Event Addis Media – Telegram
Event Addis Media
9.62K subscribers
6.11K photos
13 videos
4 files
4.73K links
Connect with Addis artistic community!

Website: https://eventaddis.com

Contact: @Tmanaye
Download Telegram
📌የገጣሚ ዮሐንስ ሞላ "በከንፈርሽ በራ'ፍ" መጽሐፍ በድምቀት ተመረቀ።

የገጣሚ ዮሐንስ ሞላ "በከንፈርሽ በራ'ፍ" የተሰኘ  ርዕስ የተሰጠው አዲስ  የግጥም መጽሐፍ ረቡዕ ጥቅምት 20 ቀን 2017 ዓ.ም  አራት ኪሎ በሚገኘው ዋልያ መጻሕፍት ውስጥ በርካታ ታዳሚያን በተገኙበት ተመርቋል።

በዕለቱም ግጥሞና ወጎች ተነበዋል፣ ሥነጽሑፋዊ ዳሰሳዎችና የሙዚቃ ዝግጅት ቀርቧል።

ገጣሚ ዮሐንስ ሞላ ከዚህ ቀደም "የብርሃን ልክፍት" እና "የብርሃን ሰበዞች" የተሰኙ መጻሕፍት አንባቢያን ማድረሱ አይዘነጋም።

ለተጨማሪው: https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
📌ፍቅር ኢትዮጵያ የአእምሮ እድገት ውስንነት ማህበር የተመሰረተበትን 30ኛ ዓመቱን ሊያከብር ነው

ፍቅር ኢትዮጵያ የአእምሮ እድገት ውስንነት ማህበር ሰላሰኛ አመት የምስረታ በዓሉን ለተከታታይ አስር ቀናቶች እንደሚያከብር አስታወቀ።

ከጥቅምት 25 አስከ ህዳር  5 2017 ዓ.ም ሠላሰኛ ዓመቱን በተለያዩ ዝግጅቶች የሚያከብረው ፍቅር ኢትዮጵያ የአእምሮ እድገት ውስንነት ብሄራዊ ማህበር ይህ ጊዜ አዲስ የታሪክ ምዕራፍ የምንከፍትበት ይሆናል ብሏል።

የማህበሩ ፕሬዚዳንት ምህረት ንጉሴ
በዓሉ የአእምሮ እድገት ውስንነት ላለባቸው ዜጎች ድጋፍ ለመስጠት ፣ ለመብታቸው ለመሟገት እና አካታችነትን ለመፍጠር ምን ያህል እንደተጋን እንድንገመግም ያስችለናል ብለዋል።

በሶስት አሰርት ዓመታት ውስጥ በጤና ፣ በትምህርት፣በማህበራዊ ጥበቃ እድሎችን ከማሳደግ፣ዜጎችን በራስ በመደገፍ እና ድምፃቸው እንዲሰማ በማድረግ አመርቂ ውጤት ማምጣታችን ግን እሙን ነው " ብለዋል።

ስኬታችንን ስናከብር ብዙ የሚቀሩን ስራዎች እንዳሉብንም እንገነዘባለን ሲሉም ፕሬዚዳንቷ ተናግረዋል።

የ30ኛ ዓመት የምስረታ ክበረ በዓሉ ለሁሉም ጎብኝዎች ክፍት በሆነው ከጥቅምት 25 እስከ 29 ቀን 2017 ዓ/ም በኢትዮ ኩባ ወዳጅነት ፓርክ በሚዘጋጅ ኤግዚቢሽንና የመዝናኛ ፕሮግራም ተጀምሮ ህዳር 05 ቀን 2017ዓ.ም በስካይ ላይት ሆቴል ይጠናቀቃል፡፡

ለተጨማሪው: https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
📌በሲኒማ ቤቶች የፊልም ስርቆት መከላከያ ሲስተምን ጨምሮ ከ140 በላይ ችግር ፈቺ የሆኑ ኘሮጀክቶችን ይዞ በመስራት ላይ እንደሚገኝ ኤስ አር ኢ ኢትዮጵያ አስታወቀ

ኤስ አር ኢ ኢትዮጵያን በሳይንስ እና ቴክኖሎጂ የላቀ ለማድረግ ከ140 በላይ ችግር ፈቺ የሆኑ  ኘሮጀክቶችን ይዞ በመስራት ላይ እንደሚገኝ ገለጸ።

