ኢትዮጵያ የተሳተፈችበት ዓለምአቀፉ የክህሎት ኦሎምፒክ ውድድር መካሄድ ጀመረ
*****************
ኢትዮጵያ በሁለቱም ፆታዎች ተወክላ የተሳተፈችበት የዓለምአቀፉ የክህሎት ኦሎምፒክ ውድድር በፈረንሳይ ትናንት መጀመሩን የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ሙፈሪያት ካሚል በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው አስታውቀዋል።
በ2016 በጀት አመት ከነበሩ በርካታ ስኬቶች ውስጥ አንዱ የሆነው የዓለም ክህሎት ማህበረሰብ አባልነት እንደነበር ሚኒስትሯ አስታውሰዋል።
ኢትዮጵያም በዚህ የክህሎት ኦሎምፒክ በወንዶች እና ሴቶች በሶስት የክህሎት ዘርፎች (ICT and Networking, CNC Machine, Furniture Making) ተወክላ ውድድሩን እየተካፈለች እንደምትገኝ ገልጸዋል።
ውድድሩ የፈረንሳዩ ፕሬዘዳንት ኢማኑኤል ማክሮን በተገኙበት በደማቅ የመክፈቻ ፕሮግራም መጀመሩ ተገልጿል።

👍42❤8
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ናይሮቢ የሚያደርገው በረራ በታቀደለት መርኃ ግብር እየተከናወነ አለመሆኑን አስታወቀ
********************
የኢትዮጵያ አየር መንገድ በኬኒያ ናይሮቢ የሚገኘው የጆሞ ኬንያታ ዓለም አቀፍ ኤርፖርት ሠራተኞች በስራ ማቆም አድማ ላይ በመሆናቸው ምክንያት ወደ ናይሮቢ የሚያደርገው በረራ በታቀደለት መርኃ ግብር እየተከናወነ አለመሆኑን አስታውቋል።
አየር መንገዱ ጉዳዩን በቅርበት እየተከታተለ እንደሚገኝ በመግለፅ በክስተቱ ለተፈጠረው መስተጓጎል ደንበኞቹን ይቅርታ ጠይቋል።
ደንበኞች የበለጠ መረጃ ለማግኘት የዓለም አቀፍ የደንበኞች አገልግሎት ማዕከል ስልክ ቁጥር በ+251 11 617 9900 ወይም በ 6787 በመደወል አልያም ናይሮቢ የሚገኘውን ትኬት ሽያጭ ቢሮ በአካል በመገኘት ማግኘት እንደሚቻል አየር መንገዱ አስታውቋል።

👍50❤14👎3
የኢቢሲ የአዲስ ዓመት ስጦታ
ፍቅር እስከ መቃብር - ክፍል ሁለት
www.youtube.com/watch?fbclid=IwY2xjawFOvgdleHRuA2FlbQIxMQABHdTddAjvUyMoh3e6vo7kZGtAcjpnC6HvGgOjNtryvP23xWIbiayJeH3Bbw_aem_kSYsBhMSBdDfrLFRKcm_9A&v=e-Ps577IOEA&feature=youtu.be

