Event Addis Media – Telegram
Event Addis Media
9.63K subscribers
6.1K photos
13 videos
4 files
4.72K links
Connect with Addis artistic community!

Website: https://eventaddis.com

Contact: @Tmanaye
Download Telegram
📌በሙሽሪት አለመገኘት ምክንያት ሰርጉ ተሰረዘ

በአዲስ አበባ ከተማ ሰሞኑን የተሰማውና ብዙዎችን ያነጋገረው የሰርግ ታሪክ፣ በወጪ ብዛት ሳይሆን በፍጻሜው አስደናቂነት መነጋገሪያ ሆኗል።

ሁሉም ነገር ተሰናድቶ፣ የሰርግ አዳራሹ አሸብርቆ፣ ምግብና መጠጡ ሞልቶ የተጠበቀው ሰርግ፣ በሙሽሪት አለመገኘት ምክንያት ሳይሳካ ቀርቷል።

ኖር ሬድዮ ታሪኩን እንዲህ ይነግራችኋል ለዓመታት በትውውቅ የቆዩትና ሙሽራው በውጭ ሀገር የሚኖረው እነዚህ ጥንዶች፣ ጋብቻቸውን ለመፈጸም የለፋ ወጪ አውጥተው ነበር።

ለምሳሌ ያህል ለክትፎ ብቻ 450 ሺህ ብር ቅድመ ክፍያ (Advance) ተከፍሎ ነበር። ዲኮሩም ከትናንትናው ጀምሮ በደማቅ ሁኔታ ተሰርቶ አልቋል።

​ነገር ግን በሰርጉ ዋዜማና በዕለቱ በተፈጠረ አለመግባባት ነገሮች ተበላሹ። ሙሽሪት "ከጋብቻ በፊት የጤና ምርመራ ማድረግ አለብን" የሚል ጥያቄ ታነሳለች። ሙሽራው በበኩሉ ይህንን ጥያቄ ለመቀበል ፈቃደኛ አልሆነም ወይም ጊዜው አልፈቀደም ተብሏል።

በዚህ መሃል "ሙሽራው ከዚህ በፊት ትዳር ነበረው፣ አምስት ልጆችም አሉት" የሚሉ ወሬዎችና ጥርጣሬዎች መፈጠራቸው ችግሩን አባብሶታል ተብሏል። ሽማግሌዎች ገብተው ለማስማማት ያደረጉት ጥረትም ሳይሳካ ቀርቷል።

​በመጨረሻም በሰርጉ ቀን ሙሽራውና ሚዜዎቹ ዘንጠው ተዘጋጅተው ቢጠብቁም፣ ሙሽሪት ግን "አልመጣም" በማለት ቀረች።

ተጋባዥ እንግዶችም አንዳንዶቹ ጉዳዩን ሰምተው ሳይመጡ ቀርተዋል። በሚሊዮኖች የሚቆጠር ወጪ የፈሰሰበት ይህ ሰርግ፣ ሙሽራው ብቻውን ከሚዜዎቹ ጋር በባዶ አዳራሽ ፎቶ ተነስቶ ወደ ቤቱ በመመለሱ ተጠናቋል።

ለተጨማሪው: https://news.1rj.ru/str/EventAddis1

ለተጨማሪው: https://news.1rj.ru/str/NorRadio1
😁2813👍10🤔4👏3💔2🤷2
📌ዝነኛው አይሾው ስፒድ አዲስ አበባ ገባ

በዓለም አቀፍ ደረጃ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ተከታዮች ያሉት ዝነኛው አሜሪካዊ ዩቲዩበር አይሾው ስፒድ (IShowSpeed) ከጥቂት ደቂቃዎች በፊት አዲስ አበባ ገብቷል።

ዩቲዩበሩ ወደ ኢትዮጵያ መምጣቱን ተከትሎም የቀጥታ ሥርጭት (Livestream) እንደሚያደርግ ይጠበቃል።

በተለያዩ የዓለም ሀገራት እየተዘዋወረ በሚያደርጋቸው አዝናኝና አስገራሚ የቀጥታ ሥርጭቶቹ የሚታወቀው አይሾው ስፒድ (IShowSpeed)፤ ከሰዓታት በኋላ ቦሌ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ እንደሚደርስ በገጹ ጽፏ ነበር።

ለተጨማሪው: https://news.1rj.ru/str/EventAddis1

ለተጨማሪው: https://news.1rj.ru/str/NorRadio1
👍10👎83
📌ኮምሽነር ሌሊሴ ዱጋ የክብር አምባሳደር ሆነዋል

ኮምሽነር ሌሊሴ ዱጋ የኢትዮጵያ የሕፃናት ደም እና ካንሰር ሕክምና ማኅበር የክብር አምባሳደር ሆነዋል።

በኢትዮጵያችን በየዓመቱ ከ6 ሺህ እስከ 8 ሺህ የሚሆኑ ሕፃናት በካንሰር በሽታ ይጠቃሉ።ይሁን እንጂ ወደ ሕክምና ማዕከላት መጥተው ሕክምና የሚያገኙት ሕፃናት ቁጥር ከ2 ሺህ አይበልጥም።

