Event Addis Media – Telegram
Event Addis Media
9.61K subscribers
6.13K photos
14 videos
4 files
4.75K links
Connect with Addis artistic community!

Website: https://eventaddis.com

Contact: @Tmanaye
Download Telegram
"ኢትዮ የምግብና መጠጥ ፌስቲቫል"

"ኢትዮ የምግብና መጠጥ ፌስቲቫል" ከሰኔ 5 እስከ 9 2016 ዓ.ም በአዲስ አበባ ኤግዚቢሽን ማዕከል ይካሄዳል።

ለ5 ተከታታይ ቀናት በሚቆየው "ኢትዮ የምግብና መጠጥ ፌስቲቫል" በምግብ፣ በመጠጥ፣ በፓኬጂንግ እና ተዛማጅ መስኮች ላይ የተሰማሩ ግብዓት አቅራቢዎች፣ አምራቾች፣ አገልግሎት ሰጪ ድርጅቶች፣ ከዘርፉ ጋር የተገናኙ አምራች እና አስመጪዎች እንዲሁም የፋይናንስ ተቋማት ይሳተፋሉ ተብሏል።

በፌስቲቫሉ ላይ የዘርፉ ባለሙያዎች የእውቅና አሰጣጥ ፕሮግራም፣ ሽልማት የሚያስገኙ ልዩ ልዩ ውድድሮች እና የመዝናኛ ፕሮግራሞች መካተታቸው ተገልጿል።

አዘጋጆቹ "ኢትዮ የምግብና መጠጥ ፌስቲቫል" በተሳካ መልኩ ይካሄድ ዘንድ የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ምዝገባ እያደረጉ መሆናቸውን ያስታወቁ እስካሁን ያልተመዘገቡ ተቋማትም በቀሩት አጭር ቀናት ምዝገባ አድርገው ይህን ፌስቲቫል እንዲቀላቀሉ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

ይህን የምግብና መጠጥ ፌስቲቫል ለመታደም ለሚፈልጉ ጎብኚዎች መግቢያው በነፃ ነው ተብሏል።

ፌስቲቫሉ የኢንዱስትሪውን የተለያዩ ባለድርሻ አካላትን በማገናኘትና በማስተሳሰር ረገድ ፋይዳ እንዳለው ተገልጿል።

ፌስቲቫሉን በአምራች ኢንዱስትሪ ኢንስቲትዩት የምግብና መጠጥ ምርምርና ልማት ማዕከል ፣አሜዚንግ ፕሮሞሽንና ኤቨንትስ ፣ ዳብ ትሬዲንግ በጋራ በመሆን አዘጋጅተዋል።

ለተጨማሪው: https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
የ"በዓሉ ግርማ ቤርሙዳ" ተውኔት ለአጭር ጊዜ በቋሚነት በብሔራዊ ቴአትር መቅረብ ሊጀምር ነው

በውድነህ ክፍሌ ተደርሶ በተሻለ አሰፍ የተዘጋጀውና በቅርቡ በአንጋፋው የሀገር ፍቅር ቴአትር ቤት ሲቀረብ የነበረው "በዓሉ ግርማ ቤርሙዳ" ተውኔት ከፊታችን ሐሙስ ግንቦት 29 2016 ዓ.ም ጀምሮ ለአጭር ጊዜ በቋሚነት በአንጋፋው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር ከምሽቱ 11:30 ጀምሮ መቅረብ እንደሚጀምር ኤቨንት አዲስ ድረገፅ ሰምቷል።

በበዓሉ ግርማ የሕይወት ታሪክ ላይ ተመሥርቶ የተሠራው "ቤርሙዳ" ተውኔት የበዓሉ ግርማ ወዳጆች በተገኙበት ከወራት በፊት ጥቅምት 17 2016 ዓ.ም ነበረ በሀገር ፍቅር ቴአትር የተመረቀው።

ለወራትም በሀገር ፍቅር ቴአትር ቤት ዘወትር እሁድ ከቀኑ 8:00 ጀምሮ በቋሚነት ለታዳሚያን ሲቀረብ ነበር።

በኮሪደር ልማቱ የተነሳም በሀገር ፍቅር ቴአትር ቤት የትርዒት አቅርቦት እንደተቋረጠ ይታወሳል።

ለተጨማሪው: https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
የሳምንቱ የኪነጥበብ ዝግጅቶች ( በአጭሩ )

