Event Addis Media – Telegram
Event Addis Media
9.62K subscribers
6.11K photos
13 videos
4 files
4.73K links
Connect with Addis artistic community!

Website: https://eventaddis.com

Contact: @Tmanaye
Download Telegram
📌የአንጋፋው ድምጻዊ ማሕሙድ አሕመድ  የሙዚቃ ሕይወት ስንብት ትልቅ ኮንሰርት ጥር 3 እንደሚካሄድ ተሰማ

"የትዝታው ንጉሥ" የሚል ቅጽል ስም የወጣለት አንጋፋው ድምጻዊ ማሕሙድ አሕመድ የሙዚቃ ሕይወት ስንብት ትልቅ ኮንሰርት ጥር 3 ቀን 2017 ዓ.ም በሚሊኒየም አዳራሽ እንደሚካሄድ ኤቨንት አዲስ ሚዲያ ያገኘው መረጃ ያመለክታል።

በዚህ የስንበት ሙዚቃ ዝግጅት በአንጋፋው ድምጻዊ ማሕሙድ አሕመድ የሙዚቃ ሕይወት ላይ የተዘጋጀ መጽሐፍ እንደሚመረቅም ተነግሯል።

በኢትዮጵያ ከ50 ዓመታት በላይ ከልጅነቱ አንስቶ የአገራችንን ሙዚቃ በተለያዩ የአገራችን ቋንቋዎች በመዝፈን፣ የአገራችንን ሙዚቃ ከአገር አልፎ በዓለም አቀፍ ደረጃ እንዲደመጡ ያደረገው  የሙዚቃ አባት ከሙዚቃ አለም ለማሰናበት ወይም ማይኩን ሊሰቅል ሲዘጋጅ እጃችንን አወዛውዘን መሸኘት አግባብነት የለውም በሚል በጆርካ ኢቨንት አዘጋጅነት ሽኝቱን በደመቀ እና በታሪክ ማስታወሻነትም ለማስቀመጥ መታሰቡን ሰምተናል፡፡

በዚህም ጥቅምት 22 ቀን  ከጋሽ ማሕሙድ ኮሚቴ በመረከብ ጥር 3 ቀን 2017 ዓ.ም. በሚለኒየም አዳራሽ ደረጃውን የጠበቀ የድምጻዊው የመጨረሻ የህይወት ዘመን ስንብት ኮንሰርት እንደሚዘጋጅ ተነግሯል ፡፡

ለተጨማሪው: https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
📌በዶ/ር ተሻለ አሰፋ የተፃፈው "የተውኔት ዝግጅት መሰረታዊያን" መጽሐፍ በሚቀጥለው ሳምንት ለንባብ ይበቃል

የአዲስ እበባ ዩንቨርስቲ የቴአትር ትምህርት ክፍል መምህር በሆነው በዶ/ር ተሻለ አሰፋ የተፃፈው "የተውኔት ዝግጅት መሰረታዊያን " የተሰኘው መጽሐፍ በሚቀጥለው ሳምንት ለንባብ እንደሚበቃ አሳታሚው የሳይንስ አካዳሚ  አስታውቋል::

"የተውኔት ዝግጅት መሰረታዊያን " መጽሐፍ ስድስት ምዕራፎች፤ 364 ገጽያለው ሲሆን ፤ ስለ ተውኔት ዝግጅት ምንነት እና ጽንሰ ሐሳባዊና ተግባራዊ ብያኔዎች፣ የአዘጋጅ ማንነት፣የዝግጅት አላባውያን እና የዝግጅት ቅደም ተከተሎችን የመሳሰሉ አርእስተ ጉዳዮችን በጥልቀት የሚተነትን መፅሐፍ ነው::

ዶ/ር ተሻለ አሰፋ የተውኔት ዝግጅት ምንነትን ለረጅም ዓመታት በሙያው ላይ ጥልቅ ጥናትና ምርምር በማድረግ ከልምዱ ጋር በማዋሃድ ያዘጋጀው መጽሐፍ እንደሆነ ገልፆአል::

መፅሐፉ በሙያው ላይ ለሚገኙ እንዲሁም በግልና በመንግስት ዩንቨርሲቲዎች ለሚያስተምሩ መምህራን እና ተማሪዎች እንዲሁም ሙያውን ለሚወዱ ሁሉ እንዲመች ተደርጎ በጥሩ ቋንቋ እንደተዘጋጀ የአሳታሚው የሳይንስ አካዳሚ አርታኢ አቶ ቴዎድሮስ አጥላው ተናግረዋል::

