ዜና: የ #ጋምቤላ ከተማ የፖሊስ አዛዥ መገደልን ተከትሎ ግጭት ተቀሰቀሰ፤ የፀጥታ መዋቅሩ “በጎሳ መከፋፈሉ” ስጋት መደቀኑ ተገለጸ
በጋምቤላ ከተማ በትላንትናው ዕለት የከፍተኛ ፖሊስ አመራር መገደላቸውን ተከትሎ ግጭት የመቀስቀሱን ስማቸው እንዲጠቀስ ያልፈለጉ የቀደሞ የክልሉ የፀጥታ አመራር እና አንድ የክልሉ ባለስልጣን ለአዲስ ስታንዳርድ ገለፁ። የተቀሰቀሰው ግጭት አሁንም ቀጥሎ እንደሚገኝና የክልሉ "የጸጥታ መዋቅር በጎሳ ክፍፍል ምክንያት ሁኔታውን መቆጣጠር እንዳልቻለም" ተናግረዋል።
ትላንት ማክሰኞ ታኅሣሥ 7 ቀን 2018 ዓ.ም. ረፋድ ላይ፣ የጋምቤላ ከተማ ፖሊስ መምሪያ አዛዥ በጥይት ተመተው መገደላቸውን ባለስልጣናት ተናግረዋል። የክልሉ ባለስልጣን ድርጊቱን ሲያብራሩ “ፖሊስ አዛዡ የተገደለው በሥራ ቦታው ላይ ነው፤ የገደሉትም አብረውት የሚሰሩ ናቸው። ይሄ በጎጥ እና በዘር ተለይቶ የተፈጸመ በጣም አሳዛኝ ድርጊት ነው” ብለዋል።
ሌላኛው ስማቸው እንዳይጠቀስ የፈለጉ የጸጥታ አመራር የነበሩ ምንጫችን በበኩላቸው፣ አዛዡና ምክትላቸው ከተለያዩ ጎሳዎች በመሆናቸው ግድያው ከአዛዡ ጀርባ በነበረ “ሴራ” የተፈጸመ እንደሆነ አመልክተዋል።
በከተማዋ ለተፈጠረው ቀውስ ዋነኛው ምክንያት የጸጥታ መዋቅሩ አባላት “በጎሳ ተከፋፍለው ግጭቱ ውስጥ መሳተፋቸው እንደሆነ” ሁለቱም ባለሥልጣናት አረጋግጠዋል።
የጸጥታ አመራሩ “ፖሊስ ሆነው ነገር ግን አማፅያን ሆነው ታጥቀው የሚዋጉ አባላት አሉ፤ ይሄ ደግሞ አይካድም” በማለት ገልጸዋል።
https://addisstandard.com/Amharic/?p=10152

Addis standard
የጋምቤላ ከተማ የፖሊስ አዛዥ መገደልን ተከትሎ ግጭት ተቀሰቀሰ፤ የፀጥታ መዋቅሩ “በጎሳ መከፋፈሉ” ስጋት መውደቁ ተገለጸ - Addis standard
አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 8/ 2018 ዓ/ም:- በጋምቤላ ከተማ በትላንትናው ዕለት የከፍተኛ ፖሊስ አመራር መገደላቸውን ተከትሎ የተቀሰቀሰው ግጭት አሁንም ቀጥሎ እንደሚገኝና የክልሉ “የጸጥታ መዋቅር በጎሳ ክፍፍል ምክንያት ሁኔታውን መቆጣጠር እንዳልቻለ” ስማቸው እንዲጠቀስ ያልፈለጉ የቀደሞ የክልሉ የፀጥታ አመራር እና አንድ የክልሉ ባለስልጣን ለአዲስ ስታንዳርድ ገለፁ። ትላንት ማክሰኞ ታኅሣሥ 7 ቀን 2018…
የ #ትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት ከፌዴራል መንግስት ጋር ለመወያየት አዲስ አበባ ገቡ
የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት ሌተናል ጄነራል ታደሰ ወረደ ትላንት ከመቀሌ ተነስተው አዲስ አበባ ገብተዋል።
ፕሬዝዳንቱ ከፌዴራል መንግስት ጋር ለሚደረገው ውይይት ልዑካን ቡድኑን እየመሩ አዲስ አበባ ማቅናታቸውን የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ቢሮ ባወጣው አጭር መግለጫ አስታውቋል።
ቢሮው ትናንት ከሰዓት በኋላ በይፋዊ የማህበራዊ ትስስር ገፁ ላይ ያወጣው መግለጫ እንደሚያመለክተው፤ የጉብኝቱ ዓላማ ከፌዴራል ባለስልጣናት ጋር በ "አጠቃላይ ጉዳዮች" ላይ ለመወያየት ነው።
ይሁን እንጂ መግለጫው ስለ ውይይቱ ዝርዝር አጀንዳም ሆነ ሌተናል ጄነራል ታደሰ ወረደ የሚያገኟቸውን የፌዴራል መንግስት የስራ ኃላፊዎች ማንነት አልጠቀሰም።
ጉብኝቱ የሚከናወነው በትግራይ ለሁለት ዓመታት ያህል የዘለቀው ጦርነት ያበቃበት የፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት ከተፈረመ ሦስት ዓመቱን በያዘበት እንዲሁም፣ በሰሜን ኢትዮጵያ ያለው ፖለቲካዊና የፀጥታ ሁኔታ አሁንም እርግጠኝነት በጎደለው ሁኔታ ላይ ባለበት ወቅት ነው።
ምንም እንኳን ስምምነቱ መሰረታዊ አገልግሎቶችን መልሶ መጀመርን እና የክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር መመስረትን ጨምሮ ዋና ዋና ተነሳሽነቶችን በዝርዝር ቢያስቀምጥም፣ የእነዚህ ተግባራት አፈጻጸም ግን አሁንም ወጥ ባልሆነ መንገድ ላይ ይገኛል።
በመቶ ሺህዎች የሚቆጠሩ ሰላማዊ ሰዎች መፈናቀል፣ በምዕራብ ትግራይ እስከአሁን እልባት ያላገኙ አለመግባባቶች መቀጠላቸው እና በክልሉ ከኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ውጪ ሌሎች የታጠቁ ኃይሎች መኖር አሁንም ድረስ ምላሽ ከሚሹ ዋና ዋና ጉዳዮች መካከል ይጠቀሳሉ።
https://www.facebook.com/share/1DCFErGiEC/