ከአስር አመት በፊት በሀገረ አሜሪካ በዋሽንግተን ዲሲ የተመሠረተው ኤስ አር ኢ የተሰኘ መሠረቱን ሳይንስና ቴክኖሎጂ ምርምርና እውቀት ላይ አድርጎ የሰው ልጆችን ህይወት ለመቀየር በማሰብ የተመሰረተ ተቋም ሲሆን በቀጣይ አለምን በሳይንስ ቴክኖሎጂ ለመቀየር ዓላማን ይዞ እየሰራ እንደሚገኝ የድርጅቱ መስራች አቶ ሳመኤል ከፈለኝ ገልጸዋል።

ተቋሙ ከሰራቸው አበይት የፈጠራ ስራዎች መካከል በሲኒማ ቤቶች የፊልም ስርቆት መከላከያ ሲስተም ፣ ከ250 በላይ ትምህርት ቤቶች ፣ ከ10 በላይ ኮሌጆች፣ ከአስራ ስድስት በላይ ዩኒቨርሲቲዎች የአፍ ላይን ዲጂታል ላይብረሪ ማሽን ተጠቃሚ ከማድረጉም በላይ  ለጎርፍ አደጋና ለመሬት መንቀጥቀጥ የአደጋ ጊዜ ማስጠንቀቂያ ቴከኖሎጂ፣ የግለሰቦችን ማንነት እራሱ ለይቶ ለማወቅ የሚያስችል ሰው ሰራሽ አስተውሎት ( አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ) ቴከኖሎጂ እንዲሁም ከ15 በላይ ዘመናዊ ቴክኖሎጂዎችን ማበርከቱን ተቋሙ በሰጠው መግለጫ አሳውቋል።

ተቋሙ ኢትዮጵያ በከፍተኛ የውጭ ምንዛሬ ወደ ሀገር ውስጥ የሚገቡ የቴክኖሎጂ ምርቶችን ሀገር ውስጥ በማምረት ለበርካታ ወጣቶች የስራ እድል በመፍጠር በኩል ጉልህ ድርሻ ያበረከተ ሲሆን በሰው ሰራሽ አስተውሎት የሚታገዝና የሚመራ የትራፊክ መብራቶችን ፣ ባዩሜትሪክ ፣ ለቱሪስቶች መረጃ የሚሰጥ የመረጃ ማዕከል ጨምሮ በርካታ የፈጠራ ስራዎችን ሰርቷል።

ለተጨማሪው: https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
📌ሠዓሊ ወንድወሰን ከበደ  የ2024  የአፍሪካ ፋሽንና ሥነ-ጥበብ ሽልማት ( AFAA ) ተሸላሚ ሆነ

ላለፉት 25 ዓመታት ከፋሽን ሰዎች ታዋቂዎችን እነ ቺኒዋ አቼቤ፣ አለን ፔተን፣ የሚ አላዴ፣ ብሬንዳ ፋሴ እና ከሰዓሊያን እነ ቼሪ ሳምባ፣ አብዱላሂ ኮንቴ እና  ኢብራሂም አል ሳላሂ በተለያዩ ዓመታት የሸለመው የአፍሪካ ፋሽንና ሥነ-ጥበብ ሽልማት ( AFRICAN FASHION & ART AWARD -AFAA ) ዘንድሮው  ከሚሸልማቸው 100 አፍሪካዊያን የፋሽን እና የሥነ-ጥበብ ሰዎች  ውስጥ  ብቸኛው ኢትዮጵያዊ  ሠዓሊ ወንድወሰን ከበደ ኾኗል።

ሠዓሊ ወንድወሰን ከበደ ለሽልማቱ ቀጥታ ተመራጭ እንዲሆን ያበቃው፤ በአፍሪካ ስልጣኔ፣ ባህል እና ፓን አፍሪካኒዝም እንዲሁም በኢትዮጵያ ስልጣኔ ፣ ባህል እና ማንነት ላይ በሠራቸው የስዕል ሥራዎች እና በተለያዩ ዓለማት በተሳተፈባቸው ዐውደ ርዕዮች ባገኛቸው እውቅናና ሽልማቶች ነው።

ሠዓሊ እና የታሪክ ባለሙያ ወንድወሰን፤  በአሁን ሰዓት የኢትዮጵያ ሠዓሊያንና ቀራፂያን ማኅበር ዋና ጸሐፊ ፤ በኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን የሥነ-ጥበብ አማካሪ፣ በኢቲ - ሜትሮፖሊታን ጋለሪ ዳይሬክተር እና ኩሬተር፣ የሀገር አማን እና ሆርን ሪቪው መጽሔቶች ካርቱኒስት እና አምደኛ፣ በኢትዮጵያ ሀገር በቀል የሕክምና ማኅበር አምባሳደር በመሆን እያገለገለ ይገኛል።

