በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በዘንድሮው የበጋ መስኖ ከ35 ሚሊዮን ኩንታል በላይ ምርት ለማግኘት ይሰራል፡- የክልሉ ግብርና ቢሮ
*****************
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በዘንድሮው የበጋ መስኖ ስራ 146 ሺህ ሄክታር ማሳን በማልማት ከ35 ሚሊዮን ኩንታል በላይ ምርት ለማግኘት እንደሚሰራ የክልሉ ግብርና ቢሮ ገልጿል።
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ግብርና ቢሮ የ2017 ዓመት የበጋ የተቀናጀ ግብርና ልማት ንቅናቄ መድረክ በዱራሜ ከተማ እያካሄደ ነው።https://www.facebook.com/EBCzena/posts/pfbid02ZPCG9ByoSgqVFYvPD64U2cJoeMKwk1fmgc2HsTa8eFMMTa9sBkRJwLbDQaJ5gdJtl

👍22❤4
ገዳ በዲሞክራሲ ዕሴቶች የበለጸገ አንድነትና ኅብረት የነገሰበት ስርዓት ነው - ከንቲባ አዳነች አቤቤ
**************************
“ገዳ በዲሞክራሲ ዕሴቶች የበለጸገ አንድነትና ኅብረት የነገሰበት ስርዓት ነው” ሲሉ የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ተናግረዋል፡፡
ከንቲባዋ የገዳ ስርዓት አንዱ መገለጫ የሆነው ኢሬቻም ህዝቡ የሚገናኝበት፤ ምስጋና የሚያቀርብበትና መልካም ምኞቱን የሚገልጽበት መሆኑን አንስተዋል።
ኢሬቻ የምስጋና፣ የሰላም፣ የይቅርታ፣ የአብሮነትና የወንድማማችነት እንዲሁም ባህላዊ እሴቶች የሚንጸባረቁበት በዓል መሆኑንም ጠቁመዋል፡፡
በዓሉ የብሔር ብሔረሰቦችን የወንድማማችነትና የእህትማማችነት ትስስር ይበልጥ እያጠናከረ መሆኑን በመግለጽም ኢሬቻ ለቱሪዝም መስህብ እየሆነ መምጣቱን አስታውቀዋል፡፡
የኢሬቻን በዓል ለማክበር ከተለያዩ አካባቢዎች የሚመጡ እንግዶችን ተቀብሎ እያስተናገደ ለሚገኘው የአዲስ አበባ ከተማ ህዝብም ከንቲባ አዳነች አቤቤ ምስጋና አቅርበዋል።
በከተማዋ የተሰሩ የኮሪደር ልማት ሥራዎች ለበዓሉ ተጨማሪ ድምቀት መፍጠራቸው የዘንድሮውን የኢሬቻ በዓል ልዩ እንደሚያደርገው መናገራቸውንም ኢዜአ ዘግቧል፡፡
ስድስተኛው የኢሬቻ ፎረም "ኢሬቻ ለባህላችን ሕዳሴ" በሚል መሪ ሃሳብ በአዲስ አበባ እየተካሄደ ይገኛል፡፡

❤23👍8👎7
በመዲናዋ እስከ ሰኞ ማለዳ 12 ሠዓት ድረስ የሞተር ብስክሌት ማሽከርከር ተከለከለ
*******************
በአዲስ አበባ ከዛሬ 6 ሠዓት ጀምሮ እስከ ሰኞ ማለዳ 12 ሠዓት ድረስ የሞተር ብስክሌት ማሽከርከር ተከልክሏል፡፡
ክልከላው የተላለፈው ለኢሬቻ በዓል አከባበር የመንገድ ትራንስፖርት ደኅንነትን ለማስጠበቅ መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትራንስፖርት ቢሮ አስታውቋል፡፡
ቢሮው እስከ ፊታችን ሰኞ መስከረም 27 ቀን 2017 ዓ.ም የሚቆየውን ክልከላ የትራንስፖርትና የትራፊክ ተቆጣጣሪዎች እንዲሁም የትራፊክ ፖሊሶች አፈፃፀሙን ተግባራዊ እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርቧል፡፡

👍8👏4
አሜሪካ የኢትዮጵያን ግብርና ምርታማነትን ለማሳደግ የተለያዩ ድጋፎችን ለማድረግና በትብብር ለመስራት ዝግጁ ናት፡- አምባሳደር ኤርቪን ማሲንጋ
*********************
አሜሪካ የኢትዮጵያን የግብርና ዘርፍ ለማዘመንና ምርታማነትን ለማሳደግ በሚደረገው እንቅስቃሴ ውስጥ የተለያዩ ድጋፎችን ለማድረግና በትብብር ለመስራት ዝግጁ መሆኗን በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር ኤርቪን ማሲንጋ ገልጸዋል።
የግብርና ሚኒስትር ግርማ አመንቴ (ዶ/ር) በኢትዮጵያ ከአሜሪካ አምባሳደር ኤርቪን ማሲንጋ ጋር ኢትዮጵያ በግብርናው ዘርፍ ከአሜሪካ መንግስት ጋር በትብብር በምትሰራባቸው ጉዳዩች ላይ ተወያይተዋል።https://www.facebook.com/EBCzena/posts/pfbid027Ep5u9V72n8GhxwVVGXzwrgZjJuQfJp7p2q3jidhS53d5N2zpBHcF8D4JrwtbFoLl

