FDRE Defense Force - የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት – Telegram
FDRE Defense Force - የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት
41.4K subscribers
34.4K photos
39 videos
9 files
9.57K links
# ቁልፍ እሴቶች
1, ከራስ በፊት ለህዝብና ለሀገር ጥቅም፣
2, ምንጊዜም የተሟላ ስብዕና፣
3, ያልተሸራረፈ ዲሞክራሲያዊ አስተሳሰብ፣
4, በማንኛውም ግዳጅ ወይም ተግባር የላቀ ውጤት።
Download Telegram
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ቅዳሜ ህዳር 15 ቀን  2016 ዓ.ም

በትራፊክ አደጋ የሚከሠተውን የሠው ህይወት እና የንብረት ውድመት ለመቀነስ ስልጠና ወሳኝ መሆኑ ተገለፀ።

በመከላከያ ጠቅላይ መምሪያ ጠቅላላ አገልግሎት በተሽከርካሪና ነዘቅ አገልግሎት ቡድን ለአሽከርካሪዎች እና ለነዘቅ ሙያተኞች ሲሰጥ የቆየው ስልጠና ተጠናቋል።

በስልጠናው ማጠቃለያ ላይ የተገኙት የጠቅላይ መምሪያው ጠቅላላ አገልግሎት ዋና ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ሜጀር ጀኔራል ታደሰ መኩሪያ ከበጀት ዓመቱ የጠቅላይ መምሪያው እቅዶች አንዱ የሥራ ላይ የአቅም ግንባታ ስልጠና እንደነበር ጠቁመው፤ ከዘመናዊ ሠራዊት መገለጫዎች ጋር ተያይዞ ወታደራዊ ስልጠና እንዲሁም የሥራ ላይ አጫጭር ስልጠናዎችን መሥጠት ለማንኛውም ተልዕኮ ስኬት ወሳኝ መሆኑን ተናግረዋል።

የአሽከርካሪዎችን እና የነዘቅ ሙያተኞችን ሙያዊ አቅም ለማሣደግ ብሎም ተቋሙ በሚፈልገው የአሠራር አግባብ ልክ መሥራት እንዲችሉ የግንዛቤ ማስጨበጫ  ስልጠና መሠጠቱ ወሳኝም ጠቃሚም እንደሆነ አክለዋል።

የጠቅላይ መምሪያው ጠቅላላ አገልግሎት የፋይናንስ ዳይሬክተር  ኮሎኔል ግርማ ታደሰ በበኩላቸው ከጊዜ ወደ ጊዜ  በሀገር አቀፍ ደረጃ እየተባባሰ የመጣውን በሰው እና በንብረት ላይ ውድመት እና አደጋ እየፈጠረ ያለውን የትራፊክ አደጋ ለመቀነስ ብሎም አሽከርካሪዎች በሰው ህይወትና ንብረት ጉዳት ሳያደርሱ  በጥንቃቄ ሙያዊ ግዴታዎችን እንዲወጡ ለማሥቻል ስልጠናው  ችግር ፈች መሆኑን አብራርተዋል።

የመከላከያ ጠቅላላ አገልግሎት የተሽከርካሪ እና ነዘቅ አገልግሎት ቡድን መሪ ሌተናል ኮሎኔል ለገሠ ድንቁ በክፍሉ ከተያዘው እቅድ አንዱ የአቅም ማጎልበቻ አጫጫጭር ስልጠናዎችን ለባለሙያዎች መስጠት በመሆኑ በቴክኒክ እና የተሽከርካሪ ደህንነት አጠባበቅ ፣በመንገድ ደንብ መተላለፍ፣ በኢንሹራንስ እና አደጋ መከላከል እና በመሳሰሉት ላይ ትኩረቱን ያደረገ ስልጠና  መሰጠቱን ገልፀዋል።

