Event Addis Media – Telegram
Event Addis Media
9.62K subscribers
6.12K photos
14 videos
4 files
4.74K links
Connect with Addis artistic community!

Website: https://eventaddis.com

Contact: @Tmanaye
Download Telegram
📌የድምጻዊ ማዲንጎ አፈወርቅ ሁለተኛ ዓመት የመታሰቢያ መርሐግብር ተከናወነ !

ከሁለት ዓመት በፊት መስከረም 17 2015 ዓ.ም በሞት የተለየን ተወዳጁ ድምፃዊ ማዲንጎ አፈወርቅ ሁለተኛ ዓመት መርሐግብር ዛሬ መስከረም 16 2017 ዓ.ም ተካሄዷል።

የህልፈቱን ሁለተኛ ዓመት ምክንያት በማድረግም ቤተሰቦቹ የሞያ አጋሮቹ እና አድናቂዎቹ በተገኙበትም የመታሰቢያ ዝግጅቱ በቅድስት ስላሴ ካቴደራል ተከናውናል።

ድምጻዊ ማዲንጎ አፈወርቅ በህይወት እያለ የሰራቸው የተጠናቀቁና እና በጅምር ላይ የነበሩ የማዲንጎ ሙዚቃዎችም አስፈላጊው ማስተካከያ ተደርጎላቸው ለህዝብ እንደሚቀርቡም ከተነገረ አንድ ዓመት ተቆጥሯል።

ድምጻዊ ማዲንጎ ሶስት የሙዚቃ አልበሞችን አበርክቷል "ስያሜ አጣሁላት" ፣ "አይደረግም" እና "ስወድላት" የአልበሞቹ ርዕሶች ናቸው ።

ለተጨማሪው:https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
📌የሳሌሚያ "ዓለም ብሬ" ሙዚቃ ተለቀቀ

በወጣቷ ድምጻዊት ሳሌሚያ በተለየ የሙዚቃ ቅርጽ የተሰራው "ዓለም ብሬ" የተሰኘ የሙዚቃ ከሰሞኑ በድምጻዊት "SALEMIA" የዩቲዩብ ቻናል በኩል ተለቋል።

የሳሌሚያ "አለም ብሬ" ሙዚቃ በእንግሊዘኛና አማርኛ የሰራችው የሙዚቃ ስራ ነው።

ለሙዚቃው የሙዚቃ ቪዲዮ የተሰርለት ሲሆን ዮናታን መስፍን ዳይሬክት አድርጎታል።

ለተጨማሪው:https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
📌"የፍቅር ካቴና" ዛሬ በልዩ ፕሮግራም ይቀርባል!

"የፍቅር ካቴና" የተሰኘ ተውኔት ዛሬ መስከረም 17 2017 ዓ.ም በልዩ ዝግጅት ከምሽቱ 12:00 ጀምሮ ቦሌ በሚገኘው ዓለም ሲኒማ ውስጥ ይቀርባል።

በአርቲስት ወይንሸት አበጀ ፕሮዲዩስ የተደረገው ይህ "የፍቅር ካቴና" ተውኔት ድርሰትና ዝግጅቱ የአለልኝ መኳንንት ፅጌ ነው።በተውኔቱ ድርብወርቅ ሰይፉ ፣ሚኪ ተስፋዬ ፣ ወይንሸት አበጀ ፣አሸናፊ ማህሌት በተዋናይነት ተሳትፈውበታል።

ለተጨማሪው:https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
📌"ሹቢቲ" የተሰኘ ነጠላ ሙዚቃ በቅርቡ ይለቀቃል

ድምጻዊ አደም መሐመድ ከድምፃዊት ሀሊማ አብደላ ጋር በጋራ ያቀነቀኑትና የ2017 ኢሬቻን በዓል በማስመልከት የጉጂ ባህልን የሚያሳይ "ሹቢቱ" የተሰኘ ነጠላ ዘፈን ለህዝብ ጆሮ ለማድረስ ዝግጅታቸውን ማጠናቀቃቸውን ገልጸዋል።

ይህን የሙዚቃ ቪዲዮ ለማሰናዳት ከ50 በላይ ባለሞያዎች የተሳተፉበት ሲሆን ለሙዚቃው ቪዲዮ ከ1.8 ሚሊዮን ብር በላይ እንደወጣበት ተነግሯል።

