Event Addis Media – Telegram
Event Addis Media
9.61K subscribers
6.11K photos
13 videos
4 files
4.73K links
Connect with Addis artistic community!

Website: https://eventaddis.com

Contact: @Tmanaye
Download Telegram
📌"ሎሚ ተራ ተራ" መጽሐፍ ለንባብ በቃ

በገጣሚ ፋሲካው ጌታቸው የተዘጋጀው "ሎሚ ተራ ተራ" የተሰኘ የግጥም መጽሐፍ ከሰሞኑ ለአንባቢያን ቀርቧል።

"ሎሚ ተራ ተራ" መጽሐፍ በይዘት የግጥም መጽሐፍ ሲሆን በ152 ገፆች ተቀንብቦ በ350 የጀርባ ዋጋ ለአንባቢያን ይደርሳል ተብሏል።

አዲስ አበባ ውስጥ ይህንን መጽሐፍ ለማግኘት እነዚህን የስልክ መስመሮች 0944233603 ፣0989894675፣0909441907 ተጠቀሙ ተብላችኋል።

ለተጨማሪው: https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
📌"በከንፈረሽ በራፍ" መጽሐፍ ልዩ ዝግጅት

የገጣሚ ዮሐንስ ሞላ "በከንፈረሽ በራፍ" መጽሐፍ የማስፈረም፣ የጨዋታና ኪናዊ መሰናዶዎች የሚቀርቡበት ልዩ ዝግጅት ቅዳሜ ጥቅምት 30 ቀን 2017 ዓ.ም ከቀኑ 7:30 ጀምሮ አራት ኪሎ በሚገኘው ዋልያ መጻሕፍት ውስጥ ይካሄዳል ተብሏል።

በዚህ ልዩ መርሐግብር መጽሐፍ መግዛት ለማይችሉ 200 መጻሕፍት በሽልማት መልክ የቀረቡ ሲሆን በተጨማሪም ገጣሚያኑ መሐመድ እድሪስ፣መንበረማርያም ኃይሉ፣ ቴዎድሮስ ካሣ፣አበባ የሺጥላ፣ ባንቺአየሁ አሰፋ፣ተሾመ ብርሃኑ፣ ሲራክ ወንድሙ፣ደሳለኝ ቢተውና ሌሎችም የግጥም ስራዎቻቸውን ያቀርባሉ።

ለተጨማሪው: https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
📌"ነገረ መጻሕፍት" ቅዳሜ ይካሄዳል።

በዛጎል የመጻህፍት ባንክ የሚዘጋጀው "ነገረ መጻሕፍት" የመጻህፍት ውይይት የቦታ ለወጥ አድርጎ ነገ ቅዳሜ ጥቅምት 30  2017 ዓ.ም ከቀኑ 8:00 ጀምሮ ምኒልክ ሆስፒታል አካባቢ በሚገኘው "FSS" አዳራሽ ውስጥ ይካሄዳል።

በዚህ መሰናዶ ላይ  ጓድ ፋሲካ ሲደልል፣ እና ኮሎኔል መርሻ ወዳጆ ተጋባዥ እንግዶች ሲሆኑ ለውይይት የሚቀርቡ አብይ ርዕሰ ጉዳይ "የታኅሣሥ ግርግር(1953 ዓ.ም) እና የግንቦቱ መፈንቅለ መንግስት(1981 ዓ.ም) " ይሰኛል።የፕሮግራሙ አዘጋጅና አቅራቢ ደራሲ እንዳለጌታ ከበደ ነው።

ለተጨማሪው: https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
📌ወደ ቦሌ ከአርዲ ቬንቸሮች ጋር ይጓዙ!!

