📌ሶስተኛው የሺህ ጋብቻ ካርኒቫል ኤክስፖ
ያሜንት ኤቨንትስ ከባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር ጋር በመተባበር የሚዘጋጀው የየሺህ ጋብቻ 2017 መርሐግብር ለሶስተኛ ጊዜ ይካሄዳል ተብሏል።
ይህንም አስመልክቶ ባህልና ስፖርት ሚኒስቴር እና ያሜንት ኤቨንትስ በጋራ ለመስራት የሚያስችል ስምምነት አድርጓል።
በ2017 የሺህ ጋብቻ ካርኒቫል ኤክስፖ ላይ ከተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት ጋብቻቸውን የሚፈፅሙ ጥንዶች የሚሳተፍበት መሆኑ ለየት ያደርገዋል ተብሏል።
ለተጨማሪው :https://news.1rj.ru/str/EventAddis1

📌ተዋናይት ፍናን ህድሩ እና ኢንፊኒክስ ኢትዮጵያ
ኢንፊኒክስ ኢትዮጵያ ተዋናይት ፍናን ህድሩን የብራንድ አምባሳደር በማድረግ አብሮ ለመስራት የሚያስችላቸውን ስምምነት ዛሬ ነሐሴ 23 2016 ዓ.ም በሐያት ሪንጀሲ ተፈራርመዋል።
ስምምነቱ የአንድ ዓመት ቆይታ አለው የተባለ ሲሆን ኢንፊንክስ ኢትዮጵያ ተዋናይት ፍናን ከብራንዱ ጋር በቅርበት በመስራት በተለይም ወጣቱን ከብራንዱ ጋር በማስተዋወቅ የራሷን ድርሻ ትወጣለች ብሎ እንደሚጠበቅ ገልጿል።
ተዋናይት ፍናን በፊልሙ ኢንደስትሪ በተለይም በወጣቱ ዘንድ ያገኘችውን ተቀባይነት እና ያላት የፈጠራ ችሎታ ከኢንፊኒከስ ብራንድ ጋር አብሮ ለመስራት ምቹ እንደሚያደርገው የተገለፀ ሲሆን ኢንፊኒከስ ከሚታወቅበት የስልክ ገበያ በተጨማሪ ወደ ቲቪ፣ ላፕቶፕ፣ ስማርት ዋች፣ ኤር ፖድ እና መሰል ምርቶችን ወደ ገበያው ለማቅረብ ያለውን ዓላማ በመደገፍ ረገድ ጉልህ ተሳትፎ ይኖራታል ተብሏል።
ኢንፊኒከስ ዓለም አቀፍ የኤሌከትሮኒክስ አምራች ኩባንያ ሲሆን በተለይም በሚያመርታቸው የስማርት ስልኮች አለም አቀፍ ተቀባይነትን ያገኘ ብራንድ ነው::
በምርቶቹ አዳዲስ ቴከኖሎጂዎችን በማስተዋወቅ የሚተወቀው ኢንፊኒከስ አሁን ደግሞ በቲቪ፣ ላፕቶፕ፣ ስማርት ዋች፣ ኤር ፖድ እና የመሳሰሉት ምርቶቹ ወደ ገበያው እየመጣ ይገኛል፡፡

📌የድምጻዊት ቬሮኒካ አዳነ አልበም ተለቀቀ
የድምጻዊት ቬሮኒካ አዳነ "መጠሪያዬ" የተሰኘ አልበም ዛሬ ሐሙስ ነሐሴ 23 2016 ዓ.ም በራሷ በቬሮኒካ አዳነ ዩቲዩብ ቻናል እና ዓለም አቀፍ የሙዚቃ መተግበሪያዎች ላይ እንደተለቀቀ ኤቨንት አዲስ ድረገፅ ተመልክቷል።
የድምጻዊት ቬሮኒካ አዳነ"መጠሪያዬ" አልበም 12 የሙዚቃ ስራዎችን የያዘ ሲሆን አልበሙ ላይ በግጥም እና ዜማ አቤል ሙሉጌታ፣አቡዲ እና ሱራፌል የሺጥላ ተሳትፈዋል በተጨማሪም በሙዚቃ ቅንብር ታምሩ አማረ ፤አዲስ ፍቃዱ፣ አብርሃም ኪዳኔ ፣ሮቤል እንዳለ በሚክሲንግ እና ማስተሪንግ ሠለሞን ኃ/ማሪያም ተሳትፈውበታል።
አልበሙ ላይ ሁለት የሙዚቃ ቪዲዮዎች ያሉት ሲሆን ክሊፑ በአሜሪካ አትላንታ መሠራቱን ተነግሯል።
ይህ አልበም አጠቃላይ ከስድስት ሚሊየን ብር በላይ ወጪ የወጣበት ሲሆን የአልበሙ ሙሉ በሙሉ ወጪ በድምጻዊት ቬሮኒካ አዳነ ፕሮዲዩስ ተደርጓል።
ይህ አልበም ዞጃክ ወርልድ ዋይድ የተሰኘ ዓለም አቀፍ የሙዚቃ ካምፓኒ በ160,000 ዶላር በመላው ዓለም ለማከፋፈል ከአርቲስቷ ጋር ተስማምተዋል፡፡

