Addis Standard Amharic – Telegram
Addis Standard Amharic
18K subscribers
4.67K photos
121 videos
3 files
3.72K links
አዲስ ስታንዳርድ በጃኬን አሳታሚ ኃ.የተ.የግ.ማ. ባለቤትነት ስር የሚታተም በኢትዮጵያ የሚገኝ ነፃ እና ገለልተኛ ሚዲያ ነው። አዲስ ስታንዳርድ አማርኛ የአዲስ ስታንዳርድ እንግሊዝኛ ሕትመት አካል ነው።
ፌስቡክ: https://rb.gy/xwxb3
ትዊተር (X)፡ https://rb.gy/34uh4
Download Telegram
ጠ/ሚ ዐቢይ አህመድ ከ #ኬንያው ፕሬዝደንት ዊልያም ሩቶ ጋር በሁለትዮሽ ጉዳዮች ላይ መከሩ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) ለአንድ ቀን የሥራ ጉብኝት #አዲስ_አበባ የገቡትን የኬንያ ፕሬዝደንት ዊልያም ሳሞይ ሩቶን ተቀብለው ማነጋገራቸውን አስታወቁ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ የፕሬዝደንቱን ጉብኝት አስመልክተው ባስተላለፉት መልዕክት፤ “ዛሬ የኬንያ ፕሬዝደንት ዊልያም ሳሞይ ሩቶን ለአንድ ቀን የሥራ ጉብኝት ተቀብያለሁ። ጉብኝቱ በሁለቱ ሀገሮቻችን መካከል ያለውን ጥልቅ፣ ታሪካዊ እና ወንድማዊ ግንኙነት የሚያንፀባርቅ ነው“ ብለዋል።

ጠ/ሚንስትሩ አክለውም ከዊሊያም ጋር ባደረጉት ውይይት የሁለቱን ሀገራት ግንኙነት ይበልጥ ማጠናከር በሚቻልባቸው ሁኔታዎች እንዲሁም በአፍሪካ ቀንድ ሰላምና ጸጥታ ዙሪያ ሃሳብ መለዋወጣቸውን ገልጸዋል።

“ይኽም በሰላም እና መረጋጋት፣ ንግግር ብሎም በአፍሪካ መር መፍትሔዎች ላይ ያለንን የወል ጽኑ አቋም የሚያሳይ ነበር” ሲሉ አክለው በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው አስፍረዋል።

የአዲስ ስታንዳርድ አማርኛ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
ፌስቡክ: https://rb.gy/xwxb3
ትዊተር (X)፡ https://rb.gy/34uh4
ቴሌግራም: https://rb.gy/rekjr
ዩቲዩብ፡ https://rb.gy/bjcbg
ድረገጽ: https://rb.gy/5td6n
ዜና: ተመድ የሱዳን ጦርነት ወደ ኢትዮጵያ ሊዛመት እንደሚችል በመግለፅ ሰፊ የቀጣናዊ ግጭት ስጋት መጋረጡን አስጠነቀቀ

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የጸጥታው ምክር ቤት፤ በሱዳን እየተባባሰና ከጊዜ ወደ ጊዜ ዓለም አቀፋዊ መልክ እየያዘ የመጣው ግጭት ወደ ጎረቤት አገራት በተለይም ወደ ኢትዮጵያ ሊዛመት እንደሚችል አስጠነቀቀ።

ይህም ሊሆን የሚችለው ውጊያው እየበረታ፣ የጦር መሣሪያዎች ስርጭት እየጨመረ እና ታጣቂ ቡድኖች ባልተጠበቁ ድንበሮች በኩል እየተንቀሳቀሱ በመሆናቸው ነው ብሏል።

ለጸጥታው ምክር ቤት ገለጻ ያደረጉት የፖለቲካና ሰላም ግንባታ ጉዳዮች ረዳት ዋና ጸሐፊ ኻሊድ ኺያሪ፤ ጦርነቱ በቅርቡ ወደ ሱዳን የኮርዶፋን ግዛት አቅጣጫ መዞሩን ገልጸዋል።

