ሐምሌ 10 ቀን 2015 ዓ.ም በአንድ ጀንበር 500 ሚሊዮን ችግኞች በኅብረት!
👎15👍10❤4👏1
"ካኤል" ዓመታዊው የወፍራም ወንዶች ውድድር በቦዲዎች መንደር
**********************************
መቅጠን እና ሸንቃጣ ሆኖ መታየት የውበት መለኪያ ሆኖ በሚታይባት ዓለም፤ የደቡብ ኦሞዎቹ የቦዲ ማህበረሰብ ጋር ግን በተቃራኒው ውፍረት ውበት ሆኖ አመታዊ የውፍረት ውድድር ይካሄድበታል።
ቦዲዎች በየዓመቱ "ካኤል" በመባል የሚታወቀውን አዲስ አመታቸውን ያከብራሉ። ይህ በዓል በሰኔ እና በሀምሌ ወር መካከል ጨረቃ ሙሉ በምትሆንበት ጊዜ ይከበራል። የዓመቱን መጀመሪያ ለመቀበል ከሚደረጉ ስነስረዓቶች አንዱ በወጣቶች መካከል የሚደረግ የሰውነት ውፍረት ውድድር ነው። ለዚህ ውድድር አስራ አራቱም የቦዲ ጎሳዎች ተወዳዳሪዎችን ያዘጋጃሉ። ታዲያ ለውድድሩ የሚዘጋጁት ተወዳዳሪዎች ያላገቡ ወንዶች ናቸው።
ለካኤል ውድድር ከየጎሳው የተወከሉት ተወዳዳሪዎች በተለየ መንገድ መቀለብ ይጀምራሉ። ለብቻቸው መኖሪያ ጎጆ ከተሰራላቸው በኋላ እስከ ውድድሩ ዕለት ከጎጇቸው መውጣት አይፈቀድላቸውም። ክልከላው ወሲባዊ ግንኙነት ማድረግንም የሚያጠቃልል ነው።https://www.facebook.com/EBCmezenagna/posts/pfbid09zE6t33k9xPJ5oGjsar1tvG5wZXKLkhZJ5WSSefn2AYsSpbNpnMZdgGJ4j4rtPVHl

👍61👎13❤9👏2
የአምስት ዓመቱ የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር ስኬት
-----------------
በ2011 ዓ.ም የመጀመሪያ ዓመት የተተከሉ ችግኞች ፡- 4.7 ቢሊዮን
ከዚህ ውስጥ በአንድ ጀንበር የተተከለ እና ክብረ ወሰን የያዘ ፡- 350 ሚሊዮን ችግኝ
በ2012 ዓ.ም የተተከሉ ችግኞች ፡- 6 ቢሊዮን
በ2013 ዓ.ም የተተከሉ ችግኞች ፡- 6.8 ቢሊዮን
በ2014 ዓ.ም የተተከሉ ችግኞች ፡- 7.2 ቢሊዮን
በ2015 ዓ.ም የሚተከሉ ችግኞች ፡- 6.5 ቢሊዮን
በዚህ ዓመት እስካሁን የተተከሉ ችግኞች፡- 3.4 ቢሊዮን
በ2015 በአንድ ጀንበር ለመትከል የታቀደው፡- 500 ሚሊዮን ችግኝ
በመጀመሪያው ምዕራፍ የአረንጓዴ አሻራ መርሐ-ግብር የተተከሉ ችግኞች፡- 25 ቢሊዮን
ከእነዚህ ችግኞች ውስጥ ግማሾቹ አገር በቀል እንዲሁም አትክልትና ፍራፍሬ ናቸው።
https://www.facebook.com/EBCzena/posts/pfbid02t7anu6qK8g6B5HPH5U3RGcZWv58QVwZPaunV5PrwUMu2LS3j6eCeEEHRRSXWU4pwl

👍95👎31❤27👏3
ለዩኒቨርሲቲ መውጫ ፈተና ከተቀመጡ ተማሪዎች ውስጥ 40.65 በመቶዎቹ የማለፊያ ነጥብ ማስመዝገባቸውን የትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ
************************
የትምህርት ሚኒስቴር ሲሰጥ የቆየው የዩኒቨርስቲ መውጫ ፈተና በሠላም መጠናቀቁን አስታውቋል።
ለመውጫ ፈተናው ሊቀመጡ ይችላሉ ተብሎ የተገመተው 240 ሺህ የሚሆኑ ተማሪዎች ቢሆኑም ለፈተናው ብቁ የሆኑት 194 ሺህ 239 ተማሪዎች ሲሆኑ ከእነዚህም 150 ሺህ 184ቱ ተማሪዎች ፈተናውን ወስደዋል ብሏል ሚኒስቴሩ በመግለጫው።
ከተፈተኑት ተማሪዎች ውስጥም 61 ሺህ 54 ተማሪዎች (40.65 በመቶ) የማለፊያ ነጥብ እንዳስመዘገቡ ገልጿል።
https://www.facebook.com/EBCzena/posts/pfbid0eSB1jBDuoYDoGA3zRfTBHXRsf2M3Bv5q3kuoQA3bdXDF32MFgSFRZmD5NeannzwXl

