Advanced Freshman – Telegram
Advanced Freshman
27.4K subscribers
650 photos
9 videos
59 files
206 links
🔔ይህ ቻናል freshman ለሚማሩ ተማሪዎች የተዘጋጀ እና በዉስጡ የተለያዩ የዩንቨርስቲ መረጃዎችን, አጋዥ መፅሐፍቶች, ቲቶሪያል, mid እና final ፈተናዎችን ሚያዘጋጅ እና ተማሪዎች ወደ ሚፈልጉበት ዲፓርትመንት እንዲገቡ ሚያግዝ ነው ::

📩Owner:- @Bekijum
Download Telegram
"እርሱ ግን ስለ መተላለፋችን ቆሰለ፥ ስለ በደላችንም ደቀቀ"

ለመላው ክርስትና እምነት ተከታዮች እንኳን ለጌታችን እና ለመድሐኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ የስቅለት በዓል በሰላም አደረሳችሁ❤️

JOIN:@ADVANCED_FRESHMAN
136👍15🙏13🥰4🔥1
ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች እንኳን ለብርሀነ ትንሳኤው አደረሳችሁ❤️

መልካም በዓል🤩🙏

JOIN:@ADVANCED_FRESHMAN
🥰327🎉3👍2🙏2
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#ሐዋሳ_ዩኒቨርሲቲ🙈

በዓልን ግቢ እያሳለፋቹ ያላችሁ ተማሪዎች ድባቡን እንዴት አያችሁት?

በሚሪንዳ እንዳትሰክሩ አደራ🥹

መልካም በዓል❤️

@ADVANCED_FRESHMAN
😭25😁17👌16👍8🤓43🔥3🥰2😍2
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
Haramya university የበዓል ድባብ🙈እንዲም ይቻላል ለካ👏👏

ለግብያቹ President ላኩ😂

@ADVANCED_FRESHMAN
🔥114👍27🥰18😱1310😁9👌5👏43
ከ2018 ዓ.ም ጀምሮ ተማሪዎች ሞባይል ስልክ ይዘው ወደ ትምህርት ቤት እንዳይሔዱ የሚያደርግ ሕግ ሊተገብር መሆኑን ትምህርት ሚኒስቴር መግለፁ ይታወቃል፡፡

ሕጉን ወደ መሬት ለማውረድ ትምህርት ሚኒስቴር ከክልል ትምህርት ቢሮ ኃላፊዎች እና ከዘርፉ አመራሮች ጋር ውይይት ለማድረግ ዕቅድ ይዟል፡፡

በሕጉ ዙሪያ ሸገር ኤፍኤም ያነጋገራቸው መምህራን ውሳኔው ጥሩ መሆኑን ገልፀው፤ ሊታዩ የሚገባቸው ሌሎች ነገሮች መኖራቸውን አንስተዋል፡፡

ተማሪዎች አሁን ላይ ክፍል ውስጥ ሞባይል ስልክ ይዘው ሲማሩ ‘’ትምህርታቸው ላይ ትኩረት ከማድረግ ይልቅ፣ ማኅበራዊ ትስስር ገጾችን መከታተል እንደሚያበዙ" ጠቅሰዋል፡፡

ስልክ መያዛቸው ከትምህርታቸው እንዲናጠቡ እያደረጋቸው መሆኑን ያነሱት መምህራኑ፤ መፅሐፍት እና ጥናት ላይ ከማተኮር ይልቅ ሌሎች ዘመን አመጣሽ ቴክኖሎጂዎች ላይ ጥገኛ እንዲሆኑ አድርጓል ብለዋል፡፡

ይሁን እንጂ ትምህርት ቤቶች ሊያሟሏቸው የሚገቡ ጉዳዮች እንዳሉ ገልፀዋል፡፡ በቂ የመፅሐፍት አቅርቦት፣ የICT ላብ፣ የኮምፒውተር ግብዓቶች እንዲሁም የተለያዩ አጋዥ መፅሐፍት ሊሟሉ እንደሚገባ አንስተዋል፡:

@ADVANCED_FRESHMAN
👍558🤓7👏3
ዶርም ውስጥ በጩቤ...

ዛሬ ጠዋት በአርባምንጭ ዩኒቨርስቲ ጫሞ ካምፓስ አንድ የሁለተኛ ዓመት ተማሪ ዶርም ውስጥ እጅግ ሰቅጣጭ በሆነ መልኩ በጩቤ ተወግቶ ህይወቱ ማለፉን ከዩንቨርሲቲው ተማሪዎች ሰምተናል።

የግቢው ተማሪዎች ካምፓሱ ላይ ተማሪ ሲወጋ ይህ የመጀመሪያው አለመሆኑንና መወጋጋትም የተለመደ እየሆነ ነው ዩንቨርሲቲውም የተማሪዎቹን ደህንነት ለመጠበቅ ጠንካራ ስራ እየሰራ አይደለም ሲሉ ስጋታቸውን አጋርተውናል።

