የ #ሆረ_ፊንፊኔ_ኢሬቻ በዓል በሰላም ተጠናቅቋል- የ #ኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ
በሚሊዮን የሚቆጠር ህዝብና አባገዳዎች፣ ሀደ ሲንቄዎች፣ ከተለያዩ የሀገራችን አካባቢዎች እና ከጎረቤት ሀገራት የመጡ እንግዶች እንዲሁም የውጭ ሀገራት ቱሪስቶች የታደሙበት የሆራ ፊንፊኔ የኢሬቻ በዓል ያለምንም የፀጥታ ችግር በሰላም መጠናቀቁን የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ አስታወቋል።
ፎቶ: አዲስ ስታንዳርድ

ዜና: #በአማራ ክልል “ባለፉት ሁለት ሳምንታት ከፍርድ ቤት ትዕዛዝ ውጭ የዘፈቀደ እስር ተፈጽሟል” ሲል ኢሰመኮ ኮነነ
የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (#ኢሰመኮ) በአማራ ክልል ከመስከረም ወር አጋማሽ 2017 ዓ.ም. ጀምሮ በርካታ ሰዎች ለሕግ አግባብ ውጭ ያለፍርድ ቤት ትዕዛዛ ለእስር ተዳርገዋል ሲል አስታወቀ፤ በማናቸውም ወቅት ቢሆን የሚፈጸም እስር ተገቢውን የሕግ እና የሰብአዊ መብቶች ድንጋጌዎች ሊከተል ይገባል ሲልም አሳስቧል።
የሰብአዊ መብቶች ድንጋጌዎችን እና መርሖችን ያልተከተሉ እስሮች በአፋጣኝ ሊቆሙ ይገባል ሲል ጠይቋል።
ኢሰመኮ ትላንት መስከረም 26 ቀን 2017 ዓ.ም ባወጣው መግለጫ በአማራ ክልል ጎንደር እና ባሕር ዳር ከተሞችን ጨምሮ በተለያዩ የክልሉ አካባቢዎች የተፈጸሙት እስሮች “በሕግ አግባብ በፍርድ ቤት ትእዛዝ ያልተፈጸሙ፣ ተጠርጣሪዎቹ ፍርድ ቤት ያልቀረቡ መሆናቸው አመላክቷል።
የመንግሥት ሠራተኞች፣ የፖለቲካ ፓርቲ አባላት፣ የሚዲያ እና የሲቪክ ማኅበረሰብ አባላትን ጨምሮ በርካታ ሰዎች ወደ ጊዜያዊ ማቆያዎች እየተወሰዱ መሆኑን የጠቆመው ኢሰመኮ ከመካከላቸው ቋሚ የሕክምና ክትትል የሚያስፈልጋቸው ሰዎች መኖራቸውን ገልጿል።
https://wp.me/pfjhHd-1sW

Addis standard
በአማራ ክልል “ባለፉት ሁለት ሳምንታት ከፍርድ ቤት ትዕዛዝ ውጭ የዘፈቀደ እስር ተፈጽሟል” ሲል ኢሰመኮ ኮነነ - Addis standard
አዲስ አበባ፣ መስከረም 27/2017 ዓ.ም፡- የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) በአማራ ክልል ከመስከረም ወር አጋማሽ 2017 ዓ.ም. ጀምሮ በርካታ ሰዎች ለሕግ አግባብ ውጭ ያለፍርድ ቤት ትዕዛዛ ለእስር ተዳርገዋል ሲል አስታወቀ፤ በማናቸውም ወቅት ቢሆን የሚፈጸም እስር ተገቢውን የሕግ እና የሰብአዊ መብቶች ድንጋጌዎች ሊከተል ይገባል ሲልም አሳስቧል። የሰብአዊ መብቶች ድንጋጌዎችን እና መርሖችን…
ዜና: #በአማራ እና #አፋር ክልል እንዲሁም በአዲስ አበባ ለሚገኙ ህጻናት ከዛሬ መስከረም 27 ጀምሮ ለአራት ቀናት የፖሊዮ ክትባት እንደሚሰጥ ተገለጸ
በአማራና በአፋር ክልል እንዲሁም #በአዲስ አበባ ከዛሬ መስከረም 27 ቀን 2017 ጀምሮ የፖሊዮ ክትባት እንደሚሰጥ ተገለጸ፡፡
ወላጆች ወይም አሳዳጊዎች ከ5 አመት በታች የሆኑ ህፃናትን ከዚህ በፊት ቢከተቡም ባይከተቡም በማስከተብ የልጆቻቸውን ጤንነት እንዲጠብቁ ጥሪ ተላልፏል፡፡