በዚሁ መሠረት የሱዳን ፈጥኖ ደራሽ ሀይል የባባኑሳን ከተማ በጎርጎሮሳውያኑ ታኅሣሥ 1 ቀን፣ የሄግሊግ የነዳጅ ማውጫን ደግሞ በታኅሣሥ 8 ቀን መቆጣጠሩን እና በደቡብ ኮርዶፋን የሚገኙ ዋና ዋና ከተሞች አሁንም በከበባ ውስጥ መሆናቸውን አስታውቀዋል።

አክለውም በሱዳን እና በደቡብ ሱዳን መካከል እየታየ እንዳለው ሁሉ ታጣቂ ቡድኖች ድንበር ተሻግረው የሚያደርጉት እንቅስቃሴ፣ ለቀጣናው መረጋጋትን ሊያሳጣ የሚችል ተጽዕኖ እንዳለው አስጠንቅቀዋል።

ተጨማሪ ይመልከቱ:
https://addisstandard.com/Amharic/?p=10202&amp=1
ዜና፡ የፈንታሌ ሚዲያ መስራች ጋዜጠኛ ፋኑኤል ክንፉ "ማንነታቸው ካልታወቁ ሰዎች" ለማምለጥ ሲሞክር ከፍተኛ ጉዳት እንደደረሰበት ገለፀ

የፈንታሌ ሚዲያ መስራች ጋዜጠኛ ፋኑኤል ክንፉ “ማንነታቸው ባልታወቁ ሰዎች” በአዲስ አበባ ከተማ “ሊፈፀምብኝ ነበር” ካለው ጥቃት ለማምለጥ ሲሞክር ከፍተኛ ጉዳት እንደደረሰበት ለአዲስ ስታንዳርድ ገለፀ።

ጋዜጠኛ ፋኑኤል በደረሰበት ጉዳት ሳቢያም ለመራመድ ከሶስት እስከ ስድስት ወር ሊፈጅበት እንደሚችል በህክምና ባለሞያተኞች እንደተገለጸለት ተናግሯል። ጋዜጠኛው ስለደረሰበት ጉዳት ለአዲስ ስታንዳርድ ሲያብራራ፣ ከወር በፊት ማለትም ህዳር 10/2018 ዓ.ም ስምንት ሰዓት አከባቢ “ሲቪል የለበሱ ሰዎች እንደሚፈልጉኝ” ከቤተሰብ ሰማሁ ሲል ይጀምራል።

በወቅቱ “የቅርብ ጓደኛው ጋር በመሄድ ጉዳዩን እንደነገረው እና ገስት ሀውስ ብታርፍ ይሻላል ብሎኝ ወደዚያው በማቅናትት እዛው ክፍል አግኝቼ ገባው” ሲል ጋዜጠኛው ገልጿል።

ሆኖም የቅርብ ጓደኛው ከሄደ ከ50 ደቂቃ በኋላ ያረፈበት ክፍል በሩ በጣም ይደበደብ እንደጀመረ ጠቅሶ፣ በወቅቱ “ክፈት የሚል እና ሀይለቃል የተሞላበት ቃል እሰማ ነበር” ብሏል።

“በሩን በጣም እየገፉት ሲመጡ ክፍሏ ከጎን የበረንዳ ኮሪደር ያላት በመሆኑ ኮሪደሩ ጋር ሆኜ ተዘጋጀሁ” ያለው ጋዜጠኛው፣ “በወቅቱ ደብድበው ሞቶ ተገኘ ልባል እችላለሁ የሚል ስጋት አደረብኝ በዚህም አራት ሜትር አከባቢ ከሚረዝም ሁለተኛ ፎቅ ላይ ዘለልኩ” ሲሉ ተናግሯል።