የዘንድሮውን የአፍሪካዊያን የፋሽን እና የሥነ-ጥበብ ሽልማት ከNovember 6th - 8th /2024 በዋና ጽሕፈት ቤቱ ደቡብ አፍሪካ እንደሚያካሂድ አፋ (AFAA) ባወጣው መግለጫ አሳውቋል ።

ለተጨማሪው: https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
📌የቀድሞ ድምጻዊ ተፈራ ነጋሽ አልበም በድጋሚ ተሰርቶ ለአድማጭ ሊደርስ ነው

በ1980 ዎቹ ከተዜሙ የድምጻዊ ተፈራ ነጋሽ አልበሞች የተውጣጡ ሙዚቃዎች በድጋሚ ተሰርተው ለአድማጭ ሊደርሱ ነው ተባለ ።

በተለያዩ ነጠላ ዜማዎቹ የሚታወቀው ድምጻዊ ፍቃዱ ትዕዛዙ "ዘንድሮ'' በተሰኘ የሙዚቃ አልበም መጠሪያ የተሰጠውን የድምጻዊ ተፈራ  ነጋሽ ስራ ይዞ መምጣቱን አስታውቋል።

"ዘንድሮ" የሚል ስያሜ የተሰጠው አልበም ከሰላሳ ዓመታት በፊት በተዜሙ ዜማዎች በልዩ ጥንቃቄ ለዚህ ዘመን በሚስማማ መልኩ እንደገና የተሰሩ ሙዚቃዎች ናቸው ተብሏል ፡፡

በድምፃዊ ተፈራ ነጋሽ በተለያዩ አልበሞች ላይ የተቀነቀኑ ሙዚቃዎችን ድምጻዊው በሙዚቃ ፈጠራ ስራዎቹ ላይ የተሳተፉ ባለሞያዎችን እና የቤተሰቦችን መብት እና ጥቅም ባከበረ ሁኔታ እንዲሁም በማስፈቀድ የሙዚቃው የቀድሞ ለዛ እና ቃናቸውን በጠበቀ መልኩ ስራውንም በከፍተኛ ጥንቃቄ እና ዘመኑ ባፈራቸው ዘመናዊ የድምፅ መሳሪያዎች በመታገዝ ከፍተኛ ወጪ ተደርጎበት እንደተሰራ ገልጿል።

"ዘንድሮ” አልበም በትዝታ ፤ በፍቅር ፤ በውለታ የሚዳስሱ ደረጃቸውን የጠበቁ ስራዎች ናቸው ተብሏል።

አልበሙንም ሰርቶ ለማጠናቀቅ አራት ዓመታት እና ከፍተኛ በጀት ማውጣቱን ድምጻዊው አስታውቋል።

ድምጻዊ ፍቃዱ ትዕዛዙ ከዚህ ቀደም በሰራቸው ተዛዘብን ፤ ሲያዴ ፤ እንቅልፌን ደርበህ ፤ ላይ ላዩን ፤ አብሮ አደጌ(ተፈራ ነጋሽ) እና ምነው ቀዘቀዘ በተሰኙት ስራዎቹ ይታወቃል፡፡

ለተጨማሪው: https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
📌የ"ፈለገ ኪን" የኪነጥበብ ዝግጅት ነገ ይካሄዳል

በኢትዮጵያ አይነ ስውራን ብሄራዊ ማህበር የሚዘጋጀው "የፈለገ ኪን" ሶስተኛው የኪነጥበብ ዝግጅት ቅዳሜ ጥቅምት 23 ከቀኑ 8 ሰአት ጀምሮ ይካሄዳል።

ባለፉት ሁለት መድረኮች እንደተደረገው ሁሉ ሶስተኛውም መርሀግብር ዓይነ ስውራንና የዓይነ ስውራን ወዳጆች የሆኑ ባለተሰጥዖዎች የሙዚቃ፣ የሥነግጥምና የተለያዩ የስነ ጽሁፍ ችሎታዎቻቸውን የሚያሳዩበት መድረክ ነው ተብሏል።

