📌ስሙ ኦዲዮ ቡክ መተግበሪያ ለዓይነስውራን
ስሙ ኦዲዮ ፕሮዳክሽን ለ17 ሺህ 260 አይነ ስውራን የመፅሐፍ ትረካ አገልግሎት ልሰጥ ነው ብሏል።
ስሙ ኦዲዮ ፕሮዳክሽን በስሙ ኦዲዮ ቡክ የሞባይል መተግበሪያው በድምፅ የተቀረፁ መፅሐፍትን ለ1 ዓመት በነፃ ለኢትዮጵያ አይነ ስውራን ብሔራዊ ማህበር አገልግሎት ሊሰጥ መሆኑን ሰምተናል።
በተቋሙ የፕሮዳክሽን ማናጀር ሩት ሀብተማርያም እንደተናገሩት ስማርት ስልክ ላላቸው የማህበሩ አባላት በሙሉ ይህንን አገልግሎት ማግኘት ይችላሉ።
እስካሁን በመተግበሪያው ወደ 200 የሚጠጉ መፅሐፍት በድምፅ የተተረኩ ሲሆን እነዚህን መፅሐፍት ለአካል ጉዳተኞች በተመቸ መልኩ ለማቅረብ ጥረት መደረጉን ነግረውናል።
በመሆኑም በስምምነቱ መሰረት አገልግሎቱን ከሚቀጥለው ሳምንት ጀምሮ እንደሚሰጥ ነው የተናገሩት።
የኢትዮጵያ አይነ ስውራን ማህበር ፕሬዚዳንት አቶ አበራ ረታ በበኩላቸው መፅሐፍትን በድምፅ በማቅረብ በኩል ተደራሽ ያላደረግናቸው የማህበሩ አባላትን ተደራሽ ለማድረግ ያግዘናል ብለዋል።
መፅሐፍትን እና እውቀትን ለአካል ጉዳተኞች ማስተላለፍ እንደሚያስፈልግም ገልጸዋል።
📍መረጃው የአራዳ ኤፍ ኤም ነው።
ለተጨማሪው: https://news.1rj.ru/str/EventAddis1

📌በእረፍት ቀንዎ ቴአትር ይመለከቱ !
አንጋፋው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር እና የቦሌው ዓለም ሲኒማ አርብ፣ ቅዳሜ እና እሁድ እነዚህን ተውኔቶች ለታዳሚያን ያቀርባሉ።
📍 የፍቅር ካቴና
ድርሰትና ዝግጅት: አለልኝ መኳንት ፅጌ
ቀን: አርብ
ሰዓት: 12:00
ቦታ: ዓለም ሲኒማ
📍 "እሳት ወይ አበባ"
ድርሰት: ሎሬት ፀጋዬ ገብረመድህን እንደጻፈው
ዳንስና ዳንስ ቅንብር: ሽፈራው ታሪኩ ቢረጋ
ቀን: አርብ
ሰዓት:11:30
ቦታ: ብሔራዊ ቴአትር
📍 ባሎች እና ሚስቶች
ድርሰት: ውዱ አለን
አዘጋጅ: ሳሙኤል ተስፋዬ
ቀን: ቅዳሜ
ሰዓት: 8:00
ቦታ: ብሔራዊ ቴአትር
📍 ባቡሩ
ድርሰት: አርኖልድ ሪድሊ
አዘጋጅ:ራሔል ተሾመ መሐመድ
ቀን: ቅዳሜ
ሰዓት:11:30
ቦታ: ብሔራዊ ቴአትር
📍 ሸምጋይ
ድርሰት:ታደለ አያሌው
አዘጋጅ: ሳሙኤል ተስፋዬ
ቀን: እሁድ
ሰዓት: 8:00
ቦታ: ብሔራዊ ቴአትር
📍 እምዩ ብረቷ
ድርሰት: ቤልቶልት ብሬሽት
አዘጋጅ: ማንያዘዋል እንዳሻው
ቀን: እሁድ
ሰዓት:11:30
ቦታ: ብሔራዊ ቴአትር
የእናንተው ኤቨንት አዲስ ድረገፅ መልካም የእረፍት ቀን ይሁንላችሁ ይላል !

📌 "ከለቻ" መጽሐፍ እሁድ ይመረቃል
በጋዜጠኛ ሐብታሙ ባንታየሁ "ከለቻ" በሚል ርዕስ የተጻፈ አዲስ መጽሐፍ ነገ እሁድ ጳጉሜን 3 2016 ዓ.ም ከቀኑ 7:00 ጀምሮ በብሔራዊ ቤተመዛግብት እና ቤተመጻሕፍት አገልግሎት (ወመዘክር ) ብላቴን ጌታ ህሩይ ወ/ሥላሴ አዳራሽ ውስጥ ይመረቃል።
"ከለቻ" መጽሐፍ በዘውግ በኩል ረጅም ልቦለድ ሲሆን በ5 ምዕራፎች ተከፍሎ፣ በ96 ተቀንብቦ በ200 ብር የጀርባ ዋጋ ለአንባቢያን ይቀርባል ተብሏል።
በዚህ መጽሐፍ የምርቃት ሥነሥርዓት ላይ ፀሐፌተውኔት አያልነህ ሙላቱ፣ ደራሲ ኃይለመለኮት መዋዕል፣ ደራሲ ጌታቸው በለጠ እና ሌሎችም ሀሳቦቻቸውን ያጋራሉ ተብሏል።