አክሎም “ዘልዬ ከወደኩኝ በኋላ ልነሳ ስል ራሴን ሳትኩ ጭልም አለብኝ” ሲሉ ገልጾ፣ “ቀና ስል አጥንቴ ተሰብሯል። በአከባቢዬ ሲቪል የለበሱ ሰዎች ነበሩ። "ይሄን እድል ደግመህ አታገኝም" ብለውኝ ሄዱ ከዛም ሰዎች ወደ ሆስፒታል ወሰዱኝ ብሏል።

“ከዛ በኋላ ለ20 ምናምን ቀናት ለማንም ጉዳዩን አልተናገርኩም ነበር” ያለው ጋዜጠኛ ፋኑኤል፣ ነገር ግን ጉዳዩ “ከሚዲያ ስራው ጋር የተገናኘ ነው” ብሎ እንደሚያምን ተናግሯል።

ተጨማሪ ያንብቡ፡ https://addisstandard.com/Amharic/?p=10205
#አዲስ_አበባ ከተማ በአጥር የተዘጉ የውስጥ ለውስጥ መንገዶችን በግብረ ኃይል የማስከፈት ስራ ተጀመረ

በአዲስ አበባ በከተማ ተለያዩ አካባቢዎች በአጥር የተዘጉ የውስጥ ለውስጥ መንገዶችን በግብረ ኃይል የማስከፈት ስራ በትናንትናው ዕለት መጀመሩን የከተማዋ መንገዶች ባለሥልጣን አስታወቀ።

ባለስልጣኑ ይህን እርምጃ መውሰድ የጀመረው፣ ከሳምንታት በፊት በከተማዋ የውስጥ ለውስጥ መንገዶችን አጥረው የዘጉ ግለሰቦች መንገዶቹን ከታኅሣሥ 4 ቀን 2018 ዓ.ም. ጀምሮ ባሉት ሰባት ተከታታይ ቀናት ውስጥ ክፍት እንዲያደርጉ የሰጠው ማስጠንቀቂያ ተግባራዊ ባለመሆኑ ነው።

ባለስልጣኑ ትናንት ባጋራው መረጃ፣ የደቡብ አዲስ አበባ መንገድ ኔትዎርክ ማኔጅመንት ቡድን መሪ ኢንጅነር ቢሊሱማ በዬቻ፤ የውስጥ ለውስጥ መንገዶች በግለሰቦች በአጥር መዝጋታቸው፤ የህብረተሰቡን በመንገድ መሰረተ ልማት የመጠቀም መብት የሚጋፋና ለትራፊክ ፍሰት መስተጓጎል መንስኤ እየሆነ እንደሚገኝ ገልፀዋል ብሏል፡፡

በመሆኑም በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ወረዳ 7 ቃሊቲ ገብርኤል ቤተክርስቲያን ጀርባ፤ የውስጥ ለውስጥ መንገዶችን በአጥር የዘጉ አካላት፣ አጥሩን እንዲያነሱ ማስጠንቀቂያ የተሰጠ ቢሆንም፤ በተሰጠው የጊዜ ገደብ ባለመነሳቱ ከወረዳው የፀጥታ አካላት ጋር በመቀናጀት በግብር ኃይል እንዲነሳ መደረጉን ገልጸዋል።

https://web.facebook.com/AddisstandardAmh/posts/pfbid0K763TCGodEANKMS2Ca5DFSMcWnBgU7U3uPXE2hQX8GfvsjPhUJKzGG8uwEp68VxDl
ዜና: ኢትዮጵያ እና አሜሪካ ከ1 ቢሊዮን ዶላር በላይ የጤና ትብብር ስምምነት ተፈራረሙ፤ የአገር ውስጥ የፋይናንስ አቅምን ለማሳደግም ቃል ገብተዋል

ኢትዮጵያ እና አሜሪካ ለኢትዮጵያ የጤና ዘርፍ በጋራ 1.466 ቢሊዮን ዶላር ለመመደብ የሚያስችል የአምስት ዓመት የጤና ትብብር የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረሙ።