መጽሐፉ ከሚቀጥለው ሳምንት ጀምሮ ለንባብ እንደሚበቃም ተገልፆል::

📍መረጃው የይትባረክ ዋለልኝ ነው።

ለተጨማሪው: https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
📌የፊልም ባለሞያው በኃይሉ ዋሴ(ዋጄ) የክብር እንግዳ የሆነበት ስብሐቲዝም የሀሳብ ውይይት ዝግጅት ነገ ይካሄዳል።

"ምን ልታዘዝ ?" ተከታታይ ድራማ፣"በእናት መንገድ" ፊልምን ጨምሮ በርካታ ፊልሞች ላይ በድርሰትና ዝግጅት ምናውቀው የፊልም ባለሞያ በኃይሉ ዋሴ(ዋጄ) የክብር እንግዳ የሆነበት ስብሐቲዝም 77ተኛ መድረክ "ጥበብ እና ዘመን" በሚል የሀሳብ ውይይት ይካሄዳል።

ውይይቱ ነገ ጥቅምት 24 ቀን 2017 ዓ.ም  ከቀኑ 8:00 ጀምሮ በብሔራዊ ቤተመዛግብት እና ቤተመጻሕፍት አገልግሎት (ወመዘክር) አዳራሽ ውስጥ ይከናወናል።

ለተጨማሪው: https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
📌"የሕይወት ታሪክ" ተውኔት ዛሬ ይመረቃል

ድርሰቱ እና ዝግጅቱ የነብዩ ባዬ እና የቢንያም ወርቁ የሆነው "የሕይወት ታሪክ" አዲስ ተውኔት ዛሬ ጥቅምት 25 ቀን 2017 ዓ.ም በአንጋፋው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር በልዩ ዝግጅት ተመርቆ ዘወትር አርብ መቅረብ እንደሚጀምር ኤቨንት አዲስ ሚዲያ ያገኘው መረጃ ያመለክታል።

ይህ ተውኔት ከዚህ ቀደም በሸገር ራዲዮ በሬድዮ ድራማ መልክ ቀረቡ የነበረ ሲሆን አሁን በመድረክ ተውኔት ቅርጽ ተሰርቷል ተብሏል።

በ"ሕይወት ታሪክ" በተውኔት ላይ ቢንያም ወርቁ እና ፀደይ ፋንታሁን ለሁለት ይተውናሉ።

ተውኔቱ በነባ ጥበባት እና ኮምኒኬሽን የቀረበ ነው።

ለተጨማሪው: https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
📌የዳዊት ፅጌ "ዳር ዳር" ነጠላ ሙዚቃ ነገ ይለቀቃል

የድምጻዊ ዳዊት ፅጌ "ዳር ዳር" የተሰኘ ርዕስ የተሰጠው ነጠላ ሙዚቃ ነገ ጥቅምት 26 ቀን 2017 ዓ.ም በራሱ የዩቲዩብ ቻናል በኩል ይለቀቃል ተብሏል።

በዚህ የነጠላ ሙዚቃ ስራ ላይ ድምጻዊ አብዱ ኪያር በግጥምና ዜማ ተሳትፏል። አበጋዝ ክብረወርቅ ሺዎታ የሙዚቃ ቅንብሩን ሰርቷል።

ድምጻዊ ዳዊት ፅጌም ስለዚህ የሙዚቃ ስራው በማህበራዊ ትስስር ገፁ" እጅግ በምወደውና በማከብረው ታላቅ ወንድሜና የሙያ አጋሬ አብዱ ኪያር (ABD) ግጥምና ዜማ ደራሲነት ”ዳር  ዳር “ የተሰኘ አዲስ ነጠላ ዘፈን የሰራሁ ሲሆን፤ በአሜሪካ በነበረን ቆይታ በ "የኔ ዜማ" ባንድ አጃቢነት የተጫወትነውንና አበጋዝ ክብረወርቅ ሺዎታ ያቀናበረውን ይህን ዜማ ማክሰኞ ጥቅምት 26 2017 11:00 ላይ በ Dawittsige official youtube channel ላይ እንደሚለቀቅ ስገልፅ በታላቅ ደስታ ነው"ብሏል።

