Event Addis Media – Telegram
Event Addis Media
9.63K subscribers
6.1K photos
13 videos
4 files
4.72K links
Connect with Addis artistic community!

Website: https://eventaddis.com

Contact: @Tmanaye
Download Telegram
📌ጋዜጠኞቹ ደመወዝ እየተከፈላቸው አይደለም ተባለ

የደቡብ ሬዲዮና ቴሌቪዥን ድርጅት ሠራተኞች ደመወዝ እየተከፈላቸው አለመሆኑንና መቸገራቸውን ተናገሩ።

በቀድሞው የደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል ይተዳደር የነበረው ‹‹የደቡብ ሬዲዮና ቴሌቪዥን ድርጅት››፣ ክልሉ ለአራት ከተከፋፈለ በኋላ፣ እያንዳንዳቸው ክልሎች የሚጠበቅባቸውን በጀት ባለመስጠታቸው፣ ቀናቶች ካለፉ በኋላ ይከፈላቸው የነበረው ደመወዝ ሙሉ በሙሉ መቆሙንና እየተቸገሩ መሆናቸውን የድርጅቱ ሠራተኞች ተናገሩ፡፡

ሪፖርተር ጋዜጣ ያነጋገራቸውና ስማቸው እንዳይገለጽ የፈለጉ የጣቢያው ሠራተኞች፣ ላለፉት ስድስት ወራት ደመወዛቸው በጊዜው እንደማይከፈላቸውና ወሩ ባለፈ በ15ኛው ቀን ይከፈላቸው የነበረ ቢሆንም፣ የሰኔ ወር ደመወዝም ግን ሙሉ በሙሉ እንዳልተከፈላቸው ተናግረዋል፡፡

ከ400 በላይ ሠራተኞች ያሉት ድርጅቱ፣ አብዛኞቹ ሠራተኞች ከተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች የተውጣጡ በመሆናቸው፣ በተለይም ከቤተሰቦቻቸው ርቀው የሚኖሩ በደመወዝ መዘግየት ምክንያት ከፍተኛ ጫና ውስጥ መግባታቸውን ገልጸዋል፡፡

‹‹የድርጅቱ ህልውና አደጋ ላይ ወድቋል›› የሚሉት ሠራተኞቹ፣ ለዚህም ወደ ሌሎች የቴሌቪዥንና የሬዲዮ ጣቢያዎች እየሄዱ መሆኑን በማሳያነት ይጠቅሳሉ፡፡

ጉዳዩን አስመልክቶ ሪፖርተር ያነጋገራቸው የድርጅቱ ምክትል ዋና ሥራ አስፈጻሚና የተቋሙ ተወካይ አቶ ዘለዓለም ገነሞ፣‹‹ድርጅቱ ችግር ውስጥም ሆኖ ቢዘገይም ሳይከፍል የቀረበት ጊዜ የለም››ሲሉ ተናግረዋል።

©️ሪፖርተር ጋዜጣ

ለተጨማሪው:https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
7😢2
📌በርካቶች የተቀባበሉት ነጠላ ሙዚቃ

በድምጻዊት ሳምራት አዘነ የተቀነቀነው "አያ ጥራኝማ" የተሰኘ ርዕስ የተሰጠው ነጠላ ሙዚቃ ዛሬ ነሐሴ 2 2017 ዓ.ም በናሆም ሪከርድስ በኩል ለአድማጮች ከተለቀቀ በኃላ ፌስቡክን ጨምሮ በተለያዩ የማህበራዊ ትስስር ገፆች ላይ በርካቶች እየተቀባበሉ ስለ ሙዚቃው እየጻፉ ይገኛሉ።

"አያ ጥራኝማ" ሙዚቃ ላይ በዜማ ይልቃል አስፋው፣ በግጥም እስጢፋኖስ መስፍን እንዲሁም በቅንብር ታምሩ አማረ ተሳትፈውበታል።

የሙዚቃ ቪዲዮውን ዮናስ ይታየው ዳይሬክት ያደረገው ሲሆን በዋሽንት ጣሰው ወንድም ተሳትፏል።

ድምጻዊት ሳምራዊት አዘነ የሙዚቃ ባለሞያ ስትሆን የኢትዮጵያን አይዶል ዳኛ እና የመረዋ ኳየር የሙዚቃ ቡድን አባል ነች።

ለተጨማሪው:https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
9👍3
📌አንጀሊና ጆሊ የቅዱስ ጴጥሮስ ሆስፒታልን ጎበኙ

ዝነኛዋ አሜሪካዊት ተዋናይት ፣ የፊልም ባለሙያ እና የሰብአዊ ድጋፍ አቅራቢ የሆኑት አንጀሊና ጆሊ በዛሬው ዕለት የቅዱስ ጴጥሮስ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታልን ጎብኝተዋል።

ተዋናይቷ ያደረጉት ጉብኝት በዋነኝነት ሆስፒታሉ እየሰጠ በሚገኘው መድሃኒቱን የተላመደ ቲቢ (ኤም.ዲ.አር ቲቢ) ህክምና ዙሪያ እየተከናወኑ ያሉ እንቅስቃሴዎችን ፣ የሚታዩ ለውጦችን እንዲሁም ድጋፍ የሚያስፈልጋቸውን ቦታዎች መለየት ላይ ትኩረት ያደረገ ነበር።