በስምምነቱ መሠረት አሜሪካ እስከ 1.016 ቢሊዮን ዶላር የምትመድብ ሲሆን፤ ኢትዮጵያ ደግሞ ከአገር ውስጥ ሀብት 450 ሚሊዮን ዶላር እንደምትሸፍን የገንዘብ ሚኒስትሩ አቶ አህመድ ሽዴ በፊርማ ሥነ-ሥርዓቱ ላይ ገልጸዋል። የመግባቢያ ስምምነቱ ከጎርጎሮሳውያኑ 2026 እስከ 2030 ያለውን ጊዜ የሚሸፍን ይሆናል ተብሏል።

የአሜሪካ መንግሥት በተጨማሪም በሥራ አፈፃፀም ላይ የተመሠረተ 150 ሚሊዮን ዶላር የገንዘብ ድጋፍ እንደሚያደርግ የገንዘብ ሚኒስቴር አመልክቷል። ድጋፉ ሙሉ በሙሉ ተግባራዊ ከሆነ የአሜሪካ አጠቃላይ የገንዘብ ድጋፍ ወደ 1.166 ቢሊዮን ዶላር ከፍ ይላል የተባለ ሲሆን፤ ይህም ኢትዮጵያ ከምትሸፍነው ጋር ተደምሮ የአምስት ዓመቱን የጤና ትብብር ጥቅል ማዕቀፍ 1.616 ቢሊዮን ዶላር ያደርሰዋል።

በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር ኤርቪን ማሲንጋ ስምምነቱ “አሜሪካ ለኢትዮጵያ የጤና ዘርፍ ያላትን ቁርጠኝነት በድጋሚ የሚያረጋግጥ ነው” ያሉ ሲሆን፤ ኢትዮጵያ የአገር ውስጥ የጤና ኢንቨስትመንቷን ለማስፋፋት የወሰደችውን ውሳኔም አድንቀዋል።

የገንዘብ ሚኒስትሩ አቶ አህመድ ሽዴ በበኩላቸው የመግባቢያ ስምምነቱን በሁለቱ መንግሥታት መካከል ያለውን መተማመን የሚያሳይ ፖለቲካዊ እና ኢኮኖሚያዊ ምልክት መሆኑን ገልጸዋል።

ተጨማሪ ይመልከቱ:
https://addisstandard.com/Amharic/?p=10213&amp=1
ዜና፡ በ #ጋምቤላ ክልል ስደተኞችን ኢላማ ያደረገ የሀሰተኛ መረጃ ስርጭት ውጥረቱን ሊያባብስ እንደሚችል የስደተኞች ኮሚሽን አስጠነቀቀ

የተባበሩት መንግሥታት የስደተኞች ከፍተኛ ኮሚሽን (UNHCR) በጋምቤላ ክልል የሚገኙ ስደተኞችን ኢላማ በማድረግ በማኅበራዊ ሚዲያ ላይ እየተሰራጨ ያለው ሀሰተኛ መረጃ አሳሳቢ መሆኑን ገልጾ፣ ሁኔታው በአስቸኳይ እልባት ካልተሰጠው ውጥረቱን ሊያባብስ እንደሚችል አስጠነቀቀ።

ኤጀንሲዉ ትናንት ባወጣው መግለጫ፣ የአሳሳች ትርክት ስርጭት በስደተኞች እና በአስተናጋጅ ማኅበረሰቦች ላይ አደጋ እንደሚፈጥር በመጠቆም፣ ለሁኔታው ሰላማዊ መፍትሔ እንዲፈለግ ጥሪ አቅርቧል።

አክሎም እንዲህ ዓይነት ንግግሮች በንጹሐን ዜጎች ላይ አደጋ እንደሚፈጥሩና አብሮ የመኖር እሴትን እንደሚጎዱ የገለጸው መግለጫው፣ ሁሉም አካላት ከጥላቻ ንግግር እንዲታቀቡ አሳስቧል።

