሳሳቢ ናቸው ብሏል።
በዘፈቀደ የዜጎችን መብት መግፈፍ፣ በፖለቲካ ምክንያት የሚደርስ የአካል ማጉደል፣ የወሲብ ጥቃት፣ የመሰብሰብ ነጻነትን መግፈፍ፣ የዘፈቀደ እስር፣ የመናገር ነጻነት መግፈፍ እገታ እና መሰወር የመሳሰሉ የሰብአዊ መብት ጥሰቶች በኢትዮጵያ በ2023 መመዝገባቸውን አስታውቋል።
በሀገሪቱ በተደጋጋሚ ከተጣሱ ሰብአዊ መብቶች መካከል ዋናዋናዎቹ የዘፈቀደ እስር እና የንጹሃን ግድያዎች መሆናቸውን ጠቁሟል።
የጥቃቱን 70 በመቶ ፈጻሚዎች የመንግስት የጸጥታ ሀይሎች ማለትም የሀገር መከላከያ ሰራዊት አባላት፣ የፌደራል እና ክልል ፖሊስ አባላት እና በመንግስት የሚደገፉ የሚሊሻ ታጣቂዎች ናቸው ብሏል።
https://addisstandard.com/Amharic/%e1%89%a0%e1%88%80%e1%8c%88%e1%88%aa%e1%89%b1-%e1%89%a02023-%e1%8a%a8%e1%89%b0%e1%88%98%e1%8b%98%e1%8c%88%e1%89%a1-%e1%8b%a8%e1%88%b0%e1%89%a5%e1%8a%a0%e1%8b%8a-%e1%88%98%e1%89%a5%e1%89%b5-%e1%8c%a5/

በሀገሪቱ በ2023 ከተመዘገቡ የሰብአዊ መብት ጥሰቶች መካከል 70 በመቶ የሚሆኑት በመንግስት የጸጥታ ሀይሎች የተፈጸሙ ናቸው - የመንግስታቱ ድርጅት - Addis standard
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 7/2016 ዓ.ም፡-የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰብአዊ ጉዳዮች ከፍተኛ ኮሚሽን ቢሮ በኢትዮጵያ የሰብአዊ መብት ሁኔታን አስመልክቶ በቅርቡ ይፋ ባደረገው ሪፖርት በኢትዮጵያ በተለይም በኦሮምያ እና አማራ ክልሎች የሚፈጸሙ ሰብአዊ መብት ጥሰቶች አሳሳቢ ናቸው ብሏል። በፕሪቶርያ የተደረሰውን የሰላም ስምምነት ተከትሎ በትግራይ የነበረው የሰብአዊ መብት ሁኔታ የተሻሻለ ቢሆንም ኢትዮጵያ በ2023…
ዜና: የሚንስትሮች ምክር ቤት የንብረት ታክስ ረቂቅ #አዋጅን በማጽደቅ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መምራቱ ተገለጸ
የሚኒስትሮች ምክር ቤት ትላንት ሰኔ 7 ቀን 2016 ዓ.ም ባካሄደው 35ኛ መደበኛ ስብሰባ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳልፏል።
ምክር ቤቱ ተወያይቶ ውሳኔ ካዳለፈባቸው ጉዳዮች መካከል የንብረት ታክስ ረቂቅ አዋጅ ይገኝታል። ከጠ/ሚኒስትር ጽ/ቤት የተገኘው መረጃ እንዳስታወቀው አዋጁ ሁለት ግቦችን ለማሳካት በሚል እንዲጸድቅ ተፈልጓል፤ በከተሞች ነዋሪ በሆነው ሕዝብ መካከል ፍትሃዊ የሃብት ክፍፍል ለማስፈን፣ የመንግስትን ገቢ በማሳደግ የመሰረተ ልማት ማሻሻያዎችን በቀጣይነት ለመተግበር።
አዋጁ በመላ ሀገሪቱ በሚገኙ ከተሞች ውስጥ ተፈጻሚነት እንደሚኖረው ያመላከተው ምክር ቤቱ ክልሎችም ይህንን አዋጅ መሰረት በማድረግ ከተጨባጭ ሁኔታቸው ጋር በተጣጣመ አኳኋን የየራሳቸውን የንብረት ታክስ ህግ እንዲያወጡ ያስችላል ብሏል።
በዚሁ መሰረት ይህንን ለማስፈጸም የሚረዳ ረቂቅ አዋጅ ተዘጋጅቶ መቅረቡን ጠቁሟል።
ምክር ቤቱም በቀረበው ረቂቅ አዋጅ ላይ ከተወያየ በኋላ ወደ ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንዲተላለፍ በሙሉ ድምጽ ወስኗል፡፡
================