ዜና: የጋምቤላ ክልላዊ መንግሥት አለመረጋጋትን ለመግታትና ሰላምን ለመመለስ ከፌዴራል ባለሥልጣናት ጋር እየሠራ መሆኑን ገለፀ
በጋምቤላ ክልል የተከሰተውን አለመረጋጋት ለመግታት እንዲሁም ሰላምና ጸጥታን ለማስፈን፣ ከፌዴራል መንግሥት ጋር በቅንጅት እየሠራ መሆኑን የክልሉ መንግሥት አስታወቀ።
የክልሉ መንግሥት ትናንት ምሽት ባወጣው መግለጫ፣ አሁን ካለው የጸጥታ ሁኔታ ጋር ተያይዞ ወንጀለኛ ያላቸውን ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ለማዋልና ለሕግ ለማቅረብ “ከፍተኛ ጥረት” እያደረገ መሆኑን ገልጿል።
ባለፉት ጥቂት ሳምንታት በክልሉ ያለው የጸጥታ ሁኔታ በከፍተኛ ሁኔታ አሽቆልቁሏል። አዲስ ስታንዳርድ በትናንትናው ዕለት በክልሉ የከፍተኛ ፖሊስ አመራር መገደላቸውን ተከትሎ ግጭት መቀስቀሱን ስማቸው እንዲጠቀስ ያልፈለጉ የቀደሞ የክልሉ የፀጥታ አመራር እና አንድ የክልሉ ባለስልጣን መግለጻቸውን መዘገቡ ይታወሳል።
እኚህ የቀድሞው የክልሉ ፀጥታ አመራር የተቀሰቀሰው ግጭት አሁንም ቀጥሎ እንደሚገኝና የክልሉ “የጸጥታ መዋቅር በጎሳ ክፍፍል ምክንያት ሁኔታውን መቆጣጠር እንዳልቻለም” ለአዲስ ስታንዳርድ ተናግረው ነበር።
ይህን ተከትሎ የክልሉ መንግሥት በመግለጫው በመደበኛ የጸጥታ ተግባር ላይ ከተሰማሩ የጸጥታ አካላት ውጭ፣ የጦር መሣሪያ ይዞ በሚንቀሳቀስ ማንኛውም ግለሰብም ሆነ ቡድን ላይ የጸጥታ ኃይሎች “አስፈላጊውን እርምጃ” እንደሚወስዱ አመልክቷል።
እንደ ክልሉ መንግሥት ገለጻ፣ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመቀናጀት ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥር ስር ለማዋል ክትትል እየተደረገ ሲሆን፣ በርካታ ግለሰቦችም በቁጥጥር ስር ውለዋል።
ዝርዝሩን ያንብቡ:
https://addisstandard.com/Amharic/?p=10157&=1

የጋምቤላ ክልላዊ መንግሥት አለመረጋጋትን ለመግታትና ሰላምን ለመመለስ ከፌዴራል ባለሥልጣናት ጋር እየሠራ መሆኑን ገለፀ - Addis standard
አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 9/ 2018 ዓ/ም:- በጋምቤላ ክልል የተከሰተውን አለመረጋጋት ለመግታት እንዲሁም ሰላምና ጸጥታን ለማስፈን፣ ከፌዴራል መንግሥት ጋር በቅንጅት እየሠራ መሆኑን የክልሉ መንግሥት አስታወቀ። የክልሉ መንግሥት ትናንት ምሽት ባወጣው መግለጫ፣ አሁን ካለው የጸጥታ ሁኔታ ጋር ተያይዞ ወንጀለኛ ያላቸውን ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ለማዋልና ለሕግ ለማቅረብ “ከፍተኛ ጥረት” እያደረገ መሆኑን ገልጿል።…
#ሶማሊያ እና #ጅቡቲ የመከላከያ ሚኒስትሮቻቸው በሞቃዲሾ ያደረጉትን ስብሰባ ተከትሎ የመከላከያ ትብብራቸውን አጠናከሩ
የሶማሊያ መንግስት የመከላከያ ሚኒስትር አህመድ ሙዓሊም ፊቂ፣ የጅቡቲ አቻቸውን ሐሰን ኡመር መሐመድን በሞቃዲሾ በሚገኘው ቢሯቸው ተቀብለው አነጋገሩ።
የጅቡቲ መከላከያ ሚኒስትር ሐሰን ኡመር መሐመድ የምሥራቅ አፍሪቃ ተጠንቀቅ ኃይል በእንግሊዝኛ ምህፃሩ (EASF) 35ኛው መደበኛ የመከላከያ እና የደህንነት ሚኒስትሮች ምክር ቤት ስብሰባ ላይ ለመሳተፍ ዋና ከተማዋ ሞቃዲሾ ገብተዋል።
ሁለቱ ሚኒስትሮች በጸጥታ እና በመከላከያ ዘርፎች ያላቸውን ስልታዊ ትብብር ማጠናከር በሚቻልባቸው ሁኔታዎች ላይ ሰፊ ውይይት አድርገዋል። በተጨማሪም ውይይቱ በአፍሪካ ቀንድ አስተማማኝ ሰላምና መረጋጋትን ለማስፈን ጥረቶችን ማቀናጀት በሚቻልባቸው ሰፋ ያሉ ቀጠናዊ ትብብሮች ላይ ማተኮሩ ተገልጿል።
በውይይቱ ወቅት የሶማሊያ መንግስት የመከላከያ ሚኒስትር አህመድ ሙዓሊም ፊቂ ፣ ጅቡቲ ላለፉት ዓመታት በሶማሊያ የመንግሥት ግንባታ ሂደት ውስጥ ላበረከተችው ጉልህ ሚና ያላቸውን ምስጋና መግለጻቸውን የሶማሊያ ብሔራዊ የዜና አገልግሎት (ሶና) ዘግቧል።
ሚኒስትሩ በተለይም ጅቡቲ በሶማሊያ የአፍሪካ ህብረት የድጋፍ እና የማረጋጋት ተልዕኮ አውሶም ውስጥ የምታደርገውን ንቁ ተሳትፎ አንስተዋል። ይህም ጅቡቲ ለሶማሊያ የምታሳየው ቀጣይነት ያለው ድጋፍ እና በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን እውነተኛ የወንድማማችነት ትስስር ማሳያ መሆኑን መናገራቸውን ዘገባው አመልክቷል።