የስደተኞች ከፍተኛ ኮሚሽኑ በሁኔታው መባባስ የምግብ እና የውሃ አቅርቦትን ጨምሮ አንዳንድ ሰብአዊ አገልግሎቶችን ለጊዜው ለማቋረጥ መገደዱን ገልጿል። ስደተኞች ከሀገራቸው ጥቃት ሸሽተው ደህንነት ፍለጋ የመጡ በመሆናቸው፣ በጅምላ ተጠያቂነት ሊፈረጁ አይገባም ሲልም አሳስቧል። ኤጀንሲው የሲቪል እና ሰብአዊ ባህሪ ያለው ጥገኝነት “ለድርድር የማይቀርብ መርህ” መሆኑን አጽንኦት ሰጥቷል።

ዝርዝሩን ለማንበብ፡ https://addisstandard.com/Amharic/?p=10216
ዜና: ምርጫ ቦርድ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በዜጎች የመደራጀት እና የፖለቲካ ፓርቲ የመመሥረት መብት ላይ የሚፈፀሙ ጥሰቶች እንዲቆሙ አሳሰበ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በዜጎች የመደራጀት እና የፖለቲካ ፓርቲ የመመሥረት ዴሞክራሲያዊ መብት ላይ የሚፈፀሙ ጥሰቶች እንዲቆሙ አሳሰበ።

ቦርዱ ዛሬ ታህሳስ 15/2018 ዓ.ም ባወጣው መግለጫ “የኮንቶማ ሕዝቦች ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ” መሥራቾች ፓርቲ ለመመሥረት የሚያስፈልጉ ሁሉንም ሕጋዊ ሠነዶች አሟልተው የመሥራች ጠቅላላ ጉባዔያቸውን ጥቅምት 30 ቀን 2018 ዓ.ም. በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ቡታጅራ ከተማ እንደሚያደርጉ ለቦርዱ ማሳወቃቸውን ገልጿል፡፡

ይህን ተከትሎ ቦርዱ ለክልሉ መንግሥት አስተዳደር፣ ለክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን፣ ለምሥራቅ ጉራጌ ዞን አስተዳደር፣ ለቡታጅራ ከተማ አስተዳደር፣ ለማረቆ ልዩ ወረዳ ኮማንድ ፖስት እና ለቡታጅራ ከተማ ሰላምና ፀጥታ ጽ/ቤት ለመሥራቾቹ የፀጥታ ድጋፍ ትብብር እንዲደረግላቸው በደብዳቤ ማሳወቁን ገልፆ የቦርዱ ባለሙያዎችም በሕጉ መሠረት በቦታው በመገኘት ታዝበው ሪፖርት እንዲያቀርቡ ተመድበው እንደነበር አስታውሷል።

ሆኖም የክልሉ የፀጥታ አካላት፤ ጉባዔ መደረግ የማይችልበትን ሁኔታ በጽሑፍ ለቦርዱ ሳያሳውቁ መሣሪያ የታጠቁ የቡታጅራ ከተማ የፀጥታ አካላት በጉባዔው ዕለት “ከተማው በኮማንድ ፖስት ሥር ስለሆነች መሰብሰብ አይቻልም” በሚል ለስብሰባ የመጡ የፓርቲው መሥራች አባላቶችን ከአዳራሽ በማስወጣት በቁጥጥር ሥር እንዳዋሏቸው ቦርዱ በታዛቢነት ከላካቸው ባለሞያዎቹ ሪፖርት መረዳት እንደቻለ መግለጫው አመልክቷል፡፡

ተጨማሪ ይመልከቱ:
https://addisstandard.com/Amharic/?p=10219
#ኢትዮጵያ_ንግድ_ባንክና#ኢትዮጵያ_አየር_መንገድ የ27.8 ቢሊዮን ብር ብድር ተፈራረሙ