📌የተስፋዬ ማሞ አዲስ መጽሐፍ ለንባብ በቃ
በሸገር ሬድዮ 102.1 "የጥበብ መንገድ" የሬድዮ ፕሮግራም አዘጋጅ፣ የማስታወቂያ ባለሞያና ደራሲ ተስፋዬ ማሞ "ከማዕበል ማዶ: ገፀ-ብዙ ስብዕና" የተሰኘ አዲስ መጽሐፍ ጷጉሜን 1 2016 ዓ.ም ለንባብ በቅቷል።
መጽሐፉ ጃፋር መጻሕፍት መደብርን ጨምሮ በተለያዩ መጻሕፍት መደብሮች ይገኛል ተብሏል።
ተስፋዬ ማሞ "ከማዕበል ማዶ" በሚል ርዕስ የጻፈውም መጽሐፍ የአውቶባዮግራፊ ዘውግ እንዳለው ኤቨንት አዲስ ድረገፅ ሰምቷል።
ደራሲ ተስፋዬ ማሞ ከዚህ ቀደም "ዕፀበለስ" እና "የጨረቃ ጥሪ" የተሰኙ መጻሕፍትን ለአንባቢያን አድርሷል።

📌"አማኑኤል ሃብታሙን እናክብር "
አርቲስት አማኑኤል ሀብታሙ "አማን በአሜሪካ የአንድ ሰው ቴአትር" በሚል ርዕስ በሀገረአሜሪካን ዝግጅቱን ሊያቀርብ እንደሆነ ኤቨንት አዲስ ድረገፅ ሰምቷል።
በዚህ መርሐግብር ላይ"አማኑኤል ሀብታሙን እናክብር" በሚል ለአርቲስት አማኑኤል ስራዎቹ እውቅና የሚሰጥበት ሥነሥርዓትም ተዘጋጅቷል ተብሏል።
ዝግጅቱም በአሜሪካ ሴልቨር ስፕሪንግ
ሴፕቴምበር 14 እና 15 2024 ይካሄዳል።

📌 ልዩ መርሐግብር በካፒታል ሆቴል
"ምስጋና እና ይቅርታ" የተሰኘ የአዲስ ዓመት ዋዜማ ልዩ መርሐግብር ጷጉሜን 3 2016 ዓ.ም ከቀኑ 8:00 ጀምሮ በአዲስ አበባ ካፒታል ሆቴል ይካሄዳል።
በዚህ ልዩ መርሐግብር ስለ "ምስጋና" እንዲሁም ስለ "ይቅርታ" ሀሳቦች በአዲስ ዓመት ዋዜማ ልዩ ልዩ ባለሞያዎች ሀሳቦቻቸውን በመድረኩ ያጋራሉ ተብሏል።

📌"ስብሐቲዝም" የሀሳብ ውይይት ዛሬ ይካሄዳል
ሐሳብ፣ ንባብ፣የውይይት መንገድ ላይ ትኩረቱን ያደረገው "ስብሐቲዝም" ኪናዊ ውይይት መድረክ ዛሬ እሁድ ጳጉሜን 3 2016 ዓ.ም ከቀኑ 8:00 ጀምሮ በብሔራዊ ቤተመዛግብት እና ቤተመጻሕፍት አገልግሎት (ወመዘክር) አዳራሽ ውስጥ ይካሄዳል ።
በዚህኛውም ዙር መድረክ "በነባር ማንነት አዲስነት ለ2017 " በሚል ርዕስ ውይይት ይካሄዳል።
አዘጋጆቹም "ከነባር ልማዶቻችን የቱን ጥለን የቱን አንጠልጥለን በነባር ማንነቶቻችን ላይ አዲስነትን ስለማዋሃድ። ኑ ከቡርሃን አዲስ ጋር እንጨዋወት።መግቢያ ምንጊዜም በነፃ ነው"ብለዋል።

📌የድምጻዊ እሱባለው ይታየው አዲስ ሙዚቃ!
የድምጻዊ እሱባለው ይታየው(የሺ) "የበርሽ አበባ" የተሰኘ ርዕስ የተሰጠው የበዓል ሙዚቃ ዛሬ ጳጉሜን 3 2016 ዓ.ም እንደሚለቀቀ ኤቨንት አዲስ ድረገፅ ከድምጻዊው ያገኘው መረጃ ያመለክታል።
በተጨማሪም ድምጻዊ እሱባለው ይታየው "በመላው ዓለም የምትገኙ ሁሉ እንኳን ለአዲሱ ዓመት በሰላም አደረሰን አደረሳችሁ እያልኩ "የበርሽ አበባ" የተሰኘ ሙዚቃዬ የራሴ በሆነው በEsubalew Yitayew Yeshi የዩቱዩብ ቻናል ላይ ዛሬ ማታ ይለቀቃል ገብታችሁ ተጋበዙልኝ መልካም በዓል ሰላም ለዓለም" ብሏል።