#ፖሊስ በአምስት ክፍለ ከተሞች ከ54 ሺህ በላይ የ #ሺሻ ዕቃዎችን እና ከ650 ኪሎግራም በላይ አደንዛዥ ዕፅ ማስወገዱን አስታወቀ
የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ በከተማዋ በተለያዩ ክፍለ ከተሞች ባካሄደው ተከታታይ እና የተቀናጀ ኦፕሬሽን፣ ለወንጀል መንስኤ ናቸው ያላቸውን በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ የሺሻ መጠቀሚያ ዕቃዎችን፣ በመቶዎች የሚቆጠሩ ኪሎ ግራም አደንዛዥ ዕፆችን እና ሀሰተኛ የገንዘብ ኖቶችን በህግ አግባብ ማስወገዱን አስታወቀ።
ፖሊስ እርምጃውን የወሰደው “የወንጀል መንስኤዎችን በጥናት በመለየት እና የወንጀል ዕቅድ የሚወጣባቸውን ስፍራዎች በማድረቅ ሰላምን ለማረጋገጥ” በሚል እንደሆነ ገልጿል።
በዚህም በቦሌ ክፍለ ከተማ ከሐምሌ 2017 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ህዳር 2018 ዓ.ም ድረስ በምሽት ጭፈራ ቤቶች፣ በፔንሲዮኖች እና በጫት ማስቃሚያ ቤቶች ላይ በተደረገ ድንገተኛ ፍተሻ 17,095 የሺሻ ዕቃዎች፣ 605 ኪሎ ግራም ሀሺሽ እና 100 ኪሎ ግራም ጫት ተይዞ መወገዱን የቦሌ ክፍለከተማ ፖሊስ መምሪያ ኃላፊ ረ/ኮሚሽነር አድማሱ ኢፋ ገልጸዋል።
በተመሳሳይ በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ባለፉት ወራት በተሰራ ኦፕሬሽን 22,750 የሺሻ ማስጠቀሚያ ዕቃዎች የተወገዱ ሲሆን፣ ከጉዳዩ ጋር በተያያዘ 209 ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ውለው በ105 የምርመራ መዝገቦች ክስ እንዲመሰረትባቸው መደረጉ ተገልጿል።
በተጨማሪም በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ በመኖሪያ ቤቶችና ሆቴሎች ውስጥ በተደረገ ፍተሻ 13,420 የሺሻ ዕቃዎች፣ 50 ኪሎ ግራም አደንዛዥ ዕፅ፣ 300 ፍሬ ትራማዶል እና ሀሰተኛ የገንዘብ ኖቶች መወገዳቸው ተጠቁሟል።
https://www.facebook.com/share/1D712bFTg9/

ዜና: ህወሓት የነዳጅ እጥረትና የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ መገታትን በመጥቀስ፣ በትግራይ ክልል “አዲስ ከበባ” መጣሉን ገለፀ
ህወሓት “የፌዴራል መንግሥት ላለፉት አሥር ወራት በትግራይ የነዳጅ አቅርቦት መገደቡ፣ በትራንስፖርት፣ በኢኮኖሚ እንቅስቃሴ እና መሠረታዊ ማኅበራዊ አገልግሎቶች ላይ መስተጓጎል ፈጥሯል” ሲል ገለፀ፤ ይህም የፕሪቶሪያው ስምምነት አተገባበር ላይ ሥጋት መፍጠሩን ጠቅሷል።
ህወሓት ትናንት ታኅሣሥ 8 ቀን 2018 ዓ.ም ባወጣው መግለጫ፣ የፌዴራል መንግሥት ለትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር የሚያስተላልፈውን የበጀት ድጋፍ ማገዱን ገልጿል። ይህም የጤና፣ የትምህርት፣ የውኃ እና የጽዳት አገልግሎቶችን ጨምሮ የመንግሥት የሥራ እንቅስቃሴዎች እንዲስተጓጎሉ ከማድረጉም በላይ፣ የመንግሥት ሠራተኞች ደመወዝ ሳይከፈላቸው እንዲቀሩ ማድረጉን አስታውቋል።
መግለጫው አክሎም በትግራይ መልሶ ማቋቋም ኢንዶውመንት ፈንድ (ኤፈርት) ሥር ያሉ ኩባንያዎች የባንክ ሂሳብ መታገዱን ኮንኗል። ይህም የድርጅቶቹ የሥራ እንቅስቃሴ እንዲቆም እና በአሥር ሺዎች የሚቆጠሩ ሠራተኞች ያለ ደመወዝ እንዲቀሩ ማድረጉን ገልጿል።
“የኢትዮጵያ መንግሥት ወደ ትግራይ የሚገባውን የነዳጅ አቅርቦት በከፍተኛ ሁኔታ ከገደበው አሥር ወራት ሊሞላው ተቃርቧል” ያለው ህወሓት “ይህም የሕዝብና የጭነት ትራንስፖርትን፣ የኢኮኖሚ እንቅስቃሴዎችን እንዲሁም ለሴቶችና ለሕፃናት የሚሰጡ የድንገተኛ አምቡላንስ አገልግሎቶችን ጨምሮ ማኅበራዊ አገልግሎቶችን ሽባ አድርጓል” ሲል ገልጿል።
ተጨማሪ ያንብቡ:
https://addisstandard.com/Amharic/?p=10161&=1

ህወሓት የነዳጅ እጥረትና የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ መገታትን በመጥቀስ፣ በትግራይ ክልል "አዲስ ከበባ" መጣሉን ገለፀ - Addis standard
አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 9/2018 ዓ/ም:- ህወሓት “የፌዴራል መንግሥት ላለፉት አሥር ወራት በትግራይ የነዳጅ አቅርቦት መገደቡ፣ በትራንስፖርት፣ በኢኮኖሚ እንቅስቃሴ እና መሠረታዊ ማኅበራዊ አገልግሎቶች ላይ መስተጓጎል ፈጥሯል” ሲል ገለፀ፤ ይህም የፕሪቶሪያው ስምምነት አተገባበር ላይ ሥጋት መፍጠሩን ጠቅሷል። ህወሓት ትናንት ታኅሣሥ 8 ቀን 2018 ዓ.ም ባወጣው መግለጫ፣ የፌዴራል መንግሥት ለትግራይ ጊዜያዊ…
ከ60 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመት ወርቅና ከ4ሚሊየን ብር በላይ ይዘው በሕገ ወጥ መንገድ ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ሥር ዋሉ
የ #ኢትዮጵያ_ፌደራል_ፖሊስ ከ60 ሚሊየን ብር በላይ የዋጋ ግምት ያለው ወርቅና ከ4ሚሊየን ብር በላይ ይዘው በሕገ ወጥ መንገድ ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ተጠርጣሪዎች ከእነኤግዚቢቱ በቁጥጥር ስር መዋላቸውን አስታወቀ።
ተጠርጣሪዎቹ በቁጥጥር ስር የዋሉት በአሶሳ ከተማ አምባ አንድ በሚባል ቦታ መሆኑን ፖሊስ ገልጿል፡፡
ተጠርጣሪዎቹ ከእነ ወርቅና ጥሬ ገንዘቡ በቁጥጥር ስር ሊውል የቻሉት በፌደራል ፖሊስ ወንጀል መከላከል የኮንትሮባንድ ቁጥጥር ፖሊስ መምሪያ ከህበረተሰቡ በደረሰው ጥቆማ መሰረት ባደረገው ክትትል መሆኑ ተጠቁሟል።
በኮንትሮባንድ ቁጥጥር ፖሊስ መምሪያ ሬጅመንት አዛዥ ዋና ኢንስፔክተር ዳኘ አለማየሁ በበኩላቸው የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ በተጠርጣሪዎቹ ላይ ምርመራ እያጣራባቸው መሆኑን ጠቅሰው የተያዘው ወርቅና ጥሬ ገንዘብም ለአሶሳ ከተማ ጉሙሩክ ቅርንጫፍ ገቢ መደረጉን ተናግረዋል።
አክለውም የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ኮንትሮባንድና ሕገ-ወጥ ንግድ በሀገር ኢኮኖሚ እና በሕጋዊ ነጋዴዎች ላይ የሚያደርሰውን ጉዳት በመገንዘብ ከሕዝብና ከመንግሰት የተጣለበትን አደራ ለመወጣት ሕዝብን ባሳተፈ መልኩ ስኬታማ የመከላከል ሥራ እያከናወነ መሆኑን መግለጻቸውን ከተቋሙ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

