BeWide Technologies
Photo
የኡምራ ጉዞን በተሻለ መልኩ ለማከናወን የሚረዳ "ኡምራ ጎ" የተሰኘ ፕላትፎርም ይፋ ሆነ!
- ሀሩን ሚዲያ፥ ሕዳር 20/2018
በቢ ዋይድ ቴክኖሎጂስ ያዘጋጀው የኡምራ ጉዞን በተሻለ መልኩ ለማከናወን የሚረዳ "ኡምራ ጎ" የተሰኘ ፕላት ፎርም በዛሬው ዕለት በአዲስ አበባ ኢንተር ሌግዤሪ ሆቴል ይፋ ሆኗል።
በፕላትርሙ ላይ በሀገራችን ከኡምራ ጋር የተያያዙ ስራዎችን የሚሰሩ ኤጀንሲዎች አጠቃላይ የሚሰጡትን አገልግሎት በግልጽ እንደሚይዝ እና የእያንዳንዱን ኤጀንሲ አጠቃላይ አገልግሎት ይገልፃሉ ተብሏል።
በተጨማሪም በፕላትሮርሙ ላይ ቁርአን ከእነ ተፍሲሩ መቅራት ያስችላል የተባለ ሲሆን፤ የሰላት ሰአት የሚጠቁም፣ የቁርአን ቲላዋ ማድመጥ የሚያስችል፣ ማስታወሻ መያዝ የሚያስችል፣ የካላንደር መቁጠሪያ ጨምሮ ሌሎችም አገልግሎቶች የተካተቱበት መሆኑን የቢ ዋይድ ቴክኖሎጂ ዋና ስራ አስፈፃሚ መኪን ሙሀመድ ገልጿል።
በኢንተር ሌግዠሪ ሆቴል እየተካሄደ በሚገኘው በዚሁ መርኅ ግብር ታላላቅ ኡለማኦች፣ የተለያዩ ኤጀንሲ ባለቤቶች የሚዲያ ባለሙያዎች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።
በመርኀ ግብሩ ላይ የተገኙት ሸይኽ ሙሀመድ ሐሚዲን (ዶ/ር) ኡምራ እስልምና ውስጥ ካሉ ኢባዳዎች ከዋናዎቹ ነው። ይህንን ትልቅ ኢባዳ በተቀላጠፈ መንገድ ለማከናወን የሚረዳ ቴክኖሎጂ ጅማሬው በራሱ የሚበረታታ ነው ብለዋል።
"ኡምራ ጎ" የተሰኘው ፕላትፎርም በአማርኛ፣አፋን ኦሮሞ፣በአፍ ሶማሌ እንግሊዝኛ እና አረብኛ በአጠቃላይ በአምስት ቋንቋቸው አገልግሎት የሚሰጥ መሆኑ የተገለፀ ሲሆን ከጥቂት ቀናት በኋላ በፕሌይ ስቶር እና አፕ ስቶር ላይ ማግኘት ይቻላል የተባለ ሲሆን አሁን ላይ "ኡምራ ጎ ዶት ኢት" ላይ አገልግሎቱን ማግኘት እንደሚቻል ተገልጿል።
© ሀሩን ሚዲያ
@BeWide_Tech

🔥8👍2❤1
BeWide Technologies
Photo
Bewide Technologies ለሱና ፋውንዴሽን እና ለዳዕዋ ቲቪ ያበለፀገውን ድረ-ገጽ አስረከበ
-ዳዕዋ ቲቪ ፣ የካቲት 9/2018 ዓ.ል.
