Event Addis Media – Telegram
Event Addis Media
9.62K subscribers
6.11K photos
13 videos
4 files
4.73K links
Connect with Addis artistic community!

Website: https://eventaddis.com

Contact: @Tmanaye
Download Telegram
📌"ነገን አብረን እንሳል" አውደርዕይ ነገ ይከፈታል

በስልሳ ተጽዕኖ ፈጣሪ አካልጉዳተኛ ሠዓሊያን የተዘጋጀው  የሥዕል አውደርዕይ ነገ አርብ ህዳር 27 ቀን 2017 ከቀኑ 8:00 ጀምሮ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ  አለ የሥነጥበብና ዲዛይን ትምህርት ቤት ውስጥ የክብር እንግዶች በተገኙበት በድምቀት ይከፈታል።

ለተጨማሪው: https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
📌ደራሲና ገጣሚ ደበበ ሰይፉ  ያነባቸው የነበሩት 650 የግል መጻሕፍት ለአብርሆት ቤተመፅሀፍት ሊበረከቱ ነው፡፡

ህይወቱ ካለፈ 24 ዓመት  ያለፈው የገጣሚ ፣ተመራማሪና የዩኒቨርሲቲ መምህር ደበበ ሰይፉ    የግል መፅሀፎች ለአብርኾት ቤተመፅሀፍት ሊበረከቱ እንደሆነ ተሰማ።

በጥልቅ አንባቢነቱ የተመሰከረለት ደበበ ሰይፉ ከ650 በላይ የመጻህፍት ዐይነቶች ነበሩት ህዳር 27 2017 ዓ.ም መፅሀፎቹ ለአብርሆት ይበረከታሉ ተብሏል፡፡

ገጣሚ ደበበ ሰይፉ ከ 1960ዎቹ ጀምሮ በቴአትር እና በሥነ ፅሁፍ መምህርነት ያገለገለ ሲሆን የህይወት ታሪኩም በተወዳጅ ሚድያ  በሲዲ በድምፅ ዶክመንተሪ ተሠርቶ መመረቁ ይታወቃል። "የብርሀን ፍቅር" እና "ለራስ የተጻፈ ደብዳቤ" የተሰኙ የግጥም መድበሎንችም  ያስነበበን የኪነ ጥበብ ሰው ነበር።

ይህንኑ የመፅሀፍ ርክክብ ምክንያት በማድረግ የደበበ ሰይፉ ቤተሰቦች ከተወዳጅ ሚድያ ጋር  የጀመሩት የማህበራዊ ሚድያ የንባብ ዘመቻ እንደሚከናወን ለማወቅ ተችሏል።

ለተጨማሪው: https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
📌አርቲስት ማስተዋል ወንደሰን የአዲስ አበባ እግር ኳስ ፌደሬሽን ምክትል ፕሬዚዳንት ሆና ተመርጣለች

የአዲስ አበባ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ዛሬ ባደረገው ጠቅላላ ጉባኤ የፕሬዝዳንትና ስራ አስፈፃሚ ምርጫ አካሂዷል።

ኢ/ር ሃይለእየሱስ ፍስሀ የአዲስ አበባ ከተማ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዘዳንት ሆነው ሲመረጡ፤ አርቲስት ማስተዋል ወንደሰን የአዲስ አበባ እግር ኳስ ፌደሬሽን ምክትል ፕሬዚዳንት ሆና ተመርጣለች።

ፌዴሬሽን አመታዊ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤውን በጊዮን ሆቴል ሲያካሂድ ለቀጣይ አራት አመታት የሚመሩትን ፕሬዝዳንትና ስራ አስፈፃሚዎችንም መርጧል።

አንጋፋዋ አርቲስት ሀረገወይን አሰፋ ፣አቶ ሲሳይ ዳኜ ፣ደ/ር ወገኔ ዋልተንጉስ ፣አቶ ኢሳያስ ታፈሰ ፣አቶ ሸሀመለ በቀለ፣አቶ በለጠ ወልዴ፣ ወ/ሮ አሰፋሽን ስራ አስፈፃሚ ውስጥ ተካተዋል።

ፌዴሬሽኑ አለብኝ የሚለውን የገንዘብ እጥረት ለመቅረፍ አርቲስቶችን ወደ ስራ አስፈፃሚ በማምጣት የማርኬቲንግ ስራዎችን ለመስራት እንዳሰበ ለማወቅ ተችሏል።

ቀደም ተብሎ በፕሬዚዳንታዊ ምርጫው ላይ አርቲስት ሰራዊት ፍቅሬ ፕሬዚዳንት እንዲሆን ግብዣ ቀርቦለት ሳይቀበለው እንደቀረም ከታማኝ ምንጭ ለመረዳት ተችሏል።

በቀጣይ ተመራጮችን በባላገሩ ሜዳ ፕሮግራም ላይ ይዘን እንቀርባለን።

Via:- ባላገሩ ስፖርት

ለተጨማሪው: https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
📌የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ሳምንት

