Advanced Freshman – Telegram
Advanced Freshman
27.4K subscribers
650 photos
9 videos
59 files
206 links
🔔ይህ ቻናል freshman ለሚማሩ ተማሪዎች የተዘጋጀ እና በዉስጡ የተለያዩ የዩንቨርስቲ መረጃዎችን, አጋዥ መፅሐፍቶች, ቲቶሪያል, mid እና final ፈተናዎችን ሚያዘጋጅ እና ተማሪዎች ወደ ሚፈልጉበት ዲፓርትመንት እንዲገቡ ሚያግዝ ነው ::

📩Owner:- @Bekijum
Download Telegram
የ2017 ዓ.ም የሪሚዲያል ተማሪዎች የማጠቃለያ የመጨረሻ ቀን ፈተና በመሰጠት ላይ ይገኛል፡፡ ፈተናው በጥብቅ ዲሲፕሊን እና የፈተና ስነ-ምግባር እየተሰጠ ነው።

77 ሺህ የሚሆኑ የሪሚዲያል ተማሪዎች በ41 ዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ በተዘጋጁ 64 የፈተና ማዕከላት የሪሚዲያል ፈተና እየወሰዱ እንደሚገኙ ትምህርት ሚኒስቴር መግለፁ ይታወሳል፡፡

የሪሚዲያል ተማሪዎች ፈተና ዛሬ ግንቦት 30/2017 ዓ.ም ይጠናቀቃል፡፡ (ምስል፦ ወለጋ ዩኒቨርሲቲ)

JOIN: @ADVANCED_FRESHMAN
17👍8💯4
Remedial ተማሪዎች ፈተናችሁ እንዴት ነበር? ቅሬታስ አላችሁ ?
🙏57💔27👌10👍82
Freshaman ተማሪዎች Final Exam ጨረሳችሁ? ምንስ Department ለመግባት አሰባችሁ? ምትፈልጉት Info ካለም ጻፉልን✍️
👍93
ፍሬሾች 2nd semester ምን ነበር የገባችሁት?
Anonymous Poll
13%
Medicine
10%
Other Health
12%
Other natural
14%
Other social
5%
Law
29%
Engineering
17%
Remedial ነኝ🙌
👍2313🔥3
Advanced Freshman
ፍሬሾች 2nd semester ምን ነበር የገባችሁት?
እስቲ ዛሬ ማታ ስለ ተወሰኑ ዲፓርትመንቶች የተወሰኑ መረጃ እነግራቿ️ለው፡፡

Like👍🔥 ግጩኝ😅
👍22514🔥11😍3
አብዛኞቻቹ ስለ ተለያዩ department መረጃዎችን ጠይቃቿል::ዘመኑ የቴክኖሎጂም አይደል ስለ ፈለጋችሁት ዲፓርትመንት Ai ን ማማከር ትችላላችሁ (በተለይ Engineering )::ግን የተወሰኑትን ለማየት ያህል፦

በመጀመርያ Other Natural እና other social ዉስጥ ያላችሁ ደግሞ በጣም ገራሚ የሆኑ ዲፓርትመንቶች ማለትም ብዙ ሰው ማያቃቸው ግን የስራ እድላቸው ሰፊ እንዲሁም ብዙም ሳትጨናነቁ ምትማሯቸዉን department suggest ላርጋችሁ😊

Natural:

🧿Agro economics(AGEC), Agribusiness(ABVM), Nutrition እነዚህን ዲፓርትመንቶች ብልጥ የሆኑ ተማሪዎች አብዛኛውን ጊዜ ይመርጧቸዋል::እያንዳንዱን በግርድፉ ለማየት ያህል

Agro economics and Agribusiness:- እነዚህ ሁለቱም 90% ተመሳሳይ ዲፓርትመንቶች ሲሆኑ ብዙ ተማሪዎች ሚሸወዱት ነገር ይሄን ዲፓርትመንት እንደ ግብርና ወይም ገበሬ እንደመሆን አርገው ነው ሚያስቡት😂ነገሩ ግን ፍፁም ዉሸት ሲሆን አብዛኛው በዉስጣቸው የያዙት course ስለ production, manufacturing, accounting, economics, business... ብቻ ምን አለፋችሁ አብዛኛው ምትማሩት ነገር እንዴት የተለያዩ product እና business idea ወደ market ማስገባት እንደምትችሉ ነው::እናላችሁ በዚህ ዲፓርትመንት የተማረ አንድ ሰው የራሱን business መጀመር ወይም በተለያዩ company እንደ NGO, Bank እና የግል company ዉስጥ የመቀጠር ትልቅ ዕድል አለዉ::ልዩነታቸው በጣም ትንሽ ነው Agribusiness ከAgroeconomics ትንሽ ቀለል ያለ እና ፈታ እያላችሁ ምትማሩት ነው(በተለይ ሐዋሳ ግቢ ካላችሁ ):: አሁን ላይ እንደሰማዉት ከሆነ እነዚህ ዲፓርትመንቶች ከsocial campus ጋር ይቀላቀሉ የሚል ህሳቤ አለ ምክንያቱም 85% ምትማሩት የsocial course ነው::

