EBC (Ethiopian Broadcasting Corporation) – Telegram
EBC (Ethiopian Broadcasting Corporation)
138K subscribers
38.2K photos
458 videos
80 files
13.1K links
EBC (Ethiopian Broadcasting Corporation) @etvafaanoromoo1
@ETVkidschannel
@EBCWORLD1
@etventertainment1
Download Telegram
የተፈጥሮም ሆነ የሰው ሰራሽ አደጋዎችን በራስ አቅም ለመቋቋም መስራት ያስፈልጋል፡- ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ
*****************

ከተረጅነት በመላቀቅ የሚያጋጥሙ የተፈጥሮም ሆነ የሰው ሰራሽ አደጋዎችን በራስ አቅም ለመቋቋም መስራት ያስፈልጋል ሲሉ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ተናገሩ።

የአደጋ ስጋት ሥራ አመራር ምክር ቤት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ በተገኙበት ውይይት እያካሄደ ነው፡፡

አደጋ በየትኛውም ወቅትና ጊዜ አይቀሬ ስለመሆኑ የተናገሩት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ ሰዎች ከተፈጥሮ ጋር በሚያደርጉት የተዛባ ግንኙነት ቁጥሩ እየጨመረ ስለመሆኑ አንስተዋል፡፡

በመሆኑም አደጋን የማስተዳደርና በራስ አቅም የመቋቋም ስራዎች ላይ በትኩረት እየተሰራ ስለመሆኑ ነው የተናገሩት፡፡https://www.facebook.com/EBCzena/posts/pfbid0EeVFxiCWx24VwdVNhM6UEr3cEaLhwQUpgyyaLsE6zMn89CnurKRB336dqAf1oA2Fl
👍451
የምክክሩ ባለድርሻዎች የትኞቹን አካላት ወክለው ተሳተፉ?

የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በአዲስ አበባ ከተማ ባከናወነው የምክክር ምዕራፍ ሂደት ውስጥ የተለያዩ ባለድርሻ አካላት ተሳታፊ ሆነዋል።

ለመሆኑ እነዚህ የባለድርሻ አካላት ወኪሎች የትኞቹን አካላት ወክለው ተሳተፉ?

1. የህብረተሰብ ክፍሎች ተወካዮች
• ከየወረዳው የተለያዩ የሕብረተሰብ ክፍሎችን እንዲወክሉ የተመረጡ ተወካዮች

2. የፖለቲካ ፓርቲዎች ተወካዮች
• በአዲስ አበባ ከተማ እና በሀገር አቀፍ ደረጃ የተመዘገቡ የፖለቲካ ፓርቲዎች

3. የተቋማት እና ማህበራት ተወካዮች (በአዲስ አበባ ከተማ የተመዘገቡ)
• የሃይማኖት ተቋማት
• ሲቪል ማህበራት
• የአሰሪዎች ማህበራት
• የሰራተኞች ማህበራት ኮንፌዴሬሽን
• የመምህራን ማህበር
• የአካል ጉዳተኞች ማህበራት
• የሙያ ማህበራት
• የቀድሞው ሠራዊት ማህበር (ተቀናሽ ሠራዊት ማህበር)
• የጋዜጠኞች ማህበር
• የዩኒቨርሲቲ መምህራን (የመንግሥት እና የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት)
• የንግድ ማህበራት ምክር ቤት
• የሴቶች እና ወጣቶች ማህበራት

4. የመንግሥት ተወካዮች (በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ ያለው ሕግ አውጪ፣ ሕግ አስፈፃሚ እና ሕግ ተርጓሚ)
• የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር
• የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክር ቤት
• የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፍርድ ቤት ዳኞች
• የአዲስ አበባ ከተማ ሲቪል ሰርቪስ ሰራተኞች
• የአዲስ አበባ ከተማ ፓሊስ ኮሚሽን

5. የተፅዕኖ ፈጣሪ ግለሰቦች ተወካዮች
• በተለያዩ ዘርፎች በህዝብ ዘንድ ቅቡልነት ያላቸው፣ አንቱታን ያተረፉ እና ተፅዕኖ መፍጠር የሚችሉ ግለሰቦች

ምንጭ፦ የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን

ኢትዮጵያ እየመከረች ነው!
👍305
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ርክበ ካህናት የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ-ጉባኤ ተጠናቀቀ
***************

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ርክበ ካህናት የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ-ጉባኤ ተጠናቀቀ።

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ የምልዓተ-ጉባኤውን መጠናቀቅ በማስመልከት መግለጫ ሰጥተዋል።

በመግለጫቸውም፤ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ወቅታዊ ጉዳዮችን አስመልክቶ የሚተላለፉ አንዳንድ መልዕክቶች ቤተ ክርስቲያንን የማይወክሉና ቅዱስ ሲኖዶስ የማይቀበላቸው እንዲሁም በጥብቅ የሚያወግዛቸው መሆናቸውንም ገልጸዋል፡፡