የአዲስ ስታንዳርድ አማርኛ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን ይቀላቀሉ፡
ቴሌግራም: https://rb.gy/rekjr
ፌስቡክ: https://rb.gy/xwxb3
ትዊተር (X)፡ https://rb.gy/34uh4
ዩቲዩብ፡ https://rb.gy/bjcbg
ድረገጽ: https://rb.gy/5td6n
ቲክቶክ፡https://rb.gy/3bghek
የሚኒስትሮች ምክር ቤት ትላንት ሰኔ 7 ቀን 2016 ዓ.ም ባካሄደው 35ኛ መደበኛ ስብሰባ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳልፏል።
ምክር ቤቱ ተወያይቶ ውሳኔ ካዳለፈባቸው ጉዳዮች መካከል የንብረት ታክስ ረቂቅ አዋጅ ይገኝታል። ከጠ/ሚኒስትር ጽ/ቤት የተገኘው መረጃ እንዳስታወቀው አዋጁ ሁለት ግቦችን ለማሳካት በሚል እንዲጸድቅ ተፈልጓል፤ በከተሞች ነዋሪ በሆነው ሕዝብ መካከል ፍትሃዊ የሃብት ክፍፍል ለማስፈን፣ የመንግስትን ገቢ በማሳደግ የመሰረተ ልማት ማሻሻያዎችን በቀጣይነት ለመተግበር።
አዋጁ በመላ ሀገሪቱ በሚገኙ ከተሞች ውስጥ ተፈጻሚነት እንደሚኖረው ያመላከተው ምክር ቤቱ ክልሎችም ይህንን አዋጅ መሰረት በማድረግ ከተጨባጭ ሁኔታቸው ጋር በተጣጣመ አኳኋን የየራሳቸውን የንብረት ታክስ ህግ እንዲያወጡ ያስችላል ብሏል።
በዚሁ መሰረት ይህንን ለማስፈጸም የሚረዳ ረቂቅ አዋጅ ተዘጋጅቶ መቅረቡን ጠቁሟል።
ምክር ቤቱም በቀረበው ረቂቅ አዋጅ ላይ ከተወያየ በኋላ ወደ ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንዲተላለፍ በሙሉ ድምጽ ወስኗል፡፡
================
የአዲስ ስታንዳርድ አማርኛ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን ይቀላቀሉ፡
ቴሌግራም: https://rb.gy/rekjr
ፌስቡክ: https://rb.gy/xwxb3
ትዊተር (X)፡ https://rb.gy/34uh4
ዩቲዩብ፡ https://rb.gy/bjcbg
ድረገጽ: https://rb.gy/5td6n
ቲክቶክ፡https://rb.gy/3bghek
ዜና: “#በአፋር እና #ሶማሊ ክልሎች አዋሳኝ አከባቢ የተቀሰቀሰው ግጭት እጅግ አሳስቦኛል” - ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን
በአፋር እና ሶማሊ ክልሎች ወሰን አከባቢ የተቀሰቀሰው ግጭት ሊቆም የገባል፣ ዘላቂ ሰላም የሚያሰፍን መፍትሔ ሊበጅለት ይገባል ሲል ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ባወጣው መግለጫ አሳሰበ።
በአፋር እና ሶማሌ ክልል አዋሳኝ አከባቢዎች በአዲስ መልክ ግጭት መቀስቀሱን የጠቆመው ኮሚሽኑ በንጹሃን ላይ ጉዳት መድረሱን፣ በአዋሳኝ አከባቢዎቹ የሚገኙ ነዋሪዎችም መፈናቀላቸውን አመላክቷል።
ኮሚሽኑ ሁኔታውን እየተከታተለው መሆኑን አስታውቆ ከሁለት ወራት በፊት በሁለቱ ክልሎች መካከል ተደርሶ የነበረው የሰላም ስምምነት መጣሱ አሳሳቢ ነው ሲል ገልጿል።
https://wp.me/pfjhHd-1cG

“በአፋር እና ሶማሊ ክልሎች አዋሳኝ አከባቢ የተቀሰቀሰው ግጭት እጅግ አሳስቦኛል” - ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን - Addis standard