በአደጉ ሀገራት የሕፃናት ካንሰር ታማሚዎች የመዳን ምጣኔ ከ85% በላይ ቢሆንም፣ በኢትዮጵያ ግን በምርመራ መዘግየት፤ በህብረተሰቡ ዘንድ ባለው የግንዛቤ ውስንነት፣ በዘርፉ በተሰማሩ ባለሙያዎች እጥረት፣ ምክንያት ውጤቱ አሁንም እጅግ ዝቅተኛ ነው።

ይህን ችግር በዘላቂነት ለመፍታትና የተቀናጀ ሙያዊ ምላሽ ለመስጠት 35 መደበኛ አባላትን እና ከ150 በላይ ተባባሪ አባላትን ይዞ ጥር 4 2018 ዓ.ም "የኢትዮጵያ የሕፃናት ደም እና ካንሰር ሕክምና ማኅበር" በይፋ ተመስርቷል።

በዚህ የማኀበሩ ምስረታ ማብሰሪያ ዝግጅት ላይም በከፍተኛ የስራ ኃላፊ ደረጃ የጤና ሁኔታ ለሕዝብ ማጋራት ባልተለመደበት ማኅበረሰብ ውስጥ የካንሰር ሕክምና እየተከታተሉ መሆናቸውን ፎቷቸውን ጭምር አያይዘው በማኅበራዊ ሚዲያ ያጋሩትና በበርካቶች ዘንድ መነጋገሪያ የሆነው የሰንበቱት የኦሮሚያ ቱሪዝም ኮሚሽን ኮሚሽነር ሌሊሴ ዱጋ ህክምናቸውን ከሚከታተሉበት ጆርዳን አማን በቪዲዮ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።

ኮሚሸነሯ በመልዕክታቸው"አላስፈላጊ ስቃይን የምናስቆምበት አዲስ የታሪክ ምዕራፍ መጻፍ አለብን" ያሉ ሲሆን በተጨማሪም የዚህ ማኅበር የክብር አምባሳደር በመሆናቸው ደስተኛ መሆናቸውን ገልጸዋል።

ለተጨማሪው: https://news.1rj.ru/str/EventAddis1

ለተጨማሪው: https://news.1rj.ru/str/NorRadio1
8👏4👍3😢1
📌የድምጻዊ ዮናታን ንብረት አዲስ ሙዚቃ ሊለቅ ነው

በፋና ላምሮት የድምፃውያን ውድድር ላይ በነበረው የላቀ ብቃት የሚታወቀው ድምፃዊ ዮናታን ንብረት፤ "እድሜ ላንቺ" የተሰኘ አዲስ ነጠላ ሙዚቃውን ለሙዚቃ አፍቃሪያን ሊያቀርብ መሆኑን አስታወቀ።

ድምጻዊ ዮናታን "እድሜ ላንቺ" በሚል ርዕስ ያዘጋጀው አዲስ የሙዚቃ ቪዲዮ የፊታችን አርብ በናሆም ሪከርድስ በኩል ለሕዝብ እንደሚደርስ ገልጿል።

ለረጅም ጊዜ ከሙዚቃ አፍቃሪያን እይታ ርቆ የቆየው ድምፃዊው፤ ቆይታው ጥራት ያላቸውን ሥራዎች ለማቅረብ በሚደረግ ዝግጅት መሆኑን ጠቅሶ ለደጋፊዎቹ ይቅርታን ጠይቋል።

በዚህ አዲስ የሙዚቃ ሥራ ላይ በግጥም ኑረዲን ኢሳ በዜማ አበበ ብርሃኔ በሙዚቃ ቅንብር ሚካኤል ኃይሉ ተሳትፈውበታል።

ድምፃዊው ይህንን ሥራውን ተከትሎ ሌሎች ተከታታይ የሙዚቃ ሥራዎችን ለታዳሚ ለማድረስ ማቀዱን አስታውቋል።

ለተጨማሪው: https://news.1rj.ru/str/EventAddis1

ለተጨማሪው: https://news.1rj.ru/str/NorRadio1
20
📌 አይሾው ስፒድ ድንገተኛ ህመም ገጠመው

በዓለም አቀፍ ደረጃ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ተከታዮች ያሉት ዝነኛው አሜሪካዊ ዩቲዩበር አይሾው ስፒድ የኢትዮጵያን ባህል ለማጣጣም ጥሬ ስጋ በልቶና ወፍራም ቡና ጠጥቶ ወደ ጭፈራው እንደገባ  ድንገተኛ ህመም ገጥሞታል።ይህንንም ከ200ሺ በላይ ሰዎች በቀጥታ ስርጭት ተመልክተዋል።

