Event Addis Media – Telegram
Event Addis Media
9.63K subscribers
6.1K photos
13 videos
4 files
4.72K links
Connect with Addis artistic community!

Website: https://eventaddis.com

Contact: @Tmanaye
Download Telegram
📌ሜንታል ሄልዝ አዲስ የሥነልቦና ውይይት

ወርሃዊው የሜንታል ሄልዝ አዲስ መርሃግብር ቅዳሜ ሕዳር 27 ቀን 2016 ዓም 6ኪሎ በሚገኘው ገብረክርስቶስ ደስታ ዘመናዊ የሥነጥበብ ሙዚየም ከቀኑ 8፡30 ጀምሮ  ይካሄዳል::

የዚህ ወር ርዕስም፡- “Embracing for mental health” የሚል ሲሆን የዚህ ወር እንግዳ የሥነልቦና ባለሞያ ናፍቆት ወ/ጻዲቅ ናቸው፡፡

ለተጨማሪው: https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
👍6
📌በግጥም ኢትዮጵያን የሚወክለው ገጣሚ

ከኅዳር 23 - 27 በጊኒ ኮናክሬ የሚካሄደው ውድድር ላይ የኢትዮጵያ የግጥም ግጥምያ ሻምዮን ናትናኤል ታደለ ኢትዮጵያን በመወከል በኦንላይን ይወዳደራል።

ውድድሩ በአህጉራዊ ደረጃ ሲዘጋጅ ይህ አራተኛው ሲሆን ከዚህ በፊት ሁለተኛውን የአፍሪካ የግጥም ውድድር ኢትዮጵያ ማሰናዳቷ ይታወሳል።

ለተጨማሪው: https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
👏129
📌"ማክሮ ኢኮኖሚ እና የዕለት ሕይወታችን" ውይይት

በዋልያ የሃሳብ እና መፅሐፍ መድረክ "ማክሮ ኢኮኖሚ እና የዕለት ሕይወታችን" የተሰኘ ውይይት ቅዳሜ ህዳር 27 ቀን 2018 ዓም ከሰዓት  8:00 ጀምሮ 4ኪሎ ኢክላስ ህንፃ ዋልያ መፃሕፍት አዳራሽ ይካሄዳል።

በኢኮኖሚ ጉዳዮች ላይ በተዘጋጀነው  የፓናል ውይይት የየዘርፉ ባለሙያዎችን የተጋበዙ ሲሆን የባንክ ባለሞያ አቶ ሙሼ ሰሙ ፣ በአዲስ አበባ ዩንቨርስቲ የአካውንቲንግ እና ፋይናንስ መምህር የሆኑት አቶ አየለ ከበደ እና የኢኮኖሚ ባለሙያ እና ቢዝነስ ዴቨሎፕመንት ማናጀር አቶ ሁሴን አሊ በመደረኩ ላይ ሀሳባቸውን ያጋራሉ ተብሏል።

የመርሐግብሩ አወያይ ይትባረክ ዋለልኝ ነው።

ለተጨማሪው: https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
📌የሙዚቀኛ መሐመድ ራጅኡ አልበም ተለቀቀ

የሙዚቀኛ መሐመድ ራጅኡ "ብርሃን" የተሰኘ ርዕስ የተሰጠው በመሳሪያ የተቀነባበረ የሙዚቃ አልበም ተለቋል።

ለማዘጋጀት አንድ ዓመት እንደወሰደ የተነገረው "ብርሃን" የሙዚቃ አልበም አስር አንድ የሙዚቃ ስብስቦችን ይዟል።

"ብርሀን" በተሰኘው ሁለተኛ አልበሙ በኪቦርድ፣ ቤዝ፣አኮስቲክ ጊታር፣ክራር፣ የሙዚቃ መሳሪያዎች የተሰሩ የሙዚቃ ስራዎች ተካተዋል።

የሙዚቀኛ መሀመድ ራጁኡ  ቁጥር 2 የጃዝ ኢንስትሩሜንታል ሙዚቃ አልበም  በአንጋፋው Nahom_Records_inc ተለቋል:-

ሊንኩን በመጫን ሙሉውን ያገኙታል 👇👇

https://youtube.com/playlist?list=PLy65qis52RcCB3_bvLo3GnOV-rNuy4_1l&si=Fg7jOvrg_bU9z-i4