ከደቂቃዎች በፊት የአርባምንጭ ዩኒቨርስቲ የሚከተለውን የሃዘን መግለጫ አውጥቷል👇

የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የሥነ- ትምህርትና  ሥነ-ባህርይ ሳይንስ ትምህርት ቤት የሳይኮሎጂ ትምህርት ክፍል የ2ኛ አመት ተማሪ የሆነው ናትናኤል ፀጉ አሰፋ  ከጓኛው ጋር በተፈጠረ የግል ፀብ በደረሰበት ጥቃት ዛሬ ጠዋት ሚያዚያ  28 ቀን 2017 ዓ/ም   ከፍተኛ ጉዳት ደርሶበታል:: በመሆኑም ሕይወቱን ለማትረፍ በአርባ ምንጭ አጠቃላይ ሆስፒታል ከፍተኛ ርብርብ ቢደረግም ሳይሳካ በመቅረቱ ማምሻውን 12:30 ላይ ሕይወቱ አልፏል።

አደጋውን ያደረሰው ተማሪ በቁጥጥር ስር ውሎ አስፈላጊው ምርመራ እየተደረገ የሚገኝ ሲሆን ዩኒቨርሲቲው የሕግ ሂደቱን በመከታተል  ውሳኔውን ተከታትሎ በአጭር ጊዜ ለሕዝብ ይፋ ያደርጋል::

አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ በተማሪ ናትናኤል ከዚህ አለም በሞት መለየት የተሰማውን ጥልቅ ሀዘን እየገለፀ ለቤተሰቡ፣ ለወዳጅ ዘመዶቹ እንዲሁም ለመላው የዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ ሁሉ መፅናናትን ይመኛል።

JOIN: @ADVANCED_FRESHMAN
😭207💔44👍278😱8😢1
Forwarded from Bright Academy
እስቲ ዛሬ ስለ  Economics ትንሽ እንበላቹ ✌️

📚Economics ብዙ ቦታ የምንሰማው ብዙ ቦታ የሚነገር የትኛውም የህይወታችን ክፍል ላይ የምንጠቀመው ሀሳብ ወይንም ቃል ነው🙈 መቼም ገንዘብ💵💸 በተነሳ ቁጥር Economy, Economics, Inflation ሲባል እንደሰማን ነው🤓 ታዲያ ይህ ትልቅ የሆነ ሀሳብ በጥናት ደረጃ በሁለት ተከፍሎ እንደሚጠና በእርግጠኝነት ሰምታችሁአል😎

1⃣-Microeconomics- በትንሿ😌

Microeconomics የሚያጠናው በትንሹ ማለትም individual households (እኛን እንደማለት ነው)😜
Firms(ሻጮች) የሚያደርጉትን ግብይት እንዲሁም መስተጋብር ሚያጠና Branch of Economics ነው😃

በአጭሯ-Microeconomics Studies the individual decision making behaviour of different economic units such as households, firms, and government at disaggregated level.

በፍፁም መርሳት የሌለባቹ Micro ከተባለ Disaggregated Level ነው ያለው ማለትም በተናጥል የሚደረግ ወይም ብቻ ለብቻ የሚደረግ ጥናት ነው እያንዳንዷን Sector ለብቻዋ ማጥናት ማለት ነው እሺ🤓

2⃣-Macroeconomics-በትልቁ🤓

ሌላኛው Macroeconomics ደግሞ ሁሉንም የ አንድን ሀገር Economy የሚዳስስ በአጠቃላይ ኢኮኖሚውን የሚያጠና ዘርፍ ነው😁

በአጭሯ-Macroeconomics studies overall or aggregate behavior of the economy such as the overall level of output, prices, and employment

አሁንም መርሳት የሌለባቹ ነገር Macroeconomics የሚያጠናው Aggregate Economy ነው በአጠቃላይ ያለውን የአንድን ሀገር ኢኮኖሚ ነው የሚያጠናው😄

ለሌሎች Share ማድረጋቹን አትርሱ🫡

   ⚡️  𝚓𝚘𝚒𝚗 𝚞𝚜 ⚡️
@BrightAcademy9_12
@BrightAcademy9_12
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
👍347🔥2🥰2👏2
Forwarded from Bright Academy
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
📣ህይወት የመውደቅ የመነሳት ጉዳይ ናት ነገር ግን አላማ ላለው ሰው ስኬት አይቀሬ ነው😏

📣ለዚህ ምስክር ከሚሆኑ ሰዎች መሀከል Alibaba አንዱ ነው።

📣አንተስ ምን ማሳካት ትፈልጋለህ ጎበዝ ተማሪ መሆን፣ ስኬታማ መሆን፣ ምን ትፈልጋለህ? ተስፋ አትቁረጥ እስከመጨረሻው ታገል።


Bright Minds Bright Futures

⚡️  𝚓𝚘𝚒𝚗 𝚞𝚜 ⚡️
@BrightAcademy9_12
@BrightAcademy9_12
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
👍315👏4🫡4🥰2😁1
ልዩ መረጃ

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ወደ ጠፈር ሊጓዙ ነው ተባለ

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ወደ ጠፈር ሊጓዙ ነው ሲል መሠረት ሚዲያ ዘግቧል።