የአማራ ክልል ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር በላይ በዛብህ እንዳስታወቁት ፖሊዮ (የልጅነት ልምሻ) በሽታ በተበከለ ምግብና ውሃ አማካኝነት የሚመጣ ተላላፊ በሽታ እንደሆነ ጠቅሰው፤ በሽታው ዘላቂ ለሆነ የአካል ጉዳትና አልፎም ለሞት የሚዳርግ እንደሆነ ገልፀዋል።
በአማራ ክልል ክትባቱን ከ4 ሚሊየን ለሚበልጡ ህፃናት ለመስጠት መታቀዱን እና ከዛሬ መስከረም 27 ጀምሮ ለአራት ተከታታይ ቀናት እንደሚሰጥ የአማራ ክልል ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር በላይ በዛብህ ገልጸዋል።
በተመሳሳይ በአፋር ክልል የህብረተሰብ ጤናና ምርምር ኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር አሕመዱ አህመድ በበኩላቸው በክልሉ 6 ዞኖችና 50 ወረዳዎች እንዲሁም በከተማ አስተዳደሮች ለሚገኙ ከ364 ሺህ በላይ ህፃናት ክትባቱ ይሰጣል ብለዋል።
በክልል ደረጃ 364 ሺህ 629 ህፃናት የሚከተቡ መሆኑን አስታውቀው ክትባቱም ከዛሬ መስከረም 27 ጀምሮ ለአራት ቀናት የሚሰጥ መሆኑን ገልጸዋል
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጤና ቢሮ በበኩሉ እድሜያቸው ከ5 ዓመት በታች ለሆኑ ህጻናት ከዛሬ መስከረም 27 ጀምሮ ለ3 ተከታታይ ቀናት ቤት ለቤት፣ በትምህርት ቤት ፣ በማቆያ፣ በማሳደጊያ ቦታዎች እና በሌሎች ህጻናት በሚገኙበት ሁሉ በአፍ በጠብታ ክትባቱ እንደሚሰጥ መገለጹን ከዋልታ ያገኘነው መረጃ ያሳያል

ዜና: ትላንት ምሽት ላይ #በአዋሽ ፈንታሌ እና አካባቢው የተከሰተው የመሬት መንቀጥቀጥ የተወሰኑ ቤቶች መፍረሳቸውና መሬት መሰንጠቁ ተጠቆመ
ንዝረቱ #አዲስ አበባ ድረስ የተሰማው እና በአዋሽ ፈንታሌ እና አካባቢው ትላንት መስከረም 26 ቀን 2017 ዓ.ም የተከሰተው የመሬት መንቀጥቀጥ የተወሰኑ ቤቶችን እንዳፈረሰ፣ መሬት እንደሰነጠቀ የሰመራ ዩኒቨርስቲ አስታወቀ።
ዩኒቨርስቲው በማህበራዊ ሚዲያ ፌስቡክ ገጹ ባጋራው መረጃ በአዋሽ ፈንታሌ እና አካባቢው የተከሰተው የመሬት መንቀጥቀጥ ከሁለት ሳምንታት በላይ እንደሆነው አመላክቷል።
ባሳለፍነው ሳምንት የሰመራ ዩኒቨርሲቲ የጂኦሎጂ ጥናት ቡድን በአዋሽ ፋንታሌ ወረዳ የመስክ ምልከታ ማድረጉን የጠቆመው የዩኒቨርስቲው መረጃ የመሬት መንቀጥቀጡ የተከሰተበትን በተለይም ሳቡሬ ቀበሌ ተገኝቶ መረጃ የመሰብሰብ እና ለማህበረሰቡ ጥንቃቄ የግንዛቤ ማስጨበጥ ስራ መስራቱንም አስታውቋል።
የዩኒቨርሲቲው ጂኦሎጂስቶች የአካባቢውን ነዋሪዎች ባነጋገሩበት ወቅት ከፈንታሌ ኮረብታማ ቦታ እና ከከሰም ግድብ ርቀው እንዲቆዩ ማሳሰባቸውን ገልጿል።
ትናንት መስከረም 26 ቀን ምሽት 2 ሰዓት ከ10 ደቂቃ ገደማ በሬክተር ስኬል 4 ነጥብ 9 የተመዘገበበት እስከ አዲስ አበባ ድረስ ንዝረቱ የተሰማ መሬት መንቀጥቀጥ መከሰቱን በርካታ አለም አቀፍ ተቋማት አስታውቀዋል።
የአሜሪካው ጂዮሎጂካል ሰርቬይ: የጀርመን እና ሌሎች አለም አቀፍ ጂዮሎጂካል ሰርቬይ የምርምር ተቋማት በአዋሽ ዙሪያ በተከታታይ የተከሰተውን የመሬት መንቀጥቀጥ የትናንቱን ጨምሮ በድረ-ገጻቸው ላይ አስፍረውታል።