ሙዚቀኛ መሐመድ ከዚህ ቀደሞ "ሰላምታ " የተሰኘው የመጀመሪያ አልበሙን በ2010 ዓ.ም ለአድማጭ አድርሷል።

ሙዚቀኛ መሐመድ የሙዚቃ ኪቦርድ መጫወት የጀመረው 1998 ዓ.ም ሲሆን ሶስት ዓመት አፍሪካ ጃዝ ስኩል ( ጃዝ አምባ ) ተምሯል።

ሙዚቀኛው ከትግርኛ ዘፋኞች መሐል ለረጅም ጊዜ  የአብርሃም ገብረመድህን ፣ የማህሌት ገብረጊዮርጊስ ፣ የሸዊት መዝገቦ ኪቦርዲስት በመሆን በብዙ አገራት ቱር አድርጓል።

ለተጨማሪው: https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
5
📌የዶናት ተክሉ 'ሞላ' ሙዚቃ ተለቀቀ

የድምፃዊት ዶናት ተክሉ' ሞላ' የተሰኘ ነጠላ ሙዚቃ በሰዋስው YouTube ቻናል ተለቋል።

በዚህ የድምጻዊት ዶናት ተክሉ ሙዚቃ ላይ ዳዊት ተስፋዬ በግጥምና ዜማ የተሳተፈ ሲሆን በቅንብርና ማስተሪንግ ያምሉ ሙዚቃ ተሳትፏል።

https://youtu.be/Vok32fKy0cA?si=7kjJcBKv-UdUNILe
3
📌"የእራት ግብዣው" ተውኔት ለመድረክ በቃ

ድርሰቱ የዣን ፒሬ ማርቲኔዝ የሆነው በቢኒያም ከተማ የተተረጎመ በሳሙኤል ተስፋዬ የተዘጋጀው "የእራት ግብዣው" ተውኔት ሐሙስ ህዳር 25 ቀን 2018 ዓ.ም በዓለም ሲኒማ ለመድረክ በቅቷል።

በተውኔቱ  ህሊና ሲሳይ፣ ተስፉ ብርሃኔ፣እታፈራሁ መብራቱ፣አንዷለም ካሳሁን ይተውኑበታል።

"የእራት ግብዣው"ተውኔት በቋሚነት ዘወትር ሐሙስ በ11:00 በዓለም ሲኒማ እንደሚቀርብ አዘጋጆች አስታውቋል።

ለተጨማሪው: https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
👍31
📌 “የአረንጓዴ ስራ ፎረም እና ባዛር”

ለማሕበረሰባችን አዳዲስ የስራ ዕድሎችን እና የቢዝነስ አማራጮችን በመፍጠር ላይ ያተኮረ ፎረም ሊከናወን ነው።

ይህ በዓይነቱ ልዩ የሆነውና በSNV (ኤስኤንቪ) እና MERCICORPS (ሜርሲኮርፕስ) ትብብር የተዘጋጀ ሲሆን በ”አረንጓዴ ስራ ፈጠራዎች” ላይ ያተኩራል። ይህ ልዩ ፎረም እና ባዛር ሕዳር 30 እና ታህሣስ 1/ 2018 ዓ.ም ሲኤምሲ በሚገኘው፣ አዲስ አበባ ዓለምአቀፍ ኮንቬንሽን ሴንተር ይካሄዳል፡፡

በዕለቱ ግብዣ የተደረገላቸውን የመንግሥት ከፍተኛ ኃላፊዎችን ጨምሮ፣ መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች፣ የግል ተቋማት እና የዘርፉ ባለሞያዎች ይገኛሉ። በባዛሩ ላይ ታዳሽ ኃይሎችን እና ከብክለት ነፃ አካባቢን የሚፈጥሩ ምርቶችን፣ ቴክኖሎጂዎችን እና አገልግሎቶችን የሚያቀርቡ በርካታ አምራቾችና ስራ ፈጣሪዎች ምርትና አገልግሎቶቻቸውን ያቀርባሉ፡፡

በሲኤምሲ፣ አዲስ ዓለምአቀፍ ኮንቬንሽን ማዕከል ከሚካሄደው የሁለቱ ቀናት ፎረም እና ባዛር በተጨማሪ፣ ታህሣስ 3 እና 4/2018 ዓ.ም ደግሞ በአዲስ አበባ፣ በተመረጡ 5 ክፍለ ከተሞች፣ ታዳሽ ምርቶች እና አረንጓዴ ፈጠራዎች የሚቀርቡበት ልዩ ባዛር ለሕዝብ ክፍት ይሆናል፡፡