📌"ቡርሻት" የጉራጊኛ የሙዚቃ አልበም !
የድምጻዊ ፀጋዬ ስሜ(ኦሴባሳ) "ቡርሻት" የተሰኘ 7ኛ አልበም ከጥቂት ቀናት በኋላ ይለቀቃል ተብሏል።
የአንጋፋው የጉራጊኛ ሙዚቃ ተጫዋች፣ ዜማ ደራሲና ገጣሚ አርቲስት ፀጋዬ ስሜ "ቡርሻት" 7ኛ የሙዚቃ አልበም በአዲስ ዓመት ዋዜማ እንደሚለቀቅ ኤቨንት አዲስ ሰምቷል።
ከዚህ ቀደም ''ክስታኔ ባንድ፣ ኬር ዬሁን፣ ኦሴባሳ(ባላገር)፣ ዬሻልቢ፣ ጥንቡሳሳም እና ሱታና'' በተሰኙ ተወዳጅ የሙዚቃ አልበም ሥራዎቹ የሚታወቀው አርቲስት ፀጋዬ ስሜ አሁን ደግሞ ለአዲስ አመት በአዲስ መንፈስ ''ቡርሻት'' ብሎ መጥቷል። ''ቡርሻት'' ተወዳጅ የጉራጊኛ ቃል ሲሆን ትርጓሜውም ናፍቆት ማለት ነው፡፡
''ቡርሻት'' ከሀገር እስከ ፍቅር፤ ከባህል እስከ ከቋንቋ፤ ከስክነት እስከ አንድነት፤ የተለያዩ ጭብጠ ሃሳቦችን ዳሶ የተሰናዳ አልበም ነው።

📌"ሦስተኛው ዓይን" የሥዕል አውደርዕይ!
የሠዓሊ መሐሪ ተሾመ "ሦስተኛው ዓይን: The third eye" የሥዕል አውደርዕይ ቅዳሜ መስከረም 4 2016 ዓ.ም ቦሌ አትላስ አካባቢ በሚገኘው
ለተጨማሪው: https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
የሠዓሊ መሐሪ ተሾመ "ሦስተኛው ዓይን: The third eye" የሥዕል አውደርዕይ ቅዳሜ መስከረም 4 2016 ዓ.ም ቦሌ አትላስ አካባቢ በሚገኘው
አናፎራ የጥበብ ማዕከል ውስጥ ለእይታ ይበቃል።ይህ የሥዕል አውደርዕይ ከአንድ ወር በላይ በእይታ ይቆያል ተብሏል።ለተጨማሪው: https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
📌"የምስራቁ ጮራ" የተሰኘ መጽሐፍ አንድ ኮፒ በሁለት ሚሊዮን ብር ተሸጠ
የምስራቅ ዕዝ 47ኛ ዓመት የምስረታ በዓልን ሲያከብር ያሳተመው የዕዙን ከምስረታ ጀምሮ እስከ አሁን ድረስ ለአገር ሰላምና እድገት ለዳር ድንበር መከበር ያበረከተውን አስተዋፅኦ እና የተከፈለውን መስዕዋትነት የሚያትተው " የምስራቁ ጮራ" የተሰኘ መፅሃፍ በበዓሉ ማጠቃለያ ፕሮግራም ላይ በተደረገው ጨረታ አንድ መፅሃፍ በሁለት ሚሊዮን ብር ተሸጧል፡፡
መፅሃፉን በጨረታ ያሸነፉት አቶ ወልደጊወርጊስ ይልቃል እንደተናገሩት ምስራቅ ዕዝ 47ኛ ዓመት የምስረታ በዓሉን ከማህበረሰቡ ጋር ማክበሩ ወታደሩ ለአገሩና ለህዝቡ ምን ያክል ዋጋ እየከፈለ እንዳለ የተረዱበት መሆኑን አውስተው እንደዚህ አይነት ወታደራዊ መፅሃፍቶች ሰራዊቱ ለአገሩ እና ለህዝቡ ሰላምና መረጋጋት እየከፈለው ያለውን መስዋዕትነት ለትውልድ ለማስተላለፍ ያላቸው ፋይዳ ከፍተኛ በመሆኑ የምስራቁ ጮራ የተሰኘው መፅሃፍም የሰራዊቱን ገድልና ጀግንነት ያካተተ መሆኑን በመረዳቴ መፅሃፉን ገዝቻለሁ ብለዋል፡፡
ሠራዊቱ ለአገሩ እየከፈለ ያለዉን መስዋዕትነት በተገቢው መንገድ ሰንዶና ፅፎ ለትውልድ በማስተላለፍ የአገራችን መከላከያ ሰራዊት ይችን አገር እንዴት አድርጎ ወደዛሬ እንዳሻገራት ለመጪው ትውልድ ማስተላለፍ ተገቢ በመሆኑና የመፅሃፉ ሽያጭ ለአገራቸው ሰላምና እድገት ሲዋደቁ ጉዳት ለገጠማቸው ጀግኖች መደጎሚያና ለምስራቅ ዕዝ ለሚያስገነባው ቤተ-መፅሃፍት እንደሚውል በመረዳቴ ይህንን ታሪካዊ መፅሃፍ በከፍተኛ ዋጋ ለመግዛት ችያለሁ ነው ያሉት፡፡
የምስራቁ ጮራ መፅሃፍ ሽያጭ 50% ለጀግኖች አምባና ቀሪው 50% ለቤተ-መፅሃፍ ግንባታ የሚውል መሆኑ በዝግጅቱ ተነግሯል።
📌መረጃው የሸገር ታይምስ ነው።
ለተጨማሪው : https://news.1rj.ru/str/EventAddis1

