FDRE Defense Force - የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት – Telegram
FDRE Defense Force - የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት
41.4K subscribers
34.4K photos
39 videos
9 files
9.57K links
# ቁልፍ እሴቶች
1, ከራስ በፊት ለህዝብና ለሀገር ጥቅም፣
2, ምንጊዜም የተሟላ ስብዕና፣
3, ያልተሸራረፈ ዲሞክራሲያዊ አስተሳሰብ፣
4, በማንኛውም ግዳጅ ወይም ተግባር የላቀ ውጤት።
Download Telegram
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ቅዳሜ ህዳር 01 ቀን 2016 ዓ.ም

የአዋሽ አርባ የውጊያ ቴክኒክ ትምህርት ቤት ብቃታችው የተረጋገጠ የሜካናይዝድና የሞተራይዝድ ምድብተኞችን እና የወታደራዊ ተሽከርካሪ አሸከርካሪዎችን እያፈራ እንደሚገኝ ተገለፀ።

የትምህርት ቤቱ ምክትል ኣዛዥና የስልጠና ሃላፊ ኮሎኔል ብርሀኑ አሰፋ ፣  ትምህርት ቤቱ የተቋሙን የሜካናይዝድና የሞተራይዝድ ምድብተኞችን እና የወታደራዊ ተሽከርካሪ አሽከርካሪዎችን ፍላጎት ለሟሟላት በመደበኛና በአጭር ኮርስ በማስተማር ብቁ ባለሙያዎችን በብዛትና በጥራት እያፈራ አንደሚገኝ ገልፀዋል።

ትምህርት ቤቱ ውጤታማነትንና ተጣጣፊነት በመከተል እየሰጣቸው ያሉት ስልጠናዎች ተጨባጭ ውጤቶችን ማስመዝገቡን የጠቆሙት ሃላፊው ፣ በዚህም ብቃታቸው በምዘና የተረጋገጠ ምድብተኞችንና አሽከርካሪዎችን ለማፍራት መቻሉን ጠቁመዋል።

በተለያዩ የአየርና ሁኔታና የመሬት ገፆች ላይ በቀንና በሌሊት ግዳጃችውን ሊወጡ የሚችሉ ምድብተኞችና ወታደራዉ አሸከርካሪዎችን ለማፍራት ዘመናዊ ሲሙሌተሮችን መጠቀማችው እና ተማሪና ተግባር ተኮር ስልጠና መሰጠታቸው  ብቁ ባለሙያዎችን  ለማፍራት  ማስቻሉን ጠቁመዋል።

አንጋፋው ብቸኛ የሆነውን የአዋሽ አርባ የውጊያ ቴክኒክ ትምህርት ቤትን የበለጠ ለማዘመን ከመሀንዲስ እና ከሎጂስቲክስ ዋና መምሪያዎች ጋር በመተባበር የመሰረተ ልማቶችን ፣ ዘመናዊ የወታደራዊ ተሽከሪካሪዎች እና የብረት ለበሰ መሳሪያዎችን ለሟሟላት እየተሰራ እንደሚገኝም ገልጸዋል።

የአዋሽ አርባ የውጊያ ቴክኒክ ትምህርት ቤት ብቁ የሜካናይዝድና የሞተራይዝድ ምድብተኞችንና ወታደራዊ አሽከርካሪዎችን ከማፍራት በተጨማሪ የተለያዩ ከባድ መሳሪያዎችን በመሞከር ውጤታማ መሆናችውን በማረጋገጥ እውቅና እየሰጠ የሚገኝ ብቸኛ ማሠልጠኛ ነው።

ዘጋቢ ብዙአየሁ ተሾመ
ፎቶግራፍ ሀይለማርያም ተፈራ

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
https://youtube.com/channel/UCgcF4HWzgNZRsmMlUlb8ebQ

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት  ቴሌግራም 
https://news.1rj.ru/str/+E_EOiTY9eq85ODI0

