Advanced Freshman – Telegram
Advanced Freshman
27.4K subscribers
651 photos
9 videos
59 files
207 links
🔔ይህ ቻናል freshman ለሚማሩ ተማሪዎች የተዘጋጀ እና በዉስጡ የተለያዩ የዩንቨርስቲ መረጃዎችን, አጋዥ መፅሐፍቶች, ቲቶሪያል, mid እና final ፈተናዎችን ሚያዘጋጅ እና ተማሪዎች ወደ ሚፈልጉበት ዲፓርትመንት እንዲገቡ ሚያግዝ ነው ::

📩Owner:- @Bekijum
Download Telegram
#NationalExam

" የኦንላይን ፈተናው አልቀረም። የሚሰራጨው ሀሰተኛ መረጃ ነው " - ትምህርት ሚኒስቴር

ትምህርት ሚኒስቴር የ2016 ዓ.ም የ 12ተኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ብሔራዊ ፈተና በበይነ መረብና በወረቀት እንደሚሰጥ መግለጹ ይታወቃል።

ሆኖም በተለያዩ ማህበራዊ ሚዲያ ገጾች የበይነ መረብ ፈተናው እንደቀረ ተደርጎ መረጃ እየተሰራጨ መሆኑን ገልጿል።

ሚኒስቴሩ ይህ በፍጹም ከእውነት የራቀ ሃሰተኛ መሆኑን አሳውቋል።

ፈተናው በሁለቱም በወረቀት እንዲሁም በኦንላይን እንደሚሰጥ አረጋግጧል።

ተማሪዎች ይሄን ተገንዝበው ዝግጅታቸውን እንዲቀጥሉ አሳስቧል።

ትምህርት ሚኒስቴር " ፈተናውን የተሳካ ለማድረግ ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር በጥምረት እየሰራን ነው ለዚህም ከፍተኛ ዝግጅት ተደርጓል " ብሏል።

ምንጭ:- TIKVAH

JOIN :@ADVANCED_FRESHMAN⭐️
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
👍30😱9😢6🫡4🔥3🆒3🙈2
Advanced Freshman
#NationalExam " የኦንላይን ፈተናው አልቀረም። የሚሰራጨው ሀሰተኛ መረጃ ነው " - ትምህርት ሚኒስቴር ትምህርት ሚኒስቴር የ2016 ዓ.ም የ 12ተኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ብሔራዊ ፈተና በበይነ መረብና በወረቀት እንደሚሰጥ መግለጹ ይታወቃል። ሆኖም በተለያዩ ማህበራዊ ሚዲያ ገጾች የበይነ መረብ ፈተናው እንደቀረ ተደርጎ መረጃ እየተሰራጨ መሆኑን ገልጿል። ሚኒስቴሩ ይህ በፍጹም ከእውነት የራቀ ሃሰተኛ…
የ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና በኦንላይን እና በወረቀት እንደሚሰጥ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት አረጋገጠ።

በተለያዩ የማኅበራዊ ትስስር ገፆች ፈተናው በኦንላይን እንደማይሰጥ የሚገልፁ መረጃዎች "ሐሰተኛ" ናቸው ያለው አገልግሎቱ፤ ፈተናው በወረቀት እና በኦንላይን የሚሰጥ በመሆኑ ተማሪዎች ይሄንን ተገንዝበው ዝግጅት ያድርጉ ብሏል።


JOIN:
@ADVANCED_FRESHMAN ⭐️
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
🥰9👍8🫡7🆒5🙏3🙉2
Natural ወይስ social ተማሪ ናችሁ?
Anonymous Poll
68%
Natural
32%
Social
🔥55🫡21👍17😎14🙏9🆒8👌5🥰3🤝3
💻ለ12ኛ ክፍል ተፈታኞች💡

የ12ኛ ክፍል ተፈታኝ ተማሪዎች እንኳን በጉጉት ስትጠብቁት ለነበረው ዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተና ሳምንት በሰላም አደረሳችሁ🥹። ይህ ለእናንተ ወሳኝ ጊዜ ነው። እስካሁን ትምህርታችሁን እያጠናችሁ ቆይታችኋል። መልካም ነው። ነገር ግን በፈተና ወቅት የምታከናውኗቸው ተግባራትም የጥናታችሁን ያህል ውጤታችሁ ላይ ተጽዕኖ አላቸው❗️። ስለዚህ በዚህ ወቅት ምን ማድረግ እንዳለባችሁና ምን ማድረግ እንደሌለባችሁ ጠንቅቃችሁ ማወቅ ይጠበቅባችኋል🤔

🤗ለዚህም ይረዳችሁ ዘንድ የሚከተሉትን ምክሮችን ከወዲሁ ተረድታችሁ ለመተግበር ዝግጁ ሁኑ!