ይምጡ! -- የመጪውን ዘመን ወሳኝ የሥራ እና የቢዝነስ ዓለም ይቀላቀሉ https://docs.google.com/forms/d/1eVgHmyojo7eF6O5nN_AG5qX9CxKwlS_y1s7yzt7Ry8U/edit

አዘጋጆች ፡ (ኤስ.ኤን.ቪ) እና MERCICORPS (ሜርሲኮርፕስ)
👍21🔥1
📌ያንጎ በኢትዮጵያ መተግበሪያውን

ያንጎ በኢትዮጵያ መተግበሪያውን ላይ አዲስ የደንበኛ ደህንነት መጠበቂያ መጨመሩን አስታወቀ።

ያንጎ ራይድ ተሳፋሪዎች በጉዞ ወቅት ሊተገብሯቸው የሚችሉየደህንነት መጠበቂያ እርምጃዎችን በሞባይል መተግበርያውውስጥ አካተተ። መተግበሪያው ተሳፋሪዎች የሚሄዱበትንመንገድ ለሚያምኑት ሰው ማጋራት ወይም የጉዟቸውን ሁኔታየሚያስረዳ አሁናዊ መረጃ ማጋራት የሚያስችል ነው።  
 
የአለምዓቀፉ የቴክኖሎጂ ኩባንያ የያንጎ ግሩፕ አካል የሆነው ያንጎ ራይድ ኢትዮጵያ ውስጥ የሚያገለግለው መተግበሪያው ውስጥ የሚገኘውን የደንበኛ ደህንነት መጠበቂያ አሻሽሏል። የተሻሻለው መተግበርያ እያንዳንዱ ተጓዥ ዝርዝር የደህንነት መስፈርቶች መሟላታቸውን የሚያረጋግጥበት አገግሎግሎት፥ በወቅታዊ የጉዞ ሁኔታ መረጃ ላይ ተመስርቶ ምን አይነት የደህንነት እርምጃዎች መወሰድ እንደሚገቡ መረጃ የሚሰጥ እንዲሁም ስለ ጉዞ ደህንነት አጠቃላይ የደህንነት መረጃዎች የሚሰጥ የማዕከል አገልግሎት የተካተተበት ነው።

ተጨማሪ ያንብቡ:https://url-shortener.me/277T
 
ለተጨማሪው: https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
8👍3
📌ዶ/ር ተሻለ አሰፋ "ቲያትር ቤቶች መጠጥ ቤት እንዳይሆኑ ያስፈራኛል" ሲል ተናገረ

ታዋቂው የቴአትር ጥበባት መምህርና አዘጋጅ ዶ/ር ተሻለ አሰፋ "ሆቴሎችም ቲያትር ማሳያ ሆነው ቲያትር ቤቶች መጠጥ ቤት እንዳይሆኑ ያስፈራኛል" ሲል ትዝብቱን ተናግሯል።

የዶ/ር ተሻለ አሰፋ ሙሉ ሀሳቡ እንደሚከተለው ይቀርባል" ባለፈው ሐሙስ "የእራት ግብዣው" የተሰኘውን ቲያትር በዓለም ሲኒማ እየተመለከትኩ ሀሳቤ ለሁለት ተከፍሎ ነበር።

በአንድ ወገን በቲያትሩ ስደሰት በሌላ በኩል ደግሞ እስካሁን ድረስ አልላቀቅ ካለኝ ጥያቄ ጋር ስሟገት ነበር። ዓለም ሲኒማ ቲያትር ቤት አይደለምኮ።

ታዲያ ለምንድነው በርካታ ድንቅ ስራዎችና በሳል ባለሙያዎች ወደዚያ የሄዱት? (የተሰደዱት ብዬ ነገሩን ማጮህ አልፈለግኩም)። ይሄ ጥያቄ ከዚህ በፊት በሌሎች ባለሙያዎችም ሲጠየቅ ሰምቻለሁ። መልስ እጠብቅ ነበር።

በተለይ ዋና ስራችሁ ቲያትር መስራት ከሆነ ቲያትር ቤቶች። መጠበቅ ብቻ ሳይሆን ደጃችሁ ድረስ መጥቼ ተሟግቻለሁ። መልስ  አላገኘሁም። እንዳይረፍድ እሰጋለሁ። በዚህ የሚቀጥል ከሆነ ሲኒማዎች ብቻ ሳይሆኑ ሆቴሎችም ቲያትር ማሳያ ሆነው ቲያትር ቤቶች መጠጥ ቤት እንዳይሆኑ ያስፈራኛል። ሙያው ታላቅ ነው። ክብር ስጡት፤ ወይም ክብር ሰጥተውት ዋጋ እየከፈሉለት ያሉትን ባለሙያዎች አክብሯቸው። ይብቃኝ መሰለኝ። ለማንኛውም የ"የእራት ግብዣው" ቲያትር ተሳታፊዎች በሙሉ ድንቅ ስራ ሰርታችኋልና እንኳን ደስ አላችሁ።