📍የኪነጥበብ ዝግጅቶች

"ወደ ግጥም" ክፍት የኪነጥበብ ዝግጅት ዛሬ ቅዳሜ ግንቦት 24 2016 ዓ.ም ከቀኑ 8:30 ጀምሮ በፈንድቃ ባህል ማዕከል ውስጥ ይካሄዳል።በዕለቱም ግጥም ፣ ሙዚቃ ፣ጨምሮ ልዩ ልዩ ኪናዊ መሰናዶዎች ይቀርባሉ ተብሏል።

የ "ግራጭ ቃጭሎች" ግጥም በአኩስቲክ የኪነጥበብ ዝግጅት ነገ እሁድ ግንቦት 25 2016 ዓ.ም ከቀኑ 9:00 ጀምሮ በደብረዘይት ቶማይ ሆቴል ውስጥ ይካሄዳል ተብሏል።

ለተጨማሪው: https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
የሳምንቱ የሥዕል መረጃዎች (በአጭሩ )

📍ሥነጥበብ

1.የአንጋፋ ሠዓሊያን የሥዕል ስራዎች የሚቀርብበት "የኢትዮጵያ ቀለም 3" የሥዕል አውደርዕይ በዚህ ሳምንት በፈንድቃ ባህል ማዕከል ውስጥ ለእይታ በቅቷል።

በዚህ የሥዕል አውደርዕይ ላይ ስራዎቻቸው የቀረበላቸው ሠዓሊያኑ ወርቁ ጎሹ ፣ ባርባራ ጎሹ ፣ገብረክርስቶስ ሰለሞን ፤ዘሪሁን የትምጌታ ፤አሸናፊ ወለደየሱስ ፣ አይናለም ገ/ማርያም ፣ አክሊሉ መንግስቱ ናቸው።

የሥዕል አውድርዕዩ ከግንቦት 21 እስከ ሰኔ 5 2016 ዓ.ም ድረስ በፈንድቃ በእይታ ላይ ይቆያል ተብሏል።

2.የሠዓሊ ዳዊት ገረሡ "አሁን" የተሰኘ የሥዕል አውድርዕይ ግንቦት 23 2016 ዓ.ም ስድስት ኪሎ በሚገኙ ገብረክርስቶስ ደስታ ዘመናዊ ቤተመዘክር ውስጥ ለእይታ በቅቷል።

ይህ የሥዕል አውደርዕይ እስከ ሰኔ 14 2016 ዓ.ም ድረስ በእይታ ላይ ይቆያል።

ለተጨማሪው: https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
የጊፍት ሪል ስቴት መንደር 3 ዘመናዊ ቅንጡ የመኖሪያና የንግድ አፓርትማዎች ምርቃት ሥነሥርዓት ተከናወነ

በሪስ ስቴት ዘርፍ ውስጥ ሀያ ዓመታት በላይ ዘመናዊ የመኖሪያ ቪላ መንደሮችን በመገንባት በቂ ልምድ ያካበተው ጊፍት ሪልስቴት፣ በተለምዶ ፈረስ ቤት ተብሎ በሚጠራው እና ደራርቱ ቱሉ አደባባይ አጠገብ የገነባቸውን ረጃጅም፣ ዘመናዊ የመኖሪያና የንግድ አፓርትማዎችን ዛሬ ግንቦት 24 2016 ዓ.ም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት ተመርቋል።

ዛሬ የተመረቀው የጊፍት ሪል ስቴት መንደር ሦስት በ54 ሺህ ሜትር ካሬ ላይ ያረፈ ነው፡፡

የጊፍት መንደር ሦስት 2117 ቤቶችን በውስጡ የያዘ መንደር ሲሆ ከ2 እስከ 24 የሚደርስ ፎቆችን ያካተተ አፓርትማዎች፣ ቪላዎች፣ ታዎን ሃውሶችና ሮው ሃውሶችን ያካተተ መንደር ነው።

ጊፍት ሪልስቴት የካ እና ሲኤምሲ ላይ በተለምዶ የጊፍት መንደር አንድና መንደር ሁለት ተብለው በሚታወቁ የመኖሪያ አካባቢዎች፣ 95 ሺህ ካሬ መሬት ላይ ዘመናዊ መንደሮችን ገንብቶ ለተጠቃሚዎች ማስተላለፉ ይታወሳል።