ስልጠናውን የሠጡት  ሻለቃ አንዱአለም አበበ በበኩላቸው ክፍሉ ባዘጋጀው ስልጠና ላይ ያላቸውን እውቀት ለሰልጣኞች በማካፈላቸው ደስተኛ መሆናቸውን ገልፀው የአሽከርካሪነት እና ተያያዥ ሙያዎች በቀጥታ ከሰው ህይወትና ከንብረት ጋር የተያያዘ በመሆኑ በሀገራችንም ይሁን በተቋማችን ያለውን የትራፊክ አደጋ በመቀነሱ በኩል አጫጭር ስልጠናዎች ከፍተኛ ሚና የሚጫወቱ ናቸው ብለዋል።

ሰልጣኞች ስልጠናው ከነበራቸው አቅም ላይ ተደማሪ እውቀት ያገኙበት ለቀጣይ ሥራቸው ይበልጥ የሚያግዛቸው መሆኑን ገልፀዋል።

ዘጋቢ ልደት አስረስ እና ሰሚራ ሃይሉ
ፎቶግራፍ ብርቱካን ረጋሳ

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
https://youtube.com/channel/UCgcF4HWzgNZRsmMlUlb8ebQ

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት  ቴሌግራም 
https://news.1rj.ru/str/+E_EOiTY9eq85ODI0

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ
https://www.facebook.com/fdredefense.official
12👍7
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ቅዳሜ ህዳር 15 ቀን 2016 ዓ.ም

ሠራዊት በፅንፈኛው ሃይል የተዘረፉ ንብረቶችን እያሥመለሠ ነው።

በሰሜን ሸዋ ዞን የምንጃር ሸንኮራ የመልካ ጅሎ ቀበሌ የአሞራ ቤት ነዋሪዎች በፀጥታ መደፍረስ ምክንያት ከአካባቢያቸው ተፈናቅለው የነበሩ ገበሬዎችን ጤፍ በማጨድና በመውቃት ዘረፋ የፈፀሙትን ፅንፈኞች ሠራዊቱ ተከታትሎ በመያዝ 22 ኩንታል ጤፍና 90  ሺ ብር ማሥመለሱን እና ለምንጃር ሸንኮራ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ አለማየሁ ግዛው ማሥረከቡን የኮሩ አዛዥ ኮሎኔል ደጀኔ ፀጋዬ ተናግረዋል።
    
ሰራዊቱ የህዝብ ልጅ ስለሆነ የደሃን እና የገበሬን ንብረት የዘረፉ ዘራፊዎችን ተከታትሎ ለመያዝ መቻሉን የገለፁት ኮሎኔል ደጀኔ አሁንም የተዘረፉ ንብረቶችን ከየ አካባቢው የፀጥታ ሃይል ጋር በመነጋገር ተከታትለን እንይዛለን ብለዋል።

ሠራዊቱ ለወንበዴና ለዘራፊ ቦታ የለውም ያሉ ሲሆን፤  ዘራፊዎቹም ለህግ ይቀርባሉ ብለዋል። ሰራዊቱ በሚተገብረው በጎ ሥራ የገበሬው እምባ አባሽ መሆኑን በተግባር ማረጋገጡንም ተናግረዋል።
 
አርሶአደሩን በመወከል ንብረቱን የተረከቡት የምንጃር ሸንኮራ ዋና አስተዳዳሪ አቶ አለማየሁ ግዛው ሰራዊቱ በተደጋጋሚ ለህዝቡ ያለውን አጋርነት እና ቀናነት በተለያዩ መገለጫዎች እያሥመሠከረ መምጣቱን ጠቁመው የእርሶአደሩን ሰብል ማስመለሱ የህዝባዊነቱ ማሣያ ነው ሲሉ ገልፀዋል።

ዘጋቢ አባተ ወልደ እየሱስ
ፎቶግራፍ አባተ ወየሱስ

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
https://youtube.com/channel/UCgcF4HWzgNZRsmMlUlb8ebQ

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት  ቴሌግራም 
https://news.1rj.ru/str/+E_EOiTY9eq85ODI0

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ
https://www.facebook.com/fdredefense.official
👍207🥰2😁2
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ቅዳሜ ህዳር 15 ቀን 2016 ዓ.ም