የሰሞኑ የመሬት መንቀጥቀጥ በአዋሽ ፈንታሌ እና አካባቢው ከፍተኛ ስጋትን መፍጠሩንም ዩኒቨርስቲው አመላክቷል።

ዜና፡ በ #አማራ ክልል በርካታ አከባቢዎች በከባድ መሳርያ የታገዙ ውጊያዎች መቀጠላቸውን ነዋሪዎች ገለጹ
በአማራ ክልል፤ በ #ምዕራብ_ጎጃምና በ #አዊ በሔረሰብ ዞን ስር በሚገኙ በርካታ አከባቢዎች በከባድ መሳርያ የታገዙ ውጊያዎች እየተካሄዱ መሆኑን ነዋሪዎች ለአዲስ ስታንዳርድ ገለጹ።
በክልሉ በሚገኙት በ #ፍኖተሠላም፣ #ቲሊሊ፣ #ጅጋ እና #ቡሬ ከተሞችም በመንግስት ጸጥታ ኃይሎች እና በ #ፋኖ ታጣቂዎች መካክለ በከባድ መሳሪያ የታገዘ ግጭት እየተካሄደ መሆኑን ነዋሪዎቹ ተናግረዋል።
በምዕራብ ጎጃም ዞን ዋና መቀመጫ የሆነችው የፍኖተሠላም ከተማ ነዋሪ እንደገለጹት፤ ቅዳሜ ነሐሴ 25/2016 ዓ.ም. የፋኖ ኃይሎች ከተማዋን ለቀው መውጣታቸውን ተከትሎ የተኩሱ እሩምታ ረገብ ብሎ እንደነበረ ገልጸዋል።
ይሁንና ከትናንት እሁድ ጀምሮ የፋኖ ታጣቂዎች ተመልሰው ወደ ከተማዋ ለመግባት በሶስት አቅጣጫ ውጊያ መክፈታቸውን ተከትሎ በአከባቢው ያለው ውጥረት ማገርሸቱን ነዋሪው አክለው ገልጸዋል።
ሙሉ ዘገባውን ለማንበብ፦ https://wp.me/pfjhHd-1t0

በምዕራብ ጎጃምና አዊ ዞን በርካታ አከባቢዎች በከባድ መሳርያ የታገዙ ውጊያዎች እየተካሄዱ መሆኑን ነዋሪዎች ገለጹ - Addis standard
አዲስ አበባ፣ መስከረም 27/ 2017 ዓ/ም፡- በአማራ ክልል፤ በምዕራብ ጎጃምና በአዊ በሔረሰብ ዞን ስር በሚገኙ በርካታ አከባቢዎች በከባድ መሳርያ የታገዙ ውጊያዎች እየተካሄዱ መሆኑን ነዋሪዎች ለአዲስ ስታንዳርድ ገለጹ። ለደህንነታቸው በመስጋት ስማቸውን እንዳንጠቅስ የጠየቁ በምዕራብ ጎጃም ዞን ዋና መቀመጫ የሆነችው የፍኖተሠላም ከተማ ነዋሪ እንደገለጹት፤ ካለፈው ሳምንት ሀሙስ ጀምሮ በከባድ መሳርያ የታገዘ…
ዜና: “አቶ ጌታቸው ረዳን ከጊዜያዊ አስተዳደሩ ፕሬዝዳንትነት አንስቻለሁ” ሲል በዶ/ር ደብረጺዮን የሚመራው #ህወሓት አስታወቀ
በዶ/ር ደብረጺዮን ገ/ሚካኤል የሚመራው የህወሓት ቡድን ዛሬ መስከረም 27 ቀን 2017 ዓ.ም ባወጣው መግለጫ #የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት ሁነው በማገልገል ላይ ያሉትን አቶ ጌታቸው ረዳን ጨምሮ አምስት ከጊዜያዊ አስተዳደሩ ካቢኔ አባላትን ከስልጣን አንስቻለሁ ሲል አስታወቀ።
በአቶ ጌታቸው ረዳ ምትክ “የጊዜያዊ አስተዳደሩ ፕሬዝዳንት የሚሆኑትን አመራር ከፌደራል መንግስቱ ጋር በመነጋገር አሳውቃለሁ” ሲል ገልጿል።
ፕሬዝዳንት ጌታቸው ረዳን ጨምሮ በጊዜያዊ አስተዳደሩ በካቢኔ አባልነት እና የተለያዩ ቢሮ ሃላፊ ሁነው በማገልገል ላይ የሚገኙት ባለስልጣናት ከዛሬ መስከረም 27 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ “ምንም አይነት አመራር መስጠት፣ ውሳኔ ማሳለፍ አይችሉም” ሲል ገልጿል።