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ለኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ሠራተኞች መኖሪያ ቤት ግንባታ የሚውል የ27.8 ቢሊዮን ብር ብድር ለማቅረብ የሚያስችል "ታሪካዊ" የተባለ ስምምነት ተፈራረመ።

ስምምነቱን የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፕሬዚዳንት ተወካይና የኮርፖሬት አገልግሎቶች ኤክስኪውቲቭ ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ ኤፍሬም መኩሪያ እና የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ መስፍን ጣሰው ትላንት ታኅሣሥ 14 ቀን 2018 ዓ.ም በባንኩ ዋና መሥሪያ ቤት ተፈራርመዋል።

አቶ ኤፍሬም መኩሪያ ባንኩ የኅብረተሰቡን ፍላጎት መሠረት በማድረግ የብድር አገልግሎቱን እያሳደገ እንደሚገኝ ገልጸው፣ በሁለቱ ግዙፍ የሀገሪቱ የኢኮኖሚ አንቀሳቃሽ ተቋማት መካከል የተደረገው ይህ ስምምነት በዓይነቱ ልዩና ታሪካዊ መሆኑን ተናግረዋል።

አክለዉም ለዚህ ስኬት የባንኩ ፕሬዚዳንት አቶ አቤ ሳኖ ያደረጉት ጥረት ከፍተኛ ሚና መጫወቱን ገልጸዋል።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ መስፍን ጣሰው በበኩላቸው፣ ስምምነቱ የአየር መንገዱን ሠራተኞች የቤት ችግር ለመፍታት ትልቅ ዕርምጃ መሆኑን ገልጸዋል።

አክለዉም ብድሩ ለአምስት ሺህ የአየር መንገድ ሠራተኞች የመኖሪያ ቤት ግንባታ ወጪን ለመሸፈን የሚዉል መሆኑን አመልክተዋል።

አቶ መስፍን ፣ አየር መንገዱ የሠራተኞቹን ችግር ለመቅረፍ ባንኩን በአጋርነት መምረጡንና ለተደረገው ትብብር በማኔጅመንቱና በሠራተኛ ማኅበሩ ስም ምስጋና አቅርበዋል።
የአደጋ ስጋት አመራር ኮሚሽን ለ #ሕፃፅ ተፈናቃዮች የሰብአዊ ድጋፍ አንዳልደረሳቸው የሚገልፁ መረጃዎችን “የተሳሳቱ” ናቸው ሲል አስተባበለ

#ኢትዮጵያ አደጋ ስጋት አመራር ኮሚሽን በ #ትግራይ ክልል ሰሜን ምዕራብ ዞን አስገደ ወረዳ በሚገኘው ሕፃፅ ጊዜያዊ መጠለያ ጣቢያ ለሚገኙ ተፈናቃዮች የሰብአዊ ድጋፍ አንዳልደረሳቸው የሚገልፁ መረጃዎችን “የተሳሳቱ ናቸው" ሲል አጣጥሏል።

ኮሚሽኑ በትግራይ ክልል የተፈናቃዮች የሰብአዊ ድጋፍን አስመልክቶ በሰጠው መግለጫ፤ በተለያዩ ማኅበራዊ ሚዲያዎች በሕፃፅ የሚገኙ ዜጎች ድጋፍ እንዳልደረሳቸው የሚገልጹ ዘገባዎች “የተሳሳቱ” እና “የመጠለያ ጣቢያውን አጠቃላይ እውነታ የማይወክሉ” ናቸው ብሏል።

መንግሥት በመጠለያ ጣቢያ ለሚገኙ ዜጎች የቅድሚያ ቅድሚያ ትኩረት በመስጠት ዓመቱን ሙሉ የምግብ ድጋፍ ሲያቀርብ መቆየቱን የገለጸው ኮሚሽኑ፣ ከመስከረም ወር 2018 ዓ.ም ጀምሮ እስከ አሁኑ የታኅሣሥ ወር ድረስ “ያልተቆራረጠ እና የተሟላ” ሰብአዊ እርዳታ እየተሰራጨ እንደሚገኝ በመረጃዎቹ ማረጋገጡን አስፍሯል።

