በአዳማ ከተማ ለሽብር ወንጀል ሊውል የነበረ በርካታ ሕገ-ወጥ የጦር መሳሪያ ተያዘ
**************
በአዳማ ከተማ ለሽብር ወንጀል ሊውል የነበረ በርካታ ሕገ-ወጥ የጦር መሳሪያ እና ጥይት በፍተሻና በሕዝብ ጥቆማ በቁጥጥር ስር ዋለ።
በአዳማ ከተማ ፖሊስ ከሌሎች የፀጥታ አካላት ጋር በመቀናጀት በከተማው በተለያዩ ጊዜያት የሽብር ተግባር ለመፈፀም መነሻቸውን አዋሽ ሰባት፣ ሰበታ እና ሌሎች አካባቢዎች በማድረግ በተሽከርካሪ ታግዘው ሕገ-ወጥ መሣሪያውን ወደ አዲስ አበባ ከተማ እና ወደ ሌሎች አካባቢዎች በማዘዋወር የሽብር ተግባር ለመፈፀም የሞከሩ አሸባሪዎችንና ተባባሪዎቻቸውን ከህብረተሰቡ በተገኘ ጥቆማ እና በተደረገ ጥብቅ ፍተሻ በቁጥጥር ስራ መዋል መቻሉ ተጠቅሷል፡፡
በዚህም 61 ቦንብ፣ 6 ሺህ የክላሽንኮቭ ጠመንጃ ጥይት፣ 4 ሺህ 983 የሽጉጥ ጥይት፣ 1 ሺህ 879 የብሬን ጥይት፣ 17 ክላሽንኮቭ ጠመንጃ፣ 18 የተለያየ አይነት ሽጉጥ፣ ዘጠኝ የብሬን ሸንሸን (ሰንሰለት)፣ አንድ ስናይፐር፣ አንድ ላውንቸር፣ ሁለት ቁንቡላ፣ አንድ የጦር ሜዳ መነጽር እና 242 ሺህ 220 ብር መያዙን የአዳማ ከተማ ፖሊስ ገልጿል።
ህገ-ወጥ የጦር መሣሪያዎችንና ጥይቶችን ለሽብር ቡድኑ ሊያስተላልፉ የነበሩ ተጠርጣሪዎች እና የመኪናው ሾፌርም ከነ-ኤግዚብቱ በቁጥጥር ሥር ውለው ምርመራ እየተጣራባቸው እንደሚገኝ የአዳማ ፖሊስ ዋና መምሪያ ጠቁሟል።
https://www.facebook.com/EBCzena/posts/pfbid02E48btinTYvnD7w27AFXY2qWzLECSxVXdHU4TykT5YxuAuSCgfJJ4HesMdwsyhtKul

👍60❤12👏7
ከአፍሪካ አንድነት ድርጅት እስከ አፍሪካ ኅብረት
*********************
• በ1955 ዓ.ም የአፍሪካ አንድነት ድርጅት ቻርተር ተፈርሞ ድርጅቱ ተመሰረተ፤
• ቻርተሩን ፈርመው ድርጅቱን የመሰረቱት 32 ሀገራት ነበሩ፤
• በ1994 ዓ.ም ድርጅቱ ወደ ኅብረት ሲሸጋገር የአባላቱ ቁጥር 53 ደረሰ፤
• በ1991 ዓ.ም በሊቢያዋ ሰርጥ በተካሄደ ጉባኤ "በሰርጥ አዋጅ" የአፍሪካ ኅብረት እንዲመሰረት ተወሰነ፤
• በ1992 ዓ.ም የአፍሪካ ኅብረት ምስረታ ሕግን ያጸደቀው የሎሜ የመሪዎች ጉባኤ ተካሄደ፤
• በ1993 ዓ.ም በሉሳካ በተካሄደ የመሪዎች ጉባኤ የኅብረቱ ሮድ ማፕ ጸደቀ፤
• ሐምሌ 2 ቀን 2003 ዓ.ም ደቡብ ሱዳን 54ኛ የኅብረቱ አባል ሆነች፤
• በ1994 ዓ.ም በደቡብ አፍሪካዋ ደርባን በተካሄደ የመሪዎች ጉባኤ የኅብረቱ መመስረት ይፋ ሆነ፣

👍47👏9❤5👎1
ኢትዮጵያ እና አንጎላ በኢኮኖሚና በፖለቲካዊ ጉዳዮች ላይ በጋራ ለመስራት ስምምነት ተፈራረሙ
**********
ኢትዮጵያ እና አንጎላ በኢኮኖሚና በፖለቲካዊ ጉዳዮች ላይ በጋራ መስራት የሚያስችላቸውን የመግባቢያ ስምምነት ተፈራርመዋል።
ስምምነቱ ሁለቱ ሀገራት ከዚህ ቀደም ያላቸውን ትብብር የሚያጠናክር እነደሆነ ተገልጿል።
በተለይም የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ አንጎላ የሚያደረገውን በረራ ማሳደግ በሚቻልባቸው መንገዶች ላይ ከስምምነት ተደርሷል።
ስምምነቱን የውጭ ጉዳይ ሚንስትር አምባሳደር ታዬ አፅቀስላሴ ከአንጎላ የውጭ ጉዳይ ሚንስትር ቴቴ አንቶኒዮ ጋር ተፈራርመዋል።
በሌላ በኩል አምባሳደር ታዬ ከዚምባብዌ የውጭ ጉዳይ ሚንስትር ዶክተር ፍሬድሪክ ሻቫ ጋር የሁለትዮሽ ውይይት አካሂደዋል።
በማህሌት ታደለ