ይህንንም “መንግስታዊም ይሁን መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማት፣ በየደረጃው ያሉ የአስተዳደር አካላት፣ የትግራይ የፀጥታ አካላት፣ የፌደራል መንግስቱ እና ክልሎች፣ አለም አቀፉ ማህበረሰብ እና ሌሎች የሚመለከቱ አካላት እንዲያውቁልን እናሳስባለን” ብሏል።
በዶ/ር ደብረጺዮን ገ/ሚካኤል የሚመራው የህወሓት ቡድን ከስልጣናቸው አንስቻቸዋለሁ ባላቸው የጊዜያዊ አስተዳደሩ ካቢኔ አባላት ምትክ አዲስ ተሿሚወችንም አስታውቋል።
https://wp.me/pfjhHd-1ta

ዜና: “አቶ ጌታቸው ረዳን ከጊዜያዊ አስተዳደሩ ፕሬዝዳንትነት አንስቻለሁ” ሲል በዶ/ር ደብረጺዮን የሚመራው ህወሓት አስታወቀ - Addis standard
አዲስ አበባ፣ መስከረም 27/2017 ዓ.ም፡- በዶ/ር ደብረጺዮን ገ/ሚካኤል የሚመራው የህወሓት ቡድን ዛሬ መስከረም 27 ቀን 2017 ዓ.ም ባወጣው መግለጫ የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት ሁነው በማገልገል ላይ ያሉትን አቶ ጌታቸው ረዳን ጨምሮ አምስት ከጊዜያዊ አስተዳደሩ ካቢኔ አባላትን ከስልጣን አንስቻለሁ ሲል አስታወቀ። በአቶ ጌታቸው ረዳ ምትክ “የጊዜያዊ አስተዳደሩ ፕሬዝዳንት የሚሆኑትን…
ዜና: መንግስት በተያዘው አመት "የሃይል አማራጭን በመጠቀም ፖለቲካዊ ፍላጎቶችን ለሟሟላት የሚደረጉ ጥረቶችን አይታገስም” - ፕሬዝዳንት #ታዬ አጽቀሥላሴ
"የሃይል አማራጭን በመጠቀም ፖለቲካዊ ፍላጎቶችን ለሟሟላት የሚደረጉ ማናቸውንም እኩይ ተግባራት መንግስት በልበ ሰፊነት የሚያልፍበት ዕድል እጅግ የጠበበ ነው" ሲሉ አዲስ የተመረጡት #የኢትዮጵያ ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀሥላሴ አስታወቁ።
6ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤትና የፌዴሬሽን ምክር ቤት 4ኛ ዓመት የሥራ ዘመን የመክፈቻ ሥነ-ሥርዓት በዛሬው ዕለት መስከረም 27 ቀን 2017 ዓ.ም ተካሂዷል።
የቀድሞዋ ፕሬዝዳንት ሣኅለወርቅ ዘውዴ የመጨረሻ የመክፈቻ ንግግር የሚጠበቅበት የሁለቱ ምክር ቤቶች ሥብሰባ ቢጠናቀቅም የቀድሞዋ ፕሬዝዳንት ምንም አይነት ንግግር ሳያደርጉ የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ሆነው ሲያገለግሉ ለነበሩት አምባሳደር ታዬ አጽቀሥላሴ ሃላፊነታቸውን አስረክበዋል።
በዚሁ ወቅት የኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት ሆነው የተሾሙት የቀድሞ የውጭ ጉዳይ ሚንስትር ታዬ አጽቀሥላሴ የመንግስትን ቀጣይ አመታዊ አቅጣጫ በሚያመላክተው ንግግራቸው “ከእንግዲህ በኢትዮጵያ ምድር ሃይልን በብቸኝነት መጠቀም መብት የመንግስት ተቋማት ብቻ መሆኑን ማረጋገጥ ይገባል” ብለዋል።
https://wp.me/pfjhHd-1te

መንግስት በተያዘው አመት "የሃይል አማራጭን በመጠቀም ፖለቲካዊ ፍላጎቶችን ለሟሟላት የሚደረጉ ጥረቶችን አይታገስም” - ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀሥላሴ ገለጹ - Addis standard