በቅንብር እና ማስተሪግ ብርሀን ዘሪሁን እና አብርሐም ኪዳኔ በማስተሪንግ እና ሚክሲንግ እንደተሳተፉበት ታውቋል።

የሙዚቃ ቪዲዮውን ዳሬክት በማድረግ አርቲስት ፋንታ ስንታየሁ እንደተሳተፍ ተገልጿል። ቀረፃውን Ya'a entertainment አከናውኖታል።

ድምጻዊ አደም መሐመድ ቅርቡ"ኦሮሚያ" የተሰኘ የአልበም ስራውን መልቀቁ ይታወሳል።

ለተጨማሪው:https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
📌በድምጻዊ ቴዎድሮስ ታደሰ ህልፈት ዙርያ እየተሰራጨ ያለው መረጃ የተሳሳተ ነው !

'Yehabesha' የተባለው እና ከ1.9 ሚልዮን በላይ የፌስቡክ ተከታዮች ያሉት ገፅን ጨምሮ በርካታ የማህበራዊ ሚድያ ተጠቃሚዎች ታዋቂው ድምፃዊ ቴዎድሮስ ታደሰ ህይወቱ እንዳለፈ መስከረም 19 2017 ዓ.ም መረጃ ሲያጋሩ ውለዋል።

እነዚህ ፅሁፎች ምንም አይነት ምንጭ ሳይጠቀስባቸው ለህዝብ የተጋሩ ሲሆን በርካታ ሰዎችም መልሰው ሲያጋሩት (ሼር ሲያደርጉት ተመልክተናል)፣ በርካታ የኢትዮጵያ ቼክ ተከታታዮችም ፅሁፉን እንድናጣራ ጥያቄ አቅርበዋል።

የመረጃ ማጣርያ ዴስካችን በዚህ ዙርያ አንድ የአርቲስቱ ጓደኛን እና አንድ የቅርብ ቤተሰብን ያነጋገረ ሲሆን በማህበራዊ ሚድያ የተሰራጨው መረጃ ሀሰተኛ መሆኑን ተናገረዋል።

"እኛም ከመሸ አይተነው ነበር፣ በርካታ ሰው ተደናግጦ ሲደውል ነበር፣ ወሬው ግን ውሸት ነው። ከእንዲህ አይነት በሬ ወለደ ፅሁፍ ምን እንደሚጠቀሙ አይገባኝም" ብለው ምላሽ የሰጡን ምንጫችን ይህ በአርቲስቱ ዙርያ ሲወራ ለሶስተኛ ግዜ መሆኑን ጠቅሰዋል።

ማህበራዊ ሚድያ ላይ የሚሰራጩ መረጃዎችን ትክክለኛነት ሳናጣራ፣ የምናምናቸው ምንጮች ሳይዘግቡት እንዲሁም ማስረጃዎችን ሳንመለከት ባለማመን እና መልሰን ለሌሎች ባለማጋራት የሀሰተኛ መረጃ ስርጭትን እንከላከል።

©️Via ኢትዮጵያ ቼክ

ለተጨማሪው:https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
📌"እርቅ ከእራስ" ውይይት ቅዳሜ ይካሄዳል

በተከታታይ እየቀረበ የሚገኘው "እርቅ ከእራስ" የውይይት  ዝግጅት "ትውልድ ለማነጽ" በሚል ርዕስ የፊታችን ቅዳሜ መስከረም 25 2017 ዓ.ም ከቀኑ 10:30 ጀምሮ ካዛንቺስ በሚገኘው ትራቩል ኢትዮጵያ ቢሮ ውስጥ ይካሄዳል።በዕለቱም ፕ/ር አህመድ ዘካሪያ፣ኢ/ር ቪጃይ ናይከር፣ሜላት ንጉሴ እና ሌሎችም ሀሳቦቻቸውን ያጋራሉ ተብሏል።

ለተጨማሪው:https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
📌"ልውጠ ቀርጽ" የሥዕል አውደርዕይ ለእይታ በቃ

የሠዓሊ ዳሪዎስ ኃ/ሚካኤል የሥዕል ስራዎች የቀረቡበት "ልውጠ ቀርጽ" የሥዕል አውደርዕይ ባሳለፍነው ሰኞ መስከረም 20 2017 ዓ.ም ጀምሮ ካዛንቺስ በሚገኘው ፈንድቃ የባህል ማዕከል ውስጥ ለእይታ በቅቷል።

