Event Addis Media – Telegram
Event Addis Media
9.61K subscribers
6.11K photos
13 videos
4 files
4.73K links
Connect with Addis artistic community!

Website: https://eventaddis.com

Contact: @Tmanaye
Download Telegram
📌አራተኛው አርኪ የሪል ስቴት ኤክስፖ በስካይ ላይት ሆቴል ተከፈተ

የቤት ሻጮችና ገዢዎች፣ እንዲሁም ገንቢዎች የተለያዩ ተቋማትን ለማገናኘትና ለማስተሳስር ዕድል ይሰጣል የተባለለት አራተኛው አርኪ ሆምስ ኤክስፖ በዛሬው ዕለት በስካይ ላይት ሆቴል በይፋ ተከፍቷል።

ከዛሬ ታህሳስ 25 እስከ ታህሳስ 27/2017 በሚካሄደው በዚህ ኤክስፖ በርካታ የቤት አልሚዎች እየገነቡት ስላለው ቤት ግንባታዉ ያለበት ደረጃ፣ ሊገነቡት ስላቀዱት ቤት፣ ቤቶቹን ዋጋ፣ ስለሚፈልጉት እቃ እና አገልግሎት ከኤክስፖ ተሳታፊዎችና ከጎብኚዎች ጋር መረጃና ልምድ ይለዋወጣሉ ተብሏል።

ወቅቱ የበዓል እንደመሆኑ በርካታ ዲያስፖራዎች ወደ ሀገር ቤት የሚገቡ በመሆኑ የኤክስፖውን ሳይጎበኙ ቤት እንዳይገዙ በሚል ሙሉ ቅድመ ዝግጅት የተደረገበት ልዩ የገና በዓል ቅናሽ መኖሩም ተገልገልፃል።

አርኪ ኤቨንት ኦርጋናይዘር ያዘጋጀው ይሄ ኤክስፖ በዘርፉ ላይ የተሰማሩ የቤት አልሚ ድርጅቶች እና አጋር አካላት እንደሚሳተፉ የተገለፀ ሲሆን ኤክስፖው መንግሥታዊና መንግሥታዊ ያልሆኑ ተቋማትን ፤ አንድ ላይ በማቀናጀት በከተማ እንዲሁም በአገር አቀፍ ደረጃ ሊሰሩ የታሰቡ መዋቅራዊ ቅንጅቶችን ለመፍጠር ምቹ ዕድል የሚፈጥር ገዥና ሻጭን በአንድ ላይ በማገናኘት በቀጥታ የሚፈልጉትን የቤት ዓይነት የሚመርጡበት ስለአጠቃላይ ሂደት በግልፅ መረጃ የሚለዋወጡበት በርካታ አማራጮች ያሉበት ለተረጋጋና ምክንያታዊ የቤት ግዥ ዉሳኔ ምቹና ዓይነተኛ አጋጣሚ እንደሚፈጥር የዝግጅት ክፍሉ ያስታወቀ ሲሆን ሁሉም ቤት ገዥ እና አልሚ ይህ ዕድል ሳያመልጠዉ ኤክስፖዉን እንዲሳተፍ ጥሪ አቅረቧል፡፡

ለተጨማሪው: @EventAddis1
📌የ"ፈለገ ኪን" የኪነጥበብ ዝግጅት ዛሬ ይካሄዳል

በኢትዮጵያ አይነ ስውራን ብሄራዊ ማህበር የሚዘጋጀው "የፈለገ ኪን" አምስተኛ የኪነጥበብ ዝግጅት ዛሬ ቅዳሜ ታህሳስ 26 ቀን 2017 ዓ.ም ከቀኑ 8 ሰአት ጀምሮ ስድስት ኪሎ በሚገኘው የማህበሩ ጽ/ቤት  ይካሄዳል።

ባለፉት አራት መድረኮች እንደተደረገው ሁሉ አምስተኛው መርሀግብር ዓይነ ስውራንና የዓይነ ስውራን ወዳጆች የሆኑ ባለተሰጥዖዎች የሙዚቃ፣ የሥነግጥምና የተለያዩ የስነ ጽሁፍ ችሎታዎቻቸውን የሚያሳዩበት መድረክ ነው ተብሏል።