ግማሽ ሚሊዮን ብር ጉቦ ሲቀበሉ "እጅ ከፍንጅ" የተያዙት የፍትሕ ሚኒስቴር ዐቃቤ ሕግ እና ግብረ አበሮቻቸው ክስ ተመሰረተባቸው
በፍትሕ ሚኒስቴር የዐቃቤ ሕግነት የሥራ መደብ ላይ ተመድበው ሲሰሩ የነበሩ ግለሰብ እና ግብረ አበሮቻቸው፣ ከአንድ ባለጉዳይ 1 ሚሊዮን ብር ጉቦ ለመቀበል ሲደራደሩና ግማሽ ሚሊዮኑን ተቀብለው ደረሰኝ ሲሰጡ "እጅ ከፍንጅ" ተይዘው ክስ እንደተመሰረተባቸው ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ አስታወቀ።
እንደ ሚኒስቴሩ መግለጫ፣ ተከሳሾቹ በወንጀል ተጠርጥረው በምርመራ ላይ በነበሩ ግለሰብ ላይ "የወንጀል ክስ እንዳይቀርብ እናደርጋለን" በማለት 1 ሚሊዮን ብር እንዲከፈላቸው ሲደራደሩ ቆይተዋል።
ይህንን ድርጊት የተገነዘቡ ጠቋሚዎች ለፍትሕ ሚኒስቴር ከፍተኛ አመራሮች መረጃውን በማቀበላቸው፣ ከፌዴራል ፖሊስ ጋር በመቀናጀት ጥብቅ ክትትል ሲደረግ ቆይቷል።
ሕዳር 16 ቀን 2018 ዓ.ም ተከሳሾቹ ከባለጉዳዩ ቤተሰቦች 500,000 (አምስት መቶ ሺህ) ብር ለጊዜው ባልተያዘ ግብረ አበራቸው የባንክ ሒሳብ በኩል እንዲገባ ካደረጉ በኋላ....
https://www.facebook.com/share/p/1DU69gr246/

የ #ኢትዮጵያ_ንግድ_ባንክ ደንበኞቹ የባንክ ሒሳባቸውን ከዲጂታል መታወቂያ ጋር እንዲያስተሳስሩ አሳሰበ
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ደንበኞቹ የባንክ ሒሳባቸውን ከፋይዳ ብሔራዊ ዲጂታል መታወቂያ ቁጥር ጋር እንዲያስተሳስሩ፣ ካልሆነ ግን ከተቀመጠው የጊዜ ገደብ በኋላ ምንም ዓይነት የባንክ አገልግሎት ማግኘት እንደማይችሉ አስታወቀ።
ባንኩ ታኅሣሥ 9 ቀን 2018 ዓ.ም. ባወጣው መግለጫ፣ ደንበኞች ወደ የትኛውም የንግድ ባንክ ቅርንጫፍ በመሄድ ባለ 16 አሃዝ የፋይዳ አካውንት ቁጥራቸውን በማቅረብ ከሒሳባቸው ጋር ማገናኘት እንዳለባቸው ገልጾ ይህንን ያላደረጉ ደንበኞች ገንዘብ ማስገባት፣ ማውጣት እና ሌሎች የባንክ አገልግሎቶችን ማግኘት እንደማይችሉ ባንኩ አስጠንቅቋል።
ባንኩ በአዲስ አበባ፣ ሐረሪ እና ድሬዳዋ ደንበኞች እስከ ጥር 1 ቀን 2018 ማስተሳሰር እንደሚችሉ ገልጾ ከጥር 2 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ ግን ግዴታ እንደሚሆን አስታውቋል።
በትልልቅ የክልል ከተሞችና በወረዳ ዋና ከተሞች ደንበኞች እስከ ጥር 30 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ የጊዜ ገደብ የተሰጣቸው ሲሆን፣ የግዴታ አፈጻጸሙ ከየካቲት 2 ቀን 2018 ዓ.ም. ጀምሮ ይተገበራል።
በገጠር ወረዳዎችና ቀበሌዎች ደግሞ....
https://www.facebook.com/share/p/19VgLAQgXB/