ባሳለፍነው ሚያዝያ ወር 2016 ዓ.ም ላይ ጊፍት ሪል ስቴት በመንግስትና የግል አጋርነት ልማት ፕሮግራም መሠረት፣ በዓይነቱ የመጀመሪያ የሆነውን የ12 ሺህ ቤቶች ግንባታ ስምምነት የተፈራረመ ሲሆን በመጀመሪያው ዙር የ4 ሺህ ቤቶች ግንባታ ስራ በለገሃር አካባቢ ግንባታቸው እየተፋጠነ ይገኛል ተብሏል።

ለተጨማሪው: https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
አርቲስት ሊዲያና ሰለሞን የብሪጅ ብረታብረትና እንጨት ስራ ብራንድ አምባሳደር በመሆን ስምምነት ፈፀመች

ብሪጅ ኃ/ቱ የተወሰነ የግል ማህበር በሞናርክ ሆቴል  አርቲስት ሊዲያና ሰለሞንን ይፋዊ ብራንድ አምባሳደር አድርጎ ሾሟል።

አርቲስት ሊዲያና ሰለሞን በሚሊዮን የሚቆጠር ብር ስምምነት እንደፈፀመች የተናገረች ሲሆን ፣ የብሪጅ ኢትዮጵያ ምርቶችና ድርጅቶች ለማስተዋወቅ የበኩሏን ድርሻ እንደምትወጣ ገልፃለች።

የብሪጅ ብረታብረትና እንጨት ስራ ኃ/ቱ የተወሰነ የግል ማህበር ስራ አስኪያጅ የሆኑት አቶ ደረጄ በላቸው፣ ከአርቲስት ሊዲያና ሰለሞን ጋር የፈፀምነው ስምምነት ድርጅታችን ወደ ላቀ ደረጃ ለማድረስ እና ተደራሽነቱን ለማስፋት በማሰብ ነው ሲሉ ተናግረዋል።

ብሪጅ በ 2002 ዓ.ም በ 50 ሺ ብር ካፒታል፣ በአነስተኛና ጥቃቅን ተደራጅቶ ስራውን የጀመረ ሲሆን፣ አሁን ከ25.5 ሚሊየን ብር በላይ ካፒታል ማፍራት ችሏል ሲሉ አቶ ደረጄ በላቸው አክለው ተናግረዋል። 

ሊዲያና ሰለሞን፣ ብሪጅ ኢትዮጵያ በስሩ ከሚያስተዳድራቸው ድርጅቶች አንዱ ከሆነው ከዳልማንት ትሬዲንግ ጋር የብራንድ አምባሳደር ውል ተፈራርማለች።

ለተጨማሪው: https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
" ምሳሌ የቤተሰብ ሽልማት" ተካሄደ

"ቤተሰብ የሀገር መሰረት ነው" በሚል መሪ ሃሳብ የመጀመሪያው ምሳሌ የቤተሰብ ሽልማት ዛሬ ግንቦት 24 ቀን 2016 ዓ.ም ተከናውኗል።

እንደ ሀገር ቤተሰብ ላይ መስራት ያለብንን ጉዳይ ችላ በማለታችን እናትነት ፤ አባትነት ላይ እንዲሁም  በአጠቃላይ ቤተሰብ የሚሉ ጉዳዮች ላይ ትውልዱ እንዲፈራ አድርጓል ያሉት የሽልማቱ አዘጋጅ እና የምቹ ቤት ኢቨንትስ የቦርድ ሰብሳቢ ወይዘሮ ሮዝ መስቲካ ናቸው።

ምቹ ቤት ኢቨንትስ ላለፉት አምስት ዓመታት "ቤቶች እና ልጆች" በሚል እናቶች አባቶች እና የተለያዩ ተጋባዦች ተሞክሮ የሚያቀርቡበትን መድረክ ሲያዘጋጅ ቆይቷል።

በነዚህ መድረኮች ተሞክሮ ሲያካፍሉ ከነበሩት መካከልም በመምረጥ በቤት እመቤት ፤በደጅ እመቤት ፤በአባወራ እና በባለ ውለታ እንዲሁም በልዩ ተሸላሚ በተሰኙ አራት ዘርፎች የመጀመሪያውን "ምሳሌ የቤተሰብ ሽልማት" አከናውኗል።

"ምሳሌ የቤተሰብ ሽልማት" ከዚህ በኋላም በቋሚነት ሀገራዊ በማድረግ በየዓመቱ በሕዝብ ምርጫ ተሸላሚዎችን እንደሚያስመርጥ እና እንደሚሸልም ተገልጿል።