ይህ የሥዕል አወድርዕይ እስከ ጥቅምት 4  2017 ዓ.ም ድረስ ይቆያል ተብሏል።

ለተጨማሪው:https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
📌የአባ ገብረ ኪዳን ግርማ መጽሐፍ ምረቃ

የርዕሰ ሊቃውንት የኔታ አባ ገብረ ኪዳን ግርማ "አሐቲ ድንግል" የተሰኘ መጽሐፋቸው ቅዳሜ ጥቅምት 2 ቀን 2017 ዓ.ም ከቀኑ 7:30 ጀምሮ በቦሌ መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን ይመረቃል።

ለተጨማሪው:https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
📌"የፍቅር እስሰ መቃብር ሲኒማቶግራፊ"

አላቲኖስ ኢትዮጵያዊ ፊልም ሰሪዎች ማሕበር ፒያሳ በሚገኘው የሩሲያ ሳይንስና ባህል ማዕከል (ፑሽኪን) አዳራሽ ውስጥ በሚያዘጋጀው የፊልም ውይይት መርሐግብር ዛሬ ሐሙስ መስከረም 23 ቀን 2017 ዓ.ም ከቀኑ 10:30 ጀምሮ" የፍቅር እስከ መቃብር ሲኒማቶግራፊ"በሚል ርዕስ ውይይት ያካሄዳል።በዕለቱም የክብር እንግዳ በመሆን የፊልም ባለሞያው ፍስሃፅዮን ንብረት  ይገኛል ተብሏል።

ለተጨማሪው:https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
📌በእረፍት ቀንዎ ቴአትር ይመለከቱ !

አንጋፋው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር  እና የቦሌው ዓለም ሲኒማ አርብ፣ ቅዳሜ እና እሁድ እነዚህን ተውኔቶች ለታዳሚያን ያቀርባሉ።

📍 ጎዶ'ን ጥበቃ

ድርሰት: ሳሙኤል ቤኬት
ትርጉም: ሀይከል ሙባረክ
አዘጋጅ: ዳግም ሲሳይ
ቀን: ሐሙስ
ሰዓት:11:30
ቦታ: ብሔራዊ ቴአትር


📍 የፍቅር ካቴና

ድርሰትና ዝግጅት: አለልኝ መኳንት ፅጌ
ቀን: አርብ
ሰዓት: 12:00
ቦታ: ዓለም ሲኒማ

📍 "እሳት ወይ አበባ"

ድርሰት: ሎሬት ፀጋዬ ገብረመድህን እንደጻፈው
ዳንስና ዳንስ ቅንብር: ሽፈራው ታሪኩ ቢረጋ
ቀን: አርብ
ሰዓት:11:30
ቦታ: ብሔራዊ ቴአትር

📍 ባሎች እና ሚስቶች

ድርሰት: ውዱ አለን
አዘጋጅ: ሳሙኤል ተስፋዬ
ቀን: ቅዳሜ
ሰዓት: 8:00
ቦታ: ብሔራዊ ቴአትር

📍 ባቡሩ

ድርሰት: አርኖልድ ሪድሊ
አዘጋጅ:ራሔል ተሾመ መሐመድ
ቀን: ቅዳሜ
ሰዓት:11:30
ቦታ: ብሔራዊ ቴአትር

📍 ሸምጋይ

ድርሰት:ታደለ አያሌው
አዘጋጅ: ሳሙኤል ተስፋዬ
ቀን: እሁድ
ሰዓት: 8:00
ቦታ: ብሔራዊ ቴአትር

📍 እምዩ ብረቷ

ድርሰት: ቤልቶልት ብሬሽት
አዘጋጅ: ማንያዘዋል እንዳሻው
ቀን: እሁድ
ሰዓት:11:30
ቦታ: ብሔራዊ ቴአትር

የእናንተው ኤቨንት አዲስ ድረገፅ መልካም የእረፍት ቀን ይሁንላችሁ ይላል !

ለተጨማሪው: https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
📌ዝክረ- ኤልያስ መልካ አምስተኛ ዓመት !