Facebook
Ethiopian Broadcasting Corporation
አሜሪካ የኢትዮጵያን ግብርና ምርታማነትን ለማሳደግ የተለያዩ ድጋፎችን ለማድረግና በትብብር ለመስራት ዝግጁ ናት፡- አምባሳደር ኤርቪን ማሲንጋ
*********************
አሜሪካ የኢትዮጵያን የግብርና ዘርፍ ለማዘመንና ምርታማነትን ለማሳደግ በሚደረገው እንቅስቃሴ ውስጥ የተለያዩ ድጋፎችን ለማድረግና በትብብር...

👍12👏3❤2
ዛሬ የ2017 የኢሬቻ ፎረም አካሂደናል።
6ኛው ዙር የኢሬቻ ፎረም አባ ገዳዎችና ሀደ ሲንቄዎች፣ አምባሳደሮች፣ የዲፕሎማቲክ ማህበረሰብ አባላት፣ የፌደራል፣ ክልልና ከተማ አስተዳደር ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች፣ ፎሌዎች፣ ዲያስፖራዎች እንዲሁም የከተማችን ነዋሪዎች በተገኙበት በዓድዋ ድል መታሰቢያ በድምቀት አካሂደናል።
ሀገራችን ኢትዮጵያ የብዝሃ ማንነቶች ባለ ፀጋ እንደመሆኗ መጠን ህዝባዊ እና ኃይማኖታዊ በዓላት አንድነትን፣ ፍቅርንና የህዝቦች ትብብርን በማፅናት ረገድ አይነተኛ ሚና የሚጫወት ሲሆን የኢሬቻ በዓል የሰላም፣ የእርቅ፣ የአንድነት፣ የአብሮነት እንዲሁም የወንድማማችነትና እህትማማችነት በዓል ሆኖ በመከበር ላይ ይገኛል።
ኢሬቻ የገዳ ስርዓት አንዱ ምሰሶ ሲሆን የምስጋና፣ የሰላም እና የወንድማማችነት ተምሳሌት ሆኖ የኦሮሞ ህዝብ ከጥንት ጀምሮ ከፈጣሪ፣ ከተፈጥሮ እና ከሰው ሁሉ ጋር ያለውን ግንኙነት የሚያድስበት ነው።
በኢሬቻ የተራራቀ ይቀራረባል፤ የተቀያየመም ይታረቃል።
https://www.facebook.com/EBCzena/posts/pfbid0GXf28LFH3EBC79miSMdmfUGLk2i9DyXvbiE6s3bDgvLNPQxvwBBgJ864MaHC1Spql?cft[0]=AZXvyoIz0E9QkVtDPr5lo-9BllbD9prGWUQ-7f1W-GwPfuYxGbnYl16i7_PVQwjdlfluhT0s1DzZkLWxemqLmIqJcOG27bBq2QwwmnRPnfn3TwSIfzqQFQsaWOD53XR_1pRKizkudSLx8j7SLJKa5Ep_MCrfdfxxoz9ph-WPNFPI6g&tn=%2CO%2CP-R

👍23❤7👎5
ለኢሬቻ በዓል የትራንስፖርት እጥረት እንዳያጋጥም በቂ ዝግጅት ተደርጓል - የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር
****************************
የኢሬቻ በዓልን ለማክበር ወደ አዲስ አበባ እና ቢሾፍቱ ለሚጓዙ የበዓሉ ተሳታፊች የትራንስፖርት እጥረት እንዳያጋጥም በቂ ዝግጅት መደረጉን የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡
ሚኒስቴሩ ኢሬቻን ለማክበር ወደ ከተሞቹ ለሚጓዙ የበዓሉ ተሳታፊዎች ከፐብሊክ ሰርቪስ ትራንስፖርት አገልግሎትና ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትራንስፖርት ቢሮ ጋር በመቀናጀት በቂ የትራንስፖር ዝግጅት ማድረጉን ገልጿል፡፡
በአዲስ አበባ በአምስቱም መግቢያ በሮች ወደ በዓሉ ማክበሪያ ቦታ የሚያደርሱ ከአዲስ አበባ ሲቲ ባስ 907 የከተማ አውቶቡሶች እንዲሁም 400 የፐብሊክ ሰርቪስ ትራንስፖርት አውቶቡሶች መዘጋጀታቸውንም ጠቁሟል፡፡
በቢሾፍቱ ለሚከበረው የኢሬቻ በዓልም 150 ሀገር አቋራጭና መለስተኛ አውቶቡሶች መዘጋጀታቸውን አመላክቷል፡፡
በአጠቃላይ ታክሲዎችን ሳይጨምር ለበዓሉ አገልግሎት የሚሰጡ 1 ሺህ 457 ተሽከርካሪዎች መዘጋጀታቸውን ከሚኒስቴሩ የተገኘው መረጃ ያሳያል፡፡