በጉብኝቱ ላይ አንጀሊና የሆስፒታሉን የቲቢና መድሃኒቱን የተላመደ ቲቢ (ኤም.ዲ.አር ቲቢ) ህክምና አገልግሎት መስጫ ዋርድ ፣ ላብራቶሪ እንዲሁም ታካሚዎችን ተዘዋውረው ተመልክተዋል።

አንጀሊና ወደ ሆስፒታሉ ከረጅም ጊዜያት በፊት መጥተው እንደነበር ያስታወሱ ሲሆን በአሁኑ ጉብኝታቸው ላይ ሆስፒታሉ ዘርፈ ብዙ ለውጦች አምጥቶ በመመልከታቸው እጅግ ደስተኛ መሆናቸውን ተናግረዋል።

አክለውም ሆስፒታሉ ድጋፍ ቢደረግለት በቀጣይ የተሻለ
አገልግሎት ለታካሚዎች መስጠት በሚያስችለው አስተማማኝ ደረጃ ላይ እንዳለ በጉብኝቱ ላይ መገንዘባቸውን ገልፀዋል።

በተጨማሪም በሆስፒታሉ በቲቢ ህክምና አገልግሎት አሰጣጥ ላይ የተገኘው እድገት በእጅጉ የሚደነቅ እና የሚያስተማምን ስለሆነ በቀጣይ በጂ.ኤች.ሲ (Global Health Committee (GHC)) በኩል ድጋፍ እናደርጋለን ብለዋል።

የሆስፒታሉ ዋና ስራ አስፈፃሚ ዶ/ር አብርሃም እሸቱ በበኩላቸው ቲቢን ለማጥፋት በሚደረገው ጥረት ውስጥ ተዋናይቱ ላሳዩት ዘላቂ ቁርጠኝነት ፣ ልግስና እና በቀጣይ ለሚያደርጉት ድጋፍ ከፍተኛ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

Via ቅዱስ ጴጥሮስ ሆስፒታል

ለተጨማሪው:https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
19🤣8🥰1
📌‘ኢመርጅ’ የሥነጥበብ አውደርዕይ ተከፈተ

አስር ሁለት ሠዓሊያ እና የፊልም ባለሞያዎች ስራዎቻቸውን ያቀረቡበት "ኢመርጅ" ዘመናዊ የሥነጥበብ አውደርዕይ ነሐሴ 7 2017 ዓ.ም በገብረክርስቶስ  ደስታ ዘመናዊ የሥነጥበብ ሙዚየም ውስጥ በይፋ ተከፍቷል።

ይህ ‘ኢመርጅ’ ዘመናዊ የሥነጥበብ አውደርዕይ ለሁለት ዓመት በድህረ ምረቃ መርሀግብር፥ ከአለ የሥነጥበብና ዲዛይን ት/ቤት በሥነጥበብ እና በፊልም ጥበብ ዘርፍ ትምህርታቸውን ተከታትለው በሰኔ 2017 ዓ.ም ያጠናቀቁ ተማሪዎች መካከል የተመረጡ ስድስት ሠዓሊያንን እና ስድስት የፊልም ባለሙያዎችን የመመረቂያ ጥናታዊ የሥራ ውጤት ለሰፊው ህዝብ ለማሳየት በዘመናዊ የሥነጥበብ ሙዚየም - ገብረክርስቶስ ደስታ ማዕከል የተዘጋጀ ዐውደርዕይ ነው።

በዚህ ዐውደርእይ ላይ የቀረቡት ስራዎች ስለ: ማህበራዊ፣ ልማታዊ ለውጥና ተጽእኖው፣ ሥነጥበባዊ የአእምሮ ህክምና፣ ሶሻል ሚዲያና ተጽእኖው እንዲሁም ከሀገር እስከ ዓለም አቀፍ እየደረሰ ስላለው የተሳሰረ ኢፍትሀዊ ብዝሀ ችግሮች ዙሪያ የሚዳስሱ ርዕሰ ጉዳዮች በዘመናዊ የሥነጥበብ አውድ ቀርበዋል።

ተሳታፊ ሠዓሊዎች፦
አለማየሁ ዳርሰማ፣ ማስተዋል ጌታ፣ ሙሉአዳም አዳነ፣ ሰሎሜ ጌታቸው፣ ቴዎድሮስ ክፍሌ፣ ዮናስ ፍቃዱ

ተሳታፊ የፊልም ባለሙያዎች፦
አቢይ ጌታሁን፣ አብርሐም ባህሩ፣ ኤልሻዳይ ይልማ፣ ጌታሁን ግርማ፣ ሊዲያ ምትኩ፣ ታደሰ በቀለ

የማዕከሉ የእይታ ሰዓት፡ ከማክሰኞ - እሁድ ከጠዋት 4:00 ሰዓት - አመሻሽ 11:00 ሰዓት
ቦታ፡ 6 ኪሎ ምስካየ ሓዙናን መድሃኒያለም ገዳም ከፍተኛ ትምህርት ቤት ጎን በሚገኘው የንግድና ኢኮኖሚ ኮሌጅ አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ቅጥር ጊቢ ውስጥ።