ተወዳጁ የሙዚቃ አቀናባሪ ኤልያስ መልካ ካረፈ ነገ አርብ መስከረም 24 2017 ዓ.ም አምስት ዓመት ይሞላዋል።

በኤልያስ መልካ አድናቂዎች ህብረት የተዘጋጁ እና የኤልያስ መልካን አምስተኛ ዓመት የሚዘክሩ መርሐግብሮች በቀጣይ ቀናት ይካሄዳሉ።

ከነዚህም የመታሰቢያ መርሐግብሮች ውስጥ ነገ ከጠዋቱ 3:30 ጀምሮ በጴጥሮስ ወጳውሎስ ቤተክርስቲያን በኤልያስ መልካ አድናቂዎች የአበባ ጉንጉን የማኖር ሥነሥርዓት ይከናወናል ።

መምጣት የሚፈልግ ሁሉ በቦታው መገኘት ይችላል ቦታው ዊንጌት አካባቢ ጴጥሮስ ወጳውሎስ ቤተክርስቲያን ነው ።

ለተጨማሪው: https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
📌 "ኢሬቻ ኮንሰርት" ዛሬ በአዲስአበባ ይካሄዳል

በኑማ ኤቨንት እና ፕሮሞሽን የተዘጋጀው "ኢሬቻ ኮንሰርት" ዛሬ አርብ መስከረም 24 ቀን 2017 ዓ.ም በአዲስ አበባ ሚሊኒየም አዳራሽ ይካሄዳል ተብሏል።

በዚህ ኮንሰርት ላይ ሐመልማል አባተ፣ ቀመር የሱፍ ፣ታደለ ገመቹ፣ ጌታቸው ኃ/ማርያም፣ አንዱዓለም ጎሳ እና ሌሎችም ስራዎቻቸውን ያቀርባሉ።

ለተጨማሪው:https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
📌በቅርቡ "የህይወት ታሪክ" አዲስ ተውኔት !

ሰዎች ሲሞቱ ደግ፣ ብርቱ፣ ቅን ይባላሉ። ይህ የሆነው ሙት አይወቀስም ስለሚባል ይሆን? ሙት ቢወቀስ ምን ይፈጠራል?በሞታችሁ ቀን የሕይወት ታሪካችሁን የሚፅፈው ማነው? የሚያነበውስ ማን ይሆን? በሕይወት ታሪካችሁ የትኛው ታሪካችሁ ነው የሚፃፈው? የተለመደው ቢለወጥ ምን ይከሰታል? የፍቅር ልኩ ምን ድረስ ነው? በሸገር ራዲዮ ቀርቦ አድናቆትን አትርፎ የነበረ ተውኔት ወደ ህያው መድረክ መጥቷል።

ድርሰትና ዝግጅት: ነብዩ ባዬ እና ቢንያም ወርቁ

ትወና: ቢንያም ወርቁ እና ፀደይ ፋንታሁን

በቅርቡ ለመድረክ ይበቃል ተብሏል።

ለተጨማሪው:https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
📌"የንባብ ባህል ለትምህርት ጥራት"

የኢትዮጰያ ቤተ መዛግብትና ቤተ መጻህፍት አገልግሎት ከዛሬ  መስከረም 24 2017 ዓ.ም ጀምሮ "የንባብ ባህል ለትምህርት ጥራት" በሚል መሪ ቃል ከጌዲዮ ዞን ትምህርት መምሪያና ከዲላ ዩንቨርስቲ ጋር በመተባበር በዲላ እና ይርጋጨፌ ከተሞች የተዘጋጀ የንባብ ሳምንት፣ ቡክፌር፣ ኤግዚቢሽን እና የፓናል ውይይት ይካሄዳል።

ለተጨማሪው:https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
📌በ"ምን ሆኛለሁ?" መጽሐፍ ላይ በሐዋሳና ሻሸመኔ ከተሞች የፊታችን ቅዳሜና እሁድ ውይይት ይካሄዳል

በ" ምን ሆኛለሁ ?" መጻሕፍ ላይ ሀዋሳ በሚገኘው ቦናፋይድ ት/ቤት ቅዳሜ መስከረም 25 ቀን 2017 ዓ. ም ከቀኑ 8፡ 00 ጀምሮ ውይይት ይካሄዳል።

"ምን ሆኛለሁ ?" ን መነሻ በማድረግ በልጆች አስተዳደግና ስብዕና ግኘንባታ ፣ ስለ ወላጅነት ፣ ስለ ማንነታችን ፣ ልጆች ከወላጆች ስለሚጠብቁትና የወላጆች የወላጅነት ሚና ዙሪያ ላይ ውይይት ይደረጋል።

በውይይቱ ላይ የስነልቦና ባለሙያዋ ትግስት ዋልተንጉስ እና ደራሲና ጋዜጠኛ ቴዎድሮስ ተ\አረጋይ ይገኛሉ። መጻሕፍ የማስፈረም መርሐ ግብር ይካሄዳል።