በተያያዘ መረጃም የድምጻዊ ዳዊት ፅጌ "የኔ ዜማ" ኮንሰርቱ የፊታችን ህዳር 7 ቀን 2017 ዓ.ም በአዲስ አበባ ሚሊኒየም አዳራሽ እንደሚካሄድ ኤቨንት አዲስ ሚዲያ ከድምጻዊው ያገኘው መረጃ ያመለከታል።

ለተጨማሪው: https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
📌የድምጻዊ ጥላሁን ገሠሠ አልባሳትና ቁሳቁስ ለዕይታ ሊቀርብ ነው

የድምጻዊ ጥላሁን ገሠሠ አልባሳት እና ቁሳቁስ ትውልድ እንዲያየው በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ጥናትና ምርምር ተቋም ጥቅምት 29 ቀን 2017 በክብር ይቀመጣል ተባለ፡፡

በዕለቱም የአርቲስቱ ቤተሰቦች፣ አድናቂዎች እና ሌሎች እንግዶች  እንደሚገኙ የድምጻዊ ጥላሁን ገሠሠ የመታሰቢያ ዝግጅት አስተባባሪ ኮሚቴ አስታውቋል፡፡

ታሪካዊ የሆኑ እና በትውልድ ቅብብሎሽ ውስጥ ኅያው ሆነው እንዲኖሩ ከድምጻዊያው ቤተሰቦች የተሰበሰቡ አልባሳት እና ቁሳቁሶችንም አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተረክቦ ለዕይታ እንዲበቃ በባለቤትነት ይረከባል ተብሏል፡፡

ድምጻዊ ጥላሁን ገሠሠን የሚያስታውስ የፎቶ ዐውደ-ርዕይ እና ሥራች በዕለቱ ለታዳሚያን እንደሚቀርቡም ተጠቁሟል፡፡

📌 መረጃው የፋና ነው።

ለተጨማሪው: https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
📌የብሔራዊ ቴአትር አዲሱ ህንፃ ተቋራጩ ከገባበት ኮንትራት ውጭ የዋጋ ጭማሪ በመኖሩ ግንባታው ተጓቷል ተባለ

ከአምሥት ዓመታት በፊት የተጀመረው የብሔራዊ ቴአትር ህንፃ ግንባታ በዋጋ ልዩነቶች ምክንያት ተቋራጩ ከመንግስት ጋር እየተደራደረ መሆኑን አራዳ ኤፍ ኤም ከምንጮቹ ሰምቷል።

ከዚህ ቀደም አፍሮ ጽዮን ኮንስትራክሽን የግንባታው ተቋራጭ የነበረ ሲሆን አሁን ኦቪድ ግሩፕ ግንባታውን እያከናወነ እንደሆነ ይታወቃል።

ኦቪድ ግሩፕ ግንባታውን ባጠረ ጊዜ ውስጥ ለመጨረስ እየሰራ ቢሆንም የግንባታ ግብዓት የዋጋ ለውጥ ስላመጣ ከመንግስት እና ከደንበኛው ጋር በመነጋገር መልስ ለመስጠት እየሞከረ እንደሆነ ነው የተገለፀው።

በዋናነት ይህ የሆነበት ምክንያት የዋጋ ልዩነቶች በመምጣታቸው ሲሆን፥ ችግሩን ለመቅረፍ ድርድር ማካሄድ አስፈላጊ ሆኖ መገኘቱን ጣቢያችን ለማወቅ ችሏል።

ኦቪድ መጀመሪያ ከገባበት ውል ነገሮችን አስተካክሎ ለማምጣት በሙከራ ላይ ነውም ተብሏል።

አዲሱ የብሔራዊ ቴአትር ህንፃ 19 ወለሎች የሚኖሩት ሲሆን፥ በ7 ሺህ ካሬ ሜትር መሬት ላይ የሚያርፍና 1 ነጥብ 5 ቢሊየን ብር ለግንባታው የተቆረጠ ወጪ አለው መባሉ ይታወሳል።

አምሥት ዓመታት የህንፃው ግንባታ የማጠናቀቂያ የጊዜ ሰሌዳ የነበረ ቢሆንም እስከ አሁን በግንባታ መጓተት ምክንያት ሊጠናቀቅ አልቻለም።