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ
https://www.facebook.com/fdredefense.official
👍162
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ቅዳሜ ህዳር 01 ቀን 2016 ዓ.ም

በኢትዮጵያ የሩዋንዳ አምባሳደር እና የእንግሊዝ ወታደራዊ አታሼ የኢትዮጵያ ወታደራዊ አካዳሚን ጎበኙ።

የኢትዮጵያ ወታደራዊ አካዳሚ አዛዥ ብርጋዲየር ጄኔራል ተመስገን አቦሴ ለእንግዶቹ ሞቅ ያለ አቀባበል አድርገውላቸዋል። እንግሊዝና ሩዋንዳ ከኢትዮጵያ ጋር ያላቸው የቆየ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ጠንካራ መሆኑን ገልፀው ይህን ጥንካሬ ለማሥቀጠል የዛሬው ጉብኝት አሥፈላጊ ነው ብለዋል፡፡

በዕለቱ ስለ ሁለቱም ሃገራት ወታደራዊ ግንኙነትና አካዳሚው ከተመሰረተ ከ1927 ዓ.ም ጀምሮ አሁን እስከደረሰበት ደረጃ ገለፃ ያደረጉት የኢትዮጵያ ወታደራዊ አካዳሚ ምክትል አዛዥ ለትምህርትና ስልጠና ዲን ሌተናል ኮሎኔል ሽዋቀና አማን ሲሆኑ የአካዳሚውን ሁለንተናዊ የሥልጠና ሂደት በተመለከተ ማብራሪያ ሠጥተዋል።

በኢትዮጵያ የሩዋንዳ አምባሳደር ሜጀር ጄኔራል ቻርለስ ካራንባ ለተደረገላቸው አቀባበል አመስግነው ኢትዮጵያ ሁለተኛ አገራችን ነች በተለያዩ ጊዜያት ኢትዮጵያ ከሩዋንዳ ጎን ነበረች አሁንም ከጎናችን ናት ጉብኝቱም የሁለቱ ወንድማማች ህዝቦች ግንኙነት ይበልጥ ተጠናክሮ እንዲቀጥል የሚረዳ ነው ብለዋል።

አምባሳደሩ ስለ ወታደራዊ አካዳሚው የተደረገላቸው ገለፃ የተለየ ስሜት እንደፈጠረባቸውና ስመ-ጥርና ገናና የሆነው ወታደራዊ አካዳሚው የጀግኖች ማፍለቂያ ስለመሆኑ ተገንዝብያለው ብለዋል፡፡

በኢትዮጵያ የእንግሊዝ ወታደራዊ አታሼ ኮሎኔል ማርክ ባቫን ለተደረገላቸው አቀባበል እና ገለፃ አመስግነው እንደተለመደው ሁሉ ወታደራዊ ትብብርን መሰረት ያደረገ የትምህርትና ስልጠናውን ለማገዝ እና አብሮ ለመስራት የእንግሊዝ መንግስት እገዛ እንደሚያደርግ ቃል ገብተዋል፡፡

ለዕጩ-መኮንኖቹም የእንግሊዝኛ ቋንቋ ችሎታ ለማሳደግ ፕሮግራም መያዙን ኮሎኔል ማርክ ባቫን ገልፀዋል፡፡ በመጨረሻም የወታደራዊ አካዳሚው እድሜ ጠገቡ ቤተ- መፃህፍት እና ስመ-ጥር የፈረስ ስፖርት ቡድንን እንዲሁም ፈረሶችን ጎብኝተዋል፡፡

ዘጋቢ ፊልሞን ገብረእግዚአብሄር
ፎቶግራፍ ፊልሞን ገብረእግዚአብሄር

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
https://youtube.com/channel/UCgcF4HWzgNZRsmMlUlb8ebQ

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት  ቴሌግራም 
https://news.1rj.ru/str/+E_EOiTY9eq85ODI0