ዓመታዊው የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ሳምንት በግዮን ሆቴል ለ4ኛ ጊዜ ዛሬ አርብ ህዳር 27 ቀን 2017 ዓ.ም ከቀኑ 8 ሰዓት ጀምሮ በይፋ ይከፈታል።

ይህ 100 የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች የሚሳተፉበት ዓመታዊ ዝግጅት ከህዳር 27 እስከ እሁድ ህዳር 29 ቀን 2017 ዓ.ም ድረስ ይቆያል ተብሏል።

100 ድርጅቶች ስራቸውን በሚያስተዋውቁበት በዚህ ዓውደርዕይ ላይ በመገኘት ስለተቋማቱ ስራ መረጃ አግኙ አዲስ ትስስሮችን ፍጠሩ ተብላችኋል።

የዝግጅቱ መግቢያ በነጻ ነው።

ማስፈንጠሪያውን ተጭነው ይመዝገቡ https://forms.gle/RKZ2moy9G6SUgNK7A
📌8ኛው ኦዳ አዋርድ ተካሄደ

በ2010 ዓ.ም  የተለያዩ የኦሮሞኛ ቋንቋ ሙዚቀኞችን እና አርቲስቶችን በመሸለም የተጀመረው ኦዳ አዋርድ ለ8ኛ ጊዜ ሽልማቱን አከናውኗል። በዘንድሮው ሽልማቱም ከሀገር አልፎ የአፍሪካ ሀገራት አርቲስቶችን አካትቶ ሽልሟል።

በጋዜጠኛ በሻቱ ቶለማርያም የተጀመረው ኦዳ አዋርድ በበሻቱ መልቲሚዲያ እና በሌሎች አጋር አካላት የተለያዩ የኪነ ጥበብ ሰዎችን ሲሸልም ቆይቶ 8ኛውን ሽልማት ከኢፌዴሪ ባሕል እና ስፖርት ሚኒስቴር ጋር በመኾን የ2017 መድረኩን አካሂዷል።

ዩጋንዳዊውን ኤዲ ኬንዞ እና የኤርትራዋ ሚለንን ጨምሮ ከስምንት የምሥራቅ አፍሪካ ሀገራት 18 አርቲስቶች በሽልማቱ ተካትተዋል።

የዓመቱ ምርጥ የግጥም መጽሐፍ እና የምርጥ መጽሐፍ ሽልማቶች የተሰጡ ሲኾን በ2016 ዓ.ም ተስፋ የተጣለባት ድምጻዊት አሳንቲ አስቹ ተሸላሚ ኾናለች።

የዓመቱ ምርጥ ሴት ድምጻዊት ለምለም ኃይለ ሚካኤል ዋሊኒ በተሰኘው ሙዚቃ አሸናፊ መኾን ችላለች።

የ2016 ዓ.ም ምርጥ የዘመናዊ ሙዚቃ አሸናፊ  ሲቦይ አጃም ኾኗል።

የ2016 ዓ.ም ምርጥ የጥንድ ሙዚቃ አደም መሐመድ እና ጫልቱ ቡልቶ አሸንፈዋል።

የ2016 ዓ.ም የሕይዎት ዘመን ተሸላሚ የጉራጊኛ ድምጻዊ ደምሴ ተካ ኾኗል።

ሌላኛው በሕይዎት ዘመን ተሸላሚ ደግሞ ክቡር ዶክተር ኪሮስ ዓለማየሁ የተሸለሙ ሲኾን ባለቤታቸው እና ልጆቻቸው ሽልማቱን ተቀብለዋል።

ምርጥ የምሥራቅ አፍሪካ አርቲስት ሽልማትን ድምጻዊት ሚለን አሸንፋለች።

የዩጋንዳው ኤዲ ኬንዞ፣ የሩዋንዳው ብሩሲ ሜሎዲ፣ የደቡብ ሱዳን እና ሌሎች አርቲስቶችም በልዩ ልዩ ዘርፎች አሸንፈዋል።

ለተጨማሪው: https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
📌የኢትዮ-ቻይና የፊልምና ቴሌቪዥን ፌስቲቫል 

በአፍሪካ የመጀመሪያው የሆነው የኢትዮ-ቻይና የፊልምና ቴሌቪዥን ፌስቲቫል በመጪው  ታህሣሥ ወር በአዲስ አበባ ኢትዮጵያ ይካሄዳል።

ፌስቲቫሉ  የጎፍ ኢንተርቴይመንት ከኢፌዴሪ ውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ፣ከኢፌዴሪ ባህልና ስፖርት ሚኒስቴር እና ከቻይና ኤምባሲ በኢትዮጵያ ጋር በጋራ መተባበር ያዘጋጁት ነው።

ይህ የኢትዮ-ቻይና የፊልምና ቴሌቪዥን ፌስቲቫል ከታህሣሥ 11 እስከ ታህሣሥ 14 ቀን 2017 ዓ.ም ለተከታታይ አራት ቀናት  በአዲስ አበባ ከተማ ይካሄዳል።

