EBC (Ethiopian Broadcasting Corporation) – Telegram
EBC (Ethiopian Broadcasting Corporation)
137K subscribers
38.4K photos
462 videos
80 files
13.2K links
EBC (Ethiopian Broadcasting Corporation) @etvafaanoromoo1
@ETVkidschannel
@EBCWORLD1
@etventertainment1
Download Telegram
በኢሬቻ በዓላት ላይ በስፋት የሚታየው "ጥቁር፣ ቀይ እና ነጭ" ቀለማት ያሉት ባንዲራ ትርጉም ምንድነው??
*********************

ከላይ ወደ ታች ጥቁር፣ ቀይ፣ ነጭ ቀለማት ያሉት የአባገዳ ባንዲራ

በተለይ በአዲስ አበባ እና በቢሾፍቱ በድምቀት በሚከበሩት የኦሮሞ ሕዝብ የኢሬቻ በዓላት ላይ በሚሳተፉ የበዓሉ ታዳሚዎች እጅ ላይ የማይጠፋው ባንዲራ አስገራሚ የቀለማቱ አደራደር እና ትርጓሜ የሚከተለውን ይመስላል፦

👉ጥቁር መደብ፦ ፈጣሪ የበላይ መሆኑን የሚገልጽ ነው። የኦሮሞ ሕዝብ ራሱ ጥቁር እንደሆነው ሁሉ ፈጣሪው /ዋቃ/ ጥቁር ነው ብሎ ያምናል። ጥቁር ቀለምም በኦሮሞ ሕዝብ ዘንድ የቀዳሚነት መገለጫ ነው። ጥቁሩ ፈጣሪ ያለው ከላይ ነው፤ ዝናብ የሚዘንበው ከላይ ባለው ጥቁር ደመና ነው፣ ራሳችን ላይ ያለው ፀጉር እስኪሸብት ድረስ ጥቁር ነው፤ የዓይናችን ብሌን ጥቁር ነው - የሚገኘውም ከላይ ነው። እናም ጥቁር ቀዳሚ የመሆን መገለጫ ነው።

👉ቀይ መደብ፦ የብቃት፣ ብስል የመሆን፣ ሙሉ ሆኖ የመገኘት እና ለሕዝብ ነፃነት መሥዋዕት የመሆን መገለጫ ነው። ሁሉም ነገር በጊዜው ሙሉ ሆኖ የመገኘት ምሳሌ ነው። የኦሮሞ ሕዝብ አንድ ነገር የብቃት ደረጃው ላይ መድረሱን ሲገልጽ “diimate” /ቀላ/ ብሎ ይገልጻል።

👉ነጭ መደብ፦ የነገሮች ፍፃሜ መገለጫ ነው። እንደ ምሳሌ፦ ጠቁሮ ዝናብ የሚሰጠን ደመና ነጭ ሲሆን አይዘንብም ማለት ነው፤ ጥቁር የነበረው የሰው ፀጉር እርጅና ሲደርስ ይሸብታል (ነጭ ይሆናል)፣ ነዶ ያለቀ እንጨት አመዱ ነጭ ነው … ስለዚህ ነጭ የፍፃሜ መገለጫ ነው ብሎ ያምናል - የኦሮሞ ሕዝብ።

#ኢሬቻ #etv #EBC
👍50👎285👏5
ወደ 8 በመቶ ወርዶ የነበረው በሀገር ውስጥ የተመረተ መድሃኒት የአቅርቦት ድርሻ መንግሥት በወሰደው የፖሊሲ ማሻሻያ እርምጃ ወደ 36 በመቶ ከፍ ሊል ችሏል
*****************