በዕለቱም ሎሬት ጸጋዬ ገብረ መድህን  ይዘከራሉ፤ አንጋፋው ከያኒ አያልነህ ሙላት ደግሞ የዕለቱ ተጋባዥ እንግዳ ሆነው እንደሚገኙ ተገልጿል።

አዘጋጆቹ "በመርሃግብሩ ላይ በመታደም ከአይነስውራን አእምሮ የፈለቁ  እምቅ፣  ጥልቅ፣ ምጡቅ  የስነ ጽሁፍ፣ የሙዚቃና የፍልስፍና ጠለ በረከቶችን ይቋደሱ " ብለዋል።

ለተጨማሪው: https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
📌ሙዚቀኛ ያምሉ ሞላና ድምጻዊ ስለሺ ታምራት ድጋሚ የተጣመሩበት "ሞገድ" ገሚስ አልበም ተለቀቀ

"ጣዲቄ" በተሰኘው ሙዚቃው የምናውቀው ድምጻዊ ስለሺ ታምራት ከሁለገቡ ሙዚቀኛ ያምሉ ሞላ ጋር የተጣምሩበት "ሞገድ" ገሚስ አልበም ትላንት ጥቅምት 21 ቀን 2017 ዓ.ም በያምሉ ሞላ ዩቲዩብ ቻናል በኩል ለአድማጮች ደርሷል።

በዚህ ገሚስ የሙዚቃ አልበም ውስጥ "እንዲህ እንዲያ" ፣"አንገቶዋ"፣ "ኧረ ጉዴ" ፣"እንዳንቺማ" የተሰኙ ርዕስ የተሰጣቸው የሙዚቃ ስራዎች እንደተካተቱበት ኤቨንት አዲስ ድረገፅ ተመልክቷል።

ለተጨማሪው: https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
📌የአንጋፋው ድምጻዊ ማሕሙድ አሕመድ  የሙዚቃ ሕይወት ስንብት ትልቅ ኮንሰርት ጥር 3 እንደሚካሄድ ተሰማ

"የትዝታው ንጉሥ" የሚል ቅጽል ስም የወጣለት አንጋፋው ድምጻዊ ማሕሙድ አሕመድ የሙዚቃ ሕይወት ስንብት ትልቅ ኮንሰርት ጥር 3 ቀን 2017 ዓ.ም በሚሊኒየም አዳራሽ እንደሚካሄድ ኤቨንት አዲስ ሚዲያ ያገኘው መረጃ ያመለክታል።

በዚህ የስንበት ሙዚቃ ዝግጅት በአንጋፋው ድምጻዊ ማሕሙድ አሕመድ የሙዚቃ ሕይወት ላይ የተዘጋጀ መጽሐፍ እንደሚመረቅም ተነግሯል።

በኢትዮጵያ ከ50 ዓመታት በላይ ከልጅነቱ አንስቶ የአገራችንን ሙዚቃ በተለያዩ የአገራችን ቋንቋዎች በመዝፈን፣ የአገራችንን ሙዚቃ ከአገር አልፎ በዓለም አቀፍ ደረጃ እንዲደመጡ ያደረገው  የሙዚቃ አባት ከሙዚቃ አለም ለማሰናበት ወይም ማይኩን ሊሰቅል ሲዘጋጅ እጃችንን አወዛውዘን መሸኘት አግባብነት የለውም በሚል በጆርካ ኢቨንት አዘጋጅነት ሽኝቱን በደመቀ እና በታሪክ ማስታወሻነትም ለማስቀመጥ መታሰቡን ሰምተናል፡፡

በዚህም ጥቅምት 22 ቀን  ከጋሽ ማሕሙድ ኮሚቴ በመረከብ ጥር 3 ቀን 2017 ዓ.ም. በሚለኒየም አዳራሽ ደረጃውን የጠበቀ የድምጻዊው የመጨረሻ የህይወት ዘመን ስንብት ኮንሰርት እንደሚዘጋጅ ተነግሯል ፡፡

ለተጨማሪው: https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
📌በዶ/ር ተሻለ አሰፋ የተፃፈው "የተውኔት ዝግጅት መሰረታዊያን" መጽሐፍ በሚቀጥለው ሳምንት ለንባብ ይበቃል

የአዲስ እበባ ዩንቨርስቲ የቴአትር ትምህርት ክፍል መምህር በሆነው በዶ/ር ተሻለ አሰፋ የተፃፈው "የተውኔት ዝግጅት መሰረታዊያን " የተሰኘው መጽሐፍ በሚቀጥለው ሳምንት ለንባብ እንደሚበቃ አሳታሚው የሳይንስ አካዳሚ  አስታውቋል::