❤27👍21👏5
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ታዬ አጽቀሥላሴ ከዚምባብዌ አቻቸው ጋር ተወያዩ
***********
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ታዬ አጽቀሥላሴ ከዚምባብዌ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ፌድሪክ ኤም ሻቫ ጋር የሁለትዮሽ ውይይት አድርገዋል።
ሁለቱ ሚኒስትሮች በሁለትዮሽ እና በባለብዙ ወገን ጉዳዮች ትብብር ላይ መምከራቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
ከውይይታቸው በኋላም ለመገናኛ ብዙኃን በሰጡት መግለጫ፤ የሁለትዮሽ ግንኙነታቸውን ወደ ላቀ ደረጃ ለማድረስ እና የባለብዙ ወገን አጋርነትን ለማጠናከር ተስማምተዋል።

👍40❤11👏2
የዓድዋ ድል መታሰቢያ የመላ አፍሪካውያን የድል ምልክት ነው - አምባሳደር ታዬ አፅቀሥላሴ
**********
የዓድዋ ድል መታሰቢያ የመላ አፍሪካውያን የድል ምልክት መሆኑን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ታዬ አፅቀሥላሴ ተናገሩ።
የአፍሪካ ሕብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ሙሳ ፋኪ ማሃመት እና ሌሎችም ኃላፊዎች፣ የአፍሪካ ሀገራት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮችን ጨምሮ የተለያዩ ሀገራት አምባሳደሮች የአድዋ ድል መታሰቢያን ጎብኝተዋል።
የኃይማኖት መሪዎችና ሌሎችም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በጉብኝቱ ተገኝተዋል።
በጉብኝቱም ወቅቱ ከነበረው ወራሪ ኃይል ኢትዮጵያን ነፃ ለማውጣት የቀደሙት ጀግኖች ያደረጉትን ትግልና የከፈሉትን መስዋዕትነት በሚመለከት በማሳያዎች ማብራሪያ ተሰጥቷቸዋል።
ከጉብኝቱ በኋላ ንግግር ያደረጉት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ታዬ አፅቀሥላሴ፤ አፍሪካውያን ነፃነታቸውን ለመቀዳጀት ያደረጉት ተጋድሎ ለፓን-አፍሪካኒዝም ንቅናቄ ማበብ መሠረት የጣለ ስለመሆኑ ገልፀዋል።
https://www.facebook.com/EBCzena/posts/pfbid0kjpY7PCqrMXyXudVndYidNDFkSRHDKE6vhR4VnPGPT6wQp4X9y6xJDNSCfuyAebgl

👍41❤12👏3
ከ23 በላይ የቱርክ ኩባንያዎች የተሳተፉበት የቢዝነስ ፎረም መካሄድ ጀመረ
****************
የኢትዮጵያ እና የቱርክ ሰካሪያ ከተማ የመዋዕለ ንዋይና ንግድ ማስተዋወቂያ መድረክ በዛሬው እለት በአዲስ አበባ መካሄድ ጀምሯል።
በመድረኩ በኢትዮጵያ መዋዕለንዋያቸውን ለማፍሰስ ፍላጎት ያላቸው 23 የቱርክ ኩባንያዎች እና በርካታ የኢትዮጵያ ባለሀብቶች መሳተፋቸው ተገልጿል።
በመድረኩ በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የፖለቲካ እና ኢኮኖሚ ጉዳዮች ሚኒስትር ዴኤታ ጽ/ቤት ኃላፊ አምባሳደር ትዝታ ሙሉጌታ (ዶ/ር)፤ ኢትዮጵያ እና ቱርክ ጠንካራ የምጣኔ ሀብት ግንኙነት እንዳላቸው ጠቅሰዋል።
መድረኩ የቱርክ ባለሀብቶች በኢትዮጵያ ያሉትን ሰፊ፣ ምቹ እና አዳዲስ የመዋዕለ ንዋይ ዕድሎች የበለጠ እንዲጠቀሙ ለማስቻል እና የሁለትዮሽ የንግድ ትስስሩን ለማሳደግ ወሳኝ መሆኑን አያይዘው ገልጸዋል።
የንግድና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት ፕሬዚዳንት ኢንጅነር መላኩ እዘዘው በበኩላቸው፤ የንግድና የመዋዕለንዋይ ግንኙነቱ መጠናከር አለበት ብለዋል።https://www.facebook.com/EBCzena/posts/pfbid0d3b3yHMiXvf8TvrF6hDtyrZQ94nSgZCKdqNWQtrtdeRq2Q7U7FaoQuwuGr2QaHhil

👍27❤10👏5👎1