📍መረጃው የአራዳ ኤፍ ኤም ነው።

ለተጨማሪው: https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
📌ፈንድቃ የጥበባትና ባህል ማዕከልን በነበረበት ስፍራ መልሶ ለመገንባት እንቅስቃሴ መጀመሩ ተገለጸ

ከከተማው የኮሪደር ልማት ስራ ጋር በተገናኘ የፈረሰው የፈንድቃ የጥበባትና ባህል ማእከል በነበረበት ስፍራ ዳግም እንዲገነባ ከተማ አስተዳደሩ መፍቀዱ ይታወሳል።

ማዕከሉ የሀገርን ባህልና ጥበብ ለማስተዋወቅ ካደረገው ጥረት አንጻር መንግስት በነበረበት ስፍራ የከተማውን ደረጃ የሚመጥን ግንባታ እንዲከናወን ፈቅዷል ሲሉ የማዕከሉ ስራ አስኪያጅ አቶ መላኩ በላይ ለመናኸሪያ ሬዲዮ ተናግረዋል።

በመሆኑም አሁን ላይ ግንባታውን ለማከናወን በግል አቅም ስለማይቻል ከተለያዩ ሀገራት ካሉ ኢትዮጵያውያን ገቢ ለማሰባሰብ መታቀዱን  ገልጸዋል። እንደ አዲስ ተገንብቶ መቅረቡ የበለጠ ማዕከሉ ደረጃውን እንዲጠብቅ ከማድረግ አንጻር የራሱ ላቅ ያለ ሚና ቢኖረውም ሰርቶ ለማጠናቀቅም ከፍተኛ ርብርብና አቅም ይፈልጋል ሲሉም አክለዋል፡፡

ግንባታው መቼ እንደሚጀመር አቶ መላኩ በውል ባይገልጹም መንግስት ባስቀመጠው ህግና ደንብ መሰረት ሰርቶ ለማጠናቀቅ እንደሚሞከር ተናግረዋል። ባህል ማዕከሉ እስከዚያው ድረስ በሌላ የከተማው ስፍራ መደበኛ ስራውን እንደሚቀጥልና አሁን ላይ የተሻለ ቦታ በማማረጥ ላይ እንደሚገኙም አመላክተዋል፡፡

እንዲህ አይነት ሀገርንና ባህልን የሚያስተዋውቁ ስፍራዎችን መንግስት ጠብቆና ህጋዊ እውቅና ሰጥቶ ማቆየቱ ከፍ ያለ ሀገራዊ ጥቅም እንዳለው ስራ አስኪያጁ ገልጸዋል።

📍መረጃው የመናኸሪያ ሬድዮ ነው።

ለተጨማሪው: https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
📌የዶ/ር ተሻለ አሰፋ "የተውኔት ዝግጅት መሰረታዊያን" መጽሐፍ ነገ ለንባብ ይበቃል

በዶ/ር ተሻለ አሰፋ የተዘጋጀው "የተውኔት ዝግጅት መሰረታዊያን " የተሰኘው መጽሐፍ ነገ ጥቅምት 28 ቀን 2017 ዓ.ም ለንባብ እንደሚበቃ ኤቨንት አዲስ ሚዲያ ያገኘው መረጃ ያመለክታል።

"የተውኔት ዝግጅት መሰረታዊያን " መጽሐፍ ስድስት ምዕራፎች፤ 364 ገጽያለው ሲሆን ፤ ስለ ተውኔት ዝግጅት ምንነት እና ጽንሰ ሐሳባዊና ተግባራዊ ብያኔዎች፣ የአዘጋጅ ማንነት፣የዝግጅት አላባውያን እና የዝግጅት ቅደም ተከተሎችን የመሳሰሉ አርእስተ ጉዳዮችን በጥልቀት የሚተነትን መፅሐፍ ነው::

ዶ/ር ተሻለ አሰፋ የተውኔት ዝግጅት ምንነትን ለረጅም ዓመታት በሙያው ላይ ጥልቅ ጥናትና ምርምር በማድረግ ከልምዱ ጋር በማዋሃድ ያዘጋጀው መጽሐፍ እንደሆነ ገልፆአል::

