Event Addis Media – Telegram
Event Addis Media
9.62K subscribers
6.13K photos
14 videos
4 files
4.75K links
Connect with Addis artistic community!

Website: https://eventaddis.com

Contact: @Tmanaye
Download Telegram
"የአባቶች የአእምሮ ጤና:የቤተሰብ ብርታት" የተሰኘ ተከታታይ የሥነልቦና ውይይት ከእሁድ ጀምሮ ይካሄዳል

የአእምሮ ጤና ተሟጋች የሆነው እና የቤተሰብ የአእምሮ ደህንነት ላይ በመስራት የሚገኘው ሜንታል ሄልዝ አዲስ “የአባቶች የአእምሮ ጤና፡ የቤተሰብ ብርታት” በሚል መሪ ቃል ተከታታይ  መርሐግብር ለማሰናዳት እየተዘጋጀ እንደሆነ አስታውቋል።

ይህም አባቶች ጤናማ እና ብርቱ ቤተሰብ በማጎልበት ረገድ ስለሚጫወቱት ወሳኝ ሚና አፅንዖት ለመስጠትም ያለመ ነው ተብሏል።

ዝግጅቱን በዓለም አቀፍ የአባቶች ቀን እሁድ ሰኔ 9 2016 ዓ.ም ከቀኑ በ9፡00 ሰዓት ጀምሮ በኢሊሊ ኢንተርናሽናል ሆቴል በርካታ አባቶች በተገኙበት አባትነትን በመዘከር የመክፈቻ ፕሮግራም እንደሚደረግ ኤቨንት አዲስ ደስታ ድረገፅ ሰምቷል።

የዚህ መርሐግብር መግቢያ ሁለት መቶ ብር ነው።

ለተጨማሪው :https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
የአርቲስት ሃጫሉ ሁንዴሳ ሽልማት በዚህ ወር ይካሄዳል

የአርቲስት ሃጫሉ ሁንዴሳ ሽልማት የፊታችን ሰኔ 22 ቀን 2016 ዓ.ም እንደሚካሄድ አዘጋጆቹ አስታውቀዋል።

ዘንድሮ ለሶስተኛ ጊዜ የሚካሄደው የሃጫሉ ሽልማት በ11 የሽልማት ዘርፎች፤ በአፋን ኦሮሞ የተሰሩ የዓመቱ ምርጥ አልበም፣ የአመቱ ምርጥ ግጥምና ዜማ ደራሲ፣ የዓመቱ ምርጥ አቀናባሪ፣ ምርጥ የባህል ዘፈን፣ ምርጥ ዘመናዊ ሙዚቃ፣ የዓመቱ ምርጥ ወንድ እና ሴት አርትስቶች፣ የኣመቱ ምርጥ አዲስ ሙዚቀኛ (ሴት እና ወንድ)፣ ምርጥ የአመቱ የሙዚቃ ቪዲዮ፣ ሲኒማቶግራፊ እና ምርጥ ባህላዊ ውዝዋዜ በሚሉ ዘርፎች እንደሚሸለሙ ታውቋል፡፡

በሽልማት ውድድሩ ውስጥ ሚካተቱ የሙዚቃ ስራዎች ከመጋቢት 22 ቀን 2015 ዓ.ም እስከ መጋቢት 21 ቀን 2016 ዓ.ም የወጡ ብቻ ናቸው ተብሏል፡፡

ለተጨማሪው :https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
እማዬ እንዳለች ኑ ቡና ጠጡ ብላለች!

በአዲስ አበባ ከተማ መስቀል አደባባይ ከዛሬ ሰኔ 8 እስከ ነገ ሰኔ 9 2016 ዓ.ም ለአዲስ አበባ ህዝብ ቡና በነፃ እየተጋበዘ ነው።

ይህ አዲስ ነገር በአዲስ ዓመት ነፃ ቡና ዝግጅት ሙዚቃ ፣ፋሽን ሾዎችን መዝናኛዎችን እና የተለያዩ አዝናኝ ዝግጅቶችን ማሰናዳታቸውን እና ህብረተሰቡ በነጻ ቡና እየጠጣ እንዲዝናና አዘጋጆቹ ታሜሶል ኮሚዩኒኬሽን አሴቲክስ ሶሉሽን እና ከሊያን ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል።

#Ads

ለተጨማሪው :https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
የወንዲ ማክ አልበም ሰኔ 14 ይለቀቃል

የድምፃዊ ወንደሰን መኮንን በመድረክ ስሙ (ወንዲ ማክ) "ይንጋልሽ" የተሰኘ አዲስ አልበም የፊታችን ሰኔ 14 2016 ዓ.ም ለአድማጮች እንደሚደርስ ኤቨንት አዲስ ድረገፅ ሰምቷል።

ድምጻዊው በይፋዊ የማህበራዊ ትስስር ገፁም "እነሆ አርብ ሠኔ 14 ቁርጥ ቀን ሆነ "ይንጋልሽ " ብለን ከንጋት የተቃጠርንበት አልበማችንን ወደ እናንተ የምናደርስበት ሠላም ያቆየን" ብሏል።

ይህም አልበም ዩቲዩብን ጨምሮ በተለያዩ ዓለምአቀፍ የሙዚቃ መተግበሪያዎች ላይ ይለቀቃል ተብሏል።

ለተጨማሪው :https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
ጋዜጠኛ ፀጋዬ ወንድወሰን የ"ቮይስ ኦፍ ሚዲያ" የኢትዮጵያ ተወካይ ሆኖ ተመረጠ፡፡

በፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት የሬድዮ እና ቴሌቪዥን ዜናዎቹ የምናዉቀውና በያዝነው አመት መጀመሪያ አዲስ ዋልታ ቴሌቪዥንን የተቀላቀለው ጋዜጠኛ ፀጋዬ ወንድወሰን የ"ቮይስ ኦፍ ሚዲያ "የኢትዮጵያ ተወካይ ሆኖ እንደተመረጠ በማህበራዊ ትስስር ገፁ አስታውቋል።

