📌"እንዴት ልሁን" ፊልም ለእይታ ሊበቃ ነው
በቅድስት ፊልም ፕሮዳክሽን ተዘጋጅቶ በኤልያና ኢንተርቴይመንት የቀረበው "እንዴት ልሁን" የተሰኘ ርዕስ የተሰጠው ፊልም ከሕዳር 6 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ በተለያዩ ሲኒማ ቤቶች ለእይታ እንደሚበቃ ኤቨንት አዲስ ድረገፅ ያገኘው መረጃ ያመለክታል።
የ"እንዴት ልሁን" ፊልም ደራሲ እና ዳይሬክተር ዮሴፍ ቸሩ (ጆሲ) ነው።በፊልሙ ላይ እንግዳሰው ሀብቴ፣ሳምሶን ግርማ፣ህይወት ጌታሁን፣ቴዎድሮስ ወዳጆ እና ሌሎችም በትወና ተሳትፈውበታል።
ለተጨማሪው :https://news.1rj.ru/str/EventAddis1

📌የገጣሚ ባንቺአየሁ አሰፋ መጽሐፍ አርብ ይመረቃል
የወጣቷ ገጣሚ ባንቺአየሁ አሰፋ አሊ "ላልዪበላይቱ" የተሰኘ ርዕስ የተሰጠው አዲስ የግጥም መጽሐፍ የፊታችን አርብ ሕዳር 6 2017 ዓ.ም ከምሽቱ 11:00 ጀምሮ በብሔራዊ ቤተመዛግብት እና ቤተመጻሕፍት አገልግሎት (ወመዘክር )አዳራሽ ውስጥ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት በድምቀት ይመረቃል።
በዕለቱም ደራሲ ኃይለመለኮት መዋዕል፣ መምህር የሻው ተሰማ፣ ገጣሚ ዮሐንስ ሞላ፣ገጣሚ አበባ የሺጥላ፣ገጣሚ መንበረማርያም ኃይሉ፣ ገጣሚ ዲበኩሉ ጌታ፣ገጣሚ ሰይፉ ወርቁ፣ ገጣሚ ቴዎድሮስ ካሣ፣ገጣሚ ፌቤን ፋንጮ፣ ደራሲ ቢንያም አቡራ ፤ድምጻዊ አብርሐም ኸይሩ የሥነጽሑፋዊ ስራዎቻቸውንና ሀሳቦቻቸውን ያጋራሉ ተብሏል።
ገጣሚ ባንቺአየሁ አሰፋ አሊ ከገጣሚነቷ ባሻገር በአራዳ ኤፍ ኤም 95.1 በጋዜጠኝነት እየሰራች ትገኛለች።

📌የኢትዮጵያ ኪነጥበብ ባለሙያዎች ከባህልና ስፖርት ሚኒስቴር ጋር ውይይት አካሄዱ
የኢትዮጵያ ኪነጥበብ ባለሙያዎች ከባህልና ስፖርት ሚኒስቴር ጋር "ኪነ ጥበብ፣ ሥነ ጥበብ ለሁለንተናዊ ልማትና ለሃገረ መንግሥት ግንባታ" በሚል መሪ ሀሳብ ዛሬ ህዳር 3 ቀን 2017 ዓ.ም በሃይሌ ግራንድ ሆቴል አካሄደዋል።
የባህልና ስፖርት ሚንስቴር - ሚንስትር ክብርት ሸዊት ሻንካ እና ሚንስትር ዲኤታዋ ክብርት ነፊሳ አልማሃዲ በመሩት መድረክ ላይ፣ መንግሥት እና ሚንስቴር መስርያ ቤታቸው ከመቼውም ጊዜ በበለጠ ሁኔታ ተቀራርቦ ለመስራት ያላቸውን ፅኑ ፍላጎት ገልፀዋል።
የጥበብ ባለሙያዎቹ በበኩላቸው ያሉባቸውን ችግሮች አስረድተዋል። ከተሳታፊ ባለሙያዎቹም መካከል ተግዳሮቶችን ብቻ ሳይቆጥሩ በተቻለ መጠን ለሃገርና ለህዝብ ጥቅም መሥራት እንደሚገባ ተናግረዋል።