መረጃው የአራዳ ኤፍ ኤም 95.1 ነው።

ለተጨማሪው: https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
የዶክ ሜዲካል ሴንተር የህክምና ቱሪዝም መርሃግብር መክፈቻ ሥነሥርዓት ተካሄደ

በዚህ የህክምና ቱሪዝም መርሃግብር መከፈቻ ላይ የማዕከሉ መስራች ዶ/ር አማኑኤል ቶሌሳን ጨምሮ የተለያዩ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል ።

የዶክ ሜዲካል ሴንተር በኳታር ትልቅ የአጥንት ህክምና አገልግሎት ከሚሰጡ ድርጅቶች መካከል ሲሆን በዶር አማኑኤል ቶሌሳ የተመሰረተው እና የአከርካሪ ቀዶ ጥገና፣ የመገጣጠሚያዎች መተካት እና የስፖርት ህክምናን ጨምሮ የተለያዩ ልዩ ልዩ አገልግሎቶችን በመስጠት የሚታውቅ ዓለም አቀፍ የህክምና ማዕከል ነው።

ለኢትዮጵያውያን ዜጎች እና ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ የከፍተኛ ደረጃ የአጥንት ህክምና አግልግሎት ለመስጠት የተነደፈውን የዶክ ሜዲካል ሴንተር ጅምር ለኢትዮጵያውያን ዜጎች የጤና አጠባበቅ ተደራሽነትን ከማጎልበት ባለፈ የህክምና ቱሪዝምን በማስተዋወቅ ኢኮኖሚያዊ እድገትን ለማምጣት እና ዓለማቀፋዊ ግንኙነቶችን ለማጠናከር ታሳቢ አድርጎ እየሰራ የሚገኝ የህክምና ተቋም ነው።

ዶ/ር አማኑኤል ቶሌሳ በኢትዮጵያ ከፍተኛ ደረጃ ያለው የህክምና አገልግሎት እንደሚያስፈልግ በመገንዘብ እነዚህን አገልግሎቶች በህክምና ቱሪዝም ፕሮግራም ለወገኖቻቸው ለማዳረስ እየሰሩ እንደሚገኙ ተገልጿል።

ይህ ፕሮግራም ከኢትዮጵያው ወደ ኳታር ሄደው መታከም ለሚያስፈልጋቸው ኢትዮጵያውያን ፣ የዲፕሎማቲክ ማህበረሰብ፣ ኢንሹራንስ ላላቸው ታካሚዎች እና የንግድ ተጓዦች በኳታር ከፍተኛ ደረጃ የአጥንት ህክምና እንዲያገኙ ታስቦ የተዘጋጀ እንደሆነ ሔሎ ኢትዮጵያ ሰምቷል።
በጋዜጠኛ ታምራት ኃይሉ የተጻፈው “ዜሮ ዓመት የስራ ልምድና ሌሎች ወጎች” የተሰኘው መጽሐፍ ሰኞ ይመረቃል

ላለፉት 22 አመታት በጋዜጠኝነት ሙያው የሚታወቀው የቁም ነገር መጽሔት ባለቤትና ዋና አዘጋጅ በሆነው ጋዜጠኛ ታምራት ኃይሉ የተጻፈውና ለህትመት የበቃው “ዜሮ ዓመት የስራ ልምድና ሌሎች ወጎች” የተሰኘው መጽሐፍ የፈታችን ሰኞ ግንቦት 26 /2016 ዓ.ም ጊዮን ሆቴል ግሮቭ ጋርደን ዎክ ከ11 ሰዓት ጀምሮ በሚካሄድ ዝግጅትእንደሚመረቅ ታውቋል፡፡

በዕለቱ የኪነ ጥበብ ቤተሰቦች፤ አርቲስቶች፤ ደራሲያንና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በሚገኙበት ደማቅ የምረቃ ስነ ስርዓት ላይ ስለ መጽሐፉ ይዘት መጠነኛ ዳሰሳ በዶ/ር ዘላለም ጌታቸው የዲላ ዩኒቨርሲቲ የቋንቋና ስነ ጽሑፍ መምህር የሚቀርብ ሲሆን አዝናኝ ትረካዎች በታዋቂ አርቲስቶችና ጋዜጠኞች ይቀርባል፡፡