የመከላከያ ሠራዊት አባላቱ ከተሰጣቸው ሀገራዊ ተልዕኮ ጎን ለጎን የአርሶ አደሩን ሰብል እየሰበሰቡ ነው።

ክፍለ ጦሩ በኦሮሚያ ክልል በሜታ ውልቂጤ ወረዳ ሉማ ጣጤሳ ቀበሌ የአቅመ ደካሞችን ሰብል አጭዶ ስብሰቧል።

የክፍለ ጦሩ አዛዥ ኮሎኔል ደሳለኝ ፈይሳ ሰራዊታችን የህዝብ ልጅ ለእናት ሀገሩ ዘብ የቆመ ለህይወቱ የማይሳሳ በአላማው የሚፀና ብርቱ ሃይል ነው ብለዋል። የዛሬው ሰብል የመሠብሠብ ሥራም የሰራዊታችንን ህዝባዊነት የሚያሳይ በመሆኑ ከግዳጅ ጎን ለጎን ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ተናግረዋል ።

ሰብል ከተሰበሰበላቸው አቅመ ደካማ አርሶ አደሮች መካከል አቶ አበበ አያኖ ሰራዊቱ ባደረገው ድጋፍ መደሰታቸውን ገልፀው ሠራዊት የሠላም ብቻ ሳይሆን የልማት ሃይል መሆኑንም አሥመሥክሯል ብለዋል።

በተመሳሳይ በምዕራብ ሸዋ ዞን በጀልዱ ወራዳ በተሶ ቀበሌ ለግዳጅ የተሰማራው ክፍለ ጦር አባላት ከሀገራዊ ተልዕኳቸው ጎን ለጎን ከራስ በፊት ለህዝብና ለሀገር የሚለውን እሴት በማሥቀደም የአርሶ አደሩን ሰብል መሰብሰቡን መቶ አለቃ ሰንደቁ መልዓክ ተናግረዋል።

በምዕራብ ሸዋ ዞን ጀልዱ ወረዳ ተሶ ቀበሌ ነዋሪ የሆኑት አርሶአደር ባይሳ ላሜሳ የሀገር መከላከያ ሰራዊት የህዝብ ልጅ መሆኑን በገሃድ ያስመሰከረ በዚህ አስቸጋሪ ገጊዜ ለአቅመ ደካማ አርሶአደሮች ሰብል የሚሰበስብ ሀገሩን የሚያስቀድም ጀግና ሰራዊት ነው አመሠግናለሁ ብለዋል።

ዘጋቢ ፍቃዱ ቡዝነህ
ፎቶግራፍ  ደረጀ ኤልያስ

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
https://youtube.com/channel/UCgcF4HWzgNZRsmMlUlb8ebQ

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት  ቴሌግራም 
https://news.1rj.ru/str/+E_EOiTY9eq85ODI0

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ
https://www.facebook.com/fdredefense.official
👍149🥰1
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ቅዳሜ ህዳር 15 ቀን 2016 ዓ.ም

        ስለ ሀገር ሁሌም የሚያዜሙ ጀግኖች

በአውሎ ንፍስ ወጀብ እየተመታ በአይኑ ብሌን ሰንደቁን እያየ በሰማይ አድማስ ቁልቁለቱን ተራራውን በምድር ወጋገን ሸጡን ኮረብታውን አሸዋማ መሬቱን ዘብጥና ገደላ ገደሉን አረንጓዴ ቢጫ ቀይ የተቀባ ቀለም እያዩ ለሀገራቸው ህይወታቸውን አሳልፈው መስጠት ፍቅር ለሀገራቸው ማውረስ ጀግንነት ለትውልድ ማስረከብ  ቃላቸው ነው።

አርማውን ለብሰው እሳት ይዘው ሰላም አንግበው ከህዝብ ተወልደው ጨለማ ብርሀን ክረምት በጋ ሳይሉ ጠላት በማባረር ጊዜያቸውን ሰላም በማረጋገጥ በጀግንነት ያሳልፍሉ።

የአለማችን ወርቃማ ኮከቦች የሰላም ሻማዎች  በብርድ ጫካ እያደሩ በዝናብ ጠላት እያደኑ ለሀገራቸው ውድ ጉልበታቸውን እየሰጡ በዘር በቀለም በሀይማኖት ሳይከፋፈሉ በሀሳብ አንድ ሆነው ስለ አንድ የሚያስቡ በንስር ወጀብ የተፈተኑ ሰማያዊ ኮከቦች ናቸው።