ሚንስቴር መሥርያ ቤቱ ይህንን መድረክ አዘጋጅቶ <<ኑ - እንማከር>> ማለቱ ከባለሙያዎቹ ልዩ ምሥጋና ተችሮታል። ግንኙነቱ ተጠናክሮ እንደሚቀጥልና በሃገር ግንባታው ረገድ መልካም ውጤት እንደሚያስገኝ ታምኖበታል።
ለተጨማሪው: https://news.1rj.ru/str/EventAddis1

📌ለአርባምንጭ ዓለምአቀፍ ስቴዲየም የገቢ ማሰባሰቢያ ትላልቅ ሁነቶች ሊካሄዱ ነው።
በአርባምንጭ ከተማ የሚገነባውን ዓለም አቀፍ ስቴዲየም የገቢ ማሰባቢያ በማስመልከት ትላልቅ ሁነቶች ሊካሄዱ እንደሆነ አዘጋጆች አስታውቀዋል።
ዛሬ የገቢ አሰባሳቢ ኮሚቴው ከእሺ ሚዲያ እና ኮሙኒኬሽን ጋር አብሮ ለመስራት ስምምነት አድረገዋል። እሺ ሚዲያ ለዚህ ስታዲየም ግንባታ ቁልፍ የገንዘብ ማሰባሰቢያ እቅዶቹን ይፋ ያደረገ ሲሆን ዝግጅቱን በሀገር ውስጥ ሬዲዮ፣ ቲቪ ጣቢያዎች፣ ጋዜጦች በስፋት እንዲሰራጭ በማድረግ ማህበረሰቡን በማሳወቅ ይጀመራል ተብሏል።
ዲጂታል ዘመቻዎች፣ አምባሳደሮች ታዋቂ/ተፀእኖ ፈጣሪ ግለሰቦችን በአምባሳደርነት በመሰየም ፕሮጀክቱን እንደያስተዋውቁ ማድረግ፣ በቀጥታ ስርጭት የሚከናወን የገቢ ማሰባሰቢያ ዝግጅት፣ ስፖንሰርሺፕ፣ የሩጫ ውድድር፣ የእግር ኳስ ግጥሚያ፣ ኮንሰርት፣ ቶምቦላ ሎተሪ፣ በመዋጮና በልገሳዎች ገቢ ማሰባሰብ እንደታሰበ ተነግሯል።
የአፍሪካ ዋንጫ እና የአለም አቀፍ ማጣሪያ ጨዋታዎችን ማስተናገድ የሚችል እንደሆነ የተነገረለት ይህ ስቴዲየም 30ሺ ተመልካች የመያዝ አቅም እንዳለው ተገልጿል። እንዲሁም የመሮጫ ትራክ ስላለው የአትሌቲክስ ውድድሮችን ማስተናገድ ይችላል።
የካፍ ስታንዳርድ የሚያሟላ ካታጎሪ ሶስት ውስጥ የሚገኝ ሲሆን እስከ 30ሺ ተመልካች ማስተናገድ የሚችል ስቴዲየም መሆኑ ተገልጿል።
አጠቃላይ የስቴዲየሙ ግንባታ ወጪ 3 ቢሊዮን ብር ሲሆን የመጀመሪያ ዙር ስራ 6 ወር እና ቀጣይ ሁለተኛ ዙር ምዕራፍ በ6 ወር በአጠቃላይ በአንድ አመት ለማጠናቀቅ ታቅዷል።

📌የጋዜጠኛ መኮንን ወ/አረጋይ "እነሆ ማሟሻ" መጽሐፍ ሊመረቅ ነው
የጋዜጠኛ መኮንን ወ/አረጋይ በርካታ ጉዳዮች የተካተቱበት እነሆ ማሟሻ" ቅጽ አንድ እና ቅጽ ሁለት መጻሕፍት ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት ቅዳሜ ሕዳር 14 2017 ዓ.ም ከቀኑ 8:00 ጀምሮ ቴዎድሮስ አደባባይ አካባቢ በሚገኘው በኤን ቢሲ ኢትዮጵያ ስቱዲዮ ሁለት(በተለምዶው ሴጣን ቤት) አዳራሽ ውስጥ ይመረቃል።