ጋዜጠኛ ፀጋዬ በማህበራዊ ትስስር ገፁ ባሰፈረው መረጃ "ቮይስ ኦፍ ሚዲያ" መቀመጫውን በህንድ ሙምባይ ከተማ ያደረገ መንግስታዊ ያልሆነ ድርጅት ነው።

የጋዜጠኞችን ሙያዊ ክህሎት እና ቤተሰቦቻቸውን  ህይወት ማሻሻል ላይ ትኩረት አድርጎ የሚሰራው ድርጅቱ በመላው ዓለም ያሉ ጋዜጠኞችን "ቮይስ ኦፍ ሚዲያ" በሚል ስያሜ ከፈረንጆቹ 2021 ጀምሮ ለማስተባበር እየሰራ ያለ ተቋም ነው። ዋና ዋና አምስት መርሆችን አሉኝ የሚለው ድርጅቱ ጋዜጠኝነትን ማስፋፋት እና የጋዜጠኞችን አኗኗር ማሻሻል ላይ አልሞ የሚሰራ ነው፡፡ 

ኢቨንት አዲስ ከጋዜጠኛ ፀጋዬ ወንድወሰን ባገኘው መረጃ  "ድርጅቱ በዋናነት የጋዜጠኞችን የመኖሪያ ቤት፣ የጤና፣ የጋዜጠኛ ልጆችን በትምህርት መደገፍን ጨምሮ የጋዜጠኞችን ክህሎት እና የድህረ ጡረታ ፈተናዎች ላይ ትኩረቱ አድርጎ ይሰራል፡፡"

"ቮይስ ኦፍ ሚዲያ" በኢትዮጵያ ለሚያደርጋቸው እንቅስቃሴዎች ጋዜጠኛ ፀጋዬ ወንድወሰንን በበጎ ፍቃደኛ ተወካይነት ሲመርጥ ፤ በዋናነት ለዚሁ ስራ በጎ ፈቃደኛ እና ተነሳሽነት ያላቸውን ሌሎች ኢትዮጵያዊያን ጋዜጠኞችንም የሚያካትት መሆኑንም ሰምተናል፡፡

ለተጨማሪው :https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
#ዮቶር_ድግስ

የግጥምና ዜማ ደራሲ አለማየሁ ደመቀ የ25 ዓመት የሙዚቃ ጉዞ የሚዘከርበት ኮንሰርት ቅዳሜ ይካሄዳል

የተወዳጁ የሙዚቃ ግጥምና ዜማ ደራሲውን አለማየሁ ደመቀን የሩብ ክ/ዘመናት የሙዚቃ ጉዞ የሚያወሳ እና እርሱንም የሚዘክር "ዮቶር ድግስ" የተሰኘ የሙዚቃ ኮንሰርት የፊታችን ቅዳሜ ሰኔ 15 2016 ዓ.ም በማሪዮት ሌግዥሪ ሆቴል ይካሄዳል ተብሏል።

በሙዚቃ ባለሙያው የ25 ዓመታት ጉዞ ውስጥ የእርሱን ተወዳጅ እና ዘመን ተሻጋሪ የግጥምና ዜማ ስራዎች ወስደው ከተጫወቱ ድምፃውያን መካከል ጎሳዬ ተስፋዬ ፣ኃይልዬ ታደሰ ፣ አብነት አጎናፍር ፣ግርማ ተፈራ ካሣ ፣ ሐሊማ አብዱራህማን፣ ሔለን በርሔ ፣ ዳዊት ፅጌ ፣ብስራት ሱራፌል ፣ አዲስ ለገሰ፣አንተነት ምናሉ ፣ አበባው ጌታቸው ፣ ዳግማዊ ታምራት ፣መስከረም ኡስማን በኮንሰርቱ ላይ እንደሚሳተፉ የሙዚቃ ስራቸውንም እንደሚያቀርቡ ተገልጿል።

ከድምጻዊያኑ በተጨማሪም ኢትዮ ለዛ ባንድ፣ ሻኩራ ባንድ፣ ብርኩማ ባንድ የተሰኙ ባንዶች ድምጻዊያንን ያጅባሉ ተብሏል።

በዕለቱም በ "ዮቶር ድግስ" ከኮንሰርቱ በተጨማሪም በቅርቡ ለአንባቢያን የደረሰው  "ዮቶር ቁጥር 2" መጽሐፍ ይመረቃል ስለመባሉ ኤቨንት አዲስ ድረገፅ ሰምቷል።

የኮንሰርቱ መግቢያ 3000 ብር ሲሆን ትኬቱን በቴሌ ብር ሱፐር አፕ ፣በማርዮት ሆቴል ፣ በአቻሬ ጫማ እንደሚገኝ አዘጋጆቹ አስታውቀዋል።

አለማየሁ ደመቀ ከ1991 ዓ.ም አንስቶ ከ250 በላይ የሆኑ የሙዚቃ ስራዎችን ለ15 ጊዜያት ያህል ተደጋግሞ የታተመውን “ዮቶር 1 : ኮብላዩ ካሕን” እና በቅርቡ ለንባብ የበቃውን “ዮቶር 2 ” ለሥነ-ጽሑፍ አፍቃሪያን ያበረከተ ሲሆን ላለፉት 25 ዓመታት በሙያው፣ በክህሎቱ እና በተሰጥዖው አገር እና ወገንን ሲያገለግል እንደቆየ ይታወሳል።

ለተጨማሪው :https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
ጋዜጠኛ ዕዝራ እጅጉ ዕውቅና ተሰጠው