በዕለቱም አብዬ መንግስቱ ለማ  ይዘከራሉ፤ አንጋፋው ደራሲ አበራ ለማ ደግሞ የዕለቱ ተጋባዥ እንግዳ ሆነው እንደሚገኙ ተገልጿል።

አዘጋጆቹ "በመርሃግብሩ ላይ በመታደም ከአይነስውራን አእምሮ የፈለቁ  እምቅ፣  ጥልቅ፣ ምጡቅ  የስነ ጽሁፍ፣ የሙዚቃና የፍልስፍና ጠለ በረከቶችን ይቋደሱ " ብለዋል።

ለተጨማሪው: https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
📌"ያልተወጋ ፍቅር "መጽሐፍ ዛሬ ይመረቃል።

በመምህርትና ገጣሚ ይሳለም አዳሙ የተዘጋጀው "ያልተወጋ ፍቅር" የተሰኘ መጽሐፍ ዛሬ ታህሳስ 26 ቀን 2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 4:00 ጀምሮ በወመዘክር አዳራሽ ይመረቃል።

በዕለቱም አርቲስት ስዩም ተፈራ፣ደራሲ የዝና ወርቁ፣ደራሲ አበራ ለማ፣ገጣሚ ፍሬሕይወት መላኩ እና ሌሎችም በክብር እንግድነት ይገኙበታል።

መምህርትና ገጣሚ ይሳለም አዳሙ ለ4 ዓመታት በመምህርነት፣ ለ12 ዓመታት በምክትል ር/መምህርነት ሠርታለች።

ለተጨማሪው: https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
📌ሀገራችን ኢትዮጵያ በሉሰበርግ ልትመሰገን ነው

‎የቀዳማዊ ኃይለሥላሴ የአውሮፓ ጉብኝትን 100ኛ ዓመት በማስመልከት በሉክሰምበርግ ከተማ ማዘጋጃ ቤት  የማስታወሻና የምስጋና ዝግጅት የፊታችን ጥር 1 ቀን 2017 ዓ.ም  ይካሄዳል።

‎በዕለቱ የኢትዮጵያና የሉክሰምበርግ ሠዓሊያን  ወቅቱን የሚያስታውስና ነጻ የፈጠራ ሥራቸውን የሚያቀርቡ ሲሆን የሥዕል ትርዒት ይከፈታል ተብሏል።

‎በመርሃግብሩ ላይ አስር የሀገራችን ሠዓሊዎች ሥራቸውን የሚያቀርቡ ሲሆን ሠዐሊና መምህር ኃይሉ ክፍሌ ሀገሩን ወክሎ ንግግር እንደሚያቀርብ ይጠበቃል።

‎የንጉሱ የሉከሰምቦርግ ጉብኝትለየት  የሚያደርገው በወቅቱ በነበረው የአንደኛው  የዓለም ጦርነት ጉዳት ምክንያት የገንዘብ  ልግስና ማድረጋቸው ሲሆን ፣በዚህ ዝግጅት  ላይም የከተማዋ ከንቲባና ንጉሳዊያን ቤተሰቦችንጨምሮ  ታላላቅ  እንግዶች  በመገኘትንግግር  እንደሚያደርጉ፣ ኢትዮጵያንም እንደሚያመሰግኑ ይጠበቃል ።

‎ተፈሪ መኮንን ት/ቤት ከዚህ የአውሮፓ ጉብኝት  በኋላ መከፈቱን ይታወሳል።

ለተጨማሪው: https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
📌የመቅረዝ ሥነኪን የኪነጥበብ ዝግጅት ሁለተኛ ዓመት ክብረ በዓል ልዩ ፕሮግራም ነገ ይካሄዳል።

አንጋፋ እና ወጣት የኪነጥበብ ባለሞያዎችን እያጣመር ለሁለት ዓመታት የዘለቀው መቅረዝ ሥነኪን ወርሀዊ የኪነጥበብ  ዝግጅት ነገ ሐሙስ ጥር 1 ቀን 2017 ዓ.ም ከምሽቱ 11:00 ጀምሮ በብሔራዊ ቤተመዛግብትና ቤተመጻሕፍት አገልግሎት (ወመዘክር )አዳራሽ ውስጥ ይካሄዳል።

በዚህ የሁለተኛ ዓመት ክብረ በዓል ልዩ ኪነጥበባዊ ዝግጅት ላይ አርቲስት እታፈራሁ መብራቱ የክብር እንግዳ በመሆን የምትገኝ ሲሆን በተጨማሪም ወጣት የኪነጥበብ ባለሞያዎች የግጥም ፣የሙዚቃ ስራዎቻቸውን ያቀርባሉ።የዚህ ዝግጅት መግቢያ በነፃ ነው።

