ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ የስራና ክህሎት ሚኒስቴርና የተጠሪ ተቋማትን የስራ እንቅስቃሴ ጎበኙ
******************
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)፥ ለፈጠራ ሀሳብና ለምርምር ምቹ የሆነ የስራ ከባቢ እንዲፈጠር ባስቀመጡት አቅጣጫ መሰረት በኢፌዴሪ ቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩት የተከናወኑ የልማት ስራዎችና የኢኖቬሽን ውጤቶችን ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ ተዘዋውረው ተመልክተዋል።
የስራና ክህሎት ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚል በወቅቱ እንደገለጹት፥ በኢንስቲትዩቱ ለፈጠራ ሀሳብ ማፍለቂያ እና ለምርምር ምቹ ምህዳር ተፈጥሯል።
ኢንስቲትዩቱ ከሀገር የልማት ግብ አኳያ ብቁ ሙያተኞችን እያሰለጠነ እንዲሁም በፈጠራና በእውቀት የሚመራ ኢኮኖሚ መገንባት የሚያስችሉ የቴክኖሎጂ ውጤቶችን እያወጣ ነው ብለዋል።
በየዓመቱ 10 ሺህ ተማሪዎችን እያሰለጠነ የሚገኘው የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩቱ፤ ዘመኑን የዋጁ ቴክኖሎጂስቶች መፍለቂያ እየሆነ መምጣቱንም መጥቀሳቸውን ኢዜአ ዘግቧል።
የኢፌዴሪ ቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ብሩክ ከድር (ዶ/ር) በበኩላቸው፥ የሀገርን ሁለንተናዊ ብልጽግና የሚያሳካ ብቁ የሰው ኃይል ስልጠና እና ምርምር ዋነኛ ትኩረታችን ነው ብለዋል።
በዚህም የኢትዮጵያን ግብርና፣ ጤና፣ ቱሪዝም፣ ኢንፎርሜሽን ኮሙኒኬሽን ቴክኖሎጂ፣ ኮንስትራክሽንና ሌሎች ዘርፎችን ይበልጥ የሚያዘምኑ በርካታ ቴክኖሎጂዎች በኢንስቲትዩቱ መፈጠራቸውን አንስተዋል።

👍23❤12
79 አባላት ያሉት የሳውዲ አረቢያ ከፍተኛ የቢዝነስ ልዑክ አዲስ አበባ ገባ
**********
በሳውዲ አረቢያ የንግድ ምክር ቤት ፌዴሬሽን የተመራ 79 አባላትን የያዘ የሳውዲ አረቢያ የኢንቨስትመንት እና የንግድ የልዑካን ቡድን ኢትዮጵያን ለመጎብኘት ማምሻውን አዲስ አበባ ገብቷል።
ጉብኝቱ የሁለቱን ሀገራት ኢኮኖሚያዊ ትስስር ለማጠናከር ያለመ ሲሆን፤ ልዑኩ በአዲስ አበባ በሚኖረው የሶስት ቀናት ቆይታም ስትራቴጂያዊ ጠቀሜታ ያላቸውን የማምረቻ ቦታዎችን እንደሚጎበኝ ይጠበቃል።
በተጨማሪም የኢትዮ-ሳውዲ አረቢያ የቢዝነስ የምክክር መድረክ እንደሚካሄድ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ አመልክቷል።
በኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤትና በሳውዲ አረቢያ አቻው መካከል የመግባቢያ ስምምነት ይፈረማል ተብሎም ይጠበቃል።

👍52❤20
172 ፍልሰተኞች ከጅቡቲ ወደ ኢትዮጵያ ተመለሱ
***************
172 ፍልሰተኞች ከጅቡቲ ወደ ኢትዮጵያ መመለሳቸውን በጅቡቲ የኢትዮጵያ ኤምባሲ አስታወቀ።
ኤምባሲውና የዓለም አቀፍ ፍልሰተኞች ድርጅት (አይ ኦ ኤም) በትብብር በሦስት ዙር 172 መደበኛ ያልሆኑ ፍልሰተኞችን በዚህ ሣምንት በአውሮፕላንና በባቡር ወደ ሀገራቸው መመለስ መቻሉ ተገልጿል።
የኢትዮ-ጅቡቲ-የመን መንገድ እጅግ አደገኛ ከመሆኑም በላይ በድንበር ተሻጋሪ ሕገ-ወጥ ቡድኖች ምክንያት ዜጎች ለድብደባ፣ እንግልት፣ ዘረፋ እንዲሁም ሞት እየተዳረጉ እንደሚገኙ ኤምባሲው ባወጣው መረጃ አስገንዝቧል።
ለዚህም ዜጎች ራሳቸውን እና ቤተሰቦቻቸውን ከዚህ መሰል አደጋ ለመጠበቅ ከሚመለከታቸው ተቋማት ጋር በትብብር በመስራት የጋራ ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ ጠይቋል።