ቴክሳስ ዳላስ የሚገኘው አድዋ የታሪክና የባህል  ህብረት  በዘንድሮው 8ኛው የአርአያ ሰው ሽልማት በግለ ታሪክ ዘርፍ ጋዜጠኛ  ዕዝራ እጅጉን ልዩ ተመስጋኝ አድርጎታል።

ጋዜጠኛ ዕዝራ፣ ጸሀፌ ትዕዛዝ አክሊሉ ኃብተወልድን የመሠሉ የሀገር ባለውለታዎችን የህይወት ታሪክ በሲዲና በዲቪዲ ያሳተመ ሲሆን ይሄንኑ ታሪክ በእንግሊዝኛ  አዘጋጅቶታል።

በተጨማሪም ከ20ዐ9 አንስቶ ባለፉት 7 ዓመታት የ45 ሠዎችን ታሪክ በሲዲ ሠርቶ  ለማስመቅ ችሏል።

በተጨማሪም በአገራችን  ታዋቂ የሆኑ እንደ ማማ በሰማይ ፤ ማህሌት፣ የአክሊሉ ማስታወሻ፤ የመሳሰሉት 30 የሚጠጉ መጽሀፎችን ወደ ድምጽ በመቀየር ማንበብ ለማይችሉ ሰዎች እዝራ እና ድርጅቱ "ተወዳጅ ሚዲያ" መላ ዘይደዋል።

በተጨማሪም የታዋቂ ኢትዮጵያን ታሪክ በባለታሪኮች እና በልጆቻቸው አሰሪነት ተጠይቆ 14 መጽሀፎችን አዘጋጅቷል፡፡

እዝራ ታሪክን የሚሰንድበት "ተወዳጅ ሚዲያ" የተሰኘ የራሱ ድረገጽ፤ ፌስቡክ እና ዩቲዩብ ያለው ሲሆን ወደ ፊት በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎችን በ10 ዓመት ጊዜ ውስጥ በአንድ ገጽ ብቻ ታሪካቸውን ጽፈው እንዲልኩ እየጣረ እንደሚገኝ ለኤቨንት አዲስ ድረገፅ ተናግሯል።

በዘንድሮው 8ኛው የአርአያ ሰው ሽልማት 16 የሚሆኑ ተሸላሚዎች ያሉ ሲሆን ከእነዚህም ውስጥ የቱሪዝም አባት አቶ ኃብተስላሴ ታፈሰ ፣አርክቴክት ፋሲል ጊዮርጊስ ፣ጸሀፌ ተውኔት አያልነህ ሙላቱ፣ ዶክተር  እንዳለጌታ ከበደ እና ሌሎችም  ይገኙበታል ተብሏል።

የአርአያ ሠው ሽልማት ሰኔ 13 2016 ዓ.ም በዮድ አቢሲኒያ የሽልማት ሥነሥርዓት ይከናወናል።

ለተጨማሪው :https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
በኢትዮጵያ ደራሲያን ማኅበር የተዘጋጀው የሥነጽሑፍ ሥልጠና በሚመጣው የክረምት ወቅት ይካሄዳል

በኢትዮጵያ ደራሲያን ማኅበር በየዓመቱ የሚዘጋጀው የክረምት የሥነጽሑፍ ስልጠና ዘንድም ለዘጠኛ ጊዜ ይካሄዳል ተብሏል።

ከዚህ በፊት በተካሄዱ ስምንት ዙሮች በርካታ የሥነጽሑፍ ወዳጆች ስልጠናውን እንደወሰዱ ተነግሯል።

በልቦለድ ክሂል ፣በልቦለድና ኢ ልቦለድ፣ በግጥም ፣ በፎክሎር ፣ በሥነጽሑፋዊ ታሪክ ፣በሥነሂስ በሌሎችም የሥነጽሑፍ ዓይነቶች ዘንድሮም ለዘጠነኛ ጊዜ ምዝገባ እንደተጀመረ ኤቨንት አዲስ ድረገፅ የደረሰው መረጃ ያመለክታል።

ለበለጠ መረጃ በተከታዩ ስልክ ቁጥር ደውሉ  0911448297 ተብላችኋል።

📍ሼር ያደርጉ:

ለተጨማሪው :https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
የጆርጋ መስፍን ‘ከሁሉ የላቀው ደግ’ የተሰኘው አልበም ባንድ ካምፕ ዴይሊ በግንቦት ወር ‘በባንድ ካምፕ ላይ የሚገኙ ምርጥ ጃዞች’ በሚል ካካተታቸው አልበሞች አንዱ እንደሆነ ኤቨንት ድረገፅ ከሙዚቃዊ ያገኘው መረጃ ያመለክታል።

የሙዚቀኛ ጆርጋ መስፍን ቀደም ሲል ‘ደጋጎቹ‘ በሚል ርዕስ ለአድማጮች ያደረሰውና በድጋሜ ተሰርቶ "ከሁሉ የላቀው ደግ" የሚል ስያሜ የተሰጠው የኢትዮ ጃዝ አልበም ባሳለፍነው ግንቦት 16 2016 ዓ.ም በሙዚቃዊ ዩቲዩብ ቻናል እና በዓለምአቀፍ የሙዚቃ ማሰራጫ መተግበሪያዎች በኩል እንደተለቀቀ ይታወሳል።

በሙዚቃ ሞያ ውስጥ ፕሮፌሽናል ሙዚቀኛ በመሆን ከ17 ዓመታት በላይ ያሳለፈው ሙዚቀኛ  ጆርጋ መስፍን ቀደም ሲል ‘የላቁት ደጋጎች’ አሁን ደግሞ ‘ከሁሉ የላቀው ደግ’ በሚል ርዕስ በቅርቡ ያወጣው አልበም ነው፡፡

የጆርጋ መስፍን"ከሁሉ የላቀው ደግ" አልበም  ግንቦት 16 2016 ዓ.ም ጀምሮ በተካሄደው "አዲስ ጃዝ ፌስቲቫል" በአፍሪካ ጃዝ ቪሌጅ ተመርቋል።