ያ ሁሉ ጉልበትና ወኔ አንድ ላይ ተደማምሮ ስፒድን አቅም ያሳጣው ሲሆን፣ ለትንሽ ጊዜ ራሱን ሊስት (Faint ሊያደርግ) እንደነበር ተናግሯል።

​ስፒድ ሁኔታውን ሲገልፅ "እንደዚህ አይነት ስሜት ገጥሞኝ አያውቅም፤ ለትንሽ ፌንት በልቼ ነበር!" በማለት የኢትዮጵያ ምግብና ሙዚቃ ጉልበት ምን ያህል ከባድ እንደሆነ መስክሯል።

ለተጨማሪው: https://news.1rj.ru/str/EventAddis1

ለተጨማሪው: https://news.1rj.ru/str/NorRadio1
😁20😨42👌1
📌የአዲስ አበባው ከፍተኛ ቅዝቃዜ

​በአዲስ አበባ ከተማ በሚቀጥሉት አስር ቀናት ውስጥ ከፍተኛ ቅዝቃዜ ሊከሰት እንደሚችል ተነገሯል።

ዝቅተኛው የሙቀት መጠን እስከ 1.4 ዲግሪ ሴልሺየስ ሊወርድ እንደሚችል የኢትዮጵያ ሚቲዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት አስጠነቅቋል።

የኢንስቲትዩቱ ምክትል ዋና ዳይሬክተር ዶክተር አሳምነው ተሾመ ለመናኸሪያ ሬዲዮ እንደገለጹት፤ ባለፉት አስር ቀናት የታየው ደረቅና ቀዝቃዛማ የአየር ሁኔታ በቀጣዮቹ ቀናትም ይበልጥ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል የትንበያ መረጃዎች አመልክተዋል።

​ከዋና ከተማዋ በተጨማሪ በመካከለኛው ምስራቅ፣ በመካከለኛው ደቡብ እና በደጋማ የሀገሪቱ ክፍሎች የሌሊቱና የማለዳው ቅዝቃዜ እጅግ ከፍተኛ እንደሚሆን ተጠቁሟል።

በእነዚህ አካባቢዎች በብዙ ቀናት የሙቀት መጠኑ ከ5 ዲግሪ ሴልሺየስ በታች ሆኖ እንደሚመዘገብ የተገለጸ ሲሆን፣ ይህም በደጋማ ስፍራዎች ለሚኖሩ ነዋሪዎችና ለግብርና ስራዎች ተጽዕኖ ሊኖረው እንደሚችል ይጠበቃል።

​ለተጨማሪው: https://news.1rj.ru/str/EventAddis1

ለተጨማሪው: https://news.1rj.ru/str/NorRadio1
7
📌ጥምቀትን በባቱ/ዝዋይ ደንበል ሀይቅ ላይ ያሳልፉ

በ9500 ብር ብቻ ሁለት የማይረሱ ቀናት ያሳልፉ

Epiphany Trip to 📍 Lake Dembel (Batu)

🗓 Date | ቀን: ጥር 10-11
January 18–19

Duration | የቆይታ ጊዜ: 2 Days / 1 Night
Tour Type | የጉብኝት አይነት: Epiphany Celebration & Cultural Experience

💰 Price | ዋጋ
• Local | መደበኛ: 9,500 Birr
• Foreigners | ፎረነር: 300 USD

Price Includes | ዋጋው የሚያካትተው
🍽️ Meals | ምግብ
🚌 Transportation | መጓጓዣ
💧 Bottled Water | የታሸገ ውሃ
Hot Drinks (Coffee & Tea) | ቡና እና ሻይ
🍷 Wine Tasting at Castel Winery | የወይን መጠጥ ሙከራ
🧑‍✈️ Guide Fee | የመሪ ክፍያ
🎟 Entrance Fees | የመግቢያ ክፍያ

Price Excludes | ዋጋው የማይያካትተው
💼 Personal Expenses | የግል ወጪዎች
🍺 Alcoholic Beverages (Outside Program) | የአልኮል መጠጥ

📞 For Booking & Details
☎️  09-19-87-45-98 / 09-39-61-61-63
📍 Visit Us: Bole Tropical Mall, 8th Floor
8
📌አርቲስት ቸርነት ፍቃዱ የ"ኒው ዌይ ኢትዮጵያ" ብራንድ አምባሳደር ሆኖ ተሾመ