የ #ሶማሊያ እና የ #ኢትዮጵያ ባለሥልጣናት የሁለትዮሽ ትብብርን ለማጠናከር በሞቃዲሾ ተገናኝተው ተወያዩ
የሶማሊያ የውጭ ጉዳይ እና ዓለም አቀፍ ትብብር ሚኒስትር አብዲሰላም አብዲ አሊ፣ በሶማሊያ የኢትዮጵያ አምባሳደር ሱሌይማን ደደፎ ጋር በሞቃዲሹ ተገናኝተው ተወያዩ።
ውይይቱ ያተኮረው በሁለቱ አገራት መካከል ያለውን ግንኙነት እና ቀጠናዊ ትብብር ይበልጥ በማጠናከር ላይ መሆኑ ተገልጿል።
በከፍተኛ ደረጃ በተካሄደው በዚህ ስብሰባ ላይ የሁለቱ ሀገራት ባለሥልጣናት እንደ ንግድ፣ ኢንቨስትመንት እና ኢኮኖሚያዊ ልማት ባሉ ዘርፎች ያላቸውን ስትራቴጂያዊ ትብብር ማሳደግ በሚቻልባቸው መንገዶች ላይ ተወያይተዋል።
በተጨማሪም በአፍሪካ ቀንድ ሰላምና ደህንነትን ለማስጠበቅ የሚደረገውን የጋራ ጥረት ማጠናከር በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ ትኩረት ማድረጋቸው ተጠቁሟል። እንደ ሽብርተኝነት፣ ድንበር ተሻጋሪ ወንጀሎች እና ፖለቲካዊ አለመረጋጋት ላሉ ቀጠናዊ ተግዳሮቶች የተቀናጀ ምላሽ መስጠት አስፈላጊ መሆኑንም አፅንዖት ሰጥተውበታል ተብሏል።
ውይይቱ በሁለቱ ጎረቤት አገራት መካከል ያለውን የቆየ ግንኙነት ያጎላ ሲሆን፤ የኢኮኖሚ አጋርነትን እና የመሠረተ ልማት ፕሮጀክቶችን ይበልጥ ማጠናከር በሚቻልባቸው ዕድሎች ላይም መክሯል።
ሁለቱም ወገኖች ለሕዝቦቻቸው ጥቅም ሲባል መረጋጋትን፣ ብልጽግናን እና ጠንካራ የሁለትዮሽ ግንኙነትን ለማምጣት በቅርበት ለመሥራት ያላቸውን ቁርጠኝነት በድጋሚ ማረጋገጣቸውን ሸበሌ ሚዲያ ዘግቧል።
ረጅም ድንበር የሚጋሩትና ታሪካዊ ትስስር ያላቸው ሶማሊያ እና ኢትዮጵያ፣ በቅርብ ዓመታት ውስጥ ዲፕሎማሲያዊ እና የደህንነት ትብብራቸውን አጠናክረዋል። በተለይም የሽብር ቡድኖችን ለመዋጋት እና ቀጠናዊ የልማት ውጥኖችን ለመደገፍ በሚደረጉ ጥረቶች ላይ በትኩረት እየሰሩ እንደሚገኝ ዘገባው አመልክቷል።

ጠ/ሚ ዐቢይ አህመድ የሶማሊያ ፕሬዝደንት ሀሰን ሼኽ ሞሃሙድን ተቀብለው አነጋገሩ
የሶማሊያ ፌደራል ሪፐብሊክ ፕሬዝደንት ሀሰን ሼኽ ሞሃሙድን ለአንድ ቀን የሥራ ጉብኝት ተቀብለው ማነጋገራቸውን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) አስታወቁ።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በይፋዊ የፌስቡክ ገፃቸው ላይ ባሰፈሩት ፅሑፍ "ባለፈው አንድ አመት እየሰራንባቸው የቆየነውን የሁለትዮሽ ግንኙነት ውይይቶች በመቀጠል ፍሬያማ ውይይት አድርገናል" ሲሉ ገልፀዋል።
በተጨማሪም ውይይቱ "የወል የቅድሚያ ጉዳዮቻችንን ለመከወን ብሎም ለጠንካራ ግንኙነት፣ ቀጠናዊ መረጋጋት እና ልማት ያለንን ቁርጠኝነት በድጋሚ ያፀና ነበር" ብለዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ይህን የገለፁት የሶማሊያ የውጭ ጉዳይ እና ዓለም አቀፍ ትብብር ሚኒስትር አብዲሰላም አብዲ አሊ፣ በሶማሊያ የኢትዮጵያ አምባሳደር ሱሌይማን ደደፎ ጋር በሞቃዲሹ ተገናኝተው መወያየታቸውን ተከትሎ ነው።

ዜና: በ #ምስራቅ_ወለጋ #ኪረሙ ወረዳ እየተባባሰ በመጣው የፀጥታ ችግር ነዋሪዎች እየተፈናቀሉ መሆኑ ተገለጸ
በ #ኦሮሚያ ክልል ምሥራቅ ወለጋ ዞን ኪረሙ ወረዳ ላለፉት አምስት ወራት እየተባባሰ የመጣው የጸጥታ ችግር ነዋሪዎችን ለከፋ መፈናቀልና ሰብዓዊ ቀውስ መዳረጉን አዲስ ስታንዳርድ ያነጋገረቻቸው ነዋሪዎች ገለጹፁ።
ነዋሪዎቹ "የፋኖ ታጣቂዎች በአካባቢው መንቀሳቀሳቸው" ለፀጥታው ችግር መባባስ ምክንያት መሆኑን ገልጸዋል።
የኪረሙ ወረዳ ባለስልጣን የሆኑት አቶ አለባቸው ወዬሳ፣ ሰሞኑን በታጣቂዎች በደረሰ የጸጥታ ችግር ከ1,000 በላይ ሰዎች መፈናቀላቸውን አረጋግጠው፣ ከተፈናቃዮቹ መካከል አብዛኞቹ የኪረሙ ወረዳ የአሹ ኩታዬ፣ የጉዲና ጅሬኛ እና የባቡ መንደሮች ነዋሪዎች መሆናቸውን ተናግረዋል።
ከጉዲና ጅሬኛ መንደር የተፈናቀሉ አንድ ነዋሪ፣ "ህዳር 23 ቀን 2018 ዓ.ም ሌሊቱን ሙሉ የዘለቀ ተከታታይ ተኩስና ግጭት ነበር" ያሉ ሲሆን "ለሕይወታቸን በመስጋት ሰብላችንንና ቤታችንን ጥለን ወደ ኪረሙ ከተማ በዘመድ ቤት ተጠልለን ነው የምንገኘው" ብለዋል።
ነዋሪው አክለውም ብዙዎቹ ተፈናቃዮች ወደ ጫካ፣ ወደ አጎራባች መንደሮች እንዲሁም ወደ ኪረሙ ከተማ በመሰደድ ለከፍተኛ ችግር እየተጋለጡ መሆኑን ጠቁመዋል።
ስሙ እንዳይጠቀስ የፈለገ የ12ኛ ክፍል ተማሪ፣ በአካባቢው ባለው አለመረጋጋት ምክንያት ትምህርቱን አቋርጦ መፈናቀሉን ተናግሯል።
ሙሉ ዘገባ: https://addisstandard.com/Amharic/?p=10164&=1