ለተጨማሪው: https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
📌"ቃልና ሙዚቃ" የተሰኘ ውይይት ነገ ይካሄዳል። ይህ ልዩ ውይይት ነገ ጥር 1 2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 3:30 ጀምሮ አራት ኪሎ በሚገኘው አለ የሥነጥበብና ዲዛይን ት/ቤት ውስጥ ይካሄዳል።በዚህ ውይይት ላይ የሙዚቃ ባለሞያዋ ትሬዛ ዮሴፍ ዳሰሳ ታቀርባለች ተብሏል።

ለተጨማሪው: https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
📌"ጀቢና"ፊልም ለእይታ ሊበቃ ነው።

በደራሲና ዳይሬክተር ሳሙኤል ተሻገር የተዘጋጀውና "ጀቢና" የተሰኘ ርዕስ የተሰጠው አዲስ ኢትዮጵያዊ ፊልም ለእይታ ይበቃል። "ጀቢና" በእውነተኛ ታሪክ የተመሰረተ ፊልም እንደሆነ የተገለፀ ሲሆን በአሁን ፊልም ፕሮዳክሽን ተዘጋጅቶ በለታሪክ ፊልም ፕሮዳክሽን የቀረበ ነው።

በፊልሙ ላይ ቤተልሔም ሸረፈዲን፣እታፈራሁ መብራቱ፣ ካሣሁን ፍስሃ(ማንዴላ)፣ ናትናኤል መኮንን፣አስራት ታደስ እና ሌሎችም ተውነውበታል።

ይህ ፊልም ጥር 5 ቀን 2017 ዓ.ም በአዲስ አበባ ከተማ በሚገኙ ሲኒማ ቤቶች ለእይታ ይበቃል ተብሏል።

ለተጨማሪው: https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
📌የድምፃዊ አህመድ ሁሴን(ማንጁስ) አልበም

የድምፃዊ አህመድ ሁሴን (ማንጁስ) "አልጣሽ" ሲል የሰየመውን የመጀመሪያ አልበሙን በዚህ ወር ለአድማጮች እንደሚያደርስ ተገልጿል።

በዚህ አልበም ወጣት እና አንጋፋ የሙዚቃ ባለሞያዎች የተሳተፉ ሲሆን በግጥም ይልማ ገብረዓብ ፣ ናትናኤል ግርማቸው ፣ መሰለ ጌታሁን ፣ ተስፋ ብርሀን በዜማው አበበ ብርሀኔ ፣ አቤል ሙሉጌታ ፣ አህመድ ተሾመ(ዲንቢ)) በቅንብር አበጋዝ ክብረ ወርቅ ሽዎታ አብዛኛውን ያቀናበረ ሲሆን ቀሪውን ከአቤል ጳውሎስ በጋራ ሰርተውታል፡፡

ይህ የድምጻዊ አህመድ ሁሴን (ማንጁስ) አዲስ አልበም ጥር 16 2017 ዓ.ም በናሆም ሪከርድስ በኩል ለሙዚቃ አድማጮች ይደርሳል፡፡

ድምጻዊው "ደሴ ላይ" ፣ "ልቤ አቃተው" እና ሌሎችም ነጠላ ሙዚቃዎች ከዚህ ቀደም ለአድማጮች አድርሷል።

ለተጨማሪው: https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
📌"KITFO film festival" ነገ ይካሄዳል!

(መግቢያው በነፃ ነው)

ፕሪስቲጅ አዲስ የኢትዮጵያን የጥበብ ኢንዱስትሪ ላቅ ወዳለ ደረጃ ለማድረስ እየሰራ የሚገኝ ተቋም ሲሆን ከ2012 ዓም ጀምሮ ወጣትና አንጋፋ ለሆኑ የፊልም ባለሙያዎች ተሞክሯቸውን ለወጣቶች ሚያጋሩበት አስተማሪ የሆነ መድረክን ገንብቷል።

ይህንን ተግባሩን ያጠናክር ዘንድ "KITFO film festival" የተሰኘ  የፊልም ፌስቲቫልመቀመጫውን አሜሪካ ካደረገው "KITFO TV" ጋር በመተባበር አዘጋጅቷል ።

ዝግጅቱም ነገ አርብ ጥር 2 ቀን 2017 ዓ.ም በአዲስ አበባ በሚገኘው የጣሊያን የባህል ማዕከል የሚካሄድ ሲሆን በዚህም ፌስቲቫል ስድስት ሀገርኛ እንዲሁም ኢንተርናሽናል ፊልሞች ይቀርባሉ።ነፃ ምግብና መጠጦችም ይኖራል።መግቢያውም ሙሉ በሙሉ በነፃ ነው።

