EBC (Ethiopian Broadcasting Corporation) – Telegram
EBC (Ethiopian Broadcasting Corporation)
138K subscribers
38.3K photos
462 videos
80 files
13.2K links
EBC (Ethiopian Broadcasting Corporation) @etvafaanoromoo1
@ETVkidschannel
@EBCWORLD1
@etventertainment1
Download Telegram
የጋራ ጥረቶቻችን ረሃብን በማጥፋት ለሁሉም የምግብ ዋስትናን የማረጋገጥ ርብርብ ፍሬ እንዲያፈራ እንደሚያስችሉ ተስፋ አለኝ፡- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
***************

ዓለም አቀፍ መሪዎችን፣ ባለሞያዎችን እና የጉዳዩ ተቆርቋሪዎችን በአንድ ላይ በማምጣት እንዲወያዩ በማድረግ የጋራ ጥረቶቻችን ረሃብን በማጥፋት ለሁሉም የምግብ ዋስትናን የማረጋገጥ ርብርብ ፍሬ እንዲያፈራ እንደሚያስችሉ ተስፋ አለኝ ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማሕበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት፤ የ"ከረሃብ ነጻ ዓለም" ጉባኤ ተሳታፊዎችን እንኳን ወደ አፍሪካ የዲፕሎማሲ መዲና በሰላም መጣችሁ ብለዋል።

በኢትዮጵያ ባለፉት ሥድስት ዓመታት በግብርና ሽግግር እና ምርታማነት ላይ በማተኮር በተሰራው ስራ የታረሰ መሬትን እጥፍ በማድረስ፣ ከፍ ያለ እሴት ባላቸው የኢንደስትሪ አዝርዕት ምርት ላይ ተስፋ ሰጪ ውጤቶች መገኘታቸውን ጠቁመዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ አያይዘውም በሚቀጥሉት ቀናት የጉባኤው ውይይቶች የጋራ ግቦቻችንን ስኬት የሚያፋጥኑ ታላላቅ ውሳኔዎች እንደሚተላለፉ እተማመናለሁ ብለዋል።
👍428👎7
የአሜሪካ ምርጫ በትራምፕ እና በሃሪስ እኩል ነጥብ ቢጠናቀቅ ምን ይፈጠራል?
**************************

የዴሞክራት ፓርቲ ፕሬዚደንታዊ እጩ ካማላ ሃሪስ እና የሪፐብሊካን ብርቱ ተፎካካሪያቸው ዶናልድ ትራምፕ በዚህ ምርጫ ባላቸው ፉክክር የተነሳ እኩል ነጥብ ቢያመጡ ምን ይሆን መጨረሻው የሚሉ ጥያቄዎች ይነሳሉ።

እንደዚህ አይነት አጋጣሚዎች የመከሰት እድላቸው ሰፊ ባይሆንም አይከሰቱም ማለት ግን አይቻልም።

አሜሪካውያን በእነሱ አቆጣጠር ከህዳር 5 ምርጫ በፊት ቀደም ሲል የእኔ ሚሉትን ወስነው እየጠበቁ የነበረ ቢሆንም፤በአሜሪካ ምርጫ ታሪክ ውስጥ እስከመጨረሻው ሰዓት የማይወስኑ እና በመጨረሻ ሀሳብ የሚቀይሩ “ስዊንግ ስቴትስ” በመኖራቸው ውጤቶችን ለመገመት አዳጋች ነው።

በአሜሪካ ሥርዓት ማን ፕሬዚደንት እንደሚሆን የሚወስነው የብሔራዊ የህዝብ ድምጽ ሳይሆን 538 አባላት ያሉት "የምርጫ ኮንግረስ" ነው።https://web.facebook.com/EBCzena/posts/pfbid0Skgh32BVYwUPXdGreLgBGPJhWedqkXmT7q2UcrpjD8xFajEgzyVo4mSYQ73n4pGCl
👍205👎2
በግብርናው ዘርፍ የሚመራው የሴፍቲኔት ፕሮግራም ዜጎችን ተጠቃሚ እያደረገ ነው፦ የግብርና ሚኒስቴር
*************

በግብርናው ዘርፍ የሚመራው የሴፍቲኔት ፕሮግራም ዜጎችን ተጠቃሚ እያደረገ መሆኑን የግብርና ሚኒስትር ግርማ አመንቴ (ዶ/ር) ገለጹ፡፡