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ
https://www.facebook.com/fdredefense.official
👍132
የኢፌዴሪ መከለከያ ሠራዊት ቅዳሜ ህዳር 01 ቀን 2016 ዓ.ም

ጀግናው ወታደር የኢትዮጵያ እና የኢትዮጵያዊያን የክብር ልኬት ነው ።

ኢትዮጵያ ሀገራችን ለመላው ጥቁር አፍሪካውያን  እና ጭቁኖች የነፃነት ምልክት ተደርጋ የምትታይበት ምስጢር ልጆቿ ብርታት፣ ፅናት እና መስዋዕትነት ናቸው። ስለ ሀገራቸው ክብር የሚሰው፣ ለነፃነታቸው እና ለክብራቸው የማይደራደሩ የኩሩ ሕዝቦች መኖሪያ የሆነች ሀገር ስላላቸው ነው። ለማንም በማይንበረከኩ ቆራጥ ልጆቿ ተከብራ እና ተፈርታ የኖረች፣ ወደፊትም የምትኖር የጀግኖች ሀገር ናት ኢትዮጵያ። 

ኢትዮጵያውያን ሰላም ወዳድ ሕዝብ ስለሆኑ በታሪካቸው በአንድም አጋጣሚ የሌሎችን ግዛት ወረው አያውቁም። ነገር ግን ሲደርሱባቸው ሀገራቸውን ለመከላከል በፍፁም ጀግንነት እና ቆራጥነት ይዋጋሉ። ፈፅሞ የባእዳንን ቀንበር መሸከም የማይችል ስለመሆናቸው አሸናፊነታቸው በቂ ማሳያ ነው።

በጀግንነት የፀናች ሀገር ጀግና ወታደር አላት። ፅኑ ሕዝቦች አሏት። ከጠላት የሚከላከሏት፣ በጀግንነት የሚያሻግሯት፣ ጨለማውን የሚገፉላት፣ ወታደር ለኢትዮጵያ ከምንም ከማንም በላይ ነው። ወታደር ኢትዮጵያን ይጠብቃታል፣ ማንም እንዳይደፍራት ይከላከልላታል፣ በኢትዮጵያ ላይ በግፍ  እጃችንን እናነሳለን ያሉትን ሁሉ ይቀጣላታል፣ እየቀጣም አደብ ያስይዝላታል።

የኢትዮጵያ ወታደር ጀግና ነው ጠላት የማይደፍረው፣ ብርቱ ነው መከራ የማይሰብረው  ፅኑ ነው፣  እሾህና አሜካላ የማያስቆመው፣ ከግስጋሴው የማያስቀረው ሃያል ነው። የኢትዮጵያ ወታደር ኢትዮጵያዊያን የወለዱት፣ ኢትዮጵያዊያን የሚያከብሩት፣ ሰንደቃቸውና ሀገራቸውን እንዲጠብቅላቸው አደራ የሰጡት ፣የሚመኩበት  የሚኮሩበት ነው።

የፅኑዋን ሀገር ጀግና ወታደር ኢትዮጵያ እና ኢትዮጵያዊያን ብቻ ሳይሆኑ አፍሪካዊያን ጭምር ይኮሩበታል። ይመኩበታል፣ በቸገራቸው ጊዜ ይጠሩታል፣ በጠሩትም ጊዜ ፈጥኖ ይደርስላቸዋል። ከጭንቅና ከችግር ይታደጋቸዋል። በክንዱ ብርታት ያበረታቸዋል። የፅኑ ሀገር ጀግና ወታደር፣ የፅኑ ሕዝብ ድንቅ መከታ፣ የታላቅ ሀገር ኀያል ወታደር። አባቶቻችን በደምና በአጥንታው ኢትዮጵያን እዚህ አድርሰዋል ዛሬም በመስዋዕትነታቸው ሀገር እየጠበቁ ላሉ ሁሉ ክብር ይድረሳቸው።