ሌግዤሪ ኢቨንት እና ኘሮሞሽን ከኒው ዌይ ኢትዮጵያ ጋር በመተባበር ባዘጋጁት መርሃ-ግብር፤ ተወዳጁ አርቲስት ቸርነት ፍቃዱ የድርጅቱ የብራንድ አምባሳደር ሆኖ በይፋ ተሰይሟል።

​ዋና ዋና የትኩረት ነጥቦች፡-

🎓 ዓለም አቀፍ የትምህርት ዕድል (2026)፡
የድርጅቱ ዋና ዳይሬክተር አቶ ዋሲሁን ዘውዱ እንዳበሰሩት፤ በያዝነው የፈረንጆቹ 2026 ዓ.ም ጀምሮ ኢትዮጵያውያን ተማሪዎች በአርሜኒያ ስቴት ዩኒቨርሲቲዎች እና ሌሎች ተቋማት የትምህርት ዕድል የሚያገኙበት መንገድ ተመቻችቷል።

🌍 የቱሪዝም ትስስር፡
ድርጅቱ በኢትዮጵያ፣ በአርሜኒያ እና በጆርጂያ መካከል ያለውን የቱሪዝም እና የባህል ግንኙነት ለማጠናከር ይሰራል፡፡

🤝 የዲፕሎማሲ ድጋፍ፡
በመርሃ ግብሩ ላይ የተገኙት በኢትዮጵያ የአርሜኒያ አምባሳደር ሳሃክ ሳርግስያን፤ ይህ የቱሪዝም እና የትምህርት ትብብር በሁለቱ ሀገራት ህዝቦች መካከል ያለውን ታሪካዊc ወዳጅነት እና ኢኮኖሚያዊ ትስስር እንደሚያሳድገው ገልጸዋል።

🗣 የአምባሳደሩ ቃል፡
አርቲስት ቸርነት ፍቃዱ በበኩሉ፤ የኢትዮጵያን የተፈጥሮ እና የታሪክ ጸጋዎች ለዓለም ለማስተዋወቅ የተሰጠውን ኃላፊነት በቁርጠኝነት እንደሚወጣ አረጋግጧል።

ℹ️ ስለ ኒው ዌይ ኢትዮጵያ፡
በ11ዱም ክልሎች የሚገኙ የቱሪስት መስህቦችን በዘመናዊ ቴክኖሎጂ የሚያስተዋውቅ ሲሆን፤ ለውጭ እና ሀገር ውስጥ ደንበኞች የተቀናጀ የጉዞ እና የቪዛ አገልግሎት ይሰጣል።

ለተጨማሪው: https://news.1rj.ru/str/EventAddis1

ለተጨማሪው: https://news.1rj.ru/str/NorRadio1
3👍2
📌አይሾው ስፒድ 310 ሚሊዮን ብር ይከፈለዋል ?

አሜሪካዊው ዩቲዩበር አይሾው ስፒድ ወደ ኢትዮጵያ የሚያደርገውን ጉብኝት ተከትሎ፣ የኢትዮጵያ መንግስት በቱሪዝም ዘርፉ በኩል ከፍተኛ በጀት መድቦለታል የሚሉ መረጃዎች በማህበራዊ ሚዲያ በስፋት እየተሰራጩ እንደሚገኙ ኖር ሬድዮ ተመልክቷል።

ወጡ በተባሉ መረጃዎች መሠረት፦
ለዩቲዩበሩ እንዲከፈል የተመደበው በጀት እስከ 310 ሚሊዮን የኢትዮጵያ ብር:- ዝርዝሩን ያንብቡ: https://news.1rj.ru/str/NorRadio1
👎266👍2👏2😱1
📌"በቅጽበቶች መካከል" የፎቶግራፍ አውደርዕይ 

በፎቶ ባለሞያዎቹ አሸናፊ የማነ፣ርብቃ ሲሳይ፣ ልዑል መኮንን የተዘጋጁ የፎቶግራፍ ስራዎች የሚቀርቡበት "በቅጽበቶች መካከል" የፎቶግራፍ አውደርዕይ ዛሬ ረቡዕ ጥር 5 2018 ዓ.ም ጀምሮ ሐያት ሪጀንሲ ውስጥ በሚገኘው ፈንድቃ የባህል ማዕከል ውስጥ ለእይታ ይበቃል ። ይህ የሥዕል አወድርዕይ እስከ ጥር 30 2018 ዓ.ም ድረስ ይቆያል ተብሏል።

ለተጨማሪው: https://news.1rj.ru/str/EventAddis1

ለተጨማሪው: https://news.1rj.ru/str/NorRadio1
📌 የድምጻዊ ብዙአየሁ ደምሴ አዲስ ሙዚቃ

የድምጻዊ ብዙአየሁ ደምሴ "መሽቶ ነጋ" የተሰኘ አዲስ ነጠላ ሙዚቃ ለአድማጮች ሊቀርብ ነው።

በዚህ የድምጻዊው የሙዚቃ ስራ ላይ በግጥም እሱባለው ይታየው፣ በዜማ ዳዊት አለማየሁ፣በሙዚቃ ቅንብር ኪሩቤል ተስፋዬ ተሳትፈውበታል።