ቅዱስ ሲኖዶስ ለቤተክርስቲያንና ለሀገራችን ህዝቦች ጠቃሚ ውሳኔ አሳልፏል ብለዋል በመግለጫቸው፡፡

በቅዱሳት መጻሕፍት ላይ ተመሥርቶ አባታዊ ምክርና ተግሣጽ ማስተላለፍ ከቀድሞ ጀምሮ የነበረ መጽሐፍ ቅዱሳዊ መሠረት ያለው መሆኑን አንስተው፤ ይሁን እንጂ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ወቅታዊ ጉዳዮችን አስመልክቶ የሚተላለፉ አንዳንድ መልዕክቶች ቤተ ክርስቲያንን የማይወክሉና ቅዱስ ሲኖዶስ የማይቀበላቸው እንዲሁም በጥብቅ የሚያወግዛቸው ናቸው ብለዋል፡፡https://www.facebook.com/EBCzena/posts/868771235277057
👍335👎3👏2
ምን እንጠይቅልዎ??
👍26👎5
ከተረጂነት እንውጣ የሚል አብዮት መቀስቀስ አለብን ፡- ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ
********************

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ከተረጂነት እንውጣ የሚል አብዮት መቀስቀስ አለብን ሲሉ ገለጹ፡፡

በማኅበራዊ ትስስር ገፃቸው ባሰፈሩት ፅሑፍ ተፈጥሯዊም ይሁን ሰው ሰራሽ አደጋ አይቀሬ ነው ያሉት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ ለዚህ ደግሞ አደጋን በራስ አቅም የማስተዳደር እና የመሸከም አቅምን ማጎልበት እንደሚገባ ነው የገለጹት፡፡

ዛሬ ባካሄዱት የአደጋ ስጋት ስራ አመራር ምክር ቤት መደበኛ ስብሰባም፤ በአዲስ መልክ የፀደቀውን የአደጋ ስጋት ስራ አመራር ፖሊሲ ማስፈንጠሪያዎችና የትግበራ ጉዳዮች ላይ ተወያይተናል ብለዋል፡፡

አያይዘውም የ2016 በጀት ዓመት የአደጋ ስጋት ሥራ አመራር ዕቅድ አፈጻጸምን መገምገማቸውን ጠቁመዋል፡፡

የአደጋ ስጋት ስራዎች በሙሉ አቅም ለመፈፀም የባህል ለውጥ ያስፈልጋል ያሉት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ ይህን የባህል ለውጥ ለማምጣት ደግሞ ልመናን የሚፀየፍ ትውልድን መፍጠር፣ የቆየውን የመደጋገፍና የመረዳዳት ማህበራዊ ዕሴት በማጠናከር እና በማጎልበት ራስን መቻል ያስፈልጋል ሲሉ ገልጸዋል፡፡

በዓድዋ ጊዜ የነበረንን የአርበኝነት ወኔ እና ተነሳሽነት ድህነትን ለማሸነፍ መጠቀም ይኖርብናል፤ ለዚህ ደግሞ እንደ ሀገር የጀመርናቸውን ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ልማቶች ማፋጠን ወሳኝ ነው ሲሉ አስገንዝበዋል፡፡https://www.facebook.com/EBCzena/posts/pfbid02uAhxUS2aG7JKaHXXjvDgQbEbqMPQRqbHU8FsVUvjYdWNUuoy4RbbDQqC3ntPfXF3l
👍4311👏5👎4
የዲፕሎማሲ ማዕከሏ - ጄኔቫ
*****************

በውብ ገጽታዋ የምትታወቀው የስዊዘርላንዷ ጄኔቭ ከተማ ስመጥር ዓለም አቀፍ የዲፕሎማሲ መቀመጫ ናት። ከዙሪክ በመቀጠል በሀገሪቱ ሁለተኛዋ ሰፊ የህዝብ ብዛት ያላት ከተማዋ፣ ፈረንሳይኛ ቋንቋ በስፋት ይነገርባታል።

የበርካታ ዓለም አቀፍ ድርጅቶች እና ዲፕሎማሲያዊ ሚሲዮኖች መቀመጫ በመሆን “የሰላም ዋና ከተማ” የሚል መጠሪያ ያገኘችው ጄኔቭ፤ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅትን ጨምሮ ከ40 በላይ ዓለም አቀፍ ተቋማትን በውስጧ ይዛለች።

ከእነዚህም ውስጥ ዓለም አቀፉ የቀይ መስቀል ኮሚቴ፣ የዓለም የጤና ድርጅት፣ የዓለም የንግድ ድርጅት፣ ዓለም አቀፉ የሥራ ድርጅት፣ የተባበሩት መንግሥታት የስደተኞች ከፍተኛ ኮሚሽን እና ዓለም አቀፉ የቴሌኮሙኒኬሽን ህብረት ይጠቀሳሉ።
https://ebc.et/newsdetails.aspx?newsid=6881
👍174
Live stream finished (3 days)
በአዲስ አበባ የተሽከርካሪ የጭስ ብክለት ልቀት መጠን ደረጃ የአፈጻጸም መመሪያ ተዘጋጀ
*************