አንጋፋው ጋዜጠኛ አለምነህ ዋሴን ጨምሮ ጋዜጠኛና ደራሲ ቴዎድሮስ ተ/አረጋይ፤ ኮሜዲያን ደረጀ ሃይሌ፤ ጋዜጠኛ በላይ በቀለ፤ ገጣሚ ታገል ሰይፉ፤ አርቲስት ታምሩ ብርሃኑ፤ ጋዜጠኛ ኤደን ገ/ህይወትና ደራሲ በሃይሉ ገ/እግዚአብሔር ቅንጭብ ታሪኮችንና ገጠመኞቻቸውን ፤ የሚያቀርቡ ሲሆን መድረኩን ጋዜጠኛ መሰለ ገብረህይወት እንደሚመራው ታውቋል፡፡

“ዜሮ ዓመት የስራ ልምድና ሌሎች ወጎች” የተሰኘው የደራሲ ታምራት ሃይሉ መጽሐፍ 20 ታሪኮችን የያዘ ሲሆን 136 ገጾች አሉት በቅድመ ህትመት የማህበራዊ ሚዲያ ዘመቻ በደራሲና ጋዜጠኛ ቴዎድሮስ ተ/አረጋይ አስተባባሪነት በአጭር ቀናት የህትመት ዋጋውን መሰብሰብ የተቻለ ሲሆን በ275 ብር ለገበያ መቅረቡ ታውቋል፡፡

ለተጨማሪው: https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
የድምፃዊ መሳይ ተፈራ "የልቤን” የተሰኘ አዲስ አልበም የፊታችን ቅዳሜ ለአድማጮች ይደርሳል

የድምፃዊ መሳይ ተፈራ ካሣ "የልቤን "የተሰኘ የመጀመሪያ አዲስ አልበም የፊታችን ቅዳሜ ሰኔ 1 2016 ዓ.ም በራሱ Mesay Tefera የዩቲዩብ ቻናል እንደሚለቀቅ ኤቨንት አዲስ ድረገጽ ሰምቷል።

በሙዚቃ አልበሙ ላይ ወጣትና አንጋፋ የግጥምና ዜማ ደራሲያን የተሳተፉበት ሲሆን ከእነዚህ መካከል ድምፃዊ ጎሳዬ ተስፋዬ ፣ ሞገስ ተካ ፣ አቤል ሙሉጌታ ፣ ናትናኤል ግርማቸዉ ፣ አቡዲ ፣ምህረታብ ደስታ፣ አንተነህ ምናሉ ፣ወንድወሰን ይሁብ ይገኙበታል።

በቅንብር ሚክሲንግና ማስተሪንግ የሙዚቃ ባለሙያዎች ሚካኤል ኃይሉ (ሚኪ ጃኖ) ታምሩ አማረ (ቶሚ) አቤል ጳውሎስና ኪሩቤል ተስፋዬ ተሳትፈውበታል።

አምስት ዓመታት እንደፈጀ የተገለጸው አልበሙ በውስጡ ቻል ቻል ፣የብቻዬ ፣ቆንጆ ነሽ፤ደህና ይግጠምሽ፤ ማካሪና ፤ ከአባይ ማዶ ፤ውረጅ ካናቴ ፤ የልቤን ፤ግድ የለሽም፤ ኸረ ተይ፤አይ አለማወቋ፤ አወሰድማዬ፤ እሳቱ የተሰኙ ርዕሰ ያላቸው የተለያዩ ጉዳዮችን የሚዳስሱ 12 የሙዚቃ ስራዎችን ይዟል።

ድምጻዊ መሳይ ተፈራ ካሣ ከዚህ ቀደም  አሰብኩት ፣ ፋሽን፣ብርቄ ነሽ፣ ደግዬ ፣ በጣም እንጂ በጣም እና ሌሎችንም ነጠላ ሙዚቃዎች ለአድማጮች አድርሷል።

ይህን የሙዚቃ አልበም ጋዜጣዊ መግለጫ ያስተባበረው ቴዲኔት ሚዲያና ኢቨንትስ ከተመሰረተበት ጊዜ ጀምሮ በታላላቅ ሀገራዊና እንዲሁም ዓለም አቀፋዊ ሁነቶችን በማዘጋጀት በማስተባበር ልዩ ልዩ መድረኮችን በመምራት የሚታወቅና የሚዲያ ኮሙኒኬሽንና የመዝናኛ ኢንተርቴይመንት ዘርፍ  ላይ በመሰማራት የተለያዩ ስራዎችን በብቁ ዝግጅት በሃላፊነት በመስራት ላይ የሚገኝ ተቋም ነው።