ኢትዮጵያ ውስጥ ካሉ ምርጥ የተፈጥሮ ቦታዎች አንዱ ወደሆነው ባሌና አካባቢው ከአርዲ ቬንቸሮች ጋር ይጓዙ።

Dinsho Park አዳር (Wild life)
ሐቤራ ፏፏቴ(Natural Attraction)
ጌሴ grassland
ጎባ ከተማ
ሳነቴ አምባ(wild life and the biggest plateau in Africa)
ቱሉ ዲምቱ (The second Highest point in Ethiopia)
ሪራ ቪሌጅ
ሀረና ጫካ አዳር(የዱር እንስሳት እና ከ1000 km Square በላይ የሚሸፍን Virgin Forest).....እና ሌሎች በርካታ ዉብ ስፍራዎች 😍

4 ቀን 3 ምሽት

ውስን ሰዎች ስለሚጓዙበት ምርጥዬ ሰዎች ቀድማችሁ ቦታ ይያዙ።

የስልክ አድራሻ:

+251984717207

+251933931106

Ads:
📌"አውደ ፋጎስ" የውይይት መድረክ እሁድ ይካሄዳል

49ኛው ዙር አውደ ፋጎስ የውይይት መድረክ እሁድ ይካሄዳል። በዚህኛው ዙር ኤደን አባተ "እውነቻ እና የድኅረ ዘመናዊነት ውጥን"" በሚል ርዕስ መነሻ ሀሳብ ታቀርባለች።ይህም ውይይት እሁድ ህዳር 1 2017 ዓ.ም ከቀኑ 8:00 ጀምሮ በብሔራዊ ቤተመዛግብት እና ቤተመጻሕፍት አግልግሎት (ወመዘክር) አዳራሽ ውስጥ ይካሄዳል።

ለተጨማሪው: https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
📌10ኛው የአፍሪካ ጨርቃጨርቅ እና ፋሽን ሳምንት!

በአፍሪካ ትልቁ የጨርቃጨርቅ እና ፋሽን ኢንዱስትሪ አውደርዕይ የሆነው "10ኛው የአፍሪካ የጨርቃጨርቅ እና ፋሽን ሳምንት" ከዛሬ አርብ ጥቅምት 29 እስከ ሰኞ ህዳር 2 ቀን 2017 ዓ.ም በአዲስ አበባ ስካይላይት ሆቴል መካሄድ ጀምሯል።

በ10ኛው የአፍሪካ የጨርቃጨርቅ እና ፋሽን ሳምንት የመክፈቻው ሥነሥርዓት ላይም የኢትዮጵያ ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር፣ የኢትዮጵያ ቱሪዝም ሚኒስቴር፣ የኢትዮጵያ ጨርቃጨርቅና አልባሳት አምራቾች ማህበር እንዲሁም የጀርመን ሁነት አዘጋጆችን ጨምሮ በርካታ እንግዶች ተገኝተዋል።

የአፍሪካ ጨርቃጨርቅ እና ፋሽን ሳምንት 10ኛ ዓመት ክብረ በዓሉን በማስመልከት በዝግጅቱ ላይ ዓለም አቀፍ ብራንዶችን፣ የኢንዱስትሪ መሪዎችን እና አዳዲስ ፈጣሪዎችን የሚያገናኝ አውደርዕይም እያካሄደ ይገኛል።

በዚህም አውደርዕይ ከ30 አገራት በላይ የተውጣጡ  ከ2 መቶ50 በላይ የፋሽን ፣ ጨርቃጨርቅ እና ቆዳ ኢንዱስትሪዎች ምርታቸውን የሚያቀርቡ ይሆናል።

በተጨማሪም ከ60 አገራት በላይ የሚመጡ ከ7ሺህ በላይ የንግድ አቀላጣፊዎች ይገኛሉም ተብሏል።

የአፍሪካ ጨርቃጨርቅ እና ፋሽን ሳምንት ከተመሠረተበት ጊዜ ጀምሮ በጨርቃጨርቅ ፣ በአልባሳት እና የቆዳ እሴት ሰንሰለቶች መካከል ንግድን በማመቻቸት በአህጉሪቱ የፋሽን መድረክ ሆኖ እንደቆየ ተገልጿል።