በዚህ የመጽሐፍ ምርቃት ሥነሥርዓት ላይም አንጋፋ እና ወጣት የመገናኛ ብዙሃን ባለሞያዎች ሀሳቦቻቸውን ያጋራሉ ተብሏል።
ከዚህ ቀደም በሸገር ኤፍ ኤም 102.1 ሬድዮ ላይ በሚያቀርባቸው የስንክሳር፣ የማሟሻ፣ የሃኪሞ መልዕክት፣ የአርብ ምሽት ቆየት ያሉ ሙዚቃዎች እና አሁን ላይ በኢንቢሲ ቴሌቪዥን በልዩ ልዩ ዝግጅቶች የምናውቀው ጋዜጠኛ መኮንን ወ/አረጋይ "እነሆ ማሟሻ" የተሰኘ የመጀመሪያ ቅጽ አንድ እና ተከታዩን ሁለት መጻህፍትን በተከታታይ ከወራት በፊት ለአንባቢያን ማድረሱ ይታወሳል።

📌የሔለን ሾው ኢምፓወር አዲስ
የሔለን ሾው ኢምፓወር አዲስ ለሁሉም የኅብረተሰብ ክፍል የሚሆን የቢዝነስ፣ የሥራ ፈጠራ፣ ትምህርት፣ የጤናና ማኅበራዊ ጉዳዮች ልዩ ዝግጅት ፊታችን ቅዳሜና እሁድ ኅዳር 7 እና 8 ቀን 2017 ዓ.ም ለሁለት ተከታታይ ቀናት በሚሊኒየም አዳራሽ ይካሄዳል።

📌የሥዕል አውደርዕይ
የሠዓሊ እስጢፋኖስ ሰለሞን "Oppressed passion" የተሰኘ ርዕስ የተሰጠው የሥዕል አውደርዕይ ሕዳር 7 ቀን 2017 ዓ.ም በአርታዊ የሥዕል ማሳያ ውስጥ ለእይታ ይበቃል።ይሄ የሥዕል አውደርዕይ እስከ ሕዳር 29 ይቆያል ተብሏል።

📌"የመንገዴ መንገድ" መጽሐፍ ለንባብ በቃ
የገጣሚ ደጀኔ ተስፋዬ "የመንገዴ መንገድ" የተሰኘ ርዕስ የተሰጠው አዲስ የግጥም መጽሐፍ ትላንት ማክሰኞ ሕዳር 3 ቀን 2017 ዓ.ም ለንባብ በቅቷል።
"የመንገዴ መንገድ" መጽሐፍ በይዘት የግጥም ስብስብ መጽሐፍ ሲሆን በ114 ገፆች ተቀንብቦ በ320 ብር የጀርባ ዋጋ ለአንባቢያን ቀርቧል።
መጽሐፉን በፒያሳ ኤዞፕ በሜክሲኮ ጃዕፋር እና በአራት ኪሎው ኢትዮ ፋጎስ (Ethio Fagos) የመጽሐፍ ማከፋፈያዎች ውስጥ ይገኛል።

📌ድምጻዊት ራሔል ጌቱ ከዳይሬክተር ቅድስት ይልማ ጋር "ውዴ" በተሰኘ ሙዚቃ ድጋሚ ተጣምሩ
ከዚህ ቀደም "ኢትዮጵያዊዬ" የተሰኘ ርዕስ በተሰጠው የሙዚቃ ቪዲዮ አብረው የሰሩት ድምጻዊት ራሔል ጌቱ እና ዳይሬክተር ቅድስት ይልማ "ውዴ" በተሰኘ አዲስ ሙዚቃ በድጋሚ እንደተጣመሩ ኤቨንት አዲስ ሚዲያ ሰምቷል።
የድምጻዊት ራሔል ጌቱ"ውዴ" ሙዚቃ ነገ አርብ ሕዳር 6 ቀን 2017 ዓ.ም ለአድማጮች ይደርሳል ተብሏል።
ለተጨማሪው: https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