በዋዜማው ስልክ መዝጋትና ከሚረብሹ ነገሮች ራስን ማራቅ ያስፈልጋል። ስልካችሁን መዝጋት ሀሳባችሁን ሊሰርቁ ከሚችሉ ማህበራዊ ሚዲያዎች መራቅ ይገባችኋል። በዚህ ወቅት ትኩረታችሁን ፈተናችሁ ላይ ብቻ አድርጉ፤

በቂ እንቅልፍ ተኙ። በፈተና ዋዜማ ለማንበብ ብላችሁ በፍጹም አታምሹ። ባጭሩ በዚህ ቀን ተጨማሪ ሰዓት ከማንበብ ይልቅ ተጨማሪ ሰዓት መተኛት የተሻለ ዉጤት አለው። በቂ እንቅልፍ አለመተኛት በፈተና ወቅት ለድብርትና ለራስ ምታት ሊዳርግና ሥራችሁን ሊያበላሽ ይችላል። ጥሩ እንቅልፍ ለመተኛት ከባድ ምግቦችን አለመመገብ፤ ብዙ ቡና አለመጠጣት፤ እና ሌሎች አነቃቂ ነገሮችን አለመውሰድ ይመከራል፤

ጠዋት ማልዶ መነሳት: በጊዜ ተነስቶ መዘጋጀት ከመቻኮል ጋር ተያይዞ ከሚመጣ መታወክ ያድናል። በተጨማርም ወደፈተናው አዳራሽ በጊዜ ለመድረስ ያስችላል፤

ቁርስ በአግባቡ መብላት: በፈተና ወቅት ቁርስ አለመብላት አእምሮአችን የሚፈልገውን ያህል ኃይል እንዳያገኝ ስለሚያደርግ ለማሰብ አቅም እንዲያንስ ያደርጋል። ስለዚህ ቀለል ያሉ ምግቦችን ተመግባችሁ መሄድ ይኖርባችኋል። ከባድ ምግቦችን መመገብ ደግሞ አእምሮአችን ምግብ የመፍጨት ሥራ ላይ ብቻ እንዲወጠር ስለሚያደርግ ድካምና እንቅልፍ ያመጣል፤

ወደ መፈተኛ ቦታው ፈተናው ከሚጀምርበት ሰዓት በፊት ቀድሞ መድረስ ያስፈልጋል። ይህም ለመረጋጋት ከፍተኛ አስተዋጽዖ አለው፤

ከቤት ስትወጡ የፅህፈት መሳሪያዎቻችሁንና የመታወቅያ ካርዳችሁን መያዛችሁን እርግጠኛ ሁኑ። ይህም ከመንገድ ከመመለስና ከማርፈድ ያድናችኋል። ትርፍ እርሳሶችን እና የእርሳስ መቅረጫዎች መያዝ በጣም አስፈላጊ ነው፤

ወደ ፈተና አዳራሽ ከመግባት በፊት ወደ መፀዳጃ ቤት መሄድ መልካም ነው። ምናልባት የፈተናው ሰዓት ረዥም ቢሆንና ሽንት ቢይዛችሁ መጨናነቅን ያመጣል። አቋርጣችሁ መውጣት ላይፈቀድላችሁ ይችላል፤

የመልስ መስጫ ወረቀቱ ላይ ስማችሁን በአግባቡ መጻፋችሁን እርግጠኛ ሁኑ። አንድ ፊደል እንኳን ብትሳሳቱ ኋላ የት/ት ማስረጃችሁ ላይ ስለሚቀመጥ ለማስቀየር ዋጋ ያስከፍላል፤

መመሪያዎችን (instructions) በአግባቡ ማንበብና መተግበር ያስፈልጋል። በእያንዳዱ ፈተና ወረቀት ላይ ወይም የፈተናው ክፍሎች ላይ የሚሰጡትን መመሪያዎች በአግባቡ ማንበብና መተግበር ይኖርባችኋል፤

