Event Addis Media – Telegram
Event Addis Media
9.62K subscribers
6.12K photos
14 videos
4 files
4.75K links
Connect with Addis artistic community!

Website: https://eventaddis.com

Contact: @Tmanaye
Download Telegram
📌“ናዋዥ” የተሰኘ አዲስ መፅሐፍ ለንባብ በቃ

በደራሲ እያዩ ዳኛው የተሰናዳውና “ናዋዥ” የተሰኘው አዲስ የግለ ታሪክ መፅሐፍ ሰሞኑን ለንባብ በቃ፡፡ መፅሐፉ በዋናነት በደራሲው የግል ህይወት ላይ የሚያጠነጥን ቢሆንም፤ ኢትዮጵያዊያን በሱዳንና በሊቢያ በኩል ወደ አውሮፓ ለመግባት የሚያደርጉትን አስከፊና አስቸጋሪ የስደት ህይወት የሚያሳይ ነው ተብሏል፡፡

ነዋሪነቱን በጀርመን ያደረገው ደራሲ እያዩ ዳኛው፤ መፅሐፉ ከደቡብ ጎንደር ክምር ድንጋይ እስከ ጣሊያን የወደብ ከተማ ትራፓኒ የዘለቀውን የስደትና የውጣ ውረድ ጉዞ የሚዳስስ መሆኑን ለአዲስ አድማስ ተናግሯል፡፡

“ናዋዥ”፤ደራሲው ልጅነቱን የአፍላ ወጣትነቱን፣ የኢትዮጵያውያንን የስደት ኑሮ፣ በሱዳንና በሰሃራ በረሃ ለማቋረጥ ስደተኞች የሚከፍሉትን መስዋዕትነት እንዲሁም በመንግሥት አልባዋ ሊቢያ የነበረውን ኑሮና በሜድትራንያን ባህር የሚያጋጥምን ፈተና ያስቃኛል፡፡

በ470 ገፅ የተቀነበበው “ናዋዥ”፤ የግለ ታሪክ መፅሐፍ በ500 ብር ለገበያ ቀርቧል፡፡

📍መረጃው የአዲስ አድማስ ጋዜጣ ነው

ለተጨማሪው :https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
📌 " አዎ ነቢይ በሀገሩ ይከበራል ! "

በቅርቡ በአጸደ ስጋ የተለየውን ሁለገቡ እና አንጋፋውን ከያኒ ነቢይ መኮንንን ለማክበር ዛሬ ሐምሌ 22 2016 ዓ.ም ልዩ ዝግጅት ተሰናድቷል።

የነቢይ ወዳጆች ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር ጋር በመተባበር ያዘጋጁት ይህ መርሐግብር ዛሬ ሰኞ ሐምሌ 22 ቀን  2016 ዓ.ም ከ11:00 ሰዓት ጀምሮ በኢትዮጵያ ብሔራዊ አዳራሽ ይካሄዳል።

በዚህ "አዎን ነቢይ በሀገሩ ይከበራል!" በተሰኘ የክብር ማስታወሻ ዝግጅት ላይ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር ሁላችሁም ተጋብዛችኋል።

ለተጨማሪው :https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
📌"ንስሩ ልጅ" የተሰኘ ፊልም ለእይታ ቀረበ

በሱራፌል መልቲሚዲያ አማካኝነት የተሰናዳው "ንስሩ ልጅ" የተሰኘ አንድ ሰዓት ከሃያ ደቂቃ ርዝማኔ ያለው እና የቤተሰብ ፊልም በዓለም ሲኒማ ለእይታ መቅረብ ጀመረ።

በኢትዮጵያ ፊልም ኢንዱስተሪ ውስጥ የተለያዩ ፊልሞችን በድርሰት ፣ በዳይሬክቲንግ እና በፕሮዲውሲንግ ስራዎች መስክ ከፍተኛ አስተዋጾ እያደረገ በሚገኘው በደራሲና ዳይሬክተር ሱራፌል ኪዳኔ አማካኝነት የተዘጋጀው "ንስሩ ልጅ" ፊልም በትናንትናው ዕለት በዓለም ሲኒማ በይፋ ተመርቋል።