ከዚህ ቀደም "ኢትዮጵያዊዬ" የተሰኘ ርዕስ በተሰጠው የሙዚቃ ቪዲዮ አብረው የሰሩት ድምጻዊት ራሔል ጌቱ እና ዳይሬክተር ቅድስት ይልማ "ውዴ" በተሰኘ አዲስ ሙዚቃ በድጋሚ እንደተጣመሩ ኤቨንት አዲስ ሚዲያ ሰምቷል።
የድምጻዊት ራሔል ጌቱ"ውዴ" ሙዚቃ ነገ አርብ ሕዳር 6 ቀን 2017 ዓ.ም ለአድማጮች ይደርሳል ተብሏል።
ለተጨማሪው: https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
📌ኮሜዲያን ደረጄ ኃይሌ የክብር እንግዳ የሆነበት ስብሐቲዝም የሀሳብ ውይይት ዝግጅት እሁድ ይካሄዳል።
ኮሜዲያን ደረጄ ኃይሌ የክብር እንግዳ የሆነበት ስብሐቲዝም 78ተኛ መድረክ "የኮሜዲው ዓለም ከሳቅ ባሻገር" በሚል የሀሳብ ውይይት ይካሄዳል።
ውይይቱ እሁድ ሕዳር 8 ቀን 2017 ዓ.ም ከቀኑ 8:00 ጀምሮ በብሔራዊ ቤተመዛግብት እና ቤተመጻሕፍት አገልግሎት (ወመዘክር) አዳራሽ ውስጥ ይከናወናል።
ለተጨማሪው: https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
ኮሜዲያን ደረጄ ኃይሌ የክብር እንግዳ የሆነበት ስብሐቲዝም 78ተኛ መድረክ "የኮሜዲው ዓለም ከሳቅ ባሻገር" በሚል የሀሳብ ውይይት ይካሄዳል።
ውይይቱ እሁድ ሕዳር 8 ቀን 2017 ዓ.ም ከቀኑ 8:00 ጀምሮ በብሔራዊ ቤተመዛግብት እና ቤተመጻሕፍት አገልግሎት (ወመዘክር) አዳራሽ ውስጥ ይከናወናል።
ለተጨማሪው: https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
📌የዘንድሮው "የሺህ ጋብቻ" ጥር 18 ይካሄዳል
በያሜንት ኤቨንትስ የሚዘጋጀው "የሺህ ጋብቻ" የዘንድሮው የጋብቻ ሥነሥርዓት ጥር 18 ቀን 2017 ዓ.ም በሚሊኒየም አዳራሽ ይካሄዳል ተብሏል።
"የሺህ ጋብቻ" ከዚህ ቀደም በ2005 እና በ2016 ዓ.ም ስኬታማ የብዙኃን ጋብቻዎችን አከናውኗል።
ዘንድሮ ከሀገር ውስጥ 1ሺህ ጥንዶችን እንዲሁም 250 የሚደርሱ ጥንዶችን ከተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት በማካተት በአጠቃላይ ከ1250 በላይ ጥንዶችን የፊታችን ጥር 18 ቀን 2017 ዓ.ም ለመዳር አስፈላጊውን ቅድመ-ዝግጅት እያደረጉ መሆኑን አዘጋጆቹ ዛሬ ሕዳር 5 ቀን 2017 ዓ.ም በሐርመኒ ሆቴል በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ አስታውቀዋል።
በዚህ ግዙፍ የጋብቻ ሥነሥርዓት በተለየ መልኩ ከሚኖሩ ክንውኖች መካከል ከ25 ሺህ በላይ የቡና ሲኒ እንዲሁም 2017 ኪ.ግ የሚመዝን ባህላዊ ዳቦ ለታዳሚዎች ይቀርባል ተብሏል።