ለተጨማሪው:https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
4
📌ግራንድ ጮሮርሳ ኮንሰርት ሊካሄድ ነው

ግራንድ ጮሮርሳ ኮንሰርት የፊታችን ነሐሴ 17 2017 ዓ.ም በኢንተርኮንቲኔንታል ሆቴል እንደሚካሄድ የፕሮግራሙ አዘጋጅ Nethor events አስታውቋል።

በግራንድ ጮሮርሳ ኮንሰርት ታዋቂዎቹ ድምጻዊያን ሄለን በርሄ ፣ዮሳን ጌታሁን፣ሌንጮ ገመቹ፣ጌታቸው ኃይለማርያም፣አኒስ ጋቢ - ጆርጂ አቡ እና ሌሎችም የሙዚቃ ስራዎቻቸው ያቀርባሉ ተብሏል።

በዝግጅቱ ላይ በአፍሪካ ረጅሙ የጮርሮሳ ምግብ በአፍሪካ ድንቃድንቅ መዝገብ ላይ ይመዘገባል ተብሏል።

የመግቢያ ክፍያ ቪአይፒ: 10,000 ቪቪአይፒ: 15,000 ብር ነው ተብሏል።

የኮንሰርቱ አዘጋጆች Nethor events እና Kenakon events ሲሆኑ "ይምጡ ባህሎቻችንን ይደግፉ እና ይደሰቱ" ብለዋል።

ለተጨማሪው:https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
5
📌የልጆች መጻሕፍት ላይ ውይይት ይካሄዳል

በኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ ብላቴን ጌታ ኅሩይ ወልደ ሥላሴ የሥነ ጥበባት ማዕከል የልጆች መጻሕፍት በኢትዮጵያ በተሰኘ ርዕስ የልምምድ ልውውጥና ሙያዊ ውይይት ይካሄዳል፡፡

ሙያዊ ውይይቱ የፊታችን ቅዳሜ ነሐሴ 10 2017 ዓ.ም ከቀኑ 8:00 ጀምሮ በኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ የብላቴን ጌታ ኅሩይ ወልደ ሥላሴ የሥነጥበባት ማዕከል ይካሄዳል።

የዕለቱ ተጋባዥ ከ120 በላይ መጻሕፍትን ለሕትመት ያበቃው የልጆች መጽሐፍ ደራሲ፣ ተርጓሚና የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የቀድሞ መምህር ዓለም እሸቱ ሲሆን በአሁኑ ወቅት ኑሮውን በሀገረ አሜሪካ አድርጓል፡፡

በዕለቱ የሥነ ጥበባት ማዕከሉ ዳይሬክተር አቶ ይታገሱ ጌትነት በኢትዮጵያ የልጆች መጻሕፍት ታሪክና ተግዳሮት ዙሪያ የመነሻ ጽሑፍ ያቀርባሉ፡፡

ይህ መርሃ ግብር በኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ እና በኢትዮጵያ ቤተመዛግብትና ቤተመጻሕፍት ትብብር በኢትዮጵያ ደራስያን ማኅበር አማካኝነት የሚሰናዳው የክረምት ወራት የሥነ ጽሑፍ ሥልጠና አንዱ አካል ሲሆን በዕለቱ በዘርፉ የተሰማሩ የልጆች መጽሐፍ ደራሲያንና ባለሙያዎችና ይሳተፋሉ፡፡

ለተጨማሪው:https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
4
📌 የአንጋፋው ደራሲ ሳህለ ሥላሴ ብርሃነማርያም ልደት በልዩ ዝግጅት ዛሬ ይከበራል

ጥበበ መድሎት የጋዜጠኝነትና የኪነ ጥበብ ሰልጣኞች አንጋፋ የኢትዮጵያ የስነ ጽሁፍ ባለውለታዎችን ለመዘከር ቀጠሮ ይዟል።

የ''መከረኞቹ'' ፣ ''ያገር ልጅ'' እና ''ባሻ ቅጣውን የመሰሉ ዘመን ተሻጋሪ የስነ ጽሑፍ ስራዎችን ያጋሩንን ጋሽ ሳሕለሥላሴን እናከብራቸው ዘንድ እንድታጅቡን በክብር ጋበዝናችሁ።

📖 ደራሲና አርታኢ ሀይለመለኮት መዋዕል

📖 ጋዜጠኛ ግርማ ፍሰሃን

📖 ደራሲና ተርጓሚ ሳህለስላሴ ብርሃነማርያም

📖 ገጣሚት ባንቻየሁ አሰፋ


ሰዓት :አርብ ነሐሴ 9 ከቀኑ - 10:30 ጀምሮ

📍 አድራሻ ካሳንችስ ኢሊሊ ኢንተርናሽናል ሆቴል

          መግቢያ በነፃ

ለተጨማሪው:https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
11🥰3👎1
📌የአርብ ምሽቱ አርትስ ስፔሻል በትኩሱ ደርሷል !!