📌 ድምጻዊ ዳዊት ፅጌ እና ሐበሻ ቢራ
ድምፃዊ ዳዊት ፅጌ "የእልል ያልኩ ሐበሻ" የብራንድ አምባሳደር ሆኖ ተመረጠ።
ወጣቱ ድምጻዊ ዳዊት ፅጌ የሀበሻን ባህላዊ እሴቶችን እንዲሁም ሐበሻ ቢራን እንዲያስተዋውቅ በሐበሻ ቢራ ፋብሪካ እንደተመረጠ በዛሬው ዕለት ይፋ ተደርጓል።
በ"የኔ ዜማ" አልበም እና በተለያዩ ነጠላ ዜማዎች ተወዳጅነትን ያተረፈው ድምፃዊ ዳዊት ፅጌ ብራንድ አምባሳደር ሆኖ በመመረጡ የሀበሻ መገለጫ የሆኑ እሴቶች በዓለም አደባባይ ጎልተው እንዲወጡ ይሰራል ተብሏል።
"እልል ያልኩ ሀበሻ "በሐበሻ ቢራ አዘጋጅነት ዛሬ ነሐሴ 23 2016 ዓ.ም በቃና ዌርሀውስ ለየት ያለ ፕሮግራም የተዘጋጅቶ የነበረ ሲሆን የኢትዮጵያዊያን ባህል፤ ዕሴት ፣ ማንነት እና ወግ ላይ ያተኮሩ በተለያዩ ክዋኔዎች ባህላዊውን ከዘመነኛው ጋር ያሰናሰኑ ዝግጅቶች ተካሄደዋል።
በዚህም ዝግጅት በምግብ አዘገጃጀት፤በፋሽን ትርዒት፤ በሙዚቃ እና በሌሎች የጥበብ ስራዎች ባህላዊው ከዘመናዊ ጋር በማሠናሠል ስራ የበረቱ ባለሞያዎች ስራዎቻቸውን አቅርበዋል።
የዛሬው የዝግጅት ዓላማ የሀበሻ መገለጫ የሆኑ አለባበሰ፣ምግብ ዝግጅት ፣ሙዚቃ እና የመሳሰሉትን በተለያዩ ሀገረኛ መድረኮች ብሎም በዓለም አቀፍ ደረጃ እንዲታወቁ ማድረግ እና እነዚህ ሁነቶች ላይ የሚሳተፉ ባለሙያዎች ጎን ለጎን ራሳቸውንም እንዲያስተዋውቁ መደገፍ እንደሆነም ተገልጿል።

📌በእረፍት ቀንዎ ቴአትር ይመለከቱ !
አንጋፋው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር እና የቦሌው ዓለም ሲኒማ አርብ፣ ቅዳሜ እና እሁድ እነዚህን ተውኔቶች ለታዳሚያን ያቀርባሉ።
📍 የፍቅር ካቴና
ድርሰትና ዝግጅት: አለልኝ መኳንት ፅጌ
ቀን: አርብ
ሰዓት: 12:00
ቦታ: ዓለም ሲኒማ
📍 "እሳት ወይ አበባ"
ድርሰት: ሎሬት ፀጋዬ ገብረመድህን እንደጻፈው
ዳንስና ዳንስ ቅንብር: ሽፈራው ታሪኩ ቢረጋ
ቀን: አርብ
ሰዓት:11:30
ቦታ: ብሔራዊ ቴአትር
📍 ባሎች እና ሚስቶች
ድርሰት: ውዱ አለን
አዘጋጅ: ሳሙኤል ተስፋዬ
ቀን: ቅዳሜ
ሰዓት: 8:00
ቦታ: ብሔራዊ ቴአትር
📍 ባቡሩ
ድርሰት: አርኖልድ ሪድሊ
አዘጋጅ:ራሔል ተሾመ መሐመድ
ቀን: ቅዳሜ
ሰዓት:11:30
ቦታ: ብሔራዊ ቴአትር
📍 ሸምጋይ
ድርሰት:ታደለ አያሌው
አዘጋጅ: ሳሙኤል ተስፋዬ
ቀን: እሁድ
ሰዓት: 8:00
ቦታ: ብሔራዊ ቴአትር
📍 እምዩ ብረቷ
ድርሰት: ቤልቶልት ብሬሽት
አዘጋጅ: ማንያዘዋል እንዳሻው
ቀን: እሁድ
ሰዓት:11:30
ቦታ: ብሔራዊ ቴአትር
የእናንተው ኤቨንት አዲስ ድረገፅ መልካም የእረፍት ቀን ይሁንላችሁ ይላል !
ለተጨማሪው: https://news.1rj.ru/str/EventAddis1