ሁነቱንም በዓለም ድቃድንቅ መዝገብ ላይ እንዲስፍር ለማድረግ የሚሠራበት ታላቅ ዝግጅት ይሆናል ተብሎ ይጠበቃል፡፡
የሺህ ጋብቻ ትልቅ ዓላማ የኢትዮጵያን እንዲሁም የአፍሪካ ሀገራት ህዝቦችን የካበተ ባህላዊ የሰርግ ሥነ-ሥርዓት አጉልቶ በማሳየት አዲስ አበባን የሃኒሙን ማዕከል ማድረግ እንደሆነ አዘጋጆቹ ገልጿል።
አጠቃላይ ለዚህ ፕሮጀክት ዕውን መሆን ያስፈልጋል ተብሎ የታቀደው በጀት 68,997,500 ብር እንደሆነ ተነግሯል።

📌በኢትዮጵያ የመጀመሪያው ባለ ቀለም ፊልም የሆነው "አስቴር" ፊልም ወደ ዲጂታል ተቀይሮ ለዕይታ ሊቀርብ ነው
በኢትዮጵያ የመጀመሪያውን ባለ ቀለም ፊልም ወደ ዲጂታል አስቀይሮ ሊያስመርቅ መሆኑን የአዲስ አበባ ባህል፣ ኪነ ጥበብና ቱሪዝም ቢሮ ኃላፊ ኂሩት ካሳው (ዶ/ር) ዛሬ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ አስታውቀዋል።
በ1983 ዓ.ም በኢትዮጵያ ፊልም ኮርፖሬሽን አማካኝነት ሀገራዊ ዘዉግ ላይ ተንተርሶ የተሰራውና "አስቴር" የተሠኘው አትዮጵያዊ ፊልም የአጻጻፍ ደረጃው ከፍ ያለና ከድርሰት እስከ ፕሮዳክሽን ሙሉ በሙሉ በሀገር ባለሞያዎች የተሰራ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
"አስቴር" የተሰኘው የመጀመሪያው ፊልም የዛሬውን የፊልም ኢንዱስትሪና የፈጠራ ክህሎትን ለማሳደግ መነሻ መሆኑን ያነሱት ኃላፊዋ፤ ቢሮው በቴክኖሎጂ ምክንያት ለዕይታ ሳይበቁ የቆዩ የቀደምት የፊልም ሥራዎችን ከሦስት ዓመታት ወዲህ ከሀገር ውጪና በሀገር ውስጥ በማፈላለግ ዲጂታላይዝድ እንዲሆኑ እየሰራ መሆኑን አሳውቀዋል፡፡
የፊታችን ህዳር 8 ቀን 2017 ከቀኑ በ8፡00 ሰዓት የፊልሙ ባለቤቶች፣ ተዋናይናዮችና የኪነ ጥበብ አፍቃሪያን በታደሙበት በአድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየም በይፋ እንደሚመረቅ ኤቨንት አዲስ ሚዲያ ሰምቷል።

📌"ታላላቆችን እናክብር" በተሰኘ ልዩ መርሐግብር 13 የቀድሞ ጋዜጠኞች ዕውቅና ሊበረከትላቸው ነው
በተወዳጅ ሚዲያ የተዘጋጀውና በ1960ዎቹና በ1970ዎቹ አገራቸውን ያገለገሉ ቀደምት ጋዜጠኞች የሚመሰገኑበት ልዩ ዝግጅት ነገ ቅዳሜ ህዳር 7 2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 3:00 ጀምሮ በአንጋፋው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር ይካሄዳል።