በዚህ ሳምንት እነዚህን ጉዳዮች ታገኛላችሁ

1.የአንጋፋው ሙዚቀኛ መላቱ አስታጥቄ  አዲስ የሙዚቃ አልበም የሚለቀቅበት ቀን ይፋ ሆነ።

2."ቴአትር በየቤታችሁ ሊገባ ነው" ተብሏል።የአፍሪካን ሬነሳንስ ቴሌቪዥን  "Arts Pluse" የተሰኘ አዲስ መተግበሪያ ይፋ ሊያደረግ ነው ።አዲሱ መተግበሪያ ምን ምን ጉዳዮች ይዟል እንነግራችኋለን።

3.መስከረም አበራ እና ቸርነት ፍቃዱ የተጣምሩበት አዲስ ሀገርኛ ፊልም ለእይታ ሊበቃ ነው።

እነዚህንና ሌሎችንም የአርትስ ስፔሻል የኪነት እና ኩነት መረጃዎች እናቀርብላችኋለን።

"አርትስ ስፔሻል"ዝግጅታችንን ይመለከቱ:

https://youtu.be/9hJNQhiM_ow?si=Bt_BmTaEvpCymvlY

📌መልካም ምሽት

ለተጨማሪው: https://news.1rj.ru/str/EventAddis1‌‌
👍53
"ቀለም" ዲጂታል መጽሔት ዛሬ ለንባብ ይበቃል

የቀለም ዲጂታል መጽሔት አዘጋጆች "የወር ሰው ይበለን! ተባብለን በተለያየን በ30 ቀናችን ይሄው በዛሬው ዕለት ቅፅ 1/ ዕትም 2 ነሐሴ 10 አመሻሽ 12:00 ላይ ለንባብ ይበቃል" ብለዋል።

የቀለም መጽሔት ቴሌግራም ቻናል ቤተሰብ ይሁኑ።
https://news.1rj.ru/str/kelemofficial
🔥31
📌 "ፓሌሮዳ" አዲስ መፅሐፍ ለንባብ በቃ

የሕክምና ባለሙያ በሆነው ዶ/ር ደሳለው ካሳሁን የተፃፈውና በስነጹሑፋ ባለሙያዎች የተመሰከረለት እንዲሁም በኢትዮጵያ ስነጽሑፍ በአዲስ አቀራረብ የተጻፈ መፅሐፍ ነዉ የተባለለት “ፓሌሮዳ” ኢትዮጽያ ለምን ? የተሰኘዉ አዲስ መፅሐፍ ለንባብ በቅቷል።

“ ፓሌሮዳ “ መጽሐፍ መጽሐፈ ሄኖክን፣ ሜታፊዚክስን፣ የህክምና አብዮትን፣ ጂኦፖለቲካንና ሀገራዊ አብርሆትን አንድ ላይ አሰናስሎ፣ ያቀረበ መጽሐፍ ሲሆን ሀገራዊ ብሎም አለመአቀፋዊ ፋይዳ ያላቸውን ሀሳቦች የያዘ መጽሐፍ ነው።

በ “ ፓሌሮዳ “ በገሃዱ አለም ተጨባጭ ሁነቶች ላይ ተመስርቶ፣ በተለያየ መነሻ የተሰባሰቡ ምሁራን የመጽሐፈ ሄኖክን መፍቻ አትላሶችን ፍለጋ አብርሆት በተሰኘ ህቡዕ ማህበር ስር ታቅፈው ከኢትዮጵያ ገዳማት እስከ የአውሮፓ የምድር ውስጥ ቤተመጻሕፍት ድረስ የሚያደርጉትን እልህ አስጨራሽ ጉዞ የሚያሳይ ሳይንሳዊ፣ መንፈሳዊ፣ ፍልስፍና ቀመስ እንዲሁም ጂኦፖለቲካዊ ልቦለድ ነው።

መፅሐፉን በ ሀሁ መጻህፍት  መደብር እና በሁሉም የመፅሐፍ መደብሮች ያገኙታል ሲል ይትባረክ ዋለልኝ ነግሮናል።

ለተጨማሪው: https://news.1rj.ru/str/EventAddis1‌‌
📌የዘቢብ መልኬ አዲስ መጽሐፍ ሊመረቅ ነው

የደራሲ ዘቢብ መልኬ "ፉካ" የተሰኘ ርዕስ የተሰጠው አዲስ መጽሐፍ የፊታችን ረቡዕ ነሐሴ 14 2017 ዓ.ም አራት ኪሎ በሚገኘው ዋልያ መጻሕፍት አዳራሽ ውስጥ ከቀኑ 10:00 ጀምሮ ይመረቃል።

"ፉካ" የደራሲ ዘቢብ መልኬ የአጫጭር ልብወለዶች ስብስብ መጽሐፍ ነው።

ደራሲዋ ከዚህ ቀደም “ስብጥር “ግጥም እና የወግ ስብስብ መፅሐፍ፣ “ኮላዥ “ የአጭር ልቦለዶች ስብስብ መጻሕፍትን ለንባብ ማብቃቷ ይታወቃል።

