Advanced Freshman – Telegram
Advanced Freshman
27.4K subscribers
650 photos
9 videos
59 files
206 links
🔔ይህ ቻናል freshman ለሚማሩ ተማሪዎች የተዘጋጀ እና በዉስጡ የተለያዩ የዩንቨርስቲ መረጃዎችን, አጋዥ መፅሐፍቶች, ቲቶሪያል, mid እና final ፈተናዎችን ሚያዘጋጅ እና ተማሪዎች ወደ ሚፈልጉበት ዲፓርትመንት እንዲገቡ ሚያግዝ ነው ::

📩Owner:- @Bekijum
Download Telegram
#ATTENTION🚨

" የበይነ መረብ (ኦንላይን) ተፈታኞች በተመደባችሁበት የፈተና ጣቢያ ተገኝታችሁ ፈተናውን እንድትወስዱ እናሳስባለን " - ትምህርት ሚኒስቴር

ትምህርት ሚኒስቴር የ12ኛ ክፍል ፈተና በበይነ መረብ (ኦንላይ) እንዲሁም በወረቀት እንደሚሰጥ በዛሬው ዕለት በድጋሚ አሳወቀ።

በሁለቱም መንገድ ለሚሰጠው ፈተና ዝግጅት ተደርጓል ብሏል።

ትላንት እና ከትላንት በስቲያ በአዲስ አበባ ያሉ አንዳንድ ትምህርት ቤቶች ለተማሪዎች " የበየነ መረብ (ኦንላይን) ፈተና ቀርቷል " እያሉ ለተማሪዎች መናገራቸውን እና የጽሁፍ መልዕክት በቴሌግራም ላይ መለጠፋቸውን የተማሪ ወላጆች እንዲሁም ተማሪዎች ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጸዋል።

እንዲህ ያለው ውሳኔ የሚተላለፈው ከማዕከል ከትምህርት ሚኒስቴር ሆኖ ሳለ ፥ ትምህርት ቤቶቹ ውሳኔውን ማን እንዳሳለፈ በይፋ ያሉት ነገር ሳይኖር በደፈናው " ቀርቷል " የሚል ነገር ብቻ ነው የነገሯቸው።

በኋላም እራሳቸው ት/ቤቶቹ ቀድሞ ያሰራጩትን ያልተረጋገጠ መረጃ በማጥፋት የኦላንይን ፈተናው እንዳልቀረ መልሰው ገልጸዋል።

ዛሬ እሁድ ትምህርት ሚኒስቴር የበየነ መረብ (ኦንላይን) ፈተናው በፍጹም እንዳልቀረ በድጋሜ አረጋግጧል።

ብሔራዊ ፈተናውን በበይነ መረብ (ኦንላይን) እና በወረቀት ለመፈተን ዝግጅቱን አጠናቅቆ የተማሪዎችን የመፈተኛ ቀን እየተጠባበቀ እንደሚገኝም አሳውቋል።

" ፈተናውን አስመልክቶ የተሳሳቱ መልዕክቶች በየጊዜው ትክክለኛ የትምህርት ሚኒስቴር ባልሆኑ ገጾች እየተለቀቁ ይገኛሉ " ሲልም ገልጿል።

ለተማሪዎች፣ ወላጆችና አሳዳጊዎች ባስተላለፈው መልዕክት ፈተናው ከዚህ ቀደም እንደተገለጸው በበይነ መረብ (ኦንላይን) እና በወረቀት እንደተማሪዎች የቀደመ ምርጫ መሰረት ይሰጣል ብሏል።

አስቀድመው በወረቀት የመረጡ ወደተመደቡበት ዩኒቨርስቲ፣ በበይነ መረብ (ኦንላይን) የመረጡም በተመደቡበት የፈተና ጣቢያ ተገኝተው ፈተናውን እንዲወስዱ በጥብቅ አሳስቧል።

የትምህርት ሚኒስቴር ፤ ተማሪዎች ከላይ በምስሉ እንደተያያዘው አይነት ከሃሰተኛ ወሬ ራሳቸውን በመከላከል ለፈተናው የሚያደርጉትን ዝግጅት እንዲቀጥሉ አሳስቧል።

ለማንኛውም መረጃ ከትምህርት ሚኒስቴር ብቻ እንዲከታተሉም አደራ ብሏል።

#TikvahEthiopia
#NationalExam
#MoE

JOIN: @ADVANCED_FRESHMAN⭐️
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
👍22🤝4🥰3🙏3👏2
የ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ መልቀቂያ ፈተና ተፈታኞች ወደ ዩኒቨርሲቲዎች መግባት ጀምረዋል።