የፊልሙ ደራሲና ዳይሬክተር ሱራፌል ኪዳኔ በፊልም ምርቃቱ መርሐግብር ላይ እንገለጸው ስድስት ዓመት በላይ የወሰደው "ንስሩ ልጅ" ፊልም በብዙ ጥናት ላይ በመመርኮዝ በታዳጊ ልጆች እና ወላጆቻቸው ላይ ትኩረት በማደረግ ልጅን ከወላጅ ጋር በማቀራረብ መልካም ትውልድን ለመፈጠር እየተሰራ ባለው ስራ ላይ ተጨማሪ ግብዓት እንዲሆን በማሰብ መዘጋጀቱን ገልጿል።

"ንስሩ ልጅ" ፊልም ለተከታዮቹ አራት ሳምንታት ዘወትር እሁድ ከረፋዱ 5:00 ሰዓት ጀምሮ በዓለም ሲኒማ እና በቀጣይ በተለያዩ ትምህርት ቤቶች እና በተለያዩ ሲኒማ ቤቶች ለእይታ የሚቀርብ ሲሆን ወላጆች ከልጆቻቸው ጋር እንዲመለከቱት ደራሲ መልዕክት አስተላልፏል።

📍መረጃው የጌች ሀበሻ ነው።

ለተጨማሪው :https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
📌አርቲስት ትንሣኤ ብርሃን ብራንድ አምባሳደር ሆነ

በኢቢኤስ ቴሌቪዥን በሚተላለፈው "እሁድን በኢቢኤስ " ፕሮግራም ላይ አቅራቢ የሆነው እና በድራማ ፣ ፊልሞች ተዋናይነቱ የምናውቀው አርቲስት ትንሣኤ ብርሃን የባሊ ምግብ ማቀነባበሪያ ብራንድ አምባሳደር ሆኖ ተሹሟል።

ባሊ ፉድ ፕሮሰሲንግ ኃላፊነቱ የተወሰነ ድርጅት አርቲስት ትንሣኤ ብርሃንን በብራንድ አምባሳደርነት የሾመው ለሚያመርታቸው በማር ወለላ የተቀመመ "QQ yammy snack" እና በኦቾሎኒ ጣዕም ለሚያመርተው "QQ coated peanut" ምርቶቹ ነው።

ይህ የብራንድ አምባሳደር የሥራ ስምምነት ፊርማ ለአንድ ዓመት ይቆያል ተብሏል።

ባሊ ፉድ ፕሮሰሲንግ ከተመሰረተ 4 ዓመታትን ያስቆጠረ ሲሆን በማር ወለላ የተቀመመ QQ yammy snack እና በኦቾሎኒ ጣዕም የሚያመርተው QQ coated peanut በማምረት ላይ የሚገኝ ድርጅት ነው።

ተቋሙ እነዚህን ጣፋጭ ምግቦች በተመጣጣኝ ዋጋ እና በከፍተኛ ጥራት ለገበያ እንደሚያቀርብ በስምምነቱ ቀን ላይ ተገልጿል።

ለተጨማሪው :https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
📌ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ከሁለት ክሶች ነፃ ተባለ

ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ በሐምሌ 2014 ዓ.ም “ጥብቅ የመከላከያ ሠራዊትን ምስጢር ማባከን”፣ “መከላከያ ሠራዊቱን መከፋፈል” እና “የመከላከያ ሠራዊቱን ስም ማጥፋት” የሚሉ ሦስት ክሶች ተመስርተውበት በቂሊንጦ ማረሚያ ቤት ሆኖ ለስድስት ወራት በእስር ላይ ነበር።

ሆኖም ግን በፌደራል ከፍተኛው ፍርድ ቤት የሕገ-መንግሥት እና የሽብር ወንጀል ችሎት ሰብሳቢ የሆኑት የተከበሩ ዳኛ ዘላለም ተስፋዬ እና የተከበሩ የቀኝ ዳኛ ወ/ሮ ሐረገውይን ተክሉ ተሰይመው የመጀመሪያ እና ሁለተኛውን ክስ ውድቅ አድርገው ሦስተኛው ክስ ደግሞ አንቀጽ ተቀይሮ እንዲከላከል በመወሰናቸው ከወህኒ ቤት በዋስ መፈታቱ ይታወሳል፡፡