ሚኒስትሩ በግብርናው ዘርፍ ለሚመራው የሴፍቲኔት ፕሮግራም ዘላቂ የኑሮ መሰረት ለሆኑ ጉዳዮች በዘንድሮው ዓመት 80 ቢሊዮን ብር በሆነ በጀት ድጋፍ መደረጉን ጠቅሰዋል፡፡

ዜጎች ከእርዳታ እና ከተረጂነት እንዲወጡ እንደሀገር የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ የሚያስችሉ ስራዎች እየተሰሩ ስለመሆኑም ተናግረዋል፡፡

በግብርናው ዘርፍ ምርት እና ምርታማነት እንዲጨምርና ዜጎች በምግብ እራሳቸውን እንዲችሉ የሴፍቲኔት ድጋፍ እና የግብርና ግብዓት ድጎማ ከፍ ማለቱንም ጠቁመዋል፡፡

ወደ አርሶ አደሩ የሚደርሰው የማዳበሪያ መጠን እንዳይቀንስም 53 ቢሊዮን ብር ድጎማ ተደርጓል ብለዋል፡፡https://web.facebook.com/EBCzena/posts/pfbid0QS2e38bNsWsSwuhrmNX2P13M6K1d4dJLEWoeBfAzkFubLTyTPRFvW7bATtx83Lm8l
👍156👎3
የሐረር ከተማ የኮሪደር ልማት ገፅታ
👏17
አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የብሪክስ ሀገራት ዩኒቨርሲቲዎች ማህበር መስራች አባል ሆነ
**************

አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ሩሲያ፣ ህንድና ብራዚልን ጨምሮ ከብሪክስ ሀገራት ዩኒቨርሲቲዎች ጋር በመሆን በጣምራ የብሪክስ ሀገራት ዩኒቨርሲቲዎች ማኅበርን በመመስረት የመጀመሪያው የምስራቅ አፍሪካ ሀገር ዩኒቨርስቲ መሆኑን አስታውቋል።

አራቱ የብሪክስ ሀገራት ዩኒቨርሲቲዎች የመሰረቱት ማህበር በትምህርት በዲፕሎማሲ በጥናትና ምርምር እንዲሁም በፈጠራ ስራ በጋራ መሰራት የሚያስችላቸው መሆኑ ተመላክቷል።

ዩኒቨርስቲው በአዲሱ የራስ-ገዝ ስትራቴጂክ እቅድ መሰረት አጋርነትና ዓለማቀፋዊነትን በትኩረት እየሰራ እንደሚገኝ በማኅበራዊ ትስስር ገጹ አስታውቋል።
👏37👍94
ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ከኢትዮጵያ በግብርናው ዘርፍ ልምድ መቅሰም እንደምትፈልግ ገለፀች
************

የግብርና ሚኒስትር ግርማ አመንቴ (ዶ/ር) ከዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ የግብርና ሚኒስትር ግሪጎር ሙታሻል ጋር ሁለቱ ሀገራት በግብርናው ዘርፍ በጋራ መስራት በሚያስችላቸው ጉዳዮች ላይ ተወያይተዋል፡፡

የግብርና ሚኒስትሩ ግርማ አመንቴ (ዶ/ር) አፍሪካ ለግብርና ልማት ምቹ የተፈጥሮ ሃብት እንዳላት ጠቅሰው፤ ነገር ግን የአፍሪካ ሃገራት ህዝባቸውን በአግባቡ መመገብ እንዳልቻሉ ተናግረዋል፡፡

ሚኒስትሩ አያይዘውም፤ ይህንን ችግር ለመቅረፍ የኢትዮጵያ መንግስት ለግብርናው ዘርፍ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ እንደሆነ አስገንዝበዋል፡፡

የዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ የግብርና ሚኒስትር ግሪጎር ሙታሻል በበኩላቸው፤ በግብርናው ዘርፍ በኢትዮጵያ ለመጣው ለውጥ እውቅና ሰጥተው፤ የሃገሪቱ መንግስትም ከኢትዮጵያ ልምድ መቅሰም እንደሚፈልግ ገልፀዋል፡፡

ኢትዮጵያ ለዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ በግብርናው ዘርፍ ልምድ ለማካፈል ያላትን ፍቃደኝነት የግብርና ሚኒስትሩ ግርማ አመንቴ (ዶ/ር) ተናግረዋል፡፡

ሁለቱ ወገኖች በቀጣይ በጋራ መስራት በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ ተባብሮ ለመስራት ከመግባባት መድረሳቸውን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
👍336👎2