📌ኤስ ኦ ኤስ የህፃናት መንደሮች በኢትዮጵያ የሐምሳኛ ዓመት ክብረበዓል በተለያዩ ሁነቶች እየተከበረ ይገኛል።
ኤስ ኦ ኤስ የሕጻናት መንደሮች በኢትዮጵያ የዓለም አቀፉ ኤስ ኦ ኤስ የሕጻናት መንደሮች ፌዴሬሽን ብሔራዊ አባል ሲሆን፣ በሕጻናት ደሕንነት እና ልማት ላይ አትኩሮ የሚሰራ ከማንኛውም ወገንተኝነት የጸዳ ድርጅት ነው።
ኤስ ኦ ኤስ የሕጻናት መንደሮች በኢትዮጵያ የተመሰረተበትን 50ኛ ዓመት በተለያዩ ሁነቶች እያከበረ የሚገኝ ሲሆን ከእዚህም ሁነቶች አንደኛ የሆነውን የችግኝ ተከላ መርሃግብር በዛሬው ዕለት ጳጉሜ 4 ቀን 2016 ዓ.ም አካሄዷል።
ወደ 250 የሚጠጉ የድርጅቱ ሰራተኞች፣ ሲቪል ማሕበረሰብ ድርጅቶች፣ የመንግስት መስሪያ ቤት ተወካዮች እና ሌሎችም በተገኙበት በዛሬው ዕለት አቦ ማዞሪያ ልዩ ስሙ ‘ጊልዶ ዋሻ‘ በተሰኘው አካባቢ የችግኝ ተከላ መርሐግብር እንደተካሄደ ተገልጧል።
ይህ የችግኝ ተከላ የ50ኛው ዓመት ክብረ በዓል አንድ አካል እንደሆነም ተነገሯል።
ከችግኝ ተከላ መርሐግብር በተጨማሪም ክብረበዓሉን ቀኤግዚቢሽን፣ በፓናል ውይይት እና የገቢ ማሰባሰቢያ ፕሮግራሞችን በማከናወን እንደሚከበር ተጠቁሟል።

📌 "ሽልማት" የሙዚቃ አልበም ተለቀቀ
አባትና ልጅ በጋራ የሰሩት አልበም ተለቋል።ወላጅ አባት ኤላ ማን እና ልጅ ክርስቲና የተጣመሩበት "ሽልማት" የተሰኘ የሙዚቃ አልበም ከቀናት በፊት በራሳቸው የዩቲዩብ ቻናልና በዓለም አቀፍ የሙዚቃ መተግበሪያዎች ላይ እንደተለቀቀ ኤቨንት አዲስ ድረገፅ ተመልክቷል።
ይህ "ሽልማት" የተሰኘ ርዕስ የተሰጠው የሙዚቃ አልበም አስር የሙዚቃ ስራዎችን በውስጡ ይዟል።

📌 ከEventAddis/ሁነት አዲስ ምስጋና አለን!
ለቤተሰቦቻችን የላቀ ምስጋና !
ዛሬ በሚጠናቀቀው 2016 ዓ.ም በ"Event Addis/ሁነት አዲስ" ቤተሰብነት አብራችሁን ለዘለቃችሁ ምስጋናችን የላቀ ነው።
በዚህ ዓመት እጥር ምጥን ያሉ አስተማማኝና ፈጣን የኪነጥበብ መረጃዎች ምንጭ ስለሆንን በጣም ደስ ብሎናል።በተለያዩ መንገድ ሀሳቦቻችሁን( አስተያየቶች ) ስለነገራችሁን ከልብ አመስጋኞች ነን።
ከቴሌቪዥን እስከ ሬድዮ ከጋዜጣ እስከ ማህበራዊ ትስስር ገፆች የምትገኙ ሚዲያዎች በኩነትም በኪነትም በኩል ያሉ ትኩስ መረጃዎቻችንን ስለመርጧችሁልን በየጣቢያዎቻችሁ በስፋት ስላሰራጫቹሁልን ከልብ እናመሰግናለን !!።
እዚህ ጋር ደግሞ የምስራች አለን !
በዚህ ዓመት የድረገፅ አገልግሎታችን በይፋ ተጀምሯል ደግሞም በ2017 አዲስ ዓመት በሬድዮ፣ በዩቲዩብ፣ ቲክቶክን ጨምሮ በአዳዲስ የሚዲያ አማራጮች ወደእናንተ መድረስ እንጀምራለን። ያድረሰን እንኑር ያኑርን።
ለሁላችሁም መልካም አዲስ ዓመት ይሁንላችሁ !
ለአስተያየት: @Tmanaye
ቴሌግራም: https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
Website: https://eventaddis.com
Facebook:https://www.facebook.com/profile.php?id=100083170462851
FB Group:https://facebook.com/groups/2009372275938661/