ዝግጅቱም የብሪክስ ሀገራት የፊልምና የቴሌቪዥን ፌስቲቫል ማስጀመሪያ ልዩ መርሐግብር ነው።

በፌስቲቫሉ ላይ በኢትዮጵያ የመጀመሪያ የሆነው"ሂሩት አባቷ ማነው ?" ጨምሮ በሁለቱም ሀገራት የተመራረጡ ታላላቅ ፊልሞች የሚታዩ ሲሆን ፣ የፓናል ውይይቶች ፣ወርክሾፖች ፣እና የትውውቅ መድረኮች የሚፈጥረ በመሆኑ ለኢትዮጵያ ሲኒማ ዘርፍ መልካም አጋጣሚን የሚፈጠር ትልቅ መድረክ ነው ተብሏል።

በዚህ ታላቅ ፌስቲቫል የመክፈቻ ሥነሥርዓት ላይ ከቻይና እንዲሁም ከኢትዮጵያ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች፣ ተጽዕኖ ፈጣሪ የፊልም ባለሞያዎች ፣ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ይገኙበታል።

ለተከታታይ አራት ቀናት የሚቆየው የኢትዮ-ቻይና የፊልምና ቴሌቪዥን ፌስቲቫል ስድስት ኪሎ በሚገኘው አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ራስ መኮንን አዳራሽ ውስጥ ይካሄዳል።

ለተጨማሪው: https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
📌ፈንድቃ በሃያት ሪጀንሲ ነገ ስራ ይጀምራል

ፈንድቃ ባህል ማዕከል በሃያት ሪጀንሲ ሆቴል ሜትሮ አዳራሽ ውስጥ ነገ ሰኞ ኅዳር 30 ቀን 2017 ዓ.ም በይፋ ስራ እንደሚጀምር  ተገልጿል። 

ፈንድቃ በካዛንቺስ ማዕከሉ ሲሰጥ የነበረውን ሙሉ አገልግሎት በሃያት ሪጀንሲ ከሳምንት እስከ ሳምንት እንደሚሰጥና መደበኛ ዝግጅቶዎቹም እንደሚቀጥሉ አስታውቋል።

የሥዕል አውደርዕይ ማቅረቢያ ቦታን ጨምሮ
ከሰኞ እስከ እሁድ ምሽት የአዝማሪ ጨዋታ በመደበኛነት የሚቀጥል ሲሆን ሰኞ ፣ ረቡዕ እና አርብ የጃዝ እና የባህል ሙዚቃዎች መቅረባቸውን ይቀጥላሉ ተብሏል።

የአገልግሎት ክፍያ ጉዳዩስ እንዴት ነው ብለው የሚጠይቁ የፈንድቃ ደንበኞች ካሉ "ፈንድቃ ዋጋውን ይዞ ስለገባ እንዳትሰጉ መግቢያው ሰኞ፣ረቡዕና አርብ ባሉ ዝግጅቶች ላይ እንደተለመደው 200 ብር ነው" ሲል የፈንድቃ ባህል ማዕከል መስራች መላኩ በላይ አስታውቋል።

ሀያት ሪጀንሲ ያለበት ቦታ ከሁሉም የአዲስ አበባ አቅጣጫዎች ለሚመጡ ደንበኞች ምች እንደሆነ የተገለፀ ሲሆን ወደ ፈንድቃ መግቢያ በር በእስጢፋኖስ ቤተክርስቲያን በኩል እንደተዘጋጀም ተገልጿል።

ፈንድቃ በሃያት ሪጀንሲ መደበኛውን የሥዕል አውደርዕይ እንደሚቀጥል ታውቋል።

ለተጨማሪው: https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
📌ቅድመ ጥምረት

- በልባችሁ የፃፋችሁት የፍቅር ታሪክ ምንድነው?

- የህይወት መንገዳችሁ በትዳር እንዲሆን ከወሰናችሁ በኋላ የፍቅር ግንኙነት ለመጀመር ስታስቡ  "ትክክለኛው" ሰው ብላችሁ በልባችሁ ያሰባችሁት ሰው ለምን የለም?

- ያለፈው ያልተሳካው የፍቅር ግንኙነት ለምን አልተሳካም? በልባችን ምንስ ጥሎ  አለፈ?

- የፍቅር ግንኙነት ከመጀመር በፊት እራሴ ጋር ምን ልጨርስ?

-በትክክል የምፈልገው ምንድነው?