መፅሐፉ በሙያው ላይ ለሚገኙ እንዲሁም በግልና በመንግስት ዩንቨርሲቲዎች ለሚያስተምሩ መምህራን እና ተማሪዎች እንዲሁም ሙያውን ለሚወዱ ሁሉ እንዲመች ተደርጎ በጥሩ ቋንቋ እንደተዘጋጀ የአሳታሚው የሳይንስ አካዳሚ አርታኢ አቶ ቴዎድሮስ አጥላው ተናግረዋል::

ለተጨማሪው: https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
📌የኢትዮጵያውያን የሰርከስ አርቲስቶች ቡድን በአምስት የአውሮፓ ሀገራት ትርዒቱን ሊያቀርብ ነው፡፡

ሠላሳ አምስት አባላት ያሉትና ሙሉ ኢትዮጵያውያን ብቻ የሚሳተፉበት ከተለያዩ የሰርከስ ማዕከላት አርቲስቶችን፣ የውዝዋዜ፣ ታዋቂ የሙዚቃ መሳሪያ ተጫዋቾችና ታዋቂ ድምጻውያንን ያካተተ ልዩ ቡድን በማዘጋጀት በፈረንሳይ ፓሪስ በሚገኝው በታዋቂው በሰርክ ፊኔክስ “ሰርክ አፍሪካ የኢትዮጵያ ኮኮቦች” በሚል ርዕሰ ትርዒቱን ፓሪስ በፊኔክስ መድረክ፣ እንዲሁም በቤልጅዬም፣ በሞናኮ ሞንቴካርሎ፣ በስዊዘርላንና በአንዶራ የሀገራችን ኢትዮጵያን ባህል፣አለባበስ፣ ሙዚቃና ጭፈራ ያካተተ ሙሉ የሰርከስ ትርኢት የያዘ ቡድን ከህዳር 04 ቀን 2017 ዓ/ም ጀምሮ ወደ ፈረንሳይ ሊጓዝ መሆኑን አፍሪካን ድሪም አርትስ እና አፍሪካን ድሪም ሰርከስ ዛሬ ጥቅምት 28 ቀን 2017ዓ/ም በቱሊፕ ኢን ኦሎምፒያ ሆቴል በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ አስታውቋል፡፡

አዘጋጆቹ ይህ ትርዒት በኢትዮጵያ የመጀመሪያ የሚሆን የሰርከስ፣ የዉዝዋዜና የሙዚቃ ባለሙያ የሚሳተፉበት ትልቅ ትርዒት መሆኑን በመግለጫው ተናግረዋል፡፡

አፍሪካን ድሪም አርትስ እና አፍሪካን ድሪም ሰርከስ በተለያዩ አለም አቀፍ ፌስቲቫሎች ላይ አርቲስቶችን በማሳተፍ የወርቅ የብር የነሃስ እና ስፔሻል ፕራይዝ ተሸላሚዎች እንዲሆኑ እና  የሀገርን ሰንደቅ አላማ ከፍ በማድረግ መልካም ገፅታዋን በመገንባት ሰርከስ የሃገር የባህል አምባሳደር እንዲሆን ከፍተኛ አስተዋፅዖ  በማበርከት በተደጋጋሚ የወርልድ ጊኒየስ ሪከርድ በማስመዝገብ እና ለዓለም አቀፍ  የሠርከስ ካምፓኒዎች  በማቅረብ ለብዙ ኢትዮጵያዊያንና አፍሪካውያን የስራ እድል ማመቻቸት ችሏል፡፡ 

ለተጨማሪው: https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
📌የመጽሐፍ ዳሰሳና የኪነጥበብ ዝግጅት

በፍቅረ ተክለማርያም (አብየ በርሶማ) "ዘሔርሙ" እና "ሰባራ ጥላ" መጻሕፍት ላይ ዳሰሳ እንዲሁም የኪነጥበብ ዝግጅት የፊታችን ቅዳሜ ጥቅምት 30 ቀን 2017 ዓ.ም ከቀኑ 10:00 ጀምሮ በብሔራዊ ቤተመጻሕፍትና ቤተመዛግብት አገልግሎት አዳራሽ ውስጥ ይካሄዳል።

በዕለቱም ደራሲ ኃይለመኮለት መዋዕል፣ ሰርፀ ፍሬስብሃት፣አርቲስት ሐረግወይን አሰፋ እና ሌሎችም ይገኙበታል ተብሏል።

ለተጨማሪው: https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
📌"ሎሚ ተራ ተራ" መጽሐፍ ለንባብ በቃ