የኢትዮጵያ መድኃኒት እና ሕክምና መገልገያ አምራቾች ማህበር 21ኛ ጠቅላላ ዓመታዊ ጉባኤውን አካሂዷል።

በጉባኤው ላይ የተገኙት የጤና ሚኒስትር ዶ/ር መቅደስ ዳባ፥ በመንግሥት ከፍተኛ ትኩረት ተሰጥቷቸው እየተከናወኑ ካሉ ስትራቴጂያዊ ተግባራት መካከል በአምራችነት የተሰማሩ ባለሃብቶችን በመደገፍ እና በማበረታታት ብሎም አዳዲስ አምራቾችን ወደ ዘርፉ በመሳብ የሀገር ውስጥ ምርትን ማሳደግና ከውጭ የሚገቡ ምርቶችን መተካት ነው ብለዋል።

በዚህ መነሻነት መንግሥት በወሰደው የፖሊሲ ማሻሻያ እርምጃ ምክንያት በየዓመቱ እየቀነስ መጥቶ 8 በመቶ ደርሶ የነበረው በሀገር ውስጥ የተመረተ መድሃኒት የአቅርቦት ድርሻ አሁን ላይ ወደ 36 በመቶ ከፍ ሊል ችሏል ብለዋል።

ከውጭ በሚገቡ ምርቶች ላይ ያለውን ጥገኝነት በመቀነስ ኢኮኖሚያዊ እድገትን ለማፋጠን አምራቾች፣ የፈጠራ ባለሙያዎች፣ ተቆጣጣሪዎች፣ የፋይናንስ ተቋማት እና ሌሎች ባለድርሻ አካላት በጋራ መረባረብ እንደሚገባቸው ጠቁመዋል።

የፕላንና ልማት ሚኒስትር ዶ/ር ፍጹም አሰፋ፥ መንግሥት እየወሰደው ባለው ወሳኝ የፖሊሲ ማሻሻያ እርምጃ የሀገር ውስጥ የሕክምና ግብዓት ምርቶች እያደጉ መምጣታቸውን ገልጸዋል።

በቀጣይም ዘርፉ ከውጭ የሚገቡ ምርቶችን መተካት ብቻ ሳይሆን በቀጣናው ብሎም በዓለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ መሆን ይጠበቅበታል ብለዋል።
https://www.facebook.com/EBCzena/posts/pfbid02dqux1JwtkdSaiGcck8B1L8E6VhuXi16wckjh337W3Xn7k7bbCCQUt8vLh56aCYmfl
👍363👏1
የሆረ ፊንፊኔ የኢሬቻ በዓል በድምቀት እየተከበረ ነው
**************
የ2017 ዓ.ም የሆረ ፊንፊኔ የኢሬቻ በዓል ባህላዊ እሴቱን በጠበቀ መልኩ በልዩ ልዩ ሁነቶች እየተከበረ ይገኛል።
የበዓሉ ሥነ-ሥርዓት በገዳ ሥርዓት መሰረት በአባ ገዳዎች ምርቃት የተጀመረ ሲሆን፤ ሌሊቱን ወደ ስፍራው ሲያቀኑ ያደሩት የበዓሉ ተሳታፊዎች በአሁኑ ሰዓት በዓሉን አድምቀውታል።
ከአዲስ አበባ እና ዙሪያዋ ወደ ሆረ ፊንፊኔ የተመሙት የበዓሉ ታዳሚዎች በባህሉ መሰረት ለፈጣሪ ምስጋና በማቅረብ ላይም ሲሆኑ፤ በባህላዊ አልባሳት ያጌጡ ወጣቶችም በቡድን ቡድን እየሆኑ ባህላዊ ዜማዎችን በማዜም በዓሉን እያከበሩ ይገኛሉ።
📷 በሜሮን ንብረት ፣ በአሰግድ ሲሳይ እና በአፎሚያ ክበበው
#ኢሬቻ #etv #EBC
👍36👎83
ከተለያዩ የኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦች የሆረ ፊንፊኔ ኢሬቻ ድምቀቶች
📷 በሜሮን ንብረት ፣ በአሰግድ ሲሳይ እና በአፎሚያ ክበበው
#ኢሬቻ #etv #EBC
👍29👎54