📌የልጅ ሚካኤል "የድሬ ልጅ" ሙዚቃ ቪዲዮ
ሙዚቀኛ ልጅ ሚካኤል (ፋፍ) "አዲስ አራዳ" የተሰኘ ሙሉ አልበሙን በዚህ ሳምንት ነሐሴ 22 2016 ዓ.ም ለአድማጮች አድርሷል።
"አዲስ አራዳ" አልበም 15 የሙዚቃ ስራዎችን ይዟል። የሙዚቃ ቅንብሩን ዮናስ ነጋሽ (ዮኒ) ሰርቶታል። አልበሙ ላይ ሳያት ደምሴን ጨምሮ በአጃቢነት (ፊቸሪንግ)የተሳተፉ ሙዚቀኞች እንዳሉበት ኤቨንት አዲስ ተመልክቷል።
እዚህ አልበም ውስጥ ከተካተቱ ስራዎች "የድሬ ልጅ"ለተሰኘው ሙዚቃ የሙዚቃ ቪዲዮ ተሰርቶለታል። ይህም የሙዚቃ ቪዲዮ ዛሬ አርብ ነሐሴ 24 2016 ዓ.ም በሙዚቀኛው የዩቲዩብ ቻናል በኩል ይለቀቃል።

📌የገጣሚና ሐያሲ በለው ገበየሁ መጽሐፍ ምርቃት
የገጣሚና ሐያሲ በለው ገበየሁ "እንኳንም መሃይም ሆንኩ" የተሰኘ መጽሐፍ ነገ ቅዳሜ ነሐሴ 25 ቀን 2016 ዓ.ም ከቀኑ 8:00 ጀምሮ በብሔራዊ ቤተመዛግብት እና ቤተመጻሕፍት አገልግሎት (ወመዘክር) አዳራሽ ውስጥ ይመረቃል።
በዚህ የመጽሐፍ ምርቃት ሥነሥርዓት ላይ ዘነበ ወላ፣ፀጋዬ ደቦጭ፣ ኃይሉ ፀጋዬ፣ በኃይሉ ገብረመድህን፣ ዘመዱ ደምስስ፣የሻው ተሰማ፣ታምሩ ብርሃኑ፣አንዱዓለም አባተ ሀሳቦቻቸውን ያጋራሉ ተብሏል።

📌"ብርቱ ንቁ ጀግና ዜጋ" ለአንድ ሺህ ሰዎች!
አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶች ስፖርት ቢሮ፣ የአዲስ አበባ ጤና ቢሮ እና ሄኖክ ኪዳነወልድ ስፖርት ስልጠናዎች በመተባበር "ብርቱ ንቁ ጀግና ዜጋ" በሚል መሪ ሀሳብ በውፍረት፣ በኮልሰትሮል፣ በስኳር፣ በደም ግፊት እና በተለያዩ ሱሶች ውስጥ ያሉና የመክፈል አቅም የሌላቸው 1000 ሰዎችን በነጻ የስፖርት እንቅስቃሴ፣የሥርዓተ ምግብና የህይወት ክህሎት ስልጠና ለመስጠት ዝግጅታቸውን ማጠናቀቃቸውን በዛሬው ዕለት ይፋ አድርገዋል።
"ብርቱ ንቁ ጀግና ዜጋ" የአካል እንቅሳቃሴ ስልጠና ጳጉሜን 2 ቀን 2016 ዓ.ም በወዳጅነት አደባባይ የሚጀመር ሲሆን ከወዳጅነት አደባባይ በተጨማሪም የአዲስ አበባ አምስቱንም የመውጫ በሮች ያማከሉ አምስት የስልጠና ቦታዎች እንደተዘጋጁ ተገልጿል።
በኮሌስትሮል ፣በስኳር ፣በደም ግፊት፣ በውፍረት ፣በሱስ እንዲሁም ሌሎች ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎች የተጠቁ ነዋሪዎች በስልጠናው የሚሳተፉ ሲሆን ጤናቸውን በአካል እንቅስቃሴ ማስተካከል የሚፈልጉ ሰዎችም በአቅራቢያቸው ካለ ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ሄደው መመዝገብ እንደሚችሉ ተገለጿል።
ስልጠናው ለሶስት ወራት የሚቆይ ሲሆን በዓመት ሶስቴ እንደሚዘጋጅና ቀጣይነት እንዳለው ተነግሯል።
ሥልጠናው ላይ የሥርዓተ ምግብና የህይወት ክህሎት ስልጠና ባለሙያዎች ለሰልጣኞች እገዛ የሚያደርጉ ይሆናል ተብሏል።በነፃ የሚሰጠው ስልጠና በገንዘብ ቢለወጥ ሠላሳ ሚልየን ብር ገደማ እንደሚያወጣ ተነግሯል።
ይሄን ስልጠና ለመስጠት ሶስቱ አካላት በቅንጅት ለመስራት የስምምነት ፊርማ ዛሬ ነሐሴ 25 2016 ዓ.ም በካፒታል ሆቴል ተፈራርመዋል።