ይሁንና፣ የፌደራል መንግሥት ዓቃቢ ሕግ ጋዜጠኛው ነፃ የተባለባቸው ከ15 ዓመት እስከ እድሜ ልክ እና ከ10 እስከ 15 ዓመት ከሚያስፈርዱበት ሁለት ክሶች “ነፃ መባል አልነበረበትም” በሚል ለጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት የይግባኝ ቅሬታውን አቅርቧል፡፡ ጋዜጠኛውም በጠበቃዎቹ በኩል ሲከራከር ቢቆይም ጉዳዩን እየመረመረው በነበረው በአቶ ሽምሱ ሲርጋጋ ሰብሳቢነት የሚመራው ችሎት ላይ “የዳኛ ይቀየርልኝ” ጥያቄ አቅርቦ ውድቅ ተደርጎበት ነበር፡፡

በወርሃ ሚያዚያ 2016 ዓ.ም ሦስቱም ዳኞች ተቀይረው በምትካቸው ሰብሳቢ የተከበሩ ዳኛ ምጽላል ኃይሌ እንዲሁም የተከበሩ ዳኛ ከበቡሽ ወርቁና የተከበሩ ዳኛ ኡመር መሐመድ የግራ እና ቀኝ ዳኛ ሆነው ተመድበዋል፡፡

ዛሬ ሐምሌ 23/2016 ዓ.ም በተከበሩ ዳኛ ምጽላል ኃይሌ ሰብሳቢነት የሚመራው ችሎት “የከፍተኛው ፍርድ ቤት ውሳኔ ትክክልና የሚነቀፍ ሆኖ ስላላገኘነው ጋዜጠኛው በነፃ እንዲሰናበት የተሰጠው ውሳኔ ጽንቷል” በሚል ፍርድ ሰጥተዋል፡፡

©️ይድነቃቸው ከበደ

@EventAddis1
📌"ሀገር በአንድ ሺህ ቀን" መጽሐፍ ምርቃት

"ሀገር በአንድ ሺህ ቀን" መጽሐፍ ነገ ይመረቃል።በወ/ሮ ፍሬዓለም ሽባባው “ሀገር በአንድ ሺህ ቀን” በሚል  ርዕስ የተፃፈ አዲስ መጽሐፍ ነገ ሐሙስ ሐምሌ 25 ቀን 2016 ዓ.ም ከቀኑ 9:ዐዐ ጀምሮ በኃይሌ ግራንድ ሆቴል ተጋባዥ እንግዶች በሚገኙበት ይመረቃል።በዕለቱም ገጣሚ ታገል ሰይፉ ፣ ጸሐፊ ተውኔት ዳግማዊ አመለወርቅ ፊይሳ ፣ ዶ/ር ይሁኔ አየለ ፣ ኪያኒ ተስፋዬ ማሞ ፣ ኢ/ሮ ቢጃይ ናይከር እና ሌሎችም ይገኛሉ ተብሏል።

መጽሐፉ የገፅ ብዛቱ 89 ሲሆን "የእኛ ቤት ኢትዮጵያ፥ከባንዲራው በታች፥ሰቆጣ ዴክለሬሽን" በሚሉ ሦስት ክፍሎች ተቀንብቦ ቀርቧል።

ለተጨማሪው :https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
📌"ለእርቃን ሩብ ጉዳይ" መጽሐፍ ምርቃት 

የደራሲ ሕይወት እምሻው "ለእርቃን ሩብ ጉዳይ" የተሰኘ አዲስ መጽሐፍ ነገ ሐሙስ ሐምሌ 25 2016 ዓ.ም ከምሽቱ 11:00 ጀምሮ አራት ኪሎ በሚገኘው ዋልያ መጻሕፍት መደብር ውስጥ ይመረቃል።

ሐያ ስምንት ታሪኮችን የያዘው አዲሱ መጽሐፏ በ208 ገፆች ተቀንብቦ በ300 ብር የጀርባ ዋጋ ለአንባቢያን ይቀርባል ተብሏል። ደራሲዋ ከዚህ ቀደም ባሪቾ ፣ ፍቅፍቂ ፣ ማታ ማታ የተሰኙ መጻሕፍትን ለንባብ አብቅታለች።

ለተጨማሪው :https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
📌የኢቢኤስ ሲኒማ እና አርቲስት ፍቃዱ ከበደ ጉዳይ