በ1999 ዓ.ም ጆርጋ ከጓደኞቹ ጋር በመሰባሰብ የቀረጸው ይህ አልበም የጆርጋ መንፈስን ያንጸባርቃል ተብሏል።

በፈረንጆቹ አቆጣጠር በ2007 የተመሰረተውና ዋና መስሪያ ቤቱን አሜሪካ ካሊፎርንያ ያደረገው ባንድ ካምፕ በግንቦት ወር ‘በባንድ ካምፕ ላይ የሚገኙ ምርጥ ጃዞች’ በሚል ካካተታቸው አልበሞች አንዱ እንደሆነ አስታውቋል።

ለተጨማሪው: https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
አርቲስት መስከረም አበራ የክብር እንግዳ የሆነችበት አንጋፋው የኪነጥበብ ምሽት ረቡዕ ይካሄዳል

በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ባህል ማዕከል የሚዘጋጀው የኪነጥበብ መርሃግብር  ረቡዕ ሰኔ 12  2016 ዓ.ም ይካሄዳል።

በዕለቱ አርቲስት መስከረም አበራ "የአንድ ግጥም፣ የአንድ ወግ" የክብር እንግዳ ሆኖ ትገኛለች።

እንዲሁም ግጥሞች፣ ወግ፣ ሙዚቃና ሞኖሎግ ተሰናድተው እናንተ ውድ ታዳሚዎቻችንን በባህል ማዕከል አዳራሽ ከቀኑ በ11: 30 ጀምሮ ይጠብቃችኃል ብለዋል አዘጋጆቹ ።

ማስታወሻ :ፕሮግራሙ ላይ ለመታደም የምትፈልጉ በአሁን ሰዓት የዩኒቨርስቲው ተማሪ ያልሆናችሁ የስነ ጽሑፍ አፍቃሪያን መግቢያው በ5ተኛ በር በኩል ነው።

ለተጨማሪው: https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
የጋዜጠኛ መኮንን ወ/አረጋይ መጽሐፍ ለንባብ በቃ

የጋዜጠኛ መኮንን ወ/አረጋይ "እነሆ ማሟሻ" የተሰኘ አዲስ መጽሐፍ ዛሬ ሰኔ 10 2016 ዓ.ም ለአንባቢያን እንደቀረበ ኤቨንት አዲስ ድረገፅ ሰምቷል።

ከዚህ ቀደም በሸገር ኤፍ ኤም 102.1 ሬድዮ ላይ በሚያቀርባቸው የስንክሳር፣  የማሟሻ፣ የአርብ ምሽት ቆየት ያሉ ሙዚቃዎች እና አሁን ላይ በኢንቢሲ ቴሌቪዥን በልዩ ልዩ ዝግጅቶች የምናውቀው የጋዜጠኛ መኮንን ወ/አረጋይ "እነሆ ማሟሻ" የተሰኘ መጽሐፍ የመጀመሪያ ቅጽ መጽሐፉ ነው ተብሏል።

መጽሐፉ በ200 ገፆች የተነበበ ሲሆን በ250 ብር የጀርባ ዋጋ ለአንባቢያን ቀርቧል።

መጽሐፉን በጃፋር ፣በእነሆ እና በእውቀት በር መጻሕፍት መደብሮች ላይ ይገኛል ተብሏል።

ለተጨማሪው: https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
የድምጻዊት ቬሮኒካ አዳነ "መጠሪያዬ" አልበም

ድምጻዊት ቬሮኒካ አዳነ"መጠሪያዬ" የተሰኘ የመጀመሪያ አልበሟን በዚህ ዓመት ነሐሴ 17 2016 ዓ.ም ለአድማጭች እንደምታደርስ ኤቨንት አዲስ ድረገፅ ያገኘው መረጃ ያመለክታል።

ዛሬ የ29ኛ ዓመት ልደቷን እያከበረች የምትገኘው ድምጻዊት ቬሮኒካ አዳነ በማህበራዊ ትስስር ገጿ"መጠሪያዬ" የተሰኘዉ ሶስት ዓመት የለፋሁበት ብዙ ያየሁበት የመጀመርያ አልበሜ ነሐሴ 17 ይለቀቃል " ብላለች።

በተጨማሪም "ከዚህ በኃላ የምለቃቸዉ ፎቶዎች ላይ ስለ አልበሙ አንድ አንድ ነገሮች እላችዋለው አዳዲስ ነገሮችም አሉ "ስትል ሀሳቧን አስፍራለች።

ይህ የድምጻዊት ቬሮኒካ አዳነ" መጠሪያዬ" የተሰኘ አዲስ አልበም ሶስት ዓመት ገደማ እንደፈጀም ተነግሯል።

ድምጻዊት ቬሮኒካ አዳነ ከዚህ ቀደም ኩርፊያ  ፣ ጥፍጥ አለኝ ፣ ተው ፣አበባዬ ፣እናነዬን ጨምሮ ሌሎችንም ነጠላ ሙዚቃዎች ለአድማጮች አድርሳለች።

ለተጨማሪው: https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
የድምጻዊ ፍፁም ቲ አልበም አርብ ይለቀቃል

የድምጻዊ ፍፁም ቲ "አያዳላም" የተሰኘ አዲስ አልበም የፊታችን አርብ ሰኔ 14 2016 ዓ.ም በፍፁም ቲ የዩቲዩብ ቻናል እና በሌሎችም የሙዚቃ መተግበሪያዎች ላይ እንደሚለቀቅ ኤቨንት አዲስ ድረገፅ ሰምቷል።