"የተውኔት ዝግጅት መሰረታዊያን " መጽሐፍ ስድስት ምዕራፎች፤ 364 ገጽያለው ሲሆን ፤ ስለ ተውኔት ዝግጅት ምንነት እና ጽንሰ ሐሳባዊና ተግባራዊ ብያኔዎች፣ የአዘጋጅ ማንነት፣የዝግጅት አላባውያን እና የዝግጅት ቅደም ተከተሎችን የመሳሰሉ አርእስተ ጉዳዮችን በጥልቀት የሚተነትን መፅሐፍ ነው::

ዶ/ር ተሻለ አሰፋ የተውኔት ዝግጅት ምንነትን ለረጅም ዓመታት በሙያው ላይ ጥልቅ ጥናትና ምርምር በማድረግ ከልምዱ ጋር በማዋሃድ ያዘጋጀው መጽሐፍ እንደሆነ ገልፆአል::

መፅሐፉ በሙያው ላይ ለሚገኙ እንዲሁም በግልና በመንግስት ዩንቨርሲቲዎች ለሚያስተምሩ መምህራን እና ተማሪዎች እንዲሁም ሙያውን ለሚወዱ ሁሉ እንዲመች ተደርጎ በጥሩ ቋንቋ እንደተዘጋጀ የአሳታሚው የሳይንስ አካዳሚ አርታኢ አቶ ቴዎድሮስ አጥላው ተናግረዋል::

መጽሐፉ ከሚቀጥለው ሳምንት ጀምሮ ለንባብ እንደሚበቃም ተገልፆል::

📍መረጃው የይትባረክ ዋለልኝ ነው።

ለተጨማሪው: https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
📌የፊልም ባለሞያው በኃይሉ ዋሴ(ዋጄ) የክብር እንግዳ የሆነበት ስብሐቲዝም የሀሳብ ውይይት ዝግጅት ነገ ይካሄዳል።

"ምን ልታዘዝ ?" ተከታታይ ድራማ፣"በእናት መንገድ" ፊልምን ጨምሮ በርካታ ፊልሞች ላይ በድርሰትና ዝግጅት ምናውቀው የፊልም ባለሞያ በኃይሉ ዋሴ(ዋጄ) የክብር እንግዳ የሆነበት ስብሐቲዝም 77ተኛ መድረክ "ጥበብ እና ዘመን" በሚል የሀሳብ ውይይት ይካሄዳል።

ውይይቱ ነገ ጥቅምት 24 ቀን 2017 ዓ.ም  ከቀኑ 8:00 ጀምሮ በብሔራዊ ቤተመዛግብት እና ቤተመጻሕፍት አገልግሎት (ወመዘክር) አዳራሽ ውስጥ ይከናወናል።

ለተጨማሪው: https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
📌"የሕይወት ታሪክ" ተውኔት ዛሬ ይመረቃል

ድርሰቱ እና ዝግጅቱ የነብዩ ባዬ እና የቢንያም ወርቁ የሆነው "የሕይወት ታሪክ" አዲስ ተውኔት ዛሬ ጥቅምት 25 ቀን 2017 ዓ.ም በአንጋፋው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር በልዩ ዝግጅት ተመርቆ ዘወትር አርብ መቅረብ እንደሚጀምር ኤቨንት አዲስ ሚዲያ ያገኘው መረጃ ያመለክታል።

ይህ ተውኔት ከዚህ ቀደም በሸገር ራዲዮ በሬድዮ ድራማ መልክ ቀረቡ የነበረ ሲሆን አሁን በመድረክ ተውኔት ቅርጽ ተሰርቷል ተብሏል።

በ"ሕይወት ታሪክ" በተውኔት ላይ ቢንያም ወርቁ እና ፀደይ ፋንታሁን ለሁለት ይተውናሉ።

ተውኔቱ በነባ ጥበባት እና ኮምኒኬሽን የቀረበ ነው።

ለተጨማሪው: https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
📌የዳዊት ፅጌ "ዳር ዳር" ነጠላ ሙዚቃ ነገ ይለቀቃል

የድምጻዊ ዳዊት ፅጌ "ዳር ዳር" የተሰኘ ርዕስ የተሰጠው ነጠላ ሙዚቃ ነገ ጥቅምት 26 ቀን 2017 ዓ.ም በራሱ የዩቲዩብ ቻናል በኩል ይለቀቃል ተብሏል።