ካነበብናቸው መፅሐፍት፣ከሰማናቸው ታሪኮች፣ሙዚቃዎች፣ካደግንበት ማህበረሰብ፣ከኖርነው ኑሮ፣ካልተሳኩ የፍቅር ግንኙነት/ቶች ተነስተን በልባችን የፃፍነው የፍቅር ታሪክ አለን።

- በፍቅር ግንኙነት መንገድ ላይ ከሚመጣው ሰው ጋር ይህን በልባችን የሰራነውን የፍቅር ታሪክ እንኖረዋለን።

እነዚህን ጉዳዮች እንመክርባቸው ዘንድ ቅድመ ጥምረት የተሰኘ አስደሳች፣ መስተጋብራዊ እና ግንዛቤ የሚያስጨብጥ የስልጠና ፕሮግራም አዘጋጆተናል።

ስልጠናው የግንኙነት አቅምን ለማወቅ እና ለጤናማ፣ አስደሳች እና ዘላቂ አጋርነት የሚያስፈልጎትን  ክህሎቶች ለመማር የሚረዳ  የስልጠና ፕሮግራም ነው።
 
ካልተሳካ የፍቅር አዙሪት ለመላቀቅ ፣ እዉነተኛ የፍቅር ግንኙነት ውስጥ ለመግባት እና ለዘላቂ ግንኙነት ጠንካራ መሰረት ለመገንባት አሁኑኑ ይደውሉ ...0946-444445
ቀን :-ቅዳሜ፣ታህሳስ 05/2017 ዓ.ም
ቦታ :- ሲ ኤም ሲ ሚካኤል ኢትዮጵያን ኢኮኖሚክ አሶሴሽን አዳራሽ
መግቢያ ዋጋ :-300 ብር ብቻ

       ኑ ና ለፍቅር ተዘጋጁ!!
ኦሲስ ሥልጠናና ማማከር ማዕከል
https://news.1rj.ru/str/+ESVZ5qsyls9lODJk

📌Ads
1
📌መቅረዝ ሥነኪን የኪነጥበብ ዝግጅት ሐሙስ ይካሄዳል

አርክቴክት ሚካኤል ሽፈራው የክብር እንግዳ የሆነበት "መቅረዝ ሥነኪን" የኪነጥበብ ዝግጅት ሀሙስ ይካሄዳል።

አንጋፋ እና ወጣት የኪነጥበብ ባለሞያዎችን እያጣመር የዘለቀው መቅረዝ ሥነኪን ወርሀዊ የኪነጥበብ  ዝግጅት ሐሙስ ታህሣሥ 3 ቀን 2017 ዓ.ም ከምሽቱ 11:00 ጀምሮ በብሔራዊ ቤተመዛግብትና ቤተመጻሕፍት አገልግሎት (ወመዘክር )አዳራሽ ውስጥ ይካሄዳል።

በዚህ ኪነጥበባዊ ዝግጅት ላይ አርክቴክት ሚካኤል ሽፈራው የክብር እንግዳ በመሆን የሚገኘ ሲሆን በተጨማሪም ወጣት የኪነጥበብ ባለሞያዎች የግጥም ፣የሙዚቃ ስራዎቻቸውን ያቀርባሉ።

የዚህ ዝግጅት መግቢያ በነፃ ነው።

ለተጨማሪው :https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
📌የሁለገቡ የሙዚቃ ሰው ኤልያስ መልካ 47ተኛ ዓመት የልደት በዓል ዛሬ ይከበራል።

ከአምስት ዓመታት በፊት ህልፈቱ የተሰማው ሁለገቡ የሙዚቃ ሰው ኤልያስ መልካ ዛሬ የ47ተኛ ዓመት የልደት በዓሉ መታሰቢያ ይከበራል።

42 ዓመት ኖሮ ከ50 በላይ አልበሞችን ያቀናበረው ሙዚቀኛ የዜማ እና ግጥም ደራሲ፣ የሙዚቃ አቀናባሪ፣ ፕሮድዩሰር የሆነው ኤልያስ መልካ የኢትዮጵያ ሙዚቃ ባለውለታ ነው።

በቅንብር ስራ ላይ በቆየባቸው 19 ዓመታት ተወዳጅነትን ያተረፉ ከ50 በላይ አልበሞችን አቀናብሯል።

የኢዮብ መኮንንን "እንደቃል" አልበም፣ የጌቴ አንለይን “መልክሽ አይበልጥሽም” አልበም፣ የቤሪን "ከምን ነፃ ልውጣ" አልበም እና ወዘተ ደግሞ ከቅንብር ባሻገር በግጥም እና ዜማ በመሳተፍ ጭምር የሰራቸው አልበሞች ናቸው።

ኤልያስ ከአማርኛ በተጨማሪ በትግርኛ፣ ኩናምኛ፣ኦሮሚኛ የተዜሙ የሙዚቃ ስራዎችንም አቀናብሯል ነጠላ ዜማዎችን እና ለማኅበራዊ አገልግሎት የሚውሉ ስራዎችንም በብዛት ሰርቷል።

ከአዳዲስ ሙዚቀኞች ጋር በመስራት ተስእጦ ያላቸውን ሙዚቀኞች ማውጣትም ሌላው መገለጫው ነው።

ኤልያስ ከተለያዩ ወጣት እና አንጋፋ ሙዚቀኞች ጋር የሰራ ሲሆን መሀሙድ አህመድ፣አረጋኸኝ ወራሽ፣ቴዲ አፍሮ፣ጎሳዬ ተስፋዬ፣አብነት አጎናፍር ጥቂት ማሳያ ናቸው ኤልያስ ያሬድ ሙዚቃ ት/ት ቤት ገብቶ ከተማራቸው ቼሎ እና ፒያኖ በተጨማሪ ድራም፣ ጊታር፣ኪቦርድ፣ቤዝ ጊታር እንዲሁም ከሐገርኛ የሙዚቃ መሳሪያዎች መካከል ደግሞ መሰንቆ እና ክራር በብቃት ይጫወት ነበር።