ይህንን የፊልም ፌስቲቫል ነገ ከቀኑ 7:00 ጀምሮ መታደም ትችላላችሁ ተብላችኋል።

ለተጨማሪው: https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
📌ኤም  ኤን ጂ ፊልም ፕሮዳክሽን እና ኢቨንት ኩባንያ የፊልም ስክሪፕት ግዢ ስምምነት ተፈራረመ። 

ስምምነቱ ኩባንያው እየሰራ ከሚገኘው የፊልም ማርኬቲንግ ሥራ በተጨማሪ በፊልሙ ኢዱስትሪውን ውስጥ ለመፍጠር ላልመው በጎ ተፅዕኖ የመጀመሪያ እርምጃ መሆኑን በፊርማ ሥነ-ሥርዓቱ ላይ አስታውቋል።

ኩባንያው በኢትዮጵያ ቢሮውን ከመክፈቱ አስቀድሞ ከፓራ ማውንት፣ ሶኒ ፒክቸርስ እና ሌሎች የፊልም ኩባንያዎች ጋር ሥራዎችን ሲሰራ የቆየ ሲሆን በኢትዮጵያ ቢሮውን በከፈተ ማግስት በተለያዩ በጎ ተግባራትን ሲፈፅም እንደቆየም ሰምተናል።

የኩባኛውን በኢትዮጵያ ሥራ መጀመር በማስመልከት በመጀመሪያ የወደቁትን አንሱ የነድያን መርጃ ማሕበር የተለያዩ የምግብ ቁሳቁሶችን ድጋፍ ያደረገ ሲሆን ከ6 ወር በኋላ ደግሞ ለንሕምያ የኦቲዝም ሴንተር የተለያዩ የንፅሕና እና መማሪያ ቁሳቁሶችን ድጋፍ ማድረግ ችሏል።

በዛሬው ዕለት የተደረገው የፊርማ ሥነሥርዓት የፊልም ሀሳብ ያላቸው ደራሲያን ስክሪፕታቸውን ሸጠው በሌሎች አካላት ሥም ለዕይታ ይበቃ የነበረበትን ልማድ በማስቀረት ደራሲያን በፊልም ፕሮዳክሽን ውስጥ እውቅና ሊሰጣቸው እንደሚገባ ለማሳየት የተደረገ እንደሆነም ከመድረኩ ለማወቅ ችለናል።

ለተጨማሪው: https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
በ3.5 ሚሊዮን ብር የታተመው የአርቲስት መሀሙድ አህመድ የህይወት ታሪክ መጻሕፍ ተመረቀ

የአርቲስት መሀሙድ አህመድ ካሁን ቀደም ያልተሰሙ የህይወት ገጽታዎች ያካተተውና በደራሲ ወሰን ደበበ ማንደፍሮ የተዘጋጀው
መጻሕፍ ትላንት ጥር 1 ቀን 2017 ዓ.ም በማሪዮት ሆቴል ተመረቋል።

አርቲስት መሀሙድ አህመድ ላለፉት 63 ዓመታት በሙዚቃው ዓለም ያሳለፋቸውን ውጣ ውረዶች ፣ የቤተሰብ የኋላ ታሪክና የወዳጅ ጓደኞቹን እንዲሁም የሙያ ባልደረባዎቹን ምስክርነት አካቶ የያዘው የሕይወት ታሪክ መጻሕፍ ለማዠጋጀት አስር ዓመታት እንደፈጀ በምርቃት ዝግጅት ላይ ተገልጿል።

ንብ ባንክ በ3.5 ሚሊዮን ብር ህትመቱን ስፖንሰር ማደርጉ
በዕለቱ ተገልጿል። መጻሕፉ ለምረቃ በበቃበት ዕለት በልዩ
ሁኔታ የታተመውንና አምስት ሺህ ብር ዋጋ የተቆረጠለት መጻሕፍ ለሽያጭ ቀርቦ በማሪዮት ሆቴል የተገኙ እንግዶች ገዝተዋል።

በልዩነት ግን ኢንጂነር ቢጃናይ እና ዶ/ር ሐውለት አሕመድ 500 መጻሕፍትን በ2.5 ሚሊዮን ብር የገዙ ሲሆን የሰን ሻይን ሪል ስቴት ባለቤት አቶ ሳሙኤል ታፈሰ በ500 ሺ ብር 100 መጻሕፍት ገዝተዋል።

ዘገባው የባላገሩ ቴሌቪዥን ነው።