በዚህ የነጠላ ሙዚቃ ስራ ላይ ድምጻዊ አብዱ ኪያር በግጥምና ዜማ ተሳትፏል። አበጋዝ ክብረወርቅ ሺዎታ የሙዚቃ ቅንብሩን ሰርቷል።

ድምጻዊ ዳዊት ፅጌም ስለዚህ የሙዚቃ ስራው በማህበራዊ ትስስር ገፁ" እጅግ በምወደውና በማከብረው ታላቅ ወንድሜና የሙያ አጋሬ አብዱ ኪያር (ABD) ግጥምና ዜማ ደራሲነት ”ዳር  ዳር “ የተሰኘ አዲስ ነጠላ ዘፈን የሰራሁ ሲሆን፤ በአሜሪካ በነበረን ቆይታ በ "የኔ ዜማ" ባንድ አጃቢነት የተጫወትነውንና አበጋዝ ክብረወርቅ ሺዎታ ያቀናበረውን ይህን ዜማ ማክሰኞ ጥቅምት 26 2017 11:00 ላይ በ Dawittsige official youtube channel ላይ እንደሚለቀቅ ስገልፅ በታላቅ ደስታ ነው"ብሏል።

በተያያዘ መረጃም የድምጻዊ ዳዊት ፅጌ "የኔ ዜማ" ኮንሰርቱ የፊታችን ህዳር 7 ቀን 2017 ዓ.ም በአዲስ አበባ ሚሊኒየም አዳራሽ እንደሚካሄድ ኤቨንት አዲስ ሚዲያ ከድምጻዊው ያገኘው መረጃ ያመለከታል።

ለተጨማሪው: https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
📌የድምጻዊ ጥላሁን ገሠሠ አልባሳትና ቁሳቁስ ለዕይታ ሊቀርብ ነው

የድምጻዊ ጥላሁን ገሠሠ አልባሳት እና ቁሳቁስ ትውልድ እንዲያየው በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ጥናትና ምርምር ተቋም ጥቅምት 29 ቀን 2017 በክብር ይቀመጣል ተባለ፡፡

በዕለቱም የአርቲስቱ ቤተሰቦች፣ አድናቂዎች እና ሌሎች እንግዶች  እንደሚገኙ የድምጻዊ ጥላሁን ገሠሠ የመታሰቢያ ዝግጅት አስተባባሪ ኮሚቴ አስታውቋል፡፡

ታሪካዊ የሆኑ እና በትውልድ ቅብብሎሽ ውስጥ ኅያው ሆነው እንዲኖሩ ከድምጻዊያው ቤተሰቦች የተሰበሰቡ አልባሳት እና ቁሳቁሶችንም አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተረክቦ ለዕይታ እንዲበቃ በባለቤትነት ይረከባል ተብሏል፡፡

ድምጻዊ ጥላሁን ገሠሠን የሚያስታውስ የፎቶ ዐውደ-ርዕይ እና ሥራች በዕለቱ ለታዳሚያን እንደሚቀርቡም ተጠቁሟል፡፡

📌 መረጃው የፋና ነው።

ለተጨማሪው: https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
📌የብሔራዊ ቴአትር አዲሱ ህንፃ ተቋራጩ ከገባበት ኮንትራት ውጭ የዋጋ ጭማሪ በመኖሩ ግንባታው ተጓቷል ተባለ

ከአምሥት ዓመታት በፊት የተጀመረው የብሔራዊ ቴአትር ህንፃ ግንባታ በዋጋ ልዩነቶች ምክንያት ተቋራጩ ከመንግስት ጋር እየተደራደረ መሆኑን አራዳ ኤፍ ኤም ከምንጮቹ ሰምቷል።

ከዚህ ቀደም አፍሮ ጽዮን ኮንስትራክሽን የግንባታው ተቋራጭ የነበረ ሲሆን አሁን ኦቪድ ግሩፕ ግንባታውን እያከናወነ እንደሆነ ይታወቃል።

ኦቪድ ግሩፕ ግንባታውን ባጠረ ጊዜ ውስጥ ለመጨረስ እየሰራ ቢሆንም የግንባታ ግብዓት የዋጋ ለውጥ ስላመጣ ከመንግስት እና ከደንበኛው ጋር በመነጋገር መልስ ለመስጠት እየሞከረ እንደሆነ ነው የተገለፀው።