📌በቀን 150 ሺህ መጻሕፍትን የሚጠርዝ ማሽን!
በቀን 150 ሺህ መጻሕፍትን የሚጠርዝ ዘመናዊ ማሽን ወደ ሥራ ማስገባቱን የትምህርት መሳሪያዎች ማምረቻና ማከፋፈያ ድርጅት አስታወቀ።
የድርጅቱ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ተመስገን ጋሩማ (ዶ/ር) እንደገለጹት፥ በ178 ሚሊዮን ብር ወጪ ከውጭ ሀገር የገባው አዲስ ማሽን በቀን እስከ 150 ሺህ መጻሕፍት የመጠረዝ አቅም አለው።
ማሽኑ በሰዓት 7 ሺህ መጻሕፍትን መጠረዝ ይችላል ያሉት ዋና ሥራ አስፈጻሚው፤ ድርጅቱ በ3 ፈረቃ እየሠራ በመሆኑ በቀን ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው መጻሕፍትን መጠረዝ እንደሚቻል ጠቁመዋል።
በርካታ የትምህርት መርጃ መጻሕፍት ከውጭ ሀገራት እንደሚገቡ ገልጸው፤ አዲሱ ማሽን መጻሕፍቱን በሀገር ውስጥ በመጠረዝ የውጭ ምንዛሬ ወጪን ለመቀነስ እንደሚረዳ ተናግረዋል።
በሀገር ውስጥ የማዘጋጀት ሒደቱ መጻሕፍት ከውጭ ሀገራት ተጓጉዘው ሲገቡ የሚወስደውን ረጅም ጊዜ የሚቀንስ መሆኑም የተገለጸ ሲሆን፤ ማሽኑ በዛሬው ዕለት ለምረቃ በቅቷል።
📌መረጃው የኢቢሲ ነው።

"የካሲናዬ" ፊልም አዘጋጅና ማያ ሚዲያ ይቅርታ ጠየቁ
በብርሃኑ ወርቁ ተዘጋጅቶ የቀረበው "ካሲናዬ" የተሰኘ የአማርኛ ፊልም ከቀናት በፊት በማያ ሚዲያ በኩል የተለቀቀ ሲሆን ፊልሙ ላይ አንዲት ሴት፣ ሱሪ አድርጋ፣ሊፒስቲክ ተቀብታ በቤተክርቲያ ውስጥ መግባቷ ይህም ድርጊቷ በፊልሙ ውስጥ መካተቱ የቤተክርስቲያንን ሥርዓት አይወክልም በሚል ብዙ የኢትዮጵያ ኦሮቶዶክስ ተዋሕዶ ምዕመናንን አሳዝኗል:: በዚህ ምክንያት በማያ ሚዲያ እና በፊልሙ አዘጋጆች ላይ ተቃውሞ ተነስቷል።
ከደቂቃዎች በፊትም ማያ ሚዲያና የፊልሙ አዘጋጅ በማያ ሚዲያ የይፋዊ የማህበራዊ ትስስር ገፁ ላይ በይፋ ይቅርታ እንደጠየቁ ኤቨንት አዲስ ድረገፅ ተመልክቷል።
ማያ ሚዲያ እና የፊልሙ አዘጋጅ"በቅርቡ በማያ ሚዲያ "#ካሲናዬ" የተሰኘ አዲስ ኢትዮጵያዊ ይዘት ያለው ፊልም መለቀቁ ይታወሳል፡፡ሃይማኖታዊ ሥርአቱን ያልጠበቀ ትዕይንት በፊልሙ ውስጥ ባለማስተዋል በመካተቱ ምክንያት ለተፈጠረው ስህተት የፊልሙ ባለሙያዋች፣ የፊልሙ አዘጋጅ እና ማያ ሚዲያ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያንን እና የእምነቱን ተከታዮች በሙሉ ልባዊ የሆነ ይቅርታ እንጠይቃለን" ያሉ ሲሆን
በተጨማሪም " ቅሬታ ያስነሳው የፊልሙን ክፍል በመቁረጥ ለእይታ አብቅተናል "ብለዋል።

