BeWide Technologies – Telegram
BeWide Technologies
292 subscribers
78 photos
18 links
Pioneering AI-powered software development, IT solutions, and branding for transformative growth. From intelligent web design and custom systems to dynamic mobile apps

Elevate your digital presence with us

Be wide—Be wise

Contact us through @BeWideTech
Download Telegram
BeWide Technologies
Photo
ቢዋይድ ቴክኖሎጂስ በአፕልኬሽን መልክ ለ አፍሪካ ቲቪ  ያበለጸገውን የ4 ሼኾችን ለበርካታ አመታት ሲያስተላልፋቸው የቆየውን  ትምህርቶች ምርቃት ዛሬ በstay easy ሆቴል ተካሄደ!
——————————

ለኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች ከ15 አመታት በላይ ግልጋሎት ሲሰጥ የቆየው አፍሪካ ቲቪ ከቢዋይድ ቴክኖሎጂስ ጋር በመተባበር በክምችት ክፍል የነበሩ የ6 ሼኾችን የደርስ ትምህርት በሞባይል አፕሊኬሽን መልክ በማዘጋጀት ከአፕ ስቶር አውርደን መጠቀም እንድንችል አዘጋጅቶ ዛሬ የካቲት 19 ቀን 2018 በስቴይ ኢዚ ሆቴል በይፋ አስመርቋል።

በዚህ የምረቃ መድረክ ላይ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠ/ም/ቤት ምክትል ተቀዳሚ ፕሬዚደንት ሸይኽ አብዱልከሪም ሸይኽ በድረዲን ፣ የምክር ቤቱ የፕሬዝዳንት ጽ/ቤት ሃላፊ ኡስታዝ አቡበከር አህመድን ጨምሮ ታላላቅ መሻዒኾች ፣ ዱዓቶችና የማህበረሰብ መሪዎች በተገኙበት በዛሬው ዕለት በአዲስ አበባ ከተማ ስቴይ ኢዚ ሆቴል የ6 መሻዒኾችን ሸሪዓዊ አስተምህሮ የያዙ የሞባይል መተግበርያዎች ተመርቀዋል ። ስለ አፕልኬሽኖቹ ገለጻ የሰጡት የBewide Technologies CEO መኪን ሙሃመድ፣ ይህን እድል በማግኘታችን ለኛ ትልቅ ክብር ነው ያሉ ሲሆን፣ በስተመጨረሻም መተግበሪያዎቹን በማውረድ የመክፈቻ ስነስርዓቱ ተጠናቋል። 

መተግበሪያቸው ይፋ የሆኑት 6ቱ መሻዒኾች ማለትም :-

1. ሸይኽ ሰዒድ አህመድ ሙስጦፋ
2.ሸይኽ ሙሐመድ ዘይን ዘህረዲን
3. ሸይኽ ኢብራሂም ሲራጅ ( ረህመቱላህ አለይሂ )
4. ሸይኽ ሙሐመድ ሐሚዲን
5. ሸይኽ ሐሚድ ሙሳ
6. ሸይኽ ሙሐመድ ፈረጅ

ሲሆኑ እስካሁን በተለያዩ መንገዶች ሲያቀርቧቸው የነበሩ ሸሪዓዊ ትምህርቶችን በእያንዳንዳቸው ስም በበለጸጉ የሞባይል መተገበርያዎች ማግኘት የሚቻልበት ነው ። የሞይባልይ መተገበርያው በአፍሪካ ቲቪ Play Store አካውንት ሚገኙ ይሆናል።

Bewide Technologies ለማህበረሰቡ መልካም ለውጥ እየሰራ የሚገኝ ድርጅት መሆኑን አስመስክሯል።

https://news.1rj.ru/str/BeWide_Tech
🔥9