በምስራቅ ወለጋ ኪረሙ ወረዳ እየተባባሰ በመጣው የፀጥታ ችግር ነዋሪዎች እየተፈናቀሉ መሆኑ ተገለጸ - Addis standard
አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 10/ 2018 ዓ/ም:- በኦሮሚያ ክልል ምሥራቅ ወለጋ ዞን ኪረሙ ወረዳ ላለፉት አምስት ወራት እየተባባሰ የመጣው የጸጥታ ችግር ነዋሪዎችን ለከፋ መፈናቀልና ሰብዓዊ ቀውስ መዳረጉን አዲስ ስታንዳርድ ያነጋገረቻቸው ነዋሪዎች ገለጹፁ። ነዋሪዎቹ “የፋኖ ታጣቂዎች በአካባቢው መንቀሳቀሳቸው” ለፀጥታው ችግር መባባስ ምክንያት መሆኑን ገልጸዋል። የኪረሙ ወረዳ ባለስልጣን የሆኑት አቶ አለባቸው…
#ኢትዮጵያ እና #ኬንያ የድንበር ንግድ ስምምነት ተፈራረሙ
የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ካሳሁን ጎፌ (ዶ/ር) እና የኬንያ የኢንቨስትመንት፣ ንግድና ኢንዱስትሪ ካቢኔ ሲክሬተሪ ሊ ኪንያንጂዩን በትናንትናው ዕለት የድንበር ንግድ ስምምነት ተፈራርመዋል።
ስምምነቱ እ.ኤ.አ ሚያዚያ 17 ቀን 2025 በኬንያ ሞምባሳ የተደረሰበት ስምምነት አካል መሆኑን የገለጹት ሚኒስትሩ አክለውም በሁለቱ ጎረቤት አገሮች መካከል ለረጅም ጊዜ የወዳጅነት እና የሁለትዮሽ ትብብር ታሪክ ውስጥ ጉልህ ምዕራፍ የሚኖረው ነው ብለዋል።
አክለውም የንግድ እንቅፋቶችን በመቀነስ አነስተኛ መጠን ያለው ድንበር ተሻጋሪ ንግድን የሚያጠናክር መሆኑን ጠቅሰው በተለይም በአሁኑ ጊዜ አብዛኛዎቹን መደበኛ ያልሆኑ ድንበር ተሻጋሪ ነጋዴዎች በተለይም ለሴቶች እና ወጣቶች ግልጽና ሊገመት የሚችል ማዕቀፍ የሚፈጥር መሆኑንም ጠቁመዋል።
ስምምነቱ ወደ ሙሉ ትግበራ ሲገባ የንግድ ዕድሎችን የሚያሰፋ ሲሆን የሁለቱ ሃገራት መንግስታትና የግሉ ዘርፍ በጠንካራ ቅንጅት መስራት ይኖርብናል ሲሉ ገልጸዋል።
በተጨማሪም ስምምነቱ የጉምሩክ አሠራሮችን ቀላል በማድረግ እና ሰነዶችን በማስማማት ደህንነቱ የተጠበቀ፣ ህጋዊ እና ዘላቂ የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ እንዲፈጠር እንደሚያደርግ ተመላክቷል።
የኬንያ ልኡካን ቡድን በቆይታቸው የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር የወጪ ንግድ ማዕከል መጎብኘታቸውን ከሚኒስቴሩ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

#ኢትዮ_ቴሌኮምና የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን በኤክስፖርት የጥራት ደረጃ የተዘጋጁ ምርቶችን በ #ዘመን_ገበያ በኩል ለሀገር ውስጥ ሸማቾች ለማቅረብ የሚያሰችል ስምምነት ተፈራረሙ
ኢትዮ ቴሌኮም እና የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን በኢንዱስትሪ ፓርኮች ውስጥ የሚመረቱ የኤክስፖርት ጥራት ያላቸውን ምርቶች በቴሌብር "ዘመን ገበያ" አማካኝነት ለሀገር ውስጥ ሸማቾች ለማቅረብ የሚያስችል የመግባቢያ ስምምነት ተፈራርመዋል።
ስምምነቱ በኢንዱስትሪ ፓርኮች ውስጥ የሚገኙ አምራቾች ለዓለም አቀፍ ገበያ የሚያቀርቧቸውን ምርቶች ለመጀመሪያ ጊዜ ለሀገር ውስጥ ሸማቾች ተደራሽ ለማድረግ ያለመ መሆኑን ኢትዮ ቴሌኮም አስታውቋል።
በ"ዘመን ገበያ" ላይ ለግብይት የሚቀርቡት ምርቶች፣ ከፍተኛ የጥራት ደረጃ ያላቸው ጨርቃ ጨርቅና አልባሳት ፣ ቆዳና የቆዳ ውጤቶች ፤ የአግሮ-ፕሮሰሲንግ ምርቶች ፤ የኤሌክትሮኒክስና ቴክኖሎጂ ውጤቶች እንዲሁም መድኃኒትና የሕክምና ግብዓቶች ይገኙበታል።
https://www.facebook.com/share/p/1APAyCV53y/

የ #ኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት በቴክኖሎጂ የተደገፈ አገልገሎት ለመስጠት ከ #ቻይናው ሁዋዌ ኩባንያ ጋር ስምምነት ተፈራረመ
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የሚሰጠውን አገልግሎት በቴክኖሎጂ የተደገፈ ለማድረግና ይበልጥ ለማዘመን የሚያስችለውን የመግባቢያ ስምምነት ከቻይናው ሁዋዌ ኩባንያ ጋር መፈራረሙን አስታወቀ፡፡
የመግባቢያ ስምምነቱን የፈረሙቱ የአገልግሎቱ ዋና ስራ አስፈፃሚ ኢንጅነር ጌቱ ገረመውና የሁዋዌ ኩባንያ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ሲሆኑ፤ ስምምነቱንም በኩባንያው ዋና መስሪያ ቤት ተካሂዷል፡፡
የተፈረመው የመግባቢያ ስምምነት በሃገራችን ስማርት ግሪድ ለማስፋፋት፣ የኤሌክትሪክ መሰረተ ልማት ዝርጋታ ለማዘመንና አስተማማኝ የኃይል አቅርቦትን ለማሳደግ የሚያስችሉ ቴክኖሎጂዎችን ከህዋዌ ጋር በትብብር ለመዘርጋት የሚያስችል መሆኑን ዋና ስራ አስፈፃሚ ኢንጅነር ጌቱ ገረመው በፊርማ ስነ ስርዓቱ ወቅት ተናግረዋል፡፡
እንደ አገልግሎቱ መረጃ ኢንጅነር ጌቱ በኢትዮጵያ የኤሌክትሪክ ተሸከርካሪ ቻርጅ መሰረተ ልማትን ለማስፋፋት ሁሉቱም ተቋማት በትብብር ለመስራት መስማማታቸውን ገልፀዋል፡፡
ዘመናዊ የኤሌክትሪክ መስመር ስርጭት መቆጣጠሪያ ለመገንባት፣ ለረጅም ጊዜ ኢነርጂ የሚያቆዩ ባትሪዎችን ለመትከልና የዘመኑ ቴክኖሎጂዎችን በኢትዮጵያ ለመተግበር ስምምነት ላይ መደረሱንም ጨመረው ጠቁመዋል፡፡
የሁዋዌ ኩባንያ ተወካዮች በበኩላቸው በፈጠራ ላይ የተመሰረቱና ዘመናዊ ቴክኖሎጂን የተላበሱ ዘላቂ የኢነርጂ መፍትሄ ቴክኖሎጂዎችን በኢትዮጵያ ለመተግበር ቁርጠኛ መሆናቸውን ገልፀዋል፡፡
ቴክኖሎጂን አውቆ የሚተገበር ሠራተኛን ለመፍጠር ክህሎት ላይ ያተኮሩ ስልጠናዎችን እንደሚያመቻቹም ተናግረዋል፡፡