ለተጨማሪው: https://news.1rj.ru/str/EventAddis1‌‌
5
📌ሁለቱም ጋዜጠኞች የገቡበት አልታወቀም

አንጋፋው ጋዜጠኛ አብዱልሰመድ መሐመድ እና ጋዜጠኛ ዮናስ አማረ ከቀናት በፊት በደኅንነት አካላት ተይዘው መወሰዳቸው እና እስካሁንም የደረሱበት እንደማይታወቅ እና ፍርድ ቤትም እንዳልቀረቡ ተሰማ።

ጋዜጠኛ አብዱልሰመድ መሐመድ ሰኞ ነሐሴ 5/2017 ቀን ላይ ማንነታቸው ባልታወቁ ሰዎች ታፍኖ መወሰዱ የታወቀ ሲሆን ከቆይታ በኋላ ግን በመንግስት የደኅንነት ኃይሎች እንደተያዘ ታውቋል፡፡

በተመሳሳይም የሪፖርተር ጋዜጣ ባልደረባ የሆነው ጋዜጠኛ ዮናስ አማረም ሐሙስ ነሐሴ 8/2017 ከቢሮ እንደወጣ በመንግስት የደኅንነት ኃይሎች ተይዞ መወሰዱ ተነግሯል።

ምንም እንኳን ጋዜጠኞች በመንግስት የደኅንነት አካላት ተይዘው ቢወሰዱም ይህ መረጃ እስከተጠናቀረበት ድረስ ያሉበት ስፍራ እንደማይታወቅ ምንጮች ተናግረዋል፡፡

ቤተሰቦቻቸውም በጭንቀት ውስጥ እንደሚገኙ ይገኛሉ፡፡ በተለይም ደግሞ የአብዱልሰመድ ባለቤት ልጇን ከተገላገለች ጥቂት ቀናት በመሆኑ በአራስ አቅም በየፖሊስ ጣቢያው ለመዞር እንደተገደደች ምንጮች አስታውቀዋል፡፡

ጋዜጠኛ ዮናስ አማረ በሪፖርተር ጋዜጣ በርካታ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ጠንካራ ዘገባዎችን እንዲሁም ቃለ ምልልሶችን በማድረግ የሚታወቅ ሲሆን ጋዜጠኛ አብዱልሰመድም በአሐዱ ራዲዮ ቀዳሜ ገበያ የተሰኘ ፕሮግራም በማዘጋጀት ለአድማጭ ሲደርስ ቆይቷል፡፡

ጋዜጠኞች ከቅርብ ዓመታት ወዲህ ለዘፈቀደ እስር፣ ገድያ እና እንገልት መዳረጋቸው የተለመደ ጉዳይ መሆኑ በርካታ ዓለም አቀፍ ሪፖርቶች ያሳያሉ፡፡

©️መረጃው የሆርን ፍሪኩዌንሲ ነው።

ለተጨማሪው: https://news.1rj.ru/str/EventAddis1‌‌
😢1210😱3🤬3
📌“በሆቴሎች ውስጥ የሚደረግ ስብሰባ አይኖርም"

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ቢሮ በሚቀጥለው በጀት ዓመት  ሁሉም ክፍለከተማዎች እና ተጠሪ ተቋማት “የሆቴል አገልግሎት ግዢ” እንዳይፈጽሙ አሳስቧል። ቢሮ ይህን ውሳኔ ያስተላለፈው የተመደበው በጀት “የታለመለትን ዓላማ ለማሳካት እንዲችል” መሆኑን አስታውቋል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለ 2018 ዓ.ም በጀት ዓመት 350 ቢሊዮን ብር ማፅደቁ ይታወሳል። ከዚህ በጀት ወስጥ 70 በመቶ የሚሆነው ለካፒታል ሥራዎች የተመደበ ነው። ቀሪው ደግሞ ለመደበኛ ሥራዎች ማስፈጸሚያ የሚውል ነው። ከተማዋ በዚህ  በጀቷ “ውጤታማ የሆኑ ሥራዎችን በቁጠባ ለማከናወን” እና “የታለመለትን ዓላማ ለማሳካት” እንድትችል ተጠሪ ተቋማት እና ክፍለ ከተማዎች በሆቴሎች ውስጥ የሚደረጉትን “ስብሰባዎች” እና “ሥልጠናዎች በመንግሥት  መሰብሰቢያ አዳራሽ ብቻ” እንዲያከናውኑ በደብዳቤ ተገልጾላቸዋል።

በከተማዋ ፋይናንስ ቢሮ ኃላፊ አቶ አብዱልቃድር ሬድዋን ተፈርሞ ለተቋማቱ የተላከው ደብዳቤ “ለልዩ ልዩ ስብሰባዎች፣ ሥልጠናዎችና ግምገማዎች የሆቴል ግዢ አገልግሎት መፈጸም እንደማይችሉ” ይገልጻል። ተቋማቱ ስብሰባ እና ሥልጠና ማካሔድ ካለባቸው በራሳቸው የመሰብሰቢያ አዳራሽ መሆን እንደሚገባው ቢሮ አስታውቋል። ለዚህ እንዲያገለግል “የመንግሥት መሰብሰቢያ አዳራሾችና ካፍቴሪያዎችን በማጠናከር መገልገል” እንዳለባቸው አሳስቧል።