Nutrition :- እቺ ደሞ ብዙ ጊዜ ሴቶች ሚወዷት ዲፓርትመንት ስቶን😁እንደምንም ይሄን ዲፓርትመንት ገብታችሁ ተምራችሁ ከወጣችሁ ስራ አጥነት ምናምን አይታሰብም በተለይ ሴቶች😃ይሄን ዲፓርትመንት ሚፈልጉት ብዙ company ዎች ሲሆኑ NGO የመጀመርያው ነው::ግን ሁሌም ቢሆን ቅድምያ ለሴቶች ሚባል ነገር አለ ወንዶችዬ🫤ወንዶች አትግቡ ሳይሆን top መሆን አለባችሁ✌️

Engineering የገባችሁ ልጆች ደግሞ ፈለጣዉን መቻል ነው እንግዲህ😤እና ደግሞ ጥሩ ዉጤት ካላችሁ በሁሉም ሊባል በሚቻል ሁኔታ አአብዛኛው አሪፍ ዲፓርትመንት ነው ::ግን አሁንም ደግሜ ምነግራችሁ ነገር ብዙ የEngineering ተማሪዎች ሀገሪቱ ዉስጥ ስላሉ ከናንተ ሚጠበቀው creative መሆን እና አሪፍ ዉጤት መያዝ 👊እዉነቱን ለመናገር ለአንድ ሀገር ምሶሶ ማነው ብትሉ Engineering ነው ቢባል ማጋነን አይሆንም:: ዶክተሩም ገብሬዉም አስተማሪውም Engineer በሰራው ነገር ነው ተጠቅመው ሃገርን ሚያገለግሉት እና Engineering ሲባል ምታጣጥሉ ሰዎች ካለማገናዘብ ችግር ስለሆነ ይቅር ተብላቿል😇

Social

Socialoch ብዙ አማራጭ ዲፓርትመንቶች ስላሉ እናንተ ለመምረጥ ብዙም ምትቸገሩ አይመስለኝም:: እናም እንደነ Logistics, marketing, management.... ያሉት ዲፓርትመንቶች ተፈላጊ ናቸው:: detail መረጃ AI ብትጠይቁ በአርፉ ይነግራቿል🫰

ሌሎች ዲፓርትመንቶችን ከዚህ በፊት ፖስት ስላረግን ከታች ያለዉን ሊንክ በመንካት ማየት ትችህላላችሁ👇👇👇

https://news.1rj.ru/str/Advanced_Freshman/2042
56🙏3😍3🤓3
📚 አካውንቲንግ (Accounting) ምንድነው?
Accounting ማለት የንግድ ወይም የድርጅት የገንዘብ ንብረት ገቢ እና ወጪ በመዘጋጀት የመቆጣጠሪያ ሂደት ነው። በአካውንቲንግ ዘርፍ ያሉ ሰዎች አካውንታንት (Accountants) በመሆን የንግድ ውሎችን ያደርጋሉ።

ይህ ዘርፍ በተለይም በልማት፣ በመንግሥታዊ ድርጅቶች፣ በግል ኩባንያዎች እና በዓለም አቀፍ ተቋማት ውስጥ ስለሚያስፈልግ የአሁኑ ዘመን አስፈላጊ ዘርፍ ነው።

📚 የትምህርት ጊዜ እና መዋቅር
በኢትዮጵያ ፣ Accounting በBachelor of Arts / Science ደረጃ በ 3 እስከ 4 አመት ይማራል።

የተማሪው ከላይ ኮርሶችን ይማራል፡፡

Financial Accounting

Management Accounting

Taxation

Auditing

Business Law

Cost Accounting

Accounting Information Systems

IFRS / GAAP Standards

💼 የስራ እድል እና ዘርፎች
በስራ ዓላማ አካውንቲንግ ብዙ አማራጮች አሉ፡፡

👇 የስራ ዓይነቶች:
Accountant – የድርጅት ገቢ እና ወጪ መዝግብ፣ መሪ መረጃ ዝግጅት

Auditor – የሂደት እና የመዝገብ ትክክለኝነት ምርመራ

Tax Consultant – የግብር እና የህጋዊ መመሪያዎች መመሪያ

Finance Manager – የገንዘብ አቅጣጫና አመራር

Budget Analyst – የቀጠሮ እቅፍና ንዴት

Forensic Accountant – ንግድ እና የገንዘብ አመናጠጥ ክስተት ምርመራ

💰 የመጀመሪያ ደረጃ ደመወዝ:
በኢትዮጵያ ፣ አካውንታንት ወርሃዊ ደመወዝ 8,000 – 18,000 ብር መካከል

በውጭ አገር ከ$2,000 እስከ $6,000 በወር

JOIN:
@ADVANCED_FRESHMAN
28👍5🔥3😱1
Happy father's day👨‍🦳
96🥰14💔10🤗4
#Remedial_Exam_Result