ለተጨማሪው: https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
ኤፍ ኤም አዲስ 97.1 ‹‹ለተሻለ ነገ እናንብብ›› በሚል መሪ ቃል ሲያካሂደው የቆየው የ100 ቀናት የንባብ ዘመቻ ተጠናቀቀ

ላለፉት አንድ መቶ ቀናት በተካሄደው የንባብ ዘመቻ በቁጥር አንድ መቶ የሚሆኑ ከተለያዩ የሕይወት ዘርፎች የተመረጡ ኢትዮጵያውያን ተካፍለዋል።

የሃይማኖት ሰዎች፣ የኪነ ጥበብ ባለሙያዎች፣ የስፖርት ሰዎች፣ የንግድና ሥራ ፈጣሪዎች፣ ምሁራንና ተመራማሪዎች፣ የገዢ እና ተፎካካሪ ፓርቲ አባላት፣ የሚዲያ ሰዎችና ከሌሎች ዘርፎች የተወከሉ ዝነኞች የንባብ ልምዳቸውን አካፍለዋል፤ የምጊዜም ምርጥ መጽሐፎቻቸውንም ጠቁመዋል።

በመቶ ቀናቱ ቆይታ የሀገር ውስጥና የውጭ ሀገር መጻሕፍት በዝነኞቹ የምንጊዜም ምርጥ መጽሐፎች እየተባሉ የተጠቆሙ ሲሆን፤ በርካታውን እጅ የሚይዙት የሀገር ውስጥ መጻሕፍት ናቸው።

በብዛት ከተጠቆሙ የሀገር ውስጥ መጽሐፎች፥ ነባር ልቦለዶች እንዲሁም የህይወት ታሪክና ግለ ታሪኮች ቅድሚያውን ወስደዋል።

ከእነዚህም መካከል፦ፍቅር እስከመቃብር፣ በሀዲስ ዓለማየሁ (ብዙ ጊዜ ተደጋሞ የተመረጠ መፅሃፍ)፣ኦሮማይ፣ በበዓሉ ግርማ፣የህይወቴ ታሪክ (ኦቶባዮግራፊ)፣ በፊታውራሪ ተ/ሐዋርያት ተ/ማርያም፣እሳት ወይ አበባ፣ በጸጋዬ ገ/መድኅን፣ የኤርትራ ጉዳይ፣ በአምባሳደር ዘወዴ ረታ፣ መጽሐፈ ትዝታ ዘዓለቃ ለማ ኃይሉ ወልደ ታሪክ፣ በመንግሥቱ ለማ፣ትዝታ፣ በሀዲስ ዓለማየሁ፣ህይወቴ፣ በደጃዝማች ወ/ሰማያት ገ/ወልድ፣የከፍተኛ ትምህርት ዘይቤ፣ በእጓለ ገ/ዮሐንስ፣ ህይወቴና የኢትዮጵያ ርምጃ፣ በግርማዊ ቀዳማዊ ኃ/ሥላሴ፣አደፍርስ፣ በዳኛቸው ወርቁ "የምንጊዜም ምርጥ" ተብለው በተሳታፊዎች በብዛት የተጠቀሱ መጻሕፍት ሲሆኑ፤ ከውጭ ሀገር መጻሕፍት መካከል ደግሞ ዘአልኬሚስትና ሌሎችም ይገኙበታል። 

ለተጨማሪው: https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
በሚሊኒየም አዳራሽ : የመዝሙር ኮንሰርት

የፊታችን እሁድ ሰኔ 2 ቀን 2016 ዓም በሚሊኒየም አዳራሽ የመዝሙር ኮንሰርት እንደተዘጋጀ ተገልጿል።

ኤልሀዳር ኢንጂነሪንግ ከዘማሪ ጳውሎስ ተገኝ ጋር በመተባበር «ዲልቢ ገለታ የሱሲፍ»የተሰኘውን የመዝሙር ድግስ በሚኒሊየም አዳራሽ የፊታችን እሁድ  ሰኔ 2 2016 ዓ.ም ቀኑ ከ7፡00 ጀምሮ ማዘጋጀቱን ዛሬ ግንቦት 27 2016 ዓ.ም በስካይ ላይት ሆቴል በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ተገልጿል።