📌 የ2016 ፊልሞች ዝርዝር
ዛሬ በሚጠናቀቀው 2016 ዓ.ም በርካታ ሀገርኛ ፊልሞች ለእይታ በቅተዋል።
በተለይ በዚህኛው ዓመት ከተለመደው የ"ሮማንስ ኮሜዲ" ፊልሞች ይልቅ በድርጊት የተሞሉ ፊልሞች በብዛት የቀረቡበት ዓመት እንደሆነ ኤቨንት ድረገፅ ያነጋገራቸው የፊልም ባለሞያዎች ይናገራሉ።
በ2016 ዓ.ም ለእይታ ከበቁ ፊልሞች ውስጥ ኤቨንት አዲስ ድረገፅ እነዚህን ሃያ ፊልሞች ለማስታወስ ያህል አቅርቧል።
1. ጥቁር አደይ: የፍፁም ካሣሁን ፊልም
2.6:00 ሠዓት ከሌሊቱ:የበኃይሉ እንግዳ ፊልም
3. ጃናሞራ : የያለው ደስታ (ራስ) ፊልም
4. ትዝታ : የዳንኤል አንማው ፊልም
5. አፊኒ: የታሪኩ መኮንን ፊልም
6.ማለዳ: የሳሙኤል ካሣሁን ፊልም
7.ባለቀ ሠዓት: የተሻለ ወርቁ ፊልም
8. እጅም አንሰጥም : የረዲ በረካ ፊልም
9.ባለ ክራር:የባዩሽ ልጅ(ሳሚ) ፊልም
10. ዜሮ ድግሪ: የአልዓዛር ሳለልኝ ፊልም
11. አል-ሞቷል: የፍፁም ክብረት ፊልም
12: ህጋዊ ድሃ: የወንድምአገኘ ለማ ፊልም
13.ጀስቲሺያ : የቅድስት ይልማ ፊልም
14. አልነጋም :የብዙአየሁ አደነ ፊልም
15. ቀይ መስመር : የኮኮብ ብርሃኔ ፊልም
17. ረብራ: የበላይ ፀጋዬ ፊልም
18. ሁለት ቅጣት: የመዝሙር ዳዊት ፊልም
19. ካሲናዬ: የብርሃኑ ወርቁ ፊልም
20.ሁለት ዓይነት: የአመሐ ዱጉማ ፀሐይ ፊልም

📌የሮፍናን ኑሪ "ፔሌ" ሙዚቃ ቪዲዮ ተለቀቀ
የሮፍናን ኑሪ ዘጠኝ የሙዚቃ አልበም ውስጥ ከተካተቱ የሙዚቃ ስራዎች "ፔሌ" ለተሰኘው ሙዚቃ የተሰራው የሙዚቃ ቪዲዮ በሙዚቀኛው የዩቲዩብ ቻናል እንደተለቀቀ ኤቨንት አዲስ ተመልክቷል።
የሙዚቃ ቪዲዮው በኪሩቤል ጥበቡ ዳይሬክት የተደረገ ሲሆን የሙዚቃው ግጥምና ዜማ እንዲሁም ቅንብር በሮፍናን ኑሪ ተሰርቷል።
ሙዚቀኛ ሮፍናን ኑሪ ስለሙዚቃ ቪዲዮው በማህበራዊ ትስስር ገፁ"የአዲስ አመት ስጦታ ይሁን" ብሏል።
ለተጨማሪው:https://news.1rj.ru/str/EventAddis1