❗️❗️ብዙ ቻናሎች ላይ እንዲህ የሚሉ መረጃዎች እየተሰራጩ ይገኛሉ::ነገር ግን ትምህርት ሚኒስቴር ምንም ዓይነት መረጃ እስካሁን አልሰጠም!! ስለሆነም ትክክለኛ መረጃ Officially እስክለቀቅ በተሳሳተ መረጃ አትረበሹ🙏

JOIN: @ADVANCED_FRESHMAN
👍27🙏158🤓4
በርካታ የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያስተማሯቸውን ተማሪዎች በሳምንቱ መጨረሻ ያስመርቃሉ።

15 በላይ ዩኒቨርሲቲዎች የ2017 ዓ.ም የተማሪዎች የምረቃ ስነ-ስርዓት ቅዳሜ ሰኔ 14/2017 ዓ.ም የሚያከናውኑ ሲሆን፤ የተወሰኑ ዩኒቨርሲቲዎች እሑድ ሰኔ 15/2017 ዓ.ም ያካሒዳሉ።

🎓 ጅማ ዩኒቨርሲቲ
🎓 አዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ፣
🎓 ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ፣
🎓 ባህርዳር ዩኒቨርሲቲ፣
🎓 አምቦ ዩኒቨርሲቲ፣
🎓 ዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ፣
🎓 እንጅባራ ዩኒቨርሲቲ፣
🎓 ራያ ዩኒቨርሲቲ፣
🎓 ሰመራ ዩኒቨርሲቲ፣
🎓 ወልድያ ዩኒቨርሲቲ፣
🎓 ቦንጋ ዩኒቨርሲቲ፣
🎓 ደባርቅ ዩኒቨርሲቲ፣
🎓 አክሱም ዩኒቨርሲቲ፣
🎓 ደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲ፣
🎓 መደ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ፣
🎓 ቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ፣
🎓 መቱ ዩኒቨርሲቲ እና
🎓 የኢትዮጵያ ሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ በሳምንቱ መጨረሻ ተማሪዎቻቸውን ከሚያስመርቁ ዩኒቨርሲቲዎች መካከል ይጠቀሳሉ።

JOIN:@ADVANCED_FRESHMAN
👍1312🥰1
ፍሬሽማን ተማሪዎች አመቱን ስንት GPA በማምጣት ወደ 2ኛ አመት አለፋችሁ?
Anonymous Poll
12%
4 😎
16%
Above 3.8 😇
17%
Above 3.5 ☺️
10%
Above 3.3 🥲
11%
Above 3 🥹
11%
Below 3 🤪
23%
I'm Remedial🙂
🔥176💔6👍1
Advanced Freshman
ፍሬሽማን ተማሪዎች አመቱን ስንት GPA በማምጣት ወደ 2ኛ አመት አለፋችሁ?
ሀገራችን ተስፋ አላት🥹🥹
😁72❤‍🔥5💔5🔥3🫡2😍1😎1
Advanced Freshman
ሀገራችን ተስፋ አላት🥹🥹
አረ አረጋጉት guys እንዲው ነው ያልኩት እንጂ GPA መስቀል matter አያረግም!!ያው ዕድል ያሰፋል እንጂ :: ዉጤት ከፍ አለ or ዝቅ አለ ማለት የናንተን ትክክለኛ potential አያሳይም!! ያው ታቁታላችሁ ግቢ ላይ ብዙ fair ያልሆነ ነገር አለ:ጎበዝ ሆናችሁ ዉጤት ሚበላሽበት ጊዜ አለ በተለያዩ ምክንያቶች....::እንደዛው ሁሉ ተኮራርጀው ወይም ፈተና አግኝተው 4 ሚያመጡ አሉ::

Anyways 4 ስላመጣችሁ ብዙም ደስ አይበላችሁ ዉጤት ዝቅ ስላለም አትዘኑ🙌በቻላችሁ አቅም ከትምህርታቹ ጎን ለጎን skill ለመማር ሞክሩ ✌️ አንዳንድ ሃሳቦችን እና ጠቃሚ ነገሮችን በዚህ ክረምት እናወራበታለን😊
🥰6922💯12🙏9👍8🤗1
Class of 2025 Commencement!

በርካታ የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች በልዩ ልዩ የሙያ መስኮች ያሰለጠኗቸውን ተማሪዎች እያስመረቁ ነው።

ከ25 በላይ ዩኒቨርሲቲዎች በዛሬው ዕለት ተማሪዎቻቸውን እያስመረቁ ይገኛሉ፡፡

ተመራቂዎቹ በተለያዩ ፕሮግራሞች ትምህርታቸውን ተከታትለው ያጠናቀቁና የመውጫ ፈተና ወስደው ያለፉ የቅድመ-ምረቃ መርሐግብር ተማሪዎች እንዲሁም የድኅረ-ምረቃ እና የስፔሻሊቲ ፕሮግራም ሰልጣኞች ናቸው፡፡

እንኳን ደስ አላችሁ!

ምስል፦ ጅማ፣ ባህርዳር፣ ደምቢ ዶሎ እና አሶሳ ዩኒቨርሲቲዎች

JOIN: @ADVANCED_FRESHMAN
👏97🙏1🤗1