#አሜሪካ ወታደሮችን ለማሰባሰብ ተግዳሮት በገጠማት ወቅት፤ ማርኮ ሩቢዮ #ኢትዮጵያ በጋዛ ለታቀደው ሰላም አስከባሪ ኃይል ወታደሮችን እንድታዋጣ ጥያቄ ማቅረባቸው ተዘገበ
የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማርኮ ሩቢዮ፣ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ኢትዮጵያ በጋዛ ለታቀደው ዓለም አቀፍ የጸጥታ ኃይል ወታደሮቿን እንድታዋጣ እንዲያስቡበት መጠየቃቸውን ‘ዘ ታይምስ ኦፍ ኢስራኤል’ የምዕራባውያን ዲፕሎማሲያዊ ምንጮችን ጠቅሶ ዘግቧል።
ዋሽንግተን በፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ የ20 ነጥብ የጋዛ እቅድ ስር የተመለከተውን ዓለም አቀፍ ኃይል ለማዋቀር በሚደረገው ጥረት፣ ጥያቄው በዚህ ሳምንት መጀመሪያ ላይ የቀረበ መሆኑ ተገልጿል።
እቅዱ በጦርነት ምክንያት ክፉኛ በፈራረሰው የፍልስጤም ግዛት ውስጥ፣ መልሶ ግንባታ እና ኢኮኖሚያዊ ማገገም ላይ ትኩረት ለሚያደርገው የሽግግር ወቅት ክትትል የሚሰጥ ዓለም አቀፍ የጸጥታ ኃይል እንዲኖር ይጠይቃል። ግዛቱ ላለፉት ሁለት ዓመታት በላይ በዘለቀው ጦርነት ምክንያት ከፍተኛ ውድመት ደርሶበታል።
ብዙ አገራት በዓለምአቀፍ ኃይሉ ውስጥ ተሳትፎ ማድረግን በጥንቃቄ እየተመለከቱት መሆኑ፣ ዩናይትድ ስቴትስ ለጸጥታ ኃይሉ ድጋፍ ለማግኘት ተግዳሮት እንዲገጥማት ማድረጉን ዘገባው አመልክቷል።
በተለይም የተልዕኮው ዓላማ በጋዛ የሚንቀሳቀሰውን ሐማስን ትጥቅ ማስፈታት መሆኑ፣ አገራቱ ለመሳተፍ እንዲሰጉ አድርጓቸዋል ተብሏል። ይህ ስጋት በዕቅድ ደረጃ ላይ የሚገኘውን የጸጥታ ኃይል አባላት የማሟላት ጥረትን እንዳወሳሰበው ተመላክቷል።
የቀረበውን ጥያቄ በተመለከተ ከኢትዮጵያ መንግሥትም በኩል ሆነ ከአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት እስካሁን የተሰጠ ይፋዊ መግለጫ የለም።
https://www.facebook.com/share/1C7X3PrwXb/

ዜና: የገንዘብ ድጋፍ እጥረት በ1.1 ሚሊዮን ሰዎች ላይ አደጋ መደቀኑን ተከትሎ ኢትዮጵያ ወደ ሀገሯ ለሚገቡ ስደተኞች የምታደርገው የዕርዳታ መርሃ ግብር ሊቀለበስ እንደሚችል የረድኤት ድርጅቶች አስጠነቀቁ
አስቸኳይ የገንዘብ ድጋፍ ካልተገኘ በሚቀጥሉት ጥቂት ሳምንታት ውስጥ ከ1.1 ሚሊዮን በላይ ለሚሆኑ ስደተኞች የሚቀርቡ መሠረታዊ አገልግሎቶች ሊቋረጡ እንደሚችሉና የኢትዮጵያ የስደተኞች ዕርዳታ መርሃ ግብር የመፍረስ አደጋ ተጋርጦበት እንደሚገኝ መንግሥት እና የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የረድኤት ተቋማት አስጠነቀቁ።
የስደተኞች እና ከስደት ተመላሾች አገልግሎት፣ የተባበሩት መንግሥታት የስደተኞች ከፍተኛ ኮሚሽን እና የዓለም የምግብ ፕሮግራም ትናንት ታኅሣሥ 10 ቀን 2018 ዓ.ም ለአዲስ ስታንዳርድ በላኩት የጋራ መግለጫ፤ የገንዘብ እጥረቱ በስደተኞች ላይ የሚደረገውን ድጋፍ “ሊቋቋሙት ወደማይችሉበት ደረጃ” አድርሶታል ብለዋል።
ተቋማቱ በመግለጫቸው በአፍሪካ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸውን ስደተኞች በመቀበል ሁለተኛ የሆነችው ኢትዮጵያ በሱዳን እና በደቡብ ሱዳን ግጭት፣ እንዲሁም በሶማሊያ በተከሰተው ድርቅ ምክንያት ወደ ሀገሯ የሚገቡ ስደተኞች ቁጥር ቢጨምርም፤ የሚገኘው የገንዘብ ድጋፍ ግን በከፍተኛ ሁኔታ ቀንሷል ሲሉ ገልጸዋል። በዚህ የገንዘብ እጥረት ምክንያትም በ2025 (እ.ኤ.አ) የሚቀርቡ የአስቸኳይ ጊዜ እርዳታ ቁሳቁሶች በ70 በመቶ መቀነሳቸውን ገልጸዋል።
የስደተኞች እና ከስደት ተመላሾች አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ወይዘሮ ጠይባ ሀሰን፤ ኢትዮጵያ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ የመጣው ጫና ባይቀንስም ስደተኞችን የመጠበቅ ግዴታዋን እየተወጣች ትገኛለች ሲሉ ተናግረዋል።
ሆኖም ይህንን ከባድ ኃላፊነት መንግሥት ብቻውን ሊወጣው አይችልም ያሉት ዋና ዳይሬክተሯ፣ ያሉ ሀብቶች ከአቅም በላይ መለጠጣቸውንና በአስተናጋጅ ማኅበረሰቦች ላይ የሚፈጠረው ጫናም እየጨመረ መምጣቱን አክለው ገልጸዋል።
ዝርዝር ዘገባውን ይመልከቱ:-
https://addisstandard.com/Amharic/?p=10166&=1