አትደንግጡ! በደንብ ተንፍሱ! ብዙ ኦክስጂን ወደ ውስጣችን ማስገባት ብዙ ምግብ እንዲቀጣጠልና ኃይል እንዲመረት ስለሚያደርግ ጉልበትና ድፍረት ይጨምርላችኋል፤

መልስ መመለስ ከመጀመራችሁ በፊት እያንዳንዱ የፈተና ክፍል ስለያዛቸው የጥያቄ አይነቶች ገረፍ ገረፍ እያደረጋችሁ ብታዩ መልካም ነው። ይህም የተሰጣችሁን ሰዓት በጥያቄው ክብደት ልክ ከፋፍላችሁ ለመጠቀም ያግዛችኋል፤

  አንዱ ጥያቄ ከከበዳችሁ ዝለሉት፤ አንድ ጥያቄ ላይ ተጠምዳችሁ ብዙ ጊዜ የምታጠፉ ከሆነ ቀጥለው ለሚጠብቋችሁ ጥያቄዎች ጊዜ ሊያጥራችሁ ይችላል። ስትዘሉት ግን የጥያቄ ወረቀቱ ላይ ምልክት ማድረጋችሁን  አትርሱ ፤

ቶሎ ለመውጣት አትቸኩሉ፤ ምንም አይጠቅማችሁም፤ ሰዓታችሁን አሟጥጣችሁ መጠቀማችሁን፤ ሁሉንም ጥያቄዎች በአግባቡ መመለሳችሁንና ማጥቆራችሁን አረጋግጡ። ጊዜ ቢተርፋችሁ ጥያቄዎቹን ለመከለስ ተጠቀሙበት፤

ያልገባችሁ ማንኛውንም ነገር ሲኖር ፈታኞችን ለመጠየቅ አትፍሩ ፤

ልክ የፈተና ወረቀቱን ከመለሳችሁበት ጊዜ ጀምሮ የዚያ ትምህርት (subject) ነገር ማክተሙን በመገንዘብ ለቀጣዩ ፈተና እራስን ማዘጋጀት ይገባል። እንጂ፤ ስላለፈው ፈተና እያሰላልሰሉ መጨነቅ ለቀጣዩ ፈተና በምታደርጉት ዝግጅት ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ ያሳድራል።

⭐️ሌላው እና ዋናው መረሳት የሌለበት ነገር ሁላችሁም በየ እምነታችሁ ፀሎት አድርጉ 🥺❤️

መልካም ፈተና እንዲሆንላችሁ ተመኘን
🚩☺️

JOIN:
@ADVANCED_FRESHMAN 📨
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
🙏223👍56🥰36🏆14❤‍🔥8🙈6👏4😘4👌3😍3🫡3
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
💻ሰኞ ትገባላችሁ እያለ ነው ብሬ 🥸😁

JOIN:
@ADVANCED_FRESHMAN ⭐️
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
😁90👍12🫡6🔥4🤝4😱3🙏3🙈2🙉1
ሁሉም ይሰጥሀል!

ወዳጄ ልፋትህ መና የሚቀር ከመሰለህ ተሸውደሀል፤ ፀሎትህ ደመና ላይ የሚንሳፈፍ ከመሰለህ የፈጣሪ አሰራር አልገባህም ማለት ነው።

ከጠየክ የማይሰጥህ ነገር የለም፤ ወዳጄ ተስፋ ቆርጠህ ልታቆም ስትል ይሄንን ሀሳብ አስታውስ "አንተ ስትጨርስ ፈጣሪ ይጀምራል!"

መልካም ዕድል
❤️

JOIN:
@ADVANCED_FRESHMAN ⭐️
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
🙏183🥰34❤‍🔥28👍20🫡6😘6
🛒ማሳሰቢያ

የዩንቨርሲቲ መግቢያ ፈተና ተፈታኝ ተማሪዎች ለፈተና ወደ ዩንቨርሲቲ ስትሄዱ፦

🚫 ይዞ መሄድ የማይቻሉ

- የሀኪም ማዘዣ የሌለው መድሃኒት በሽሮፕም ሆነ በታብሌት፣
- የህክምና መስጫ መርፌ፣
- የአንገት ሀብል፣
- የፀጉርና የጆሮ ጌጥ፣
- ከጋብቻ ቀለበት ውጭ ፈርጥ ያለው የጣት ቀለበት እና የእጅ አንባር አድርገው መምጣት እንደማይችሉ ፖሊስ ጥብቅ ማሳሰቢያ ሰጥቷል።