10ኛው የአፍሪካ ጨርቃጨርቅ እና ፋሽን ሳምንት ከዛሬ ጥቅምት 29 ጀምሮ እስከ ህዳር 02 ቀን ለአምስት ቀናት በስካይ ላይት ሆቴል የሚቆይ ነው ተብሏል።

ለተጨማሪው: https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
📌"ጠይም ጤዛ" መጽሐፍ ለንባብ በቃ

የጋዜጠኛና ገጣሚ ተሾመ ብርሃኑ "ጠይም ጤዛ" የተሰኘ ርዕስ የተሰጠው የግጥም መጽሐፍ ዛሬ ጥቅምት 29 ቀን 2017 ዓ.ም ለአንባቢያን ቀርቧል።

"ጠይም ጤዛ" መጽሐፍ ሐምሳ የግጥም ስራዎችን በውስጥ የያዘ ሲሆን 94 ገፆች ተቀንብቦ በ300 የጀርባ ዋጋ ለአንባቢያን ቀርቧል።

ተሾመ ብርሃኑ በማህበራዊ ትስስር ገፁ "እንሆ ጠይም ጤዛ ቤቷ ገብታለች። ዛሬ ከማተሚያ ቤት መደበኛ ህትመቶችን ተረክበናል። ልዩ ህትመቶን ቀድማችሁ የገዛችሁ በጣም በቅርቡ ባላችሁበት ከምስጋና ጋር እናደርሳለን።ነገ ቅዳሜ ጥቅምት 30 አራት ኪሎ ዋልያ መጻሕፍት ከቀን 7 ሰዓት ከ30 ጀምሮ መገኘት ለምትችሉ ከሌሎች ዕውቅ ደራሲያን ጋር እንጠብቃችኋለን። የጥበብ ውጤቶን እያጣጣማችሁ ጠይም ጤዛን በአካል ትወስዳላችሁ" ብሏል።

ጋዜጠኛና ገጣሚ ተሾመ ብርሃኑ ከዚህ ቀደም በ2011 ዓ.ም በሆሄ የሥነጽሑፍ ሽልማት ላይ የዓመቱ ምርጥ የግጥም መደብል አሸናፊ የሆነበት "ኮብላይ ዘመን" መጽሐፍን ለአንባቢያን አድርሷል።

በተጨማሪም በጀርመን ባህል ማዕከል (ጎተ)አወዳዳሪነት ከተለያዩ ደራሲዎች ጋር በጋራ በተሰናዳው "ሠላሳዎቹ" የአጫጭር ልቦለዶች ስብስብ መጽሐፍ ውስጥም ስራው ታትሞለታል።

ለተጨማሪው: https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
📌"የእድሜ ልክ" የሥዕል አውደርዕይ ዛሬ ይከፈታል።

"የእድሜ ልክ" የተሰኘ የሥዕል አውደርዕይ ለእይታ ሊበቃ ነው። የሠዓሊ ሚኪያስ አሰፋ "የእድሜ ልክ" የተሰኘ ርዕስ የተሰጠው የሥዕል አውደርዕይ ዛሬ ቅዳሜ ጥቅምት 30 ቀን 2017 ዓ.ም ቦሌ ማተሚያ አካባቢ በሚገኘው ለማ ጉያ የሥነጥበብ ማሳያ ውስጥ ለእይታ ይበቃል። ይሄም የሥዕል አውደርዕይ እስከ ህዳር 13 ቀን 2017 ዓ.ም ድረስ ይቆያል ተብሏል።

ለተጨማሪው: https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
📌"የእግዜር ጣት" ተውኔት ነገ ለእይታ ይበቃል

በአንጋፋው ከያኒ ጌትነት እንየው ተደርሶ በዘካርያስ ረታ የተዘጋጀው "የእግዜር ጣት" የተሰኘ ተውኔት ነገ እሁድ ህዳር 1 ቀን 2017 ዓ.ም ከ10:00 ጀምሮ ፒያሳ አራዳ ፖስታ ቤት ግቢ ውስጥ በሚገኘው በክቡር ዶ/ር ተስፋዬ አበበ(ፋዘር ) የኪነ-ጥበባት ማዕከል ውስጥ በእይታ ይበቃል።