አልበሙን ወንድወሰን ይሁብ በሪኮርዲንግ ፕሮዲዩሰርነት ያዘጋጀው ሲሆን በርካታ የሙዚቃ ባለሞያዎች ተሳትፈውበታል ተብሏል።

"አያዳላም" አልበም ይጣራል ፣ድክም አለኝ፣ እኔ አልዋስም፣ አዲስ አበባን ጨምሮ አስር የሙዚቃዎች ስራዎችን ይዟል ተብሏል። ከእነዚህም የሙዚቃ ስራዎች ውስጥ ለአንዱ የሙዚቃ ቪዲዮ ተዘጋጅቶለታል።

ድምጻዊ ፍፁም ቲ ይህን አልበም ለመስራት ከአሜሪካ አትላንታ ወደ ኢትዮጵያ ሲመላለስ እንደቆየ አስታውቋል።

ድምጻዊው ፍፁም ቲ "አዲስ አባ" በተሰኘው ሙዚቃ ስራው በርካቶች ያስታውሱታል።

ለተጨማሪው: https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
የድምጻዊት Iri Di ገሚስ አልበም !

ከኢትዮጵያ ሐመር የተገኘችው ዓለምአቀፏ ድምጻዊት Iri Di ገሚስ አልበሟን የፊታችን ሀሙስ ትለቃለች።

በቅርቡ በሮፍናን ኑሪ "ኖር " አልበም ውስጥ "መንገድ" በተሰኘው ሙዚቃ ላይ በአጃቢ ድምጻዊት የሰማናት ትውለደ ኢትዮጵያዊቷ lri Di በእንግሊዝኛ "Sound of Rain" የተሰኘ ርዕስ የተሰጠችውን ገሚስ አልበሟን ሐሙስ ሰኔ 13 2016 ዓ.ም ለአድማጮች እንደምትደርስ ኤቨንት አዲስ ድረገፅ ከድምጻዊቷ ያገኘው መረጃ ያመለክታል።

ከደቡብ ኢትዮጵያ ሐመር የተገኘችው ድምጻዊት Iri Di በእንግሊዝኛና ፈረንሳይኛ ቋንቋቸው በተለያዩ መድረኮች ላይ  የሙዚቃ ስራዎቿን አቅርባለች።

Iri Di ከድምጻዊነቷ ባሻገር የሙዚቃ ግጥምና ዜማ ደራሲ እንዲሁም ጊታሪስት ነች።

ድምጻዊቷ ከዚህ ቀደም ወየ መላ ፣ ባርዴዴ፣ ሌት ናይት ቡና የተሰኙ ሙዚቃዎችን ጨምሮ ሌሎችንም ሙዚቃዎች ለአድማጮች አድርሳለች።

የቀደመ ሙዚቃዎቿን በስሟ በተከፈተው የዩቲዩብ ቻናሏ https://youtu.be/okSTVC-FJtw?si=csHO8TRQeybxIC0Q መከታተል ትችላላችሁ ተብላችኋል።

ለተጨማሪው: https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
በአንጋፋው ወመዘክር አዳራሽ "የወር ወንበር" የተሰኘ ወርሃዊ ዝግጅት መካሄድ ሊጀምር ነው

በአንጋፋው የኢትዮጵያ ቤተመዛግብትና ቤተመጻሕፍት አገልግሎት  (ወመዘክር አዳራሽ) "የወር ወንበር" የተሰኘ ወርሃዊ ዝግጅት መካሄድ ሊጀምር እንደሆነ ኤቨንት አዲስ ድረገፅ ከአገልግሎቱ ያገኘው መረጃ ያመለክታል።

ተቋሙ በማህበራዊ ትስስር ገፁ"የኢትዮጵያ ቤተ መዛግብትና ቤተ መጻሕፍት ወመዘክር ነባሩ የሐሳብ ክምችታችን ነው። በዚሁ ክምችት አጠገብ ተቀምጠን አንዳንድ ሐሳቦችን በወር ለአንድ ቀን ከአንድ ቀንም ለአንድ ሠዓት ተኩል ረግተን ብንወያይ ደህና ነው " ብሏል።

በመጀመሪያው ወር  “የወር ወንበር” ፕሮግራም የፊታችን ቅዳሜ ሰኔ 15 2016 ቀን ከቀኑ 10:30 ጀምሮ “ከርሠ ግጥም” በሚል አርዕስት የሦስት ግጥሞች ምልከታ ላይ ውይይት ይካሄዳል ተብሏል።

በዚህ ውይይት ላይ መነሻ ሀሳብ በይኩኖ አምላክ መዝገቡ የሚቀረብ ሲሆንበኢትዮጵያ ቤተ መዛግብት እና ቤተ መጻሕፍት (ወመዘክር) ግቢ ኅሩይ ወልደ ሥላሴ አዳራሽ ውስጥም ውይይቱ ይካሄዳል ተብሏል።

ለተጨማሪው: https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ሙዚየም ሊታደስ ነው

አምስት ኪሎ የሚገኘው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ሙዚየም ሙሉ ህንፃ እድሳት ሊደረግለት እንደሆነ ተነግሯል።

ዛሬ ሰኔ  11 2016 ዓ.ም የኢትዮጵያ ቅርስ ባለስልጣን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ሙዚየም ህንፃ እድሳትን ለማከናወን ከሀብታሙ ጠቅላላ ስራ ተቋራጭ  ጋር የውል ስምምነት አድርጓል።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ሙዚየም ህንፃ ሙሉ ጥገና እንደሚደረግለትና የጥገና ፕሮጀክቱን ለማጠናቀቅ የአንድ ዓመት ጊዜ እንደሚወስድ በስምምነቱ ላይ ተገልጿል፡፡

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ሙዚየም በእውቁ አርክቴክት በጋሻውበዛ ተስፋሚካኤል በደርግ ጊዜ የተነደፈ ሲሆን በጥሬ ህንጻ (brutalism) የዓለም ህንጻዎች መዝገብ የሰፈረ ብቸኛው የአገራችን ዘመናዊ ህንጻ ነው።