ዘማሪ ጳውሎስ ተገኝ በዝማሬው ዓለም ውስጥ በመቆየት እና በርካታ የመዝሙር ስራዎችን በመስራት ይታወቃል።ሶስት አልበሞችን እና የተለያዩ መዝሙሮችን ከተለያዩ ዘማሪዎች ጋር በመስራት፣እንዲሁም 'ሙጫ ካዮ' ከተሰኘ የህፃናት ህብረት ጋር በመሆን ሁለት ቪሲዲዎችን በመስራት ለአማኞች አድርሷል።

በዚህ ፕሮግራም ለመሳተፍ የመግቢያ ዋጋው በነፃ ስለሆነ  መጨናነቅ እንዳይፈጠር ከጠዋቱ 4:00 ጀምሮ በሚሊኒየም አዳራሽ በሚካሄደው የመዝሙር ድግስ እንዲገኙ ጥሪ ተላልፏል።

ለተጨማሪው: https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
"ማለዳ" የተሰኘ ሀገርኛ ፊልም ተመረቀ

በድሮ ፒክቸር ተዘጋጅቶ የቀረበው”ማለዳ” የተሰኘ የሳሙኤል ካሣሁን ፊልም ትላንት ግንቦት 26 2016 ዓ.ም ጥሪ የተደረገላቸው የጥበብ ቤተሰቦች እና እንግዶች በተገኙበት በቀይ ምንጣፍ ሥነ -ሥርዓት ተመርቋል።

በፊልሙ ላይ ታሪኩ ብርሃኑ(ባባ)፣ መታሰቢያ ታደሰ ፣ ዘላለም ይታገሱ እና ሌሎችም በተዋናይነት ተሳትፈዋል።

“ ማለዳ “ፊልም የቤተሰብ ድራማ ዘውግ  እንደዳለው የተገለፀ ሲሆን ግንቦት 30 ሰኔ 1,2 እና ሰኔ 7,8 እና 9  በተመረጡ ሲኒማ ቤቶች መታየት ይጀምራል።

የ"ማለዳ" ፊልም አዘጋጅ ሳሙኤል ካሣሁን ከዚህ ቀደም ከተሳተፈባቸው ፊልሞች መካከል አሚን ፣አስርቱ ቀናት፣ የታሰረ ፍቅር ፣ ጊዜ ለኩሉ ፣ ትመጪ እንደሁ ፣ ቁልፉን ስጪኝ ፣ተከፍሏል ፣ ከሽሽት መልስ ይገኙበታል።

ለተጨማሪው: https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
አርቲስት ፍቃዱ ከበደ የክብር የእንግዳ የሆነበት አንጋፋው የኪነጥበብ ምሽት ረቡዕ ይካሄዳል

በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ባህል ማዕከል የሚዘጋጀው የኪነጥበብ መርሃግብር ነገ  ረቡዕ ግንቦት 28 2016 ዓ.ም ይካሄዳል።

በዕለቱ አርቲስት ፍቃዱ ከበደ"የአንድ ግጥም፣ የአንድ ወግ" የክብር እንግዳ ሆኖ  ይገኛል።

እንዲሁም ግጥሞች፣ ወግ፣ ሙዚቃና ሞኖሎግ ተሰናድተው እናንተ ውድ ታዳሚዎቻችንን በባህል ማዕከል አዳራሽ ከቀኑ በ11: 30 ጀምሮ ይጠብቃችኃል ብለዋል አዘጋጆቹ ።

ማስታወሻ :— ፕሮግራሙ ላይ ለመታደም የምትፈልጉ በአሁን ሰዓት የዩኒቨርስቲው ተማሪ ያልሆናችሁ የስነ ጽሑፍ አፍቃሪያን መግቢያው በ5ተኛ በር በኩል ነው።

ለተጨማሪው: https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
ተዋናይ አማኑኤል ሐብታሙ ከ42 ቀናት እስር በኋላ ዛሬ ዳይሬክተሩን ዳግማዊ ፈይሳ ጨምሮ ከ20 ተጠርጣሪዎች ጋር ፍርድ ቤት ቀረበ

ተዋናይ አማኑኤል ሐብታሙ እስራኤል አገር "እብደት በሕብረት" የተሰኘ ቴአትሩን ለማሳየት አውሮፕላን ሊሳፈር ሲል ሚያዝያ 15 ቀን 2016 ዓ/ም ከአዲስ አበባ ኤርፖርት በፖሊሶች ተይዞ ወደ አዲስ አበባ ፖሊስ ተወስዶ መታሰሩ ይታወሳል።