በዚህ ልዩ የምስጋና ዝግጅት ላይ 13 የቀድሞ ጋዜጠኞች ዕውቅና ይበረከትላቸዋል ተብሏል።
በምስጋና ዝግጅቱ ላይ ይታደማሉ ተብለው የሚጠበቁት ተመስጋኝ ጋዜጠኞች አቶ አስፋው ኢዶሳ፣ወይዘሮ አባይነሽ ብሩ፣አቶ ሀዲስ እንግዳ፣አቶ ዋጋዬ በቀለ፣ወይዘሮ ሚሊየን ተረፈ፣አቶ ሀይሉ ወልደፃድቅ፣አቶ ተሾመ ብርሀኑ ከማል፣አቶ ተክሉ ታቦር፣ አቶ ይንበርበሩ ምትኬ፣ አቶ ታዬ በላቸው፣አቶ ግርማይ ገብረፃድቅና አቶ ኢሳያስ ሆርዶፋ ናቸው።
ዝግጅቱ ላይ እንደሚመሰገኑ ከተመረጡ በኃላ ህይወታቸው ያለፈው የሚድያ ሰው ሙለጌታ ወልደሚካኤልም በልጆቻቸው አማካይነት ዕውቅናው ይበረከትላቸዋል ተብሏል።
እነዚህ ዕውቅና የሚቸራቸው አንጋፋ የሚድያ ሰዎች ከዚህ ቀደም ተገቢውን ዕውቅና ሳያገኙ የቀሩና በሌሎች የሽልማት መርሀግብሮች ያልተካተቱ ነበሩ።
በሁሉም ተመስጋኞች የህይወት ታሪክ ላይ በቂ ጥናት እና ምርምር መደረጉንም ለማወቅ ተችሏል።
በዕለቱ የቀድሞ ጋዜጠኞችን የቆየ ድምፅና ቪድዮ የሚያሳይ አጭር ዘጋቢ መሰናዶ የሚኖር ሲሆን የሙያ ማህበራት፣የሚድያ ኃላፊዎች፣የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የጋዜጠኝነት መምህራን እና ሌሎችም ታላላቅ እንግዶች ይታደማሉ፡፡
የመርሀግብሩ አዘጋጅ ጋዜጠኛ ዕዝራ እጅጉ የተወዳጅ ሚድያ እና ኮምዩኒኬሽን ዋና ስራ አስፈፃሚ ሲሆን ከዚህ ቀደም የ45 ሰዎችን ታሪክ በሲዲ የ20 ሰዎችን ታሪክ ደግሞ በመፅሐፍ ያሳተመ ነው።

📌የገጣሚ ባንቺአየሁ አሰፋ መጽሐፍ ዛሬ ይመረቃል
የወጣቷ ገጣሚ ባንቺአየሁ አሰፋ አሊ "ላልዪበላይቱ" የተሰኘ ርዕስ የተሰጠው አዲስ የግጥም መጽሐፍ ዛሬ አርብ ሕዳር 6 2017 ዓ.ም ከምሽቱ 11:00 ጀምሮ በብሔራዊ ቤተመዛግብት እና ቤተመጻሕፍት አገልግሎት (ወመዘክር )አዳራሽ ውስጥ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት በድምቀት ይመረቃል።
በዕለቱም ደራሲ ኃይለመለኮት መዋዕል፣ መምህር የሻው ተሰማ፣ ገጣሚ ዮሐንስ ሞላ፣ገጣሚ አበባ የሺጥላ፣ገጣሚ መንበረማርያም ኃይሉ፣ ገጣሚ ዲበኩሉ ጌታ፣ገጣሚ ሰይፉ ወርቁ፣ ገጣሚ ቴዎድሮስ ካሣ፣ገጣሚ ፌቤን ፋንጮ፣ ደራሲ ቢንያም አቡራ ፤ድምጻዊ አብርሐም ኸይሩ የሥነጽሑፋዊ ስራዎቻቸውንና ሀሳቦቻቸውን ያጋራሉ ተብሏል።
ለተጨማሪው: https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