አዲስ አበባ፣ መስከረም 27/2017 ዓ.ም፡- “የሃይል አማራጭን በመጠቀም ፖለቲካዊ ፍላጎቶችን ለሟሟላት የሚደረጉ ማናቸውንም እኩይ ተግባራት መንግስት በልበ ሰፊነት የሚያልፍበት ዕድል እጅግ የጠበበ ነው” ሲሉ አዲስ የተመረጡት የኢትዮጵያ ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀሥላሴ አስታወቁ። 6ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤትና የፌዴሬሽን ምክር ቤት 4ኛ ዓመት የሥራ ዘመን የመክፈቻ ሥነ-ሥርዓት በዛሬው ዕለት መስከረም…
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
ዜና: መንግስት #በሊባኖስ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የነበሩ 51 ኢትዮጵያውያን ወደ አገራቸው መመለሱን አስታወቀ
በሊባኖስ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የነበሩ 51 #ኢትዮጵያውያን ወደ አገራቸው ተመልሰዋል ሲል የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ።
በሊባኖስ የሚገኙ ኢትዮጵያውያንን ወደ ሀገራቸው ለመመለስ ቀዳሚ ትኩረቱን አድርጎ መንግስት እየሰራ ነው ሲሉ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ነብያት ጌታቸው መናገራቸውን የሚኒስቴር መስራቤቱ መረጃ ያሳያል።
በቀጣይም ሌሎች ለችግር ተጋላጭ የሆኑ ዜጎቻችንን ወደ አገራቸው ለመመለስ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመተባበር እየተሠራ መሆኑን ተናግረዋል ብሏል።
51ዱ ኢትዮጵያውያን በቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱም ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር፣ ሴቶች እና ማኀበራዊ ጉዳዮች ሚኒስቴር እና ከኢትዮጵያ አደጋ ሥጋት አመራር ኮሚሽን ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች አቀባበል አድርገውላቸዋል።
በተያያዘ ዜና ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በሊባኖስ የሚገኙ ዜጎች አንጻራዊ ደኀንነት ወደ አለበት የሊባኖስ አካባቢ እንዲንቀሳቀሱ ማድረግ እና ቅድሚያ የሚሰጣቸውን ህጻናት እና ሴቶችን ወደ አገራቸው ለመመለስም ሁሉንም አማራጮች ለመጠቀም ከተለያዩ አካላት ጋር ጥረት እየተደረገ መሆኑን ጠቁሟል።
================
የአዲስ ስታንዳርድ አማርኛ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን ይቀላቀሉ፡
ቴሌግራም: https://rb.gy/rekjr
ፌስቡክ: https://rb.gy/xwxb3
ትዊተር (X)፡ https://rb.gy/34uh4
ዩቲዩብ፡ https://rb.gy/bjcbg
ድረገጽ: https://rb.gy/5td6n
ቲክቶክ፡ https://rb.gy/jgdsjm