📌 "የማይከስም እሳት" መጽሐፍ ምርቃት
በደራሲ አርሴማ በቀለ የተጻፈው "የማይከስም እሳት" የልቦለድ መጽሐፍ ዛሬ ሰኞ ነሐሴ 27 2016 ዓ.ም ከምሽቱ 11:00 ጀምሮ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት ይመረቃል።
"የማይከስም እሳት" መጽሐፍ በይዘት በእውነተኛ ታሪክ ላይ የተመሰረተ ልቦለድ ሲሆን በ4 ምዕራፎች ተከፍሎ፣ በ264 ገፆች ተቀንብቦ፣ በ400 ብር የጀርባ ዋጋ ለአንባቢያን ይቀርባል ተብሏል።
በዚህ የመጽሐፍ ምርቃት ሥነሥርዓት ላይ መምህርና ደራሲ ስሜ ታደሰ፣ የሥነልቦና ባለሞያው ዮሐንስ ከበደ እና ሌሎችም ሀሳቦቻቸውን ያጋራሉ።

📌 "ግጥም ሲጥም" ረቡዕ ይካሄዳል
"ግጥም ሲጥም "ለሁሉም ክፍት የሆነ የኪነጥበብ መድረክ ረቡዕ ነሐሴ 29 2016 ዓ.ም ከምሽቱ 12:00 ጀምሮ ገርጂ በሚገኘው ደስክ አዲስ ውስጥ ይካሄዳል።
የግጥም ሲጥም አዘጋጆችም "ዓመቱ ሊሸኝ ተተኪውም ሊገባ ነው። እኛም ወር ጠብቀን ይኸው ገርጂ በሚገኘው ደስክ አዲስ ልንከሰት ሆነ።
የጻፋችሁትን፣ የተዘጋጃችሁበትን፣ ሰው ጋር ቢቀርብ የምትሉትን ሁሉ ይዛችሁ ብትመጡ እናንተን ለማየት ከሚመጡ ጥበብ ወዳድ ምርጥዬ ሰዎች ጋር ትተዋወቃላችሁ" ብለዋል።
የዚህ ኪነጥበባዊ ዝግጅት መግቢያ በጊዜ መገኘታችሁ ነው ተብላችኋል።
ለተጨማሪው :https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
"ግጥም ሲጥም "ለሁሉም ክፍት የሆነ የኪነጥበብ መድረክ ረቡዕ ነሐሴ 29 2016 ዓ.ም ከምሽቱ 12:00 ጀምሮ ገርጂ በሚገኘው ደስክ አዲስ ውስጥ ይካሄዳል።
የግጥም ሲጥም አዘጋጆችም "ዓመቱ ሊሸኝ ተተኪውም ሊገባ ነው። እኛም ወር ጠብቀን ይኸው ገርጂ በሚገኘው ደስክ አዲስ ልንከሰት ሆነ።
የጻፋችሁትን፣ የተዘጋጃችሁበትን፣ ሰው ጋር ቢቀርብ የምትሉትን ሁሉ ይዛችሁ ብትመጡ እናንተን ለማየት ከሚመጡ ጥበብ ወዳድ ምርጥዬ ሰዎች ጋር ትተዋወቃላችሁ" ብለዋል።
የዚህ ኪነጥበባዊ ዝግጅት መግቢያ በጊዜ መገኘታችሁ ነው ተብላችኋል።
ለተጨማሪው :https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
📌ባይራ እና መዲና ዲጂታል መጽሔቶች
መዲና እና ባይራ የተሰኙ ሁለት ዲጂታል መጽሔቶች በሳምንቱ መጨረሻ ቀናት ለንባብ በቅተዋል።
ሁለቱም ዲጂታል መጽሔቶች በጥበባዊ እና ማህበራዊ ጉዳዮች ላይ ትኩረታቸውን አድርገው በቅጽ በፈረጅ በፈረጁ ተሰናድተው ቴሌግራምን ጨምሮ በዲጂታል ማሰራጫዎች ለአንባቢያን ይቀርባሉ።
የመዲና ዲጂታል መጽሔት "ቅጽ 6" ለንባብ የበቃ ሲሆን መጽሔቷን ለማንበብ ይህንን የቴሌግራም ገጽ ይጠቀሙ ተብለዋል።
https://news.1rj.ru/str/Medinamagazine
በሌላ በኩል ባይራ ዲጂታል መጽሔት"ቅጽ 1 ቁጥር 8" ማንበብ ለሚፈልጉ አንባቢያን ደግሞ በእነዚህ የማህበራዊ ሚዲያ አማራጮች እንደተለቀቀ አዘጋጆቹ አስታውቀዋል።
ቴሌግራም- https://news.1rj.ru/str/Bayradigital
ድረገጽ (Website) https://bayradigital.com/