🚫 በተጨማሪም ፦
- ተንቀሳቃሽ  ስልክ፣ 
- አይ-ፓድ፣
- ታብሌት፣
- ላፕቶፕ፣
- ስማርት ሰዓት፣
- ሲዲ፣
- ሚሞሪ ሪደርና ኦ-ቲጂ ኮንቨርተር እንዲሁም ፎቶ የሚያነሱ እና ድምፅ የሚቀርፁ የቴክኖሎጂ ውጤቶችን ይዞ መገኘት በጥብቅ
#የተከለከለ መሆኑን ተገልጿል።

🔵የተከለከሉ መሣሪያዎችን በዩኒቨርሲቲዎቹ ግቢ ውስጥም ሆነ በዙሪያው ይዞ መገኘት፣ ፈተና ከተጀመረ ከ30 ደቂቃ በኋላ ወደ ፈተና ክፍል መግባት እና ፈተናው ተጀምሮ 45 ደቂቃ ሳይሞላ ከፈተና ክፍል መውጣት እንዲሁም በዩኒቨርሲቲ ግቢ ወስጥ በግልም ሆነ በቡድን ከፍተኛ ድምጽ ማሰማት የተከለከለ ነው።


JOIN: @ADVANCED_FRESHMAN⭐️
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
👍22🫡8🤝5❤‍🔥4🙏21
#ATTENTION🚨

" የበይነ መረብ (ኦንላይን) ተፈታኞች በተመደባችሁበት የፈተና ጣቢያ ተገኝታችሁ ፈተናውን እንድትወስዱ እናሳስባለን " - ትምህርት ሚኒስቴር

ትምህርት ሚኒስቴር የ12ኛ ክፍል ፈተና በበይነ መረብ (ኦንላይ) እንዲሁም በወረቀት እንደሚሰጥ በዛሬው ዕለት በድጋሚ አሳወቀ።

በሁለቱም መንገድ ለሚሰጠው ፈተና ዝግጅት ተደርጓል ብሏል።

ትላንት እና ከትላንት በስቲያ በአዲስ አበባ ያሉ አንዳንድ ትምህርት ቤቶች ለተማሪዎች " የበየነ መረብ (ኦንላይን) ፈተና ቀርቷል " እያሉ ለተማሪዎች መናገራቸውን እና የጽሁፍ መልዕክት በቴሌግራም ላይ መለጠፋቸውን የተማሪ ወላጆች እንዲሁም ተማሪዎች ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጸዋል።

እንዲህ ያለው ውሳኔ የሚተላለፈው ከማዕከል ከትምህርት ሚኒስቴር ሆኖ ሳለ ፥ ትምህርት ቤቶቹ ውሳኔውን ማን እንዳሳለፈ በይፋ ያሉት ነገር ሳይኖር በደፈናው " ቀርቷል " የሚል ነገር ብቻ ነው የነገሯቸው።

በኋላም እራሳቸው ት/ቤቶቹ ቀድሞ ያሰራጩትን ያልተረጋገጠ መረጃ በማጥፋት የኦላንይን ፈተናው እንዳልቀረ መልሰው ገልጸዋል።

ዛሬ እሁድ ትምህርት ሚኒስቴር የበየነ መረብ (ኦንላይን) ፈተናው በፍጹም እንዳልቀረ በድጋሜ አረጋግጧል።

ብሔራዊ ፈተናውን በበይነ መረብ (ኦንላይን) እና በወረቀት ለመፈተን ዝግጅቱን አጠናቅቆ የተማሪዎችን የመፈተኛ ቀን እየተጠባበቀ እንደሚገኝም አሳውቋል።

" ፈተናውን አስመልክቶ የተሳሳቱ መልዕክቶች በየጊዜው ትክክለኛ የትምህርት ሚኒስቴር ባልሆኑ ገጾች እየተለቀቁ ይገኛሉ " ሲልም ገልጿል።