በገጣሚ ፋሲካው ጌታቸው የተዘጋጀው "ሎሚ ተራ ተራ" የተሰኘ የግጥም መጽሐፍ ከሰሞኑ ለአንባቢያን ቀርቧል።

"ሎሚ ተራ ተራ" መጽሐፍ በይዘት የግጥም መጽሐፍ ሲሆን በ152 ገፆች ተቀንብቦ በ350 የጀርባ ዋጋ ለአንባቢያን ይደርሳል ተብሏል።

አዲስ አበባ ውስጥ ይህንን መጽሐፍ ለማግኘት እነዚህን የስልክ መስመሮች 0944233603 ፣0989894675፣0909441907 ተጠቀሙ ተብላችኋል።

ለተጨማሪው: https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
📌"በከንፈረሽ በራፍ" መጽሐፍ ልዩ ዝግጅት

የገጣሚ ዮሐንስ ሞላ "በከንፈረሽ በራፍ" መጽሐፍ የማስፈረም፣ የጨዋታና ኪናዊ መሰናዶዎች የሚቀርቡበት ልዩ ዝግጅት ቅዳሜ ጥቅምት 30 ቀን 2017 ዓ.ም ከቀኑ 7:30 ጀምሮ አራት ኪሎ በሚገኘው ዋልያ መጻሕፍት ውስጥ ይካሄዳል ተብሏል።

በዚህ ልዩ መርሐግብር መጽሐፍ መግዛት ለማይችሉ 200 መጻሕፍት በሽልማት መልክ የቀረቡ ሲሆን በተጨማሪም ገጣሚያኑ መሐመድ እድሪስ፣መንበረማርያም ኃይሉ፣ ቴዎድሮስ ካሣ፣አበባ የሺጥላ፣ ባንቺአየሁ አሰፋ፣ተሾመ ብርሃኑ፣ ሲራክ ወንድሙ፣ደሳለኝ ቢተውና ሌሎችም የግጥም ስራዎቻቸውን ያቀርባሉ።

ለተጨማሪው: https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
📌"ነገረ መጻሕፍት" ቅዳሜ ይካሄዳል።

በዛጎል የመጻህፍት ባንክ የሚዘጋጀው "ነገረ መጻሕፍት" የመጻህፍት ውይይት የቦታ ለወጥ አድርጎ ነገ ቅዳሜ ጥቅምት 30  2017 ዓ.ም ከቀኑ 8:00 ጀምሮ ምኒልክ ሆስፒታል አካባቢ በሚገኘው "FSS" አዳራሽ ውስጥ ይካሄዳል።

በዚህ መሰናዶ ላይ  ጓድ ፋሲካ ሲደልል፣ እና ኮሎኔል መርሻ ወዳጆ ተጋባዥ እንግዶች ሲሆኑ ለውይይት የሚቀርቡ አብይ ርዕሰ ጉዳይ "የታኅሣሥ ግርግር(1953 ዓ.ም) እና የግንቦቱ መፈንቅለ መንግስት(1981 ዓ.ም) " ይሰኛል።የፕሮግራሙ አዘጋጅና አቅራቢ ደራሲ እንዳለጌታ ከበደ ነው።

ለተጨማሪው: https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
📌ወደ ቦሌ ከአርዲ ቬንቸሮች ጋር ይጓዙ!!

ኢትዮጵያ ውስጥ ካሉ ምርጥ የተፈጥሮ ቦታዎች አንዱ ወደሆነው ባሌና አካባቢው ከአርዲ ቬንቸሮች ጋር ይጓዙ።

Dinsho Park አዳር (Wild life)
ሐቤራ ፏፏቴ(Natural Attraction)
ጌሴ grassland
ጎባ ከተማ
ሳነቴ አምባ(wild life and the biggest plateau in Africa)
ቱሉ ዲምቱ (The second Highest point in Ethiopia)
ሪራ ቪሌጅ
ሀረና ጫካ አዳር(የዱር እንስሳት እና ከ1000 km Square በላይ የሚሸፍን Virgin Forest).....እና ሌሎች በርካታ ዉብ ስፍራዎች 😍

4 ቀን 3 ምሽት

ውስን ሰዎች ስለሚጓዙበት ምርጥዬ ሰዎች ቀድማችሁ ቦታ ይያዙ።

የስልክ አድራሻ:

+251984717207

+251933931106

Ads:
📌"አውደ ፋጎስ" የውይይት መድረክ እሁድ ይካሄዳል

49ኛው ዙር አውደ ፋጎስ የውይይት መድረክ እሁድ ይካሄዳል። በዚህኛው ዙር ኤደን አባተ "እውነቻ እና የድኅረ ዘመናዊነት ውጥን"" በሚል ርዕስ መነሻ ሀሳብ ታቀርባለች።ይህም ውይይት እሁድ ህዳር 1 2017 ዓ.ም ከቀኑ 8:00 ጀምሮ በብሔራዊ ቤተመዛግብት እና ቤተመጻሕፍት አግልግሎት (ወመዘክር) አዳራሽ ውስጥ ይካሄዳል።

ለተጨማሪው: https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
📌10ኛው የአፍሪካ ጨርቃጨርቅ እና ፋሽን ሳምንት!

በአፍሪካ ትልቁ የጨርቃጨርቅ እና ፋሽን ኢንዱስትሪ አውደርዕይ የሆነው "10ኛው የአፍሪካ የጨርቃጨርቅ እና ፋሽን ሳምንት" ከዛሬ አርብ ጥቅምት 29 እስከ ሰኞ ህዳር 2 ቀን 2017 ዓ.ም በአዲስ አበባ ስካይላይት ሆቴል መካሄድ ጀምሯል።

በ10ኛው የአፍሪካ የጨርቃጨርቅ እና ፋሽን ሳምንት የመክፈቻው ሥነሥርዓት ላይም የኢትዮጵያ ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር፣ የኢትዮጵያ ቱሪዝም ሚኒስቴር፣ የኢትዮጵያ ጨርቃጨርቅና አልባሳት አምራቾች ማህበር እንዲሁም የጀርመን ሁነት አዘጋጆችን ጨምሮ በርካታ እንግዶች ተገኝተዋል።

የአፍሪካ ጨርቃጨርቅ እና ፋሽን ሳምንት 10ኛ ዓመት ክብረ በዓሉን በማስመልከት በዝግጅቱ ላይ ዓለም አቀፍ ብራንዶችን፣ የኢንዱስትሪ መሪዎችን እና አዳዲስ ፈጣሪዎችን የሚያገናኝ አውደርዕይም እያካሄደ ይገኛል።

በዚህም አውደርዕይ ከ30 አገራት በላይ የተውጣጡ  ከ2 መቶ50 በላይ የፋሽን ፣ ጨርቃጨርቅ እና ቆዳ ኢንዱስትሪዎች ምርታቸውን የሚያቀርቡ ይሆናል።

በተጨማሪም ከ60 አገራት በላይ የሚመጡ ከ7ሺህ በላይ የንግድ አቀላጣፊዎች ይገኛሉም ተብሏል።

የአፍሪካ ጨርቃጨርቅ እና ፋሽን ሳምንት ከተመሠረተበት ጊዜ ጀምሮ በጨርቃጨርቅ ፣ በአልባሳት እና የቆዳ እሴት ሰንሰለቶች መካከል ንግድን በማመቻቸት በአህጉሪቱ የፋሽን መድረክ ሆኖ እንደቆየ ተገልጿል።

10ኛው የአፍሪካ ጨርቃጨርቅ እና ፋሽን ሳምንት ከዛሬ ጥቅምት 29 ጀምሮ እስከ ህዳር 02 ቀን ለአምስት ቀናት በስካይ ላይት ሆቴል የሚቆይ ነው ተብሏል።

ለተጨማሪው: https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
📌"ጠይም ጤዛ" መጽሐፍ ለንባብ በቃ

የጋዜጠኛና ገጣሚ ተሾመ ብርሃኑ "ጠይም ጤዛ" የተሰኘ ርዕስ የተሰጠው የግጥም መጽሐፍ ዛሬ ጥቅምት 29 ቀን 2017 ዓ.ም ለአንባቢያን ቀርቧል።

"ጠይም ጤዛ" መጽሐፍ ሐምሳ የግጥም ስራዎችን በውስጥ የያዘ ሲሆን 94 ገፆች ተቀንብቦ በ300 የጀርባ ዋጋ ለአንባቢያን ቀርቧል።