ኤልያስ መልካ ከሙዚቀኛነቱ ባሻገር ለሙዚቀኛው መብት መከበር ከፍተኛ ትግል አስተዋፅኦ ያበረከተ ነው።

ኤልያስ መልካ በሙዚቃ ካበረከታቸው ስራዎች አንፃር ብዙ ሊወራለት እና ሊነገርለት እንዲሁም በስራዎቹ ላይ ሰፊ ጥናት ሊደረግ የሚገባ ትልቅ የሙዚቃ አቀናባሪ ነው።
📌ስድስተኛው የቴሌቪዥን ጣቢያ ከአየር ላይ ወረደ

ኢትዮጵያ ባለፉት ስድስት ወራት ቢያንስ በአንድ ወር አንድ የቴሌቪዥን ጣቢያ ስርጭቱን የሚያቋርጥባት ሀገር ሆናለች፡፡

የቴሌቪዥን ጣቢያዎቹ ከአየር ላይ መውረድ በሚዲያ ዘርፍ ላይ የሚፈጥረው አሉታዊ ተጽእኖ እንደተጠበቀ ሆኖ የጋዜጠኞች የስራ ዋስትናና ሰርቶ የመኖር ሁኔታ ላይ ጥላ ያጠላል ተብሏል፡፡

ብዙዎቹ የቴሌቪዥን ጣቢያዎች ጋዜጠኞቻቸውን በትነው ከገቢዎች ሚኒስቴር ጋር ግብ ግብ ላይ ሲሆኑ በጋዜጠኞቻችው ተከሰው ፍርድ ቤት የሚመላለሱም እንዳሉም ተነግሯል።

ባለፉት ስድስት ወራት ብቻ ቲቪ 9፤ፕራይም ቲቪ፤ ከገበሬው ቲቪ፤ ናሁ ቲቪ፤ ኦቢኤስ ቲቪና ኢሳት ቲቪ ስርጭታችውን በሳተላይት ላይ ማስቀጠል ያልቻሉ ሚዲያዎች እየሆኑ ነው፡፡

ለጣቢያዎቹ ከአየር ላይ መውረድ የተለያዩ ችግሮች ቢጠቀሱም ከገንዘብ የውጭ ምንዛሪ ማሻሻያ በኃላ በዶላር የሚከፈለው የሳተላይት ኪራይ ክፍያ ዋጋ መናር በዋናነት የሚጠቀስ ችግር ነው፡፡ የሀገሪቱ ኢኮኖሚ ከሚያመነጨው የንግድ እንቅስቃሴ በቂ ማስታውቂያ አለማግኘትና ከዚህ በፊት ከፍተኛ በጀት ለማስታወቂያ ይመድቡ የነበሩ እንደ ቢራ ፋብሪካ ዓይነት ግዙፍ ተቀማት ማስታወቂያ እንዳያስነግሩ በሕግ መከልከላቸው ጣቢያዎቹ ተወዳዳሪ ሆነው ህልውናቸውን ለማቆየት ደንቃራ ሆኗል፡፡

በእያንዳንዱ የቴሌቪዥን ጣቢያ ውስጥ ቢያንስ  10 አስር ጋዜጠኞች በቀሚነት ይሰራሉ ብንል 60 ያህል ጋዜጠኞች ከስራ ውጭ ሆነዋል ማለት ነው።

መረጃው የጋዜጠኛ ታምራት ኃይሉ ነው።

ለተጨማሪው :https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
📌ቅድመ ጥምረት

- በልባችሁ የፃፋችሁት የፍቅር ታሪክ ምንድነው?

- የህይወት መንገዳችሁ በትዳር እንዲሆን ከወሰናችሁ በኋላ የፍቅር ግንኙነት ለመጀመር ስታስቡ  "ትክክለኛው" ሰው ብላችሁ በልባችሁ ያሰባችሁት ሰው ለምን የለም?

- ያለፈው ያልተሳካው የፍቅር ግንኙነት ለምን አልተሳካም? በልባችን ምንስ ጥሎ  አለፈ?

- የፍቅር ግንኙነት ከመጀመር በፊት እራሴ ጋር ምን ልጨርስ?

-በትክክል የምፈልገው ምንድነው?