በፍፁም ከተማ

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
https://youtube.com/channel/UCgcF4HWzgNZRsmMlUlb8ebQ

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት  ቴሌግራም 
https://news.1rj.ru/str/+E_EOiTY9eq85ODI0

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ
https://www.facebook.com/fdredefense.official
👍181
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ቅዳሜ ህዳር 01 ቀን 2016 ዓ.ም

በደቡብ ሱዳን ዓለም አቀፍ የምግብ ድርጅት ለግዳጅ አገልግሎት የሚውሉ ተሽከርካሪዎችን ለ16ኛ ሞተራይዝድ ሰላም አስከባሪ ሻለቃ በጊዜያዊነት ድጋፍ አደረገ ፡፡

በዩናሚስ ሴክተር ኢስት የግዳጅ ቀጠና ላይ ተሰማርቶ ግዳጁን እየተወጣ የሚገኘው የ16ኛ ሞተራይዝድ ሰላም አስከባሪ ሻለቃ አሁን ያለውን የግዳጅ ቀጠና ስፋት እና በክረምት ወቅት መንገዶች  ለተሸከርካሪ ምቹ ያለመሆናቸዉን ግምት ውስጥ በማሥገባት የአለም የምግብ ድርጅት አራት ሽረፕ ተሽከርካሪዎችን  በድጋፍ  መሰጠቱን የሞተራይዝድ ሻለቃው አዛዥ ኮሎኔል ተፈራ መላክ ገልፀዋል፡፡

ከዓለም አቀፉ የምግብ ድርጅት በጊዜያዊነት ድጋፍ የተደረጉልን እነዚህ ሽረፕ ተሽከርካሪዎች ለጉዞ አስቸጋሪ በሆኑ ጭቃማና ጎርፍ በሚሞላባቸው መንገዶች  በተለይም በክረምት ወቅት ለሌሎች ተሸከርካሪዎች ጉዞ አስቸጋሪ የሆኑ መንገዶችን በቀላሉ መውጣት የሚችሉ  በመሆናቸው ግዳጃችንን ለመወጣት ጉልህ ሚና አላቸዉ ለድጋፉ እናመሠግናለን ብለዋል፡፡

የ16ኛ ሞተራይዝድ ሰላም አስከባሪ ሻለቃ ምክትል አዛዥ ለሎጅስቲክስ ሌተናል ኮሎኔል ከማል ገለቶ በበኩላቸው ከዓለም ምግብ ድርጅት በጊዜያዊነት የተረከብናቸው ተሸከርካሪዎች ላይ ተገቢውን ጥንቃቄና እንክብካቤ በማድረግ ቀጣይነት ያለው የትራንስፖርት አገልግሎት በማቅረብ ሰራዊታችን ከቦታ ቦታ ተንቀሳቅሶ ግዳጁን እንዲወጣ እናደርጋለን ብለዋል።

ሌተናል ኮሎኔል ከማል የሽረፕ ተሸከርካሪ ሹፌሮችን ከተባበሩት መንግስታት ድርጅት ሰላም  ማስከበር ተልዕኮ አብዬ ግዛት ትራንስፖርት ኃላፊ የተመራውን  የባለያዎች ቡድን ተቀብለው ስለ ተሽከርካሪዎች ቴክኒካዊ አሰራርና አጠቃቀም በንድፈ- ሃሳብ በተግባር ልምምድ በማድረግ ቴከኒካል ድጋፍ መሰጠቱንም ጨምረው ገልፀዋል፡፡ 

ዘጋቢ ፍቃዱ ጋሻው
ፎቶግራፍ ገነት ሙሌ

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
https://youtube.com/channel/UCgcF4HWzgNZRsmMlUlb8ebQ

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት  ቴሌግራም 
https://news.1rj.ru/str/+E_EOiTY9eq85ODI0

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ
https://www.facebook.com/fdredefense.official
👍144