የኢቢኤስ ሲኒማ ቻናል ጾታ አሳስቶ የጠየቀው ጥያቄ ዛሬ በሀገራችን ማህበራዊ ትስስር ገፆች መነጋገሪያ ሆኗል። 

ኢቢኤስ ሲኒማ ለተመልካቾቹ በየዕለቱ በሚያቀርበው ጥያቄው የአርቲስት ፍቃዱ ከበደ ፎቶን በመጠቀም "የዚህችን ተዋናይት ሙሉ ስም እና ከሰራቸው ፊልሞች  መካከል አንድ ጥቀስ ?" በማለት የጠየቀው ጥያቄ መነጋገሪያ ሆኗል።በዚህም ከአርቲስቱ ጋር ውዝግብ ውስጥ ገብተዋል።

አርቲስቱም በማህበራዊ ትስስር ገፁ " አንዳንድ ቴሌቪዥን ጣቢያዎች ነገር ፈልገዋችሁ ታዋቂ ለመሆን ሲሞክሩ አይገርምም?። በርግጥ ጉዳዩን ጠበቃዬ ይዞታል እኔ የ3 ልጆች አባት ፆታዬ ወንድ ኢትዮጵያዊ ነኝ። ከቴሌቪዥን ጣቢያው ጋር በቅርብ በጠረጴዛ ዙሪያ ውይይት የምናደርግ ይሆናል" ስለማለቱ ኤቨንት አዲስ ድረገፅ ተመልክቷል።

ለተጨማሪው :https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
📌ሜንታል ሄልዝ አዲስ የሥነልቦና ውይይት

ወርሃዊው የሜንታል ሄልዝ አዲስ መርሃግብር ቅዳሜ ሐምሌ 27 ቀን 2016 ዓም አትላስ አካባቢ በሚገኘው በአዶር አዲስ ሆቴል ከቀኑ 10፡00 ጀምሮ ይካሄዳል::

የዚህ ወር ርዕስም፡- “የጭንቀት ስነልቦናዊ ትንታኔ” የሚል ሲሆን የዚህ ወር እንግዳ ዶ/ር አወቀ ምህረቱ ናቸው፡፡

ለመታደም ይህን መስፈንጠሪያ ይጫኑና ይመዝገቡ፡፡
https://forms.gle/bGmE6wXeZroTGrV86

ለተጨማሪው :https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
📌አውደ ፋጎስ 41ኛ ዙር የውይይት መድረክ

41ኛው ዙር አውደ ፋጎስ የውይይት መድረክ እሁድ ይካሄዳል። በዚህኛው ዙር የስትራቴጂክ ጉዳዮች አማካሪ ዮናስ ግርማይ "ዓለምአቀፍ ግኑኝነትን መሳሪያ ማድረግ" በሚል ርዕስ መነሻ ሀሳብ ያቀርባል።ይህም ውይይት እሁድ ሐምሌ 28 2016 ዓ.ም ከቀኑ 8:00 ጀምሮ በብሔራዊ ቤተመዛግብት እና ቤተመጻሕፍት አግልግሎት (ወመዘክር) አዳራሽ ይካሄዳል።

ለተጨማሪው :https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
📌 ዶቃ ፊልም በቴሌቲቪ የፊልም መተግበሪያ መታየት ሊጀምር ነው።

ለተወሰነ ጊዜ በዓለም ሲኒማ በእይታ ላይ የቆየው የቅድስት ይልማ "ዶቃ" ፊልም በቅርቡ ይፋ በተደረገው ቴሌቲቪ የፊልም መተግበሪያ ላይ መታየት እንደሚጀምር ኤቨንት አዲስ ድረገፅ ሰምቷል።

ኤቨንት አዲስ ድረገፅ እንደደረሰው መረጃ ከሆነ "ዶቃ" ፊልም ከሃገር ውጪ ለሚገኙ ተመልካቾች ደግሞ "አማዞን ፕራይም" ላይ መታየት ጀምሯል ተብሏል።

"ዶቃ" ፊልም ድርሰቱን ቤዛ ሀይሉ እና ቅድስት ይልማ የሰሩት ሲሆን  ቅድስት ይልማ ፊልሙን ዳይሬክት አድርጋለች።

ፊልሙ ለረጅም ጊዜያት ከፊልም ኢንዱስትሪው ጠፍታ የነበረችውን አርቲስት ማህደር አሰፍን ወደ ፊልም መድረክ የመሰለ ፊልም ነው።

በተጨማሪም ፊልሙ ላይ በተዋናይነት  ድርብወርቅ ሰይፉ (እማ ቸርነት) ፣ግሩም ዘነበ ፣ወንጌል ጥላሁን እና ሌሎችም ተሳትፈዋል። የፊልሙ ኤክስኪዩቲቭ ፕሮዲዩሰር ማህደር አሰፋ ናት።

