EBC (Ethiopian Broadcasting Corporation) – Telegram
EBC (Ethiopian Broadcasting Corporation)
138K subscribers
38.3K photos
462 videos
80 files
13.1K links
EBC (Ethiopian Broadcasting Corporation) @etvafaanoromoo1
@ETVkidschannel
@EBCWORLD1
@etventertainment1
Download Telegram
በክልሎችም መነቃቃትን የፈጠረው የመዲናዋ የኮሪደር ልማት
*****************

በአዲስ አበባ የተገነቡ እና እየተገነቡ ያሉ የኮሪደር ልማት ስራዎች ከተማዋን እንደ ስሟ ውብ እና ሳቢ እያደረጓት ይገኛሉ።

የኮሪደር እና የወንዝ ዳርቻ ልማት እንዲሁም የገበታ ለሀገር እና ገበታ ለሸገር ፕሮጀክቶች ኢትዮጵያ ዓለም አቀፍ ጉባኤዎችን እንድታስተናግድ ይበልጥ ተመራጭ እያደረጓት ነው።

የአዲስ አበባ የኮሪደር ልማት የክልል ከተሞችም ልምድ እየቀሰሙበት የሚገኝ መልካም ተሞክሮ ነው።

የሀዋሳ ከተማ ከንቲባ መኩሪያዬ መርሻዬ ከኢቲቪ ጋር በነበራቸው ቆይታ፤ የአዲስ አበባ የኮሪደር ልማት ለክልሎች መነቃቃት እንደፈጠረ ተናግረዋል።

ከአዲስ አበባ የኮሪደር ልማት ተሞክሮ በመውሰድ በሀዋሳ ከተማም የመጀመሪያው ምዕራፍ የኮሪደር ልማት ስራ መጀመሩን ጠቅሰዋል።
https://web.facebook.com/EBCzena/posts/pfbid02aMMGfSkkotFDD9sb3sKtQAWiomwtKMKSdAoePMAkS3qCsVSYbjcKLDhPaJffmcG6l
👍23👎43
በኢትዮጵያ ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ የአትክልት ምርቶች በመርከብ ለአውሮፓ ገበያ ተላኩ
**************

በኢትዮጵያ ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ የአትክልት ምርቶች በመርከብ ተጓጉዘው ለአውሮፓ ገበያ መላካቸውን የግብርና ሚኒስቴር ገለፀ፡፡

ኢትዮ ቬጅ ፍሩ ሃላፊነቱ የተወሰነ የግል ኩባንያ በተሰኘ የአትክልትና ፍራፍሬ አምራች ድርጅት በኢትዮጵያ ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ ሹገር ስናብ እና ማንጄቱት የተባሉ የአትክልት ምርቶችን በመርከብ በማጓጓዝ ወደ ኔዘርላንድ መላኩ ተጠቅሷል።

በዚህም 12 ቶን ሹገር ስናብ እና ማንጄቱት የአትክልት ምርቶችን ዘመናዊ የማቀዝቀዣ እና አዳዲስ ቴክኖሎጂ የተገጠመለት ኮንቴነር በመጠቀም ጅቡቲ ወደብ ከደረሰ በኃላ በመርከብ እንደሚላክ ተገልጿል።

የአትክልት ምርቱ ከቆቃ ተነስቶ በመርከብ ተጓጉዞ በ23 ቀናት ውስጥ ኔዘርላድ እንደሚደርስም ከግብርና ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
👍2919👏8👎1
አዲሱ የባንክ አሰራር ረቂቅ አዋጅ የፋይናንስ ዘርፉ ቀጣይነት ላለው የምጣኔ ሀብት እድገት ሚናውን እንዲወጣ ያግዛል - የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ
***************

አዲሱ የባንክ አሰራር ረቂቅ አዋጅ የፋይናንስ ዘርፉ ቀጣይነት ላለው የምጣኔ ሀብት እድገት ሚናውን እንዲወጣ አስተዋጽኦ እንደሚያደርግ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ አስታወቀ።

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የበጀት፣ ፕላንና ፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ማሻሻያ እና ባንክ አሰራር ረቂቅ አዋጆች ላይ ከብሔራዊ ባንክ የስራ ኃላፊዎች ጋር የአስረጂ መድረክ አካሂዷል።

በአስረጂ መድረኩ በረቂቅ አዋጆቹ ላይ ግልጽነት ሊፈጠርባቸው ይገባል የተባሉ ጉዳዮች ተነስተው በባንኩ አመራሮች ማብራሪያ ተሰጥቷል።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገዥ ማሞ ምህረቱ፣ ባንኩ የረዥም ዓመታት የኢኮኖሚና የፖለቲካ አደረጃጀቶች ዋና ዋና የሚባሉ የኢኮኖሚ ግቦችን በማሳካት ቁልፍ ሚና የተጫወተ ተቋም መሆኑን አስታውሰዋል።
https://web.facebook.com/EBCzena/posts/pfbid02hnqcgx5CxJco7wJXAoV53Lv3uoqGH1YwtQBwZvjKt5QozWGwU1NSz6iyLetv3mf2l
👍202
ርዕሰ መስተዳድር ነጋሽ ዋጌሾ የሚዛን አማን የአየር ማረፊያና የደንቢ ሎጅ ግንባታ ያለበትን ደረጃ ተመለከቱ
*************