📌ጋዜጠኛ መስከረም ጌታቸው ከማኅበረ ቅዱሳን ብሮድካስት አገልግሎት ኃላፊነት እንደለቀቀች አስታወቀች።
ጋዜጠኛ መስከረም ጌታቸው ለአምስት ዓመታት ካገለገለችበት ከማኅበረ ቅዱሳን ብሮድካስት አገልግሎት ተቋም እንደለቀቀች ኤቨንት አዲስ ድረገፅ ከጋዜጠኛዋ ይፋዊ የማህበራዊ ትስስር ገፅ ላይ ከተሰራጨው መረጃ ተመልክቷል።
ጋዜጠኛዋ "ለ5 ዓመታት በመደበኛነት ካገለገልሁበት (እኔው ከተገለገልሁበት) የማኅበረ ቅዱሳን ብሮድካስት አገልግሎት ተቋም ኃላፊነት ለቀቅሁ" ብላለች።
መልቀቋንም ለማሳወቅ እንደምክንያት ሁለት ጉዳዮችን ጠቅሳለች "መልቀቄን ማሳወቅ እንዳልነበረብኝ አውቃለሁ ነገር ግን ሚዲያ አገልግሎት ላይ ነኝና ስለ2 ምክንያት ጻፍኩት አንደኛ ከዚህ በኋላ ለምጽፋቸውና ለማደርጋቸው ኃላፊነት የምወስደው እኔ መሆኔን ለማሳወቅ ሁለተኛ በቀጣይ በሚዲያ አገልግሎት መገናኘታችን ስለማይቀር ለቅቄ እንጂ ደርቤ እንዳልሆነ ለመግለጥ ነው" ያለች ሲሆን
"በመጨረሻም በሕይወቴ አስቤ በማላውቀው የመደበኛ አገልግሎት ቤቱን እንዳገለግል እግዚአብሔር እድሉን ስለሰጠኝ አመሰግነዋለሁ " በማለት ምስጋናዋን አቅርባለች።
በቀጣይም "በጥቂት ቀናት ውስጥ ቀጣይ መዳረሻዬን አሳውቃለሁ" ብላለች።

📌በያሬድ የሙዚቃ ት/ቤት ውስጥ የተገነባው ማዕከል እስካሁን ስራ አለመጀመሩ ተገለጸ
ለዓመታት በግንባታ መጓተት ምክንያት ቆይቶ የነበረው "አሸናፊ ከበደ የሙዚቃዊ ጥበባት ማዕከል" ተመርቆ ለስራ ዝግጁ ከሆነ ወራት ቢያስቆጥርም አሁንም ስራ አለመጀመሩን ያሬድ የሙዚቃ ትምህርት ቤት ለመናኸሪያ ሬዲዮ አስታውቋል።
አዳራሹ ዘመናዊ ሳውንድ ሲስተም ስለሚያስፈልገው መጓተቱን ያስታወቁት ፒያኒስትና በያሬድ የሙዚቃ ት/ቤት የአሸናፊ ከበደ ሙዚቃዊ ጥበባት ማዕከል ዳይሬክተር አቶ ግርማ ይፍራሸዋ ናቸው።
በአዳራሹ የሚገጠመው ዘመናዊ ሳውንድ ሲስተም ከውጭ ሀገር የሚገባ በመሆኑና እስካሁን ባለው ሂደት ገብቶ ባለመጠናቀቁ አዳራሹ ስራ ሳይጀምር መቆየቱን አቶ ግርማ ይፍራሸዋ ተናግረዋል። ከውጭ የሚመጡትን እቃዎች ከመጠበቅ ውጭ አዳራሹ ለስራ ምቹና ብቁ ነው በማለት ከመጪው መስከረም ወር በፊት እንዲጠናቀቁ እየተሰራ እንደሚገኝም አቶ ግርማ አክለው ገልጸዋል።
የያሬድ ሙዚቃ ት/ቤት ሁለገብ አዳራሽ ለተለያዩ የት/ቤቱ የሙዚቃ ተማሪዎችና ባለሙያዎች እንዲሁም ለተለያዩ ከት/ቤቱ ውጭ ለሚገኙም የሙዚቃ ባለሙያዎች የኦርኬስትሬሽንና መሰል ስራዎች ማሳያ እንደሚሆን መገለጹ ይታወሳል።
📌መረጃው የመናኸሪያ ሬዲዮ ነው።