ካነበብናቸው መፅሐፍት፣ከሰማናቸው ታሪኮች፣ሙዚቃዎች፣ካደግንበት ማህበረሰብ፣ከኖርነው ኑሮ፣ካልተሳኩ የፍቅር ግንኙነት/ቶች ተነስተን በልባችን የፃፍነው የፍቅር ታሪክ አለን።

- በፍቅር ግንኙነት መንገድ ላይ ከሚመጣው ሰው ጋር ይህን በልባችን የሰራነውን የፍቅር ታሪክ እንኖረዋለን።

እነዚህን ጉዳዮች እንመክርባቸው ዘንድ ቅድመ ጥምረት የተሰኘ አስደሳች፣ መስተጋብራዊ እና ግንዛቤ የሚያስጨብጥ የስልጠና ፕሮግራም አዘጋጆተናል።

ስልጠናው የግንኙነት አቅምን ለማወቅ እና ለጤናማ፣ አስደሳች እና ዘላቂ አጋርነት የሚያስፈልጎትን  ክህሎቶች ለመማር የሚረዳ  የስልጠና ፕሮግራም ነው።
 
ካልተሳካ የፍቅር አዙሪት ለመላቀቅ ፣ እዉነተኛ የፍቅር ግንኙነት ውስጥ ለመግባት እና ለዘላቂ ግንኙነት ጠንካራ መሰረት ለመገንባት አሁኑኑ ይደውሉ ...0946-444445
ቀን :-ቅዳሜ፣ታህሳስ 05/2017 ዓ.ም
ቦታ :- ሲ ኤም ሲ ሚካኤል ኢትዮጵያን ኢኮኖሚክ አሶሴሽን አዳራሽ
መግቢያ ዋጋ :-300 ብር ብቻ

       ኑ ና ለፍቅር ተዘጋጁ!!
ኦሲስ ሥልጠናና ማማከር ማዕከል
https://news.1rj.ru/str/+ESVZ5qsyls9lODJk

📌Ads
📌የደጃፍ ፖድካስት ምዕራፍ ሶስት ነገ ይጀምራል።

በዳዊት ተስፋዬ የሚዘጋጀውና በበርካቶች ዘንድ ተወዳጅ የሆነው "ደጃፍ ከዳዊት ተስፋዬ ጋር" የፖድካስት ዝግጅት ምዕራፍ ሶስቱ ነገ ሐሙስ ታህሳስ 3 ቀን 2017 ዓ.ም ይጀምራል ተብሏል።

የምዕራፍ ሶስት ክፍል አንድ እንግዳ በመሆን በቅርቡ "አንድ ቃል" የተሰኘ የሙዚቃ አልበም ለአድማጮች ያደረሰው ድምጻዊ ሚካኤል በላይነህ በእንግድነት ይቀርባል።

ለተጨማሪው: https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
📌ተወዳጇ አርቲስት መሠረት መብራቴ በሎስአንጀለስ ሲቲ ካውንስል ተሸለመች።

በተለያዩ ፊልሞች፣ ቴአትሮች እና በማስታወቂያ ስራዎቿ አድናቆት የተቸራት፤ ጎን ለጎንም በምታበረክተው የበጎ አድራጎት አገልግሎት የበርካቶችን አክብሮትና ፍቅርን የተጎናፀፈችው አርቲስት መሠረት መብራቴ
በሎስአንጀለስ ከተማ Los Angeles city council እና U.S  Africa institute በጋራ ባዘጋጁት “Humanitarian Waward” የካውንስሉ አባላት በተገኙበት የእውቅና እና የክብር ሽልማት ተበርክቶላታል።

ካውንስሉ አርቲስቷ ለኢትዮጵያ የህፃት የልብ ህሙማን መርጃ ማእከል በበጎ ፈቃድ አምባሳደርነት እየሰጠች ያለውን አገልግሎት በማክበር በተለይም በአሜሪካን ሀገር የነበራትን  የተሳካ የገቢ ማሰባሰቢያ መርሀግብር በመጥቀስ የተለየ እውቅና እንደሚሰጠውና ለዚህ አገልግሎቷም አክብሮት እንዳለው በመግለፅ የእውቅናና የክብር ሰርተፊኬት አበርክቶላታል።

Via ሔሎ ኢትዮጵያ

ለተጨማሪው: https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
📌ተወዳጁ "የፍቅር ካቴና" ተውኔት ነገ አርብ በዓለም ሲኒማ በክብር ከመድረክ ይሰናበታል

ከአስር ዓመት በኃላ በድጋሚ ባሳለፍነው ዓመት ግንቦት 2 2016 ዓ.ም በዓለም ሲኒማ ወደ መድረክ የተመለሰው "የፍቅር ካቴና" ተውኔት ነገ አርብ  ታህሳስ 4 2017 ዓ.ም ከምሽቱ 12:00 ጀምሮ በክብር ከመድረክ ይሰናበታል ተብሏል።

በአርቲስት ወይንሸት አበጀ ፕሮዲዩስ የተደረገው ይህ "የፍቅር ካቴና" ተውኔት ድርሰትና ዝግጅቱ የአለልኝ መኳንንት ፅጌ ነው።

በተውኔቱ ድርብወርቅ ሰይፉ ፣ሚኪ ተስፋዬ ፣ ወይንሸት አበጀ ፣አሸናፊ ማህሌት በተዋናይነት ተሳትፉበታል።ተውኔቱም ዘወትር አርብ አመሻሽ ላይ ሲቀርብ ቆይቷል ።

በአርቡ የመዝጊያው መርሐግብር ላይ የቴአትር ወዳጆች እንድትገኙላቸው አዘጋጆቹ ጋብዘዋል።

ለተጨማሪው: https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
📌መቅረዝ ሥነኪን ዝግጅት ዛሬ ይካሄዳል