ከትግራይ ክልል ውጪ በሁሉም ክልሎች እና በሁለቱ የከተማ አስተዳደሮች የ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ፈተና ከሐምሌ 3-11/2016 ዓ.ም እንደሚሰጥ ይታወቃል።

ምስል፦ ዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ

JOIN:
@ADVANCED_FRESHMAN ⭐️
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
🙈19👍10😱4🔥3🫡3
በመረጃ በኩል ክፍተት እንዳለ እያየን ነው :: ትምህርት ሚኒስቴር ሚለው ሌላ ት/ቤቶች ሚሉት ሌላ🙁 መናበብ የለም....በተቻለን አቅም ትክክለኛ የሆኑ መረጃዎችን ከታማኝ መረጃ ምንጮች እናደርሳቿለን::

🙌 ለማንኛውም እኛ የምንላችሁ ነገር ቢኖር እራሳችሁን  አረጋጉ Confused አትሁኑ! ምንም ሆነ ምን መፈተናችሁ አይቀርም! So እናንተ ፈተናው ላይ ብቻ Focus አድርጉ! በርቱልን ! እንወዳችኋለን
❤️

መልካም ዕድል🫶

JOIN:
@ADVANCED_FRESHMAN⭐️
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
🥰51👍24🙏12❤‍🔥5👌5
ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የ12ኛ ክፍል የመጀመሪያ ዙር የማኅበራዊ ሳይንስ ተፈታኝ ተማሪዎችን መቀበል ጀምረዋል።

ምስል፦ ወራቤ፣ ወሎ፣ ደምቢ ዶሎ እና መቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲዎች

JOIN:
@ADVANCED_FRESHMAN⭐️
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
🙈15👍12👏4🤩3❤‍🔥2🔥2🫡1
GOV CBT.xlsx
18.2 KB
👨‍💼የመንግስት ት/ቤቶች የ12ኛ ክፍል ፈተና የዩንቨርስቲ ምደባ

JOIN:
@ADVANCED_FRESHMAN⭐️
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
👍12❤‍🔥5👏5🙏4
PRIVATE CBT.xlsx
28.1 KB
👨‍💼የPrivate ት/ቤቶች የ12ኛ ክፍል ፈተና የዩንቨርስቲ ምደባ

JOIN:
@ADVANCED_FRESHMAN⭐️
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
👍11👏3🙏3❤‍🔥2
🖊 የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና የሚወስዱ ተማሪዎች ከቅዳሜ ሰኔ 29/2016 ዓ.ም ጀምሮ ወደሚፈተኑበት ተቋማት ገብተዋል።

💻ዛሬ በርካታ ዩኒቨርሲቲዎች ለተፈታኞች ገለፃ ሲሰጡ የዋሉ ሲሆን ሌሎች ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ነገ ኦረንቴሽን እንደሚሰጡ ይጠበቃል።

JOIN:
@ADVANCED_FRESHMAN⭐️
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
👍27🙈7👏4🔥3🙏3👌21🎉1
#Tigray_National_Exam

በትግራይ ክልል የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ መልቀቂያ ፈተና ዛሬ መሰጠት ይጀምራል፡፡

ፈተናው በክልሉ በሁለት ዙር ከሐምሌ 2-12/2016 ዓ.ም በመቐለ፣ ራያ፣ አዲግራት እና አክሱም ዩኒቨርሲቲዎች ይሰጣል፡፡

የመጀመሪያው ዙር ፈተና ከሐምሌ 2-5/2016 ዓ.ም የሚሰጥ ሲሆን፤ ከ31 ሺህ በላይ የማኅበራዊ እና የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች በዚህ ዙር ለፈተና እንደሚቀመጡ ይጠበቃል፡፡ ተፈታኞች በአጠቃላይ የፈተና ዲሲፕሊን ዙሪያ ገለፃ በተቋማቱ ተደርጎላቸዋል፡፡

በዛሬው የመጀመሪያ ቀን ፈተና በጠዋቱ መርሐግብር እንግሊዝኛ፤ በከሰዓት መርሐግብር ሒሳብ ፈተና የሚሰጥ ይሆናል፡፡፡

JOIN:@ADVANCED_FRESHMAN ⭐️
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
👍232🔥2👏2