ተሾመ ብርሃኑ በማህበራዊ ትስስር ገፁ "እንሆ ጠይም ጤዛ ቤቷ ገብታለች። ዛሬ ከማተሚያ ቤት መደበኛ ህትመቶችን ተረክበናል። ልዩ ህትመቶን ቀድማችሁ የገዛችሁ በጣም በቅርቡ ባላችሁበት ከምስጋና ጋር እናደርሳለን።ነገ ቅዳሜ ጥቅምት 30 አራት ኪሎ ዋልያ መጻሕፍት ከቀን 7 ሰዓት ከ30 ጀምሮ መገኘት ለምትችሉ ከሌሎች ዕውቅ ደራሲያን ጋር እንጠብቃችኋለን። የጥበብ ውጤቶን እያጣጣማችሁ ጠይም ጤዛን በአካል ትወስዳላችሁ" ብሏል።

ጋዜጠኛና ገጣሚ ተሾመ ብርሃኑ ከዚህ ቀደም በ2011 ዓ.ም በሆሄ የሥነጽሑፍ ሽልማት ላይ የዓመቱ ምርጥ የግጥም መደብል አሸናፊ የሆነበት "ኮብላይ ዘመን" መጽሐፍን ለአንባቢያን አድርሷል።

በተጨማሪም በጀርመን ባህል ማዕከል (ጎተ)አወዳዳሪነት ከተለያዩ ደራሲዎች ጋር በጋራ በተሰናዳው "ሠላሳዎቹ" የአጫጭር ልቦለዶች ስብስብ መጽሐፍ ውስጥም ስራው ታትሞለታል።

ለተጨማሪው: https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
📌"የእድሜ ልክ" የሥዕል አውደርዕይ ዛሬ ይከፈታል።

"የእድሜ ልክ" የተሰኘ የሥዕል አውደርዕይ ለእይታ ሊበቃ ነው። የሠዓሊ ሚኪያስ አሰፋ "የእድሜ ልክ" የተሰኘ ርዕስ የተሰጠው የሥዕል አውደርዕይ ዛሬ ቅዳሜ ጥቅምት 30 ቀን 2017 ዓ.ም ቦሌ ማተሚያ አካባቢ በሚገኘው ለማ ጉያ የሥነጥበብ ማሳያ ውስጥ ለእይታ ይበቃል። ይሄም የሥዕል አውደርዕይ እስከ ህዳር 13 ቀን 2017 ዓ.ም ድረስ ይቆያል ተብሏል።

ለተጨማሪው: https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
📌"የእግዜር ጣት" ተውኔት ነገ ለእይታ ይበቃል

በአንጋፋው ከያኒ ጌትነት እንየው ተደርሶ በዘካርያስ ረታ የተዘጋጀው "የእግዜር ጣት" የተሰኘ ተውኔት ነገ እሁድ ህዳር 1 ቀን 2017 ዓ.ም ከ10:00 ጀምሮ ፒያሳ አራዳ ፖስታ ቤት ግቢ ውስጥ በሚገኘው በክቡር ዶ/ር ተስፋዬ አበበ(ፋዘር ) የኪነ-ጥበባት ማዕከል ውስጥ በእይታ ይበቃል።

በተውኔቱ ላይ አላዶር ሽፈራው፣ዳግማዊ የኔዓለም፣ልዑል አስፋው፣ሔኖክ ጥላሁን፣ሰላማዊት ታሪኩ ተውነውበታል።

ለተጨማሪው: https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
📌የድምጻዊ ሚካኤል በላይነህ አልበም ዛሬ ይመረቃል

የድምጻዊ ሚካኤል በላይነህ "አንድ ቃል" አልበም ዛሬ ቅዳሜ ጥቅምት 30 ቀን  2017 ዓ.ም በማርዮት ሆቴል ውስጥ ይመረቃል ተብሏል።

በዚህ የሙዚቃ አልበም ምርቃት ድግስ ሌሎችም የሙዚቃ ባለሞያዎች ስራዎቻቸውን ያቀርባሉ።

ድምጻዊ ሚካኤል በላይነህ በማህበራዊ ትስስር ገጹ" ወዳጆቼ አዲሱን ‘አንድ ቃል’ አልበሜን ቅዳሜ ጥቅምት 30 በማርዮት ሆቴል እንደማስመርቅ ስነግራችሁ በልዩ ደስታ ነው" ብሏል።

ለተጨማሪው: https://news.1rj.ru/str/EventAddis1