©️ኢትዮ ቲዩብ

ለተጨማሪው: https://news.1rj.ru/str/EventAddis1‌‌
6👍3👏2
📌የደበበ እሸቱ የቀብር ሥነ ስርዓት ነገ ይፈፀማል

የአርቲስት ደበበ እሸቱ የቀብር ሥነ ስርዓት ነገ ከቀኑ 8 ሰዓት በመንበረ ፀባኦት ቅድስት ስላሴ ካቴድራል ይፈጸማል።

የአርቲስት ደበበ እሸቱ ሥርዓተ ቀብር በተመለከተ በብሔራዊ ቴአትር የቀብር አስፈፃሚ ኮሚቴ መግለጫ ሰጥቷል።

አርቲስት ደበበ እሸቱ /ጋሽ ደቤ/ በኢትዮጵያ ዘመናዊ የኪነ ጥበብ ታሪክ ታላቅ ዐሻራ ያኖረ አርቲስት እንደነበር ተገልጿል።

የአርቲስት ስርዓተ ቀብር ነገ ከቀኑ 8 ሰዓት በመንበረ ፀባኦት ቅድስት ስላሴ ካቴድራል እንደሚፈጸም ተገልጿል።

ከዚያ በፊት አምስት ሰዓት ላይ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር የክብር ሽኝት እንደሚደረግለትም ታውቋል።

ለተጨማሪው: https://news.1rj.ru/str/EventAddis1‌‌
7😭5🖕2
📌ስፑትኒክ በኢትዮጵያ የሬዲዮ ሥርጭት ጀመረ

የስፑትኒክ አፍሪካ ፕሮግራም በአዲስ አበባና አካባቢዋ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የማሕበረሰብ ሬዲዮ 99.4 ኤፍ ኤም ለአድማጮች መቅረብ ጀምሯል።

ስፑትኒክ በሀገሪቱ አንጋፋ በሆነው ዩኒቨርሲቲ የሬዲዮ ጣቢያ በስፑትኒክ ኢትዮጵያ ጋዜጠኞች በአማርኛና በእንግሊዝኛ የተዘጋጁ የትንታኔ ፕሮግራሞችን ለ6 ሚሊየን አድማጮች ማቅረብ መጀመሩ ተመላክቷል፡፡

ስፑትኒክ ዓለም አቀፍ የዜና ወኪል እና የሬዲዮ ማሰራጫ በ36 ቋንቋዎች ፕሮግራሞቹን የሚያቀርብ ሲሆን÷ በዓለም ዙሪያ 15 የይዘት ማዕከላት አሉት፡፡

በአማርኛ ቋንቋ የሚሠራ ብቸኛው የሩሲያ ሚዲያ የሆነው ስፑትኒክ ዘርፈ ብዙ የይዘት ማዕከሉን በፈረንጆቹ 2025 በአዲስ አበባ ከፍቷል፡፡

በተጨማሪም በ7 የአፍሪካ ሀገራት ማለትም በናይጄሪያ፣ ጊኒ፣ ዛምቢያ፣ ካሜሩን፣ ማሊ፣ ኒጀር እና ቦትስዋና ፕሮግራሞቹን እያስተላለፈ ይገኛል፡፡

በአፍሪካ ባሕል ዙሪያ በሚያዘጋጃቸው ፕሮግራሞቹ በምርጥ የሬዲዮ መጽሄት እና በምርጥ የሬዲዮ ፕሮግራም ምድቦች የሕብረቱን ሽልማት አግኝቷል፡፡

ስፑትኒክ አፍሪካ የአፍሪካ ብሮድካስቲንግ ሕብረት አባል እና ተሸላሚ እንዲሁም ሰሜናዊ አፍሪካን በሚሸፍነው የዓረብ ብሮድካስቲንግ ሕብረት አባል ነው ሲል FMC ዘግቧል።

ለተጨማሪው: https://news.1rj.ru/str/EventAddis1‌‌
15👎2👏2🥰1
📌ቻናል 1 ቴሌቪዥን ነሐሴ 18 ይጀምራል

ኢትዮጵያውያን ቤተሰቦችን በአንድ ላይ ለማሰባሰብ ዓላማ በማድረግ ስያሜውን "ቻናል 1" ያለው ቻናል ዋን ቴሌቪዥን ጣቢያ ነሐሴ 18  2017 ዓ.ሞ ከቀኑ 6:00 ጀምሮ  "እሁድን አንድ ላይ" በተሰኘ ፕሮግራም መደበኛ ስርጭቱን እንደሚጀምር  ኤቨንት አዲስ ሚዲያ ከጣቢያው ያገኘው መረጃ ያመለክታል።

ጣቢያው ቀደም ብሎ በርካታ ፕሮግራሞችን እያዘጋጀ እንደከረመ እና አዳዲስ የፕሮግራም ይዘቶችን ለተመልካች ይዞ ለመምጣት ዝግጅት ሲያደርግ እንደቆየ ተገልጿል።