በተውኔቱ ላይ አላዶር ሽፈራው፣ዳግማዊ የኔዓለም፣ልዑል አስፋው፣ሔኖክ ጥላሁን፣ሰላማዊት ታሪኩ ተውነውበታል።

ለተጨማሪው: https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
📌የድምጻዊ ሚካኤል በላይነህ አልበም ዛሬ ይመረቃል

የድምጻዊ ሚካኤል በላይነህ "አንድ ቃል" አልበም ዛሬ ቅዳሜ ጥቅምት 30 ቀን  2017 ዓ.ም በማርዮት ሆቴል ውስጥ ይመረቃል ተብሏል።

በዚህ የሙዚቃ አልበም ምርቃት ድግስ ሌሎችም የሙዚቃ ባለሞያዎች ስራዎቻቸውን ያቀርባሉ።

ድምጻዊ ሚካኤል በላይነህ በማህበራዊ ትስስር ገጹ" ወዳጆቼ አዲሱን ‘አንድ ቃል’ አልበሜን ቅዳሜ ጥቅምት 30 በማርዮት ሆቴል እንደማስመርቅ ስነግራችሁ በልዩ ደስታ ነው" ብሏል።

ለተጨማሪው: https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
📌መቅረዝ ሥነኪን የኪነጥበብ ዝግጅት ሐሙስ ይካሄዳል

ተወዳጇ አርቲስት ህሊና ሲሳይ የክብር እንግዳ የሆነችበት"መቅረዝ ሥነኪን" የኪነጥበብ ዝግጅት ሀሙስ ይካሄዳል።

አንጋፋ እና ወጣት የኪነጥበብ ባለሞያዎችን እያጣመር የዘለቀው መቅረዝ ሥነኪን ወርሀዊ የኪነጥበብ  ዝግጅት ሐሙስ ህዳር 5 ቀን 2017 ዓ.ም ከምሽቱ 11:00 ጀምሮ በብሔራዊ ቤተመዛግብትና ቤተመጻሕፍት አገልግሎት (ወመዘክር )አዳራሽ ውስጥ ይካሄዳል።

በዚህ ዝግጅት ላይ ተወዳጇ አርቲስት ህሊና ሲሳይ የክብር እንግዳ በመሆን የሚገኙ ሲሆን በተጨማሪም ወጣት የኪነጥበብ ባለሞያዎች የግጥም ፣የሙዚቃ እና የዳንስ ስራዎቻቸውን ያቀርባሉ።

የዚህ ዝግጅት መግቢያ በነፃ ነው።

ለተጨማሪው :https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
📌"እንዴት ልሁን" ፊልም ለእይታ ሊበቃ ነው

በቅድስት ፊልም ፕሮዳክሽን ተዘጋጅቶ በኤልያና ኢንተርቴይመንት የቀረበው "እንዴት ልሁን" የተሰኘ ርዕስ የተሰጠው ፊልም ከሕዳር 6 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ በተለያዩ ሲኒማ ቤቶች ለእይታ እንደሚበቃ ኤቨንት አዲስ ድረገፅ ያገኘው መረጃ ያመለክታል።

የ"እንዴት ልሁን" ፊልም ደራሲ እና ዳይሬክተር ዮሴፍ ቸሩ (ጆሲ) ነው።በፊልሙ ላይ እንግዳሰው ሀብቴ፣ሳምሶን ግርማ፣ህይወት ጌታሁን፣ቴዎድሮስ ወዳጆ እና ሌሎችም በትወና ተሳትፈውበታል።

ለተጨማሪው :https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
📌የገጣሚ ባንቺአየሁ አሰፋ መጽሐፍ አርብ ይመረቃል

የወጣቷ ገጣሚ ባንቺአየሁ አሰፋ አሊ "ላልዪበላይቱ" የተሰኘ ርዕስ የተሰጠው አዲስ የግጥም መጽሐፍ የፊታችን አርብ ሕዳር 6 2017 ዓ.ም ከምሽቱ 11:00 ጀምሮ በብሔራዊ ቤተመዛግብት እና ቤተመጻሕፍት አገልግሎት (ወመዘክር )አዳራሽ ውስጥ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት በድምቀት ይመረቃል።