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ርዕሰ መስተዳድር ዶ/ር ኢ/ር ነጋሽ ዋጌሾ የሚዛን አማን ሀገር አቀፍ የአየር ማረፊያና የደንቢ ሎጅ ግንባታ የስራ እንቅስቃሴ ያለበትን ደረጃ ተመልክተዋል።

ርዕሰ መስተዳድሩን ጨምሮ ሌሎች የክልል፤ የቤንች ሸኮ ዞን እንዲሁም የሚዛን አማን ከተማ አስተዳደር ከፍተኛ አመራሮች በግንባታ ላይ የሚገኙ ሰራተኞችን በስፍራው ተገኝተው አበረታተዋል።

አመራሮቹ የሚዛን አማን ሀገር አቀፍ የአየር ማረፊያ የስራ ሁኔታን ተዘዋዉረው መጎብኘታቸውን የክልሉ ኮሙዩኒኬሽን ቢሮ መረጃ ያመለክታል።

በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ሃሳብ አመንጪነት እየተገነቡ ከሚገኙ ግዙፍ ሀገራዊ ፕሮጀክቶች መካከል የገበታ ለትውልድ ፕሮጀክት አካል የሆነው በቤንች ሸኮ ዞን እየተገነባ የሚገኘው የደንቢ ሎጅ ግንባታ የስራ እንቅስቃሴም ምልከታ ተደርጎበታል።
👍244
የጅግጅጋ ከተማ የኮሪደር ልማት ስራን በ6 ወራት ጊዜ ውስጥ ለማጠናቀቅ ማቀዱን ኮሚቴው ገለፀ
************

የጅግጅጋ ከተማ የኮሪደር ልማት ኮሚቴ የከተማዋን ኮሪደር ልማት ፕሮጀክት በ6 ወራት ጊዜ ውስጥ ለማጠናቀቅ ማቀዱን ገለፀ፡፡

በሶማሌ ክልል የጅግጅጋ ከተማ የኮሪደር ልማት ፕሮጀክት ኮሚቴ በጅግጅጋ ከተማ የኮሪደር ልማት የስራ ሂደትን ገምግሟል።

በሶማሌ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኢብራሂም ዑስማን ሰብሳቢነት በተካሄደው የጅግጅጋ ከተማ የኮሪደር ልማት ፕሮጀክት ኮሚቴ የግምገማ መድረክ በከተማው እየተካሄደ ያለው የኮሪደር ልማት ፕሮጀክት የስራ ሂደት አፈፃፀም ግምገማ መደረጉን የክልሉ መገናኛ ብዙኃን ዘግቧል።

በጅግጅጋ ከተማ እየተካሄደ ባለው የኮሪደር ልማት ፕሮጀክት በአሁኑ ጊዜ በአራት ኪሎ ሜትር ላይ ስራው በጥሩ ሁኔታ እየተካሄደ መሆኑን እና በአጠቃላይ ፕሮጀክቱን በ6 ወራት ጊዜ ውስጥ ለማጠናቀቅ መታቀዱ ተገልጿል።
👍32
የኢትዮጵያ አየር መንገድ አፍሪካን ከእስያ በማገናኘት የጎላ አበርክቶ እንዳለው ተገለፀ
***************

የኢትዮጵያ አየር መንገድ አፍሪካን ከእስያ በማገናኘት የጎላ አበርክቶ እንዳለው የሲንጋፖር የጉዞና ጭነት አገልግሎት ወኪሎች ገለፁ፡፡

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በሲንጋፖር ለሀገሪቱ ለተጓዦች፣ የጉዞና የጭነት አገልግሎት ወኪሎች የማበረታቻ ሽልማት መስጠቱ ይታወቃል፡፡

ኢነርጂያ፣ ሲንጋፖር ፖስት ኃ/የተ/የግ/ ማህበር፣ ኤርሰርቭ ግሩፕ፣ ሲቲስቴት ትራቭል፣ እና ኤር ፍራይት ሲንጋፖር እውቅና የተሰጣቸው ተቋማት ናቸው።

የሲቲስቴት ተራቭል ዋና ዳይሬክተር አልበርቶ ሆ እንዳሉት፤ የኢትዮጵያ አየር መንገድ በሲንጋፖር ያዘጋጀው ሁነት አየር መንገዱ ምን ያህል ታላቅና እንዴት ውጤታማ እንደሆነ ለመረዳት አስችሎኛል።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ አፍሪካን ከሲንጋፖር ለማስተሳሰር የሚያደርገው አስደናቂ እንቅስቃሴ አድናቆት የሚቸረው መሆኑን ገልጸዋል፡፡
https://web.facebook.com/EBCzena/posts/pfbid0UW31kyh9nzYLdKWTNyJGx9JXWPxYxGH51vjHrty2U58RGvbAAft5SXgfecRNewQFl
👍265