YouTube
ፍቅር እስከ መቃብር - ክፍል ሁለት | Fiker Eske Mekaber Episode 2 Etv | Ethiopia | News zena
ፍቅር እስከ መቃብር - ክፍል ሁለት | Fiker Eske Mekaber Episode 2 #fikereskemekaber #ፍቅርእስከመቃብር #ሀዲስአለማየሁ #ፊልም #በዛብህ #ሰብለ #ሰብለወንጌል #bezabehe #sebele #hadisalemayehu #ebc #etv #ebcnews #EBCTelevision #etvnews #EBCቲቪ #ኢቢሲ #ኢቲቪ #ebc #etv #ebcnews #EBCTelevision…
👍61❤26👏5
አንጋፋው የኢትዮጵያ ሬዲዮ ስርጭት ከጀመረ ዛሬ 89 ዓመት ሞላው
****************
በብሮድካስት መገናኛ ብዙሃን ታሪክ ስሙ ቀድሞ የሚነሳዉ "የኢትዮጵያ ሬዲዮ" አገልግሎት መስጠት ከጀመረ ዛሬ መስከረም 2/2017 ዓ.ም 89 ዓመት አስቆጥሯል፡፡ የኢትዮጵያ ሬዲዮ ስርጭት የጀመረዉ በዛሬዉ እለት መስከረም 2/1928 ዓ.ም ነበር፡፡
የኢትዮጵያ ሬዲዮ ታሪክ ከዚህ ይጀምራል፡-
"ግርማዊ ቀዳማዊ ሃይለ ስላሴ ንጉሰ ነገስት ዘኢትዮጵያ በነገሱ በሁለተኛዉ አመት ኢትዮጵያን ከአለም መንግስታት ጋር የሚያገናኝ "ያለ ሽቦ ቃል የሚያሳልፍ መኪና" የሚቆምበት ቤት ሲመሰረት በሀምሌ 14 ቀን 1923 ዓ.ም የመጀመሪያዉን የማእዘን ድንጋይ አኖሩ"
ቀዳማዊ ሃይለ ስላሴ የሬዲዮ ጣቢያ በኢትዮጵያ ለማቋቋም ስራ ሲጀምሩ ቴክኖሎጅዉ በአለም ላይ ገና ለጋ ነበር፡፡
በአዲስ አበባ ንፋስ ስልክ በሚባለዉ አካባቢ በ1923 ዓ.ም መሰረት የተጣለለት የሬዲዮ ጣቢያ ግንባታ በታህሳስ ወር 1927 ዓ.ም ተጠናቆ በአመቱ አገልግሎት መስጠት ጀመረ፡፡
ቀዳማዊ ሃይለ ስላሴ "ይህ የምትሰሙት ድምፅ የእኔ የንጉሳችሁ ቀዳማዊ ሃይለ ስላሴ ነዉ" በማለት የመጀመሪያዉን መልዕክት በሬዲዮ ጣቢያዉ አሰሙ፡፡
https://www.facebook.com/EBCzena/posts/pfbid02167v3QyFdWwqUZcVpS1qzhz5CJpRqymEcuSgnoscripteBuKN5ArZ8SUBaKUmFkpcc3PBl

Facebook
Log in or sign up to view
See posts, photos and more on Facebook.
👍33❤14
ኢትዮ-ቴሌኮም እና የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት በተለያዩ ጉዳዮች ላይ በጋራ ለመስራት ተስማሙ
**********
የኢሚግሬሽን እና ዜግነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ሰላማዊት ዳዊት እና የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ስራ አስፈፃሚ ፍሬህይወት ታምሩ እንዲሁም የሁለቱ ተቋማት የስራ ሃላፊዎች በተገኙበት በትብብር ለመስራት በሚያስችሉ ጉዳዮች ዙሪያ ምክክር መደረጉን ከአገልግሎቱ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።
የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገለልግሎት የሚሰጣቸውን አገልግሎቶች ከማዘመን አኳያ፣ ከእጅ ንክኪ ነፃ አገልግሎት መስጠትን ጨምሮ የውስጥ አሰራሮችን ከማዘመንና ቀልጣፋ የደንበኞች አገልግሎት አሰጣጥ ስርዓትን ከመዘርጋት አንፃር ከኢትዮ ቴሌኮም ጋር በትብብር ለመስራት ከስምምነት መደረሱን የተቋሙ ዋና ዳይሬክተር ሰላማዊት ዳዊት ተናግረዋል።
የኢትዮ-ቴሌኮም ዋና ስራ አስፈፃሚ ፍሬህይወት ታምሩ በበኩላቸው፥ ዲጂታል ኢትዮጵያን እውን በማድረግ አኳያ ተቋማቸው የተሰጠውን ሃላፊነት በብቃት እየተወጣ መሆኑን ጠቅሰው፤ የትብብር ስምምነቱ የዲጂታላይዜሽን አተገባበርን ለማላቅ ትልቅ ዕድል የሚሰጥ መሆኑን ጠቁመዋል።

👍44❤1
Forwarded from ETV መዝናኛ
የኢቢሲ የአዲስ ዓመት ስጦታ
ፍቅር እስከ መቃብር ክፍል ሁለት ከደቂቃዎች በኋላ በኢቢሲ
************
በጉጉት የሚጠበቀው ፍቅር እስከ መቃብር ተከታታይ ፊልም ዛሬ ከቀኑ 08፡00 ሰዓት ጀምሮ በኢቢሲ ዜና እና በኢቢሲ መዝናኛ ቻናሎች ይተላለፋል።
ፊልሙን ባመቸዎት ጊዜ ለመመልከት የኢቢሲ ወርልድ የዩቲዩብ ቻናልን https://www.youtube.com/@EBCworld ሰብስክራይብ ያድርጉ።

👍22❤11👏11