👍32❤7
ሕጉ ምን ይላል - ውለታና ስጦታ
****************
‘‘…ውለታስ ይሄው ነው ወይ?
ብድርስ ይሄው ነው ወይ?
ወረታስ ይሄው ነው ወይ?
ሰው አልወጣልኝም እኔስ አወይ አወይ!! ’’
ይህ የኬኔዲ መንገሻ ዘፈን አዝማች የዛሬውን ውለታ እና ስጦታን በተመለከተ ሕጉ ምን እንደሚል የምናይበት ፅሑፍ መግቢያ አድርገነዋል።
እማሆይ ወለተገብርኤል የዚህችን ዓለም ነገር በቃኝ ብለው ከመመንኮሳቸው በፊት ከሟች ባለቤታቸው ጋር ከነበራቸው የእርሻ መሬት ላይ ድርሻቸው የሆነው 1.65 ሄክታር ይደርሳቸዋል። ሆኖም ‘የእንጀራ ልጄ ባል’ ነው ያሉት ግለሰብ መሬታቸውን በጉልበት ይዞ መጠቀም ጀመረ።
ይሄኔ ነበር አቶ ደረጀ እማሆይ ረዳት ማጣታቸውን አይቶ የቀረባቸው። ይዞታቸውንም ከግለሰቡ ተከላክሎ ረዳት አለኝታ ሆናቸው። ወደ አንድ ቤተክርስቲያን ወስዷቸው በእማሆይ አባባል ‘‘አብረን እንበላለን ልጄ ነው ብለሽ ፈርሚ’’ ብሎ የሆነ ሰነድ ላይ አስፈረማቸው።ይህ የሆነው በ1998 ዓ.ም የመጋቢት 23 ቀን ነበር።
ከዚያም አቶ ደረጀ መሬቱን እያረሰ እማሆይንም እየረዳቸው ቆይቶ። ከአንድ ዓመት በኋላ ምን እንደነካው እንጃ….. እማሆይ እንደሚሉት ‘‘አቅመ ደካማ መሆናቸውን አይቶ’’ እርዳታውን ያቋርጣል።
እማሆይም እድሜያቸው የገፋ አቅመ ደካማ በመሆናቸው የሚረዳቸው አጥተው ተራቡ። ሌላ አማራጭ ሲያጡም ወደ ቤተ ክርስቲያን ገብተው ተጠለሉ።
ለውለታቸው ለሰጡት መሬት ቀለብ እንኳን ተነፈጉ። እማሆይ ነገሩን ለፈጣሪ ብቻ ሰጥተው አልተውትም።
https://www.ebc.et/newsdetails.aspx?newsid=6859

👍37❤4
በአዲስ አበባ ከተማ በተካሄደው የምክክር ምዕራፍ የተሰበሰቡ አጀንዳዎች መዳረሻቸው የት ነው?
**************
በኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን አስተባባሪነት በአዲስ አበባ ከተማ በተከናወነው የአጀንዳ ልየታ የምክክር ምዕራፍ መድረክ አጀንዳዎች ከባለድርሻ አካላት መሰብሰባቸው ይታወቃል፡፡
ታዲያ እነዚህ የተሰበሰቡ አጀንዳዎች በምን መልኩ ለሀገራዊ ምክክር ጉባኤ ይቀርባሉ?
• በምክክር ምዕራፉ ከአዲስ አበባ ከተማ የተሰበሰቡ አጀንዳዎች ከፌዴራል፣ ከክልሎች እንዲሁም ከድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ባለድርሻ አካላት ጋር በጋራ ሆነው ለኮሚሽኑ ምክር ቤት ይቀርባሉ፡፡ በተመሳሳይ በሌሎች አማራጮች ከዜጎች የሚመጡ አጀንዳዎችም ለኮሚሽኑ ምክር ቤት ይቀርባሉ፡፡
• ለኮሚሽኑ ምክር ቤት የሚቀርቡትን አጀንዳዎች የኮሚሽኑ ምክር ቤት በሚያዘጋጀው አሰራር ስርዓት መሰረት በየፈርጁ ለይቶ ያዘጋጃቸዋል፡፡
• የተዘጋጁት አጀንዳዎች ለሀገራዊ ምክክር ጉባኤ አመቺ በሆነ መልኩ ኮሚሽኑ በመቋቋሚያ አዋጁ በተሰጠው ስልጣን መሰረት ይቀርጻቸዋል፡፡
• ኮሚሽኑ የቀረጻቸውን የአጀንዳ ስብስቦች ለህዝብ በማሳወቅ እና በሀገራዊ ምክክር ጉባኤው ተሳታፊ የሚሆኑ ባለድርሻ አካላትን በመጋበዝ የመጨረሻ የሆነውን የሀገራዊ ምክክር ጉባኤ ያካሂዳል፡፡
ኢትዮጵያ እየመከረች ነው!
ምንጭ፡-የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን

👍34👎5❤3👏2
ቦይንግ የአፍሪካ ቢሮውን ዋና መቀመጫ በአዲስ አበባ ለመክፈት ለምን ወሰነ? የዓለም አቀፍ አቬሽን ባለሙያው ቃኝቶታል https://www.facebook.com/EBCzena/posts/pfbid02DMnZnPnJqD2cJaFXQh6dceuXL2t3KR5gh9R2ECvQCnkpiPQzeQFB4Q5h7pS76ubcl
Facebook
Ethiopian Broadcasting Corporation
ቦይንግ የአፍሪካ ቢሮውን ዋና መቀመጫ በአዲስ አበባ ለመክፈት ለምን ወሰነ? የዓለም አቀፍ አቬሽን ባለሙያው ቃኝቶታል
*******************************
ግዙፉ የአሜሪካ ኩባንያ የሆነው እና ለ150 አገራት የንግድ እና ወታደራዊ የአውሮፕላን ምርት የሚያቀርበው ቦይንግ፤ የአፍሪካ ቢሮውን ዋና...

👍35❤5👎3
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከሲንጋፖር ፕሬዚዳንት ታርማን ሽሙጋርተናም ጋር ተወያዩ
************************
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከሲንጋፖር ፕሬዚዳንት ታርማን ሽሙጋርተናም ጋር ተወያይተዋል፡፡
መሪዎቹ በፕሬዚዳንቱ ጽ/ቤት በኢስታና ተገናኝተው በፓለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ማኅበራዊ ጉዳዮች ላይ መክረዋል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በማኀበራዊ የትስስር ገጻቸው ላይ ከፕሬዚዳንት ታርማን ሽሙጋርተናም ጋር “የሁለትዮሽ ግንኙነታችንን ለማጠናከር እና አዳዲስ የትብብር መስኮችን ለማጠናከር ተስማምተናል” ብለዋል፡፡

👍52❤33👎6
ምርጫ ትክክለኛ የስልጣን ባለቤት ህዝብ መሆኑን የሚያሳይ የህዝብ መሻት መገለጫ ነው - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
*********
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ለህንዱ ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ የእንኳን ደስ አለዎት መልዕክት አስተላልፈዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በመልዕክታቸው፥ "ወዳጄ ናሬንድራ ሞዲ፣ ሰላማዊ የሆነ እና የህዝብን መሻት ያከበረ ምርጫ በማካሄድዎ እንኳን ደስ አለዎት" ብለዋል።
"ይህ በራሱ በሀገሪቱ ዴሞክራሲ እያበበ ስለመሄዱ ግልጽ ማሳያ እና ታላቅ ስኬት ነው" ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ላይ ባሰፈሩት መልዕክት።
አክለውም፥ ምርጫ ትክክለኛ የስልጣን ባለቤት ህዝብ መሆኑን የሚያሳይ፣ የህዝብ መሻት መገለጫ ነው ብለዋል።

👍41❤14👎3👏2
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በደቡብ አፍሪካ የተካሄደው ምርጫ የዴሞክራሲ መርሆዎችን ያከበረ መሆኑን ገለጹ
************
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በደቡብ አፍሪካ የተካሄደው ምርጫ የዴሞክራሲ መርሆዎችን ያከበረ መሆኑን በመጥቀስ፤ ለፕሬዚዳንት ሲሪል ራማፎሳ ያላቸውን የእንኳን ደስ አለዎት መልዕክት አስተላልፈዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት፥ በሀገሪቱ የተካሄደው ምርጫ ፍትሐዊ፣ ግልፅ እና ሰላማዊ እንዲሆን ለሰጡት አመራር ራማፎሳን አድንቀዋል።
ይህም ፕሬዚዳንቱ ለህዝብ ፍላጎት እና ሁሉንም ለሚያስተሳስሩት የዴሞክራሲ እሴቶች መከበር ያላቸውን ቁርጠኝነት የሚያሳይ ነው ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትሩ።

❤38👍20👎7
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) እና ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው በሲንጋፖር የኦርኪድ አበባ በስማቸው ተሰየመላቸው
***********
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) እና ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው በሲንጋፖር የመጀመሪያ ቀን ጉብኝታቸው፥ በብሔራዊው የእፅዋት ማዕከል ባህላዊውን እፅዋት የመሰየም ሥነሥርዓት ተካፍለዋል።
በሥነሥርዓቱም በኢትዮዽያ እና በሲንጋፖር መካከል ያለውን መልካም ወዳጅነት እና የጋራ መንፈስ ለማመላከት ‘አራንዳ ዐቢይ አሕመድ፣ ዝናሽ ታያቸው' የተሰኘ የኦርኪድ አበባ በስማቸው እንደተሰየመላቸው ከጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

👍24❤9👎5