አማኑኤል በታሰረ ከ42 ቀናት በኋላ በዛሬው ዕለት ግንቦት 28 ቀን 2016 ዓ/ም ፖሊስ ፍርድ ቤት አቅርቦት የነበረ ሲሆን ፍርድ ቤቱ ፖሊስ የጠየቀውን ተጨማሪ ጊዜ ቀጠሮ በመፍቀድ ለሰኔ 11 ቀን ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል።

ተዋናይ አማኑኤል ሐብታሙ በተጨማሪም በቅርቡ በፖሊስ ተይዞ ለእስር የበቃው የ"እብደት በሕብረት" ቴአትር አዘጋጅ አንጋፋው ከያኒ ዳግማዊ ፈይሳን ጨምሮ ሌሎች 20 ሰዎችን በአንድ መዝገብ ለፌደራል መደበኛ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ ጊዜ ቀጠሮ ወንጀል ችሎት ቀርበው ሁሉንም ለሰኔ 11 ቀን 2016 ዓ/ም ተለዋጭ ቀጠሮ እንደተሰጣቸው ማረጋገጥ ችያለሁ።

መረጀው የያሬድ ሹመቴ ነው።

ለተጨማሪው: https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
የኪናዊ ዲጂታል መጽሔቶች ጥቆማ!

በኪነጥበብ፣ በሥነጥበብ ፣በሥነጽሑፍ፣ ማኅበራዊና ባህላዊ ጉዳዮች ላይ ትኩረታቸውን አድርገው ለአንባቢያን እየደረሱ ከሚገኙ ዲጂታል መጽሔቶች ውስጥ እንደ ኤቨንት አዲስ ድረገፅ የተወሰኑትን እንነግራችኋለን።

📍ቃላት

ቃላት ዲጂታል መጽሔት ሥነ-ጽሑፍ ፣ ኂስ ፣ ሙዚቃ፣ሲኒማ እና ሌሎችም ጉዳዮች ላይ ትኩረቱን ያደረገ ኪናዊ ዲጂታል መጽሔት ነው።

ቃላት ዲጂታል መጽሔት እስካሁን አስራ አንድ መጽሔቶችን ለአንባቢያን አድርሷል።

የቃላት የዲጂታል መጽሔት የቴሌግራም ገፅ:
https://news.1rj.ru/str/Words2014

📍ባይራ

ባይራ ዲጂታል መጽሔት በሥነጽሐፍ ፣በኪነጥበብና ማህበራዊ ፣ ባህላዊ ጉዳዮች ላይ የሚያተኮር ዲጂታል መጽሔት ነው።

ባይራ ዲጂታል መጽሔት ከስድስት በላይ ዲጂታል መጽሔቶችን ለአንባቢያን አድርሷል።

የባይራ ዲጂታል መጽሔቶች የቴሌግራም ገፅ:
https://news.1rj.ru/str/Bayradigital


📍 መዲና

መዲና ዲጂታል መጽሔት በኪነጥበብ፣ ሥነጽሑፍ እና በሌሎችም ጉዳዮች ላይ ትኩረቱን አድርገው ለአንባቢያን እየደረሰ የሚገኝ ዲጂታል መጽሔት ነው።

የመዲና ዲጂታል መጽሔት የቴሌግራም ገፅ:
https://news.1rj.ru/str/Medinamagazine


ኤቨንት አዲስ ድረገፅ እነዚህን ኪናዊ ዲጂታል መጽሔቶች በየገፆቻቸው እየገባችሁ እንድታነቡ ይጋብዛል።

ለተጨማሪው: https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
የአርቲስት ዘሪቱ ከበደ የመጀመሪያ ልጅ አረፈ

የአርቲስት ዘሪቱ ከበደ የ17 ዓመት የመጀመሪያ ልጇ ክርስቲያን ላቃቸው በድንገተኛ ህመም በህክምና ሲረዳ ቆይቶ ዛሬ ግንቦት 28 2016 ዓ.ም ከዚህ ዓለም በሞት መለየቱ ተሰምቷል።

ባለቤቷ ( የ3 ልጆቿ አባት ) የተወዳጁ የምንጊዜም የኢትዮጵያ እግር ኳስ ተጫዋች የመንግስቱ ወርቁ ልጅ ላቃቸው መንግስቱ  ነው።

በድንገት ያረፈው ክርስቲያን ላቃቸው  የ11ኛ ክፍል ተማሪ ነበር።

📍መረጀው የጌጡ ተመስገን ነው።

ለተጨማሪው: https://news.1rj.ru/str/EventAddis1