መመሪያውን ያዘጋጀው የአዲስ አበባ አካባቢ ጥበቃ ባለሥልጣን በሰነዱ ዙሪያ ዛሬ ከባለድርሻ አካላት ጋር ተወያይቷል።

ማንኛውም አሽከርካሪ የተሽከርካሪውን የጭስ ብክለት ልቀት መጠን በወጣው ደረጃ (ስታንዳርድ) አሟልቶ መንቀሳቀስ እንዳለበት በተዘጋጀው መመሪያ ተመላክቷል።

አሽከርካሪዎች የተሽከርካሪን የጭስ ብክለት ልቀት መጠን ሊቀንሱ የሚችሉ አማራጭ የቴክኖሎጂ ወጤቶችን ጥቅም ላይ ማዋል እንደሚገባቸው ተጠቅሷል።

የተሽከርካሪውን የጭስ ብክለት ልቀት መጠን በየዓመቱ የማስመርመር ግዴታ እንዳለባቸውም ተጠቁሟል።

ድንገተኛ የጭስ ብክለት ልቀት መጠን ፍተሻ በሚደረግበት ጊዜም ተሽከርካሪውን የማስመርመር ግዴታ እንዳለባቸው ተመላክቷል።

የአዲስ አበባ አካባቢ ጥበቃ ባለሥልጣን ዋና ሥራ አስኪያጅ ዲዳ ድሪባ በውይይ መድረኩ እንደገለጹት፥ መመሪያው ከተሽከርካሪ የሚወጣውን የጭስ ብክለት ለመቀነስ የሚያስችል ነው።

ሰነዱ በዘርፉ ፍትኃዊና ተጠያቂነት ያለበት፣ ግልጽና ቀልጣፋ የክትትልና የቁጥጥር ሥርዓት ለመዘርጋት የሚያግዝ መሆኑንም ነው የጠቆሙት።

ይህም የአየር ብክለትን በመከላከል በጤና ላይ የሚደርሰውን አሉታዊ ተጽዕኖ ለማስቀረት እንደሚያስችል ተናግረዋል።

የበካይ ጋዝ ልቀት መቀነሻ ቴክኖሎጂን በመጠቀም የተሽከርካሪዎችን የነዳጅ ፍጆታ ለመቀነስ እንደሚያግዝም ገልጸዋል።

ይህም የሀገሪቱን የውጭ ምንዛሬ ወጪ ለመቀነስ እንደሚያስችልም ጠቁመዋል ሲል ኢዜአ ዘግቧል።
👍248👎5👏1
የኢትዮጵያ ልዑካን ቡድን በ3ኛው የብሪክስ አባል ሀገራት ተወካዮች ስብሰባ ላይ እየተሳተፈ ነው
***********

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገዥ እና በብሪክስ የኢትዮጵያ ዋና ተወካይ አቶ ማሞ ምህረቱ የተመራ የኢትዮጵያ ልዑካን ቡድን ዛሬ በሩስያ በጀመረው 3ኛው የብሪክስ የአባል ሀገራት ተወካዮች ስብሰባ ላይ እየተሳተፈ ይገኛል።

አቶ ማሞ በስብሰባው ላይ ባደረጉት ንግግር፥ በተለዋዋጭ እና ሊተነበይ በማይቻል የዓለም ኢኮኖሚ እና ፖለቲካ ምኅዳር ውስጥ ብሪክስ ሀገራትን እና ሃብቶችን በማሰባሰብ ዓለም አቀፍ ተግዳሮቶችን በአጋርነት መንፈስ ለመቅረፍ አረጋጊ ኃይል ሆኖ ሊያገለግል እንደሚችል ጠቅሰዋል።

ኢትዮጵያ የብሔራዊ የብሪክስ ተሳትፎ ስትራቴጂን በብሔራዊ የሚኒስትሮች አስተባባሪ ኮሚቴ ማፅደቋን ጨምሮ ወደ ብሪክስ ማዕቀፍ በተሳለጠ ሁኔታ መግባቷን ለማረጋገጥ የተወሰዱ እርምጃዎችንም አብራርተዋል።

በብሪክስ አባል ሀገራት መካከል በንግድ፣ ኢንቨስትመንት፣ ቱሪስት ፍሰትና ሌሎች መስኮች ያለውን የኢኮኖሚ ግንኙነት ማሳደግ እንደሚገባ እንዲሁም የልማት ፋይናንስን በመጨመር አካታች እና ዘላቂ ልማትን መደገፍ እንደሚያስፈልግ ገልጸዋል።

አዲሱ የልማት ባንክ ቅድሚያ የሚሰጣቸው ጉዳዮች ከኢትዮጵያ የልማት ትልሞች ጋር የተጣጣሙ በመሆናቸው ኢትዮጵያ በተቻለ ፍጥነት ወደ ባንኩ ትቀላቀላለች ብለው እንደሚጠብቁም ተናግረዋል።

ስብሰባው ከሰኔ 3-4 ቀን 2016 ዓ.ም ለሚካሄደው የብሪክስ አባል ሀገራት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ስብሰባ ግብዓት የሚሆኑ የተለያዩ አጀንዳዎች ላይ መምከር መቀጠሉን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
👍5423👏6