📌"ፍቅር እስከ መቃብር" ድራማ ተለቀቀ
የደራሲ ሀዲስ አለማየሁ ዘመን አይሽሬ መጽሐፍ የሆነው"ፍቅር እስከ መቃብር" መጽሐፍ ወደ ተከታታይ የቴሌቪዥን ድራማ ተቀይሮ ዛሬ መስከረም 1 2017 ዓ.ም በቴለቪዥን መታየት የሚጀምር ሲሆን አስቀድሞ ትላንት ሌሊት በኢቢሲ ይፋዊ የዩቲዩብ ቻናል ተለቋል።
ተከታታይ ድራማው ከዩቲዩብ በተጨማሪም ዛሬ
በኢቢሲ ዜና ቻናል ከቀኑ 8፡00 ሰዓት እና በመዝናኛ ቻናል ደግሞ ከቀኑ 11፡30 ጀምሮ ይተላለፋል፡፡ እንዲሁም በድጋሚ ምሽት ከዜና በኋላ በሁለቱም ቻናሎች እንደሚተላለፍ ኤቨንት አዲስ ድረገጽ ከጣቢያው ያገኘው መረጃ ያመለክታል።
"የፍቅር እስከ መቃብር" የልብ ወለድ መጽሐፍን ‘ሰው መሆን ፊልም ፕሮዳክሽን’ ወደ ተከታታይ የቴሌቪዥን ድራማ በመቀየር በአራት ምዕራፍ፣ በ48 ክፍሎችና በአማካይ 45 ደቂቃ ርዝማኔ እንዲኖረው ሆኖ እንዲሰራ ስምምነት ከኢቢሲ ማድረጋቸው አይዘነጋም።
በተጨማሪም ውሉ ላይ ‘ሰው መሆን ፊልም ፕሮዳክሽን’ በአምስት ወራት ጊዜ ውስጥ የድራማውን የመጀመሪያ ምዕራፍ ማለትም (ከክፍል1-12) የተጠናቀቁ ሥራዎችን እንዲሁም በቀጣይ ዘጠኝ ወራት ውስጥ ሙሉ ለሙሉ (48 ክፍሎች) አጠናቅቆ ለማስረከብ ከኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን ጋር ስምምነት ላይ መድረሳቸው ይታወሳል።
ለተጨማሪው:https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
የደራሲ ሀዲስ አለማየሁ ዘመን አይሽሬ መጽሐፍ የሆነው"ፍቅር እስከ መቃብር" መጽሐፍ ወደ ተከታታይ የቴሌቪዥን ድራማ ተቀይሮ ዛሬ መስከረም 1 2017 ዓ.ም በቴለቪዥን መታየት የሚጀምር ሲሆን አስቀድሞ ትላንት ሌሊት በኢቢሲ ይፋዊ የዩቲዩብ ቻናል ተለቋል።
ተከታታይ ድራማው ከዩቲዩብ በተጨማሪም ዛሬ
በኢቢሲ ዜና ቻናል ከቀኑ 8፡00 ሰዓት እና በመዝናኛ ቻናል ደግሞ ከቀኑ 11፡30 ጀምሮ ይተላለፋል፡፡ እንዲሁም በድጋሚ ምሽት ከዜና በኋላ በሁለቱም ቻናሎች እንደሚተላለፍ ኤቨንት አዲስ ድረገጽ ከጣቢያው ያገኘው መረጃ ያመለክታል።
"የፍቅር እስከ መቃብር" የልብ ወለድ መጽሐፍን ‘ሰው መሆን ፊልም ፕሮዳክሽን’ ወደ ተከታታይ የቴሌቪዥን ድራማ በመቀየር በአራት ምዕራፍ፣ በ48 ክፍሎችና በአማካይ 45 ደቂቃ ርዝማኔ እንዲኖረው ሆኖ እንዲሰራ ስምምነት ከኢቢሲ ማድረጋቸው አይዘነጋም።
በተጨማሪም ውሉ ላይ ‘ሰው መሆን ፊልም ፕሮዳክሽን’ በአምስት ወራት ጊዜ ውስጥ የድራማውን የመጀመሪያ ምዕራፍ ማለትም (ከክፍል1-12) የተጠናቀቁ ሥራዎችን እንዲሁም በቀጣይ ዘጠኝ ወራት ውስጥ ሙሉ ለሙሉ (48 ክፍሎች) አጠናቅቆ ለማስረከብ ከኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን ጋር ስምምነት ላይ መድረሳቸው ይታወሳል።
ለተጨማሪው:https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
📌በእረፍት ቀንዎ ቴአትር ይመለከቱ !
አንጋፋው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር እና የቦሌው ዓለም ሲኒማ አርብ፣ ቅዳሜ እና እሁድ እነዚህን ተውኔቶች ለታዳሚያን ያቀርባሉ።
📍 የፍቅር ካቴና
ድርሰትና ዝግጅት: አለልኝ መኳንት ፅጌ
ቀን: አርብ
ሰዓት: 12:00
ቦታ: ዓለም ሲኒማ
📍 "እሳት ወይ አበባ"
ድርሰት: ሎሬት ፀጋዬ ገብረመድህን እንደጻፈው
ዳንስና ዳንስ ቅንብር: ሽፈራው ታሪኩ ቢረጋ
ቀን: አርብ
ሰዓት:11:30
ቦታ: ብሔራዊ ቴአትር
📍 ባሎች እና ሚስቶች
ድርሰት: ውዱ አለን
አዘጋጅ: ሳሙኤል ተስፋዬ
ቀን: ቅዳሜ
ሰዓት: 8:00
ቦታ: ብሔራዊ ቴአትር
📍 ባቡሩ
ድርሰት: አርኖልድ ሪድሊ
አዘጋጅ:ራሔል ተሾመ መሐመድ
ቀን: ቅዳሜ
ሰዓት:11:30
ቦታ: ብሔራዊ ቴአትር
📍 ሸምጋይ
ድርሰት:ታደለ አያሌው
አዘጋጅ: ሳሙኤል ተስፋዬ
ቀን: እሁድ
ሰዓት: 8:00
ቦታ: ብሔራዊ ቴአትር
📍 እምዩ ብረቷ
ድርሰት: ቤልቶልት ብሬሽት
አዘጋጅ: ማንያዘዋል እንዳሻው
ቀን: እሁድ
ሰዓት:11:30
ቦታ: ብሔራዊ ቴአትር
የእናንተው ኤቨንት አዲስ ድረገፅ መልካም የእረፍት ቀን ይሁንላችሁ ይላል !
ለተጨማሪው: https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
አንጋፋው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር እና የቦሌው ዓለም ሲኒማ አርብ፣ ቅዳሜ እና እሁድ እነዚህን ተውኔቶች ለታዳሚያን ያቀርባሉ።
📍 የፍቅር ካቴና
ድርሰትና ዝግጅት: አለልኝ መኳንት ፅጌ
ቀን: አርብ
ሰዓት: 12:00
ቦታ: ዓለም ሲኒማ
📍 "እሳት ወይ አበባ"
ድርሰት: ሎሬት ፀጋዬ ገብረመድህን እንደጻፈው
ዳንስና ዳንስ ቅንብር: ሽፈራው ታሪኩ ቢረጋ
ቀን: አርብ
ሰዓት:11:30
ቦታ: ብሔራዊ ቴአትር
📍 ባሎች እና ሚስቶች
ድርሰት: ውዱ አለን
አዘጋጅ: ሳሙኤል ተስፋዬ
ቀን: ቅዳሜ
ሰዓት: 8:00
ቦታ: ብሔራዊ ቴአትር
📍 ባቡሩ
ድርሰት: አርኖልድ ሪድሊ
አዘጋጅ:ራሔል ተሾመ መሐመድ
ቀን: ቅዳሜ
ሰዓት:11:30
ቦታ: ብሔራዊ ቴአትር
📍 ሸምጋይ
ድርሰት:ታደለ አያሌው
አዘጋጅ: ሳሙኤል ተስፋዬ
ቀን: እሁድ
ሰዓት: 8:00
ቦታ: ብሔራዊ ቴአትር
📍 እምዩ ብረቷ
ድርሰት: ቤልቶልት ብሬሽት
አዘጋጅ: ማንያዘዋል እንዳሻው
ቀን: እሁድ
ሰዓት:11:30
ቦታ: ብሔራዊ ቴአትር
የእናንተው ኤቨንት አዲስ ድረገፅ መልካም የእረፍት ቀን ይሁንላችሁ ይላል !
ለተጨማሪው: https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
📌“አቴቴ አያና ሐዎታ” ዘጋቢ ፊልም ሊመረቅ ነው
በኑቢያ ፊልም ፕሮዳክሽን የተዘጋጀው “አቴቴ አያና ሐዎታ” የተሰኘ የእናቶች(አቴቴ)ዘጋቢ ፊልም መስከረም 8 ቀን 2017 ዓ.ም በሸራተን አዲስ ሆቴል ይመረቃል።
ዘጋቢ ፊልሙ በገዳ ሥርዓት እና በኦሮሞ ማህበረሰብ ውስጥ ሴቶች ሚና ያላቸውን ልዩ ወጎች፣ ፍልስፍናዎች እና ታሪካዊ ፋይዳዎች በጥልቀት ያሳያል የተባለ ሲሆን የሲንቄን ሥርአትና የልጃገረዶች ወዮማ ሥርአትን የሚያብራራና የሚገልጽ እንደሆነም ተገልጿል።
ዘጋቢ ፊልሙ መስራት ሁለት ዓመት የወሰደ ሲሆን በፊልሙ ላይም በኦሮሞ ታሪክ ከፍተኛ ምርምርና ጥናቶችን ያደረጉ ምሁራን የተሳተፉበት ሲሆን ስራው ዓለማቀፋዊ እንዲሆን በጥራት የተሰራ ነው ተብሏል።
ይህ በዓይነቱ ልዩ የሆነ የእናቶች (አቴቴ) ዘጋቢ ፊልም ታሪኩን ከማስተዋወቅ ባለፈ በገዳ ሥርዓት ውስጥ ሴቶች እና እናቶች ያላቸውን ልዩ ስፍራ አጉልቶ የሚያሳይ እንደሆነ ተነግሯል።
በኑቢያ ፊልም ፕሮዳክሽን የቀረበ ዘጋቢ ፊልሙ በሮብሰን ዋቤ ፕሮዲዩሰር እና ዳይሬክተርነት የተሰራ እንደሆነ ተገልጿል።
በአጠቃላይ ይህንን ዶክሜንተሪ ሰርቶ ለመጨረስ አራት ሚሊዮን ብር ፈጅቷል ተብሏል።
የዘጋቢ ፊልሙ ጥሪ የተደረገላቸው የክብር እንግዶች፣ ታዋቂ አርቲስቶች፣ አባ ገዳዎች፣ የሲንቄ እናቶች፣ የኦሮሞ ስራ ፈጣሪዎች እና ሌሎችም እንግዶች በተገኙበት የፊታችን መስከረም 8 ቀን 2017 ዓ.ም ከቀኑ 9 ሰዓት በሸራተን አዲስ ሆቴል ይመረቃል።