በመግለጫው ዝርዝር መረጃ መሠረት፣ ባለፉት አራት ወራት ውስጥ በአስገደ ወረዳ ሕፃፅ ጊዜያዊ መጠለያ ጣቢያ ለሚገኙ 14 ሺህ 413 ዜጎች ድጋፍ ሲደረግ ቆይቷል። በተጨማሪም ከአጎራባች መጠለያ ጣቢያ የሚገኙ ዜጎችን ጨምሮ "በመስከረም ወር 16 ሺህ 775፤ በጥቅምት ወር 18 ሺህ 290፤ በኅዳር ወር 17 ሺህ 813 እንዲሁም በታኅሣሥ ወር የሚያስፈልገው ለ14 ሺህ 413 ዜጎች የሚያስፈልግ ምግብ ተሰራጭቷል" ሲል ኮሚሽኑ በዝርዝር አስቀምጧል።

በዚህም
https://web.facebook.com/AddisstandardAmh/posts/pfbid0SiJBRD3Q5R3C7KbsxJTWYZSjqjsHoD27BEmYPUR5TK6ua8NxyPDYDrmqNY2Esyhel
ዜና፡ ጠ/ሚ ዐቢይ ከዊሊያም ሩቶ ጋር ያደረጉት ውይይት ሳፋሪኮም እና ኢትዮ ቴሌኮም በአፍሪካ ቀንድ በጋራ ለመስራት እንዲችሉ ድጋፍ መስጠቱ ተገለፀ

በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) እና በኬንያው ፕሬዝዳንት ዊሊያም ሩቶ መካከል በአዲስ አበባ የተካሄደው ውይይት፤ ሳፋሪኮም እና ኢትዮ ቴሌኮም በጋራ እንዲሰሩ የፖለቲካ ድጋፍ አስገኝቷል ተባለ። ይህም በአፍሪካ ቀንድ ያለውን የዲጂታል እና የመሠረተ ልማት ትብብር ለማሳደግ አዲስ እርምጃ መሆኑ ተገልጿል።

ከውይይቱ በኋላ የወጡ መግለጫዎች፤ መሪዎቹ በሁለቱ የቴሌኮም ኩባንያዎች መካከል ስልታዊ አጋርነት እና ኢንቨስትመንት እንዲኖር ለመደገፍ መስማማታቸውን አመልክተዋል። ስምምነቱ የኢኮኖሚ ትስስርን ለማጠናከር እና ቀጣናዊ ግንኙነትን ለማስፋፋት እየተደረገ ያለው ሰፊ ጥረት አካል መሆኑም ተጠቁሟል።

መሪዎቹ የዲጂታል መሠረተ ልማት ለንግድ እና ለፈጠራ እድገት ቁልፍ መሆኑን ገልጸው፤ ለአፍሪካ የልማት፣ የሰላም እና የመረጋጋት ጉዞ በጋራ ለመስራት ያላቸውን ቁርጠኝነት በድጋሜ አረጋግጠዋል።

ፕሬዝዳንት ሩቶ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መግለጫ፤ ውይይቱ የኢኮኖሚ ትስስርን ማጠናከር እና ለሁለቱም አገራት ዜጎች ተጨባጭ ጥቅም በሚያስገኙ ተግባራት ላይ ያተኮረ መሆኑን ገልጸዋል።

አክለውም “የኢኮኖሚ ትብብርን ለማሳደግ፣ ቀጣናዊ መረጋጋትን ለማስፈን እና ሕዝቦቻችንን ተጠቃሚ የሚያደርጉ ተግባራትን ለመደገፍ በጋራ እንሰራለን” ብለዋል።

ተጨማሪ ያንብቡ:
https://addisstandard.com/Amharic/?p=10221&amp=1