አንጋፋ እና ወጣት የኪነጥበብ ባለሞያዎችን እያጣመር የዘለቀው መቅረዝ ሥነኪን ወርሀዊ የኪነጥበብ  ዝግጅት ዛሬ ሐሙስ ታህሣሥ 3 ቀን 2017 ዓ.ም ከምሽቱ 11:00 ጀምሮ በብሔራዊ ቤተመዛግብትና ቤተመጻሕፍት አገልግሎት (ወመዘክር )አዳራሽ ውስጥ ይካሄዳል።

በዚህ ኪነጥበባዊ ዝግጅት ላይ አርክቴክት ሚካኤል ሽፈራው የክብር እንግዳ በመሆን የሚገኘ ሲሆን በተጨማሪም ወጣት የኪነጥበብ ባለሞያዎች የግጥም ፣የሙዚቃ ስራዎቻቸውን ያቀርባሉ።

የዚህ ዝግጅት መግቢያ በነፃ ነው።

ለተጨማሪው :https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
የቀን ለውጥ..

ውድ ቤተሰቦቻችን ለታህሳስ 5 የነበረው ቀጠሮአቸን ለታህሳስ 12,2017 ዓ.ም እንደተላለፈ ስናሳውቅ ከታላቅ ይቅርታ ጋር ነው።

- በልባችሁ የፃፋችሁት የፍቅር ታሪክ ምንድነው?

- የህይወት መንገዳችሁ በትዳር እንዲሆን ከወሰናችሁ በኋላ የፍቅር ግንኙነት ለመጀመር ስታስቡ  "ትክክለኛው" ሰው ብላችሁ በልባችሁ ያሰባችሁት ሰው ለምን የለም?

- ያለፈው ያልተሳካው  የፍቅር ግንኙነት ለምን አልተሳካም? በልባችን ምንስ ጥሎ  አለፈ?

- የፍቅር ግንኙነት ከመጀመር በፊት እራሴ ጋር ምን ልጨርስ?

-በትክክል የምፈልገው ምንድነው?

ካነበብናቸው መፅሐፍት፣ከሰማናቸው ታሪኮች፣ሙዚቃዎች፣ካደግንበት ማህበረሰብ፣ከኖርነው ኑሮ፣ካልተሳኩ የፍቅር ግንኙነት/ቶች ተነስተን በልባችን የፃፍነው የፍቅር ታሪክ አለን።

- በፍቅር ግንኙነት መንገድ ላይ ከሚመጣው ሰው ጋር ይህን በልባችን የሰራነውን የፍቅር ታሪክ እንኖረዋለን።

እነዚህን ጉዳዮች እንመክርባቸው ዘንድ ቅድመ ጥምረት የተሰኘ  አስደሳች፣ መስተጋብራዊ እና ግንዛቤ የሚያስጨብጥ የስልጠና ፕሮግራም አዘጋጆተናል።

ስልጠናው የግንኙነት አቅምን ለማወቅ እና ለጤናማ፣ አስደሳች እና ዘላቂ አጋርነት የሚያስፈልጎትን  ክህሎቶች ለመማር የሚረዳ  የስልጠና ፕሮግራም ነው።
 
ካልተሳካ የፍቅር አዙሪት ለመላቀቅ ፣ እዉነተኛ የፍቅር ግንኙነት ውስጥ ለመግባት እና ለዘላቂ ግንኙነት ጠንካራ መሰረት ለመገንባት አሁኑኑ ይደውሉ ...0946-444445
ቀን :-ቅዳሜ፣ታህሳስ 12/2017 ዓ.ም
ቦታ :- ሲ ኤም ሲ ሚካኤል ኢትዮጵያን ኢኮኖሚክ አሶሴሽን አዳራሽ
መግቢያ ዋጋ :-300 ብር ብቻ

       ኑ ና ለፍቅር ተዘጋጁ!!
ኦሲስ ሥልጠናና ማማከር ማዕከል
https://news.1rj.ru/str/+ESVZ5qsyls9lODJk

📌Ads
📌"ቀይ ካርድ" ፊልም ዛሬ ለእይታ በቃ።

በኖላዊ ፊልም ፕሮዳክሽን የተሰናዳው የየአብስራ ዶጮ "ቀይ ካርድ" የተሰኘው ሀገርኛ ፊልም  ዛሬ ታህሳስ 4 2017 ዓ.ም በሁሉም ሲኒማ ቤቶች ለእይታ በቅቷል።

"ቀይ ካርድ" የተሰኘው ፊውቸር ፊልም አንጋፋ እና አዳዲስ ተዋንያን የተሳተፉበት በድርጊት የታጀበ ልብ አንጠልጣይ የወንጀል ፊልም እንደሆነ ተገልጿል።