ለተጨማሪው: https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
11🤔4👍2🙏1
📌"ነገረ ኢትዮጵያውያን" መጽሐፍ ይመረቃል

በላዕከ ወንጌል በኃይሉ በቀለ የተፃፈው "ነገረ ኢትዮጵያውያን " የተሰኘ አዲስ መፅሐፍ ታህሳስ 11 ከቀኑ 8:00 ሰዓት ጀምሮ በቅድስት ስላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ 4ተኛ ፎቅ ላይ በሚገኘው የስብከተ ወንጌል አዳራሽ በርካታ ተጋባዥ እንግዶች በተገኙበት በድምቀት ይመረቃል።

ለተጨማሪው: https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
🥰76
📌ቲክቶከሮቹ በአፈንጋጭ አለባበሳቸው ታሰሩ

የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ከሀገራችን ባህልና ሥነ-ምግባር ያፈነገጠ አስነዋሪ አለባበስ ለብሰው በአደባባይ እና በቴሌቪዥን በቀጥታ ስርጭት ለሕዝብ የታዩ ተጠርጣሪዎች ላይ  ምርመራ መጀመሩን አስታወቀ።

የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ  በ3ኛው የG-Power TikTok Creative Award ላይ ከኢትዮጵያ ሕዝብ ባህልና ሥነ-ምግባር  ባፈነገጠ አኳሃን ሰውነታቸውን  የገላለጠ አለባበስ ለብሰው በአደባባይና በቴሌቪዥን ቀጥታ ስርጭት ለሕዝብ የታዩ ተጠርጣሪዎችን ከነግብረ-አባሮቻቸው ጋር በቁጥጥር ሥር አውሎ ምርመራ ማጣራት መጀመሩን አስታውቋል።

‎የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ሰሞኑን በሀገራችን አዲስ አበባ ከተማ በተካሄደው 3ኛው የG-Power TikTok Creative Award ላይ ከኢትዮጵያ ሕዝብ ባህል እና መልካም ሥነ-ምግባር በተቃራኒ በሕዝብ ዘንድ ተቀባይነት የሌለው አስነዋሪ አለባበስ ለብሰው በአደባባይ እና በቴሌቪዥን ቀጥታ ስርጭት የታዩ፣ ዝግጅቱን በስፖንሰርነት የደገፋ እና ፕሮግራሙን ያቀነባበሩ ተጠርጣሪዎች:-

‎1ኛ. ወንጌላዊት ገብረ እንድርያስ በርሄ፣
‎2ኛ. በርከት ፀጋዬ ጅፋር፣
‎3ኛ. መቅድም ደረጄ መንግስቱ፣
‎4ኛ. ግሩም ገዛሀኝ ቀጭኔ እና
‎5ኛ. ዮሃንስ መኮንን ሀ/ማርየም ‎የተባሉ ግለሰቦች መሆናቸውን ገልጿል።

የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ከህብረተሰቡ ባህልና እሴት ያፈነገጡ አለባበሶችና መጤ ባህሎች ተስፋፍተው በትዉልዱ ላይ አሉታዊ ተጽእኖ እንዳያስከትሉ ተጠርጣሪዎቹ ላይ የሕግ ተጠያቂነትን ለማረጋገጥ የጀመረውን ምርመራ አጠናክሮ እንደሚቀጥል ያስታውቃል።

©️ የፌዴራል ፖሊስ

ለተጨማሪው: https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
👍4011😁9👎5💯4🤝2
📌ሶፊ ሾው ከአሻም ቴሌቪዥን ታገደ

አሻም ሚዲያ ትሬዲንግ አክሲዮን ማህበር ጋዜጠኛ ሶፎንያስ ዋሲሁን በኮንትራት ውል በዜና አቅራቢነት እንዲሁም በቅርቡ በጣቢያችን ‹‹ሶፊ ሾው›› ሲል በሰየመው የመዝናኛ ዝግጅቱ  በአሻም የቴሌቪዥን እና በዩትዩብ ገፅ እያዘጋጀ ሲያቀርብ እንደነበረ ይታወቃል፡፡