👍18❤14👎11👏2
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ለ2017 ዓ.ም የኢሬቻ በዓል የእንኳን አደረሳችሁ የመልካም ምኞት መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡
የመልዕክቱ ሙሉ ቃል እንደሚከተለው ይቀርባል፡፡
****************************
የተከበርከው የኦሮሞ ሕዝብ ሆይ እንኳን አስቸጋሪውን የክረምት ወቅት አልፈህ ለብሩሁ ብራ ተሸጋገርክ!
ኢሬቻ ዕርቅ ነው፤ ፈጣሪ ደግሞ ዕርቅ ይወዳል። የተጣሉ ሰዎች ቂም ይዘው ለኢሬቻ ወደ መልካ አብረው አይወርዱም። ኢሬቻ መትረፍረፍ ነው! ኢሬቻ ምስጋና ነው! ኢሬቻ ልምላሜ ነው!
ለምለም ሣር ክብርን ፣ ፍቅርን እና መልካም ምኞትን ይወክላል። ብራ ሽግግር ነው፤ ያለፈውን ወደኋላ ትተን ወደ አዲስ ተስፋ በንጹሕ ኀሊና እንሻገራለን፡፡ ከሕዝቡ እሴት ውስጥ ጎልቶ የሚታየውም ይህ ነው። ኢሬቻ አንድነት ነው። ኢሬቻ ኅብረት ነው። ከኢሬቻው መልካ የሚቀርም ሆነ ወደ ኋላ የሚል የለም። አባቶችና እናቶቻችን አቆይተው ያወረሱን እሴት ማዳላት የለውም። ሰው ሁሉ እኩል ነው።https://www.facebook.com/EBCzena/posts/pfbid02bEL6g1NiBCN1i2sdmHNKdcRg5yUeGRvSCMyzbHXneu7W6NFTPUkXbubeaQojN6Wzl?cft[0]=AZWHmKRdmvlDjRcoVO8IYeLnKAhksg1svHIv4HJI1pprZErYWIzh38MsSWdgH5cqtLZ63n8IZVl48BYtLNm0q9ruGOcZQSPxsCqCslPdmG2gn81wqjMCIc8-tFZ7uWNM76GhOA6rJ6dWCLbCc8iDzhoJ&tn=%2CO%2CP-R

👍42👎14❤10
እንኳን ለ2017 ዓ.ም የኢሬቻ በዓል በሰላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን ፡- ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ
*******
የሰላም፣ የአንድነትና የብራ ንጋት መልካም ምኞት ምልክት የሆነው ኢሬቻ፤ የኦሮሞ ህዝብ በጋራ ወጥቶ ፈጣሪውን የሚያመሰግንበት ትልቅ በዓል ነው።
ዝናብ ሰጥቶ ያበቀለውን ፈጣሪ፣ የክረምቱን ጎርፍና በረዶ በሰላም አሳልፎት ብሩህ በሆነና በተስፋ ወደ ተሞላው ብራ ያሻገረውን ፈጣሪ፤ ለማመስገን ወደ መልካ (ወንዝ) ወጥቶ የኢሬቻን ስርዓት ይፈጽማል።
ብራ ለፍጥረት ሁሉ ልዩ ነው። ለሁሉም የሚተርፍ ነገር አለው። ብራ ምድሩ በልምላሜ ተሞልቶ፣ በአበቦች ውበት አጊጦ፣ ጋራው ሸንተረሩ ዓይንን የሚማርክበት ወቅት ነው። የአበቦች መዓዛ አካባቢን የሚያውድበት ጊዜ ነው።https://www.facebook.com/EBCzena/posts/pfbid0TVUdP2g4AqhPbTaGn38UGztp8CDCWZn8ZqxGhgpE1tVZscjqQ9MokyNw9EcJHbdnl

እንኳን ለ2017 ዓ.ም የኢሬቻ በዓል በሰላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን!
የሰላም፣ የአንድነትና የብራ ንጋት መልካም ምኞት ምልክት የሆነው ኢሬቻ፤ የኦሮሞ ህዝብ በጋራ ወጥቶ ፈጣሪውን የሚያመሰግንበት ትልቅ በዓል ነው።
ዝናብ ሰጥቶ ያበቀለውን ፈጣሪ፣ የክረምቱን ጎርፍና በረዶ በሰላም አሳልፎት ብሩህ በሆነና በተስፋ...

👍24❤5👎4