📌የድምፃዊ ንዋይ ደበበ እና የአይዳ ሐሰን ወንድ ልጅ የሆነው ሰላም ንዋይ ከዚህ ዓለም በሞት ተለይቷል።
በጋብቻ ተሳስረው አሜሪካን አገር ለረጅም አመት የኖሩት ንዋይ ደበበና አይዳ ሀሰን ከቅርብ ዓመታት በፊት በይፋ መለያየታቸውን ቢገልፁም እንደቤተሰብ ብዙም አልተራራቁም።
በትዳር ሕይወታቸው ፅናት ንዋይ የተባለች ሴት ልጅና ሰላም ነዋይ የተባለ ወንድ ልጅ በጋራ ያፈሩት ንዋይና አይዳ ልጆቻቸውን ያሳደጉት ቨርጂንያ ውስጥ ሲሆን፣ ሰላም ከጊዜ በኋላ በገጠመው የጤናእክል የተነሳ ሕክምና ሲከታተል ቆይቷል።
በተለይ የኩላሊት ኢንፌክሽን ተጠቂ በነበረበት ሰዓት አንድ ኩላሊት እናቱ አይዳ ሰጥታው ንቅለ ተከላ ማድረጉ ይታወሳል።
ከልጅነቱ ጀምሮ ተጨዋች፣ ሳቂታ እና ቀልድ የሚወድ ተወዳጅ ልጅ ነበር ትምህርቱን ተከታትሎ ያጠናቀቀው እዚያው አሜሪካን አገር ሲሆን፣ ሲበዛ አዛኝ ልብ የነበረውና ሰዎችን መርዳት የሚያስደስተው ሰላም ከዚህ ዓለም በሞት ተለይቷል።
ንዋይ ደበበ ዛሬ ማታ ወደ አሜሪካን ይጓዛል ተብሏል።
©️መረጃው የሁሉአዲስ ነው