📌"ትንሿ ቤተ-መጻሕፍት ተመረቀች "
በደራሲ የዝና ወርቁ መኖሪያ ቤት የተሰራችው ትንሿ የልጆች ቤተ-መጻሕፍት ባሳለፍነው ዕሁድ ነሐሴ 26 ቀን 2016 ዓ.ም ተመርቃለች።
በደራሲዋ ሃሳብ አመንጭነት ላለፉት 7 ዓመታት "ችግኝ፤ የአንድ መንደር ልጆች የንባብና የውይይት ክበብ" በሚል የአካባቢውን ልጆች በመኖርያ ቤቷ ሳሎን በማሰባሰብ የንባብ ችሎታቸውን እንዲያዳብሩ ስታደርግ ቆይታለች።
አሁን ደግሞ እዛው በመኖርያ ቤቷ ጊቢ ውስጥ ቤተ-መጻሕፍት የሰራች ሲሆን ቤተ-መጻሕፍቱ የአካባቢው ልጆች ተሰባስበው የሚያነቡበትና የሚያስፈልጋቸውን መጽሐፍ በውሰት እንዲያገኙበት ታስቦ የተሰራ ነው ተብሏል።
የዝና ወርቁ "በአሁን ጊዜ በተለይ ከተማ ላይ ሁሉም ግቢውን አጥሮ የሚኖርበት ጊዜ ነው ፣ ልጆች አካባቢያቸው ከሚኖሩ እኩዮቻቸው ጋር አብረው የማሳለፍ ዕድላቸው አናሳ ነው። አካባቢን ማወቅ ሀገርን ማወቅ በመሆኑ ልጆቹ እርስ በእርሳቸው እንዲተዋወቁና በንባብ ራሳቸውን እንዲያበለጽጉ በማሰብ ይህን ስራ ልጀምረው ችያለው"ስትል ተናግራለች።
በዕለቱ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ፣ የአካባቢው ነዋሪዎችና የመገናኛ ብዙኃን ባለሙያዎች ተገኝተዋል።
የመጀመሪዋ የአጭር ልቦለድ ሴት ደራሲ የሆነችው የዝና ወርቁ በርካታ የስነ-ጽሑፍ ስራዎችን ለንባብ ያበቃች ሲሆን የተሸጠው ሰይጣን ፣ የመመረቂያው ልብስ ፣ የደራሲዋ ፋይል ፣ የአፍንጮ በር ወፎች ፣ ይቅርታ፣ መፍቻውና ሌሎች የተሰኙ ስራዎቿ ተጠቃሽ ናቸው።
📍መረጃው የኢትዮጵያን ሪድስ ነው።

📌 "ከለቻ" መጽሐፍ እሁድ ይመረቃል
በጋዜጠኛ ሐብታሙ ባንታየሁ "ከለቻ" በሚል ርዕስ የተጻፈ አዲስ መጽሐፍ የፊታችን እሁድ ጳጉሜን 3 2016 ዓ.ም ከቀኑ 7:00 ጀምሮ በብሔራዊ ቤተመዛግብት እና ቤተመጻሕፍት አገልግሎት (ወመዘክር ) ብላቴን ጌታ ህሩይ ወ/ሥላሴ አዳራሽ ውስጥ ይመረቃል።
"ከለቻ" መጽሐፍ በዘውግ በኩል ረጅም ልቦለድ ሲሆን በ5 ምዕራፎች ተከፍሎ፣ በ96 ተቀንብቦ በ200 ብር የጀርባ ዋጋ ለአንባቢያን ይቀርባል ተብሏል።
በዚህ መጽሐፍ የምርቃት ሥነሥርዓት ላይ ፀሐፌተውኔት አያልነህ ሙላቱ፣ ደራሲ ኃይለመለኮት መዋዕል፣ ደራሲ ጌታቸው በለጠ እና ሌሎችም ሀሳቦቻቸውን ያጋራሉ ተብሏል።