የገንዘብ ድጋፍ እጥረት በ1.1 ሚሊዮን ሰዎች ላይ አደጋ መደቀኑን ተከትሎ ኢትዮጵያ ወደ ሀገሯ ለሚገቡ ስደተኞች የምታደርገው የዕርዳታ መርሃ ግብር ሊቀለበስ እንደሚችል የረድኤት ድርጅቶች አስጠነቀቁ -…
አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 11/ 2018 ዓ/ም:- ስቸኳይ የገንዘብ ድጋፍ ካልተገኘ በሚቀጥሉት ጥቂት ሳምንታት ውስጥ ከ1.1 ሚሊዮን በላይ ለሚሆኑ ስደተኞች የሚቀርቡ መሠረታዊ አገልግሎቶች ሊቋረጡ እንደሚችሉና የኢትዮጵያ የስደተኞች ዕርዳታ መርሃ ግብር የመፍረስ አደጋ ተጋርጦበት እንደሚገኝ መንግሥት እና የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የረድኤት ተቋማት አስጠነቀቁ። የስደተኞች እና ከስደት ተመላሾች አገልግሎት፣…
#የመን 180 #ኢትዮጵያውያን ስደተኞች በህገወጥ መንገድ በሻብዋ የባህር ዳርቻ መድረሳቸውን አስታወቀች
የመን የሚገቡ መደበኛ ያልሆኑ ስደተኞች ቁጥር በከፍተኛ ሁኔታ እየጨመረ ባለበት በዚህ ወቅት 180 ኢትዮጵያውያን ስደተኞች በሀገሪቱ ደቡብ ምስራቅ በሚገኘው የሻብዋ የባህር ዳርቻ መድረሳቸውን የየመን የአገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ።
ሚኒስቴሩ ትናንት እሁድ ዕለት ባወጣው መግለጫ፣ የሽብዋ አካባቢ ፖሊስ 180 ስደተኞች በአራት ሶማሊያውያን በሚመራ የኮንትሮባንድ ጀልባ ከአፍሪካ ቀንድ የተነሱ ኢትዮጵያውያን ዜጎች መሆናቸውን ገልጿል ብሏል።
መግለጫው እንዳስታወቀው፣ የሻብዋ አካባቢ የፀጥታ ባለስልጣናት የስደተኞችን ፍልሰት ለመግታት እና ህገ-ወጥ ሰርጎ ገብነትን ለመከላከል አስፈላጊውን እርምጃ እየወሰዱ ነው።
በተመሳሳይ፣ ዓለምአቀፉ የስደተኞች ድርጅት ያወጣው የቅርብ ጊዜ መረጃ እንደሚያሳየው በህዳር ወር 17,659 ስደተኞች ወደ የመን ገብተዋል። በጥቅምት ወር ደግሞ የገቡት ስደተኞች ቁጥር 17,685 ነበር።
እንደ ዓለም አቀፉ የስደተኞች ድርጅት የተፈናቃዮች መከታተያ መረጃ ከሆነ፥ ጅቡቲ በ67 በመቶ ቀዳሚዋ የስደተኞች መነሻ አገር ሆና ቀጥላለች። በመቀጠል ሶማሊያ 31 በመቶ እንዲሁም ኦማን 2 በመቶ የሚሆነውን ድርሻ ይዘዋል።
ምንም እንኳን የመን የፀጥታ ሁኔታዋ እና በአገሪቱ ያለው የሰብአዊ ቀውስ እየተባባሰ ቢመጣም፣ ወደ ባሕረ ሰላጤው አገራት ለመሻገር ለሚሞክሩ በሺዎች ለሚቆጠሩ አፍሪካውያን ስደተኞች እንደ ዋና መሸጋገሪያ መስመር ሆና ማገልገሏን ቀጥላለች። ከእነዚህም መካከል አብዛኛዎቹ በኮንትሮባንድ አዘዋዋሪዎች እጅ ለከፋ መከራ እና ብዝበዛ እንደሚጋለጡ ዥንዋ ዘግቧል።

የ #ኢትዮጵያ አየር መንገድ በረራዎችን ያቋረጠበት የአየር ፀባይ ለዉጥ በ #ደሴ እና አካባቢው የደረሱ ሰብሎችን አወደመ
በ #አማራ ክልል ደቡብ ወሎ ዞን ደሴ ከተማና አካባቢዋ በድንገት በተቀየረ የአየር ሁኔታ ምክንያት የኢትዮጵያ አየር መንገድ በረራዎቹን ለማቋረጥ መገደዱን አስታወቋል።
አየር መንገዱ ለበረራ አመቺ ያልሆነ የአየር ፀባይ በመከሰቱ የታህሳስ 12 አና 13 ቀን በረራዎቹን መሰረዙን ትናንት ባወጣው መግለጫ ገልጿል።
አየር መንገዱ ከሚቲዎሮሎጂ በሚያገኘው መረጃ መሠረት ሁኔታውን እየተከታተለ የአየር ሁኔታው ሲስተካከል በረራዎቹ ወደ መደበኛ አገልግሎታቸው እንደሚመለሱ አመልክቶ በአገልግሎቱ መቋረጥ ለተፈጠረው መጉላላት ይቅርታ ጠይቋል።
በተመሳሳይ በደሴ ዙሪያ ወረዳ በተለይም በደረባ እና በአደይ ቀበሌዎች ታህሳስ 11 ቀን ከቀኑ 9 ሰዓት ጀምሮ በረዶ ቀላቅሎ በጣለው ከባድ ዝናብ በደረሱ ሰብሎች ላይ ከፍተኛ ውድመት ማድረሱን የወረዳው ግብርና ልማት ጽህፈት በት አስታዉቋል።
የወረዳው ግብርና ልማት ጽሕፈት ቤት ምክትል ሃላፊ አቶ ሁሴን የሱፍ በረዶው ለመሰብሰብ ደርሰው በነበሩ ሰብሎች ላይ በድንገት በመጣሉ ከፍተኛ ብክነት ማስከተሉን ጠቅሰዋል።
ምክትል ኃላፊው አክለውም ሰሞኑን የሚታየው ዝናብ በደረሱ ሰብሎች ላይ ጉዳት እያደረሰ በመሆኑ ፣ አርሶ አደሩ ከሰላም ስራዎች በተጨማሪ የደረሱ ሰብሎችን በተደራጀ ሁኔታ በመሰብሰብ የሚደርሰውን ተጨማሪ ውድመት እንዲከላከል ጥሪ አቅርበዋል።