🙏1
📌"ፍቅር እስከ መቃብር" ድራማ በቅርብ ቀን በመደበኛው ስርጭት በኢቲቪ መዝናኛ መተላለፍ ይጀምራል ተብሏል።
በቀናት ልዩነት በተከታታይ እስከ ክፍል አራት ድረስ ሲተላለፍ የቆየው "ፍቅር እስከ መቃብር" ተከታታይ የቴሌቪዥን ድራማ በቅርብ ቀን በመደበኛው ስርጭት በዋናነት በኢቲቪ መዝናኛ ቻናል መተላለፍ እንደሚጀምር ኤቨንት አዲስ ድረገፅ ከጣቢያው ያገኘው መረጃ ያመለክታል።
ቴሌቪዥን ጣቢያው የሚከተለውን ብሏል"የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን የተመልካቹን ፍላጎት ለማርካት የትዝታችንን ምልክት የንባብ ልምምዳችን በኩር የስነጽሑፍ ሥራዎች ቁንጮ የሆውን የክቡር ዶ/ር ሀዲስ አለማየሁ ታላቁን የፈጠራ ሥራ ‹‹ ፍቅር እስከ መቃብር ›› መፅሐፍን ዓለም አቀፍ ደረጃውን ጠብቆ ወደ ፊልም በመቀየር እንድትመለከቱት የአዲስ ዓመት ስጦታ በማድረግ አበርክቷል።
ይኸም ስጦታ ከመስከረም 1-5 2017 ዓ.ም የፊልሙን አራት ክፍሎች በETV ዜና ቻናል፣ በETV መዝናኛ ቻናል ፣ በEBC World የYOU TUBE ገፅ እና በፌስ ቡክ ቲክቶክ እና ኹሉም ማህበራዊ ሚዲያ ገጾች ለክቡራን ተመልካቾቻቸን ቀርቧል።
በቀጣይም ከጥቂት ቀናት በኋላ የ‹‹ፍቅር እስከ መቃብር›› ፊልም ሁሉም ክፍሎች በዋናነት በETV መዝናኛ ቻናል መተላለፍ ይጀምራሉ።
የፍቅር እስከመቃብርን ትረካ በኢትዮጵያ ራድዮ በወጋየሁ ንጋቱ ተከታትላችሁ ትዝታ የተጋራችሁ አድማጮቻችን ታላቁ ስራ በታላቅ የፊልም ጥበብ ተገልጦ በመደበኛነት እንድትከታተሉን የዘመን ትዝታም እንድትጋሩ በታላቅ አክብሮት እንጋብዛችኋለን "።