በዋናነት ይህ የሆነበት ምክንያት የዋጋ ልዩነቶች በመምጣታቸው ሲሆን፥ ችግሩን ለመቅረፍ ድርድር ማካሄድ አስፈላጊ ሆኖ መገኘቱን ጣቢያችን ለማወቅ ችሏል።

ኦቪድ መጀመሪያ ከገባበት ውል ነገሮችን አስተካክሎ ለማምጣት በሙከራ ላይ ነውም ተብሏል።

አዲሱ የብሔራዊ ቴአትር ህንፃ 19 ወለሎች የሚኖሩት ሲሆን፥ በ7 ሺህ ካሬ ሜትር መሬት ላይ የሚያርፍና 1 ነጥብ 5 ቢሊየን ብር ለግንባታው የተቆረጠ ወጪ አለው መባሉ ይታወሳል።

አምሥት ዓመታት የህንፃው ግንባታ የማጠናቀቂያ የጊዜ ሰሌዳ የነበረ ቢሆንም እስከ አሁን በግንባታ መጓተት ምክንያት ሊጠናቀቅ አልቻለም።

📍መረጃው የአራዳ ኤፍ ኤም ነው።

ለተጨማሪው: https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
📌ፈንድቃ የጥበባትና ባህል ማዕከልን በነበረበት ስፍራ መልሶ ለመገንባት እንቅስቃሴ መጀመሩ ተገለጸ

ከከተማው የኮሪደር ልማት ስራ ጋር በተገናኘ የፈረሰው የፈንድቃ የጥበባትና ባህል ማእከል በነበረበት ስፍራ ዳግም እንዲገነባ ከተማ አስተዳደሩ መፍቀዱ ይታወሳል።

ማዕከሉ የሀገርን ባህልና ጥበብ ለማስተዋወቅ ካደረገው ጥረት አንጻር መንግስት በነበረበት ስፍራ የከተማውን ደረጃ የሚመጥን ግንባታ እንዲከናወን ፈቅዷል ሲሉ የማዕከሉ ስራ አስኪያጅ አቶ መላኩ በላይ ለመናኸሪያ ሬዲዮ ተናግረዋል።

በመሆኑም አሁን ላይ ግንባታውን ለማከናወን በግል አቅም ስለማይቻል ከተለያዩ ሀገራት ካሉ ኢትዮጵያውያን ገቢ ለማሰባሰብ መታቀዱን  ገልጸዋል። እንደ አዲስ ተገንብቶ መቅረቡ የበለጠ ማዕከሉ ደረጃውን እንዲጠብቅ ከማድረግ አንጻር የራሱ ላቅ ያለ ሚና ቢኖረውም ሰርቶ ለማጠናቀቅም ከፍተኛ ርብርብና አቅም ይፈልጋል ሲሉም አክለዋል፡፡

ግንባታው መቼ እንደሚጀመር አቶ መላኩ በውል ባይገልጹም መንግስት ባስቀመጠው ህግና ደንብ መሰረት ሰርቶ ለማጠናቀቅ እንደሚሞከር ተናግረዋል። ባህል ማዕከሉ እስከዚያው ድረስ በሌላ የከተማው ስፍራ መደበኛ ስራውን እንደሚቀጥልና አሁን ላይ የተሻለ ቦታ በማማረጥ ላይ እንደሚገኙም አመላክተዋል፡፡

እንዲህ አይነት ሀገርንና ባህልን የሚያስተዋውቁ ስፍራዎችን መንግስት ጠብቆና ህጋዊ እውቅና ሰጥቶ ማቆየቱ ከፍ ያለ ሀገራዊ ጥቅም እንዳለው ስራ አስኪያጁ ገልጸዋል።

📍መረጃው የመናኸሪያ ሬድዮ ነው።

ለተጨማሪው: https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
📌የዶ/ር ተሻለ አሰፋ "የተውኔት ዝግጅት መሰረታዊያን" መጽሐፍ ነገ ለንባብ ይበቃል

በዶ/ር ተሻለ አሰፋ የተዘጋጀው "የተውኔት ዝግጅት መሰረታዊያን " የተሰኘው መጽሐፍ ነገ ጥቅምት 28 ቀን 2017 ዓ.ም ለንባብ እንደሚበቃ ኤቨንት አዲስ ሚዲያ ያገኘው መረጃ ያመለክታል።