ለተጨማሪው: https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
ተወዳጁ ተዋናይ አማኑኤል ሐብታሙን ጨምሮ ብዛታቸው 20 እንደሆኑ በፖሊስ ለፍርድ ቤት የቀረበ ማመልከቻ ላይ የተጠቀሱት ተጠርጣሪዎች ዛሬ በድጋሚ ፍርድ ቤት ቀርበዋል።

አማኑኤል በታሰረ ከ42 ቀናት በኋላ ግንቦት 28 ቀን 2016 ዓ/ም ከያኒ ዳግማዊ ፈይሳን ጨምሮ ሌሎች 20 ግለሰቦችን ፖሊስ ፍርድ ቤት አቅርቦት የነበረ ሲሆን ፍርድ ቤቱ ፖሊስ የጠየቀውን ተጨማሪ ጊዜ ቀጠሮ በመፍቀድ ለሰኔ 11 ቀን ተለዋጭ ቀጠሮ መስጠቱ ይታወሳል።

ዛሬ ሰኔ 11 ቀን 2016 ዓ/ም በዋለው ችሎት ፖሊስ በድጋሚ ተጨማሪ የ14 ቀናት የምርመራ ጊዜ እንዲፈቀድለት የጠየቀ ሲሆን የተከሳሽ ጠበቆች የተጨማሪ ምርማራ ጊዜ ጥያቄው ውድቅ እንዲደረግ ሰፊ ክርክር አድርገዋል።

ተዋናይ አማኑኤል ሐብታሙን ጨምሮ ለሌሎቹም ጠበቃ ሆነው ከቀረቡት ጠበቆች መሐል አንዱ የሆኑት ጠበቃ አያሌው እንደገለጹልኝ ከሆነ፤ ከዚህ ቀደም ፍርድ ቤቱ ፖሊስ ተከሳሾችን በተናጠል ዘርዝሮ እንዲያቀርብ ያዘዘውን ትዕዛዝ ተግባራዊ አለማድረጉን በክርክሩ ላይ በማንሳት፤ በቀጠሮ ማራዘሚያ ጥያቄው ላይ በተቀመጠው ምክንያት መሰረት "በማሕበራዊ ሚዲያ ሀሰተኛ መረጃ በማሰራጨት" ተብሎ የተጠቀሰው ወንጀል ማሕበራዊ ሚዲያ አደባባይ ላይ ያለ ምንም የተለየ ጊዜ የሚያስጠይቅ ጉዳይ አለመሆኑን አንስተው ተከራክረዋል።

ሰፊ ክርክር ከተደረገ በኋላ ጠበቆች ባነሱት የመከራከሪያ ሃሳብ መሰረት የተከሳሾች ምርመራ መዝገብ ለፍርድ ቤቱ ቀርቦ ፍርድ ቤቱ አቤቱታ እና ዝርዝር ማስረጃዎች በመመልከት የዋስትና መብት ፈቃድን ወይም የጊዜ ቀጥሮ ፈቃድ ላይ ተገቢውን ትዕዛዝ ለመስጠት የፊታችን ሐሙስ ሰኔ 13 ቀን 2016 ዓ/ም ጠዋት 4፣00 ሰዓት ላይ ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል።

መረጃው የያሬድ ሹመቴ ነው።

ለተጨማሪው: https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
በዕይታ ላይ ያሉ የሥዕል አውደርዕዮች

📍የሠዓሊ ኃይለገብርኤል ንጉሴ የሥዕል ስራዎች የሚቀረበብት "The light Path" የሥዕል አውደርዕይ ከቅዳሜ ሰኔ 8 2016 ዓ.ም ጀምሮ መስቀል አደባባይ አካባቢ በሚገኘው የአዲስ አበባ ሙዚየም ውስጥ ላይ በእይታ ይገኛል።ይህም የሥዕል አውደርዕይ እስከ ሰኔ 23 2016 ዓ.ም በእይታ ላይ ይቆያል ተብሏል።

📍 የእውቁ ሠዓሊ ብሩክ የሺጥላ "የይቅርታ ጉዞ" የተሰኘ የሥዕል አውደርዕይ ሰኔ 6 2016 ዓ.ም ቦሌ አትላስ መብራት አካባቢ በሚገኘው የኢትዮጵያ ሜትሮፖሊታን የሥዕል ማሳያ ውስጥ ለእይታ በቅቷል።ይህ የሥዕል አውደርዕይ እስከ ሰኔ 23 2016 ዓ.ም በእይታ ላይ ይቆያል።

📍የሠዓሊ ዮናታን ወንደሰን ሥዕል ስራዎች የሚቀርቡበት "ከአጥሮች ባሻገር" የሥዕል አውደርዕይ ከአርብ ሰኔ 7 2016 ዓ.ም ጀምሮ ካዛንቺስ በሚገኘው ፈንድቃ የባህል ማዕከል ውስጥ ለእይታ በቅቷል። ይህ የሥዕል አወድርዕይ እስከ ሰኔ 21 2016 ዓ.ም ይቆያል ተብሏል።

📍የሠዓሊ ዳዊት ገረሡ "አሁን" የተሰኘ የሥዕል አውድርዕይ ከግንቦት 23 2016 ዓ.ም ጀምሮ ስድስት ኪሎ በሚገኙ ገብረክርስቶስ ደስታ ዘመናዊ ቤተመዘክር ውስጥ በእይታ ይገኛል።እስከ ሰኔ 14 2016 ዓ.ም በእይታ ላይ ይቆያል።

ለተጨማሪው: https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
Event Addis Media
Photo
የሐሙስ መረጃዎች

የሳምንቱ ኪናዊ መረጃዎች ቀጥሎ ይቀርባሉ!

መረጃውን ሲጠቀሙ ምንጭ ይጠቅሱ!