ይህ በሆነበት ከትላንት ሕዳር 29 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ በተለያዩ የማህበራዊ ሚድያ አማራጮች ስለ ጋዜጠኛው ከኢትዮጵያዊነት ባሕል፣ ወግ እንዲሁም ሃይማኖት ያፈነገጠ ተግባር ሲፈጽም የሚያሣይ መረጃ በድምጽ፣ በጽሁፍና በተንቀሳቃሽ ምስል ጭምር ሲዘዋወር ተመልክተናል፡፡

አሻም ይህንኑ በማህበራዊ ሚዲያ ስለ ጋዜጠኛው የተሰራጨውን መረጃ ተከትላ ስለ ተሰራጨበት መረጃ ሶፎኒያስን ማብራሪያ እንዲሰጥበት ጠይቃለች፡፡ በዚህም ሶፎኒያስ <<አሁን ራሴን ለማስተካከል፤ለማከም ፀበል ገብቻለሁ>> የሚል አጭር ምላሽ ከመስጠት ውጭ ተጨማሪ ያለው ነገር የለም።

ስለሆነም አሻም ሚድያ ትሬዲንግ አ.ማ. የኢትዮጵያን ባህል እና ወግ እንዲሁም የህብረተሰቡን እሴት እና ሃይማኖት ያከበረ የምትመራበት ኤዲቶሪያል አላት፡፡ ይሁን እንጂ ጋዜጠኛው የሚዲያውን ኤዲቶሪያልም ሆነ የማህበረሰቡን እምነት ፣ እሴት፣ ወግ፣ ባህልና ሃይማኖት የሚጻረር ተግባር ተሰራጭቶበት በመመልከቷ እጅጉን እያዘነች ድርጊቱ የሚዲያ ተቋሟን የማይወክል ይልቁንም በጽኑ የምታወግዘው መሆኑን ለውድ ተመልካቾቻችን እና ተከታታዮቻችን ለመግለጽ እንወዳለን፡፡

ከዚህም በተጨማሪ አሻም ሚዲያ ትሬዲን አክሲዮን ማህበር ጋዜጠኛ ሶፎኒያስ ዋሲሁን በፈጸመው ከባድ የማህበረሰባዊ እሴት እና ኤዲቶሪያል ጥሰት ጭምር የነበራትን የስራ ውል ከዛሬ ሕዳር 30 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ ማቋረጡዋን ለመግለጽ ትወዳለች፡፡

©️አሻም ቴሌቪዥን

ለተጨማሪው: https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
15👏12
📌 ዛሬ የኤልያስ መልካ ልደት ነው!

ኤልያስ መልካ በሕይወት ቢኖር ዛሬ የ48ተኛ ዓመት ልደቱን ያከብር ነበር።

በልደቱ ቀን ይህን ታላቅ የሙዚቃ ሰው ለኢትዮጵያችን የሙዚቃ ዘርፍ አበርክቶው እናመሰግናለን እንላለን።

42 ዓመት ኖሮ ከ50 በላይ አልበሞችን ያቀናበረው ሙዚቀኛ የዜማ እና ግጥም ደራሲ፣ የሙዚቃ አቀናባሪ፣ ፕሮድዩሰር የሆነው ኤልያስ መልካ የኢትዮጵያ ሙዚቃ ባለውለታ ነው።

በቅንብር ስራ ላይ በቆየባቸው 19 ዓመታት ተወዳጅነትን ያተረፉ ከ50 በላይ አልበሞችን አቀናብሯል።

የኢዮብ መኮንንን "እንደቃል" አልበም፣ የጌቴ አንለይን “መልክሽ አይበልጥሽም” አልበም፣ የቤሪን "ከምን ነፃ ልውጣ" አልበም እና ወዘተ... ደግሞ ከቅንብር ባሻገር በግጥም እና ዜማ በመሳተፍ ጭምር የሰራቸው አልበሞች ናቸው።

ኤልያስ ከአማርኛ በተጨማሪ በትግርኛ፣ ኩናምኛ፣ኦሮሚኛ የተዜሙ የሙዚቃ ስራዎችንም አቀናብሯል ነጠላ ዜማዎችን እና ለማኅበራዊ አገልግሎት የሚውሉ ስራዎችንም በብዛት ሰርቷል።

ከአዳዲስ ሙዚቀኞች ጋር በመስራት ተስእጦ ያላቸውን ሙዚቀኞች ማውጣትም ሌላው መገለጫው ነው።

ለመጀመሪያ ጊዜ አብረውት ከሰሩ የወቅቱ ጀማሪ ሙዚቀኞች መካከል ዘሪቱ ከበደ፣ ሚካያ በኃይሉ፣ ኃይሌ ሩትስ፣ ሚካኤል በላይነህ፣ኢዮብ መኮንን ይጠቀሳሉ።