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 8/2016 ዓ.ም፡- በአፋር እና ሶማሊ ክልሎች ወሰን አከባቢ የተቀሰቀሰው ግጭት ሊቆም የገባል፣ ዘላቂ ሰላም የሚያሰፍን መፍትሔ ሊበጅለት ይገባል ሲል ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ባወጣው መግለጫ አሳሰበ። በአፋር እና ሶማሌ ክልል አዋሳኝ አከባቢዎች በአዲስ መልክ ግጭት መቀስቀሱን የጠቆመው ኮሚሽኑ በንጹሃን ላይ ጉዳት መድረሱን፣ በአዋሳኝ አከባቢዎቹ የሚገኙ ነዋሪዎችም መፈናቀላቸውን አመላክቷል።…
ዜና: ኢድ አል አደሃ አረፋ በዓልን የተቸገሩ ወገኖችን በመደገፍ ማሳለፍ ይገባል- #የእስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ም/ቤት
ሕዝበ ሙስሊሙ የኢድ አል አድሃ አረፋ በዓልን ሲያከብር በሃይማኖቱ አስተምህሮ መሰረት የተቸገሩ ወገኖችን በማሰብና ያለውን በማካፈል መሆን እንዳለበት #የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት አስታወቀ፡፡
ምክር ቤቱ መላውን የእስልምና ዕምነት ተከታዮች እንኳን ለ1 ሺህ 445ኛው ዓመተ ሂጅራ የኢድ አል አድሃ አረፋ በዓል አደረሳችሁ ሲል መልዕክት አስተላልፏል።
መልካም ምኞቱ ባስተላለፈበት መግለጫው ሙስሊሙ ህብረተሰብ በዓሉን ሲያከብር በሃይማኖቱ አስተምህሮ መሰረት የተቸገሩ ወገኖቹን በማሰብና ያለውን በማካፈል እንዲሆን አስገንዝቧል።
የምክር ቤቱ ፕሬዝዳንት ሃጂ ኢብራሂም ቱፋ በሰጡት መግለጫ፤ ህዝበ ሙስሊሙ በዓሉን ሲያከብር በተለያዩ ምክንያቶች ከቤት ንብረታቸው ተፈናቅለው በጊዜያዊ መጠለያ የሚገኙ ወገኖችን፣ አቅመ ደካሞችንና አሳዳጊ የሌላቸውን ህጻናት በመደገፍ እንዲያከብር ጥሪ አቅርበዋል፡፡
እንደዚሁም ህዝበ ሙስሊሙ ከሌሎች እምነት ተከታዮች ጋር አንድነቱንና ወንድማማችነቱን በሚያጠናክር መልክ በዓሉን ማሳለፍ እንዳለበት መናገራቸውን ከኤፍቢሲ ያገኘነው መረጃ ያሳያል።
የኢድ አል አረፋ በዓል ከፆምና ፀሎት ሀይማኖታዊ ሥርዓት በኋላ የሚከናወንና በእስልምና ሃይማኖት ትልቅ ሥፍራ የሚሰጠው መሆኑን አስታውቀዋል፡፡
በዓሉ አላህ የነብዩ ኢብራሂምን ፍቅርና እምነት ፍጹምነትን ለማስተማር ልጃቸውን ለመስዋዕትነት እንዲያቀርቡ ያዘዘበት፤ እርሳቸውም ለፈጣሪ የነበራቸው እምነትና ፍቅር ጥግ በሚያሳይ ፍጹምነት የሚወዱት ልጃቸውን እስማኤልን ወደ መሰዊያው ያቀረቡበት መታሰቢያ በዓል ነው።

ሰሜን ሽዋ ዞን ሚዳ ወረሞ ወረዳ የ #ኢትዮጽያ ንግድ ባንክ ቅርንጫፍ በታጣቂ ሀይሎች መዘረፉ ተገለፀ
በ #አማራ ክልል ሰሜን ሽዋ ዞን ሚዳ ወረሞ ወረዳ የኢትዮጽያ ንግድ ባንክ ሰኔ 06/2016 ዓ.ም በታጠቁ ሀይሎች መዘረፉ ተገለፀ።
በባንኩ ሬማ ቅርንጫፍ ላይ የተፈጸመው ዝርፊያ የገንዘብ መጠን ከ 2 ሚሊዮን ብር በላይ መሆኑን የወረዳው ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሠይድ ኢብራሂም ገልፀዋል።
ዝረፊያው "ህገ- ወጥ ፅንፈኛ" ሲሉ በጠራቸው በአካባቢዉ በሚንቀሳቀሱ የታጠቁ ሀይሎች" የተከወነ መሆኑን አስተዳዳሪው ተናግረዋል።
አቶ ሠይድ አክለውም "የአካባቢዉን ሰላም፣ ዕድገትና መለወጥ የማይፈልጉ ፅንፈኛ ሀይሎች" ያሏቸው ታጣቂዎቹ፤ "ከዚህ በፊት ለአጎራባች መርሃቤቴ ወረዳ የተላከዉን ሰዉ ሰራሽ የአፈር ማዳበሪያ አስገድደዉ ወስደዋል" ብለዋል።
በቀጣይም ተመሳሳይ ድርጊት እንዳይፈፀም ሰላም ወዳዱ የወረዳችን ህዝብ ድርጊቱን በጥብቅ እንዲያወግዝ መጠየቃቸውን ከወረዳው ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ አመላክቷል።