በኢትዮጵያ የቴክኖሎጂ ዘርፍ በፈጠራ ስራዎቹ ስሙ እየጎላ የመጣው Bewide Technologies፣ ከሱና ፋውንዴሽን ጋር በመተባበር ሲያከናውን የቆየውን የዌብሳይት ልማት ፕሮጀክት በስኬት አጠናቆ አስረክቧል። በዚሁ የርክክብ መርሃ-ግብር ላይ የፋውንዴሽኑ ከፍተኛ አመራሮች የተገኙ ሲሆን፣ ተቋሙ ወደ ዲጂታል መድረክ የሚያደርገውን ሽግግር የሚያፋጥኑ ስራዎች መከናወናቸው ተገልጿል። የፋውንዴሽኑ ማኔጂንግ ዳይሬክተር ዶክተር ኑሩ ሙሀመድ ባደረጉት ንግግር፣ በአሁኑ ወቅት ዲጂታሉ ዓለም ላይ መገኘት ለወቅቱ ዳዕዋና ተደራሽነት ወሳኝ መሆኑን ጠቁመው፣ ይህ የዌብሳይት ስራ የፋውንዴሽኑን ራዕይ ለማሳካት ትልቅ አቅም እንደሚፈጥር አብራርተዋል።
የፋውንዴሽኑ ምክትል ሥራ አስፈፃሚ ሸይኽ ሰዒድ ኺያር በበኩላቸው ወጣቶቹ ላሳዩት የፈጠራ ብቃትና ለሰሩት ጥራት ያለው ስራ አድናቆታቸውን የገለጹ ሲሆን፣ የሱና ፋውንዴሽን ዋና ሥራ አስኪያጅና ቻንስለር ዶክተር ሸይኽ ሙሀመድ ሃሚዲን የቢዋይድ ቴክኖሎጂስ ወጣቶች እያበረከቱት ያለውን አስተዋፅኦ በልዩ ሁኔታ አድንቀዋል። ሸይኹ አክለውም "ሁሉም ሙስሊም ሀብት ያለው በሀብቱ፣ እውቀት ያለው በእውቀቱ ከሱና ዩኒቨርሲቲ ጎን መቆም አለበት" በማለት ጥሪ ያቀረቡ ሲሆን፣ ለወጣቶቹም ውጤታማ ስራ የላቀ ዱዓ አድርገውላቸዋል። በዕለቱም ለኩባንያው ከፋውንዴሽኑ ዋና ሥራ አስፈፃሚ የምስጋናና የእውቅና ሰርተፍኬት ተበርክቶላቸዋል።
Bewide Technologies ከዚህ ቀደም ከ Africa TV ጋር በመተባበር ከ4 በላይ ሞባይል አፕሊኬሽኖችን በማልማት፣ በተለይም የዶክተር ሸይክ ሙሀመድ ሃሚዲን ደርሶችና ፈትዋዎች በዲጂታል አማራጭ ተደራሽ እንዲሆኑ ማድረጉ ይታወሳል። ኩባንያው ከሶፍትዌር ልማት ባለፈ በብራንዲንግ እና በቴክኖሎጂ አቅም ግንባታ ላይ የሚሰራ ሲሆን፣ እንደ Umrago ያሉ የራሱን የፈጠራ ውጤቶች ለገበያ በማቅረብ በዘርፉ ቀዳሚነቱን እያስመሰከረ ይገኛል። ይህ የቅርብ ጊዜ አጋርነትም ተቋሙ ለማህበራዊ ለውጥና ለዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ያለውን ቁርጠኝነት በድጋሚ ያረጋገጠበት ሆኗል።
በኢብራሂም ደሊል
°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°
Youtube: https://www.youtube.com/@DaewaTV1
facebook: https://www.facebook.com/daewa.tv
Telegram: https://news.1rj.ru/str/daewa_tv
©ዳዕዋ ቲቪ
ጉዞ ስንቅን ይዞ

Facebook
Log in or sign up to view
See posts, photos and more on Facebook.
👏5🔥4❤1
"May this Ramadan purify your heart and bring you closer to Allah."
Ramadan Kareem.
Bewide Technologies
Be Wide - Be Wise
@BeWide_Tech
Ramadan Kareem.
Bewide Technologies
Be Wide - Be Wise
@BeWide_Tech
❤5