ኤልያስ መልካ ከሙዚቀኛነቱ ባሻገር ለሙዚቀኛው መብት መከበር ከፍተኛ ትግል እና ወደር የለሽ አስተዋፅኦ ያበረከተ እንዲሁም ሙዚቀኛው የልፋቱን እንዲያገኝ ሙዚቃን በስልክ መተግበሪያ (App) እንዲገበያይ የመጀመሪያውን እርምጃ የተራመደ ታላቅ የሙዚቃ እና የፈጠራ ሰው ነበር።

ለተጨማሪው: https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
42🕊4🔥3
📌ቲክቶከር አዶናይ ታሰረ

የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ አዶናይ ብርሃነ ሀ/ሚካኤል የተባለ ተጠርጣሪን በቁጥጥር ሥር አውሎ ምርመራ እያጣራ መሆኑን ገልጿል።

አዶናይ ብርሃነ ሀ/ሚካኤል በቁጥጥር ሥር ሊውል የቻለው ‎ከኢትዮጵያ ሕዝብ ባህል እና መልካም ሥነ-ምግባር በተቃራኒ በሕዝብ ዘንድ ተቀባይነት የሌለው አስነዋሪ አለባበስ ለብሰው በአደባባይ እና በቴሌቪዥን ቀጥታ ስርጭት የታዩት አምስት ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር በዋሉበት የወንጀል ጉዳይ ጋር በተያያዘ መሆኑን የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ አስታውቋል።

ዕውቅና እና ገንዘብ ለማግኘት ብቻ በማሰብ ሚዲያዎችን ኃላፊነት በጎደለው አኳሃን እየተጠቀሙ በተለይ ወጣቱ ትውልድ በመልካም ሥነ ምግባር ተቀርጾ ሀገርን የሚጠቅሙ ተግባራትን እንዳያከናውንና በተቃራኒው በትውልዱ ላይ ርካሽ ባህልን ለመጫ የሚደረገው ተግባር ለመከላከል የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ የጀመረውን ምርመራ አጠናክሮ እንደሚቀጥል ያስታውቃል።

ለተጨማሪው: https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
😁18👏9😡92
📌አሻም ቴሌቪዥን ሙሉ በሙሉ ተቋረጠ

አሻም ቴሌቪዥን ስራውን ለመቀጠል አቅም ስለሌላው ሙሉ በሙሉ ስርጭቱን እንዳቋረጠ በማህበራዊ ትስስር ገፁ አስታውቋል።

ጣቢያው በቴሌቪዥንም ሆነ በየትኛውም የማህበራዊ ሚዲያ አማራጮቿ ከዛሬ ታህሳስ 01 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ ሙሉ በሙሉ በይፋ ስርጭቱን ማቆሙን ገልጿል።

አሻም ቴሌቪዥን ከተጠቀሰው ጊዜ ጀምሮ የአሻም ሚዲያ መታወቂያ በመያዝ ወይም የሚዲያዋን ሎጎ በመጠቀም በየትኛውም ሁነት (Event) ፣ በእቅድ ዜና ወይም ፕሮግራም ፣ በስልጠና መድረክ ፣ ቃለ-መጠይቅ እና በመሰል ጉዳዮች ላይ የሚገኙ (የሚሳተፉ) ባለሞያዎች የሚዲያ ተቋሙን እንደማይወክሉ ለሁሉም የግልና መንግስታዊ ተቋማት እንዲሁም ግለሰቦች  ጭምር በትህትና ለማሳወቅ እንወዳለን ብሏል።

አሻም ሚዲያ ትሬዲንግ አክሲዮን ማህበር ባለፉት 8 ዓመታት ጀምሮ በማህበራዊ ፣ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ጉዳዮች ዙሪያ በዜናና ወቅታዊ እንዲሁም በመዝናኛ ዝግጅቶች መረጃዎችን በቴሌቪዥን እና በተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያ አማራጮች ሲያሰራጭ ቆይቷል።

ለተጨማሪው: https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
😭426😢3🔥2👍1
📌"ጎላ ጉህ"  ያሬድ ሹመቴ ነው