📍ሙዚቃ

- የድምፃዊ ጉቱ አበራ “ጋፊኮ” የተሰኘ የመጀመሪያ አልበም ነገ አርብ ሰኔ 14 2016 ዓ.ም የድምጻዊው ዩቲዩብ ቻናልን ጨምሮ በተለያዩ ዓለምአቀፍ የሙዚቃ መተግበሪያዎች ላይ ይለቀቃል ተብሏል። "ጋፊኮ" አልበም ስምንት የሙዚቃ ስራዎችን ይዟል። ጉቱ አበራ ከዚህ ቀደም ሀዋንሀዋ፣ ዴሚ፣ አነቱ፣ኢዮሌ የተሰኙ ሙዚቃዎችን ለአድማጮች ማድረሱ አይዘነጋም።

-የድምፃዊ ወንደሰን መኮንን በመድረክ ስሙ (ወንዲ ማክ) "ይንጋልሽ" የተሰኘ አዲስ አልበም ነገ አርብ ሰኔ 14 2016 ዓ.ም ለአድማጮች እንደሚደርስ ኤቨንት አዲስ ድረገፅ ሰምቷል።14 ሙዚቃዎችን የያዘው አልበሙ ግጥም እና ዜማው በራሱ በወንዲ ማክ ተሰርቷል። በፍቅር፣ በማህበራዊ እና ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ የሚያጠነጥን እንደሆነ ተነግሯል።ይህም አልበም ዩቲዩብን ጨምሮ በተለያዩ ዓለምአቀፍ የሙዚቃ መተግበሪያዎች ላይ ይለቀቃል ተብሏል።

- የድምጻዊ ፍፁም ቲ "አያዳላም" የተሰኘ አዲስ አልበም ነገ አርብ ሰኔ 14 2016 ዓ.ም በፍፁም ቲ የዩቲዩብ ቻናል እና በሌሎችም የሙዚቃ መተግበሪያዎች ላይ ይለቀቃል።አልበሙን ወንድወሰን ይሁብ በሪኮርዲንግ ፕሮዲዩሰርነት ያዘጋጀው ሲሆን በርካታ የሙዚቃ ባለሞያዎች ተሳትፈውበታል ተብሏል።

- በቅርቡ በሮፍናን ኑሪ "ኖር " አልበም ውስጥ "መንገድ" በተሰኘው ሙዚቃ ላይ በአጃቢ ድምጻዊት የሰማናት ትውለደ ኢትዮጵያዊቷ lri Di በእንግሊዝኛ "Sound of Rain" የተሰኘ ርዕስ የተሰጠችውን ገሚስ አልበሟን ዛሬ ሐሙስ ሰኔ 13 2016 ዓ.ም ለአድማጮች እንደምትደርስ ኤቨንት አዲስ ድረገፅ ከድምጻዊቷ ያገኘው መረጃ ያመለክታል።Iri Di ከድምጻዊነቷ ባሻገር የሙዚቃ ግጥምና ዜማ ደራሲ እንዲሁም ጊታሪስት ነች።ድምጻዊቷ ከዚህ ቀደም ወየ መላ ፣ ባርዴዴ፣ ሌት ናይት ቡና የተሰኙ ሙዚቃዎችን ጨምሮ ሌሎችንም ሙዚቃዎች ለአድማጮች አድርሳለች።

- ተወዳጁ የሙዚቃ ግጥምና ዜማ ደራሲውን አለማየሁ ደመቀን የሩብ ክ/ዘመናት የሙዚቃ ጉዞ የሚያወሳ እና እርሱንም የሚዘክር "ዮቶር ድግስ" የተሰኘ የሙዚቃ ኮንሰርት የፊታችን ቅዳሜ ሰኔ 15 2016 ዓ.ም በማሪዮት ሌግዥሪ ሆቴል ይካሄዳል ተብሏል።በሙዚቃ ባለሙያው የ25 ዓመታት ጉዞ ውስጥ የእርሱን ተወዳጅ እና ዘመን ተሻጋሪ የግጥምና ዜማ ስራዎች ወስደው የተጫወቱ ድምፃውያ የሙዚቃ ስራቸውንም ያቀርባሉ።በዕለቱም በ "ዮቶር ድግስ" ከኮንሰርቱ በተጨማሪም በቅርቡ ለአንባቢያን የደረሰው "ዮቶር ቁጥር 2" መጽሐፍ ይመረቃል ስለመባሉ ኤቨንት አዲስ ድረገፅ ሰምቷል።

📍ሥነጽሑፍ ፣ ኪነጥበብ ፤ የሀሳብ ውይይት

- በዛጎል መጻሕፍት ባንክ የሚዘጋጀው "ነገረ መጻሕፍት" የመጽሐፍ ውይይት የፊታችን ቅዳሜ በኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ ይካሄዳል። በዚህ ሳምንት መምህርና ደራሲ ኃይለመለኮት መዋዕል የሕይወት ልምዳቸውን የሚያጋሩበትና የሚወዷቸውን በኢትዮጵያውያን የተጻፉ ሰባት መጻህፍትን የሚጠቁበት መርሐግብር ይካሄዳል ።የዕለቱ አወያይ ደራሲ እንዳለጌታ ከበደ ነው። ይህ መርሐግብር ቅዳሜ ሰኔ 2016 ዓ.ም ከቀኑ 8:00 እስከ 10:30 ይካሄዳል።

- በአንጋፋው የኢትዮጵያ ቤተመዛግብትና ቤተመጻሕፍት አገልግሎት  (ወመዘክር አዳራሽ) "የወር ወንበር" የተሰኘ ወርሃዊ ዝግጅት መካሄድ ሊጀምር እንደሆነ ኤቨንት አዲስ ድረገፅ ከአገልግሎቱ ያገኘው መረጃ ያመለክታል።በመጀመሪያው ወር  “የወር ወንበር” ፕሮግራም የፊታችን ቅዳሜ ሰኔ 15 2016 ቀን ከቀኑ 10:30 ጀምሮ “ከርሠ ግጥም” በሚል አርዕስት የሦስት ግጥሞች ሀሳብ ላይ ውይይት ይካሄዳል ተብሏል።