ለተጨማሪው: https://news.1rj.ru/str/EventAddis1

ለተጨማሪው: https://news.1rj.ru/str/NorRadio1
👍5
📌 "ኢትዮጵያ የሚለው ስም ከ8.3 ሚ ጊዜ በላይ ተፅፏል፤ ሪፖስት ተደርጓል "

አይሾስፒድ ወደ ኢትዮጵያ መምጣቱን ተከተሉ "ኢትዮጵያ" የሚለው ስም በዓለምአቀፍ ደረጃ ከፍተኛ የሚዲያ ሽፋን አግኝቷል።

በአጠቃላይ በፌስቡክ፣ዩቲዩብ፣ ኤክስ፣ ቲክቶክ፣ የተለያዩ ዌብ ሳይቶች ብቻ ያውም ፕራይ ቬት ባልሆኑት "ኢትዮጵያ የሚለው ስም ከ8.3 ሚሊየን ጊዜ በላይ ተፅፏል ሪፖስት ተደርጓል።

ይህም በሰዓት 172,000 ጊዜ ማለት ነው። ያውም እያንዳንዱ ኮሜንት ተቆጥሮ አይደለም። ይህ ቁጥር በቀናት ውስጥ ከ20- 50 ሚሊየን ይደርሳል ተብሏል።

ለተጨማሪው: https://news.1rj.ru/str/EventAddis1

ለተጨማሪው: https://news.1rj.ru/str/NorRadio1
👍1713🔥1
ለአፄ ቴዎድሮስ እንደ ብራዚል ዓይነት ግዙፍ ሀውልት

አፄ ቴዎድሮስ የሚመጥን ልክ እንደ ህንድ እና ብራዚል ሀገራት የሚገኙ ግዙፍ ሀዉልቶች ጎንደር ላይ ለማቆም ፍላጎትና እቅድ መኖሩ ተበሰረ።

የንጉሠ ነገሠት አፄ ቴዎድሮስ 207ኛ ዓመት የልደት በዓል  በጎንደር ከተማ በልዩ ልዩ ዝግጅቶች እየተከበረ ነው።

ዛሬ ጥር 06 የሚከበረው የአጼ ቴዎድሮስ ልደት ጥምቀትን  በጎንደር አንዱ አካል የኾነና ለጎንደር ከተማ ተጨማሪ የቱሪዝም ሃብት ነው።

አጼ ቴዎድሮስ  የኢትዮጵያን ታላቅነት እና አንድነት ለማጽናት እስከ ሕይወት መስዋዕትነት የከፈሉ  ጀግና መሪ ነበሩ።  ቴዎድሮስ  ትውልዱ ለሀገሩ አንድነት ፣ሉዓላዊነት፣ ከብር እና ኩራት እንዲሠራ ታላቅ አርዓያ ናቸው።

ከዘመናቸው የቀደሙት ቴዎድሮስ አፍሪካ በጨለማ በነበረችበት ዘመን በሀገራቸው ላይ የመጀመሪያው ፋብሪካ ያቋቋሙ፣ የጦር መሣሪያ የሠሩ፣ ከመዘናቸው የቀደሙ ባለ ራዕይ መሪም ነበሩ። ለሀገራቸው አንድነት እና ሥልጣኔ ባበረከቱት አስተዋጽኦ፣ በጀግንነታቸው ሲወሱ የሚኖሩት አጼ ቴዎድሮስ ታሪካቸውን በሚዘክር መልኩ የልደት በዓላቸው  እየተከበረ ነው።

በመርሃ ግብሩ መልዕክት ያስተላለፉት የከተማው ከንቲባ አፄ ቴዎድሮስ የሚመጥን ልክ እንደ ህንድ እና  ብራዚል ሀገራት የሚገኙ ግዙፍ ሀዉልቶች ጎንደር ላይ ለማቆም ፍላጎትና እቅድ መኖሩን አብሰራዋል።

©️Dire tube

ለተጨማሪው: https://news.1rj.ru/str/EventAddis1

ለተጨማሪው: https://news.1rj.ru/str/NorRadio1
28👏4👍1👎1
📌ቬሮኒካ አዳነ በናይጄሪያ አሳዛኝ ነገር ገጠማት

"የሚያሳዝን ቀን ነበር በናይጄሪያ ያሳለፍኩት"

ኢትዮጵያዊቷ የሙዚቃ ኮከብ ቬሮኒካ አዳነ በመላው አፍሪካ ትልቅ ግምት የሚሰጠውን የ9ኛው የአፍሪካ ሙዚቃ ሽልማት (AFRIMA) በአሸናፊነት አጠናቃለች። ቬሮኒካ በናይጄሪያ ሌጎስ በተካሄደው በዚህ ደማቅ ስነ-ስርዓት ላይ፦"The Best Artist, Duo or Group in African Traditional Music" በሚለው ዘርፍ አህጉራዊ ተፎካካሪዎቿን በመብለጥ ድልን ተቀዳጅታለች።

ከሽልማቱ በስተጀርባ ያለው አሳዛኝ ክስተት ምንድን ነው?