የወጣቷ ገጣሚ ባንቺአየሁ አሰፋ አሊ "ላልዪበላይቱ" የተሰኘ ርዕስ የተሰጠው አዲስ የግጥም መጽሐፍ ዛሬ አርብ ሕዳር 6 2017 ዓ.ም ከምሽቱ 11:00 ጀምሮ በብሔራዊ ቤተመዛግብት እና ቤተመጻሕፍት አገልግሎት (ወመዘክር )አዳራሽ ውስጥ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት በድምቀት ይመረቃል።
በዕለቱም ደራሲ ኃይለመለኮት መዋዕል፣ መምህር የሻው ተሰማ፣ ገጣሚ ዮሐንስ ሞላ፣ገጣሚ አበባ የሺጥላ፣ገጣሚ መንበረማርያም ኃይሉ፣ ገጣሚ ዲበኩሉ ጌታ፣ገጣሚ ሰይፉ ወርቁ፣ ገጣሚ ቴዎድሮስ ካሣ፣ገጣሚ ፌቤን ፋንጮ፣ ደራሲ ቢንያም አቡራ ፤ድምጻዊ አብርሐም ኸይሩ የሥነጽሑፋዊ ስራዎቻቸውንና ሀሳቦቻቸውን ያጋራሉ ተብሏል።
ለተጨማሪው: https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
📌 "ለዝና" የተሰኘ ነጠላ ሙዚቃ ተለቀቀ
የወጣቱ ድምጻዊ ሳሙኤል ፍቃዱ "ለዝና" የተሰኘ ርዕስ የተሰጠው ሙዚቃ ትላንትና ሕዳር 6 ቀን 2017 ዓ.ም በናሆም ሪከርድስ ዩቲዩብ ቻናል በኩል ለሙዚቃ አድማጮች ቀርቧል።
የዚህ ነጠላ ሙዚቃ ግጥም እና ዜማ በድምጻዊ ሳሙኤል ፍቃዱ የተሰራ ሲሆን በሙዚቃ ቅንብር እና ሚክስ ማስተር ሮቤል ዳኜ ተሳትፎበታል።
ድምጻዊ ሳሙኤል ፍቃዱ ከዚህ ቀደም "ነይ " "አይናለም" "አይከረም" የተሰኙ ነጠላ ሙዚቃዎችን ለአድማጮች አድርሷል።

📌የሕይወት ተፈራ አዲስ መጽሐፍ ለንባብ ሊበቃ ነው
የደራሲ ሕይወት ተፈራ "ተድባብ" የተሰኘ ርዕስ የተሰጠው አዲስ መጽሐፍ በቅርቡ ለአንባቢያን እንደሚደረስ ኤቨንት አዲስ ሚዲያ ከዋልያ መጻሕፍት ያገኘው መረጃ ያመለክታል።
ሕይወት ተፈራ ከዚህ ቀደም "ማማ በሰማይ" "ምንትዋብ" እና "ኅሠሣ" የተሰኙ መጻሕፍትን ለአንባቢያን ማቅረቧ ይታወሳል።
ለተጨማሪው: https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
የደራሲ ሕይወት ተፈራ "ተድባብ" የተሰኘ ርዕስ የተሰጠው አዲስ መጽሐፍ በቅርቡ ለአንባቢያን እንደሚደረስ ኤቨንት አዲስ ሚዲያ ከዋልያ መጻሕፍት ያገኘው መረጃ ያመለክታል።
ሕይወት ተፈራ ከዚህ ቀደም "ማማ በሰማይ" "ምንትዋብ" እና "ኅሠሣ" የተሰኙ መጻሕፍትን ለአንባቢያን ማቅረቧ ይታወሳል።
ለተጨማሪው: https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
📌ኤቨንት አዲስ ሚዲያ በቲክቶክ !