በዕለቱም ደራሲ ኃይለመለኮት መዋዕል፣ መምህር የሻው ተሰማ፣ ገጣሚ ዮሐንስ ሞላ፣ገጣሚ አበባ የሺጥላ፣ገጣሚ መንበረማርያም ኃይሉ፣ ገጣሚ ዲበኩሉ ጌታ፣ገጣሚ ሰይፉ ወርቁ፣ ገጣሚ ቴዎድሮስ ካሣ፣ገጣሚ ፌቤን ፋንጮ፣ ደራሲ ቢንያም አቡራ ፤ድምጻዊ አብርሐም ኸይሩ የሥነጽሑፋዊ ስራዎቻቸውንና ሀሳቦቻቸውን ያጋራሉ ተብሏል።

ገጣሚ ባንቺአየሁ አሰፋ አሊ ከገጣሚነቷ ባሻገር በአራዳ ኤፍ ኤም 95.1 በጋዜጠኝነት እየሰራች ትገኛለች።

ለተጨማሪው :https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
📌የኢትዮጵያ ኪነጥበብ ባለሙያዎች ከባህልና ስፖርት ሚኒስቴር ጋር ውይይት አካሄዱ

የኢትዮጵያ ኪነጥበብ ባለሙያዎች ከባህልና ስፖርት ሚኒስቴር ጋር "ኪነ ጥበብ፣ ሥነ ጥበብ ለሁለንተናዊ ልማትና ለሃገረ መንግሥት ግንባታ" በሚል መሪ ሀሳብ ዛሬ ህዳር 3 ቀን 2017 ዓ.ም በሃይሌ ግራንድ ሆቴል አካሄደዋል።

የባህልና ስፖርት ሚንስቴር - ሚንስትር ክብርት ሸዊት ሻንካ እና ሚንስትር ዲኤታዋ ክብርት ነፊሳ አልማሃዲ በመሩት መድረክ ላይ፣ መንግሥት እና ሚንስቴር መስርያ ቤታቸው ከመቼውም ጊዜ በበለጠ ሁኔታ  ተቀራርቦ ለመስራት ያላቸውን ፅኑ ፍላጎት ገልፀዋል።

የጥበብ ባለሙያዎቹ በበኩላቸው ያሉባቸውን ችግሮች አስረድተዋል። ከተሳታፊ  ባለሙያዎቹም  መካከል ተግዳሮቶችን ብቻ ሳይቆጥሩ በተቻለ መጠን ለሃገርና ለህዝብ ጥቅም መሥራት እንደሚገባ ተናግረዋል።

ሚንስቴር መሥርያ ቤቱ ይህንን መድረክ አዘጋጅቶ <<ኑ - እንማከር>> ማለቱ ከባለሙያዎቹ ልዩ ምሥጋና ተችሮታል። ግንኙነቱ ተጠናክሮ እንደሚቀጥልና በሃገር ግንባታው ረገድ መልካም ውጤት እንደሚያስገኝ ታምኖበታል።

ለተጨማሪው: https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
📌ለአርባምንጭ ዓለምአቀፍ ስቴዲየም የገቢ ማሰባሰቢያ ትላልቅ ሁነቶች ሊካሄዱ ነው።

በአርባምንጭ ከተማ የሚገነባውን ዓለም አቀፍ ስቴዲየም የገቢ ማሰባቢያ በማስመልከት ትላልቅ ሁነቶች ሊካሄዱ እንደሆነ አዘጋጆች አስታውቀዋል።