ሺህ ጊዜ ሙተው ሺህ ጊዜ ሀገራቸውን የሚወዱ ለሀገራቸው ክብር የሚንሰፈሰፉ ሀገር ወዳዶች ናቸው።

የአበው ታሪክ የተፃፈላት አድዋ የተግባር ምሳሌ የሆነላት ችግርን በጋራ የሚጋፈጡ ሰላም ወዳዶች ሁሌም የሚታገሉላት ታግለው የሚያሸንፉላት አፅንተው የሚያሻግሯት ናት ።

ከችግርና መከራ ሀገርን የቀየሩ አርቆ አሳቢ ከጥላቻ ይልቅ ለሰላም እጃቸውን ለውድ ሀገራቸው የሚዘረጉ አጥንታቸውን የሚከሰክሱ ደማቸውን የሚያፈሱ የሰላም ጥበበኞችን ማየት መታደል ነው ።
         
በሞላልኝ ገብያው

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
https://youtube.com/channel/UCgcF4HWzgNZRsmMlUlb8ebQ

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት  ቴሌግራም 
https://news.1rj.ru/str/+E_EOiTY9eq85ODI0

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ
https://www.facebook.com/fdredefense.official
10👍5🥰1
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ቅዳሜ ህዳር 15 ቀን 2016 ዓ.ም

የመከላከያ ትምህርትና ስልጠና ዋና መምሪያ የኢንስፔክሽን ቡድን የጦላይ የከፍተኛ ባለሌላ ማዕረግተኛ ማሰልጠኛ ሁኔታን ተመለከተ፡፡

ኢንስፔክሽን ቡድኑ በማሰልጠኛ ትምህርት ቤቱ እየተሰሩ ያሉ የሥልጠና ስራዎችን እና መሰረተ ልማቶችን ተመልክቷል።
 
የስልጠና ዋና መምሪያ የስነ ምግባር ክትትል ቡድን መሪ ሌተናል ኮሎኔል ዳንኤል መላኩ ለሰልጣኞች እየተሰጠ ያለው የሥልጠና ሂደት ጥሩ በሆነ አግባብ እየሄደ መሆኑን ገልፀው በተለይ የማሰልጠኛ ትምህርት ቤቱ አሰልጣኞች የሥልጠና ቅድመ ዝግጅት በማመቻቸት ሰልጣኙ በቂ ግንዛቤ እዲያገኙ በማድረግ ረገድ ውጤታማ ሥራ እየተሠራ መሆኑን ተገንዝበናል ብለዋል፡፡

በማሰልጠኛ ትምህርት ቤቱ በርካታ መሰረተ ልማቶች  ማለትም የነዳጅ ዲፖ፣ የጅምናዜምና መሰናክል ወረዳ፣ መኖሪያ ቤት፣ዘመናዊ ቄራ ፣ የሆስፒታል እደሳ፣ ዘመናዊ መፀዳጃ ቤቶች ግንባታ በፈጣን እንቅስቃሴ እየተከናወነ መሆኑን መመልከታቸውን ተናግረዋል ።

ሻለቃ ታደለ ታየ በበኩላቸው የጦላይ ማሠልጠኛ ሰልጣኞችን በመቀበል የተለያዩ ሙያዊ እና ወታደራዊ ስልጠናዎችን በመስጠት ጥሩ መሪ ሆነው እንዲወጡ  በማሥቻሉ ረገድ የዘመናዊ ሰራዊት ግንባታ ድርሻውን እየተወጣ ነው ብለዋል።
                                                 
ዘጋቢ ኃይለማርያም ተሾመ
ፎቶ ግራፍ አድሱ ባየ

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
https://youtube.com/channel/UCgcF4HWzgNZRsmMlUlb8ebQ

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት  ቴሌግራም 
https://news.1rj.ru/str/+E_EOiTY9eq85ODI0

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ
https://www.facebook.com/fdredefense.official
👍85🔥1