ቃልኪዳን ጥበቡ ፣ኤርሚያስ ታደሰ ፣ይሄነው አበበ ፣አንተነህ ጌታቸው እና ሌሎችም በትወና ተሳትፉበውታል።

1:30 ረዝማኔ ያለው ፊልሙ ሁለት አመት የፈጀ ሲሆን በአጠቃላይ ከ3 ሚልየን ብር በላይ ወጪ ተደርጎበታል።

"ቀይ ካርድ" ፊልሙ ውስጥ ባሉ ገፀ ባህሪያት የተፈጠረ እራሱን የቻለ ምናባዊ የፍትህ ስርዓት ሲሆን በዋናነት የሚያጠነጥነው በአንድ መስሪያ ቤት ውስጥ የተፈፀመን ሚስጥራዊ የወንጀል ታሪክ ለመፍታት በሚደረገው ጥረት ውስጥ የሚጋጥመውን ውጣውረድ እና ካለፈ ህይወት ጋር የሚደረግ የአይምሮ ግጭትን የሚያሳይ ተጨባጫ እውነት ላይ ያተኮረ በድርጊት የታጀበ ልብ አንጠልጣይ ፊልም ነው
ሲል የፊልሙ አዘጋጅ የአብስራ ዶጮ ለአርትስ ቴሌቪዥን ገልጿል።

ለተጨማሪው :https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
📌ደራሲ አዳም ረታ ከደራሲ እንዳለጌታ ከበደ ጋር ያደረጉት ሥነጽሑፋዊ ውይይት ተለቀቀ

አንጋፋው ደራሲ አዳም ረታ ከደራሲ እንዳለጌታ ከበደ ጋር "በነገረ-መጻሕፍት" ልዩ ዝግጅት ያካሄዱት ሥነጽሑፋዊ ውይይት በእንዳለጌታ ከበደ መልቲሚዲያ ዩቲዩብ ቻናል በኩል ለተመልካች ቀርቧል።

በዚህ ከአንድ ሠዓት በላይ በወሰደው ውይይት ላይ በርካታ ሥነጽሑፍ ጉዳዮች ተነስተዋል።

ደራሲ አዳም ረታ እንዲህ ዓይነት ረጅም ቃለመጠይቅ ሲያደርግ ከበርካታ ዓመታት በኃላ ይህ የመጀመሪያው ነው።

ሙሉ ውይይቱን በዚህ ሊንክ መከታተል ትችላላችሁ:

https://youtu.be/MpI5r6JjCwY?si=E2mtRmmWciKWPYO0

ለተጨማሪው :https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
📌የየሺህ ጋብቻ ብራንድ አምባሳደሮች

አርቲስት ተስፋዓለም ታምራትና ቃልኪዳን አበራ እንዲሁም አርቲስት ይገረም ደጀኔ እና ፅዮን ዮሴፍ የዘንድሮው የ"የሺህ ጋብቻ" የጋብቻ ፌስቲቫል ብራንድ አምባሳደር በመሆን ተሹመዋል።

በያሜንት ኤቨንትስ የሚዘጋጀው "የሺህ ጋብቻ" የዘንድሮው የጋብቻ ሥነሥርዓት ጥር 18 ቀን 2017 ዓ.ም በሚሊኒየም አዳራሽ ይካሄዳል ተብሏል።

ዘንድሮ ከሀገር ውስጥ 1ሺህ ጥንዶችን እንዲሁም 250 የሚደርሱ ጥንዶችን ከተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት በማካተት በአጠቃላይ ከ1250 በላይ ጥንዶች የፊታችን ጥር 18 ቀን 2017 ዓ.ም ጋብቻቸውን ይፈፀማሉ።

በዚህ ግዙፍ የጋብቻ ሥነሥርዓት በተለየ መልኩ ከሚኖሩ ክንውኖች መካከል ከ25 ሺህ በላይ የቡና ሲኒ እንዲሁም 2017 ኪ.ግ የሚመዝን ባህላዊ ዳቦ ለታዳሚዎች  ይቀርባል ተብሏል።

ሁነቱንም በዓለም ድቃድንቅ መዝገብ ላይ እንዲስፍር ለማድረግ የሚሠራበት ታላቅ ዝግጅት ይሆናል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

የሺህ ጋብቻ ትልቅ ዓላማ የኢትዮጵያን እንዲሁም የአፍሪካ ሀገራት ህዝቦችን የካበተ ባህላዊ የሰርግ ሥነ-ሥርዓት አጉልቶ በማሳየት አዲስ አበባን የሃኒሙን ማዕከል ማድረግ እንደሆነ አዘጋጆቹ ገልጿል።

አጠቃላይ ለዚህ ፕሮጀክት ዕውን መሆን ያስፈልጋል ተብሎ የታቀደው በጀት 68,997,500 ብር እንደሆነ ተነግሯል።

"የሺህ ጋብቻ"  ከዚህ ቀደም በ2005 እና በ2016 ዓ.ም ስኬታማ የብዙኃን  ጋብቻዎችን አከናውኗል።

የጋብቻ ፌስቲቫሉ በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን በቀጥታ ስርጭት ይተላለፋል።

ለተጨማሪው: https://news.1rj.ru/str/EventAddis1