👍51👎16❤5👏3
የዩኒቨርሲቲ መውጫ ፈተና ከወሰዱ የግል የትምህርት ተቋማት ተማሪዎች ውስጥ የማለፊያውን 50 በመቶ እና ከዛም በላይ ውጤት ያስመዘገቡት 17.2 በመቶ ብቻ ናቸው
**************************
በዩኒቨርሲቲ መውጫ ፈተና 62.37 በመቶ የመንግሥት የትምህርት ተቋማት እና 17.2 በመቶ የግል የትምህርት ተቋማት ተማሪዎች የማለፊያውን 50 በመቶ እና ከዛም በላይ ውጤት አስመዝግበዋል።
የትምህርት ሚኒስቴር ከሰኔ 30 ቀን ጀምሮ ለስድስት ቀናት ሲሰጥ የቆየውን የዩኒቨርሲቲ መውጫ ፈተና በስኬት አጠናቋል።
የትምህርት ሚኒስቴር የከፍተኛ ትምህርት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ሳሙኤል ክፍሌ (ዶ/ር) ፈተናውን አስመልክተው ዛሬ መግለጫ ሰጥተዋል።
የመውጫ ፈተናውን ከ48 የመንግሥት ተቋማት 84 ሺህ 627 እና ከ171 የግል ተቋማት ደግሞ 109 ሺህ 239 በድምሩ 194 ሺህ 239 ተማሪዎች ፈተናውን ለመውሰድ ብቁ ሆነው መመዝገባቸውን ሳሙኤል (ዶ/ር) አስታውቀዋል።
https://www.facebook.com/EBCzena/posts/pfbid0oZjUwuw5Tumr56TUEZirVgdgH9N6a4ehxJXUtci3hYFbPyAQv5kGw8Sx7FejgNT6l

👍91👎18❤9👏9
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የዘጠኝ ኤጲስ ቆጶሳት ሹመት ተከናወነ
******************************
የኤጲስ ቆጶሳቱ ሹመት በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ፓትሪያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማቲያስ መሪነት በመንበረ ፓትሪያርክ ቅድስተ ቅዱሳን ማርያም ገዳም ተካሂዷል።
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ባደረገው የኤጲስ ቆጶሳት ምርጫ መሠረት ለዘጠኙ ቆሞሳት በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት መሪነት በሊቃነ ጳጳሳት አንብሮተ ዕድ ተፈጽሟል።
በዚህ መሰረት
1. ቆሞስ አባ ክንፈ ገብርኤል ተ/ማርያም አባ ገሪማ ተብለው የጌዲኦ፣ አማሮና ቡርጅ ሀገረ ስብከት፣
2. ቆሞስ አባ ሳህለ ማርያም ቶላ አባ ገብርኤል ተብለው የምዕራብ ሸዋ ሀገረ ስብከት፣
3. ቆሞስ አባ ስብአት ለአብ ሀይለማርያም አባ ጢሞቲዎስ ተብለው የዳወሮ ኮንታ ሀገረ ስብከት፣
4. ቆሞስ አባ አምደሚካኤል ኃይሌ አባ ኤልሳዕ ተብለው የምስራቅ ወለጋ ሀገረ ስብከት፣
5. ቆሞስ አባ ሀይለማርያም ጌታቸው አባ በርቶሎሜዎስ ተብለው የድሬደዋ ሀገረ ስብከት፣
6. ቆሞስ አባ ጥላሁን ወርቁ አባ ኤፍሬም ተብለው የቡኖ በደሌ ሀገረ ስብከት፣
7. ቆሞስ አባ ዘተ/ሀይማኖት ገብሬ አባ ኤጲፋንዮስ ተብለው የሆሮ ጉድሩ ሀገረ ስብከት፣
8. ቆሞስ አባ እስጢፋኖስ ገብሬ አባ ዳንኤል ተብለው የምዕራብ ወለጋ ሀገረ ስብከት እና
9. ቆሞስ አባ ወ/ገብርኤል አበበ አባ ኒቆዲሞስ የምስራቅ ሀረርጌ ሀገረ ስብከት ሆነው መሾማቸውን የኢኦተቤ መገናኛ ብዙኀን አገልግሎት ሥርጭት ድርጅት መረጃ ያመለክታል።

👍76❤13👎13👏4
በኢትዮጵያ አይዶል የመክፈቻ ሥነ ስርዓት ላይ የኢቢሲ ዋና ስራ አስፈጻሚ ፍስሃ ይታገሱ ያደረጉት ንግግር https://www.youtube.com/watch?v=iCkkYOlgLKI
YouTube
በኢትዮጵያ አይዶል የመክፈቻ ሥነ ስርዓት-የኢቢሲ ዋና ስራ አስፈጻሚ ፍስሃ ይታገሱ
በኢትዮጵያ አይዶል የመክፈቻ ሥነ ስርዓት-
የኢቢሲ ዋና ስራ አስፈጻሚ ፍስሃ ይታገሱ
t #EbcEntertainment #Ethiopian #Ebc #meznagna #

👍23👎11❤2