የድምጻዊት የማርያም ቸርነት "የደጋ ሰው" አልበም ላይ አብዛኞቹን ግጥሞች የጻፈውና ያስደመመን "ጎላ ጎህ"  የተባለው ባለ ብዕር ስም ያሬድ ሹመቴ እንደሆነ ደጃፍ ፖድካስት ላይ ተናግሯል።

ይሄ  ጎላ ጎህ የሚባለው ሰው ማነው ስትሉ ለከረማችሁ ሙሉ መልሱን ራሱ ያሬድ ሹመቴ ይነግራችኋል።

ሊንክ:https://youtu.be/tm9PercKdUI?si=8rUTaybnEUjzQQKM

ለተጨማሪው: https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
👍25🔥126😱3
📌አንባቢያን መጽሐፍ የሚቀያየሩበት ልዩ ዝግጅት

የአዲስ የሥነጽሑፍ ፌስቲቫል አካል የሆነ  "ሥነ ጽሑፍ እና ነገረ ሐቲት" የተሰኘ መርሐግብር ተዘጋጅቷል።

ቅዳሜ ታህሳስ 4 ፣ 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 4:00 – 12:00 ከቤት እስከ ከተማ ፡ የከተማ ማዕከል ውስጥ በተዘጋጀው በዚህ መሰናዶ የመጽሐፍ ወዳጆች አዳዲስ እና የቆዩ መጻሕፍትን የሚሸጡበት፣የመጻሕፍት ልውውጥ፣እንዲሁም ያነበቡትን መጽሐፍ  በሌላ የሚቀያየሩበት እና ስለ ሥነ ጽሑፍ ጥልቅ ውይይት የሚያደርጉበት ይሆናል ስለመባሉ ኤቨንት አዲስ ሰምቷል።

በውይይቱ ላይ ከኢትዮጵያ ቡክ ፎረም ዳዊት ብርሃኑ ፣ ከኢትዮጵያ ሳይንክ አካዳሚ ሐያሲ ቴዎድሮስ አጥላው፣ ጸሐፌ ተውኔት መዓዛ ወርቁ እንዲሁም ሌሎችም ተጋባዥ እንግዶች ይገኙበታል።

ለተጨማሪው: https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
👍54
📌 የሮማን ተወለደ "ዮዲታ" መጽሐፍ ዛሬ ይመረቃል

ሮማን ተወልደብርሃን የጻፈችውና የክርስትና እናቴ በሰጠችኝ ሁለተኛ ስሜ "ዮዲታ" የተሰኘ ርዕስ ሰጥቼዋለሁ ያለችውን መጽሐፏን በዚህ ሳምንት ለንባብ አብቅታለች።

"ዮዲታ" የተሰኘው መጽሐፏ በይዘት ግለታሪክ ሲሆን ዛሬ ቅዳሜ ታህሳስ 4 ከቀኑ 8:00 ጀምሮ ገሐር በሚገኘው በአዲሱ ጃፋር የመጽሐፍት መደብር ውስጥ ይመረቃል።

በጃፋር መጽሐፍት መደብር በኩል ለንባብ የበቃ መጽሐፏ በቀጣይ በተለያዩ የኢትዮጵያ አካባቢዎች እንደሚሰራጭም ደራሲዋ ገልጻለች።

ደራሲ ሮማን ተወለደብርሃን አስቀድማ ጉራማይሌና የነፍስ እኩያዎች የተሰኙ መጽሐፍትን በቡድን እንዲህም ለታዳጊዎች ደናደን የተሰኙ መጽሐፍትን ለንባብ አብቅለታች።

ለተጨማሪው: https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
25
📌ኢትዮጵያዊው ዓለም አቀፍ ሽልማት አሸነፈ

ኢትዮጵያዊው የፊልም ባለሙያ ቤዛ ኃይሉ 'አላዛር' በተሰኘ ፊልም ዓለም አቀፍ ሽልማት አሸነፈ::

በፊልም ጽሁፍ አዘጋጁና ዳይሬክተሩ የተሠራው ፊልም፤ የ "ዳካር ኮርት የ2025 ዓለም አቀፍ የአጭር ፊልም ፌስቲቫል ግራንድ ፕሪ ሽልማት አሸናፊ ለመሆን በቅቷል፡፡

ለ36 ደቂቃዎች የሚዘልቀው “አላዛር” ፊልም፣ ለምርጥ ዳይሬክተር የሚሰጠውን “አባባካር ሳም ማክሃራም” የተሰኘውን ሽልማት መቀዳጀቱንም አዘጋጆቹ አስታውቀዋል፡፡

ፊልሙ በዘመናዊቷ ኢትዮጵያ የገበሬ ማህበረሰብ ሐይማኖት፣ አመክንዮና አምልኮ ዙሪያ በማጠንጠን ተመልካቾችን ስሜታዊ መዋዥቅ ውስጥ ሰቅዞ እንደሚይዝ ዳኞቹ ለምርጫቸው በሰጡት ማብራሪያ መናገራቸውን ስፑትኒክ ዘግቧል፡፡

ለተጨማሪው: https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
43👍8👏3🔥1
📌"ከርቤ" ፊልም አርብ ይለቀቃል !