📌"ዝክረ ጥበባት"
"ዝክረ ጥበባት" የኪነጥበብ ዝግጅት ነገ አርብ ጳጉሜን 1 2016 ዓ.ም ከቀኑ 11:30 ጀምሮ በጊዮን ሆቴል ይካሄዳል። በዚህ የኪነጥበብ ዝግጅት ላይ ግጥም፣ ሙዚቃ፣ ወግ፣የአንድ ሰው ተውኔትና ሌሎችም ጥበባዊ ዝግጅቶች ይቀርባሉ ተብሏል።

📌የተስፋዬ ማሞ አዲስ መጽሐፍ
በሸገር ሬድዮ 102.1 "የጥበብ መንገድ" የሬድዮ ፕሮግራም አዘጋጅ፣ የማስታወቂያ ባለሞያና ደራሲ ተስፋዬ ማሞ "ከማዕበል ማዶ" የተሰኘ አዲስ መጽሐፉን በቅርቡ ለአንባቢያን እንደሚያደርስ አስታውቋል።
በማህበራዊ ትስስር ገፁም"ከሁለት ዓመት በላይ አንገቴን ቀብሬ ለፍቼበታለሁ።ብዙ ሰዎች እንዲያዩልኝ ሰጥቼ እጅግ ልብ የሚያሞቁ አስተያየቶችን ሰብስቤአለሁ።ግን የእውነት ቀኑ ደረሰ ወደኋላ የሚያስኬድ ምንም መንገድ የለም።በቅርብ ቀን ማለትን ግን ፈራሁ።ምን ብፈራ ግን የቁርጥ ቀን አለውና አይቀርልኝም እየመጣሁ ነው። በአዲሱ አመት 2017ን በሥነጽሑፍ በረከታቸው አሐዱ ከሚሉት መሐል ለመሆን መንገድ ላይ ነኝ"ብሏል።
ተስፋዬ ማሞ ከዚህ ቀደም "ዕፀበለስ" እና "የጨረቃ ጥሪ" የተሰኙ መጻሕፍትን ለአንባቢያን አድርሷል።

📌ስሙ ኦዲዮ ቡክ መተግበሪያ ለዓይነስውራን
ስሙ ኦዲዮ ፕሮዳክሽን ለ17 ሺህ 260 አይነ ስውራን የመፅሐፍ ትረካ አገልግሎት ልሰጥ ነው ብሏል።
ስሙ ኦዲዮ ፕሮዳክሽን በስሙ ኦዲዮ ቡክ የሞባይል መተግበሪያው በድምፅ የተቀረፁ መፅሐፍትን ለ1 ዓመት በነፃ ለኢትዮጵያ አይነ ስውራን ብሔራዊ ማህበር አገልግሎት ሊሰጥ መሆኑን ሰምተናል።
በተቋሙ የፕሮዳክሽን ማናጀር ሩት ሀብተማርያም እንደተናገሩት ስማርት ስልክ ላላቸው የማህበሩ አባላት በሙሉ ይህንን አገልግሎት ማግኘት ይችላሉ።
እስካሁን በመተግበሪያው ወደ 200 የሚጠጉ መፅሐፍት በድምፅ የተተረኩ ሲሆን እነዚህን መፅሐፍት ለአካል ጉዳተኞች በተመቸ መልኩ ለማቅረብ ጥረት መደረጉን ነግረውናል።
በመሆኑም በስምምነቱ መሰረት አገልግሎቱን ከሚቀጥለው ሳምንት ጀምሮ እንደሚሰጥ ነው የተናገሩት።
የኢትዮጵያ አይነ ስውራን ማህበር ፕሬዚዳንት አቶ አበራ ረታ በበኩላቸው መፅሐፍትን በድምፅ በማቅረብ በኩል ተደራሽ ያላደረግናቸው የማህበሩ አባላትን ተደራሽ ለማድረግ ያግዘናል ብለዋል።
መፅሐፍትን እና እውቀትን ለአካል ጉዳተኞች ማስተላለፍ እንደሚያስፈልግም ገልጸዋል።
📍መረጃው የአራዳ ኤፍ ኤም ነው።