ዛሬ የገቢ አሰባሳቢ ኮሚቴው ከእሺ ሚዲያ እና ኮሙኒኬሽን ጋር አብሮ ለመስራት ስምምነት አድረገዋል። እሺ ሚዲያ ለዚህ ስታዲየም ግንባታ ቁልፍ የገንዘብ ማሰባሰቢያ እቅዶቹን ይፋ ያደረገ ሲሆን ዝግጅቱን በሀገር ውስጥ ሬዲዮ፣ ቲቪ ጣቢያዎች፣ ጋዜጦች በስፋት እንዲሰራጭ በማድረግ ማህበረሰቡን በማሳወቅ ይጀመራል ተብሏል።

ዲጂታል ዘመቻዎች፣ አምባሳደሮች ታዋቂ/ተፀእኖ ፈጣሪ ግለሰቦችን በአምባሳደርነት በመሰየም ፕሮጀክቱን እንደያስተዋውቁ ማድረግ፣ በቀጥታ ስርጭት የሚከናወን የገቢ ማሰባሰቢያ ዝግጅት፣ ስፖንሰርሺፕ፣ የሩጫ ውድድር፣ የእግር ኳስ ግጥሚያ፣ ኮንሰርት፣ ቶምቦላ ሎተሪ፣ በመዋጮና በልገሳዎች ገቢ ማሰባሰብ እንደታሰበ ተነግሯል።

የአፍሪካ ዋንጫ እና የአለም አቀፍ ማጣሪያ ጨዋታዎችን ማስተናገድ የሚችል እንደሆነ የተነገረለት ይህ ስቴዲየም 30ሺ ተመልካች የመያዝ አቅም እንዳለው ተገልጿል።  እንዲሁም የመሮጫ ትራክ ስላለው የአትሌቲክስ ውድድሮችን ማስተናገድ ይችላል።

የካፍ ስታንዳርድ የሚያሟላ ካታጎሪ ሶስት ውስጥ የሚገኝ ሲሆን እስከ 30ሺ ተመልካች ማስተናገድ የሚችል ስቴዲየም መሆኑ ተገልጿል።

አጠቃላይ የስቴዲየሙ ግንባታ ወጪ 3 ቢሊዮን ብር ሲሆን የመጀመሪያ ዙር ስራ 6 ወር እና ቀጣይ ሁለተኛ ዙር ምዕራፍ በ6 ወር በአጠቃላይ በአንድ አመት ለማጠናቀቅ ታቅዷል።

ለተጨማሪው: https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
📌የጋዜጠኛ መኮንን ወ/አረጋይ "እነሆ ማሟሻ" መጽሐፍ ሊመረቅ ነው

የጋዜጠኛ መኮንን ወ/አረጋይ በርካታ ጉዳዮች የተካተቱበት እነሆ ማሟሻ" ቅጽ አንድ እና ቅጽ ሁለት መጻሕፍት ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት ቅዳሜ ሕዳር 14 2017 ዓ.ም ከቀኑ 8:00 ጀምሮ ቴዎድሮስ አደባባይ አካባቢ በሚገኘው በኤን ቢሲ ኢትዮጵያ ስቱዲዮ ሁለት(በተለምዶው ሴጣን ቤት) አዳራሽ ውስጥ ይመረቃል።

በዚህ የመጽሐፍ ምርቃት ሥነሥርዓት ላይም አንጋፋ እና ወጣት የመገናኛ ብዙሃን ባለሞያዎች ሀሳቦቻቸውን ያጋራሉ ተብሏል።

ከዚህ ቀደም በሸገር ኤፍ ኤም 102.1 ሬድዮ ላይ በሚያቀርባቸው የስንክሳር፣  የማሟሻ፣ የሃኪሞ መልዕክት፣ የአርብ ምሽት ቆየት ያሉ ሙዚቃዎች እና አሁን ላይ በኢንቢሲ ቴሌቪዥን በልዩ ልዩ ዝግጅቶች የምናውቀው ጋዜጠኛ መኮንን ወ/አረጋይ "እነሆ ማሟሻ" የተሰኘ የመጀመሪያ ቅጽ አንድ እና ተከታዩን ሁለት መጻህፍትን በተከታታይ ከወራት በፊት ለአንባቢያን ማድረሱ ይታወሳል።