በሂስትሪ ፊልም ካምፓኒ ተሰርቶ የቀረበው "ከርቤ" ፊልም አርብ ታህሳስ 10 ልክ 12:00 ሲል በNahom_Multimedia ዩቲዩብ ቻናል በኩል  ይለቀቃል።

ጭብጡን በጓደኛው ታላቅ በደልና ታላቅ ውለታ መሃል ገብቶ የተወጠረው አባት ነገሮችን ለመፍታት በሚከፍለው መስዋትነት እና በቀረው ቤተሰብ መካከል የተፈጠረውን ክስተት የሚያሳይ ልብ አንጠለጣይ ፊልም ነው።

በስዩም በላይ Produced የተደረገ ሲሆን ፊልሙን ዳይይሬክት ያደረገው አለባቸው አራጌ፣ ሲኒማቶግራፊውን  ዳንኤል ግርማ፣  በትወና ደግሞ በሄኖክ ወንድሙ፣ መዓዛ ገ/ሕይወት ፣ የአብሥራ ታደሠ፣ ከድር ሁሴን፣ ይሁኔ ምንዋጋው፣ ሰርካለም ደምሴና ሌሎችም ተሳትፈውበታል፡፡

ፊልሙ አርብ ታህሳስ 10 ምሽት በNahom_Multimedia ዩቲዩብ በኩል ለተመልካች ይደርሳል።

ፊልሙ የሚለቀቅበት ቻናል ሊንክ ይኸው

https://youtube.com/@nahommultimedia?si=YqGl8THSPt1GIv7D
9👍9
📌የያንጎ ፌሎውሺፕ ኢትዮጵያን ጨምሮ በስድስት የአፍሪካ ሀገራት ተጀመረ

ይህም የቀጣዩን ትውልድ ዐቅም በሳይንስ እና ቴክኖሎጂ እንዲሁም በምኅንድስና እና ሒሳብ ዘርፍ ለማጎልበት የሚያስችል ነው::

ዓለም አቀፋዊ የቴክኖሎጂ ተቋም የሆነው ያንጎ ግሩፕ፣ የያንጎ ፌሎውሺፕ ቀጣይ ምዕራፍ - በመላው አፍሪካ የሳይንስ እና ቴክኖሎጂ እንዲሁም የምኅንድስና እና ሒሳብ ዘርፍ ችሎታን ለማጎልበት ዓልሞ እንደተነደፈ አስታውቋል። 

ያንጎ ፌሎውሺፕ፣ ወጣቶችን በማማከር እና አቅጣጫ በመጠቆም እንዲሁም ግብዓቶችን እና የግንኙነት መረቦችን በመዘርጋት፣ ተሳታፊዎች ማኅበረሰባቸውን የሚጠቅሙ ሐሳቦችን እንዲያመነጩ ብሎም ወደ ተግባር እንዲቀይሩ እገዛ ያደርጋል።

በዛምቢያ እና በአይቮሪኮስት በተሳካ ሁኔታ የተጀመረው የያንጎ ፌሎውሺፕ ፕሮግራም አድማሱን በማስፋት ወደ አራት ተጨማሪ ሀገራት፣ ማለትም ኢትዮጵያ፣ ሞዛምቢክ፣ ጋና እና ሴኔጋል ደርሷል።

መዳረሻዎቹን እያሰፋ የመጣው የያንጎ ፌሎውሺፕ ፕሮግራም፣ የገንዘብ ድጋፍን እና የባለሙያዎችን ሰፊ እገዛ ያካተተ ከመሆኑም ባሻገር፣ በድንበር ያልተገደበ ሰፊ የፌሎው ተጠቃሚ ማኅበረሰብ ግንኙነቶችን በማመቻቸት ተሳታፊዎች ለኅብረተሰባቸው መፍትሔ ፈጣሪ እንዲሆኑ የሚያስችል ነው።

ተጨማሪ ያንብቡ: https://url-shortener.me/460W
4👍1👎1