ድምፃዊቷ በሽልማት ስነ-ስርዓቱ ላይ ለምን አልታየሽም ለሚሏት ደጋፊዎቿ በማህበራዊ ትስስር ገጿ በሰጠችው ምላሽ በናይጄሪያ የገጠማት ነገር አስከፊ እንደነበር እንዲህ ስትል ገልጻለች.. ተጨማሪውን ያንብቡ:- https://news.1rj.ru/str/NorRadio1/23
🖕156😁4🤔2💩2👎1👏1
📌 የገና ኢግዚቢሽን ውዝግብ አስነሳ

በአዲስ አበባ ኤግዚቢሽን ማዕከል ለ2018 ዓ.ም የገና በዓል የተሰናዳው የንግድ ባዛር እና ኤግዚቢሽን መጠናቀቁን ተከትሎ በተፈጠረ የክፍያ ውዝግብ፣ አገልግሎት አቅራቢ ድርጅቶች እና ታዋቂ ግለሰቦች ንብረታቸውን ማውጣት አለመቻላቸው ተሰማ።

የውዝግቡ መነሻ የ2018 ዓ.ም የገና እና የፋሲካ በዓልን በኤግዚቢሽን ማዕከል እንዲያሰናዳ ጨረታውን አሸንፎ ውል የወሰደው "ዳሰማ ትሬዲንግ" የተሰኘው ተቋም ነው። ይህ ተቋም ለዝግጅቱ ድምቀት እና አገልግሎት አሰጣጥ ከተለያዩ አካላት ጋር የኮንትራት ስምምነት ፈጽሞ ነበር።

ከእነዚህም መካከል "አብረሃም የድግስ ዕቃ አከራይ" በኤግዚቢሽን ማዕከሉ ውስጥ የተተከሉትን ድንኳኖች በማቅረብ፣ እንዲሁም አንጋፋው ድምጻዊ ዳዊት ጽጌ የመድረክ እና የሙዚቃ ሥራዎችን ሙሉ በሙሉ በኮንትራት ወስደው አገልግሎት ሲሰጡ ቆይተዋል።

ኤግዚቢሽኑ መጠናቀቁን ተከትሎ እነዚህ የአገልግሎት ሰጪ ተቋማት ንብረታቸውን ከማዕከሉ ለማውጣት ያደረጉት ሙከራ ሳይሳካ ቀርቷል። ለዚህም በምክንያትነት...

ዝርዝሩን ያንብቡ:https://news.1rj.ru/str/NorRadio1/25
7😢2🍌1
📌ልዑል ሲሳይ እና 10 ነፃ ትኬቶች

ከድምፃዊ ልዑል ሲሳይ ጋር ኑ ቡና ጠጡ ነፃ 10 ትኬቶች አዘጋጅተናል። ይህን ፖስት ለ10 ሰዎች ሼር ያደርጉ።

ከተወዳጁ ድምፃዊ ልዑል ሲሳይ ጋር ቡና እየጠጣችሁ መስራት የምትፈልጉዋቸውን ስራዎች ከእሱ ጋር የምታወሩበት እና የምትወያዩበት መድረክ የፊታችን ቅዳሜ እንደሚካሄድ ይታወቃል።

የራሳችሁን ሥራዎች እንዲሁም ያለውን ልምድ አንድ ለአንድ በሚፈጠረው መድረክ ላይ ስለሰራቸው ሙዚቃዎች እንዲሁም ቀጣይ ስለሚያስባቸው ስራዎቹ የሚያካፍልበት የሲንክ አፕ ቻት ፕሮግራም ሲሆን በዚህ ፕሮግራም ላይ መሳተፍ ለምትፈልጉ ሙዚቃ ላይ ፍላጎት ያላችሁ እንዲሁም የድምፃዊው አድናቂ ለሆናችሁ አድናቂዎች 10 ነፃ ትኬቶችን አዘጋጅተናል።

ትኬቱን ለማግኘት ይህ ፖስት ለአስር ሰዎች ሼር ያድርጉ:

📅️️️️ ቀን ፡ ጥር 9
⏰️️️️️️️ ከቀኑ 9 ሰዓት ላይ
📍️️️️ቦታ ፡ ጋዬ ቡና ልደታ ባልቻ ሆስፒታል ፊት ለፊት ( ካፕስቶን ህንፃ )