"ዶቅ" ፊልም ባሳለፍነው ዓመት ከሰኔ 22 2015 ዓ.ም ጀምሮ ነበር ቦሌ በሚገኘው ዓለም ሲኒማ ለተወሰኑ ቀናት ለዕይታ የቀረበው።

ለተጨማሪው :https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
📌የድምጻዊ አብዱ ኪያር "ፓፓፓ" የሙዚቃ አልበም በዩቲዩብ በተለቀቀ አንድ ወር ውስጥ ብቻ ከ18 ሚሊዮን አምስት መቶ ሺህ በላይ ተመልካቾችን እንዳገኘ ድምጻዊው በማህበራዊ ትስስር ገፁ ከአሰራጨው መረጃ ኤቨንት አዲስ ድረገፅ ተመልክቷል።

ድምጻዊው በማህበራዊ ትስስር ገፁ ለአድናቂዎቹና አድማጮቹ የምስጋና መልዕክቱን አስተላልፏል።

በአልበሙ ላይ በቅንብር ስማገኘሁ ሳሙኤል፣ ኪሩቤል ተስፋዬ፣ ካሙዙ ካሳ እና ዳዊት ቦስኮ ተሳትፈዋል። ሚክሲንጉን የሰሩት ስማገኘሁ ሳሙኤል እና ኪሩቤል ተስፋዬ ሲሆኑ  ማስተሪንግ ደግሞ በአበጋዝ ክብረወርቅ ተሰርቷል።

"ፓፓፓ" የሙዚቃ አልበም ሰኔ 21 2016 ዓ.ም ነበር ለአድማጮች የደረሰው።

ለተጨማሪው :https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
የድምጻዊ ልዑል ኃይሉ "እስኪ አሙቁላት" የተሰኘ የሙዚቃ ቪዲዮ ዛሬ ይለቀቃል ተብሏል

በሁለገብ ሙዚቀኛ አልያስ መልካ ፕሮዲዩስ ከተደረጉ የሙዚቃ አልበሞች መካከል አንደኛው የሆነ የድምጻዊ ልዑል ኃይሉ "እሳቱ ሠዓት" አልበም ውስጥ ከተካተቱ የሙዚቃ ስራዎች "እስኪ አሙቁላት" ለተሰኘው ሙዚቃ የተሰራው የሙዚቃ ቪዲዮ ዛሬ ለተመልካቾች እንደሚደርስ ኤቨንት አዲስ ድረገፅ ሰምቷል።

የዚህን የሙዚቃ ግጥም ፣ዜማ ፣ ቅንብርና ማስተሪጉን ኤልያስ መልካ ሠርቷል።የሙዚቃው ቪዲዮው ዛሬ ሐምሌ 26 2016 ዓ.ም ናሆም ሪከርድስ በኩል ይለቀቃል።

ለተጨማሪው: https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
📌በእረፍት ቀንዎ ፊልም ይመልከቱ !

እነዚህ አራት የፊልም ማሳያዎች(ሲኒማ ቤቶች) ዛሬን ጨምሮ በሳምንቱ መጨረሻ ቀናት እነዚህን ፊልሞች ለተመልካቾች ያቀርባሉ: ምስሎቹን ይመልከቱ።

የሲኒማ ቤቶቹ አድራሻ:

✔️ሲኤምሲ ሚካኤል አካባቢ : ጋስት ሲኒማ

✔️ለም ሆቴል አካባቢ: ቫምዳስ ሲኒማ

✔️ጉርድ ሾላ አካባቢ : ሴንቸሪ ሲኒማ

✔️ቦሌ አካባቢ : ዓለም ሲኒማ

መልካም የእረፍት ቀናት ይሁንላችሁ !

https://news.1rj.ru/str/EventAddis1

https://news.1rj.ru/str/EventAddis1

ለተጨማሪው :https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
በእረፍት ቀንዎ ቴአትር ይመለከቱ !