ቻናል 1 ወደ መደበኛ ስርጭቱ ሲገባ ከ80 መቶ በላይ አዳዲስ (ኦርጂናል)ይዘት ያላቸው ኢትዮጵያዊ ድራማዎች፣ ኮሚዲዎች፣ ሪያሊቲ ሾዎች፤ጌም ሾዎች፣ ስፖርታዊ ፕሮግራሞች፣ ሙዚቃዎች፣ ትምህርታዊ ፕሮግራሞች፣ የልጆች ዝግጅቶች ለትውልድ በሚመጥን መልኩ የተዘጋጁ ሲሆን ቀሪዎቹ 20 ከመቶ የሚሆኑት ይዘቶችም የኢትዮጵያን ቤተሰብ ባህልና ወግ እና ልምድ ግምት ውስጥ ያስገቡ ፕሮግራምች ናቸው ተብሏል።

በፕሮግራም አቅራቢነት ናፍቆት ትዕግሥቱ፣ሊያ ሳሙኤል፣ ስንታየሁ ብዙነህ እና ሌሎችም በጣቢያው በሚተላለፉ ፕሮግራሞች ላይ እንደሚሳተፉ ተገልጿል።

ቴሌቪዥን ጣቢያው ሙሉ በሙሉ የመዝናኛ ጣቢያው ባይሆንም ዋና ትኩረቱ መዝናኛ እንደሆነም ተነግሯል።

"ቻናል 1" ቴሌቪዥን ጣቢያ ሳምንቱን ሙሉ የ24 ሰዓታት ስርጭት ይኖረዋል ተብሏል።

ጣቢያው በኢትዮ-ሳት ላይ በ11545 H 45000 ፍሪኩዌንሲ ላይ ይገኛል።

ለተጨማሪው:https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
👍128
📌ኢትዮጵያ የፈቃድ ሞትን ተግባራዊ ልታደርግ ነው

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ባለፈው ጥር ወር በሕክምና ባለሙያ የታገዘ ሞት የሚፈቅድ አዋጅ ማፅደቁን ተከትሎ፤ ጤና ሚኒስቴር ሕጉን ተግባራዊ ለማድረግ የሚያስችል መመሪያ ማውጣቱ ተዘግቧል።

ረቂቅ መመሪያው ውሳኔው ከመተላለፉ በፊት በትንሹ ሶስት የጤና ባለሙያዎች በምርመራው ላይ መስማማት እንዳለባቸው ይደነግጋል። በተጨማሪም የቅርብ ዘመዶች የሕመምተኛው ሕይወት ማቆያ ድጋፍ እንዲነሳ በጽሁፍ በፈቃዳቸው መጠየቅ እንደሚችሉ ያስቀምጣል።

አዋጁ በመሳሪያ ላይ ብቻ የተመሠረተ የአተነፋፈስ ስርዓት እንዲቋረጥ ይፈቅዳል፡፡ ሕጉ ተግባራዊ የሚሆነው የልብ እና የመተንፈሻ አካላት የአሠራር ሥርዓት መመለስ በማይቻልበት ደረጃ ሥራቸውን ሲያቆሙ ወይም የአንጎል ሞት ሲረጋገጥ ብቻ ነው።

ሕጉ በማይድን ህመም የሚሰቃዩ ዜጎችን ለመርዳት ያለመ ነው ተብሏል ሲል ሰፑትኒክ ዘግቧል፡፡

ለተጨማሪው: https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
8🤬2🕊1
📌የደብረ ታቦር በዓል በደብረታቦር ከተማ ተከበረ

የደብረ ታቦር ዓመታዊ በዓል በዛሬው ዕለት በደብረታቦር ኢየሱስ ቤተክርስቲያን ተከብሯል፡፡

በዓሉ በክርስትና እምነት ተከታዮች ዘንድ በየዓመቱ ነሐሴ 13 የሚከበር ሲሆን÷ በደብረታቦር ከተማ ርዕሰ አድባራት ደብረ ታቦር ኢየሱስ ቤተክርስቲያን ሐይማኖታዊ ሥርዓቱን ጠብቆ በደማቅ ሁኔታ ተከብሯል፡፡

ከበዓሉ አከባበር ጎን ለጎን የክልሉ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ በደብረታቦር ኢየሱስ ሙዚየም ለመገንባት የመሰረት ድንጋይ ማስቀመጡን የቢሮው የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ አበበ እምቢያለ ለፋና ዲጂታል ተናግረዋል፡፡

ለተጨማሪው: https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
26
📌የቲያትር ቲኬት ዋጋ 200 ብር ሆነ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቲያትር የመግቢያ ትኬት ዋጋን ከስምንት ዓመት በፊት ከነበረበት 80 ብር ወደ 200 ብር ማሳደጉን አስታውቋል።

ቲያትሩ ከ1948 ዓ.ም. ጀምሮ አገልግሎት ሲሰጥ የቆየ ሲሆን፣ ኪነጥበብ ከፍ ማለት እና መከበር አለበት በሚል ዋጋዉን ለማሻሻል ጥናት ሲደረግ መቆየቱ ተገልጿል።