🎟️️️️ ተጨማሪ ትኬቶችን ለመግዛት
- መደበኛ - 500 ብር ( ከ ነፃ ቡና ጋር )
- ቪአይፒ - 1000 ብር ( ከነፃ ቡና እና ምግብ ጋር )

ያለውን ቦታ ውስን ስለሆነች አሁኑኑ ትኬቱን ይቁረጡ

ትኬትዎን ለመቁረጥ ከዚህ በታች ባለው ሊንክ ይመዝገቡ👇️️️️️️
https://linktr.ee/SyncUp.chat

ለተጨማሪው: https://news.1rj.ru/str/EventAddis1

ለተጨማሪው: https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
6👏2🥰1😁1👌1
📌የኢትዮጵያዊ ምግቦች ፌስቲቫል ተዘጋጅ

የአዲስ አበባ ቱሪዝም ኮሚሽን ኢትዮጵያዊ ምግቦች የሚቀርቡበት ፌስቲቫል ሊያዘጋጅ መሆኑን አስታወቀ፡፡

"ጋስትሮኖሚ" የተሰኘው ፌስቲቫሉ የሚዘጋጀው የአዲስ አበባ ቱሪዝም ኮሚሽን ጎልደን ግሩፕ ሆስፒታሊቲ ከተሰኘ ድርጅት ጋር በመተባበር ነው፡፡

የፊታችን ቅዳሜና እሁድ ክፍት በሚሆነው በዚህ ፌስቲቫል ላይ ኢትዮጵያዊ ምግቦች፣ የምግብ ግብአት አቅራቢዎች በሆቴሎችና በዘርፉ የተሰማሩ ከ100 በላይ ድርጅቶች ተሳታፊ ይሆናሉ ተብሏል፡፡

የአዲስ አበባ ቱሪዝም ኮሚሽነር አቶ ሁንዴ ከበደ የጥምቀት ከተራ በአልን አስታኮ በተዘጋጀው በዚህ ፌስቲቫል ላይ በርካታ የውጭ አገር ዜጎች የሚታደሙ ሲሆን ከ20 ሺህ በላይ ሰዎችም ይጎበኙታል ተብሎ እንደሚጠበቅ መግለጻቸውን ኤ.ኤም.ኤን ዘግቧል፡፡

ፌስቲቫሉ በሚሊኒየም አዳራሽ ጥር 9 እና 10 ለሁለት ቀናት ለህዝብ ክፍት ሆኖ እንደሚቆይ በዘገባው ተመላክቷል፡፡

ለተጨማሪው: https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
4❤‍🔥1👎1
📌የኢትዮጵያ ፖስፖርት 90ኛ ደረጃ ላይ ይገኛል

በ'Henley' የፓስፖርት መለኪያ የኢትዮጵያ ፓስፖርት ከአለም 90ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል።

በአለማችን ላይ የሚገኙ 199 ፓስፖርቶችን እና 227 የጉዞ መዳረሻዎችን መሰረት በማድረግ የፓስፖርቱ ባለቤቶች ያለ ቪዛ ምን ያህል ቦታዎች መሄድ እንደሚችሉ በማየት ደረጃ የሚሰጠው የ'Henley' የ2026 የፓስፖርት ደረጃ ይፋ ሆኗል።

የኢትዮጵያ ፓስፖርት ኢራን፣ ሲንጋፖርና ታይላንድን ጨምሮ ወደ 43 መዳረሻዎች ያለ ቪዛ በመውሰድ..ተጨማሪውን ያንብቡ: https://news.1rj.ru/str/NorRadio1/28
3😁3
📌ታዋቂው ራፐር ኢትዮጵያን ማየት እፈልጋለሁ አለ

የአይሾው ስፒድ አስደናቂ የኢትዮጵያ ቆይታ ሌላኛውን ዝነኛ አሜሪካዊ ራፐር ዲዲጂን (DDG) ወደ ኢትዮጵያ እንዲሳብ አድርጎታል።

በኢትዮጵያ ባህልና እስክስታ ቀድሞውኑ የሚማረከው ዲዲጂ፣ አሁን ደግሞ በቀጥታ ስርጭት በተመለከተው እውነታ ረክቶ "ምድረ ቀደምቷን" ለመጎብኘት ያለውን ጽኑ ፍላጎት በይፋ አጋርቷል።

የአይሾው ስፒድን የቀጥታ ስርጭት ከተመለከተ በኋላ ከፍተኛ መነሳሳት ስለተፈጠረበት ዲዲጂ በኤክስ (X) ገጹ ወደ ኢትዮጵያ የመምጣት ፍላጎቱን አጋርቷል።