የዜና ምንጩ ጠ/ሚኒስትሩ ጠፈር ላይ በመሆን ለአለም ህዝብ የሰላም መልዕክት ለማስተላለፍ ማቀዳቸዉን አረጋግጫለሁ ማለቱን ዳጉ ጆርናል ሰምቷል።

የጉዞ እቅዱ ከተሳካ ወደ ጠፈር የተጓዙ የመጀመርያው የአለማችን መሪም ያደርጋቸዋል።

በአለም ታሪክ ወደ ጠፈር (space) የተጓዙ ሰዎች ቁጥር 721 እንደሆነ የታሪክ ድርሳናት ያሳያሉ፣ ከእነዚህ ውስጥ አብዛኞቹ የጠፈር ተመራማሪዎች ሲሆኑ ከቅርብ አመታት ግን ጥቂት ሰዎች ከፍተኛ ገንዘብ በመክፈል የዝቅተኛው ንፍቀ ክበብ የጠፈር ጉብኝት አድርገዋል።

Via መሠረት ሚዲያ

JOIN:@ADVANCED_FRESHMAN
🤣136👍17😁143🔥2😎2🎉1🏆1
#RemedialExam

የ2017 ዓ.ም የሪሚዲያል ተማሪዎች ፈተና ከግንቦት 25-30/2017 ዓ.ም ይሰጣል፡፡

መርሐግብሩ እንደሚያሳየው ከማዕከል የሚሰጠው ፈተና ለአምስት ቀናት የሚቆይ ሲሆን፤ ግንቦት 25/2017 ዓ.ም ለተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች በሚሰጠው የባዮሎጂ ትምህርት ፈተና ይጀመራል፡፡

በኢድ አል አድሃ (አረፋ) በዓል ምክንያት ፈተናው አርብ ግንቦት 29/2017 ዓ.ም የማይሰጥ መሆኑን መርሐግብር ያሳያል፡፡

ፈተናው ግንቦት 30/2017 ዓ.ም ለተፈጥሮ ሳይንስ እና ለማኅበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች በሚሰጠው የእንግሊዝኛ ትምህርት ፈተና እንደሚጠናቀቅ ይጠበቃል፡፡

የ2017 ዓ.ም የሪሚዲያል ተማሪዎች የማጠቃለያ ግምገማ ከ100% ከማዕከል ብቻ እንደሚሆን ትምህርት ሚኒስቴር መግለፁ ይታወሳል፡፡

JOIN:@ADVANCED_FRESHMAN
👍2118🥰5😱1
ሬሜዲያል ተማሪዎች መልካም ፈተና ተመኘንላችሁ ብዙም አትጨናነቁ እሺ🙏 ምክንያቱም ፈጣሪ ለናንተ ያለው ብቻ ነው ሚሆነው🥰

ፈጣሪ ቀጣይ አመት የFreshman ተማሪ ያድርጋችሁ😊

@ADVANCED_FRESHMAN
🙏25632🥰28🤗7🔥6💯4😱2
#RemedialExam

የ2017 ዓ.ም የሪሚዲያል ተማሪዎች ፈተና ከዛሬ ግንቦት 25/2017 ዓ.ም ጀምሮ ለአምስት ቀናት ይሰጣል።

ፈተናው በኦንላይን የሚሰጥ ሲሆን፤ በዛሬው ዕለት ለተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች የባዮሎጂ ትምህርት ፈተና በሦስት ክፍለ ጊዜ ይሰጣል።

JOIN: @ADVANCED_FRESHMAN
👍1813🙏6🤓2
💫 ለመላው የእስልምና 🕌 እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለ1446ተኛው የኢድ አል አድሃ (አረፋ) በዓል በሰላም አደረሳችሁ !

✨️መልካም በዓል ይሆንላቹ ዘንድ ቻናላችን ይመኛል !

JOIN: @ADVANCED_FRESHMAN
36🙏7👍5🥰3
የ2017 ዓ.ም የሪሚዲያል ተማሪዎች የማጠቃለያ የመጨረሻ ቀን ፈተና በመሰጠት ላይ ይገኛል፡፡ ፈተናው በጥብቅ ዲሲፕሊን እና የፈተና ስነ-ምግባር እየተሰጠ ነው።

77 ሺህ የሚሆኑ የሪሚዲያል ተማሪዎች በ41 ዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ በተዘጋጁ 64 የፈተና ማዕከላት የሪሚዲያል ፈተና እየወሰዱ እንደሚገኙ ትምህርት ሚኒስቴር መግለፁ ይታወሳል፡፡

የሪሚዲያል ተማሪዎች ፈተና ዛሬ ግንቦት 30/2017 ዓ.ም ይጠናቀቃል፡፡ (ምስል፦ ወለጋ ዩኒቨርሲቲ)

JOIN: @ADVANCED_FRESHMAN
17👍8💯4
Remedial ተማሪዎች ፈተናችሁ እንዴት ነበር? ቅሬታስ አላችሁ ?
🙏57💔27👌10👍82