ዜና: ዶ/ር ደብረጺዮን ገ/ሚካኤል በሚመሩት “#የህወሓት ቡድን አመራር ላይ ህጋዊ እርምጃ መውሰድ እጀምራለሁ” - ጊዜያዊ አስተዳደሩ
#የትግራይ ግዜያዊ አስተዳደር ዶ/ር ደብረጺዮን ገ/ሚካኤል በሚመሩት “የህወሓት ቡድን አመራር ላይ ህጋዊ እርምጃ መውሰድ እጀምራለሁ” ሲል አስጠነቀቀ፣ የጸጥታ ሀይሉ በበኩሉ በከልሉ ምንም አይነት ረብሻ አልታገስም ሲል አስታውቋል።
የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ትላንት መስከረም 27 ቀን 2017 ዓ.ም አመሻሽ ባወጣው መግለጫ በክልሉ ስርአት አልበኝነት እንዲፈጠር እየሰራ ነው ባለው የእነ ደብረጺዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) “የህወሓት ቡድን ላይ አስፈላጊውን ህጋዊ እርምጃ እወስዳለሁ” ሲል አስጠነቀቀ።
በዶ/ር ደብረጺዮን ገ/ሚካኤል የሚመራው የህወሓት ቡድን መስከረም 27 ቀን 2017 ዓ.ም ባወጣው መግለጫ የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት ሁነው በማገልገል ላይ ያሉትን አቶ ጌታቸው ረዳን ጨምሮ አምስት ከጊዜያዊ አስተዳደሩ ካቢኔ አባላትን ከስልጣን አንስቻለሁ ሲል ማስታወቁን መዘገባችን ይታወሳል።
ይህንንም ተከትሎ ግዜያዊ አስተዳደሩ በወጣው መግለጫ ህወሓት ለሁለት መከፈሉን ተከትሎ ጉባኤ ያካሄደው የእነ ደብረጺዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) ቡድን “መፈንቅለ መንግስት አውጆብኛል” ሲል ኮንኗል።
ህጋዊ እርምጃ በምወስደበት ወቅት “ለሚደርስ ማናቸውም ጉዳት ይኼው ቡድን እና አመራሮቹ ብቻ ተጠያቂ እንደኾኑ ህዝቡ ይወቅልኝ” ሲልም አሳስቧል።
wp.me/pfjhHd-1th

ዶ/ር ደብረጺዮን ገ/ሚካኤል በሚመሩት “የህወሓት ቡድን አመራር ላይ ህጋዊ እርምጃ መውሰድ እጀምራለሁ” - ጊዜያዊ አስተዳደሩ - Addis standard
አዲስ አበባ፣ መስከረም 28/2017 ዓ.ም፡- የትግራይ ግዜያዊ አስተዳደር ዶ/ር ደብረጺዮን ገ/ሚካኤል በሚመሩት “የህወሓት ቡድን አመራር ላይ ህጋዊ እርምጃ መውሰድ እጀምራለሁ” ሲል አስጠነቀቀ፣ የጸጥታ ሀይሉ በበኩሉ በከልሉ ምንም አይነት ረብሻ አልታገስም ሲል አስታውቋል። የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ትላንት መስከረም 27 ቀን 2017 ዓ.ም አመሻሽ ባወጣው መግለጫ በክልሉ ስርአት አልበኝነት እንዲፈጠር…
ዜና: #በባህር ዳር ከተማ ሊካሄድ የነበረው 11ኛው የጣና ፎረም ለሶስተኛ ጊዜ ተራዘመ
የአፍሪካ ሰላም እና ጸጥታ ጉዳዮች ላይ የሚመክረው እና #በአማራ ክልል ባህር ዳር ከተማ የሚካሄደው ዓመታዊው የጣና ፎረም ጉባኤ ለሶስተኛ ጊዜ ተራዘመ።
11ኛው ጉባኤ መጀመሪያ ሊካሄድ ቀን ተቆርጦለት የነበረው ባለፈው ዓመት ከጥቅምት 2-4 ቀን 2016 ዓ.ም ነበር።
ሆኖም ጉባኤው “ባልተጠበቁ ሁኔታዎች ምክንያት” እንደተራዘመ የፎረሙ ጽህፈት ቤት የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የሰላም እና ደህንነት ጥናቶች ተቋም አስታውቆ ነበር።