ልጥፉም ከ730 ሺህ በላይ ዕይታን አግኝቷል። በርካታ ተከታዮቹና ሌሎች ዓለምአቀፍ ተጽዕኖ ፈጣሪዎችም ጉዞውን እንደሚደግፉና ምድረ ቀደምት ወደ ሆነችው ኢትዮጵያ የሚያደርገው ጉዞ ስኬታማ እንዲሆንለት እያበረታቱት ይገኛሉ።

ለተጨማሪው: https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
😁73🔥3👍2😱2
📌ለኢትዮጵያ ፍልስፍና አስፈላጊ መሆኑ ተገለፀ

ኢትዮጵያ አሁን ያለችበትን ችግሮች ለመፍታት ውይይትና አመክንዮ ላይ የተመሰረተ ማህበረሰብ እንደሚያስፈልግ ተነግሯል።

ማህበረሰቡ ፍልስፍና ላይ ያለውን አረዳድና የዘርፉን ፋይዳ በሚመለከት የፍልስፍና መምህሩ ዶክተር ፋሲል መራዊ ከአራዳ ኤፍ.ኤም ጋር በነበራችው ቆይታ እንዳሉት ፥ ከዚህ ቀደም ፍልስፍና ከሃይማኖትና እሴት ጋር የሚቃረን አድርጎ የማሰብ የተሳሳተ አረዳድ መኖሩን ጠቅሰዋል።

ነገር ግን አሁን ላይ ፍልስፍናዊ ሃሳቦችን ማስተናገድ የሚችል ትውልድ እየተፈጠረ መሆኑን አስረድተዋል።

ፍልስፍና ሚና ያለው መሆኑንና ወጣ ካሉ ሃሳቦች ባሻገር የነገ መንገዱን በራሱ ልክ መስፋት የሚችል ጠያቂ ትውልድ ለመፍጠር እንደሚያግዝም አስረድተዋል።

በተመሳሳይ ሌላኛው የፍልስፍና መምህር ዶክተር ዳኛቸው አሰፋ ይህንን ሃሳብ አጠናክረዋል።

በኢትዮጵያ ፍልስፍና እየዳበረ መምጣቱን የገለፁት ምሁራኑ፥ አንድ ሕዝብ መለወጥ እና መዘመን እንዲችል ሃሳብ መሰረታዊ መሆኑን ብሎም ሃሳብ በሂደት ሲያረጅ ደግሞ ፍልስፍናዊ ጥያቄዎችን ማንሳትና የክርክር ባህልን ማዳበር አስፈላጊ ስለመሆኑም ነው ያብራሩት።

©️ዘገባው የአራዳ ኤፍ አም ነው።

ለተጨማሪው: https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
13👎2😁2
📌አዲስ ማለዳ ለጋዜጠኞች ማስታወቂያ አውጥቷል

ክፍት የሥራ ማስታወቂያ
1.  የሥራ መደብ፡- ሪፖርተር
የትምህርት ደረጃ፡- በጋዜጠኝነትና ሥነ ተግባቦት እንዲሁም በተዛማጅ የትምህርት መስኮች የመጀመሪያ ዲግሪ ያለው/ት
ልምድ፡- ቢያንስ ከአንድ ዓመት በላይ የሰራ/ች፣ በህትመትና ዲጂታል ሚዲያ ላይ የሰራ/ች ቢሆን ይመረጣል
ብዛት፡- 2
ደመወዝ፡- በድርጅቱ ስኬል መሠረት

2.  የሥራ መደብ፡- አርታኢ
የትምህርት ደረጃ፡-  በጋዜጠኝነትና ሥነ ተግባቦት እንዲሁም በተዛማጅ የማኅበራዊ ሳይንስ የትምህርት መስኮች የመጀመሪያ ዲግሪ ያለው/ት፡፡ በሌላ ትምህርት መስክ የተማሩ ቢሆንም በሥራ ላይ የቆዩ ከሆነ መወዳደር ይችላሉ፡፡
ልምድ፡- አራት ዓመትና ከዚያ በላይ፣ በህትመትና በዲጂታል ሚዲያ ላይ የሰራ/ች
ብዛት፡- 1
ደመወዝ፡- በድርጅቱ ስኬል መሠረት
አድራሻ፡-  አዲስ አበባ፣ ቦሌ ሆምስ (ከቦሌ ወደ ገርጂ በሚወስደው መንገድ ላይ ከአርጀንቲና ኤምባሲ ጀርባ)

ኢሜይል፡-  addismaleda@gmail.com
ይህ ማስታወቂያ ከወጣ በኋላ ባሉት ተከታታይ አምስት የሥራ ቀናት የትምህርትና የሥራ ልምድ ማስረጃዎን ያስገቡ!

ለተጨማሪው: https://news.1rj.ru/str/EventAddis1

ለተጨማሪው: https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
5