"የተውኔት ዝግጅት መሰረታዊያን " መጽሐፍ ስድስት ምዕራፎች፤ 364 ገጽያለው ሲሆን ፤ ስለ ተውኔት ዝግጅት ምንነት እና ጽንሰ ሐሳባዊና ተግባራዊ ብያኔዎች፣ የአዘጋጅ ማንነት፣የዝግጅት አላባውያን እና የዝግጅት ቅደም ተከተሎችን የመሳሰሉ አርእስተ ጉዳዮችን በጥልቀት የሚተነትን መፅሐፍ ነው::

ዶ/ር ተሻለ አሰፋ የተውኔት ዝግጅት ምንነትን ለረጅም ዓመታት በሙያው ላይ ጥልቅ ጥናትና ምርምር በማድረግ ከልምዱ ጋር በማዋሃድ ያዘጋጀው መጽሐፍ እንደሆነ ገልፆአል::

መፅሐፉ በሙያው ላይ ለሚገኙ እንዲሁም በግልና በመንግስት ዩንቨርሲቲዎች ለሚያስተምሩ መምህራን እና ተማሪዎች እንዲሁም ሙያውን ለሚወዱ ሁሉ እንዲመች ተደርጎ በጥሩ ቋንቋ እንደተዘጋጀ የአሳታሚው የሳይንስ አካዳሚ አርታኢ አቶ ቴዎድሮስ አጥላው ተናግረዋል::

ለተጨማሪው: https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
📌የኢትዮጵያውያን የሰርከስ አርቲስቶች ቡድን በአምስት የአውሮፓ ሀገራት ትርዒቱን ሊያቀርብ ነው፡፡

ሠላሳ አምስት አባላት ያሉትና ሙሉ ኢትዮጵያውያን ብቻ የሚሳተፉበት ከተለያዩ የሰርከስ ማዕከላት አርቲስቶችን፣ የውዝዋዜ፣ ታዋቂ የሙዚቃ መሳሪያ ተጫዋቾችና ታዋቂ ድምጻውያንን ያካተተ ልዩ ቡድን በማዘጋጀት በፈረንሳይ ፓሪስ በሚገኝው በታዋቂው በሰርክ ፊኔክስ “ሰርክ አፍሪካ የኢትዮጵያ ኮኮቦች” በሚል ርዕሰ ትርዒቱን ፓሪስ በፊኔክስ መድረክ፣ እንዲሁም በቤልጅዬም፣ በሞናኮ ሞንቴካርሎ፣ በስዊዘርላንና በአንዶራ የሀገራችን ኢትዮጵያን ባህል፣አለባበስ፣ ሙዚቃና ጭፈራ ያካተተ ሙሉ የሰርከስ ትርኢት የያዘ ቡድን ከህዳር 04 ቀን 2017 ዓ/ም ጀምሮ ወደ ፈረንሳይ ሊጓዝ መሆኑን አፍሪካን ድሪም አርትስ እና አፍሪካን ድሪም ሰርከስ ዛሬ ጥቅምት 28 ቀን 2017ዓ/ም በቱሊፕ ኢን ኦሎምፒያ ሆቴል በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ አስታውቋል፡፡

አዘጋጆቹ ይህ ትርዒት በኢትዮጵያ የመጀመሪያ የሚሆን የሰርከስ፣ የዉዝዋዜና የሙዚቃ ባለሙያ የሚሳተፉበት ትልቅ ትርዒት መሆኑን በመግለጫው ተናግረዋል፡፡

አፍሪካን ድሪም አርትስ እና አፍሪካን ድሪም ሰርከስ በተለያዩ አለም አቀፍ ፌስቲቫሎች ላይ አርቲስቶችን በማሳተፍ የወርቅ የብር የነሃስ እና ስፔሻል ፕራይዝ ተሸላሚዎች እንዲሆኑ እና  የሀገርን ሰንደቅ አላማ ከፍ በማድረግ መልካም ገፅታዋን በመገንባት ሰርከስ የሃገር የባህል አምባሳደር እንዲሆን ከፍተኛ አስተዋፅዖ  በማበርከት በተደጋጋሚ የወርልድ ጊኒየስ ሪከርድ በማስመዝገብ እና ለዓለም አቀፍ  የሠርከስ ካምፓኒዎች  በማቅረብ ለብዙ ኢትዮጵያዊያንና አፍሪካውያን የስራ እድል ማመቻቸት ችሏል፡፡ 

ለተጨማሪው: https://news.1rj.ru/str/EventAddis1