- "አውደ ፋጎስ" 39ኛው ዙር የሀሳብ ውይይት የፊታችን እሁድ ሰኔ 16 2016 ዓ.ም በወመዘክር አዳራሽ ይካሄዳል።በዚህኛው ዙር " የ "የማ" ወንዶች በአሊጎሪካዊ እና ነገረ ፍካሬ እይታ "በሚል ርዕሰ ጉዳይ በደራሲ ቢኒያም አቡራ መነሻ ሀሳብ አቅራቢነት በሙዚቃ ባለሞያዋ ትሬዛ ዮሴፍ አወያይነት ከቀኑ 8:00 ጀምሮ ይካሄዳል።

- "ሆሄ ተስፋ የኪነጥበብ መድረክ" የፊታችን እሁድ ሰኔ 16 2016 ዓ.ም ከቀኑ 8:00 ጀምሮ መገናኛ ዋኣች ሕንፃ ላይ በሚገኘው "ጣዕም ባህላዊ ምግብ ቤት" ውስጥ ይካሄዳል ተብሏል።በዝግጅቱ ላይም ወጣት የሥነጽሑፍ ባለሞያዎችም የሥነጽሑፍ ስራዎቻቸውን ያቀርባሉ ተብሏል።

📍ሥነጥበብና (ሥዕል )

በዕይታ ላይ ያሉ የሥዕል አውደርዕዮች

- የሠዓሊ ኃይለገብርኤል ንጉሴ የሥዕል ስራዎች የሚቀረበብት "The light Path" የሥዕል አውደርዕይ ከቅዳሜ ሰኔ 8 2016 ዓ.ም ጀምሮ መስቀል አደባባይ አካባቢ በሚገኘው የአዲስ አበባ ሙዚየም ውስጥ ላይ በእይታ ይገኛል።ይህም የሥዕል አውደርዕይ እስከ ሰኔ 23 2016 ዓ.ም በእይታ ላይ ይቆያል ተብሏል።

- የእውቁ ሠዓሊ ብሩክ የሺጥላ "የይቅርታ ጉዞ" የተሰኘ የሥዕል አውደርዕይ ሰኔ 6 2016 ዓ.ም ቦሌ አትላስ መብራት አካባቢ በሚገኘው የኢትዮጵያ ሜትሮፖሊታን የሥዕል ማሳያ ውስጥ ለእይታ በቅቷል።ይህ የሥዕል አውደርዕይ እስከ ሰኔ 23 2016 ዓ.ም በእይታ ላይ ይቆያል።

- የሠዓሊ ዮናታን ወንደሰን ሥዕል ስራዎች የሚቀርቡበት "ከአጥሮች ባሻገር" የሥዕል አውደርዕይ ከአርብ ሰኔ 7 2016 ዓ.ም ጀምሮ ካዛንቺስ በሚገኘው ፈንድቃ የባህል ማዕከል ውስጥ ለእይታ በቅቷል። ይህ የሥዕል አወድርዕይ እስከ ሰኔ 21 2016 ዓ.ም ይቆያል ተብሏል።

-የሠዓሊ ዳዊት ገረሡ "አሁን" የተሰኘ የሥዕል አውድርዕይ ከግንቦት 23 2016 ዓ.ም ጀምሮ ስድስት ኪሎ በሚገኙ ገብረክርስቶስ ደስታ ዘመናዊ ቤተመዘክር ውስጥ በእይታ ይገኛል።እስከ ሰኔ 14 2016 ዓ.ም በእይታ ላይ ይቆያል።

አዘጋጅ: ናቲ ማናዬ

ቀን: ሰኔ 13 2016 ዓ.ም

አዲስ አበባ ኢትዮጵያ

በድረገጻችን በተሻለ አቀራረብ ያንብቡ:

https://eventaddis.com

ቴሌግራም: @EventAddis1
Event Addis Media
ተወዳጁ ተዋናይ አማኑኤል ሐብታሙን ጨምሮ ብዛታቸው 20 እንደሆኑ በፖሊስ ለፍርድ ቤት የቀረበ ማመልከቻ ላይ የተጠቀሱት ተጠርጣሪዎች ዛሬ በድጋሚ ፍርድ ቤት ቀርበዋል። አማኑኤል በታሰረ ከ42 ቀናት በኋላ ግንቦት 28 ቀን 2016 ዓ/ም ከያኒ ዳግማዊ ፈይሳን ጨምሮ ሌሎች 20 ግለሰቦችን ፖሊስ ፍርድ ቤት አቅርቦት የነበረ ሲሆን ፍርድ ቤቱ ፖሊስ የጠየቀውን ተጨማሪ ጊዜ ቀጠሮ በመፍቀድ ለሰኔ 11 ቀን ተለዋጭ…
በእነ አርቲስት አርቲስት አማኑኤል ሀብታሙ መዝገብ ከተከሰሱት ከ5፣7፣8ተኛ  ተከሳሾች ውጪ ያሉት በ50 ሺህ ብር ዋስ እንዲወጡ ፍርድ ቤቱ ወስኗል።

በዚህ መዝገብ ከተከሰሱት ውስጥ አርቲስት አማኑኤል ሀብታሙ ፣ ዳግማዊ አመለወርቅ ፈይሳ ፣ ፍላጎት አብርሃም (የልጅ ማኛ)ን ጨምሮ 17 ሰዎች በ50 ሺህ ዋስ እንዲለቀቁ ፍርድ ቤት እንደወሰነ ተሰምቷል።

መረጃው የSirak Temesgen ነው።

ለተጨማሪው: https://news.1rj.ru/str/EventAddis1