ጉባኤው ሚያዚያ ወር 2016 ዓ.ም. እንደሚካሄድ ጽህፈት ቤቱ በጊዜው አስታውቆ የነበረ ቢሆንም በተባለው ጊዜ ሳይካሄድ ለሁለተኛ ጊዜ ተራዝሟል።
“አፍሪካ እየተሻሸለ በመጣው የዓለም ሥርዓት ውስጥ” የሚል መሪ ቃል የያዘው 11ኛው ጉባኤ ከጥቅምት 15-17 2017 ይካሄዳል ተብሎ ተጠብቆ ነበር
ነገር ግን ፎረሙ በፌስቡክ ገጹ ባወጣው መግለጫ “11ኛው የጣና ከፍተኛ የጸጥታ ጉዳዮች ፎረም [እ.ኢ.አ] ወደ 2025 መተላለፉን የጣና ፎረም ሴክሬታሪያት ለማሳወቅ ይወዳል” ብሏል
ፎረሙ አክሎም የጣና ፎረም ሴክሬታሪያት ከጣና ፎረም ቦርድ ጋር በመሆን ፎረሙ የሚካሄድበትን ቀጣይ ቀን ይፋ እንደሚያደርግ አሳውቋል
የጣና ፎረም የሚካሄድበት የአማራ ክልል ላለፈው አንድ ዓመት በፌደራል መንግስቱ እና በፋኖ ኃይሎች መካከል ውጊያ እየተካሄደበት ይገኛል
የአማራ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ትናንት መስከረም 27 ቀን 2017 ዓም አመሻሽ ባወጣው መግለጫ የጣና ፎረምን በምታስተናግደው ባህርዳር ከተማ “ተጠምዶ የነበረ ፈንጂ ጉዳት ሳያደርስ” መምከኑን አስታውቋል
የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን በዚሁ መግለጫው “ጽንፈኛው ኃይል ያጠመደው” ሲል በክልሉ የሚንቀሳቀሰው ታጣቂ ቡድን ተጠያቂ ማድረጉን ከቢቢሲ ያገኘነው መረጃ ያሳያል

በ19ኛው ክፍለ ዘመን ከ #መቅደላ ተዘርፎ የነበረ ጋሻ ወደ #ኢትዮጵያ ሊመለስ ነው ተባለ
እ.ኤ.አ በ1868 የተደረገውን የመቅደላ ጦርነት ተከትሎ በ #እንግሊዝ ወታደሮች ተዘርፎ የነበረው ጋሻ ወደ ኢትዮጵያ ሊመለስ መሆኑ ተገለጸ።
ጋሻው የቀዳማዊ አፄ ኃይለ ሥላሴ የልጅ ልጅ በሆኑት በልዑል ኤርሚያስ ሳህለ-ሥላሴ ከእንግሊዝ ጨረታ ቤት በቅርቡ ተገዝቷል።
ልዑል ኤርሚያስ የኢትዮጵያን ባህላዊ ቅርሶች ለመጠበቅ በሚሠራው ‘ሮያል ኢትዮጵያን ትረስት’ በተሰኘው ድርጅታቸው በኩል ጋሻውን ለማስመለው ስኬታማ ድርድር ማከናወናቸው ተገልጿል።
ጋሻው በየካቲት 2016 ዓ.ም. ለጨረታ ቀርቦ የነበረ ቢሆንም የኢትዮጵያ መንግስት ያሳደረውን ጫና ተከትሎ ከጨረታው እንዲወጣ ተደርጎ ነበረ።
ይህንን ጋሻ ለማስመለስ ‘ሮያል ኢትዮጵያን ትረስት’ ከታሪክ ተመራማሪው ከዶ/ር አሉላ ፓንክረስት ጋር በትብብር መሰራቱ ተጠቁሟል።
ዶ/ር አሉላ ፓንክረስት፣ ኢትዮጵያን ከፋሽስት ኢጣልያን ነጻ ለማውጣት የታገሉት የሲልቪያ ፓንክረስት የልጅ ልጅ እንዲሁም ቅርስ በማስመለስና የኢትዮጵያን ታሪክ በረቂቅ አዋቂ የነበሩት የፕሮፈሰር ሪቻርድ ፓንክረስት ልጅም ናቸው።
ጋሻው በህዳር ወር ወደ ኢትዮጵያ ከመመለሱ በፊት “ኢትዮጵያ በመስቀለኛ መንገድ” በሚል በኦሃዮ በሚገኘው ቶሌዶ የስነ ጥበብ ሙዚየም ውስጥ በሚዘጋጀው ኤግዚቢሽን ላይ ይታያል የተባለ ሲሆን ሲመለስም በኢትዮጵያ ብሔራዊ ሙዚየም ውስጥ ይቀመጣል ተብሏል።

ዜና: ለሁለተኛው ዙር የኮሪደር ልማት ተነሺዎች 5 ቢሊየን ብር ካሳ፣ 100 ሄክታር ምትክ መሬትና የሁለት አመት የቤት ኪራይ ክፍያ ተዘጋጅቷል - ከንቲባዋ