ለተማሪዎች፣ ወላጆችና አሳዳጊዎች ባስተላለፈው መልዕክት ፈተናው ከዚህ ቀደም እንደተገለጸው በበይነ መረብ (ኦንላይን) እና በወረቀት እንደተማሪዎች የቀደመ ምርጫ መሰረት ይሰጣል ብሏል።

አስቀድመው በወረቀት የመረጡ ወደተመደቡበት ዩኒቨርስቲ፣ በበይነ መረብ (ኦንላይን) የመረጡም በተመደቡበት የፈተና ጣቢያ ተገኝተው ፈተናውን እንዲወስዱ በጥብቅ አሳስቧል።

የትምህርት ሚኒስቴር ፤ ተማሪዎች ከላይ በምስሉ እንደተያያዘው አይነት ከሃሰተኛ ወሬ ራሳቸውን በመከላከል ለፈተናው የሚያደርጉትን ዝግጅት እንዲቀጥሉ አሳስቧል።

ለማንኛውም መረጃ ከትምህርት ሚኒስቴር ብቻ እንዲከታተሉም አደራ ብሏል።

#TikvahEthiopia
#NationalExam
#MoE

JOIN: @ADVANCED_FRESHMAN⭐️
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
👍22🤝4🥰3🙏3👏2
የ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ መልቀቂያ ፈተና ተፈታኞች ወደ ዩኒቨርሲቲዎች መግባት ጀምረዋል።

ከትግራይ ክልል ውጪ በሁሉም ክልሎች እና በሁለቱ የከተማ አስተዳደሮች የ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ፈተና ከሐምሌ 3-11/2016 ዓ.ም እንደሚሰጥ ይታወቃል።

ምስል፦ ዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ

JOIN:
@ADVANCED_FRESHMAN ⭐️
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
🙈19👍10😱4🔥3🫡3
በመረጃ በኩል ክፍተት እንዳለ እያየን ነው :: ትምህርት ሚኒስቴር ሚለው ሌላ ት/ቤቶች ሚሉት ሌላ🙁 መናበብ የለም....በተቻለን አቅም ትክክለኛ የሆኑ መረጃዎችን ከታማኝ መረጃ ምንጮች እናደርሳቿለን::

🙌 ለማንኛውም እኛ የምንላችሁ ነገር ቢኖር እራሳችሁን  አረጋጉ Confused አትሁኑ! ምንም ሆነ ምን መፈተናችሁ አይቀርም! So እናንተ ፈተናው ላይ ብቻ Focus አድርጉ! በርቱልን ! እንወዳችኋለን
❤️

መልካም ዕድል🫶

JOIN:
@ADVANCED_FRESHMAN⭐️
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
🥰51👍24🙏12❤‍🔥5👌5
ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የ12ኛ ክፍል የመጀመሪያ ዙር የማኅበራዊ ሳይንስ ተፈታኝ ተማሪዎችን መቀበል ጀምረዋል።

ምስል፦ ወራቤ፣ ወሎ፣ ደምቢ ዶሎ እና መቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲዎች

JOIN:
@ADVANCED_FRESHMAN⭐️
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
🙈15👍12👏4🤩3❤‍🔥2🔥2🫡1
GOV CBT.xlsx
18.2 KB
👨‍💼የመንግስት ት/ቤቶች የ12ኛ ክፍል ፈተና የዩንቨርስቲ ምደባ

JOIN:
@ADVANCED_FRESHMAN⭐️
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
👍12❤‍🔥5👏5🙏4
PRIVATE CBT.xlsx
28.1 KB
👨‍💼የPrivate ት/ቤቶች የ12ኛ ክፍል ፈተና የዩንቨርስቲ ምደባ

JOIN:
@ADVANCED_FRESHMAN⭐️
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
👍11👏3🙏3❤‍🔥2
🖊 የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና የሚወስዱ ተማሪዎች ከቅዳሜ ሰኔ 29/2016 ዓ.ም ጀምሮ ወደሚፈተኑበት ተቋማት ገብተዋል።

💻ዛሬ በርካታ ዩኒቨርሲቲዎች ለተፈታኞች ገለፃ ሲሰጡ የዋሉ ሲሆን ሌሎች ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ነገ ኦረንቴሽን እንደሚሰጡ ይጠበቃል።

JOIN:
@ADVANCED_FRESHMAN⭐️
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
👍27🙈7👏4🔥3🙏3👌21🎉1