EBC (Ethiopian Broadcasting Corporation) – Telegram
EBC (Ethiopian Broadcasting Corporation)
138K subscribers
38.2K photos
458 videos
80 files
13.1K links
EBC (Ethiopian Broadcasting Corporation) @etvafaanoromoo1
@ETVkidschannel
@EBCWORLD1
@etventertainment1
Download Telegram
ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ከኢትዮጵያ በግብርናው ዘርፍ ልምድ መቅሰም እንደምትፈልግ ገለፀች
************

የግብርና ሚኒስትር ግርማ አመንቴ (ዶ/ር) ከዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ የግብርና ሚኒስትር ግሪጎር ሙታሻል ጋር ሁለቱ ሀገራት በግብርናው ዘርፍ በጋራ መስራት በሚያስችላቸው ጉዳዮች ላይ ተወያይተዋል፡፡

የግብርና ሚኒስትሩ ግርማ አመንቴ (ዶ/ር) አፍሪካ ለግብርና ልማት ምቹ የተፈጥሮ ሃብት እንዳላት ጠቅሰው፤ ነገር ግን የአፍሪካ ሃገራት ህዝባቸውን በአግባቡ መመገብ እንዳልቻሉ ተናግረዋል፡፡

ሚኒስትሩ አያይዘውም፤ ይህንን ችግር ለመቅረፍ የኢትዮጵያ መንግስት ለግብርናው ዘርፍ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ እንደሆነ አስገንዝበዋል፡፡

የዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ የግብርና ሚኒስትር ግሪጎር ሙታሻል በበኩላቸው፤ በግብርናው ዘርፍ በኢትዮጵያ ለመጣው ለውጥ እውቅና ሰጥተው፤ የሃገሪቱ መንግስትም ከኢትዮጵያ ልምድ መቅሰም እንደሚፈልግ ገልፀዋል፡፡

ኢትዮጵያ ለዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ በግብርናው ዘርፍ ልምድ ለማካፈል ያላትን ፍቃደኝነት የግብርና ሚኒስትሩ ግርማ አመንቴ (ዶ/ር) ተናግረዋል፡፡

ሁለቱ ወገኖች በቀጣይ በጋራ መስራት በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ ተባብሮ ለመስራት ከመግባባት መድረሳቸውን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
👍336👎2
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
"እንኳን ወደ ቀደምት ምድር ኢትዮጵያ በደህና መጣችሁ" - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
👏23👍1312👎1
ኦሮምኛን አቀላጥፈው የሚናገሩት ጃፓናዊቷ የቦረና ጎሳ አባል
**********

ኦሮምኛን አቀላጥፈው የሚናገሩት ጃፓናዊቷ የቦረና ኦሮሞ የመልዩ ጎሳ አባል በኦዳ ቡሉ ስርዓት ለመካፈል ምስራቅ ቦረና ዞን አሬሮ ወረዳ ገጠራማ ስፍራ ተገኝተዋል፡፡

በጃፓን ወላጆቿ ያወጡላቸው ስም ቺካጌ ኦባሱሌት ይሁን እንጂ፤ ከቦረና ኦሮሞ ማንነት ጋር ተዋህደው የመልዩ ጎሳ አባል ከሆኑ በኋላ ሎኮ ዱባ ካሩ (ዶ/ር) በሚል ስማቸው ይታወቃሉ፡፡

ከ20 ዓመት በፊት በቦረና ምድር ተገኝተው ለሁለተኛ ድግሪ (ማስተርስ) ጥናታዊ ፅሁፋቸው ሲሰሩ ከቦረና ህዝብ ጋር በእጅጉ እንዳስተዋወቃቸው ይገልፃሉ፡፡

ለመጀመሪያ ጊዜ ቦረና ጋዩ በሚባል የመልዩ ጎሳ በሚገኙበት ስፍራ ማረፊያቸው ያደረጉት ጃፓናዊቷ፤ ኦሮምኛ ቋንቋን በዚሁ ስፍራ መማራቸውን ይገልጻሉ፡፡
https://ebc.et/newsdetails.aspx?newsid=8386
👍2512
አምባሳደር ገነት ተሾመ የሹመት ደብዳቤያቸውን ለሩሲያ ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን አቀረቡ
*****************

በሩሲያ የኢትዮጵያ አምባሳደር ገነት ተሾመ (ዶ/ር) የሹመት ደብዳቤያቸውን ለሩሲያ ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን አቅርበዋል።

ፕሬዝዳንት ፑቲን ሩሲያ ከኢትዮጵያ ጋር ጠንካራ ወዳጅነት እና የሁለትዮሽ ግንኙነት እንዳላት ገልጸዋል።

ሩሲያ በቅርቡ በካዛን ከተማ 16ተኛውን የብሪክስ መሪዎች ጉባኤ በስኬት ማጠናቀቋንና የሩሲያ-አፍሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮችን ስብስባን ለማስተናገድ ዝግጅት ማጠናቀቋን ጠቁመዋል።

በተጨማሪም ሩሲያ በኢኮኖሚ፣ በንግድ፣ በቴክኖሎጂ ሽግግር፣ በሰብዓዊ ጉዳዮች ከአጋር እና ወዳጅ አገራት ጋር በጋራ ለመሥራት ዝግጅት መሆኗን ፑቲን መግለጻቸውን በሩሲያ የኢትዮጵያ ኤምባሲ መረጃ ያመለክታል።
👍427
የኤ350-1000 አውሮፕላን የኢትዮጵያ አየር መንገድ ስኬታማ ጉዞ ማሳያ ነው - ሌተናል ጄኔራል ይልማ መርዳሳ
****************

የኤ350-1000 አውሮፕላን የኢትዮጵያ አየር መንገድ ስኬታማ ጉዞ ማሳያ ነው ሲሉ የኢትዮጵያ አየር ኃይል ዋና አዛዥ እና የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ የቦርድ ሰብሳቢ ሌተናል ጄነራል ይልማ መርዳሳ ተናገሩ፡፡

የኢትዮጵያ አየር መንገድ 124 አውሮፕላኖችን ለመግዛት ማዘዙን በቅርቡ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ይፋ ማድረጋቸው ይታወቃል፡፡

ይህም አየር መንገዱ በተፋጠነ የስኬት ጉዞ ላይ መሆኑን የሚያመላክት እርምጃ መሆኑን ነው የገለጹት፡፡

በዚህም አየር መንገዱ በአፍሪካ የመጀመሪያ የሆነውን ኤ350-1000 የመንገደኞች አውሮፕላንን ትናንት ከኤርባስ ኩባንያ የተረከበ ሲሆን፤ በዛሬው እለትም አውሮፕላኑ አዲስ አበባ ገብቷል፡፡

የኢትዮጵያ አየር ኃይል ዋና አዛዥ እና የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ የቦርድ ሰብሳቢ ሌተናል ጄኔራል ይልማ መርዳሳ፤ ኤ350-1000 አውሮፕላን የኢትዮጵያ አየር መንገድ ስኬታማ ጉዞ ማሳያ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
https://web.facebook.com/EBCzena/posts/pfbid02z3D8s8CkyjUkpQRJuj253wC7tH5hS7J7UN1gKn2tVa2umUJqpdtdzoeSA8zT6zmpl
👍211
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የጌዴኦ ዞን የቡና ምርት
👍5113