አንጋፋው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር  እና የቦሌው ዓለም ሲኒማ አርብ፣ ቅዳሜ እና እሁድ እነዚህን ተውኔቶች ለታዳሚያን ያቀርባሉ።

📍 የፍቅር ካቴና

ድርሰትና ዝግጅት: አለልኝ መኳንት ፅጌ
ቀን: አርብ
ሰዓት: 12:00
ቦታ: ዓለም ሲኒማ

📍 "እሳት ወይ አበባ"

ድርሰት: ሎሬት ፀጋዬ ገብረመድህን እንደጻፈው
ዳንስና ዳንስ ቅንብር: ሽፈራው ታሪኩ ቢረጋ
ቀን: አርብ
ሰዓት:11:30
ቦታ: ብሔራዊ ቴአትር

📍 ባሎች እና ሚስቶች

ድርሰት: ውዱ አለን
አዘጋጅ: ሳሙኤል ተስፋዬ
ቀን: ቅዳሜ
ሰዓት: 8:00
ቦታ: ብሔራዊ ቴአትር

📍 ባቡሩ

ድርሰት: አርኖልድ ሪድሊ
አዘጋጅ:ራሔል ተሾመ መሐመድ
ቀን: ቅዳሜ
ሰዓት:11:30
ቦታ: ብሔራዊ ቴአትር

📍 ሸምጋይ

ድርሰት:ታደለ አያሌው
አዘጋጅ: ሳሙኤል ተስፋዬ
ቀን: እሁድ
ሰዓት: 8:00
ቦታ: ብሔራዊ ቴአትር

📍 እምዩ ብረቷ

ድርሰት: ቤልቶልት ብሬሽት
አዘጋጅ: ማንያዘዋል እንዳሻው
ቀን: እሁድ
ሰዓት:11:30
ቦታ: ብሔራዊ ቴአትር

የእናንተው ኤቨንት አዲስ ድረገፅ መልካም የእረፍት ቀን ይሁንላችሁ ይላል !

ለተጨማሪው: https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
📌የድምጻዊ ሚካኤል በላይነህ "አንድ ቃል" የተሰኘ ርዕስ የተሰጠው የሙዚቃ አልበም በቅርቡ እንደሚለቀቅ ድምጻዊው በማህበራዊ ገፁ ካሰራጨው መረጃ ኤቨንት አዲስ ድረገፅ ተመልክቷል።

ድምጻዊ ሚካኤል በላይ በይፋዊ የማህበራዊ ሚዲያ ትሰስር ገፆቹ ከደቂቃዎች በፊት "ውድ ወዳጆቼ በቅርቡ በአዲስ አልበም እንደምንገናኝ ስገልፅላችሁ በደስታ ነው" ብሏል።

ለተጨማሪው: https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
📌አፍታ ሜይራ ግሩፕ ከብራይት ጋር 25/75 የብድር አቅርቦት በጋራ ለመስራት ተፈራረሙ::

በአፍታ ሜይራ ግሩፕ ስር የሚገኘው አፍታ ሜይራ ሪል ስቴት በዘመናዊ ቴክኖሎጂ በማስገንባት ላይ የሚገኘውን ዘመናዊ ቤቶችን ለቤት ፈላጊው እጅግ ተመጣጣኝ በሆነ ዋጋ እያቀረበ ይገኛል።

በመሆኑም ብራይት የፋይናንስ ተቋም ለቤት ፈላጊዎች ከብድር ጋር በተያያዘ  የፋይናንስ ድጋፍ ለማድረግ በቀጣይም አብረው የሚሰሩባቸውን ዝርዝር ጉዳዮች ላይ የጋራ ውል ስምምነት ፈፅመዋል በቅርቡም ሚድያዎች በተገኙበት የጋራ መግለጫ እንደሚሰጡ አሳውቀዋል።

አፍታ ሜይራ ሪል ስቴት የቤት ችግርን ዘመኑን በሚመጥን ተፈጥሯዊ ውበት የተላበሱ ቤቶችን በዓለማቀፉ SAGA እና FOG የዲዛይን ንድፍ ሐሳብ በመገንባት እና በመሸጥም ላይ ይገኛል።

በሐምሌ 26 2016 ዓ.ም በተለይ ለሀገራችን የቤት ፈላጊውን እና የፋይናንስ ፍላጎትን ለመፍታት ታሳቢ ያደረገ ስምምነት ነው።

ለተጨማሪው :https://news.1rj.ru/str/EventAddis1