#በአዲስ አበባ በመከናወን ላይ ያለው ሁለተኛው ዙር የኮሪደር ልማት ስራ በአጠቃላይ 2817 ሄክታር መሬት እንደሚሸፍን፣ 132 ኪሜ ርዝመት እንዳለው የከተማዋ ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቢቤ አስታወቁ
በልማቱ ለሚነሱ የግል ባለይዞታዎች 5 ቢሊየን ብር የሚደርስ ካሳ በጀት መያዙን በመግለጽ 100 ሄክታር የሚጠጋ ምትክ መሬትና የሁለት አመት የቤት ኪራይ ክፍያም እንደተዘጋጀላቸው ገልጸዋል
በግንባታ ስራው ከተካተቱ የመሰረተ ልማት ስራዎች ውስጥ የመንገድ ግንባታ፣ የአረንጓዴ ቦታዎች ግንባታ፣ የብስክሌት መንገድ፣ የእግረኛ መንገድ፣ የህፃናት መጫወቻዎች፣ የታክሲና አውቶቢስ መጫኛና ማውረጃ ተርሚናሎች ይኖሩታል ብለዋል
በተጨማሪም የመኪና ማቆሚያ ፓርኪንጎች፣ የስፖርት ማዘውተሪያ ቦታዎች፣ የህዝብ መጸዳጃ ቦታዎች፣ የፍሳሽ ማስወገጃ መስመሮች፣ ደረጃውን የጠበቀ የከተማ መብራት የቴሌኮም መሰረተ ልማት እንዲሁም የደህንነት መጠበቂያ ቴክኖሎጂዎች ዝርጋታ ስራ እንደሚኖሩት ጠቅሰዋል
ሁለተኛውን ዙር የኮሪደር ልማት ስራውን በፍጥነት ለማጠናቀቅ በቂ ቅድመ ዝግጅት መደረጉን የጠቆሙት ከንቲባዋ በመልሶ ማልማቱ ተነሺ ለሆኑ ነዋሪዎች የመኖሪያ ቤቶችን፣ በቂ የመስሪያ ሼዶችን፣ ትምህርት ቤቶችን ጨምሮ የተለያዩ የመሰረተ ልማት ዝርጋታ እንዲሁም ከ 500 በላይ የሚሆኑ የንግድ ሱቆችን ለነዋሪዎቻችን ዝግጁ አድርገናል ብለዋል
https://web.facebook.com/AddisstandardAmh/posts/pfbid02fAh1JHaio61PS1B1ET631YqSZyhmF2FUNRWeQtKhdDyw8DKcyHkDsBmp6WUgHN5Cl

በአዋሳኝ አካባቢዎች የሚነሱ የማንነትና አስተዳደር ወሰን ጉዳዮች የመጨረሻ እልባት እንዲያገኙ በትጋት ይሰራል - አቶ አገኘሁ ተሻገር
በ #ትግራይና #አማራ ክልል አዋሳኝ አካባቢዎች የሚነሱ የአስተዳደር ወሰንና የማንነት ጉዳዮችን “በሪፈረንደም የመጨረሻ እልባት እንደያገኙ በትጋት እንደሚሰራ” የፌደሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አቶ አገኘሁ ተሻገር ገልጸዋል።
አፈ ጉባኤው ይህን የገለጹት ዛሬ መስከረም 28 ቀን 2017 ዓ.ም. በተካሄደው የፌደሬሽን ምክር ቤት 6ኛ የፓርላማ ዘመን 4ኛ አመት የስራ ጊዜ 1ኛ መደበኛ ስብሰባ ላይ ነው።
ምክር ቤቱ በዛሬው ዕለት ባካሄደው ስብሰባ ለሰላም እጦት መነሻ ናቸው የተባሉ የማንነትና የአስተዳደር ወሰን ጉዳዮችን መፍትሄ ለመስጠት የተጀመረው ጥረት እንዲጠናከር የቀረበው እቅድም ሙሉ ድጋፍ አግኝቷል ተብሏል።
በተለይ በትግራይና አማራ ክልል አዋሳኝ አካባቢዎች የሚነሱ የአስተዳደር ወሰንና የማንነት ጉዳዮች በብሄራዊ ደረጃ የተቋቋመው ኮሚቴ ከሚሰራው ስራ ጋር በመናበብ ተፈናቃዬችን ወደ ቀያቸው ከተመለሱ በኋላ የጋራ አስተዳደር አቋቁሞ በሪፈረንደም እልባት ለመስጠት ይሰራል ተብሏል።
ምክር ቤቱ በተጨማሪ የሕገመንግሥት ትርጉምና ውሳኔ አፈፃፀም ክትትል ቋሚ ኮሚቴ ከሕገ መንግሥት ትርጉም ጋር በተያያዘ ያቀረባቸውን የውሳኔ ሃሳቦች መርምሮ አጽድቋል ሲል ኢቢሲ ዘግቧል።