በሌላ በኩል በ" ምን ሆኛለሁ ? " መጻሕፍ ላይ ሻሸመኔ በሚገኘው ታንስቶሲና ሆቴል አዳራሽ እሁድ መስከረም 26 ቀን 2017 ዓ. ም ከጠዋቱ 3፡00 ጀምሮ የአጋፔ የትምህርት ማዕከል ቤተሰቦች በተገኙበት ውይይት ይካሄዳል።

"ምን ሆኛለሁ ? " ን መነሻ በማድረግ በልጆች አስተዳደግና ስብዕና ግኘንባታ ፣ ስለ ወላጅነት ፣ ስለ ማንነታችን ፣ ልጆች ከወላጆች ስለሚጠብቁትና የወላጆች የወላጅነት ሚና ዙሪያ ላይ ውይይት ይደረጋ።

በውይይቱ ላይ የስነልቦና ባለሙያዋ ትግስት ዋልተንጉስ እና ደራሲና ጋዜጠኛ ቴዎድሮስ ተ\አረጋይ ይገኛሉ። መጻሕፍ የማስፈረም መርሐ ግብር ይካሄዳል።

ለተጨማሪው:https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
📌ዝክረ- ኤልያስ መልካ አምስተኛ ዓመት!

በዚህ ሠዓት በጴጥሮስ ወጳውሎስ ቤተክርስቲያን በኤልያስ መልካ አድናቂዎች የአምስተኛ ዓመት መታሰቢያ የአበባ ጉንጉን የማኖር ሥነሥርዓት እየተከናወነ ይገኛል።

በኤልያስ መልካ አድናቂዎች ህብረት የተዘጋጁ እና የኤልያስ መልካን አምስተኛ ዓመት የሚዘክሩ መርሐግብሮች በቀጣይ ቀናት ይካሄዳሉ።

ለተጨማሪው:https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
📌የሠዓሊ ዮሐንስ ባዩ "ምስጋና"አውደርዕይ!

የ"እርሳስ ቤተጥበብ" መስራች ሠዓሊ ዮሐንስ ባዩ "ምስጋና" በሚል ርዕስ ያዘጋጀው ለየት ያለ የሥነጥበብ አውደርዕይ ከፊታችን ማክሰኞ መስከረም 28 2017 ዓ.ም ጀምሮ ይካሄዳል።

የሠዓሊ ዮሐንስ ባዩ "እርሳስ ቤተ ጥበብ / Ersas art studio / የተመሰረተበትን እና የሠዓሊውን የ10 ዓመት የሙያ ጉዞ ለማክበር የተዘጋጀ የሥዕል አውደርዕይ እና የሥዕል መጽሃፍ ምርቃት በማርዮት ሆቴል መስከረም 28 በልዩ ፕሮግራም እና ግብዣ ጥሪ ለተደረገላቸው እንግዶች እንዲሁም ከመስከረም 29 - ጥቅምት 1 2017 ለጥበብ አድናቂዎች ክፍት ይሆናል ተብሏል።

ሠዓሊ ዮሐንስ ባዩ የ"እርሳስ ቤተ ጥበብ" መስራች እና የሙሉ ጊዜ ሠዓሊ ሲሆን ላለፉት ዓመታት በሙያው በተለያዩ የሥነ ሥዕል እና የ ሞዛይክ ጥበብ ለግለሰቦች፣ለ ኤምባሲዎች፣ ለሆቴሎች፣ለመንግስት እና ለተለያዩ ተቋማት በመስራት እንዲሁም በሀገር ውስጥ እና በባህር ማዶ ሀገራት የሀገራችንን የኢትዮጵያን ስም ከፍ የሚያደርጉ ወደ 20 የሚጠጉ የሥዕል ዐውደርዕዮችን አቅርቧል።

የተለያዩ ዓለም አቀፍ ሽልማቶችን (Oscar of young African 2019) ጨምሮ በማግኘት እውቅናን ያተረፈ ወጣት ሠዓሊ ነው።

በእውነታዊ / realistic / የአሳሳል ዘይቤ የሚታወቀው ሠዓሊው ውበትን፣እምነትን፣ ምስጋናን እና ተስፋን በሥዕሎቹ አጉልቶ ያሳየናል::

ለተጨማሪው:https://news.1rj.ru/str/EventAddis1