ለተጨማሪው: https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
📌የሔለን ሾው ኢምፓወር አዲስ

የሔለን ሾው ኢምፓወር አዲስ ለሁሉም የኅብረተሰብ ክፍል የሚሆን የቢዝነስ፣ የሥራ ፈጠራ፣ ትምህርት፣ የጤናና ማኅበራዊ ጉዳዮች ልዩ ዝግጅት ፊታችን ቅዳሜና እሁድ ኅዳር 7 እና 8 ቀን 2017 ዓ.ም  ለሁለት ተከታታይ ቀናት በሚሊኒየም አዳራሽ ይካሄዳል።

ለተጨማሪው: https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
📌የሥዕል አውደርዕይ

የሠዓሊ እስጢፋኖስ ሰለሞን "Oppressed passion" የተሰኘ ርዕስ የተሰጠው የሥዕል አውደርዕይ ሕዳር 7 ቀን 2017 ዓ.ም በአርታዊ የሥዕል ማሳያ ውስጥ ለእይታ ይበቃል።ይሄ የሥዕል አውደርዕይ እስከ ሕዳር 29 ይቆያል ተብሏል።

ለተጨማሪው: https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
📌"የመንገዴ መንገድ" መጽሐፍ ለንባብ በቃ

የገጣሚ ደጀኔ ተስፋዬ "የመንገዴ መንገድ" የተሰኘ ርዕስ የተሰጠው አዲስ የግጥም መጽሐፍ ትላንት ማክሰኞ ሕዳር 3 ቀን 2017 ዓ.ም ለንባብ በቅቷል።

"የመንገዴ መንገድ" መጽሐፍ በይዘት የግጥም ስብስብ መጽሐፍ ሲሆን በ114 ገፆች ተቀንብቦ በ320 ብር የጀርባ ዋጋ ለአንባቢያን ቀርቧል።

መጽሐፉን በፒያሳ ኤዞፕ በሜክሲኮ ጃዕፋር እና በአራት ኪሎው ኢትዮ ፋጎስ (Ethio Fagos) የመጽሐፍ ማከፋፈያዎች ውስጥ ይገኛል።

ለተጨማሪው: https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
📌ድምጻዊት ራሔል ጌቱ ከዳይሬክተር ቅድስት ይልማ ጋር "ውዴ" በተሰኘ ሙዚቃ ድጋሚ ተጣምሩ

ከዚህ ቀደም "ኢትዮጵያዊዬ" የተሰኘ ርዕስ በተሰጠው የሙዚቃ ቪዲዮ አብረው የሰሩት ድምጻዊት ራሔል ጌቱ እና ዳይሬክተር ቅድስት ይልማ "ውዴ" በተሰኘ አዲስ ሙዚቃ በድጋሚ እንደተጣመሩ ኤቨንት አዲስ ሚዲያ ሰምቷል።

የድምጻዊት ራሔል ጌቱ"ውዴ" ሙዚቃ ነገ አርብ ሕዳር 6 ቀን 2017 ዓ.ም ለአድማጮች ይደርሳል ተብሏል።

ለተጨማሪው: https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
📌ኮሜዲያን ደረጄ ኃይሌ የክብር እንግዳ የሆነበት ስብሐቲዝም የሀሳብ ውይይት ዝግጅት እሁድ ይካሄዳል።

ኮሜዲያን ደረጄ ኃይሌ የክብር እንግዳ የሆነበት ስብሐቲዝም 78ተኛ መድረክ "የኮሜዲው ዓለም ከሳቅ ባሻገር" በሚል የሀሳብ ውይይት ይካሄዳል።

ውይይቱ እሁድ ሕዳር 8 ቀን 2017 ዓ.ም  ከቀኑ 8:00 ጀምሮ በብሔራዊ ቤተመዛግብት እና ቤተመጻሕፍት አገልግሎት (ወመዘክር) አዳራሽ ውስጥ ይከናወናል።

ለተጨማሪው: https://news.1rj.ru/str/EventAddis1