ኤቨንት አዲስ ሚዲያ በቲክቶክ ስርጭቱን ጀመረ
ከዚህ ቀደም በድረገፅ፣ በቴሌግራም እና በፌስቡክ አማራጮች ብቻ ዕለታዊ ተመራጭና አማራጭ የኪነጥበብ እና ሁነት መረጃዎችን ሲያቀረብ የቆየው ኤቨንት አዲስ ሚዲያ በቲክቶክ የማኀበራዊ ትስስር ገፅ ከዛሬ ሕዳር 8 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ በይፋ መረጃዎችን ማቅረብ ጀምሯል።
ሊንክ: tiktok.com/@eventaddis1
በተጨማሪም በቅርቡ በሌሎችም የማህበራዊ ትስስር ገፅ አማራጮች እንመጣለን።እናመሰግናለን ።
ቴሌግራም: https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
ድረገፅ: https://eventaddis.com/
Facebook:https://www.facebook.com/profile.php?id=100083170462851

📌የዝነኛው የቴአትር መምህር መጽሐፍ ሊመረቅ ነው
የ"በዓሉ ግርማ: ቤርሙዳ" "የአና ማስታወሻ"ን ጨምሮ በርካታ ተውኔቶችን ያዘጋጁትና በአዲስአበባ ዩኒቨርስቲ የቴአትር ጥበባት ት/ክፍል ውስጥ ተፈሪና ተወዳጅ የሆኑት ዶ/ር ተሻለ አሰፋ ያዘጋጁት "የተውኔት ዝግጅት መሰረታዊን " መጽሐፍ ሊመረቅ እንደሆነ ተሰምቷል።
እነሆ ዝርዝሩን: https://vm.tiktok.com/ZMhtWffUL/

📌 በኢትዮጵያ የመጀመሪያው ባለ ቀለም ፊልም የሆነው "አስቴር" ፊልም ወደ ዲጂታል ተቀይሮ ከ34 ዓመታት በኃላ ለዕይታ ቀርቧል።
እነሆ ዝርዝሩን በድምጻችን ይስሙ: https://vm.tiktok.com/ZMhtWffUL/
ለተጨማሪው: https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
እነሆ ዝርዝሩን በድምጻችን ይስሙ: https://vm.tiktok.com/ZMhtWffUL/
ለተጨማሪው: https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
📌ገጣሚ ሜሮን ጌትነት ወደ መድረክ ልትመለስ ነው
ለረጅም ጊዜ ከመድረክ እርቃ የቆየችው ሁለገቧ ከያኒ ሜሮን ጌትነት የፊታችን ታህሳስ ወር ላይ በሚካሄድ አንድ የኪነጥበብ ዝግጅት ላይ ስራዎቿን እንደምታቀርብ ተሰምቷል።
እነሆ ዝርዝር መረጃዎን በድምጻችን ይስሙ:
https://vm.tiktok.com/ZMhtvQybR/
ለተጨማሪው: https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
ለረጅም ጊዜ ከመድረክ እርቃ የቆየችው ሁለገቧ ከያኒ ሜሮን ጌትነት የፊታችን ታህሳስ ወር ላይ በሚካሄድ አንድ የኪነጥበብ ዝግጅት ላይ ስራዎቿን እንደምታቀርብ ተሰምቷል።
እነሆ ዝርዝር መረጃዎን በድምጻችን ይስሙ:
https://vm.tiktok.com/ZMhtvQybR/
ለተጨማሪው: https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
❤1
📌በ"ማለዳ ኮኮቦች" ፕሮግራም የምናውቀው ፍፁም አስፋው አዲስ የቴሌቪዥን ዝግጅት ሊጀምር ነው።
"የማለዳ ኮኮቦች" እና "ቅን ልቦች"የተሰኙ የቴሌቪዥን ፕሮግራሞችን ሲያቀርብ የቆየው ሁለገቡ የፊልም ባለሞያው ፍፁም አስፋው "ፎቶ እና ጨዋታ" የተሰኘ የቴሌቪዥን ፕሮግራም በአባይ ቴሌቪዥን ሊጀምር እንደሆነ ኤቨንት አዲስ ሚዲያ ሰምቷል።
እነሆ ዝርዝር መረጃዎን በድምጻችን ይስሙ:
https://vm.tiktok.com/ZMhnf3xPS/