ይህ ውሳኔ የኪነጥበብን ደረጃ ከፍ ለማድረግ እና የቲያትር ቤቱን አገልግሎት ለማሻሻል ያለመ መሆኑ ተጠቁሟል።

የቲያትር ቤቱ ኃላፊዎች፣ የቲኬት ዋጋው ከዚህ ቀደም በጣም ዝቅተኛ ስለነበር፣ አሁን የተደረገው ጭማሪ ሳይሆን 'ማሻሻያ' ነው ሲሉ አብራርተዋል። የዋጋ ማሻሻያው "ማንንም የማይጎዳ መልኩ" መሆኑን በማስረገጥ፣ የቲኬት ዋጋው ለሁሉም ትያትሮች በ200 ብር መወሰኑን ገልጸዋል።

ኦንላይን ትኬት ሽያጭ እና ሌሎች ለውጦች
ከተመሠረተ 70 ዓመታትን ያስቆጠረው ብሔራዊ ቲያትር፣ አዳዲስ ለውጦችን በማምጣት ተመልካቹን ለማርካት መዘጋጀቱን አስታውቋል።

ከለውጦቹ መካከል ተመልካቾች ከየቤታቸው ሆነው ትኬት መግዛት የሚያስችላቸውን 'ኦንላይን' የቲኬት ሽያጭ ሥርዓት ማመቻቸቱ ተገልጿል።

በተጨማሪም፣ የቲያትር ቤቱ ኃላፊዎች በቀጣይ ሁሉም ክልሎች የሚሳተፉበት ሥልጠና በብሔራዊ ቲያትር እንደሚሰጥ አስታውቀዋል። ይህ የዋጋ ማሻሻያ እና ሌሎች ተያያዥ ለውጦች የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቲያትርን ወደ ተሻለ ደረጃ ለማምጣት እና ዘመናዊ አገልግሎቶችን ለመስጠት እንደሚያግዝ ይጠበቃል ሲል ካፒታል ጋዜጣ ዘግቧል።

ለተጨማሪው: https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
👏2213🤯3👍1😱1😭1
📌የኢትዮጵያ ቀዳማዊት እመቤት መዝሙር

ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው "ያዘኝ" በሚል ርዕስ አዲስ የመዝሙር ቪድዮ በቅርቡ ለህዝብ እንደሚያደርሱ ጽህፈት ቤታቸው አስታውቋል።

"ያዘኝ" የሚለው የአዲሱ መዝሙር ርዕስ፣ "በፈተና ጊዜ እግዚአብሔር ደግፎኛል" የሚል መንፈሳዊ ትርጉም ያለው ሲሆን፣ መዝሙሩም ተመሳሳይ የምስጋና እና የተስፋ መልዕክትን ይዞ እንደሚመጣ ይጠበቃል።

ይህ ስራቸው፣ ከዚህ ቀደም ካወጧቸው መዝሙሮች እና ካሳተሟቸው መጽሐፍት የቀጠለ የጥበብ ስራቸው አካል ነው።

ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው፣ ከመዝሙር ጥበብ ስራዎቻቸው በተጨማሪ፣ በጽህፈት ቤታቸው በኩል በተለያዩ ማህበራዊ ስራዎች ላይ ተሳትፎ እንደሚያደርጉ ሲገለጽ ቆይቷል።

የአዲሱ የመዝሙር ቪድዮ መቼ እንደሚለቀቅ ዝርዝር መረጃው ገና ይፋ አልተደረገም።

ለተጨማሪው: https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
😁13👎87
📌በአርቲስት ሸዋፈራው ደሳለኝ  ምክንያት "ከትዳር በላይ" ቴአትር ዛሬ ከመድረክ ይሰናበታል

በቴዎድሮስ ተ/አረጋይ ተጽፎ በዳግማዊ አመለወርቅ ፈይሳ የተዘጋጀው "ከትዳር በላይ" የኮሜዲ ቴአትር ከወራት በኃላ በአርቲስት ሸዋፈራው ደሳለኝ ምክንያት ዛሬ ከመድረክ እንደሚሰናበት ኤቨንት አዲስ ሚዲያ ከተውኔቱ ደራሲ ቴዎድሮስ ተ/አረጋይ ያገኘው መረጃ ያመለክታል።

ባለፉት 6 ወራት በዓለም ሲኒማ ሲታይ የቆየው "ከትዳር በላይ" ቴአትሩ ከመድረክ የሚወርድበት ምክንያት አርቲስት ሸዋፈራው ደሳለኝ በተዋናይነት የሚሳተፍበት "ወደ ማዶ" የተሰኘ ቴአትር በቅርቡ ዓለም አቀፍ ጉዞ ስለሚያደርግ እንደሆነም ተነግሯል።

ከየካቲት 23 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ በዓለም ሲኒማ ሲቀረብ የቆየው ቴአትሩ ዛሬ ነሐሴ 14 2017 ዓ.ም ከምሽቱ 12:00 ጀምሮ ከመድረክ ይሰናበታል።

በቴአትሩ ላይ መስከረም አበራ፣ ሸዋፈራው ደሳለኝ፣ የማታወርቅ ታደሰና መዓዛ ገብረሕይወት፣ ዕፀሕይወት አዳንከኝ፣ ቸርነት ፍቃዱ በተዋናይነት ተሳትፈውበታል።

ለተጨማሪው: https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
13👏3